ለሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም 11 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለፀ
በማዕከላዊ ጎንደር ሐገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንደነት ገዳም፣ ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም ቢሆንም መነኮሳቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር ተጋርጦባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል።
ገዳማዊያኑ የሚቀምሱት እህል፣ የሚለብሱት ልብስ በመጠኑ የተሟላላቸው ቢሆንም ከጾም፣ ጸሎት መልስ ስጋቸውን የሚያሳርፉበት ቤት የላቸውም፣ በአንድ ደሳሳ ጎጆ ቤት ውስጥ ለሶስት ለአራት የሚያድሩበት በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ዉስጥ እንደሚገኙ ነው የተገለፀው።
ገዳማዊያኑን ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገው፣ በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፣ ገዳሙም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት፣ በሐገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት በመሰራት ላይ ይገኛል ተብሏል።
ገዳሙ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የሚገልጹ እና የሚያሳዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እንዲሁም ትሁፊት በጠበቀ መልኩ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን በማስተላለፍ ሕብረተሰቡ መረጃዉ ኖሮት የተቻለውን ድጋፍ እንዲያደርግ ተደርጎ በዚህም እስካሁን 11,000,000 (አስራ አንድ ሚሊዮን) ብር የሚያህል የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም 1,200,000 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር የሚሆን የአይነት ድጋፍ ማሰባሰብ እንደተቻለ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 11 (አስራ አንድ) ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን በነዚህ ጊዜያት በመጀመሪያው ምዕራፍ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።
ከተሰሩ ስራዎች መካከል ፡-
❖ የእናቶች በዓት ወይም ቤት በጥሩ ሁኔታ ተሰርቷል።
❖ 170 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ ለእናቶችም ለአባቶችም ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረው ቦታ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ለገዳማዊያን እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን ተደርጓል።
❖ በአካባቢው ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት ያልነበረ ሲሆን አሁን የሶላር መብራት ተሟልቶ የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል።
❖ ቤተ-እግዚአብሔር ወይም ማዕድ ቤት ተሰርቷል፤ የሚያስፈልጉ ሙሉ ቁሳቁሶችም ተሟልቷል።
❖ ገዳማዊያኑ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸውን የምግብ አቅርቦት ችግር እና የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
❖ ለገዳማዊያኑ የእደ-ጥበባት ውጤቶችን ማምረቻ ሼድ ግንባታ ተከናውኗል እንዲሁም የሸማ ስራ ሙያ እንዲሰለጥኑ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፣ ለስራው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች እና የጥሬ እቃ ግብዓቶችም ተሟልተዋል።
❖ የሻማ እና የጧፍ መስሪያ ማሽን ግዢ ተከናውኗል።
❖ አካባቢው በተደጋጋሚ በድርቅ የሚጠቃ በመሆኑ ለገዳማዊያኑ የተሻለ ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
❖ ወደ ገዳሙ የሚያደርስ 8 (ስምንት) ኪሎ ሜትር ደረጃ አንድ የጠጠር መንገድ ሥራ ተሰርቷል።
❖ የእናቶች የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ተከናውኗል
❖ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ማቡኪያ ማሽን፣ የብረታ ብረትና የእንጨት መስሪያ ማሽነሪ ግዥ ተፈጽሟል
❖ የገዳሙ ይዞታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ያልነበረው በመሆኑ የገዳሙ ህጋዊ ይዞታ እንዲረጋገጥ ተደርጓል።
❖ ገዳማዊያኑ ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዲያመነጩ በማሰብ በሃሙሲት ከተማ የሸቀጣ ሸቀጥ እና የንዋያት ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ተከፍቶ ወደ ስራ ተገብቷል።
❖ ለግንባታ የሚውል በሃሙሲት ከተማ 30ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግስት በሊዝ በመውሰድ የአብነት ት/ቤት፣ አለማዊ ት/ቤት እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ በተጨማሪም ሌሎችም ገዳማዊያን አስፈላጊ የሆኑ የልማት ስራዎች የሚሰሩበት ይሆናል።
ከሚዲያው አካባቢ በተለይም ቲክቶክ አንዳንድ ቲክቶክሮች የገዳሙ አባቶችን ሆነ የቤተክርስቲያን መዋቅር ምንም አይነት መረጃ ሳይጠይቁና ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በይመስለኛል ብቻ፣ የገዳሙንም የተከታዮቻቸውንም ክብር በማይመጥን መልኩ ተገቢና ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን ማሰራጨት ተገቢ አይደለም ተብሏል።
በቀጣይ ለሚሰሩት የልማት ሥራዎች ማከናወኛ የሚሆን ድጋፍን ለማሰባሰብ በቀጣይም የተለያዩ መርህ-ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል።
ለአብነትም፡-
❖ ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ምዕመኑ ከገዳሙ በረከት እንዲያገኙ እንዲሁም ገዳሙን እንዲጎበኙ የጉዞ መርሃግብር ተዘጋጅቷል።
❖ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሚከናወን ይሆናል።
❖ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቃውንት ቤተክርስቲያን በተገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉባኤ ይኖረናል፤
❖ የሚዲያ ንቅናቄ ዘመቻውም እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም ከቤተ ክርስቲያን የሚዲያ አካላት ጋር በመነጋገርም ዶክሜንተሪዎችን እንዲሰሩና ምዕመኑ ገዳማዊያኑ ያሉባቸውን ችግሮች በመረዳት ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማስቻል ስራዎች የሚሰሩ ይሆናል፡፡

ዐቢይ ጾም ሰኞ የካቲት 17 ይገባል
በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡-
ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡
ቅድስት
ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን ቅድስት የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡
ምኩራብ
ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡
መጻጉዕ
ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡
ደብረ_ዘይት
ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡
ገብርኄር
ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡
ኒቆዲሞስ
ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
ሆሳዕና
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡

በቤታችሁ ለመገልገል ክፈሉ? በየትኛው መመሪያስ ነው ይሄን ያህል የሚያስከፍሉን?
አንድ ወዳጄ ከሰሞኑን አግብቶ ስንጫወት የሰርግ ወጭ ነገር ተነሳ።
አንድ ወጭ ላይ አስደገምሁት አረጋገጠልኝ።
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ በሥርዓተ ቤ/ክ ለማግባት 10,000 ብር ተጠይቆ ከፍሏል።
አስቡት ወጣቱ ጠፋ ምናምን የሚል አስተዳደር እንደእግዚአብሔር ቃል ራሴን ጠብቄ ኑሬያለሁ አሁን በክብር በቤቴ በስጋ ወደሙ ልሞሸር ይገባል ብሎ ሲመጣ ትክፍላለህ ሲባል።
በዚህ ስገረም አንዱ እንዲህ አለኝ እኔ እንዳውም ላገባ ስል ቤ/ ክ አጥቼ ብዙ ለፋሁ አለኝ። ለምን? ስለው ብትከፍልም ብዙ ሰርግ አለብን ሥርዓቱን አንፈጽምም እያሉ አንድ ቦታ ባለቤቴን ስለሚያውቋት እሽ አሉን አለኝ።
ተመልከቱ ወጣቱ ቤተ ክርስቲያኔ ብሎ ሲመጣ ሰው በዛብን ሲባል?
ደሞ ወዲህ የእግዚአብሔር ልጅነትን ለማግኘት ክርስትና ለማስነሳት ሲመጡ ይህን ያህል ብር ክፈሉ ሲባሉ….
ልጅነትን በገንዘብ?
አንዲት ደሃ ወልዳ ልታስጠምቅና ከክርስቲያንም ሕብረት ልትጨምር ስትሄድ ክፈይ ስትባል…😭
እውነት ነው አገልግሎቱ ገንዘብ ያስፈልገዋል። ነገር ግን ከመንግስት ቀጥላ ከፍተኛ ገቢ አላት የምትባልና ብዙ የሰው ኃይል የምታስተዳድር ቤ/ክ ለልጅነት ጥምቀት እና ወጣቱ ዓለምን ትቶ ለራሱን ጠብቆ ወደ መቅደስ ሲመጣ እንደመሸለም ማስከፈል ምን ማለት ነው?
ለሰርግ ከፍለን፣ ለጥምቀተ ክርስትና ከፍለን፣ ለሙት ዓመት መታሰቢያ ከፍለን፣ ለቀብር ቦታ ከፍለን፣ በጸሎት አስቡኝ ለማለት ከፍልን እንችለዋለን?
ደግሞ ከአጥቢያ አጥቢያ ያለው የክፍያ መጠን ልዩነት እኮ አንዱ ቀጥታ ገነት ሚያስገባ የሌላው ደግሞ ማያስገባ ነው ሚመስለው።
ሙዳዬ ምፅዋቱ ለማን ነው ሚዞረው? ታቦት ቁሞ ለማን ነው ሚለመነው? ለአገልግሎት እያላችሁ አይደል?
