Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
💧  የሕይወት ውሃ💦



ሳምራዊቷ ሴት ፥ ያንቀን እንደዋዛ
ከቤቷ ወጥታ ፥ ማድጋዋን ይዛ
ጉድጓዱ ጋ መጣች ፥ ውሃ ልትቀዳ
በዚያም ቆሞ ነበር ፥ አንድ ድንቅ እንግዳ

እርሱም ተጠግቶ ፥ ውሃ አጠጪኝ ቢላት
ስላላወቀች ፥ ማን እንዳናገራት
ጠላቶች ሳለን ፥ እንዴት እንዲህ አልከኝ
አንተ አይሁዳዊ ፥ እኔ ሳምራዊት ነኝ

ብላም ስትናገር ፥ ጌታ ቸር ነውና
እንዳላት አይቶ ፥ የቀና ልቦና
በቅዱስ ቃሉ ፥ ሸክሟን ቢያቀልላት
የደረቀ ሕይወቷን ፥ ቢያለመልምላት
ወደ ቤቷ ሄደች ፥ እንስራዋን ጥላ
ከ'ንግዲህ አልጠማም ፥ እረክቻለው ብላ
እንዲህ ያለ ታሪክ ፥ አለ ደግሞ ሌላ


አባ በበረሃ ፥ በዋሻ ይኖራሉ
ታዲያ አንድ ቀን ፥ ጸሎት ላይ እያሉ
አንዲት ኢትዮጵያዊት ፥ ካ'ሜሪካ የመጣች
ቪዲዮ ልትቀርፅ ፥ ወደ እርሳቸው መጣች
ከሃገሯ ወጥታ ፥ ብዙ ስለቆየች
ገዳማትን ሁሉ ፥ በመዞር እያየች
ንግሡን በዓላቱን ቪድዮ አንስታ
በረከት አግኝታ ፥ በዚያውም ተዝናንታ
ለመክረም ነበረ ፥ ሀሳቧ እና እቅዷ
እስክታገኝ ድረስ ፥ አባን በመንገዷ


ታዲያ ገፃቸውን አይታ ፥ እጅግ አሳዘኗት
የልብሳቸው ማደፍ ፥ የፊታቸው መክሳት
"እኚህን አባት ዛሬ ፥ በገንዘብ ረድቼ
መመለስ አለብኝ ፥ በረከት አግኝቼ "
ብላ አጠገባቸው ፥ ቁጭ ስትል ደክሟት
ጸሎቱን ጨርሰው ፥ መስቀል አሳለሟት

አባቶችን ቀርቦ ፥ ደፍሮ ማነጋገር
ከዚህ በፊት ብዙም ፥ አታውቅ ስለነበር
"በምሳ ሰዓት ፥ ቆሎ ያዙ ምነው ?"
ብላ እንደዋዛ ፥ ብትጠይቃቸው
"ልጄ...!" አሉ አባ ፥ "ይኸው ነው ምሳዬ
ይኽን ያላሳጣኝ ፥ ይመስገን ጌታዬ "

" ቤትዎስ ወዴት አለ?"
"ያው እዚያ ....! ፥ ከድንጋይ የተፈለፈለ"
"ዉይ !? ያ..ቦታ? ፥ ጉድጓድ የመሰለ ?
"ጌታችንስ ቢሆን ፥ እንዲህ ኖሮ የለ?

"አባ እርሱስ ልክ ነዎት! ፥
ግን አሁን እኔ ፥ ምን ልርዳዎት?"
"ልጄ ምንም አልፈልግም "
"ኧረ ተዉ አባ..? ፥እንዳው ምንም ምንም ?"
"አዎ ! እግዚአብሔር ይመስገን ፥ ሁሉ ነገር አለኝ"
"አይ አባቴ ¡ ፥ ሳይዎት እንደዚያ አልመሰለኝ"
"ልጄ.....!?ምን የጎደለ አዬሽ ? ፥ ዛሬ በኔ ሕይወት ?"
"ይኸው ብርድና ሙቀት ፥ ሲፈራረቅበት!"
አለችና ወዲያው ፥ መፍትሄ አቀረበች
ያ'ሜሪካን ምቾት ፥ ድሎት እያሰበች

"አባ በክረምት ወራት ፥ ያ ብርድ ሲመጣ
ሂተር ሚባል አለ ፥ ሙቀት የሚያወጣ "

"ነው?" አሉ አባ ፥
"ፍጥረትን የሚያሞቅ ፥ እንደ ፀሐይ የለ?
ብሉኮውም አለ ፥ ይሄን የመሰለ "

"አባ... ወይ ደግሞ ፋን አለ ፥ ሙቀቱን የሚያበርድ "
"ልጄ ..የሰማዩ ንፋስ ፥ ለዚያ አይደል የሚወርድ "
"ወይ ልምጣ ይሆን ፥ ምግብ መጠጥ ይዤ ?
ላዛኛ አርስቶ ፥ ከሆቴል አዝዤ ?"

"ልጄ.. የጠራሻቸው ፥ እኚህ ምግቦች ሁሉ
እዚህ ካ'ሉት ዛፎች ፥
ከሙዝ ከብርቱካን ፥ በ'ውነት ይበልጣሉ ?"
" እርሱስ ልክ ነዎት ፥ አባ ለጤናም ይሻላል
አሜሪካም አገር ፥
ፍራፍሬ ብቻ ፥ መብላት ተጀምሯል " ስትላቸው

"ልጄ.. ፥ ከዚያ ነው የመጣሽ ?
እንኳን ለሃገርሽ ፥ ለምድርሽ አበቃሽ
እስኪ ደግሞ ፥ እኔም ልጠይቅሽ ?
አሜሪካን ሃገር ፥ የሚሄዱ ሁሉ
በሃብት በምቾት ፥ በደስታ ይኖራሉ
ይህን ነው ሰዎች ፥ ሁልጊዜ የሚሉ
ታዲያ እንዲያ ብትኖሩ ፥ እንዲያም ቢመቻችሁ
በእውነት ልጄ ፥ ደስተኞች ናችሁ?"
ብለው ቢጠይቋት
መልሱ አስጨንቋት
አሜሪካን ገባች ፥ በሃሳቧ በርራ
ቁጭ ባለችበት ፥ ውቅያኖስ ተሻግራ

ታሰባት ያ የሩጫ ፥ የወከባው ሕይወት
ጊዜ የሚያሳጣው ፥ ተመስገን ለማለት
ጭንቀቱ ውጥረቱ ፥ የሚያጎብጥ ጀርባ
ሆድ እየጠገበ ፥ ነፍስ ግን ተርባ
24 ሰዓትን ፥ በሶስት ከፋፍሎ
8ቱን ለስራ፣ 8ቱን ለትምህርት፣
8ቱን ለእንቅልፍ ፥ በማለት ደልድሎ
በስጋ መሮጥ ፥ ነፍስን ኋላ ጥሎ

በገንዘብ ብዛት ፥ በምቾት በድሎት
በነዚህ እርካታ ፥ የሚገኝ መስሎት
በቴክኖሎጂ ፥ በእውቀትም ብዛት
ያንን በመበደር ፥ ይህንም በመግዛት
ከሰው ሲፎካከር ፥ እግዚአብሔርን ረስቶ
በውጪ ወፍሮ ፥ በውስጥ ግን ከስቶ
የለበሰው ልብስ ፥ አንዳች ሳያምርበት
ያ ጣፋጩ ምግብም ፥ ካንሰር ሲሆንበት
እውቀቱም ስራውም ፥ በዝቶ ሲያስጨንቀው
መድኃኒት ቢወስድም ፥ ጭንቀቱ ማይለቀው
የቤቱ የመኪናው ፥ የዕቃው ጋጋታ
የትምህርቱ ውጤት ፥ የስራው ሁኔታ
ደስ ሳያሰኘው ፥ ሳይሰጠው እርካታ
ሆኖ የቀረውን ፥ ተላላ ከርታታ

ያንን የወገኗን ፥
የራሷንም ሕይወት ፥ አሁን ስትመዝነው
ለካ ሁሉም ከንቱ ፥ በእውነት ከንቱ ነው
ጠቢቡ ሰለሞን ፥ በመጽሐፍ እንዳለው
እግዚአብሔር ያለው ነው ፥ ሁሉ ነገር ያለው
ብላ እያሰበች ፥ አይኗ እንባን ሲያቀርር
አባ በለሆሳስ ፥ ይናገሩ ጀመር

"መልሱን አወኩት ፥ ገና ሳትመልሺ
ለርሱ ተይው ልጄ ፥ አይዞሽ አታልቅሺ
ግን ወደፊት ፥ ይህንን አትርሺ
የጎደላችሁን ፥ ሊሞላ የሚችለው
ዘላቂ እርካታን ፥ ደስታን የሚያድለው
ሀብትና ንብረት ፥
እውቀት ዝና አይደለም ፥ እግዚአብሔር ብቻነው
ለዚህ ነው
ድንጋይ ላይ የሚተኛው ፥ እያመሰገነ
ደስታ ሰላም ያጣው ፥
ተመስገን የማይል ፥ ባለ አልጋው ሆነ
እናም
ትልቅ ነገር ነው ፥ ልጄ የተማርሺው
እዚያ ስትመለሽ ፥ አደራ እንዳትረሺው
አሁን የያዝሺውን ፥ መሳሪያ የያዙ
ቀርጸው የሚሄዱ ፥ አሉ እጅግ ብዙ
ታዲያ ምን ያደርጋል?
ዛፉን ተራራውን ፥ ድንጋዩን ቢያነሱ
በበዓሉ በንግሱ ፥ ፎቶ ቢጨርሱ
አየንስ ማለቱ ፥ ምን ጥቅም ይሰጣል ?
ለማየቱማ.....
ከአይሁዶችም እኮ ፥ ጌታን አይተውታል

እኔ... ዛሬ ፥ ካ'ንቺ ምፈልገው
ቃሉ ለመንገድሽ ፥ ብርሃን እንድሆን ነው
ሌላ አልፈልግም ፥ ሁሉ አለኝ
እግዚአብሔር ይመስገን
የሚያስፈልገኝን ፥ እርሱ መች ነፈገኝ
የአፍንጫዬ እስትንፋስ ፥ የልቤ ምት አለ
ሌላ የለም ስጦታ ፥ ይሄን የመሰለ"
ብለው ጨረሱ አባ ፥ በዋሻ እየኖሩ
ሁሉ አለኝ ብለው ፥ ኮርተው ተናገሩ
በዚህም .....
የዚያችን ልጅ ፥ ሕይወቷን ቀየሩ

እንደ ሳምራዊቷ፥
ውሃ ልትቀዳ ፥ ከጉድጓዱ መጥታ
አንደተመለሰች ፥ ሕይወትን አግኝታ
ይህችም ልጅ፥
ቪዲዮ ልትቀዳ ፥ ሄዳ ከበረሃ
ቀድታ ተመለሰች ፥ የህይወትን ውሃ (2)


🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
    🙏 ወለወላዲቱ ድንግል   🙏
        🙏ወለመስቀሉ ክቡር 🙏

ይቆየን......
📜 መንፈሳዊ ግጥም📜


🛑 እውነት አለቀሰች🛑
▱▱▱▱▱▱▱▱


ልብ ያለህ አስተውል፥   ጆሮ ያለህ ስማ
እግርህ እንዳይገባ፥  ከክህደት ከተማ።
የያዝከውን አጽና ፥ ልብህ አይጨነቅ
ለጥያቄህ መልስም ፥  ሊቃውንትን  ጠይቅ።



     ለእውነት የቆመ፥ ሃይማኖቱን የሚያውቅ
    ንባብ ትርጓሜን ፥ ጠንቅቆ የሚዘልቅ
    ተናገር ዩሐንስ ፥ አንተ ልሳነ ወርቅ።
    ቄርሎስን  ጠይቀው ፥ የተዋህዶን ምስጢር
     የክርስቶስ ነገር ፥ እንዴት እንደነበር።
     ከብሉይ ከሐዲስ ፥ በማቀነባበር
     እንዳመሰጠረው ፥ በብዙ ምስክር።



ነቢዩ ኢሳያስ ፥ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ
መዝሙረኛው ዳዊት ፥ ሐዋርያው ሉቃስ
አባ ዝክረ ማርያም ፥ ወአባ ጴጥሮስ
የስነ ዘፍጥረት ሊቅ ፥ ኤጲፋኒዮስ
ዝም አትበል ተናገር ፥ ቅዱስ ሳዊሮስ
በሥጋው ማክበሩን ፥ አምላክ ክርስቶስ።



     ጊዮርጊስ ተናገር ፥ አንተ የጥዋት ጮራ
     ክርስቶስ መሲሕም ፥ ተብሎ እንደሚጠራ።
     ወልድ ቅብዕ በማለት፥ ክህደት አስተማሩ
     የሥግው ቃል ነገር ፥ መች ገባቸው ዳሩ
     የተዋሕዶ ምስጢር ፥ ሳይገባቸው ቅሉ
     ሃይማኖት ከምስጢር ፥ ይደባልቃሉ።



ክርስቶስ በሥጋ ፥ እንደሞተ ሲያውቁ
በሥጋስ መክበሩን፥ እንዴት አላወቁ
ሊቃውንት እያሉ ፥ ለምን አይጠይቁ
በተዋሕዶ ከበረ ፥ ብለው ሲናገሩ
ለዚህ ብሂላቸው ፥ የታል ምስክሩ።



   ግብርን በማፋለስ....
    አንድ ገጽ ካለው ፥ ከሰባልዮስ
    አንድነትን ትቶ ....
    ሁለት አካል ካለው ፥ ከእርጉም ንስጥሮስ
    መንፈስ ቅዱስ፥ ሕጸፅ ካለው ከመቅዶንዮስ
    ወልድ ፍጡር ካለው፥ ከእርጉም ከአርዮስ
    የዚህ ክህደቱ ፥ በምንም አያንስ።



ፈላጊዋ ጠፍቶ፥ እውነት አለቀሰች
ግብራቸው ተቃርኖ፥ ሀሰት ጥላት ሄደች።
ዳሩ ግን ወገኔ ፥ ይህ ክህደት ነውና
ቀኑ ሳይመሽብህ ፥ መንገድህን አቅና
እውነትን ከፈለክ ፥ ታገኛለህና
እረፍት ስላላት ፥ የህይወት ጎዳና
የያዝከውን ይዘህ ፥ በሃይማኖት ጽና።

    🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
      🙏 ወለወላዲቱ ድንግል 🙏
        🙏ወለመስቀሉ ክቡር🙏

ይቆየን ○○○○○○○○
ሰላም የቻናታችን ቤተሰቦች፡ መልካም ሰንበት ተመኘንላችሁ🙏
   á‰ áˆ°áˆ˜ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።


     📜መስቀል ሾር ያለች መስቀል📜
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

በአይሁድ ህሊና ፥
ያልታቀደ ህማም -  ያልተሴረ ስቃይ
ይኸው መስቀሉ ስር - ይኸው እግሮቹ ላይ።
ዮሐንስ አልቅሶ ፥
ሙሾ ያልደረተለት - በልቡ ርህራሄ
ያልተደመጠ ሞት ፥
ያልታወጀ ቅጣት - ያልተሰማ ኤሎሄ!!
አባሽ ያጣ ቁስል - አይዞን ያጣ ወዮ!
አድስ ጎልጎታ - አድስ ቀራንዮ።
በጽሞና ችንካር - ሕማም ሲንቀለቀል
ይኸው መስቀሉ ስር - የወደቀች መስቀል።

የዚህ ሰው እናቱ ...........
ማበስ ማትችለውን ፥
የግልገሏን ቁስል - ታግሳ እያየችው
ከግርግም አንስታ፥
እስከ ቀራንዮ - መቼ ተለየችው !?
እንደሚሸለት በግ ፥
በቁጣቸው ገመድ - አስረው ሲጎትቱ
በእምባ ተሸፍና ፥
ትከተለው ነበር - እረኛዋ እናቱ
የቤተልሔም ወርቅ - ከርቤ ተሸልሞ
የሰራዊት ሞገስ - መስቀል ተሸክሞ!
አንድ በአንድ አጥንቱ - በጉልህ ሲቆጠር
ቸሩ እንደ ነውረኛ፥
በሙት አደባባይ - በግፍ ሲጠረጠር !


ያቺ ብላቴና ......
የግብጽ በረሀ - ስደተኛይቱ
ከእቅፏ አስጠግታ ፥
ማባበል ሲሳናት - እንደ ልጅነቱ
በምን አለቃቀስ ፥
አዝተዛዝናው ይሆን - የልቧን ስር ጥቃት
ስፍር የጠበበው - የግርፋትህ ልክ እየሰነጠቃት!
በምን እርሟን ታውርድ ፥
በፊቷ ቀሚስክን - ሲካፈሉ ገፍፈው
ይህን የጭንቅ ቀን - ምን ይዛ ትለፈው?
በምን አመክንዮ ፥
በደልክን አስልታ - ትቀበል ፍርድህን?
ሠላሳ ሦስት አመት ፥
ጠንቅቃ ታውቃለች - ንፁህ መሆንህን!!
በዝምታ ክራር.....፥
ሕማም ምትደረድ - ሐዘንተኛ እናትህ
ታውቀዋለች እና
የገዳይክን ሸንጎ - አትለምንም ፍትህ !



የሕማም ሰው አንተ!......እስቲ መልስልኝ?
የደረሰብህ ግፍ፥
የወረሰህ ሐዘን - ሲተነተን ልኩ
የትኛው በደል ነው?
የሚሰረስርህ - በተለየ መልኩ?
የይሁዳ ግብር ....?
ላገለገሉት ልብ - ሳይሰስቱ ቅንጣት
ከማቁሰል በባሰ - አሳሳም መቀጣት
ወይስ የጴጥሮስ ቃል?
ሁሉ እንኳን ቢሸሽህ - እንዳይተውህ ምሎ
ፈራጅ ፊት ሲከዳህ - አላውቀውም ብሎ
ወይስ መጻጉዕ ነው!?
የድኅነትን መረብ .....
በፍቅር ዘርግቶ - ለፈወሰው እጅህ
ስለ ሃና ክብር ፥
የግፈኛ ጥፊ - የከፈለህ ልጅህ?
ወይስ አርብ ዕለት ነው?
አብረንህ ልንምት - እንወዳለን ያሉህ
ልከኛ ወዳጆች - ብቻህን ሲተውህ
የሾህ አክሊል ነው ወይ?
የግርፋትህ ልክ - ጨፍፎ ሚያልብህ!?
ወይስ የእናት አምባ.......?
የግር እሳት ሆኖ - የሚለበልብህ???
......ባክህ መልስልኝ!??........



ስፍር አልባ ሕማም ፥
ከአካልህ ተስጎ - እየመገመገህ
መስቀል ስር ተደፍታ፥
ማርያም ስታለቅስ - እንዴት አደረገህ?
የራሔልን አምባ....
ያነጠፈ መዳፍ - በችንካር ቢጣመም
ይብሳል ወይ ቁስሉ?
የእናትን መንታ እምባ - አይቶ ከመታመም?


እንኳንስ ቆማ ልትሸኝህ - ጨክና ከገዳይ ደሴት
አይኖቿን ጨፍና እስክትገልጥ - አይንህን ማታምነዋ ሴት
የሰማይ የምድር ራስ - በሾህ ዘውድ ለሞት ሲሾሙህ
የግርግም በኩር አራሷን - እርቃንክን ገፍፈው ሲያቆሙህ
ምን ጥበብ ሊተነትነው - ህማሟን ለክቶ በቃል
መኖሯን ለሸኘች ምስኪን - ስንት ዋይ ስንት እምባ ይበቃል ?


መንገዷ የእግሮቿን ሲሳይ - ይረግፋል በርምጃህ ስፍር
ስቃይዋን አምቃ የምትጎድል - ለፍቅርህ ለአሳብህ ክብር
ያንተ እኮ ፅኑ ግርፋት - ማዳን ነው ሕማምህ መልኩ
የርሷስ ሞት የርሷስ ስንጥቃት - ምንድነው ማሰርያ ልኩ
"ኮብልለህ ድንገት ካይኖቼ - ድንጋጤ ክፉኛ ደፋኝ
እይዘው እጠራው አጣሁ - እርምህን ሶስት ቀን ብትጠፋኝ"
ያለችህ ምስኪን እናትህ...........
እንኳንስ ከሞት ተዋድቀህ - ቆመህም የልቧ ስጋት
ማያምንህ ስስት አንጀቷ - አርብ ዕለት እንዴት አረጋት??



እኔማ አድፋም ልጅህ .....
ክራሬን አበጃጅቼ - ዜማዬን ባለሰልሰው
ሐዘኗ ምላሴን ይዞ - እንባዋ ክሬን በጠሰው
አግዘኝ ዮሐንስ ጥልቁ - ቋንቋዬን ምናብ ጠበበው!
አጥምቀኝ የእባዋን ምስጢር - ክፋቴን ካረጣጠበው
ምን እውቀት፣ ምንስ መታገስ፣ ምን ፍቅር ምንስ ዝምታ
መልቶበት ያመሰጠረው - የዓይኗን ስር ዕምባ ጠብታ
ብዕሬን ቀለም ተስኖት - ትብ እጄ ተርበተበተ
መጋቢ ምስጢር ዮሐንስ - ነባቤ መለኮት አንተ
ግልግል የራቀው ምጧ - አንጀቷን ሲያርመሰምሰው
ከሐዘኗ ተሟግቶ ልብህ - ምንብሎ ፅናት ለገሰው???


.............ለካ.......
ኩልትፍትፍ ባዶ አንደበቴ - ከደጅሽ ሲደነጋገር
ያአሳቤ ጸሎት ሲጠፋኝ - ሲጨንቀኝ ስንቱን ለመንገር
ብሶቴን በምልጃሽ ቀሚስ - ከልለሽ የምትደብቂው
የሐዘን ልክ የመከራን ጫፍ - በልጅሽ ስለምታውቂው
እንደርሷ የምሬትን ልክ - ተርጉሞት ያለፈ ማነው ?
የአርብ ዕለት ሺራፊ ሰከንድ - ለማርያም ስንት ዘመን ነው?



በስቃዩ አካሏ ነዶ - እንደ እሳት ቢንቀለቀልም
ለሁሉ ያሞተውን ፍቅር - ከማክበር ላፍታም አትጎድልም
ምን ተዓምር፣ ምንስ ምልዓት፣ ምን ውበት፣ ምን ቅድስና
ምን ቋንቋ፣ ምንስ ልህቀት፣ ምን ቅኔ፣ ምንስ ምስጋና
ሊያወድስ ይተካከላል - የርሷን ልብ የርሷን ኅሊና ?

አግዘኝ ዮሐንስ ጥልቁ - ድፍረቴን መጠን ጠበበው
ሐጥኡን ገደል ኅሊና - የሰማይ ሙግት ገጠመው
መልሰኝ ካለማወቄ - የቃሌ ድርድር ላያምር
መለኮት ስማ ታቅፋ - ኃይለእሳት ላስተኛች ተዓምር
የዓይኗን ስር ምስጢር ልሞግት! ዘመኔ ደርቆ ቢረግፍም
የልቧን ስሜት ሚሞላ - ቅንጣት ሀቅ ታግዬ አልጽፍም
ሺ..ብቀኝ የማልጨርስሽ ...........
ሺ...ብረቅቅ የማልዳስስሽ - በጸጋሽ ጥላ ሳትነኪኝ
እናቴ የነፍሴ ፊደል - ስማርሽ  እንድኖር ባርኪኝ።🙏
እናቴ የነፍሴ ፊደል - ስማርሽ  እንድኖር ባርኪኝ።🙏


ገጣሚት  . .ኅሊና ደሳለኝ




የእመቤታችን  በረከቷ ይደርብን
ቃልኪዳኗ ይጠብቀን✝️🙏


www.tgoop.com/markonalfikru
www.tgoop.com/markonalfikru
www.tgoop.com/markonalfikru
ከተመቸዎ 🄻🄸🄺🄴ካልተመቸዎ🄳🄸🅂🄻🄸🄺🄴በማድረግ ያሳውን
😍መንፈሳዊ እንቆቅልሽ😍
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የማይለመድ እንግዳ __________?
Anonymous Quiz
15%
ፍቅር
18%
ሰይጣን
55%
ሞት
12%
ጸሎት
📜 መንፈሳዊ ግጥም📜
▬▬▬▬▬◈▬▬▬▬▬

🎤 ታላቅ ነው ልደቱ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

በጉዞ ላይ ነበር - ጌታችን ሲወለድ
ሊፈፅም ሲመጣ - የአባቱን ፈቃድ
በቤቴሌሒም ዋሻ - በዛች በግርግም
ከሠው ልጅ ተገኘ - መድሀኒአለም


እረኞች በሌሊት - በስራ ላይ ሳሉ
በጌታ ብርሃን - ዙሪያውን ተሞሉ
መላዕክት ከሰው - ጋር በአንደ ላይ ዘመሩ
የጌታን መወለድ - ለእረኞች ሲያበስሩ
ምስጋና ለእግዚአብሔር - በላይ በአርያም
ለሠው ልጅ ይሁን - በምድርም ሠላም
ብለው ተቀኙለት - ለሠራዊት ጌታ
ስጋ ለብሶልና - ሰይጣንን ሊረታ!!


ይሄ ታላቁ ቀን - ከመሆኑ በፊት
ተገልፆ ነበር - የክርስቶስ ልደት
ለሠበዐ ሠገል - እርሱን ላከበሩት
የጌታን መወለድ - ባይናቸው ለማየት
እጅ መንሻ ይዘው - ሠጡት በእጃቸው
የልባቸውን ፍቅር - ለመግለፅ ፈልገው
እውነተኛ ካህን - አንተ ብቻ ነህ
ከሀያላን ሁሉ - አቻ የሌለህ
ለማየት ፈልገው - ለአምላካቸው
ንፁህ ባህሪ ነህ - እንከን የሌለብህ
ሠዎችን አንፅተህ - የአንተ ለአረግህ
ብለው ለመናገር - ለሀያላን ጌታ
ወርቅ አቀረቡለት - ለክብሩ ስጦታ


ኢሳያስ በትንቢት - ከሩቅ ተመልክቶ
መከራውን  ፃፈ - ላምላኩ ራርቶ
የጌታውን እመም - ያየውን አበሳ
በአንባ እየተራጨ - በትንቢቱ አበሳ
ሠባ ሠገልም - ይህንን ተረድተው
የጌታ ስቃዩን - ለመግለፅ ቢያሻቸው
በበረት ተኝተው - የነበሩ እንስሳት
ፈክተው ተነሡ - በእኩለ ሌሊት
እነሱም ሊያከብሩ - የአማኑኤል ልደት

እንስሳቱም አውቀው -  የእነርሱን ጌታ
እስትንፋስ ገበሩ - ለዋለው ውለታ
የጌታን መወለድ - መገኘት በበረት
በምድር ፈጠረ - ታላላቅ ታምራት
ድንቅ ድንቅ ነገራት - ሆኑ በዕለቱ
እውነቱም የጌታ - ታላቅ ነው ልደቱ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወመስቀሉ ክቡር
ይቆየን !!
ልጆችሽ
▬▬▬▬▬▬▬

የሰማይን ምጥቀት . . .
የምድርን ስፋት
የባህርን ጥልቀት . . .
ጥበብን ማን መርምሮ አገኛት
እርሱ እግዚአብሔር ሠራት
አያትም ሰፈራት

ጥበብ እናቴ
ቤተክርስቲያን ድኅነቴ
የሕይወት ቤት መሠረቴ
እንደ እንቁ የሚያበሩ ከዋክብት ልጆችሽ
ምስክሮች ሁነው ዘመን አሻገሩሽ

ዛሬም በኛ ልብ ውስጥ ጸንተሽ ትኖሪያለሽ
የአብራክሽ ክፋዮች ቢቆጠር ስራቸው
በገድል ትሩፋት ይህው በእኛ ዘንዳ የታወቁ ናቸው
ነገስታት ነበሩ ጠፈር የታጠቁ
በጥበብ የላቁ ምስጢር ያራቀቁ
ወልድ ዋሕድ ብለው ኃይማኖት ያጸኑ
ሰውን ሰው ያረጉ ሀገርን ያቀኑ
በአጥንታቸው ድንበር ቅጥሩን የቀጠሩ
በደማቸው ድርሳን ታሪክ የዘከሩ
ገዳም የገደሙ ደብር የደበሩ
መስቀሌ የተከሉ አለት የወቀሩ
ፊደል በገበታ ቆጥረው የቀመሩ
የሰማይ ስርዓት በምድር የሰሩ
እኒያ ብርቱ ልጆች እንደ እንቁ የሚያበሩ

የአምላክን ሰው መሆን የልደቱን ምስጢር
የክርስቶስ ፍቅሩን የመስቀሉን ነገር
ውለታውን ሰፍሮ ለመክፈል ብድሩን
ቢተጉ . . . ቢያስሱት . . . ገፀ በረከቱን
ስጦታው አንድ ሆኖ . . .” ምስጋናን ” . . . አገኙት
በቀንና ሌለት ቢያዜሙ ቢቀኙት
የምድር ብልፅግና የአፍላጋትን እውቀት
ቢበሉት ቢበሉት . . . . ቢጠጡት ቢጠጡት
ልባቸው ባይረካ ቢቃጠል በፍቅር
ከአርያም ደርሶ ከመላዕክት ሀገር

ሉቁ ቅደስ ያሬድ. . . . ሰማያዊ
ድምፀ መልካም . . . . ማህሌታዊ
“ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ እምሰማይ” እያለ
ሃሌ ሉያ ብሎ መላዕክት መሰለ
ባኮስ ጃንደረባ ቀዳማዊ ሐዋርያ
ሕጽዋ ለሕንደኬ ንግስተ ኢትዮጵያ

አፄ ካሉብ መናኝ ንግስናው በርሃ
ቅዱሳን ነገስታት አብርሃ ወአጽብሃ
ገብረ ማርያም ላሊበላ . . . ነአኩቶ ለአብ ይምርሃ
የጻድቅ ከተማ የጥበባት ማዕድ
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘደብረ ነጎድጓድ
የወንጌል ገበሬ . . . አርበኛ ተጋዳይ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንኀስ ቅዱስ . . .
. . . የኃይማኖት ተክል ካህናተ ሰማይ
የእውቀት ብርሃን . . . የምስራቅ በር መውጫ
ዓምደ ሃይማኖት . . . አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ፀሎት ትሩፋቱ . . . መጠለያ አንባ
አባ ሳሙኤል . . . ዘዋልድባ
በግብጽ ንሂሳ ምስራች ተሰማ
ገና በማህጸን ጌታው የመረጠው የወንጌሌ አውድማ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብሎ እንደ መላእክቱ ምስጋናን ወደደ
ጸጉር የለበሰ ወተት የማይቀምስ ህፃን ተወለደ
ለሰው ልጆች አምባ ተጋዳይ አርበኛ
በበረሃ ኖረ አንበሳና ነብሩን አዴርጎ ጓደኛ
ገዳምን ገደመ ልጆቹን አጸና
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያን ባረከ ዝቋላን አቀና
የሰው ልጅ እንዳይወድቅ በኃጢአት ጎዳና
ዲያቢሎስ እንድማር አምላኳን ተማፅና
ሲኦልን ያንኳኳች የእርቅ ሐዋርያ
ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ . . . ኮከብ ዘአቅሉሲያ

ጥበብ እናቴ ቤተክርስቲያን ድኅነቴ
የሕይወት ቤት መሠረቴ
እንደ እንቁ የሚያበሩ ከዋክብት ልጆችሽ
ምስክሮች ሁነው ዘመን አሻገሩሽ
ዛሬም በኛ ልብ ውስጥ ጸንተሽ ትኖሪያለሽ
እስከ መቼ?
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

በዱሩ በዋሻው ጤዛ እየላሱ
ድንጋይ ተንተርሰው ጥሬ እየቀመሱ
መከራ መስቀሉን ከፊታቸው ስለው
ስለ አንቺ ተጥለው
እንደ መጻተኛ በሰው ዘንድ ተቆጥረው
ፂማቸው ተነጭተው ቁልቁሊት ተሰቅለው
በሰይፍ እና በእሳት እጅግ ተፈትነው
ቆዳቸው ተገፎ
ጥርሳቸው ረግፎ
ዝንቱ ውእቱ ፍሬ ሃይማኖት
ብለው መቀበሉን መልእክት
አርቀው በማየት ብራናውን ፍቀው
በደም የከተቡሽ ተዋህዶ አንቺን ነው
ቢያነፈንፉ ጉባኤ ካለባት
ታሪክሽን ቢያጠፉ ግራኝ እና ጉድት
ያደረሱት ጥፋት የታሪክ ጠባሳ
በልጆችሽ ልብ ውስጥ ቢልም አልረሳ
ማነው የጨከነ ቆርጦ የተነሳ
እንባሽን ሊያብስ ሀዘንሽን ሊያስረሳ
ብራናውን ዳምጠው
ቀለሙን በጥብጠው

ለኛ ያቆዩልን ተጨንቀው ተጠብበው
ይህን ሁሉ ድካም ትውልድ ካልገባው
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱ
ምን ጥቅም ይሰጣል ... መባል ለትውልዱ
እምነትን ከምግባር ባንድ ካላስኬዱ
አንተ ግን
ቀና ቢሉ ላፍታ በደም የከተቧት
ሰለ እርሷ መስክረው ያለፉ ሰማዕታት
አደራ በሊታ እጅግ አሳፋሪ
ሆነህ ሲያገኙህ ወጭቱን ሰባሪ
ዋ
ምን ትመልስ ይሆን ከፊታቸው ቆመህ
የአባትህን ርስት አደራውን በልተህ
ልጄ! ባክህ አስተውል
የወላድ መካን አትሁን ደጁም አይዘጋ
ፍጠን አሁኑኑ አትሮንሱንም ዘርጋ
አንተ የናቡቴ ልጅ ክፈልላት ዋጋ
ናቡቴን አስበው ያን የተገፋው ሰው
በኤልዛቤል ክፋት ደሙ የፈሰሰው
ለርስቱ ነበረ ሞትን የቀመሰው

በተፈለፈለው ዋሻ ስር
ስለሷ ያነቡ በፍቅር
ቅዱሳን ናቸው ምስክር
ሀጢያት አይብቀል በቤቷ
እንዳይበላሽ ውበቷ





@markonalfikru
@markonalfikru
@markonalfikru
ሰንበት ተማሪ ነኝ!

ትዕዛዙን ልከተል ፣ ያቅሜን የምታትር
ዘወትር በምስጋና ፣ ስሙን የምዘክር
ከማህሌቱ ቆሜ ፣ ኪዳኑን አድርሼ
ሰዓተ ሩፋዱን ፣ ፆሜ አስቀድሼ
እርሱ እንደወደደኝ ፣ ልወደው የምሻ
ቀዳሚ የምገኝ ፣ ከፀበሉ ቅምሻ

በትጋት፣በፍቅር
ምስጢር ፣ ምመረምር
አጋንንት የሚጥል ፣ ንፁህ እምነት ያለኝ
የብርሃን ኮከብ ፣ ሰንበት ተማሪ ነኝ።
ስለ ማህተቤ አንገቴን የምሰጥ
ለሚያልፍ ማዕበል ፣ የማልንቀጠቀጥ
ወንጌልን ገልጬ ፣ የምማር አንድምታ
የረቀቀ ምስጢር ፣ ቅኔ የምፈታ

የትግስቴን አጥር ፣ ክፋት የማይንደው
ጠፊ እንግዳ ስብከት ፣ ልቤን የማይወስደው
እምነቴን አስይዤ ፣ ለንዋይ የማልወድቅ
ዝሙትን የምሸሽ ፣ የማልዋሽ ፣ የማልሰርቅ
ሰባት ጊዜ ብወድቅ ፣ ሰባቴ ምነሳ
በጥበብ በብልጠት ፣ የማጠፋ አበሳ

መመላለስ ሳይሆን ፣ መመለስ የምመኝ
የፃድቅ አወዳሽ ፣ ሰንበት ተማሪ ነኝ።
መልካም ምግባር ይዤ ፣ ከደጁ ማልጠፋ
ተግሳፅ የምቀበል ፣ ክብር የማልገፋ
በሽብሻቦ እልልታ ፣ በያሬድ ዝማሬ
በውዳሴ ማርያም ፣ በኢየሱስ ፍካሬ

ቀኔን የማሳምር
በፈተና ዓለም ፣ ምሬት የማልሰፍር
ለውበት ሰግጄ ፣ ተስፋዬን የማልሸጥ
እንደ ወይራ በትር ፣ የማልለማመጥ
ሰንበት ተማሪ ነኝ ...
በቅዱሳን ስፍራ ፣ ፀሎት አደርሳለሁ
የወላዲተ አምላክ ፣ምልጃዋን አምናለሁ።
ሰንበት ተማሪ ነኝ! )

ትዕዛዙን ልከተል ፣ ያቅሜን የምታትር
ዘወትር በምስጋና ፣ ስሙን የምዘክር
ከማህሌቱ ቆሜ ፣ ኪዳኑን አድርሼ
ሰዓተ ሩፋዱን ፣ ፆሜ አስቀድሼ
እርሱ እንደወደደኝ ፣ ልወደው የምሻ
ቀዳሚ የምገኝ ፣ ከፀበሉ ቅምሻ

በትጋት፣በፍቅር
ምስጢር ፣ ምመረምር
አጋንንት የሚጥል ፣ ንፁህ እምነት ያለኝ
የብርሃን ኮከብ ፣ ሰንበት ተማሪ ነኝ።
ስለ ማህተቤ አንገቴን የምሰጥ
ለሚያልፍ ማዕበል ፣ የማልንቀጠቀጥ
ወንጌልን ገልጬ ፣ የምማር አንድምታ
የረቀቀ ምስጢር ፣ ቅኔ የምፈታ

የትግስቴን አጥር ፣ ክፋት የማይንደው
ጠፊ እንግዳ ስብከት ፣ ልቤን የማይወስደው
እምነቴን አስይዤ ፣ ለንዋይ የማልወድቅ
ዝሙትን የምሸሽ ፣ የማልዋሽ ፣ የማልሰርቅ
ሰባት ጊዜ ብወድቅ ፣ ሰባቴ ምነሳ
በጥበብ በብልጠት ፣ የማጠፋ አበሳ

መመላለስ ሳይሆን ፣ መመለስ የምመኝ
የፃድቅ አወዳሽ ፣ ሰንበት ተማሪ ነኝ።
መልካም ምግባር ይዤ ፣ ከደጁ ማልጠፋ
ተግሳፅ የምቀበል ፣ ክብር የማልገፋ
በሽብሻቦ እልልታ ፣ በያሬድ ዝማሬ
በውዳሴ ማርያም ፣ በኢየሱስ ፍካሬ

ቀኔን የማሳምር
በፈተና ዓለም ፣ ምሬት የማልሰፍር
ለውበት ሰግጄ ፣ ተስፋዬን የማልሸጥ
እንደ ወይራ በትር ፣ የማልለማመጥ
ሰንበት ተማሪ ነኝ ...
በቅዱሳን ስፍራ ፣ ፀሎት አደርሳለሁ
የወላዲተ አምላክ ፣ምልጃዋን አምናለሁ።
አንቺዬ
በጣቶችሽ እርሳስ የተሳሉ ሁሉ፤
ያመሰግኑሻል ብጽዒት እያሉ፤
እኮ .......ሁሉም በየግሉ፣
ሠዓሊያን በሥዕሉ ፣
ዜመኛው በዜማ፣
የቅኝቱን ጉልበት......
ከነፍሱ ሲያስማማ፣
ገጣሚያን በግጥሙ፣
ገድልሽን ሲነድፉ ብዕር እያደሙ፣
ቅናት ይሉት ስሜት ተጋባብኝ እና፣
ለቅኔ ለመዝሙር ቆምኩኝ ለምስጋና፤
እንኳን ለእናትዬ እንኳን ለማር--- ያሜ፣
መራራ አንደበቴን
ለቀየረችልኝ በጣፈጠ ቃና፥
እንኳንስ በብዕሬ፥
በእስትንፋሴ ዜማ፥
ሲያንስባት ነው እንጂ
ቆዳዬ ተገፎ ቢከትብ በደሜ፤
አስታውሰዋለሁ!.....
ነፍሴ ተጨንቃ መድረሻ ጠፍቷት፣
ስጋዬ ገልፍቶ ፥
....ድድር ኃጢያቴ ነፍሴን ሲያስጉዛት፣
እናቴ ድንግል ባልኩበት ማግስት፣
ከዕድፌ ነፃሁ፥
ዳግም ሰው ኾንኩኝ ፥
ስጋ ለበስኹ አግቸ ምህረት፣
ሳመሰግናት!.....
በመውደድ ዜማ ስቀኝ ከፊቷ ባትረካ ነፍሴ፣
እንደ ቅዱስ..... ኤፍሬም .....በጣመ ውዳሴ፣
እንደ ቅዱስ ያሬድ ዜማዬ ባይጥምም፣
ማርያምን! ....,ማርያምን......
ስለ እናትነትሽ ዝም ብዬ አላልፍም።

ማርያምን!......
ስምሽ ጣፋጭ ነው ከወይን የላቀ፣
አንቺን የተጠጋ፣አንቺን የያዘ ሰው
እንደምን ፀደቀ?!
አሁን እናትዬን ስሟን ስነሳሳው
ጠላት ይቃጠላል፣
ምድር አስጨንቃው
ሠማይ ልጥቀስ ይላል፣
እንኳን ማረር መክሰል
ቡን ቢል አልተውም
አንቺን ከማመስገን!...፣
መች ፍርኃት አውቅና
ሺህ ወጥመድ ቢጠመድ ፣
በአንቺ ታምኛለኹ አልቀርም ከመንገድ ፤

"ማርያም" ይላል ትውልድ ሁሉ፤
"አዛኝ" ይላል ተገፍቶ እንደ መውደቅ ብለው ቀና ያሉ፣
"አማላጅ" ይላል ከአምላኩ የታረቀ፣
ስራሽ ድንቅ ሆኖ በትውልዱ አንደበት ስምሽ [እ]ረቀቀ፤
እኔም ተነሳኹ፣
በድልብ ኃጢያት:-
የደነደነ ሽንፈት የጣለው ልቤን [እ]ረታኹ፣
ይኼው ተነሳኹ!.......
ለድንግልናሽ:-
ለንጽህናሽ፣
ለቅድስናሽ:-
ለፈጣን ምልጃሽ :-
ቅኝቴን ልቀኝ ላዜም ለፍቅርሽ፣
ከደጅሽ መጣኹ፤
ካንቺ እርቄ!....
አልቦ ህይወቴ እያስጨነቀኝ፣
እልፍኘ ኦና ኖኅ እየራቀኝ፣
የእምባዬ ግለት ፊቴን ሲፈጀኝ፣
የነፍሴ አምላክ" እነኋት " ብሎ እናቱን ሰጠኝ፤

Âś   ሚስጥረ     Yenatua Lij
በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው⛪️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ሰላም ላንተ ይሁን ፥ የታቦር ተራራ
የተገለጠብህ ፥ የአምላክ ድንቅ ስራ
ቅዱሱ ተራራ ፥ የምስጢራት ደብር
ግርማው የታየብህ ፥ በገናና ክብር
ልብሱ ነ....ጭ ሆነ ፥ ድንገት ተለወጠ
አንደ ፀሐይ በራ ፥ ምስጢር ተገለጠ

ቡሄ ቡሄ በሉ ፥ ሰዎች ተደሰቱ
ጨለማ ሲገፈፍ ፥ ሲነጋ ሌሊቱ
ከክህደት የሚያድን፥ ከጥርጥር መንፈስ
እውነት በዚያ ታይቷል፥ ልብን ሞልቶ ሚፈስ

ለፈሪሳውያን ፥ ለአዋቂ ነን ባዮች
በሙሴ ህግ አለን ፥ ተከራካሪዎች
እነሙሴ መጥተው ፥ ለርሱ መሰከሩ
ኋላ መገለጡን ፥ ቀድመው እንዳወሩ

አንድም ስለሰው ልጅ፥ ስለ ማንነቱ
ልባቸው ለሚስት ፥ ስለ አምላክነቱ
ኤልያስ ነህ ለሚሉት፥ ኤልያስ መጣላቸው
ሙሴ ለሚሉትም ፥ ሙሴን ጠራላቸው
የሚያነሳ የሚያኖር ፥ ፈጣሪ አምላካቸው
ከያሉበት ጠርቶ ፥ በዚያ አስቆመላቸው

ኤልያስም አለ..............
ዮርዳኖስን ብከፍል፥ ሰማይን ብለጉም
ምልክትን ባደርግ ፥ እሳትን ባወርድም
ኃይልን ብጎናፀፍ ፥ ጠላትን ባርድም
አምላኬን በኔ ስም ፥ ሲጠሩት አልድም
ብሎ መሰከረ ፥ ልቡ እየተነካ
ጌታው በርሱ መጠን ፥ ስለማይለካ

ሙሴም እንዲህ አለ ...........
በሲና በረሃ ፥ ከላይ መና ባወርድ
ከአለት ውሃ ባፈልቅ ፥ ደመናን ብጋርድ
ታምራትን ባደርግ ፥ ባህርን ብከፍልም
የአባቶቼን አምላክ ፥ ጌታን አላኽልም
የአብርሐምን አምላክ ፥ በርሱ ልክ አሎንም !!
አንኳን መሆን ቀርቶ ፥ ያሰቡት ለምን ነው ?
ጌታን #ማየት እንኳን ፥ እጅግ መታደል ነው
ብሎ ተናገረ...... ፥ ስለ አማኑኤል ክብር
በአምሳለ ተዋህዶ ፥ በምጢሩ ደብር

አንድም አሮን እና ፥ ማርያም እህቱ
በሲፓራ ዮቶር ፥ በኢትዮጵያዊቱ
ሙሴን ቢያቆጣቸው፥ ጥቁሯን በማግባቱ
እግዚአብሔር አለ.........
ባርያዬን በቤቴ ፥ እኔ ሹሜዋለሁ
ነብያት ባስነሳ ፥ ምሳሌ እሰጣለሁ
አልያም በራእይ ፥ ሆኘ አገለጣለሁ
ሙሴን ግን ዝምበሉት ፥ እኔ እታየዋለሁ
አፍለአፍ በግልጥ ሆኜ፥ አናግረዋለሁ
ብሎ ስለነበር ፥ ትንቢት ተፈጸመ
አፍለአፍ ተናገሩ ፥ በግልፅ አብሮት ቆመ

አንድም የህያዋን ፥ የሙታን አምላክ ሲል
ኤልያስ ከህያዋን፥ ሙሴን ከመቃብር
የነብያት እና ፥ የሐዋርያት ጭምር
ጥንት የነበረና፥ ዘለዓለም የሚኖር
በአልፋና ኦሜጋ ፥ በ'ውነተኛው ባ'ንዱ
ብሉይና ሐድስ ፥ እዚያው ተዋሐዱ
በአንድ እምነት ሆነው፥ በፊቱ ሰገዱ

አንድም የስላሴ ፥ ምስጢር ተገለጠ
በብሩህ ደመና ፥ አብ ድምፁን ሰጠ
እኛም ከወልድ ጋር፥ ባንድ ቆመን ሳለን
የምወደው ልጄን ፥ እርሱን ስሙት አለን
በብርሃን አምሳል ፥ መንፈስ ቅዱስ ታየን
ልጅም በአባቱ ዘንድ፥ ያለውን ክብር አየን
ለማይጠፋ እርስቱ ፥ ለመንግሥቱ ለየን

አንድም ነገረ ጾም ፥ ለሚጠራጠሩ
አርባ ቀንና ሌት ፥ በጾም የከበሩ
ሙሴና ኤልያስ ፥ ሁለቱ ተጠሩ
የተራራው ምስጢር ፥ ተገልጦ ያየነው
ቢቀኙት አያልቅም ፥ እጅግ የበዛ ነው
ቢነገር > > >> >> >> !

ከአለም ተረት ተረት፥
ከሌለው መሰረት
ከይሆናል ግምት ፥
ውልየለሽ መላ-ምት
ከይምሰል ብልሃት ፥ ከልብ-ወለድ ትርክት

ኑ በዚህ ተራራ.........!!
ኑ ቃሉን እንስማ ፥ እንኑር በርሱ እቅፍ
ከወጀብ ማዕበሉ ፥ ከነፋስ እና ጎርፍ
በአለም ከምናየው.. ..
ከጥፋት ርኩሰት ፥ እንሽሽ እንትረፍ
ከሚጋየው መቅሰፍት ፥ እናምልጥ እንለፍ
በማደሪያው ገብተን ፥ በቅዱሱ መቅደስ
ከዘርፋፋው ልብሱ ፥ ዳስሰን እንፈወስ

ኑ በዚህ ተራራ.... ...
ከቅዱሳን ጋራ ፥ አንቁም በኅብረት
ቤተ ክርስቲያንን ፥ ቅጥሯን እንሙላት
ለጥያቄያችን መልስ፥ ወደ የሚገኝባት
የሚያለቅሱት እምባ ፥ የሚታበስባት
የታመሙት ሁሉ ፥ የሚፈወሱባት
ያቀረቀሩትም ፥ ቀና የሚሉባት
ጥላቻ ያይደለ ፥ ፍቅር የነገሠባት
ከሁከት የራቀች ፥ ሰላም የበዛበት
በዚች መሆን ለኛ ፥ መኖሩ መልካም ነው
አምባ መጠጊያችን ፥ክርስቶስ በርሷ ነው

ኑ በዚች ተራራ........
ልባችሁ አይፍራ!
ከሊቅ እስከ ደቂቅ
ትንሽ እስከ ትልቅ ፥ ከእቅልፍ ተነሱ
የእምነት ጋሻችሁን ፥ ሰይፋችሁን አንሱ
ተቃዋሚው በዝቷል ፥
ፍቅር ከአለም ጠፍቷል
ገንዘብ አምላኪና ፥ ርኩሰቱም ታይቷል
አሳዳጃችንም ፥ ጠላት አፉን ከፍቷል

ኑ በዚች ተራራ ...........
ልባችሁ አይኩራ
ለሰላሟ መርከብ ~ ለዚች ላ'ማናዊት
ካባችሁ እስኪወድቅ ~ እንደ ቅዱስ ዳዊት
እንዘምር ለጽዮን~ለመአምላክ ለእናቱ
አድስ ቅኔ እንቀኝ ~ እንውደቅ በፊቱ
ማደርያውን እና ~ ስሙን እናወድስ
የጠላትን ቅጥር ~ በእልልታ እንደርምስ

እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ እናት ተደፍራለች
በጠላት እጅ ወድቃ ፥ ልጆቼን ትላለች
ንፁሐን ልጆቿ ፥ እምነቴን ስላሉ
ደማቸው ፈሰሰ ፥ በገፍ ተገደሉ
የቀጥተኛዋን ፥ መንገድ የሚያፈርሱ
የዳቢሎስ ልጆች ፥ አጥፊዎች ተነሱ
በግፍ የሚጠሏት ፥ አሳዳጆች በዙ!

የገዛ ልጆቿም ፥ እንደ እርብቃ ማህፀን
እኔ'በልጥ እኔ'በልጥ፥ ብኩርና ሽተን
ባ'ንድ እትብቷ ታስረን ፥ በሆዷ ተኝተን
ለማያልፈው መንግሥት ....
ህዝብ የምንሆነውን ፥ ዓላማ ዘንግተን
ለዚያውም ትልቁን ...
የሰማይ አርማውን ፥ መስቀሏን አንግተን
በምድራዊ ሀሳብ ፥ ክልል እና ወሰን
ላላፊ እና ጠፊ ፥ ለማትረባዋ አለም
በቅድስቲቱ ምድር ፥ በዳግማዊት ሳሌም
ያልተሰማ ሮሮ ፥ ያልታየ ጉድ የለም

አቤቱ ዝም አትበል!!
ጌታ ሆይ ዝም አትበል ፥ ይህ እስከመቼ ነው ?
የቀድሞ ምህረትህ፥ ይቅርታህ ወደትነው?

ለያህዌ ለአዶናይ......
ለእግዚአብሔር ኤልሻዳይ፥ ሁሉ ለሚቻለው
እባክህ አሁን አድን ፥
አሁን አቅና እያልን ፥ እንድንማፀነው
በአንድ ልብ ሆነን ፥ እንድንለምነው
በዚህ መሆን ለኛ ፥ መኖሩ መልካም ነው።

✍️,,,,,,,,,,,,  ማሩ አብዬ

ነሐሴ 12/2012 ዓ.ም
2025/03/04 07:24:05
Back to Top
HTML Embed Code: