Telegram Web
ፍርድ ገምድ
የመጨረሻ ክፍል

ሜሪ ፈለቀ

ከአምስት ዓመት በኋላ የአባቴ አባት አያቴ አርፎ ለቅሶ ልደርስ ሄድኩ።ከማንም ሳላወራ ቀብሬ ልመለስ አቅጄ ነበር የደረስኩት። አባቴ ለቅሶው ላይ አልነበረምና ያለበትን አውቅ ከሆነ እየደጋገሙ በየተራ ያደናቁሩኝ ጀመር። እስከማስታውሰው ከአባቴ ጋር ብዙም የማይዋደዱት ወንድሙ ፤ ልጅ ሆኜ ከዘመዶቼ ሁሉ አብዝቼ የማቀርበው አጎቴ እጄን ይዞ እየመራ ወደውስጥ ይዞኝ ገብቶ በመጨነቅ ስለአባቴ ጠየቀኝ። ተፈጥሮ የነበረውን ሳስረዳው ግራ የተጋባ መሰለ። «በምን ሂሳብ ነው ሞገስን ለእናትህ ሞት ተጠያቂ ያደረግከው?» አለኝ። የሞቷ ቀን የተፈጠረውን እና የሀሳቤን መላ ምት እየነገርኩት አቋረጠኝ።

«ሞገስ በምን ምክንያት ነው የሞተችው አለህ?»
«ምንም አላለኝም። ማለትም አይጠበቅበትም ነበር።» እንደማመናጨቅ ዓይነት አቋረጠኝ። ሲጨናነቅ ከቆየ በኋላ «ሂድ እና አባትህን ካለበት ፈልገህ ይቅርታ ጠይቀው። ወይኔ ወንድሜን!! » ብሎ የሞተው አባቱ ሳይሆን ወንድሙ ይመስል ማልቀስ ጀመረ።

«ለምንድነው ይቅርታ የምጠይቀው? እናቴን ስለቀማኝ?»
«አንተ እንከፍ ሞገስ ለእናትህ ሞት ያበረከተው ምናምኒት አስተዋዕፆ የለም። ክፉ መገጣጠም ሆኖ የዛን እለት እርሙን እጁን ሲያሳርፍባት አየኸው እንጂ እናትህን ነፍሱ እስኪወጣ ነበር የሚወዳት። » አለኝ። ሲንቆራጠጥ ደቂቃ ፈጅቶ ደሜን ያቀዘቀዘ ታሪክ ነገረኝ።

«እናትህ ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራት። ከአባትህ በላይ የምትወደው ሰው ነበር። ከመሞቷ ከዓመታት በፊት ነው የምልህ። በኋላ አንድም አንተ ህፃን ስለነበርክ አንተን ከአባትህ ላለመለያየት ሁለትም በፍቅር የወደቀችለት ሰው በሰዓቱ ያልበሰለ እና ያልረጋ በመሆኑ ወደቤቷ ፊቷን መለሰች። ለአባትህ የተፈጠረውን ሁሉ ነግራው ይቅር ብሏት ነው አብረው የኖሩት። እሷን ከሚያጣ ዝቅ ማለትን ነበር የመረጠው። እሷ ግን እንደበፊቱ መሆን አቃታት። ከመሞቷ ከሳምንታት በፊት ከዛ ሰው ጋር መልሳ መገናኘት ጀመረች። አባትህም ለማወቅ ጊዜ አልፈጀበትም። እንደዛም ሆኖ ድጋሚ ይቅር ሊላት ዝግጁ ነበር። የዛን እለት ጠዋት ፀቡ ፍታኝ ብላው ነበር። አንተም ትልቅ በመሆንህ ደስተኛ ያልሆንኩበት ትዳር ውስጥ አልቆይም ብላ ስትወስን ያን ሁሉ ዘመን የጠበቃት ፍቅረኛዋ ሊቀበላት ቃል ገብቶላት ነበር። አብረው የሚኖሩትን የፍቅር ህይወት ሲያንሾካሽክላት ዓመታትን የባጀው ፍቅረኛዋ አባትህን ፍታኝ ብላ እቤቱ ስትመጣ ሀሳቡን ቀይሮ አገኘችው። ትነግረው የነበረው ሞገስም ትዳሩ እንዳንገሸገሸው፤ ትዳራቸው በሁለቱም በኩል እንዳበቃ ነበር። በመጨረሻዎቹ ቀናት ግን ድጋሚም እንደበደለችው እያወቀ ቤቱን ላለማፍረስ መታገሉን ሲሰማ ሞገስ ላይ እንደዛ የከፋ በደል መፈፀም አቃተው። ያኔ ነው ወደቤቷ ተመልሳ የዛን ከሰዓት ራሷን ያጠፋችው። »

«በፍፁም ይሄ ሊሆን አይችልም።እውነትስ ቢሆን ደግሞ አንተ ይሄን ሁሉ ነገር እንዴት አወቅክ?» እያልኩት ጭንቅላቴ መልሱን አቀበለኝ። እጄ ለቦክስ ተጨበጠ። ሸሸኝ።

«እንዳሰብከው ነው!! እኔን ለመቅጣት እና ለመበቀል የምታጠፋውን ጊዜ ያለበደሉ የቀጣኸውን አባትህን ለመካስ ተጠቀምበት።» ቢለኝም እጄ ታዝዞ አልተመለሰልኝም።

«የገዛ ወንድምህን ሚስት? እንዴት ዓይነት ክህደት ነው?» የራሴው እጅ እስኪያመኝ በጡጫ አንጉዬው ቀብሩን ሳልቀብር ወጣሁ። እንደእብድ ጭንቅላቴን ይዤ መንገድ ለመንገድ ብቻዬን እያወራሁ ተጓዝኩ። «አባቴ ሞቶ ቢሆን?» የሚል ሀሳብ ጭንቅላቴ ጓዳ ብልጭ ድርግም እያለ ጠጅ እንደጠጣ ሰው ጉልበቴን ይዞ አወለጋገደኝ።

ከቀናት ፍለጋ በኋላ ነበር መጠጥ ቤቱ ውስጥ ያገኘሁት።ለብዙ ደቂቃዎች ዝምም እንደተባባልን ቆየን። አሁንም ደግሜ

“ይቅርታ!” አልኩት። እጄን እጆቹ ላይ እያሳረፍኩ። አሁንም አልመለሰልኝም። የሚሞቅ እንባ እጄ ላይ ጠብ አለ። እናቴ ከሞተችበት ቀን በላይ ከፋኝ።

“ለምንድነው እውነቱን ያልነገርከኝ?” አልኩት

“እናትህ እኮ ነች! በህይወት ኖራ የማትክስህን ውድቀቷን ከቂም ውጪ ምን ሊጠቅምህ ልንገርህ?”

“ይቅር በለኝ!” አልኩት ድጋሚ

…….. ነገሩስ ጨርሰናል ….,,,

ውብ ዋሉልኝማ ❤️♥️♥️♥️

@maninet1
betsiroyal
1
ፍቅረኛዬ የተከራየችውን ቤት ቀይራ ወደ አዲሱ ቤት እቃ ስናጓጉዝ ሳለ በአጋጣሚ ዳጎስ ያለ ደብዳቤ እጄ ገባ ።

የሰው ልጅ የተሸጎጠ ነገር ለማወቅ ያለው ስምጥ ፍላጎት አይለካም ፤ ከተገለጠ ሙሉ ነገር የተሸፈነው ግማሽ ነገር ቀልቡን ያስተዋል።

በፍጥነት...

የዳጎሰ ወረቀቱን እና ፖስት ካርዶቹን መኪናዬ ውስጥ ሸጉጬው ተመለስኩ።

"የት ሄደህ ነው ?"

እንዳልሰማው ወደ እሷ እየተራመድኩ ሆን ብዬ ተደናቀፍኩ
"እኔን" አለች ተደናግጣ

አሁን ቀልቧን መበተኔን አየሁት ፤ "Attention divert" ማድረግ በተፈጥሮ መካኔን አውቃለሁ ።

አንዳንድ እውነት ውጤቱ ብቻ ምስክር ነው!!!

በጣም የናፈቀኝን ሰው ለማግኘት አይነት ሲመሽ ወደ ቤቴ በረርኩ የዳጎሰውን ወረቀት ለማንበብ።

ደረስኩ

የድሮ ፍቅረኛዋ የፃፈውን ደብዳቤ ማንበብ ጀመርኩ ፤ ፖስት ካርዱ ላይ የፃፋቸው ሃሳቦች ህይወት አላቸው ፤ ወረቀት ላይ ያሰፈራቸው ፅሁፎች ትናንት የሄዱበት መንገዶችን ይናገራል።

እንደሚያከብራት ፣

ሰርፕራይዝ ለማድረግ የሚሄድባቸው ልፋቶች ፣ ስለ ነገ ልጆቻቸው ስም ፤ ስለ ነገ መንገዳቸው የሚያወራት ፣

ስታኮርፍ የሚለማመጥበት መንገድ ፣ የእሷ የሆኑትን የሚያከብርበት ፤ የእሷን ጉዳይ ጉዳዩ አድርጎ መቁጠሩን ካነበብኩ በኋላ መለመላዬን የቀረው እስኪመስለኝ አስደነገጠኝ።

መቼ ነው የእሷ የሆነውን እንደምወድ በማስረጃ ያሳየኋት ፤ መቼ ነው ስለነጋችን እንድትናፍቅ አድርጌ የማውቀው ?

መቼ ነው ያልጠበቀችውን ባልጠበቀችው ሰዓት አድርጌ አስገርሜ የማውቀው ?

የጣዕም ልኬቷን ሰቅሎታል ፤ ሁሉም ሰው የራሱ የኑሮ ቀለም ቢኖረውም የእኔ እና የእሱ ሁኔታ ሩቅ ነው ።

እሷ ለእሱ የምትሆነውን ሩብ ያህል የምትሆንልኝ አይመስለኝም ፤ የጣዕም ልኬታችን በመጣንበት መንገድ መሞረዱ እሙን ሆኖ ሳለ የመጣችበትን መንግድ በጥንጡም ለመረዳት እንዴት አልሞከርኩም ?

አብሪያት ያለችውን ልጅ ትናንት እንዴት በጥበብ ለማወቅ አልጣርኩም ?

እንዴት ቀልቦን አልገዛኋትም ?

በዙሪያችን ፣ በእጃችን ያሉንን አለማወቅ የሚያክል ድክመት ያለ አልመስል አለኝ ።
© Adhanom Mitiku

@maninet1
@betsiroyal
👍42
የምናፈቅረው 'ሰውን' ወይስ 'ሰውነትን' ነው?
░▒▓█▓▒░▒▓█▓▒░▒▓█▓▒
..........በእኔ በኩል ከልባችን በላይ ሥጋችን የተዋኻደ ነበር፤ ጠረኗ ያሰክረኛል፡፡ ከንፈሯ ከንፈሬን ደርቆ ውሃን እንደተራበ መሬት ይናፍቀዋል፤ የዓይኖቿ ብሌኖች በመሐፀን እንዳለ ሕፃን በፈሳሽ የተከበቡ ናቸው። መቼ ነው የምታለቅሰው? የሚያስብሉ፤ ቸልተኝነቴ አጥንቷ ድረስ ዘልቆ እንደሚያማት ይገባኛል፡፡

ብዙ ጊዜ ዕንባ በዓይኖቿ ሲሞላ ታዝቢያለሁ፡፡ ግን አታለቅስም ነበር፣ ዕልኸኛ ናት፡፡ ዕልዃን እወደዋለሁ፡፡ ሲበዛባት አለቀሰች፤ ዕንባዋ እንደ ጠበል ከተጠናወተኝ የጅልነት መንፈስ የሚፈውሰኝ መስሏት፡፡ ሐዘኗ ውስጤን ያመኝ ነበር፡፡ ተገናኝተን በተለያዬን ቁጥር፣ ካላፈቀርኳት ለምን ጊዜዋን አባክናለሁ? እል ነበር ለራሴ... ያ ሐሳቤ ግን ከከንፈሬ አልፎ አያውቅም፡፡ ዛሬ ላይ ግን ቅጥ ያጣ ራስ ወዳድነት ነበረ እላለሁ።

ለሴት ልጅ ሰውነት በፍቅር መውደቅ፣ ማንነትን ከማፍቀርም በላይ ኃያል እና አደገኛ ነገር ነው፡፡ ብዙዎች ሰውነትን እና ሰውን በማፍቀር መካከል ያለውን ከጸጉር የቀጠነ መስመር መመልከት ተስኗቼው ሲወድቁ አይቻለሁ፡፡

ትዳር ሲፈራርስ፣ ልጆች ሲበተኑ ተመልክቻለሁ፡፡ ይመርመር ቢባል “የፍቅር” ተብለው የተገጠሙ ግጥሞቻችን እና የተዘፈኑ ዘፈኖቻችን የቆንጆዎችን ቆዳ ማለፍ የተሳናቼው የገላ አምልኮዎች ሳይሆኑ አይቀሩም፤እንደ ንቅሳት ቆዳ ላይ የተሳሉ ቆዳ ሲጨማደድ አብረው የሚኮማተሩ። ያቺን ቀጭን መስመር ማዬት የሚቻለው፣ እውነተኛ የፍቅር መነፅር ካጠለቅን፣ አልያም ከራስ ወዳድነት ሕመም ከተፈወስን ወይም ደግሞ ጸጉር ሰንጣቂ ነፍስ ካለን ብቻ ነው፤ ይቻላል ወይ? ይላሉ ብዙዎች፣ ካልቻላችሁ መጭውን ቻሉት ከማለት ሌላ ምን ይባላል?!
░▒▓█ ░▒▓█▓▒░▒▓█▓▓
📚 አልተዘዋወረችም
✍️ አሌክስ አብረሃም
📄 17
👍2🥰2👏2
ፀጉር ቆራጩ ደምበኛውን ያዝናናል ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች በማጫወት ላይ ነው።
“ያ ይታይሃል?...አስፖልቱ ዳር የተቀመጠው ልጅ..?”
“አዎ”
“ከምታስበው በላይ ጅል ነው”
“እንዴት? ”
“ቆይ ላሳይህ” አለና ፤ወጣ ብሎ ልጁን ጠርቶ ወደ ውስጥ አስገባው።
“ተመልከት እንግዲህ..”

ከኪሱ አንድ የአምስት ብርና አንድ የአስር ብር ኖት አወጥቶ ሁለቱንም መሬት ላይ ጣላቸው ከዛ ልጁን “ ከሁለቱ ትልቁን ብር አንስተህ ሂድ” አለው። ይሄኔ ያ ልጅ አምስቷን ብር ብድግ አርጎ ወደ መጣበት ይመለሳል።
“አየህ ይሄን ደደብ?...በዚ እድሜው አምስት ብርና አስር ብርን መለዬት አይችልም!!”
“በጣም ሚገርም ነው” አለ ፀጉሩን ሊቆረጥ የመጣው ሰውዬ ባዬው ነገር የእውነትም ተገርሞ።

አስተናግዶት ከጨረሰ በኋላ ተሰነባብተው ተለያዩ። ይሁን እንጂ ያ ሰውዬ ቅድም ባየው ነገር ተገርሞ ብቻ ሊቀር ስላልፈለገ ልጁ ወዳለበት ሄዶ ያሳሰበውን ነገር ጠየቀው
“እውነት አንተ..አስር ብር እና መቶብርን መለየት አትችልም?”
“አዪዪ..” አለ ልጁ
“አዪዪ..10 ብሩን ያነሳሁ ቀንማ ጨዋታው ያበቃል”

by Yosef Gezahegn

@maninet1
@maninet1
@betsiroyal
🔥5👏2
* ይለቀቅ?
👍5🔥1
የሐበሻ ቀልዶች .pdf
32.1 MB
📙የሀበሻ ቀልዶች
✍️አሰፋው መኮንን
@maninet1
@maninet1
@betsiroyal
👍4
አገባሁ...ወለድኩ...ደገምኩ...ሠለስኩ:: እሱን እያፈቀርኩ ከወንድሙ ሦስት ልጆች ወለድኩ:: እሱን እየተመኘው ወንድሙን አገባሁ:: ካሳለፍናቸው 3 የUniversity ጓደኝነት አመታት በኃላ እንደተመረቅን ነበር ላገኘው እንደምፈልግና ብቻውን እንዲመጣ የነገርኩት ገና ተደላድሎ ከመቀመጡ ነው " አፈቅርሀለው" ያልኩት ::ሳቀ በሀይል ሳቀ
"አንቺ ያምሻል እንዴ ለቁም ነገር ነው ምፈልግህ ስትይኝኮ ምን ሆነች ብዬ ስንት ነገር ነው ጥዬ የመጣሁት ትቀልጃለሻ አንቺ ሆሆ " አየሁት .. እነዛ መጀመሪያ ካየዋቸው ቅፅበት ጀምሮ ራሴን ያሳጡኝን አይኖቹን ትኩር ብዬ አየዋቸው ::ሚያረገው እየጠፋው ሁሌ እንደሚጠራኝ
" ቃሊ የምርሽን ነው እንዴ "
"አዎ አፈቅርሀለው" ፊቱን በአንዴ ወደ ግራ የተገባ ፊት ቀይሮ " ከመቼ ጀምሮ ቃሊ?"
"ከመጀመሪያው የሁለተኛ አመት የትምርት ቀናችን ከማክሰኞ ከመስከረም 22 ጀምሮ" ደነገጠ " ቃሊ please አታሹፊብኝ " ፊቱ ሲቀላ እየታወቀኝ መጣ
"ምንም እንድትለኝ አይደለም ብንጋባ ብታፈቅረኝ ምንምን በደስታ ልሞትብህ ስለምችል አላቅም ግን እህቴ ነሽ ምናምን እንዳትለኝ ደሞ" መንተባተብ ጀመርኩ ::
"ቃሊ"
"ወዬ" ልቤ በፍጥነት ስትመታ ይታወቀኛል
"ኤላኮ ያፈቅርሻል" ፊቱ ማላቀውን እሱን ሆነብኝ..ውስጤ ሲፈረከስ ተሰማኝ ኤላ ማለት? ኤላ የሱ ወንድም? ማለት መንታ ወንድሙ ኤላ ? ኤላ ጓደኛዬ? ኤላ ኤላ ውስጤ ተተራመሰ.....በመልክም በአመልም ምንም አለመመሣሠላቸው ሲገርመኝ ነበር ሶስቱን የጓደኝነት አመታት ያሳለፍነው :: ሁሌም አብረን ነበርን እሱም..ኤላም...እኔም :: በሁለት መንታ ወንድማማቾች መሀል ያለው ብቸኛ ጓደኛቸው በመሆኔ ጊቢ ውስጥ እንደኔ ደስተኛ ሰውም የነበረ መኖሩን እኔንጃ እኔን መሀል አርገው ሲተራረቡ መስማት...ሲበሻሸቁ...አንዳቸው እንዳቸው ላይ ሲቀልዱ ...እጄን የኔው ተፈቃሪ እንደቀልድ በቦክስ ሲመታኝ ኤላ ሲቆጣው...ተሸክመውኝ ሲሯሯጡ ላየን 3 መንታዎች እንጂ ማልዛመዳቸው መሆኔን ማንም አይጠረጥርም አንዳንዶቹ ደሞ የማንኛው ናት እንደሚሉም አቃለው :: የጊቢው ሴቶች ደሞ ኤላን ይወዱት ስለነበር እንዳጣብሳቸው ሚወተውቱት እኔን ነው ኤላ ግን ወይ ፍንክች ስለሚል ማጣበሱ አልተሳካልኝም ነበር :: ሲፈጥረኝ ከሴት አትዋደጂ ያለኝ ይመስል ከልጅነቴ ጀምሮ ሴት ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም ጊቢ ገብቼም የመጀመሪያውን freshman አመት ከማንም ጋር አልግባባም ነበር ከዛ ግን ሁለተኛ አመት ላይ ምንማረውን ትምርት መርጠን ስንመደብ እነሱን አገኘው ለዛም ነበር በጓደኝነታችን ደስተኛ የነበርኩት :: ከ6ኪሎ ጊቢ በታች ያሉ ማሚ ቤቶች ሄደን ምሳ ስንበላ በእጄ ከአንድ ጉርሻ በላይ ስጎርስ አላስታውስም በሁለቱ የፉክክር ጉርሻ ነበር ጠግቤ ምነሣው በዛ ላይ ሳየው ገና ልቤ የደነገጠለት ልጅ ጓደኛ ሆኜ ስስቅ መዋል ..ደስታ ማለት እኔ ነበርኩ:: "ጉድና ጅራት ወደ ኃላ ነው" አሉ....ያን ቀን "ኤላኮ ያፈቅርሻል " ሲለኝ ጉሮሮዬም ልቤም አይምሮዬም ደረቀብኝ ጎኔ ያለውን ግማሽ ኮካ አንስቼ ጨለጥኩት ::
"ኤላ የቱ" አይኖቼ ሲፈጡ ይታወቀኛል
"ቃሊ ኤላ የኛ ነዋ "ፊቱ የማላቀው ቋንቋ ፅሁፍ ሆነብኝ አየዋለው አይገባኝም ::
"ከመቼ ጀምሮ?" እሱ እንዳለኝ እኔም አልኩት ማወቄ ይቀይረው ያለ ነገር ይመስል
"ካየሽ ቀን ጀምሮ ቃሊ ትዝ ይልሻል class እንደጀመርን ካፌ አጊኝተንሽ ብቻሽን ከምትበዪ ከኛ ጋር ምሳ አብረን እንብላ ብዬሽ አብረሽን የዋልሽ ቀን " እንዴት እረሳዋለው ያን ቀን በአይን ካፈቀርኩት ሰውጋር አምላክ አገናኘኝ ብዬ በደስታ ስፈነድቅ ነበር የነጋው :: ፀጥ ብዬ ሳየው ወሬውን ቀጠለ "ያን ቀን ማለት ኤላ ካላስተዋወከኝ ብሎ ሲለምነኝ ነበር ታውቂያለሽ ቃሊ ኤላን ከማህፀን ጀምሮ ሳውቀው ከአፉ ወቶ ሚያውቀው የሴት ስም ያንቺ ብቻ ነበር :: ቃሊ ኤላ አንቺን ስለማግባት ካንቺ ስለመውለድ ብቻ ነውኮ ሚያልመው ደሞ እሱም ከዛሬ ነገ እነግራታለው እያለ ነውኮ የተመረቅነው ቃሊ ኤላን ያዢው ወንድሜ እስከነፍሱ የሚያፈቅራት ሴት ታፈቅረኛለች ብሎ ማሰቡ ለኔም በሽታ ነው ቃሊ ደና ዋይ ኤላን ያዢው" ብሎኝ ነበር በተቀመጥኩበት ጥሎኝ የሄደው "ኤላን ያዢው" ይሄን ነበር ያለኝ :: .....እኔም ኤላን በእጄ በልቤ እሱን ይዤ ይኸው ሶስተኛ ልጃችንን ወለድን:: .....ኤላ ህልሙን ኖረ እሺ እኔስ?? የሱ ህልም ማስፈጸሚያ ልሆን ነበር የተፈጠርኩት? ያፈቀሩትን ስለማግኘት ኤላ ያሟላው እኔ ያጎደልኩት መስፈርትስ ምን ነበር??? ልጆቼስ አጎታቸውን በልቤ አግብቼ እንደምኖር ያወቁ እንደሆነ እንዴት ይዳኙኝ ይሆን ? እንጃ....ሁሉም ያፈቀረውን አያገባም..ልክ እንደኔ::


By ቃል_ኪዳን


@maninet1
👍61😱1
በኢያሪኮ ከተማ አዝርግ.pdf
53 MB
📓ርዕስ፦ በኢያሪኮ ከተማ
✍️ደራሲ፦ አዘርግ

በደራሲው ፍቃድ የቀረበ

📚 @maninet1
👍3
[ Cultic Poetry - A Letter To Thyself ]

ኮቴህ ደረቅ ነው ፥ ዳናህ የለው ገድ
እስኪ አርፈህ ውድቅ ፥ አትወላገድ
ምን ልትፈጥር ነው ፥ የምትታገል?
አውቀህ ተሰበር ፥ ድቀቅ እንደ ገል

በቄንጥ አትርገጥ ፥ መውደቅ ፍራቻ
መንገድ ዳር ፍሰስ ፥ እንዳራሙቻ
እንቅፋት ሆነህ ፥ ሌላውንም ጣል
እሱስ ከመውደቅ ፥ ለምን ያመልጣል?

ልብህን ሰብረህ ፥ በል ቅደማቸው
ደምህን ሲያዪ ፥ ይፍላ ደማቸው
ስልክህን ዝጋ ፥ ከደጃፍህ ጋር
ሳራህን ተዋት ፥ ግባ ወደ አጋር

ማነው ጓደኛ ፥ ወዳጅ ምንድነው?
ስሱ ልብህን ፥ በል አደንድነው!
ምን አውራ ቢሆን ፥ ዶሮ አይጠመድ
እርባና ቢስ ነው ፥ ዘመድና አመድ

በርህ ላይ ጠላት ፥ ይንከላወሳል
ሰይፍህን ሞርድ ፥ ሻሞላህን ሳል
ግራህን መትቶ ፥ ቀኙን ላለ ሰው
ለጥፊው ምላሽ ፥ ዐይኑን አፍስሰው

ከእሪያ ተማር ፥ ሁን ታጥበህ ጭቃ
የጲጥፋራ ሚስት ፥ ትርታህ ጨቅጭቃ
ፍቀድ ልብስህን ፥ ታውልቅ መንጭቃ

[
አንቺም
ዳግማዊት ማርያም ፥ ፅድቁ ሚርብሽ
የዘመኔ አዳኝ ፥ ሲሻ ሊያድርብሽ
ብስራት ያለልሽ ፥ ሆኗል ስብራት
ቁርሳችን ሆነ ፥ የሻገተ ራት
በሺ ፍለጋ ፥ በብዙ ትግል
አገኘኹ ብሎ ፥ ንፅኂት ድንግል
መላክ ሲመጣ ፥ ዜና ለፋፊው
"ወንድ አውቃለሁ" በይ ፥ ቀልቡን ግፈፊው
]

ሙንጨራህን ተው ፥ ግጥምህን ቅደድ
የማይወድህን ፥ አንተም አትውደድ
ቃል የሰነፍ ነው ፥ አፈሙዝ ታጠቅ
ዝረፍ ከደሀው ፥ ካለው ላይ ንጠቅ

ማንም አይኑርህ ፥ ማንም አትኑረው
እያሪኮህን ፥ ብቻህን ዙረው
አታልቅስብን ፥ አትነፋረቅ
በዝምታ ውስጥ ፥ ከሞትህ ታረቅ!

ጎልጎታ ጫፍ ላይ ፥ ወጥተህ ተራራ
"ልሞት ነው" ብለህ ፥ አታስፈራራ
ምን ይጎዳና ፥ አንድ ኃጥዕ ሞቶስ
እንኳን አንተና ፥ ሞቷል ክርስቶስ
ኡኡታ ጩኸት ፥ አያስፈልግም
ማለት ነው`ንጂ ፥ ዝም ብሎ ፍግም!

ቢወዱኝ ብለህ ፥ ታግለሀል ብዙ
በልብ ገፉህ ፥ ባፍ ቢጋብዙ
አይፈልጉህም ፥ አትፈልጋቸው
ለርኩስ አይሆንም ፥ ንፁህ አልጋቸው!
ዓለም ገፋችህ ፥ ካለም ገንጥላ
ልክ እንደራስህ ፥ ሌላውን ጥላ!

እርም እርሙን ብላ ፥ ወይንህን ጠጣ
ከቶ አይግደድህ ፥ ማንም ቢቆጣ
እንኳን ለነገ ፥ ለዛሬ አትስጋ
አርብ 'ሮብ ሳትል ፥ አነክት ሥጋ
ተፀየፋቸው ፥ ቄሱና ሼኹን
በግነት ሲሹ ፥ አንተ ፍየል ኹን

በሾላ ዛፍ ላይ ፥ አትንጠላጠል
ትበልጥሀለች ፥ አንዲቷ ቅጠል
መርዘሙንማ ፥ እረዝመኸዋል
ግን አዳኝህኝ ፥ መች አይተኸዋል?

አካልህ የለው ፥ የሥጋ ሙዳ
ችጋር ወዳጅህ ፥ ኪስህ ቤርሙዳ
የያዝከው ሁሉ ፥ ዋጋ አልባ ጠጠር
ባርኮቱን ሳይሆን ፥ ብጉርህን ቁጠር!

ሲያይህ ይድነቀው ፥ ይግረመው እግዜር
አፍርቶ ሲያየው ፥ የበተነው ዘር

፨ ፨ ፨

በዚህ ሁሉ ግን ፥ ይህን አትርሳ
ታመውት ነበር ፥ ያንተ ነቀርሳ
በ'ነሱም ነበር ፥ ባንተ ያየነው
የሆንከው ሁሉ ፥ የሆኑትን ነው!

፨ ፨ ፨

[የሁለት ዓመት ታዳጊ የሆነ ግጥም - ፌስቡክ እንዳስታወሰኝ]
ዮናታን ጌታቸው
ከራሱ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ
🔥21
ብያት ነበር አንድሺ አንድ ጊዜ ነግሪያት፤ ትዳር ብለን ጎጆ ሳንመሰርት፣ ህይወትን በአንድ ጣራ ስር አሀዱ ብለን ሳንጀምራት በፊት............ደጋግሜ
ትዳር እጅጉን የከበረ የህይወት መዓድ ነው፣ ሊዳፈሩት የማይገባ በክብር የሚቋደሱት ቅዱስ ገበታ.........
ትዳር በፍቃድ መፍሰስ ነው፣ እንደውሀ........ በገዛ ፍቃድ ራስን ማፍሰስ፣ እንዳይታፈሱ ሆኖ፣ ሳይሰስቱ፣ ቆንጥረው ሳያስቀሩ አጋሬ ካሉት ሰው እግር ስር ካለስስስስት መፍሰስ፤ በፍቅር.........መቼም ላይታፈሱ..............

እንዳልኩት ሆነ........ እንዳልታፈስ ሆኜ ፈሰስኩ........
ግን.........ሳተች፤ የነገርኳትን ረስታው ይሁን ንቃው እንጃ..........ቆረሰቺኝ፣ እኔነቴን ሸራረፈችው፤ ሊጋሩት የማይገባን ተፈጥሮ አጋራችው። እሷነቷን፣ እኔነቴን ፣ሴትነቷን፣ ወንድነቴን በአንድ ሸክፋ አጋራቻቸው........... ለዛውም ከራሴ በላይ ለማምነው ወዳጄ። ወሬ አይደለም የሰማሁት፤ በአይኔ ነው ያየሁት በአይኔ በብረቱ............ ከዛስ ምን አደረኩ?

ሁለቱንም ባሉበት እጅ ከፍንጅ ፣ ከራሴ በላይ አምናችሁ ነበር እናንተ ግን.......፣ ፍቺ ምናምን.......... በፍጹጹጹም። ይልቁንስ.......... ምንም እንዳላየ እንዳልሰማ ሆኜ ከወትሮው ፍቅሬን ሳልቀንስ ተበቀልኳቸው። ለህሊና ዳኛ ለጸጸት ቁራኛ አሳልፌ ሰጠኋቸው። ከህሊና በላይ ተበቃይ ከወዴት አለ!? አንዳሰብኩት ነው የሆነው እንዳቀድኩት......

ከአንድም ስንቴ ራሴን ለሞት አሳልፌ እስከመስጠት መስዋትነት የከፈልኩለት ባልንጀራዬ ጸጸቱን መቋቋም ቢያቅተው በገዛ አንደበቱ ለፈለፈልኝ እግሬ ላይ ወድቆ እያለቀስ፣ “ባለቤትህን አስነወርኳት፤ ለውለታህ ይህን መለስኩልህ ማረኝ” አለኝ...........

እኔስ ምን አደረኩ? ፈነከትኩት አና......ቱን በጠርሙስ፣
ለምን እንደዛ አደረክ ብዬ አይደለም፤
አላምንህም ባለቤቴም አንተም ይህን አታደርጉም ከፈጣሪዬ እኩል ነው የማምናችሁ ብዬ............

ታሰርኩ........ባለቤቴ ልትጠይቀኝ መጣች። ከደህንነቴ በላይ የሰማቸው አሳስቧት ነው የመጣችው። ከገዛ አንደበቴ በገዛ ጆሮዋ ልታረጋግጥ............

«የሰማሁት እውነት ነው ወዴ?»
«ምን ሰማሽ»
«እሾህ ሲወጋው የምታነባለትን ጓደኛህን ፈነከትከው?»
«አዎ»
«ለምን?»
«ባንቺ መጣብኛ?»
«እ.......አ...አ...አመንከው?»(ተንተባተበች፤ ፈስ ያለበት....)
«ምኑን?»
«አ......ይ ማለቴ...... ባንቺ መጣብኝ ስትል!?»
«ባለቤትህን አስነወርኳት አለኝ»
«እ........»(በድንጋጤ ደርቃ ቀረች)
«ምነው?»
«አ....አ....አ.....ይ ምንም። ምን አይነት ባለጌ ሰው ነው! እንደዛ እየሆንክለት እንዴት ትዳርህን ለማፍረስ እዚህ ድረስ ይጓዛል.........? ሆሆሆሆሆ»

«እኮ እኔም ለዛ እኮ ነው አናቱን የፈነከትኩለት። ስፈነክተው ደሞ ዝም ብዬ አይደለም፤ ከፈጣሪዬ እኩል እንደማምንሽ እየነገርኩ፣ እንኳን እሱ አንቺ ራስሽ በገዛ አንደበትሽ አዎ እውነት ነው ብትዪኝ እንኳ እስከማላምንሽ ድረስ እንደማምንሽም ጭምር እየነገርኩት ነው የፈነከትኩት፤ ልክ አይደለሁ.........?»

ሳግ ተናነቃት.........እንባዋ አመለጣት.......... ስታለቅስ አለቅጥ ታሳዝነኝ ነበር.........ነበር ነው አሁን ግን አንዳች የደስታ ስሜት መላ ሰውነቴን አጥለቀለቀኝ፣ ደስስስስስ...... አለኝ። ጸጸት ሲሸነቁጣት፣ ስሜቷን መቆጣጠር እስኪያቅታት፣ በውብ ጉንጮቿ ላይ ኩልል በሚሉ የእንባ ዘለላዎቿ ውስጥ የጸጸት ረመጥ ይታየኛል........ሲፈጃት፣ ሲለበልባት..............

«ለምንድነው ምታለቅሽው የኔ እናት?»

«እሺ ነገሩ እ.....እውነት ቢሆንስ?(ሳግ እያደናቀፋት)»

ሆነ ነዋ በቃ........ሆነ። ከጸሀይ በታች አዲስ ነገር የለም፤ መኖር ይቀጥላል። ኢሄንን እኮ ነው ደጋግሜ የነገርኩሽ፤ ተንበርክኬ ቀለበት ያጠለኩልሽ እለት በገዛ ፍቃዴ እንዳልታፈስ ሆኜ ነው የፈሰስኩት ምንም እስካይቀረኝ፣ ጠብታ ስንኳ...........ታዲያ የትኛው የፈሰሰ ውሀ እንደታፈሰው ልታፈስ? የትኛውም በደል ፣ የትኛውም ስህተት ከፈሰስኩበት ትዳር፣ ከፈሰስኩበት ማንነትሽ አያፍሰኝም ካለሞት በቀር...........

የውስጧ ማዕበል ከቅድሙ በባሰ አናወጣት። እንባዋ በጉንጮቿ መንታ መንገድ አበጀ፣ ለቅሶዋ ሳግ ባፈነው ድምጽ ታጀበ...........

«እባክሽ አታልቅሽ የኔ እናት ነፍሴን አታስጨንቂያት»

አንዲት ቃል ተነፈሰች የመጨረሻ........የመሰናበቻ.....

«እኔ ላንተ የምገባ ሴት አይደለሁም።»

ሔደች........ቀናት አለፉ ሳምንታት...... ወራት...... ድምጿ ጠፋ ከነዘመድ አዝማዶቿ.......

ተፈታሁ.........ቤተሰቦቿ ከቤተሰቦቼ በአንድ ተሰባስበው ጠበቁኝ.........የሰላም ያይደለ፣ የደስታ ያይደለ ስብስብ፤ ጽልመት የወረረው፣ ጨለማ የነገሰበት ስብስብ፣ ጥቁር ግርማሞገስ የተጎናጸፈ ጭንቀትን የሚያነግስ ስብስብ........

እግሬ የቤቴን ደጃፍ እንደረገጠ ጫጫታና ወከባ........ ቤቱ ተተራመሰ.......ለቅሶ........ ወንድሟ መጣ

«ኤፍራታ ይህን አስቀምጣልህ ሔዳለች» ብሎ ደብዳቤ ሰጠኝና ተጠመጠመብኝ።
«ወዴት?»ልቤ ያሰበው እንዲሆን እየተመኘሁ ጠየኩ

«ራሷን አጥፍታለች»

እንደአዲስ ለቅሶ........ሶስት ወጣቶች ከበውኛል....... በድንጋጤ አንድ ነገር እንዳልሆን፣ ወይ ራሴን እንዳልጎዳ ሊይዙኝ........መሰለኝ...........

ደብዳቤውን ከፈቼ አነበብኩት ከዛስ?
ፈገግ.......... በዛ ሁሉ ሁካታ መሀል፣ በዛ ሁሉ ጫጫታ መሀል እንዳይሆን ይሆናል ተብዬ ስጠበቅ እኔ ግን ምን ሆንኩ?........... ፈገግ አልኩ............

እቅዴ ሰመረ..........ያባከኑኝን፣ ያጎደሉኝን፣ የካዱኝን፣ ያቆሰሉኝን የኔ ያልኳቸውን ሰዎች......... ሳልሰነዝር መታኋቸው........ከባድ ምት፣ ሊቋቋሙት የማይቻል......... ሳልነካ አቆሰልኳቸው፣ ከመሰረታቸው አነዋወጥኳቸው....... ናድኳቸው፣ ደረመስኳቸው..........በገዛ እጃቸው....... ከራሳቸው አፋጀኋቸው..........

ለወደዳቸው ካለስስት የፈሰሰ ማንነቴን ጠላሁት። በቃ ራሴን በምወድ ሰአት እንደራሴ ወደድኳቸው። ራሴን ስጠላ ደሞ እንደራሴ ጠላኋቸው።

ለዛም ነው ሞቷን ሲነግሩኝ ፈገግ ያልኩት ከወዳጄ እብደት ጋር ደሞ ይበልጥ ያስፈግጋል..........ህ...... ግን የውስጤን ማን ተረድቶልኝ!.........አሁን የት ነኝ?..........ጸበል ለምን? የሚስቱ መርዶ አሳቀው........ እናስ? እናማ በጤናው አይደለም.......... ስለዚህ ጸበል.........

አሁን ግን ጸበሉ ምኔን እንዳጠበው እንጃ ይጨንቀኝ ጀምሯል.....ጸጸት መልሶ ለኔ ሊሆን ነው መሰለኝ.....



ገፀ ሕይወት
3👍2😢1
አባቴ ካጠገቡ የማትጠፋ ራዲዮ ነበረችው። ኹለት ስፒከር አላት ካሴትም ታጫውታለች...

ፀሐይ በራኺን አስሬ ይሰማታል። አክስቴ ትመስለኝ ነበር፤ ድምጿ እኛ ቤት አይጠፋም ስትዘፍን እኩል እላለሁ ከሙዚቃው ጋር...

"መጀመርታ ፍቅሪ
ኣብ መን ተጀመረ
ኣዳምን ሔዋንን
አለም ምስተፈጥረ
ኣነ ከይፈለጥኩ
አብ ልበይ ሐደረ
እንታይ እሞ ክገብር
ዕድለይ ካብ ኮነ አይ..አይይ*

አባቴ ወታደር ነበር። ጠይም ነው መከፋቱ ፊቱ ላይ ብዙ አይታይም፤ ማጣቱ በየምክንያቱ አንደበቱ ላይ አይንፀባረቅም ....ዝምም ይላል

ረጋ ያለ ነው ።

ጥርሱን ሳያሳይ ነው ደስ ብሎኛል ፈገግታ ፈገግ የሚለው፤ ተገርሜያለሁ ፈገግታ ፈገግ የሚለው ተበድያለሁ ፈገግታ ፈገግ የሚለው አጠገቤ ሲሆን እረጋጋለሁ።

ሰሞኑን ሰውነቴ እንደከሳ፤ ፊቴ ማዘን እንደታከከው፤ ድብርት ነገር እንዳንጃበበብኝ አወቀ። አባትም አይደል? ንብረቱም አይደለሁ? ዋጋ ከፍሎብኝም የለ?

ፊቴን አይቶ "ደህና ነህ ህሉፌ ...?" አለኝ።

'እ ...ትንሽ ደከመኝ...
አሻግሬ ማየት እያቃተኝ... ቶሎ ቶሎ እጅ እየሰጠው ..." አልኩት።

ረጅም ሰዓት ዝም አለ ...

"ታስታውሳለህ በረሃ እያለሁ የምፅፍላችሁ ደብዳቤ፤ በርቱልኝ፥ ምን ጎደላችሁ፥ እወዳችኋላሁ፥ በቅርብ እደውልላችዋለሁ፥ እመጣለሁ፥ ዓይነት ይዘት ያለው ፅሁፍ ?! ።"

"ባሩድ እየሸተተኝ ነበር፥ አብሬው የዋልኩት ጓደኛዬ ሞቶብኝ፥ ፍንጣሪ ጥንት መ'ቶኝ፣ ጠላት ሊፈጀን እያቀደብን፣ ጀኔራላችን ምሽግ ሰብራችሁ ግቡ ሊለን እንደሚችል እያወቅን፥ የተቀበረ ቦንብ ልንረግጥ እንደምችል እያወኩ፥ ከአውሮፕላን የተወረወረ ፈንጅ ሊያወድመን እንሚችል እያወኩ፥ ነበር...አሻግሬ ተስፋ የማየው..."

ፋታ ወስዶ ቀጠለ...

"ልጆቼን እንደማገኛቸው፥ አባት እንደምሆንላቸው፥ ሚስቴን ዳግም እንደማገኛት ፤ቤተክርስትያን እንደምሳለም የፈንጂ ድምፅ ሳልሰማ እለት እለት የወደቀ ሬሳ ሳልሻገር እንደምኖር ተስፋ አደርግ ነበር ...

ስለመግደል የሚታቀድበት ስፍራ ላለመሞት የሚዘየድበት ቦታ አንድ ቀን እንደማልኖር አምን ነበር ...!

ተስፋን ሙጥኝ ብዬ ነው ዛሬን ያየሁት ። ያጋጠመኝን መውደቅ እና ሃዘን ህመም ችላ ብዬ ነው ያን በርሀ የተሻገርኩት !!

አጆኻ ዝወደይ ..
ሁሉም ሰው መስቀል አለው ልዩነቱ አይነቱ እና አሸካከሙ ነው !!"

By Adhanom Mitiku

@maninet1
@betsiroyal
2
ሌላ ሴት ልታገባ ያልክ ቀን እንኳ ብደውልልህ እሷን ትተህ እኔ ጋር ነው አይደል የምትመጣው? እለዋለሁ ሁሌ …. ፈገግ ብሎ ያየኝና “ደፋር ኮ ነሽ….ይለኛል።

ካለሁ ነገር ሁሉ እኔን አስበልጦ እንደሚወደኝ አውቃለሁ። ሲሳሳልኝ:ከራሱ ሲያስቀድመኝ: ሲጨነቅልኝ: ለኔ ሲኖር አይቻለሁ። ( በእርግጥ እንዲ ማለት ከባድ ይመስላል። እኔ ግን አይኑን ሳያርገበግብ : ይሄን ልጅ ግን ምን አስነክታው ነው እስኪባል የሚያውቁን ሁሉ እስኪገረሙ ድረስ ….ሳናድደዉ :ሳበሳጨው ችሎ በክፉ ቀናቶቼ ላይ ለደስታዬ ሲፈጋ: አብሮነታችንን ለማቆም ብዙ ሲለፋ አውቅ ነበር።)

ይመስለኛል የበዛ መውደዱ: የትም አይሄድም ብዬ እንዳስብ ለኛ እንዳልጨነቅና በተወዳጅነት ተኮፍሼ ለሚሰጠኝ መውደድና ክብር ትንሽ እንኳ አፀፌታን መስጠት የማልችል ሴት አደረገኝ።

ከዛ በአንዱ ቀን በትንሽ ነገር ተጋጨንና ….ሂድልኝ አልኩት። ለመነኝ:አስለመነኝ….ከቀልቤ መሆን ያልቻልኩት እኔ ግን ግድ አልሰጠኝምና ምንም እንደጎደለብኝ አልተሰማኝም። መሄዱ እንደሚያም: እንዴት እንደሚናፍቀኝ ለመረዳት ብዙ ረፈደብኝ።

ሄደ። ከዛ አልተመለሰም። ልመልሰዉ ሞከርኩ….መሄድ አለማምጄው ኖሮ መመለስ አቃተኝ።

እናማ አሁን የገፋሁት እኔ: ወዶኛል አይጠላኝም ያልኩት እኔ: በተራዬ እጅግ እየናፈቀኝ:እያመመኝ :እያስመሰልኩ አብሮነታችን ማክበር ያልቻልኩት እኔ … ሲያቅፈኝ ህይወት እንደሚቀለኝ: ችግሮቼን ችሎ ማሸነፍ ብቻን ያለማመደኝ እሱ እንደነበር:በጣም እንደሚናፍቀኝ :በጣም እንደማመሰግነው ያልነገርኩት እኔ የሄደበትን ቀን ሻማ እያበራሁ አከብራለሁ።

በስመአብ ጊዜው እንዴት ይሮጣል? አትመጣም በቃ?

By Ma Hi

@maninet1
4
ሲራክን አገባለው ብዬ ማልቀስ ከጀመርኩ ወዲያ እማዬም አባዬም ቤተሰቡም ጎረቤቱም  ሁሉ እኔን እንደ ሞኝ ነው የሚያዩኝ ። እማዬም ሞኝነቴን ከርዝመቴ ጋር እያገናኘች " ከኩዮቿ ስትረዝም ነውኮ ጉድ የመጣው ድሮም ረጅም ሰው ሞኝ ነው " ትላለች በርግጥ ሞኝ ምን ማለት እንደሆነም መጀመሪያ አካባቢ አላውቅም ነበር ቡሀላ የሆነቀን አክስቴ የኔን ካላገባው ወሬ ሰምታ
"አንቺ ሞኝ ጅላንፎ ጅል ሲራክኮ ቢወልድ ያደርስሻል በዛ ላይ እሱቴ ምን በወጣው ያቺን መልአክ መሳይ እጮኛውን ትቶ ሆሆሆሆ እኩያሽን ፈልጊ ምን ውርንጭላ ናት ይቺ" ብላኝ ነው ሞኝነት የጅልነት ተመሳሳይ ፍቺ መሆኑን የደረስኩበት ። አክስቴ ያን ቀን ስለ ሲራክ እጮኛ መልኣክ መምሰል ስትናገር መልአኮች ምን ይምሰሉ ምን ሳላውቅ እርግፍ አረገው ነው የደበሩኝ (ይቅርታ እንግዲ እግዚአብሔር ምን ላርግ በሲራክ መጡብኛ) ሴጣንንም ብትመስልኮ ያቺ ሚያገባት ሴትዮ ሴጣንን እጠላ ነበር ማን መልኣክ ምሰይ አላት  ብቻ ሲራክ መልአክ ምትመስል እጮኛ አለችው ። ግን እጮኛ ምንድን ነው ሚያረግለት? እጮኛ ማለት ሚገባ ሰው መሆኑን ከአክስቴ አወራር ገብቶኛል ሲራክ ግን እጮኛ ሲያስጠላበት !!
የዛን እለት እንባዬን እያዘራው ሄድኩ እነ ሲራክ ቤት ቀጥ ብዬ ቤታቸው ስገባ የሲራክ እናት ዳንቴላቸውን እየሰሩ አገኘዋቸው ሳግ በተናነቀው ድምፄ 
"እማማ ሲራክስ" እንባዬ በጉንጮቼ ያለማቋረጥ ይወርዳል።
" እንዴ በሞትኩት እመብርሀን ድረሽ ምንድን ነው ሚጡሻ ምን ሆነሽ ነው ምታለቅሽው ሲራክ ምን አርጎሽ ነው ልጄ" አሉኝ ዳንቴላቸውን ጥለው ወደኔ እየመጡ ።
"ሲራክ ሌላ ሚያገባት እጮጬኛም አለችው ደሞ ደሞ መልኣክ ነው የምትመስለው ብላኛለች አክስቴ ደሞ ሲራክ እኔን አያገባኝማ " ብዬ ለቅሶዬን አቀለጥኩት
" ምን ጉድ ነው ዘንድሮ ኧረ ተይ ሚጡ ተይ (ለኔ)
ምነው አፌን ቢቆርጠው እንደው ለሲራኬ ነው ምድርሽ ያልኳት ቀን (ለራሳቸው)" እንባዬን እና ንፍጤን በለበሱት ነጠላ እየጠረጉ
ሲራክን እንደማገባ እንጂ ማን አንደዛ ብሎ እንደነገረኝ ረስቼው ነበር አሁን እሳቸው እንዳሉኝ ራሳቸው አስታወሱኝ ። አዎ እሳቸው ናቸው እነሱ ደጃፍ ላይ ባልና ሚስት እቃቃ እየተጫወትን እኔና ስምረት እኔ ነኝ ሚስት ምሆነው ተባብለን ስንጣላ  የገላገሉ መስሏቸው እኔን ረጅምም ስለሆንኩ ባል ከሚሆነው ከሄኖክ ጋር ስለማልመጣጠን ለዛሬ እኔ ሚዜ እንድሆን ሲነግሩኝ " እኽ እና ሁሉም ሚጫወቱት ወንዶችኮ አጭር ናቸው መቼም ላላገባ ነው እንዴ " ብዬ ለንቦጬን ስጥል(እማዬ ናት ሳኮርፍ ለንቦጭሽን አትጣዪ ምትለውእንደውነታው ከሆነ ግን ምንም አልጣልኩምኮ ሲጀመር ለንቦጭ ሚባልም እቃ የለኝም ) ብቻ እሱን ነገር ስጥል ራሳቸው ናቸው በቃ አንቺ ሲራክን  ታገቢያለሽ ብለው የነገሩኝ ። ይኸው አሁንም አክስቴ ያለችው ውሸት መሆኑን እንዲያረጋግጡልኝ  ጎናቸው አለቅሳለው
" ደሞ ደሞ እኔ ሚካኤን አልመስልማ እማማ "በእንባ በታመቁ አይኖቼ እያየዋቸው መልሳቸውን እጠብቃለው ከማውቃቸው መልኣክት ሚካኤልን ለምን እንደመረጥኩ ግን እንጃ
"ማለት ሚካኤልን ደሞ እዚ ምን አመጣው"
"ሲራክ ሚፈልገው መልኣክ ማግባት አይደል" መሀል መሀል ላይ ሳግ እያቋረጠኝ
" ቅዱስ ሚካኤል ድረስ  ምን ስትይ አመጣሽው አንቺ ልጄን ልታስቀፅፊ ነው እንዲ ምትይ አበስኩ ገበርኩት እንደው እመብርሀን ይቅር ትበልሽ ሆሆ  "
"ታዲያ እጫጩ ኛውስ "
ሳያስቡት ሳቃቸው እያመለጣቸው " እጮኛ ማለት እንኳን ማትችዪ ድንቢጥ እንደው ምን ብለሽ ነው ይሄን ሲራክን ምታገቢው በይ "
" ችግር የለውምኮ እማማ እስኪያገባኝ እለማመዳለው " ለቅሶዬን አቁሜ
" ሚጣሹ እንግዲያውስ እረፊው ሲራክ አያገባሽም !!"
"ለምን?" እየተኮሳተርኩ
"ማግባት ምን እንደሆነ ግን ታውቂያለሽ " አይኖቼን እያዩ
ደነገጥኩ ግን ምንድን ነው መጋባት ወዲያው አይምሮዬ ላይ የመጡት ጓደኞቼ የቃቃ ባልና ሚስቱ ነበሩ ቀልጠፍ ብዬ
"እንደ ሄኖክና ስምረት መሆን ነዋ"
"እኮ በቃ ሲራክ ደሞ ካንቺጋ እንደዛ አይሆንም"
"ኧህ እኮ ለምን ?"
" አንቺ ሄኖክን ያላገባሽው ከሱ ስለምትረዝሚ አይደል ሚጢሹ ሲራክም ቁመት ስለምበልጣት አላገባትም ብሏል እንግዲ እረፊው " አሳመኑኝ እውነታቸው ትንሿ ጭንቅላቴ ውስጥ ነብስ ዘራች
"እንጂ መልኣክ ስላለው አደለማ ?" የመላእክ መምሰሉ ጉዳይ እየከነከነኝ
" ኧረ እቴ ረዥም እኩያውን ሊያገባ ፈልጎ ነው አንቺም የቁመት እኩያ ስታገኚ ታገቢያለሽ እሺ ሚጢሹ" አመንኩበት ።
በቃ እንደውም ሲራክን አላገባም!

by kalkidan solomon

@maninet1
👍21
#መቄዶንያ

" ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው !! "

መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው እግዛ እንዲደረግ ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።

ዛሬ “ በሰይፉ ኢቢኤስ የዩቱብ ቻነል ” ድጋፍ ማድረጊያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው።

ደጋጎች ሁሉ ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

የድጋፍ ማድረጊያ አማራጮች ከላይ ተያይዘዋል።

መቄዶንያ “ ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” ማለቱ አይዘነጋም።

በቀጥታ ይከታተሉ 👇
https://www.youtube.com/live/q0bMjwt9PvM?feature=shared

@maninet1
የጊዜ_አጠቃቀም_ጥበብ_በዶክተር_ኢዮብ_ማሞ_@only_amharic_books_on_telegram.pdf
16.8 MB
የመፀሀፉ ስም ፦ የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ
ፀሐፊ ፦ በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ገፅ ፦ 149
መጠን ፦ 16.8MB
@maninet1
👍1
ሰላም እንዴት ናችሁ የኛ 558 ታማኝ ቤተሰቦች?
የተለያዩ ሐሳብ ያልችሁ እዚህ ግሩፕ ላይ አድሚን መሆን የምትፈልጉ @betsiroyal ላይ አውሩኝ።
ማንነት/ IDENTITY pinned «ሰላም እንዴት ናችሁ የኛ 558 ታማኝ ቤተሰቦች? የተለያዩ ሐሳብ ያልችሁ እዚህ ግሩፕ ላይ አድሚን መሆን የምትፈልጉ @betsiroyal ላይ አውሩኝ።»
ኔግሮ የሚባል ፍሬንድ ነበረኝ ፀባይኛ ነው፣ ሌባ ነው፥ እናቱን ይወዳታል፥ ትምህርት አይገባውም፤ ተንኮል፣ ኳስ ፣ጆተኒ ፣ ትረባ ጎበዝ ነበር።

በአንድ ሴሚስተር መቶ እና ሁለት መቶ መፅሃፍ ይሰርቃል መቼ? ...እንዴት?...ከማን?... አላውቅም!

መጨረሻ ላይ ውጤቱን እየሳቀ ይነግረኛል።
አንድ ቀን እንኳን ሲሰርቅ ተይዞ አያውቅም !

የሰረቀውን መፅሐፍ ሲሸጥ አብሬው ሄጄ አውቃለሁ። ከሚገዙት ጋር ደምበኛ እንደሆነ ሰላምታ አለዋወጣቸው ያስታውቃል። አሻሻጡ የሰረቀ ፣ ሳይለፋበት ያመጣ አይመስልም፤ በቸልታ አይደለም። በርጋታ እንደትልቅ ሰው... "አይሆንም...፣ ይቅር...፣በቃ፣ ጨምር " እያለ ነው ።

እናቱን "ሸቅዬ... እዛ ማዶ ያሉት ሃብታም ሰዎች፤ ለእናትህ ስጣት ብለው ብር ሰጡኝ" እያለ እንደሚሰጣት ነገሮኝ ያውቃል ።

ሰባተኛ ክፍል ፣ ስምንተኛ ክፍል እያለን እናቱን ያግዛት ነበር ። ይወዳታል፤ አወዳደዱ እንደትልቅ ሰው ነው። "ማሚዋ ደብሯታል ...አሟታል. . . ገበያ ቀዝቅዞባታል" እያለ ያስብላታል።

ከጓደኛው አይሰርቅም። ለጓደኛው ለኔ ለሚለው ሰው ይሳሳል።

አይኖቹ ትናንሽ ናቸው፣ አካባቢውን በትኩረት ያያል፣ ከወሬ ሁኔታን ያያል። ሌባ መሆኑን ብዙ የሩቅ ሰዎች አያውቁም።

ኔግሮ ቁርንጫጭ ፀጉር ያለው፣ ድቅቅ ያለ ገላ ያለው፣ ሲስቅ ቀጭን ድምፅ የሚያወጣ ልጅ ነበር ።

አንዳንድ ቀን ይፎርፍና ሜዳ ጥግ ውኃ ልኩ ጋር ብቻውን ይሆናል ። ዝም ይላል ኳስ አይጫወትም። ቀጭን ድምፅ እያወጣ የሚስቃት ሳቅ አትኖርም። ለመኮረጅ ብዙ አይሰቃይም።

...ጨዋታ ያበዛል...።

ስለ አባቱ አላውቅም፤ እናቱ ግን ትምህርት ቤታችን በር ጎን ላይ ቃርያ ፣ ቲማቲም፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ድምብላል፣ ኮሰረት፣ ስኳር ድንች ...ምናምን ይሸጣሉ። ብዙ ደንበኛ ያላቸው አይመስለኝም። ስንወጣ ስንገባ የደራ ገበያ አንድም ቀን አይቼ አላውቅም ።

ኔግሮ የትምርት ቤት ስሙ መቆያ ነው። እኛ ነን ኔግሮ የምንለው።

እኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ የሰፈሩ ልጆች ሲጠሩት ሰምተን መሰለኝ መቆያን ትተን ኔግሮ የምንለው።

መቆያ የሚባለው ክላስ ስም ሲጠራ ብቻ ነው። ኔግሮ ሲባል ነው እሱም ደስ የሚለው።

የሆነ ቀን ሃይሚ ግርማ መፅሃፍ ጠፍቶብኝ ኔግሮ ሰጠኝ አለችኝ። ጠየኩት "ከራሷ ቦክመህ ለራሷ ገጫሃት ኣ?" ስለው ፤ ሲስቅ የሚያወጣትን ቀጭን ድምፅ አውጥቶ ሳቀ "ባክህ እኔ እንደኔ ችስታ እናት ካለው ቤተሰብ አልሰርቅም "አለ ።

ከስምንት ወደ ዘጠኝ ስንዘዋወር ኔግሮ ታስሯል አሉን። ስሰማ "ዕድሜው ለእስር ደርሷል ወይ?" ብዬ ያኔ አልጠየኩም።

የመንግስት ትምህርት ቤት ስለተማርን ለብዙ ነገር ከዕድሜያችን በላይ ነበርን። የሚታሰሩት በግሩፕ የሚጣሉ ልጆች ስለነበሩ ብዙ አልገረመኝም።

መስከረም አስራ ሰባት ቀን ኔግሮ ሞተ አሉን። እናቱን ስናያቸው ጥቁር ለብሰዋል፥ ጉስቁልናው ብሶባቸዋል። ጉሊት የደረደሩት ከዚህ ቀደም ለመሸጥ ከሚደረድሩት በዐይነትም በመጠንም ቀንሶ አየሁ ።

ሞትን ያኔ ነበር በቅርብ ያወኩት ....በቅርብ የማውቀው፣ ሲያወራ የሰማሁት፣ አብሬው የተጫወትኩት ጓደኛዬ ሞተ ሲባል። ያኔ ነው ለመጀመሪያ ግዜ ያመንኩት።

የታሰሩበት ክፍል የነበረው ካቦ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ፖሊስ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ታሞ ነው ይላሉ ....
ኔግሮ ሞተ። እውነት ነበር!

"ልጅ ይሞታል እንዴ?!" አልኩኝ
ለምን መቆያ አሉት ግን እናቱ??
በዛ ዕድሜው እንዴት በዛ ልክ አሰበላቸው??
በምን ይሆን የሚፅናኑት??
ለምን ሌባ ሆኖ ለጓደኞቹ ታመነ??

እንዴት የሰረቀውን እንደትልቅ ሰው አስቦ ተከራክሮ ሸጠ?? ላለፋበት ነገር እንዴት ዋጋ ሰጠ?? ለምን ምንም ከሌላቸው ሰዎች አልሰርቅም አለ??

በዛ ዕድሜው እንዴት አረጀ ?
እሺ ይሁን መርህ እና ሌብነት እንዴት አብሮ ሄደለት!!

እኔንጃ ኔግሮ ግን ሞተ አሉ !!!

By Adhanom Mitiku

@maninet1
3
ዕድሜዋ ወደ አርባዎቹ እየገሰገሰ ነው....በህይወት ውጣውረድ የዛለ ፊቷ አሁንም ድረስ ድንቡሽቡሽነቱን አላጣም። ዘውትር ለብሳት በምትዞረው አንድ ሺቲ ሙሉ ከተማውን ከጫፍ እስከ ጫፍ ታካልለዋለች። ካልነኳት ማትነካ ብቸኝነትንና ባይተዋርነትን የመረጠች ብቸኛ ነፍስ ናት። ፀጉሯን ማንጨብረር ወይም እንደ 90ዎቹ አፍሮ አርጎ ማቆየት ያስደስታታል። በዛ ድንቡሽቡሽ ገጿ እና ሺ ሀሳብ ቢያጠቃውም ፍንክች ባላለ ሰውነቷ እዚህም እዛም ትባዝናለች።
.
" ሰሚራ " ማህበረሰቡ እብድ የሚል ቅፅላ ሰጥቶ ቢያገላትም ፤ ለኔ ግን የተነጠቀችው ወጣትነት ፤ የተነጠቀችው ህልሟ ጎልቶ ይታየኛል። እደርስበታለሁ ካለችበት ፤ እኖረዋለሁ ካለችው ህይወት ተብትቦ ያደናቀፋት ማህበረሰብ ቀፅላ ሰጥቶ ቁስሏ ላይ ሌላ ቁስል የጨመረላት ምስኪን ነፍስ። የዛሬን አያርገውና አይምሮዋ ከመታወኩ በፊት እንደማንም ጤነኛና ለፍቶ አዳሪ ነበረች። በአንድ ወቅት ለምርመራ በሄድችበት ጊዜ የአባላዘር በሽታ እንዳለባት በሀኪሞች ይነገራታል። ከህይወት ጋ ግብግብ በገጠመችበት ወቅት ፤ አጋዥ ደጋፊ በሌላት ወቅት ይሄን መስማቱ ለእሷ የሞት ታህል ነበር።
.
ዐቅመ ቢስነቷ የእጇ ማጠር ፈውስን ነፍጎ በሽታዋን አበረታባት። ዕለት ተዕለት እየፀናባት ማህበረሰቡ የሚያስተውለው ደረጃ ሲደርስ ሁሉም አገለላት። ተፀይፎ በቃሽኝ ከማለት አልፎ ቅስምን የሚሰብሩ ቃላት እያቀበለ ጨርቋን አስጣላት። ከምላሳቸው ያወጧት ስንዝር ቃል ህልምና ውስጥኗን የቀረቻትን ጥቂት ተስፋ ይዞት ገደል ገባ። ጣት ጠቆሙባት መታመሟ ሳያንስ እብድ ነሽ ብለው የእብደት አክሊል አላበሷት....አሜን ብላ መኖር ቀጠለች።
.
ሳያት ታሳዝነኛለች ፤ እንዲህ ካረጋት ማህበረሰብ ጋር አሁንም ድረስ ተቻችላ ትኖራለች። ከሁሉ ከሁሉ ስታረገው ሳይ የሚያስደስተኝ አንድ ነገር አለ ። ብር እጇ ላይ ከሌለ መሃል አስፓልት ላይ ወጥታ መንገድ ትዘጋለች። ሚያውቋት ሹፌሮችም ባህሪዋን ስለሚያውቁ ገንዘብ ይሰጧታል።
.
ይሄን ስታረግ ሳይ ውስጤ ይረካል። ከመንገዷ ያደናቀፏትን ለደቂቃዎችም ቢሆን መንገዳቸውን አደናቅፋለች። ምትቀበለው ገንዘብ ለሞራሏ ካሳ ባይሆናትም ከኑሮ ወጪ ግን ይታደጋታል። ፖሊስ ቢመጣ ሰማይ ቢገለበጥ ከተቀመጠችበት ፍንክች አትልም።  ታድያ በተቀበለችው ገንዘብ ቡና ልትጠጣ የጀበና ቡና ሻጮች ጋር ትሄዳለች። ማያውቋት ፈርተው የከለከሏት እንደው ትንሽ ግርግር መፍጠሯ አይቀርም። አምነው ለሰጧት ግን ሂሳበቸውን ሰጥታ ሲኒ በስርዓት መልሳ ካገኘች ጫት ካላገኘች ገረባ ሸክፋ ጥጓን ይዛ እየቃመች አልያም ተኝታ ቀኗን ታሳልፋለች።
.
ሚግባቧት ፍቅር ይሏታል ለሌቹ ደሞ በስሟ ይጠሯታል። ከወደደችህ በፍቅር ከጠላችህ ደሞ በስድብ አቀባበል ማድረጓ የተለመደ ነው። አንድ ጊዜ በመንገድ ሳልፍ ምን አበሳጭቷት እንደሆነ ባላውቅም ውሃ ደፍታ አጥምቃኛለች። ብቻ የአንደበታችን ኃይል እንደምናስበው ቀላል አይደለም። መጠገን ከሚችለው በላይ መስበር ይችልበታል። ይች ሴት ምን አልባትም አለውልሽ ሚላት ቢኖር መጨረሻዋ እንዲህ ባልሆነ ነበር። ለኛ ተራ እና ፌዝ መስለው ሚታዩን ቃላት በለሌላው ህይወት ላይ እንደ ደውል ቀን በቀን ያቃጭላሉ።

[ ጥሩቤል ]

@maninet1
4
የጥቁር ልብስ ልክፍት

« ለቅሶ አለብኝ... ልብስ ምረጥልኝ» ብላ የተከፈተ ቁምሳጥኗ ፊት ለፊት አቆመችኝ። የተጠቀጠቀ የጥቁር ልብስ መአአአአአት።

'ይጥቆር እንጂ ደግሞ ለለቅሶ ልብስ መረጣ የምን ቅብጠት ነው። ' አልኩ በሆዴ ... ታዝቤያት። እጄን በግዴለሽነት ሰድጄ አንዱን ጥቁር ጎተትኩትና ፊቷ ዘረጋሁት። ቀሚስ ነበር።

“ ውይ ... ይሄንን ቀሚስማ ሰዓሊው ወዳጄ ሲሞት ለቅሶ ደርሼበታለሁ ፤ አልለብስም።»

«ለለቅሶ የለበስሽውን ቀሚስ አትደግሚም? »

«ሀዘን ይደገማል? » ጥያቄዬን በጥያቄ። «በል ሌላ ምረጥ!»

ምን አከራከረኝ፤ ያነሳሁትን ወለል ላይ ጥዬ ሌላ ጥቁር መዘዝኩ። ባለአንገት ሹራብ።

«ዘፋኙ ጓደኛዬን ቀብሬበታለሁ እሱን። ቀይር»

ሆሆ... ጥዬ ሌላ መዘዝኩ። ሸሚዝ

« የጋዜጠኛ እህቴን አስከሬን በሱ ነበር የሸኘሁት። »

ጣልኩ። አነሳሁ። አንዱን ቀብራበታለች።
ጣልኩ.. አነሳሁ። ለአንዷ አንብታበታለች።
ወለሉ በጥቁር ልብስ፣ ጆሮዬ በሙታን ፕሮፋይል ተሞላ።

እንደ ድንገት አንዷን ሳብኳት። የምታምር ጥቁር ሱሪ። አማረችኝ።

«አታምርም? »

«በጣም ታምራለች። ለምን ይህቺን አትለብሻትም? »

«ቆጥቤያት ነውኮ። በጣም የምወደው ሰው ሲሞት ነው የምለብሳት። »

«ማን ሲሞት?»

«አንተ ነሃ የኔ ፍቅር!»

« ያድኅነነ ከመዓቱ ይሰውረነ ! ምነው በናትሽ»

«ከልቤ ነውኮ። የዛሬ ወር ሾፒንግ ወጥቼ ተሰቅላ ሳያት ትዝ ያልከኝ አንተ ነህ። እንዴት እንደምወድህም ያወቅኩት ያኔ ነው። »

« እርፍ!»

« እርፍ ስትል ነውኮ እለብሳታለሁ ያልኩህ! በዛ ላይ ሰሞኑን እያሳለህ ነው... »

«ምን በወጣኝ ነው የምትወጂኝ በማርያም? ካልጠፋ ሰው እኔን ለምን ወደድሽኝ በሩፋኤል?! »

« ኧረ አንተ ብቻ አይደለህም ውዴ። ያንተን እንደውም ከገዛሁት ቆየሁ። ቁም ሳጥን ውስጥ አልከተትኳቸውም እንጂ... አባቴ... መምህሬ... ክርስትና እናቴ ፣ የእህቴ ባል ፣ ያ ደሞ አቀናባሪው... በየተራቸው ሲታመሙ ጊዜ... “ድንገት ከሞቱ ብዬ” የምለብሰው ገዝቼ አስቀምጫለሁ። እኛ የኪዳነምሕረቱ ቄስ... እኚያ ሰባኪው አወቅካቸው? የምወዳቸው ? ቄሱ... ? ከሰሞኑ ታመዋል ሲሉ ሰምቻለሁ። ከዛሬው ቀብር መልስ... ለሳቸው ለቅሶ የሚሆን ነገር ታጋዛኛለህ »

አሃ... !
ለካ አልቃሾች አዲስ ጥቁር ሲሸምቱ..፣ አዲስ ድንኳን ሲጎትቱ፣ አዲስ ሙሾ ሲሸመድዱ፣ አዲስ አለቃቀስ ሲለማመዱ... መደንገጥ ነበረብን?

ለካ የሞት መላዕኮቻችንን ከምንጠብቅ ፣ አልቃሾቻችን አዲስ ጥቁር ልብስ እስኪገዙ ብንጠብቅ፣ መች እንደምንሞት ይገለጥልን ኖሯል !?

አሳዘነችኝ።
ቁም ሳጥን ሙሉ ልብስ አገላብጣም፣ ለዛሬው ለቅሶ የምትለብሰው ጥቁር አላገኘችም። በርግጥ... እኔ ጋር ገና ያልለበስኩት ጥቁር ካፖርት አለ። «ልስጥሽ?» አልላት ነገር ፈራኋት።

«ሲያምር! እኔ ስሞት ለብሰኸው ትቀብረኛለህ!»
ብትለኝስ?
©ERMI

@maninet1
1😁1
2025/07/08 13:40:40
Back to Top
HTML Embed Code: