👉 ዘወረደ ብለን የጀመርነውን ተነስቷል ብለንም ለማክበር ለማመስገን እግዚአብሔር በሠላም ያድርሰን !!
መልካም ሱባኤ ለሁላችንም 👏
መልካም ሱባኤ ለሁላችንም 👏
#RECORD ❗️
በ30 ደቂቃ 10 Mil ብር ለ መቄዶንያ አሰባሰቡ!
አጠቃላይ የሰበሰቡትን የብር መጠን 77 ሚሊየን
ብር በማድረስ ሪከርዳቸውን አስጠብቀዋል!
ቀሲስ ዶክተር መምህር ዘበነ ለማ
በ30 ደቂቃ 10 Mil ብር ለ መቄዶንያ አሰባሰቡ!
አጠቃላይ የሰበሰቡትን የብር መጠን 77 ሚሊየን
ብር በማድረስ ሪከርዳቸውን አስጠብቀዋል!
ቀሲስ ዶክተር መምህር ዘበነ ለማ
#ዘወረደ
‹‹ ዘወረደ » ማለት የወረደ ማለት ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማያት ወደ መሬት ፣ ከልዕልና ወደ ትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ነው ።
ይህ ሳምንት አምላክ ሰው ፣ ሰው አምላክ ፣ ልዑሉ ትሑት ፣ ትሑቱ ልዑል ፤ ረቂቁ ውሱን ፤ ውሱኑ ረቂቅ የመሆኑ ምሥጢር የሚወሳበት ሳምንት ነው ። ይኸውም ‹‹ ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው ›› በማለት ከሰማይም የወረደው ወደ ሰማይም የወጣው ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ኾኖ በተዋሕዶ ከብሮ ሰው የኾነ አንዱ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን ነግሮናል ። ( ዮሐ 3 ፥ 13 )
ይህ ኀይለ ቃል በዘወረደ ሰንበት በቅዳሴው ክፍለ ጊዜ የተነበበው ይህን ምሥጢር ለማጉላት ነው ፡፡ የሶርያው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም ‹‹ ሰው ሰውኛውን ተመላለስ አለ ፤ የሰውነት ሥራን ሠራ ፤ ይቅር ባይ ሰው ወዳጅ ነውና ። በልዩ አመጣጡ ሰው ሆኖ አዳነን ፡፡ ›› በማለት ቃሉን ጠብቆ ጊዜውን አክብሮ ከሰማይ መውረዱን መስክሯል ( ዮሐ 1 ፥ 14 )
መተርጉማን ‹‹ በልዩ አመጣጡ አዳነን ›› የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ ‹‹ ቀድሞ ያድነን የነበረው በመልአክ ፣ በጸጋና በረድኤት እያደረ ነበር ፤ ዛሬ ግን ያዳነን ራሱ በሥጋ ተገልጦ ሰው ሆኖ ነውና ያአሁኑ አመጣጡ ልዩ ነው ›› ሲሉ ያመሠጥሩታል ።
የመናፍቃን መዶሻ የኾነው ታላቁ ሊቅ ቄርሎስም ‹‹ ያዳነን ራሱ እግዚአብሔር ነው እንጂ አማላጅ ወይም መልአክ አይደለም ፤ በባዕድ ደም በዕሩቅ ብእሲ ሞት አላዳነንም ራሱ በደሙ አዳነን እንጂ :: ›› ሲል ተናግሯል ።
‹‹ ዐምስት ሺ ዐምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ እወለዳለሁ በሜዳህ ድኬ በመስቀሌና በሞቴ አድንሃለሁ ›› ብሎ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ከሰዓቱ አንድ ሰዓት ፣ ከዕለቱ አንድ ዕለት ፣ ከወሩ አንድ ወር ፣ ከዓመቱ አንድ ዓመት ሳያዛንፍ ሳያተርፍ ፣ ሳይቀንስ ሳይጨምር ሰው ሆኖ በጽኑዕ ቀጠሮው መጥቶ ማዳኑን ተናግሯል ::
ዘመኑ ሲፈጸም መለኮት ምድራዊ ሰውነትን ገንዘብ ሊያደርግ ሥጋ ደግሞ ሰማያዊ እውቀትን ገንዘብ ሲያደርግ አካላዊ ቃል እግዚኣብሔር ወልድ ከሰማይ መውረዱን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ‹‹ የዘመነ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ ። ›› ( ገላ 4 ፥ ፬ ) ብሎ እንደተናገረ የጠፋውን አዳምን ፍለጋ ከአባቱ ዕሪና ሳይነጠል ከክብሩ ሳይጎድል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን የምናዘክርበት ሳምንት ነው ።
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ ቅድመ ዓለም የነበረ ዛሬም ያለ ፤ ወደ ፊትም ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም የሚኖር ከላይ የወረደውን እርሱን አይሁድ ሰቀሉት በቃሉ የሚያድን የሁሉ ጌታ መሆኑን ምንም አላወቁምና ›› በማለት በዚህ ሳምንት ጌታችን እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጥልን ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ መከራ መቀበሉን ያዘክራል ፡፡ ዳግመኛም ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ጾመ ሕርቃል ይባላል ፡፡

«ዝክረ ኒቅያ» ሀገር አቀፍ የሊቃውንት ጉባኤ ሊዘጋጅ ነው !
የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም
<<የሊቃውንት ብዛት ለዓለም መድኃኒት ነው>>
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ ታሪካዊና በዓይነቱ ልዩ የሆነ <<ዝክረ ኒቂያ>> የተሰኘ ሀገር አቀፍ የሊቃውንት የምክክር ጉባኤ ከሚያዚያ 20 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለማካሔድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የጉባኤውን ዓላማ እና ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ ዛሬ ሰኞ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሕዝብ ግኑኝነት ጽ/ቤት መግለጫ በሊቃውንት ጉባኤ ተሰጥቷል፡፡
በቀደምት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥያቄዎችና የኑፋቄ ትምህርቶች ሲነሱ መልስ ለመስጠት ሊቃውንቱ ተሰባስበው ምላሽ የሚሰጡ መሆኑንና አሁንም በቤተ ክርስቲያን ላይ በነገረ ሃይማኖት እንዲሁም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተለያዩ ኑፋቄና ቀኖናዊ ጥያቄዎች እየተነሱ በመሆኑ የሊቃውንት መሰባሰብ አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ጉባኤው ከጥር 26-29 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለማካሄድ ታቅዶ እንቅስቃሴ ሲደረግ የቆየ ቢሆንም፡-
1ኛ) ጉባኤው በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንት የሚታደሙበት እንደመሆኑ፥ በተለይ በጠረፉ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ መምህራንን በበቂ ቊጥር ለማካተት እንዲቻል ፥ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ ፤
2ኛ) በጥር ወር በርካታ ሀገራዊ ክንውኖችና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት በየአካባቢው የሚካሄዱ በመሆናቸው የጉባኤው መካሄጃ ጊዜ እንዲስተካከል ከአንዳንድ አህጉረ ስብከት በተደጋጋሚ አስተያየት በመሰጠቱ ፤
3ኛ) ጉባኤው ከዘመናት ቆይታ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድና በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ውይይቶችን በማካሄድ ፥ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚጠቅም የውሳኔ ሐሳብና አስተያየት የሚያቀርብ ፥ አልፎም የአቋም መግለጫ የሚያወጣ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ከመካሄዱ ጥቂት ቀደም ብሎ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፥ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፥ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፥ የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ከሚያዝያ 20-25 ቀን 2017 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሚካሄድ ይሆናል።
በጉባኤው፡- ያለውን ማጽናት፣ የጠመመውን ማቅናት፣ የጠፋውን መፈለግ፣ ሊቃውንቱን እርስ በእርስ ማስተዋወቅና ቤተክርስቲያን ያለችበትን ችግር ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ እና ብፁዓን አበው በተገኙበት ለምልአተ ጉባኤው ጥያቄ የሚቀርብ እና ምላሽ እንዲሰጥበት እንደሚደረግ ግቡን ማድረጉ ተገልጧል፡፡
ከመላው የሀገሪቱ ክፍል ከተቻለም ከውጭው ዓለም ያሉ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የሚሰባሰቡ ሲሆን በጊዜው በኒቂያ እንደተደረገው በዚህ ጉባኤም 318 ሊቃውንት የሚታደሙ እንደሆነ በመግለጫው ተገልጧል፡፡
በብፁዕ አቡነ እንድርያስ ሰብሳስቢነት የሚመራው የሊቃውንት ጉባኤ ከ 15 በላይ አባላት ያለው መሆኑ በመግለጫው ላይ ለማስታወስ ተሞክሯል፡፡

የዐቢይ ጾም ሥያሜዎች
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዐዋጅ ከሚጾሙት ሰባቱ አጽዋማት አንዱና ትልቁ ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡ ይህ ጾም በተለያዩ ሥያሜዎች ይታወቃል፡፡ የይኸውም፡- ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ኢየሱስ፣ ጾመ ሁዳዴ፣ ዐርባ ጾም በመባል ይታወቃል ፡፡ እነዚህንም እንደሚከተለው እንመለከታቸዋለን፡-
ዐቢይ ጾም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው ጾም ስለሆነ “ዐቢይ ጾም” ይባላል፡፡
ጾመ ሁዳዴ
በጥንት ዘመን ገባሮች ለባለርስቱ የሚያርሱት መሬት “ሁዳድ” ይባል እንደነበር ዐቢይ ጾምም ሠራኤ ሕግ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመውና ምእመናን ይህን እያሰቡ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ የሚጾሙት ስለሆነ “ጾመ ሁዳዴ” ይባላል፡፡
የካሣ ጾም
የቀድሞዎቹ ሰዎች አትብሉ የተባሉትን በመብላታቸው ከገነት ለመባረር ለውርደትና ለሞት ለሲዖል ባርነት ተዳርገዋል፡፡ ዳግማዊ አዳም የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በሆድ ምክንያት ድቀት አግኝቶት ረኃበ ጸጋ ደርሶበት የነበረውን ቀዳማዊ አዳምንና ልጆቹን በፈቃዱ በጾመው ጾም ካሠን፡፡ ስለዚህ ዐቢይ ጾም “የካሣ ጾም” ይባላል፡፡
የድል ጾም
አዳምና ሔዋን በገነት ሳሉ በምክረ ከይሲ ተታለሉና ድል ሆኑ፤ ተስፋ አበውን ሊፈጽም የመጣ ክርስቶስም ዲያብሎስን ድል ያደርግልን ዘንድ ተጠምቆ ሳይውል፣ ሳያድር ከዚህ ዓለም ርቆ ወደ ገዳም በመሄድና ከሰው ተለይቶ ፵ መዓልትና ሌሊት በመጾም ዲያብሎስን፣ ፈቃደ ሥጋችንን ድል የምናደርግበትን ኃይል አጎናጸፈን፤ ስለዚህ ዐቢይ ጾም ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ ድል የተነሡበት ዲያብሎስ ያፈረበት ስለሆነ “የድል ጾም” ይባላል፡፡
የመሸጋገሪያ ጾም
ነቢዩ ሙሴ ፵ ቀንና ሌሊት በሲና ተራራ ጾሞ እሥራኤል ዘሥጋን ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኦሪት ያሸጋገረ ሲሆን፤ ክርስቶስም እሥራኤል ዘነፍስ የተባልነውን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ፵ መዓልትና ሌሊት በመጾም ያሸጋገረን በመሆኑም “የመሸጋገሪያ ጾም” ተብሎ ይጠራል፡፡
ጾም አስተምህሮ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ድካም ሁሉን ማድረግ ሲቻለው መምህረ ትሕትና ነውና አርአያውን ሊተውልን ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ እኛን ወደ እርሱ በፍቅረ ይስበን ዘንድ አስቀድሞ ወደ እኛ መጣ፡፡ መጥቶም ረኃባችንን ተራበ፣ ድካማችንን ደከመ፣ ፈተናችንን ተፈተነ፡፡ ስለዚህ በጾሙ ትሕትናን ትዕግሥትንና ድል ማድረግን ስላስተማረበት ጾሙ “ጾመ አስተምህሮ” ይባላል፡፡
ቀድሶተ ገዳም
እነ ዮሐንስ፣ እነ ኤልያስ የኖሩትን የብትሕውና ኑሮ ለባሕታውያን፣ ለመነኮሳት ባርኮ ስለ ሰጠ፤ ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በገዳም ከአራዊት ጋር ኖሮ በዲያብሎስ ተፈትኖ ድል አድርጓልና ጾሙ “የቀድሶተ ገዳም ጾም” ይባላል፡፡
የሥራ መጀመሪያ ጾም
ጌታችን የማስተማር ሥራውን ከመጀመሩ፣ አንቀጸ መንግሥተ ሰማያትን ከማስተማሩ አስቀድሞ የጾመው በመሆኑም “የሥራ መጀመሪያ ጾም” ተብሎ ይጠራል፡፡ ስለሆነም ሐዋርያት እርሱን አብነት አድርገው ሠራቸውን በጾም ጀመሩ፡፡