ከተለያዩ ወረዳ ማእከላት እና ግንኙነት ጣቢያዎች ለተውጣጡ የደረጃ አንድ ተተኪ መምህራን ሥልጠና መሰጠቱን በማኅበረ ቅዱሳን የአሶሳ ማእከል ገለጸ።
የካቲት ፬/፳፻፲፯ ዓ. ም
ማኅበረ ቅዱሳን በአሶሳ ማእከል በስብከተ ወንጌልና በዜማ አገልግሎት ዋና ክፍል አዘጋጅነት ከወረዳ ማእከላት እና ከግንኙነት ጣቢያዎች ለተውጣጡ ከ26 በላይ ለሚሆኑ ሰባኪያነ ወንጌል የደረጃ አንድ ተተኪ መምህራን ሥልጠና በመንበረ ሠላም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ አዳራሽ ውስጥ ከጥር 30 እስከ የካቲት 02/2017 ዓ.ም ድረስ ተሰጥቷል።
የማእከሉ የስብከተ ወንጌልና የዜማ አገልግሎት ዋና ክፍል አስተባባሪ ዲያቆን ወርቁ ጋሹ እንዳሉት የተሰጠው ሥልጠና በነገረ ሃይማኖት፣ነገረ ቅዱሳን ፣በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ፣ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲሁም በሐዋርያዊ ተልዕኮ ትምህርቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አስተባባሪው አክለውም ሥልጠናው ተተኪ ሰባኪያነ ወንጌልን ማፍራት፣ ምእመናን በአካባቢያቸው ቋንቋ ትምህርተ ወንጌልን አንዲማሩ እና ሠልጣኞች ባገኙት ዕውቀት አዳዲስ አማንያንን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዲያደርጉ ነው ብለዋል፡፡

በአውሮፓ ማእከል የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት የገጽ ለገጽ ስብስባ ማካሄዱ ተገለጸ።
የካቲት ፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማእከል የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት የዘንድሮውን ዓመት የገጽ ለገጽ ስብሰባ በዴንማርክ ኮፐንሀገን ከተማ ደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ከጥር 30 እስከ የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂደዋል።
በስብሰባው የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ዴሬሳ፣ አገልጋይ ካህን ቀሲስ ኃይለ ጊዮርጊስና የዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ አባላት ተገኝተዋል።
በዚህም የማእከሉ የ6 ወራት የአገልግሎት አፈጻጸም፣ የንዑሳን ማእከላትና የግንኙነት ጣቢያዎች አሁናዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል በመምከር ለቀጣይ የማእከሉ የአገልግሎት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
"መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት" በሚል ርእስም በአባ ዘሚካኤል በማኀበራዊ ሕይወት ዙሪያ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ከመደበኛ የአገልግሎት ክንውን በተጨማሪም መንፈሳዊ ሕይወትን በሚመለከት የምክክር መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡
የገጽ ለገጽ ስብሰባ፥ የማእከሉ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት በአካል በመገናኘት ይበልጥ የሚተዋወቁበትና የሚወያዩት በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ ልዩ መርሐግብር ነው፡፡

ዕቅበተ እምነትና ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ጉባኤ መካሄዱን በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ታቦር ማእከል አስታወቀ ።
የካቲት ፭/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ታቦር ማእከል ዕቅበተ እምነትና ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ጉባኤ ከየካቲት 01- 02/02/2017 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም ቤ/ክ አከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ መምህረ መምህራን የኔታ በጽሐ ዓለሙ በደ/ታቦር ደ/ልዑላን መድኃኔዓለም ቤ/ክ የ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር መምህር፣ መ/ር ልሳነወርቅ አእምሮ የጉባኤ ቤቱ የሐዲሳት መምህር እና መ/ር ተመስገን ዘለዓለም በፍኖተ ሰላም ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት የሐዲሳት መምህር ተገኝተዋል።
መምህራኑም ዕቅበተ እምነትና ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ትኩረት ያደረገ ማብራሪያ በትምህርት እና በምክረ አበው መልኩ ሰጥተዋል።

“ሃሎ መምህር” የተሰኘ ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት መጀመሩ ተገለጸ።
የካቲት ፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት “ሃሎ መምህር” የተሰኘ ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።
የስብከተ ወንጌልና ዕቅበተ እምነት ዋና ክፍል ምክትል ኃላፊ ዲያቆን ዐብይ ጌታሁን እንደገለጹት አገልግሎቱ በዋናነት የስብከተ ወንጌልን ተልዕኮ ለማዳረስ በተለይ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ምዕመናንን በእምነታቸው እንዲጸኑ ለማድረግና ከአዳዲሰ አማንያን የሚመጡ ጥያቄዎችን ለመመለስ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተጀመረ 5 ቀን የሆነው ይህ አገልግሎት ከ 30 እስከ 40 ለሚሆኑ ምዕመናን ለጠየቋቸው ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱን በመግለጽ ሰዓቱን ያልጠበቁ የስልክ ጥሪዎችን ለማስተናገድ ፈተና እንደሆነባቸው አክለው ገልጸዋል።
በዚህም ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 4፡00 - 10፡00 ሰዓት አገልግሎቱ የሚሰጥ ሲሆን ሰኞ፣ ረቡዕና ዓርብ በኦሮምኛና በአማርኛ እንዲሁም ማክሰኞና ዓርብ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ም/ኃላፊው የምዕመናን ተሳትፎ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው “በተለያየ ምክንያት መማር ያልቻሉ፣ ጥያቄ የፈጠረባቸውና በአካል መገኘት ለማይችሉ ምዕመናን በያሉበት ስልክ በመደወል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት ቢችሉ ከሃይማኖት እንዳይወጡና ከቤተ ክርስቲያን እንዳይለዩ ይረዳቸዋል” በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

፲፫ተኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 23 እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የካቲት ፰/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አማካኝነት በየሁለት ዓመቱ የሚዘጋጀው ፲፫ተኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 23/6/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበበ በዳዳ ገልጸዋል።
ሥራ አስፈጻሚው እንደገለጹት የመርሐ ግብሩ ዓላማ በከፍተኛ የት/ት ተቋማት የሚማሩ ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች በቤተ ክርስቲያን አሁናዊ ሁኔታና በማኅበረ ቅዱሳን በአጠቃላይ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዙሪያ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ግንዛቤ የማስጨበጥና የበለጠ ለማገልገል እንዲተጉ ለማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቀዋል።
አክለውም ከ43 ማእከላት የተወጣጡ 450 የግቢ ጉባኤ አገልግሎት ዋና ክፍል አባላትና ተሳታፊዎች እንዲገኙ እንደ ዕቅድ የተያዘ ቢሆንም አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታና በበጀት እጥረት ምክንያት ከ300 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል ብለዋል።
ሴሚናሩ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን ማኅበሩ በግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር ለመገምገም እና ለወደፊት የተሻሉ አቅጣጫዎች ለማስቀመጥ እንደሚያግዝ ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ወጣቶች መንፈሳዊ አገልግሎትን እና ቤተ ክርስቲያንን እንዲያውቁ በግቢ ጉባኤያት በኩል እያስተማረ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ አበበ አያይዘውም የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት ሲልኩ ወደ ግቢ ጉባኤያት መሄድና መማር እንዲችሉ በማድረግ በሁለቱም በኩል እንዲጠነክሩ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።