እስኪያለውን ገንዘብ ሀቅን ይዛችሁ አከፋፍሉት ለገጠር ለከተማ ይበቃል እኮ!
እኛ በተቀደሰችውና ፍጽምት በሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ለሰከንድ አንገት ደፍተን አናውቅም። በምድርም በሰማይም አለኝታችን ናትና!
በአስተዳደራዊ ጉዳይ ግን በስንቱ እንሸማቀቅ!!
ይህን ጉዳይስ ቅዱስ ሲኖዶስ ያውቀዋል?
ለቅዳሴው ሳያስከፍሉን አንድ በሉን!
(አንባቢ ሆይ ደግሞ በውስጥ መነጋገር ይቻል ነበር ምናምን በሉ አሏችሁ)
© መስከረም ጌታቸው

Forwarded from ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈ (👑 ናኦልዮጵያ ኢዮባዊ 👒)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ጾምን የምንጾመው ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ ነው::" ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የዐቢይ ጾምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ !
የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ /አዲስ አበባ)
ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው መነሻ <<ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ወደ በረኻ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡>> በማለት የጌታችንና አምላካችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጾሙን ጥንተ ነገር አውስተዋል።
ቅዱስነታቸው በአርባ ቀናት ውስጥ የጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዲያቢሎስ መፈተንና ድል መንሳትም አብራርተው ሲያወሱ <<በዚህ ጊዜ የጌታችን መልስ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” የሚል ነበረ፤
ጌታችን በዚህ አባባሉ የዲያብሎስን ክፉ ሐሳብ የሚንድ እንጂ የእሱ ታዛዥ አለመሆኑን ኣሳየ፤ ዲያብሎስ በዚህ ሳያበቃ በትዕቢት በፍቅረ ንዋይና በባዕድ አምልኮ ሊጥለው ደጋግሞ ሙከራ አደረገ፤ ግን አልተሳካለትም፤>> ብለዋል።
ቅዱስነታቸው የመጾማችንን ምክንያት ሲያጠይቁ <<...የዲያብሎስን ፈተናዎች እንዴት በድል ማለፍ እንደምንችል ጌታችን በተግባር ኣሳይቶናል፤ ጌታችን ዲያብሎስን ያሸነበፈበት ስልት በመንፈስ ልዕልና እንጂ በዱላም፣ በካባድ መሳሪያም ኣይደለም፤ አለመሆኑንም የድርጊቱ ሂደት በግልጽ ያመለክታል፤ እንግዲያውስ እኛም ዲያብሎስን የምናሸንፈው በዚህ የመንፈስ ልዕልና ነው ማለት ነው::... ስለሆነም ጾምን የምንጾመው በዚህ ስልት ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ ነው::
ከዚህ አኳያ ዲያብሎስን ለማሸነፍ መጾም ግድ ስለሆነ ጌታችን በከፈተልንና ባሳየን መንገድ እንጾማለን>> ብለዋል።
ስንጾምም <<የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት፣ ከዚያም ከቃሉ በተነገረን መሠረት የተራቡትን ልንመግብ፣ የተራቈቱትን ልናለብስ፣ የተጣሉትን ልናስታርቅ፣ ፍትሕ ያጡትን ፍትሕ እንዲያገኙ ልናደርግ፣ ለንኡሳን የሕብረተ ሰብ ክፍሎች የተለየ ትኵረት ልንሰጥ፤ እኩልና ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል በሰው ልጆች መካከል ልናረጋግጥ፣ ሰብኣዊ ክብር እንዳይነካ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ አደገኛ የቃላት ውርወራና መነቃቀፍ እንዲቀር ልናደርግ ነው፤>> በማለት አጽንዖት ሰጥተው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

#ዘወረደ_አራት_ነገሮች_ይነገሩበታል 👇
1.የአዳም ከገነት ወደ ምድረ ፋይድ መውረድ
2.የወረደውን ለመመለስ የአካላዊ ቃል ከሰማይ መውረድ
3.ከሰማይ የወረደው ጌታ የተሰቀለበት የዕፀ መስቀል ከኢየሩሳሌም ወደ ፋርስ መውረድ
4.ክርስቶስ የወረደለት የእኛ ሰውነት ከጽድቅ ከቅድስና ወደ ኃጢአት መውረድ በሥጋ ወደ መቃብር በነፍስ ወደ ሲኦል ይነገርበታል!
ለአራቱም ከፍታ/መመለስ/ትንሣኤ/ዕርገት አላቸው 👇
1.አዳም ወደ ገነት ተመልሷል
2.ክርስቶስም ወደ ሰማይ ዐርጓል
3.ዕፀ መስቀሉም በንጉሠ ሮም ኅርቃል አማካይነት በምእመናነ ኢየሩሳሌም ጾምና ጸሎት በ 614 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል
4.እኛም በንስሐ እናርጋለን (ወደ ጽድቅ ወደ ቅድስና እንመለሳለን)
አጠቃላይ የጾሙ ምሥጢርም ይኸው ነው
ከፍታ የሚነገርበት በይቅርታ እግዚአብሔርን የምንመስልበት የሥጋ ሳይሆን የመንፈስ ለውጥ የምናሳይበት ነው!
👉ጾም ዕድል ነው
• የመለወጥ እድል
• ንስሓ የመግባት ዕድል
• የመቁረብ ዕድል
• ራስን የማየትና የማዳመጥ
• የጽሙና የፀጥታና የመረጋጋት ዕድል
• የጸሎትና የስግደት
• የማስቀደስ ...ከመላእክት ጋር ከቅዱሳን ከጻድቃን ከሰማዕታት ጋር የማመስገን ዕድል
• በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን የምሕረት ፊት የማየት ዕድል ነው!!!
ጾሙን ለምሕረትና ለበረከት ድል ለመንሣት ያድርግልን🙏
ሠናይ ዐቢይ ጾም!
Via ------- መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእግዚአብሔር አንድነት #በሰንበተ #ክርስቲያን (#እሑድ) #ቀን #የሚነበብ #የኪዳነ #ምሕረት #ድርሳን #ይህ #ነው።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለእናቱ መልሶ ለሚወዱሽ ሰዎች ሁሉ መሸጋገሪያ ሁኝ አላት። በአንቺ መሰላልነት ከምድር ወደ ሰማይ ያርጋሉ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ ብዬ በወንጌል ለሐዋርያት እንደተናገርሁኝ። (ዮሐ. 12፥32)
የምስበው በምንድን ነው? የቸርነቴ መሰላል አንቺ አይደለሽም? አባቴ የመረጣቸውን ሁሉ በአንቺ ወደ እኔ አቀርባለሁ።
መድኃኒታችን ክርስቶስ ለእናቱ ለማርያም እንደዚህ አላት።
እኛስ ለወደደን ፈጣሪያችን ምን ዋጋ እንከፍለዋለን? ቸር እናትን ይቅር ባይ ንግሥትን ለአስገኘልን ምን እንከፍለዋለን? ፊትዋ ከፀሐይና ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ የሚያበራ፣ ከበረድ ከወተት ንጹሕ የሆነች፣ ነገሥታቱ ቤት ካለው የተክል ቦታ ዕፅዋት ይልቅ መዓዛዋ የሚያውድ፣ ከመላእክት ይልቅ ኅሊናዋ ንጽሕ የሚሆን፣ ክርስቶስን በሥጋ የጸነሰች፣ ከልዑላኑ ከነቢያት ከሐዋርያት የበለጠች ከክቡራን ይልቅ የከበረች የነቢያትና የዳዊት ልጅ ይህች ድንግል ናት። የሴቶች ሁሉ መመኪያ የምእመናንም ሁሉ ክብራቸው ይህች ናት።
ስለዚህም ለአከበራት ለአነጻት ለአብ፣ ከእርሷ ተወልዶ ሰው ለሆነ ለወልድ፣ ከሥጋና ከነፍሷም ላልተለየ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ስግደት ይገባል እንላለን። ለዘለዓለሙ አሜን።
መድኃኒታችን ለእናቱ እንዲህ አላት የቃል ኪዳንሽን መጽሐፍ የጻፈው ያጻፈው፣ አንብቦ የተረጎመ፣ ቃሉን ሰምቶ በልቡ የጠበቀ ሰው ሁሉ ከአንቺ ዋጋቸውን ያገኛሉ። ከእኔና ከአንቺም ጋር በአንድነት ይኖራል፤ ለዘለዓለሙ አሜን።
ምንጭ፦
ድርሳነ ኪዳነ ምሕረት፣ ገጽ 130 – 131፣ ቁጥር 1 – 8፣ 2001 ዓ.ም

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሥርዓተ ማህሌት በጃቴ ኪዳነ ምህረት በሊቃውንቱ አሸብርቋል