Forwarded from Dr. Eyob Mamo
መጎዳትን ሲሸሽ የኖረ ሰው ጸጸት
“ከጓደኞቼ ጋር ግንኙነቴን በጠበኩት ኖሮ!”
(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)
ብሮኒ በምትሰራበት በዚህ አዛውንት የመጨረሻቸውን ምእራፍ በሚያሳልፉበት ማረፊ ቦታ የምታየው የአንዳንድ ሰራተኞች ሁኔታ ቢያበሳጫትም እርሷ ግን ለአዛውንቱ ያላትን ርህራሄ ከመግለጽ ወደኋላ አትልም ነበር፡፡ በዚያ ቦታ የሚሰሩት አንዳንድ ሰራተኞች ብሮኒ ለአዛውንቶቹ የምታሳየው ርህራሄ አይመቻቸውም፡፡ በዚያ ስፍራ ያላቸው የስራ ዘመን ለእነሱ ገንዘብ የማግኛና “የተሻለ” ስራ እስኪያገኙ ድረስ መቆያ ነው፡፡ የብሮኒ አመለካከት ግን ከዚህ ለየት ያለ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
አንድ ቀን በርኒ የተሰኘ አንድ አዛውንት ለመመገብ ተቀምጦ ነበር፡፡ እርሱ የፈለገው የምግብ ምርጫ ዶሮ ሆኖ ሳለ ያገለገለችው ሴት ግን ያቀረበችለት የበግ ስጋ ነበርና ብሮኒ ምግቡን ከእርሱ ፊት በማንሳት ሁኔታውን በማሳሰብ ልታስቀይርለት ሄደች፡፡ አስተናጋጇ፣ “የተሰጠውን አርፎ ይበላል” በማለት በክፉ መለሰችላት፡፡ “የጠየቀውን ከዶሮ የተሰራ ምግብ መስጠት እየቻልን ለምን ያንን አናደርግለትም” በማለት ብሮኒ ጥያቄዋን ደግማ ብታቀርብም “የቀረበለትን የበግ ስጋ ካልበላው በረሃብ መሞት ይችላል” የሚል መራራ ድምጽ የተቀላቀለበት መልስ ተሰጣት፡፡ ብሮኒ የዚህችን ጨካኝ ሴት ባህሪይ ባትቀበለውም በዚህ ደካማ አመለካከት ተጽእኖ ውስጥ በመሆኗ ግን አዘነችላት፡፡ ወዲያውኑ አንዲት ተወዳጅ ሰራተኛ ቀረብ ብላ፣ “ብሮኒ፣ ስለዚህች ሴት ብዙ አትጨነቂ፣ ባህሪዋ እንደዚህ ስለሆነ ተያት” በማለት አረጋጋቻት፡፡
ብሮኒ ዘወር ብላ ስትሄድ ዶሪስ የተሰኘችው እድሜዋ በጣም የገፋ ሴት ልክ ወደ አንድ ጉዳይ የመሄጃው ሰዓት እንደደረሰበት ሰው ሮዝ ቀለም ያለውን ቀሚሷን ለብሳ ተቀምጣለች፡፡ ብሮኒ ራሷን በማስተዋወቅ ቀረብ ስትላት ዶሪስ ፈገግ ብላ ፊቷን አዞረችባት፡፡ ብሮኒ የዶሪስን ሁኔታ ተመልክታ ሰላም መሆኗን ስትጠይቃት፣ ዶሪስ በድንገት እምባዋን መቆጣጠር አልቻለችም፡፡ ብሮኒ አጠገቧ በመቀመጥ እጇን ያዘቻት፡፡ ዶሪስ በፍጥነት እምባዋን ማፍሰስ በማቆም ከብሮኒ ጋር መወያየት ጀመሩ፡፡
ዶሪስ ለብሮኒ ራሷን ከፈት በማድረግ፣ “እዚህ ቦታ ከመጣሁ ጀምሮ ብቸኝነት ሊገድለኝ ነው … ለካስ ብቸኝነት ሰውን ሊገድለው ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰው እንዲነካኝና ቅርበቱን እንዲገልጽልኝ እራባለሁ” አለቻት፡፡ ለካስ ብሮኒ እጇን ያዝ በማድረጓ ምክንያት ነው ያንን የናፈቃትን በሰው የመነካት ሁኔታ ስላገኘች ዶሪስ እምባዋን መቆጣጠር ያልቻለችው፡፡
ብሮኒ ዶሪስን ለማወቅ ያላት ፍላጎት ስለጨመረ እንድታወራት መንገድን ስላመቻቸችላት ዶሪስ መናገር ቀጠለች፣ “ከሁሉም በላይ የሚናፍቁኝ ጓደኞቼ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ በሕይወት የሉም፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ አሁን እኔ ባለሁበት አይነት ሁኔታ ነው ያሉት፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የት እንዳሉም አላውቅም፡፡ የት እንዳሉ ባውቅ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ጓደኞችሽ ሁል ጊዜ ከአንቺ ጋር እንዲቆዩ ትመኛለሽ፡፡ ሕይወት ግን ይቀጥልና የሚያውቅሽ፣ የሚገነዘብሽና ስለታሪክሽ መረጃ ያለው ሰው አጠገብሽ እስከማይቀር ድረስ ብቸኛ ሆነሽ ራስሽን ታገኚዋለሽ፡፡”
ብሮኒ የዶሪስን ጸጸት በመጠኑም ቢሆን ለማርገብ ስትል በሕይወት የሚገኙትን የዶሪስን ጓደኞቿ ለማግኘት ሙከራ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት ከገለጸችላት በኋላ በመጠኑም ቢሆን ተሳክቶላታል፡፡ ከአንዳንዶቹ ጋር በደብዳቤና በስልክም ጭምር እንዲገናኙ ለማድረግም በቅታለች፡፡
ብሮኒ የዶሪስን ሁኔታ በቅርብ ካጠናች በኋላ ግንዛቤዋን ስትሰበስበው፣ የዶሪስ አመጣጥ ብዙ ሰዎች የሚያልፉበት የተሳሳተ የግምት ጎዳና ነው፡፡ ዶሪስ የኖረችው ኑሮ “የሩቅ ወዳጅነት” በሚል ፍልስፍና ይነዳ የነበረ ሕይወት ነው፡፡ ይህንን አመለካከቷን ስትገልጠው እንዲህ ትላለች፣ “ሰዎችን በሩቁ ባቆየሃቸው ቁጥር በሰዎች ምክንያት የሚመጣብህንም ጉዳትና ቁስል እንዲሁ በሩቁ ታቆየዋለህ፡፡ ማንም ሰው ካልቀረበህ፣ ማንም ሰው ሊጎዳህ አይችልም፡፡ ስለዚህ፣ በተቻለህ መጠን ከጓደኞችህ ጋር ያለህን ግንኙነት በሩቁ አድርገው፡፡”
የዚህ አመለካከት መጨረሻው ብቸኝነት ነው፡፡ በብዙ ሰዎች መካከል በአንድ ቤት እየኖርክ እንኳን የብቸኝነት ስሜት ሊጫጫንህ ይችላል፡፡ በአካባቢህ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ምንም ያህል ብዙ ቢሆን፣ የውስጥህን የሚገነዘብ ሰው ከሌለና እስከነማንነትህ የሚቀበልህ ሰው ካላገኘህ ብቸኝነት ከነችግሩ ይከተልሃል፡፡
ብሮኒ የዶሪስን ሁኔታ በሚገባ ተገንዝባዋለች፡፡ ዶሪስ ጓደኛን ከመቅረብ ሊመጣ ይችላል ብላ ካሰበችው የመጎዳት ሁኔታ ራሷን ለመጠበቅ ስትል እድሜዋን በሙሉ በገለልተኝነት ያሳለፈች ሴት ነበረች፡፡ በመጨረሻ ግን ለረጅም አመታት ይዛ የቆየችው የገለልተኛነት አመለካከት ወስዶ ያደረሳትን ስፍራ አልወደደችውም፡፡ ጸጸቷ እዚህ ጋር ነው፡፡ “ከጓደኞቼ ጋር ግንኙነቴን በጠበኩት ኖሮ! ብጎዳም እንኳን ጓደኞቼ ማንነቴን እንዲያውቁኝ በፈቀድኩኝ ኖሮ! ግንኙነቴን የጠበቀና ግልጽነት የተሞላው አድርጌው በሆነ ኖሮ!”
ለእነዚህ በእድሜአቸው መጨረሻ ላይ በጸጸት ውስት ለሚገኙ ሰዎች ብሮኒ የነበራት ርህራሄ ይህ ነው አይባልም፡፡ አንዱን ጸጸት ሰምታ ሳትጨርስ የሌላውን ትሰማለች፡፡ አሁን ደግሞ ይህኛው ለብዙዎች አረጋውያን የህሊና ሸክም የሆነው ጸጸት ገጠማት፡- “ከጓደኞቼ ጋር ግንኙነቴን በጠበኩት ኖሮ!” ከዚህ የተዛባ አመለካከት የተነሳ መጎዳትን ፍርሃት ከጓደኞቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በሩቅ በሩቁ የሚያደርጉ ሰዎች ከዚያ ለባሰና ለከፋ ጉዳት ራሳቸውን ያዘጋጁታል፡፡
ጊዜው ካለፈብህ በኋላ እዳትጸጸት ከጓደኞችህ ጋር ያለህን ግንኙነት አታባክነው!
ይቀጥላል . . .

ኃውልት ሆናችሁ እንዳትቀሩ!
በዚህ ሁሉም ነገር በፍጥነት በሚጓዝበትና በሚለዋወጥበት ዓለም ውስጥ ባሉበት ቆሞ መቅረት የሚባል ነገር የለም፡፡
ከዘመኑ ጋር ወደ ፊት ከመራመድ ይልቅ እንደ ኃውልት ባለንበት የቆምንባቸው እያንዳንዶቹ ቀናት ወደ ኋላ የቀረንባቸው ቀናት መሆኑ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡
ከዚህ ከቆሞ-ቀርንት ከሚመጣ ኋላ-ቀርነት ለመዳን . . .
1. ካለማቋረጥ አሁን ካላችሁበት የእውቀት ደረጃ አልፎ በመሄድ በአዲሱና ከዘመኑ ጋር በሚራመደው ተራማጅ እውቀት ራሳችሁን አዘምኑ፡፡
2. ዘወትር በምታደርጉት እንቅስቃሴ ከሰው ጋር ከመፎካከር ራሳችሁን በመጠበቅ ካወጣችሁት ከፍ ያለ ግብ አንጻር ተንቀሳቀሱ፡፡
3. ካለማቋረጥ የራሳችሁን እድገት፣ የስራችሁን ስኬታማነትና የአቅጣጫችሁን ትክክለኛነት መገምገምን አትርሱ፡፡
4. ሁል ጊዜ ካለፈው ስህታችሁ በመማር ራሳችሁን አሻሽሉ፡፡
5. ዘወትር ከሚሆነውና ከማይሆነው ነገር ይልቅ በነገሩ ላይ ያላችሁ አመለካከት ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ አመለካከታችሁን ጠብቁ፡፡
6. ሁል ጊዜ ወደ እናንተ ለሚመጡ እድሎች የተዘጋጃችሁ ሁኑ፡፡
7. በመጨረሻም ሁል ጊዜ ራሳችሁን ባለመገደብ አዳዲስ ነገሮችን ሞክሩ፣ ምናልባት የማታውቁትን ማንነታችሁንና እምቅ ብቃታችሁን ታገኙት ይሆናልና፡፡
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

የራእይ ጉልበት
በሕይወታችሁ በፍጹም መፍትሄ ሊያገኙ እንደማይች እስከሚመስላችሁ ድረስ የሚመጡ ፈተናዎችና ችግሮች አሉ?
እነዚህ ፈተናዎችና ችግሮች ብዙ ነገር ሞክራችሁ እንኳና ልባችሁን ከመጎተትና ተስፋ ከማስቆረጥ ላያባሩ ይችላሉ፡፡ ለእንደዚህ አይነቶች ከባድ ፈተናዎች መፍትሄ እንዲሆን ፈጣሪ የሰጣችሁ ታላቁ ስጦታ የራእይ ስጦታ ነው፡፡
ለተለያዩ ችሮች የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን የመውሰዳችሁ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለሁሉም ነገር መነሻ የሆነው ራእያችሁን የማወቅና የመከታተል ጉዳይ እጅጉን ሊታሰብበት ይገባል፡፡
• ከዚህ በፊት በሰራችሁት ስህተትና በወሰናችሁት አጉል ውሳኔ ምክንያት ጸጸት ውስጥ ካላችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱ ላይ ማተኮር ትጀምራላችሁ፡፡
• ሕይወታችሁን ሁሉ ሰጥታችሁት ሳለ ትቷችሁ የሄደ ወዳጅ፣ ጓደኛ፣ ፍቅረኛ ወይም የትዳር አጋር ሁኔታ እጅጉን ከጎዳችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ሕይወታችሁ በአንድ እናንተን ባልፈለገ ሰው ላይ ብቻ ከመንጠልጠል ይላቀቅና ራሳችሁን መምራትና ማሻሻል ትጀምራላችሁ፡፡
• ያላችሁበት የኑሮ ደረጃ በጣም የሚያታግልና ከባድ ከሆነባችሁና በዚሁ ሁኔታ እስከወዲያኛው እንደምትቀጥሉ እያሰባችሁ ከሰጋችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ የዛሬውን ኑሯችሁን አልፋችሁ የተሻለ የወደፊት ውስጥ እንደምትገቡ ተስፋን ትጨብጣላችሁ፡፡
• በሆነ ባልሆነው የሚናወጥ ስሜትና ተስፋ-ቢስነት የሚያጠቃችሁ ከሆነ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ውስጣችሁ ራእያችሁን በማሰብ፣ ስለእሱ በማቀድና ወደ ተግባር በመግባት ስለሚሞላ ለተስፋ ለመቁረጥ ጊዜም አይሰጣችሁም፡፡
ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላችሁም የተፈጠራችሁለትን ራእያችሁን ለማወቅ ጊዜን ውሰዱ! ራሳችሁን አሰልጥኑ! እሱን ተከታተሉ! መላውን ካላወቃችሁበት አጋዥ አግኙ!
ይህንን በማድረግ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ተመልከቱ!

Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
በቃ አንዳንዴ ሕይወት እንዲህ ነው!
ምንም ያህል ሕይወት አስቸጋሪ ሁኔታን ቢያቀብላችሁም . . .
1. ያላችሁን ትልቅ ሕልም፣
2. ያላችሁን ጠንክሮ የመስራት ልማድ፣ እና
3. ያላችሁን ተስፋ ያለመቁረጥ መንፈስ በፍጹም አትልቀቁ!
አንዳንዴ . . .
• አንዳንዴ ሁሉም ነገር ጠማማ ይሆንብኛል፣ እምቢ ይላል፣ ያስቸግራል . . . በቃ አንዳንዴ እንዲህ ነው!
• አንዳንዴ ገና ጠዋት ይጀምርና እስከማታ ጥሩ ስሜት የማይሰጡኝ ገጠመኞች በተከታታይ ያጋጥሙኛል . . . በቃ አንዳንዴ እንዲህ ነው!
• አንዳንዴ ሰው ሁሉ የተመካከረ እስከሚመስ ድረስ ባህሪው አስቸጋሪ ይሆናል . . . በቃ አንዳንዴ እንዲህ ነው!
• አንዳንዴ ለማከናወን ያሰብኳቸውን ነገሮች ለመጀመርና ተግባራዊ ለማድረግ መነሳሳቱን አጣለሁ . . . በቃ አንዳንዴ እንዲህ ነው!
• አንዳንዴ ቀድሞ የነበረኝን የመጓጓት ስሜት አጣዋለሁ . . . በቃ አንዳንዴ እንዲህ ነው!
አንዳንዴ ሁኔታዎች እንደዚህ ሲሆኑ፣ እኔም “የአንዳንዴ ሰው” እንዳልሆንና እንደሁኔታው ብቅ ጥልቅ የሚል ሕይወትና ልምምድ እንዳይኖኝ መጠንቀቅ አለብኝ፡፡
ይህ እንዳይሆን ካስፈለገ . . .
1. ይህ ሁኔታ እኔ ጋር ብቻ ያለ ሁኔታ እንደሆነ ከማሰብና ተስፋ ከመቁረጥ መጠንቀቅ አለብኝ፡፡ ማንኛውም ሕይወቱን ከልቡና በሙሉ ኃይሉ ለመኖር ወዲህ ወዲያ የሚል ሰው ይህንን ስሜት ይጋራዋል፡፡
2. በወቅቱ የሚሰማኝ ስሜትም ሆነ የማልፍበት ሁኔታ ቋሚ እንደሆነና እንደማይለወጥ ከማሰብና ተስፋ ከመቁረጥ መጠንቀቅ አለብኝ፡፡
3. በምንም አይነት ሁኔታም ሆነ ስሜት ውስጥ ባልፍም ፈጽሞ ላቆማቸው የማይገባቸውን ተግባሮችና ሃላፊነቶችን እንዳሉ ማስታወስና አቅሜ በፈቀደው መልክ በተግባር መጽናት አለብኝ፡፡

ዝግጁ ናችሁ?
የኢቲኬር የ1 አመት ጉዞ የሚበሰርበት
እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የምርት አስተዋዋቂ የሚገኝበት
የኢቲኬር 1ኛ አመት ክብረበዓል
ቅዳሜ ግንቦት 19 2015 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል
www.etcareproduct.com
#icare #youcare #wecare
#etcare
@etcareofficial
የኢቲኬር የ1 አመት ጉዞ የሚበሰርበት
እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የምርት አስተዋዋቂ የሚገኝበት
የኢቲኬር 1ኛ አመት ክብረበዓል
ቅዳሜ ግንቦት 19 2015 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል
www.etcareproduct.com
#icare #youcare #wecare
#etcare
@etcareofficial
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ራእይ እያለ እንደሌለ!
(“ራእይን ማወቅና መኖር” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)
ከራእይ አውድ አንጻር፣ ይህንን ጽሑፍ የምናነብ ሰዎች በሶስት እንከፈላለን፡-
1. ምንም አይነት ራእይ የሌለን ወይም ራአያችንን የማናውቅ፡፡
2. ራእይ እያለንና እያወቅነው በዚያ አቅጣጫ መሄድ ያልቻለን፡፡
3. ራእያችንን በማወቅ በዚያ አቅጣጫ መንገድ የጀመርን፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ በዚህ ምድር ላይ ካለምንም ራእይ (ካለምንም ዓላማ ማለት ነው) የሚወለድ ሰው አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ ልዩነቱ ያለው ከተወለድን በኋላ የምልፍባቸው ሁኔታዎችና ያሳደጉን ሰዎችም ሆነ የአካባቢያችን ሕብረተሰብ የአኗኗር ዘይቤ ያመጣብን ጫና ራእይ እያለን ልክ እንደሌለን ኖረን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡
ራእይ እያለን ልክ እንደሌለው ሰው ታስረን እንድንቀመጥ ከሚያደርጉን እንቅፋቶች መካከል የሚገኙትን ይገኙበታልና በጥንቃቄ መመልከቱና ከመንገዳችን ላይ ማስወገዱ አስፈላጊ ነው፡፡
1. ባለፈው ታሪክ መኖር
የራእይ ጉዳይ ከወደፊታችን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ የወደፊታችንን በሚቀርጽ ጉዳይ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ካላቸው ነገሮች አንዱ የኋላችን ላይ የማተኮር ሁኔታ ነው፡፡ ያለፈው ታሪካችንና ልምምዳችን በወደፊቱ ራእያችን ላይ መልካም መዋጮን የማድረጉን ያህል ወደ ኋላ ሊጎትተንም እንደሚችል በማሰብ ያለፉ ስህተቶችን በጥንቃቄ መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡
ሕይወት እስከኖርን ድረስ የስህተትም ሆነ የስኬት ልምምዶች እንዳሉ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህን የተለያየ ገጽታ ያላቸውን ልምምዶች በተገቢው መንገድ መያዝ ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በሃሳባችን እየተመላለሰ ውስጣችንን የሚያደክመውን ያለፈ ስህተት ጉዳይ ማሸነፍ አስፈላጊ ነው፡፡ ልናተኩር የሚገባን በወደፊት ራእያችን ላይ ሊሆን ሲገባው ባለፈው ታሪክ መያዝና ወደኋላ መጎተት ከብዙ ስኬታማ ጉዞ የሚገታን ጉዳይ ነው፡፡
2. የስኬት ማጣት ፍርሃት
ፍርሃት ብዙ አይነት ገጽታ አለው፡፡ ይህ ስኬትን የማጣት የፍርሃት አይነት ማንኛውም አዲስ ነገርን ለመጀመር የሚፈልግ ሰው የሚጋፈጠው ፍርሃት ነው፡፡ በፊታችን ልንገባበት የምናስበውና ራእይ ብዙ ነገራችንን ዋጋ ሊያስከፍለን ስለሚችል ምናልባት ካልተሳካ ሊደርስብን ይችላል የምንለው ቀውስ ያስፈራናል፡፡ በተሳካ ሁኔታ ወደፊት ለመቀጠል ግን ይህንን እንቅፋት ማሸነፍ ግን የግድ ነው፡፡
የስኬት ማጣትን ፍርሃት ለማስወገድ ካስፈለገ የስኬትን ትርጉም በሚገባ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ ስኬት ማለት አለመድከም፣ አለመወላወል፣ እንቅፋትን አለመጋፈጥ፣ አለመውደቅና … እንደሆነ ከማሰብ መጠበቅ አለብን፡፡ በዚያ ምትክ ስኬት ማለት የብዙ ውጣ ውረዶች ጎዳና መሆኑን በመገንዘብ ሁኔታዎች ለጊዜው ተሳኩም አልተሳኩም ከራእያችን አቅጣጫ አንጻር ወደፊት የመሄድን ልምምድ ማዳበር የግድ ነው፡፡
3. ሰው-ተኮር መሆን
በእያንዳንዱ በምናደርገው ነገር ላይ ሰዎች ያላቸው አመለካከት ምን እንደሆነ የመጨነቅ ዝንባሌ ካለን፣ ራእያችንን በጽንአትና በትኩረት ለመከተል ያስቸግረናል፡፡ ራእዩን ለይቶ ለማወቅ፣ ለመቅረጽና ለመከተል በተነሳ ሰው ላይ ሰዎች የተለያዩ ወደ ኋላ ሊጎትቱ የሚችሉ አመለካከቶችን ሊያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ ይህንን የተለመደ እውነታ ደግሞ ለማለፍ የቆረጠ ማንነት ያስፈልጋል፡፡
እኛ እውነት ሆኖና በሚገባ ገብቶን በምንከተለው ራእይና ዓላማ ላይ ሰዎች ምንም አይነት አመለካከት ለመያዝ መብት እዳላቸው መቀበል ልቦናን ያሳርፋር፡፡ ሰዎቹ የሚያስቡትና የሚናገሩት ላይ ከማተኮር ይልቅ ራእያችን ላይ ማተኮር ስኬታማ ያደርገናል፡፡ በተጨማሪም፣ የሚቃረን ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች ከመስማት ይልቅ ሊያበረታን የሚችል ሃሳብ ያላቸው ሰዎች አካባቢ መሆን ይበጃል፡፡
4. የክህሎት ችግር
አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን ራእያቸውን ወደማወቅ ቢመጡም ያንን በውስጣቸው የሚያውቁትን ራእይ በምን መልኩ መስመር እንደሚያስይዙት፣ እንደሚገልጹትና ተግባራዊ ወደመሆን እንደሚያመጡት መላውን አያውቁትም፡፡ ይህ ሁኔታ ከክህሎት ጋር የተገናኘ ሁኔታ ነው፡፡ አንድ ሰው ራእዩን ካወቀ በኋላ ወደ የት እንደሚወስደው ካላወቀ ያንን ክህሎት የማሳደግ ጉዞ ሊጀምር ይገባዋል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የክህሎቱ አቅም ሲያንሳቸውና ያንንም ማሳደግ ካልፈለጉ አንድ ሰው ሊኖረው የሚገባውን ራእይ-ተኮር ጉዞ ከብዙ ፍልስፍና ጋር በማነካካት የራእይ እውነታ የማጣጣል ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ አንዳንድ ሰዎች፣ የምንኖረው አስቀድሞ የተወሰነልንን ነገር ስለሆነና እኛ በዚያ ነገር ላይ ምንም ቁጥጥር ስለሌለን የመጣውን ዝም ብለን መቀበል እንዳለብን ያስባሉ፡፡ ይህ የተዛባ ፍልስፍና ከራእይ ቀጠና ያወጣናል፡፡
(መጽሐፉን ለመግዛት፡- 0924126841)

Forwarded from Elite Ambassadors
FOCUS!
Imagine you're on a path to achieving your goals, but suddenly, the dogs start barking. Their noise is distracting, but remember, dogs bark. It's what they do. You can't control their barks, but you can control your response. Ignore them, focus on your journey, and keep moving forward. Life is too short to let the barking dogs of distraction steer you off course. Stay true to your purpose, keep your eye on the prize, and stay focused. Embrace the challenge, keep pushing, and one day you'll look back and realize that those barking dogs were just background noise on your path to greatness.
Have beautiful dream!
great time @ etcare torhayiloch!

My REALIZATIONS about GETTING STARTED.
1) You only need ONE thing to get started. One smile can start a friendship. One hand can lift a soul. One candle can wipe out darkness. One word, one child, one teacher, one pen and one book can change the world. Be that ONE.
2) You don’t have to be smarter than the rest. You just need to be more disciplined than the rest and get started.
3) Conquer yourself. Your success or failure in life or at work isn’t about other people. It’s your procrastination and excuses. Success happens when you grow yourself, not outgrow others. Winners focus on winning. Losers focus on winners.
4) Nothing changes if nothing changes. When you change how you see things, both you and the things you see change. You see the world what you carry in your heart.
5) Every teacher once was a student. Every winner once was a loser. Every expert once was a beginner. Small steps taken every day leads you to your success.
6) Perseverance is the multiplier of Talent and Potential. Success is not about who has more talent, but who is hungrier. A river cuts through a rock not because of its power, but its persistence. You can do anything you set your mind to, but it takes action, persistence, and the courage to face your fears.
7) Stress comes from ignoring things that you should not be ignoring. Break down the task and start small. A journey of 1000 miles start with one step. Don't wait to be in the mood to do a certain task. Motivation follows action. Get started, and you'll find your motivation will follows. Don't worry about the darkness when you take that first step, for that is when the stars shine brightest.
8)You can become a person of value in a matter of months. Every mountain top is within your reach if you keep climbing. If you aren’t winning, you must be learning.
9) Once you start, no matter how long you have travelled in the wrong direction, you can always turn around. When you can’t change a situation, change yourself. Intelligence is the ability to adapt to change.
10) Risk is better than regret. Take that first step. The biggest risk is not getting started. If you want something you’ve never had, then you must do something you’ve never done.
Don’t procrastinate. Take that first step.
Written By
Cedric Ng

ቀኑ የሰላም ቀን ነው!
የዛሬዋ ቀን የሰላምና ደስ የምትል ቀን ናት!
• ዛሬ ከምንም ነገር በፊት ሰላማችሁን አስቀድሙ!
• ሰላማችሁን ከሚረብሽ ሰው ራቁ!
• ሰላማችሁን ከሚነጥቅ ንግግር ተቆጠቡ!
• ሰላማችሁን ከሚቀማችሁ ተግባር ራሳችሁን ጠብቁ!
• ሰላማችሁን ከሚወስድ ማሕበራዊ ሚዲያ ተጠበቁ!
ሁሉም ነገር የሚጥመው በቅድሚያ ሰላም ስንሆን ነው!
የሰላም ቀን ይንላችሁ!
ይህንን የሰላም መልእክት ቢያንስ ለሶስት ሰዎች በማጋራት የሰላም መሳሪያ ሁኑ!
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የዛሬዋ ቀን የሰላምና ደስ የምትል ቀን ናት!
• ዛሬ ከምንም ነገር በፊት ሰላማችሁን አስቀድሙ!
• ሰላማችሁን ከሚረብሽ ሰው ራቁ!
• ሰላማችሁን ከሚነጥቅ ንግግር ተቆጠቡ!
• ሰላማችሁን ከሚቀማችሁ ተግባር ራሳችሁን ጠብቁ!
• ሰላማችሁን ከሚወስድ ማሕበራዊ ሚዲያ ተጠበቁ!
ሁሉም ነገር የሚጥመው በቅድሚያ ሰላም ስንሆን ነው!
የሰላም ቀን ይንላችሁ!
ይህንን የሰላም መልእክት ቢያንስ ለሶስት ሰዎች በማጋራት የሰላም መሳሪያ ሁኑ!
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
በቃ ልመዱት !!!
• ሰዎች “አደርገዋለሁ” ብለው የገቡላችሁን ቃል ኪዳን ላይፈጽሙ ይችላሉ - ልመዱት!
• ዛሬ የሚወዷችሁና የሚያከብሯችሁ ሰዎች ነገ ሊጠሏችሁና ሊንቋችሁ ይችላሉ - ልመዱት!
• ዛሬ ምስኪን መስለው ለሕልውናቸው በእናንተ እርዳታ ላይ የተደገፉ ሰዎች ነገ ውለታ-ቢስ ሆነው ልታገኟቸው ትችላላችሁ - ልመዱት!
• ሰዎች የሆናችሁትን ማንነት ሳይሆን ያላችሁን ቁሳቁስ አይተው እንደቀረቧችሁ ልትደርሱበት ትችላላችሀ - ልመዱት!
• አንዳንድ ሰዎች በሰላሙ ጊዜ የሰሙትን ምስጢራችሁን ግንኙነታችሁ ሻከር ሲል ለወሬና እናንተንው ለማጥቃት ሊጠቀሙበት ይችላሉ - ልመዱት!
እነዚህንና እነዚህን መሰል በማንኛውም ሕብረተሰብ መካከል የሚንጸባረቁ የሰዎች ባህሪያትን መልመድ ማለት፣ ሁል ጊዜ ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር እንደማናገኝ መገንዘብና ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡
ከሰዎች የምንጠብቀውን መልካም ነገር ስናገኝ ደስ የመሰኘታችንንና ሰዎቹንም የማመስገናችን ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለማንኛውም አይነት ወጣ ያለ የሰዎች ሁኔታ ራስን ማዘጋጀትና ከሁኔታው ባሻገር አልፎ ለመሄድ የውስጥ ውሳኔን መወሰን እጅግ ጠቃሚ ልምምድ ነው፡፡
እንደሰው የመለዋወጥ ሁኔታ የሚለዋወጥ ሰባራ ማንነት እንደሌላችሁ ለራሳችሁ የምታስመሰክሩበት ቀን ይሁንላችሁ!

Forwarded from Etcare Official®️ (Kloud ፲፩)
በህብረት ስራ ማህበራት አማካይነት የሚመረቱ የግብርና ምርቶች በቀጥታ ለሸማቹ ማድረስ እንዲችሉና አምራቹም ባመረተው ምርት ተጠቃሚ ሆኖ የተሻለ አምራች እንዲሆን በ ኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢትዮጲያ ህብረት ስራ ኮሚሽን የተለያዩ አማራጮችን አቅዶ እየሰራ ይገኛል። በዚህም መሰራት ከሳምንት በፊት ኮሚሽኑ በስካይላይት ሆቴል ባዘጋጀው የባለድርሻ አካላት ምክክር እና ትስስር ፕሮግራም ድርጅታችን እንዲገኝ በተጋበዘው መሰረት የድርጅታችን መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማቲዎስ መባ የተገኙ ሲሆን በምክክር መድረኩ ከተገኙ የፌዴራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች እና የህብረት ስራ መሀበራት አመራሮች ጋር በቀጣይ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዬች ላይ ምክክር አድርገዋል።
www.etcareproduct.com
#etcare #icare #youcare #wecare
@etcareofficial
www.etcareproduct.com
#etcare #icare #youcare #wecare
@etcareofficial
Forwarded from Ambassador
ዲሲፕሊን!
ዲሲፕን ማለት አንድን ነገር የማድረግ ፍላጎቱ ባይኖረንም እንኳ ጠቃሚ ስለሆነ ብቻ ራስን በማስገደድ በየእለቱ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዲሲፕሊን ማለት አንድን ነገር የማድረግ ፍላጎት እያለን ሳለ፣ ነገሩ ጥቅመ-ቢስና ጎጂ ስለሆነ ብቻ ራሳችንን በመግዛት ከማድረግ ራስን መከልከል ማለት ነው፡፡
በእነዚህ በሁለቱ የዲሲፕሊን ትርጉሞች መሰረት የማያቋርጥ ልምምድ ያለው ሰው 80 በመቶው የሕብረተሰቡ ክፍል ያልተለማመደው አስገራሚ ልምምድ ላይ ደርሷል፤ ለላቀ ስኬትም ራሱን እያዘጋጀ ነው፡፡ ይህ የዲሲፕሊን ልምምድ ወደ አንድ አስገራሚ ዓለም ያሻግረዋል፡፡ ይህ አስገራሚ ዓለም የልማድ ዓለም ነው፡፡
ልማድ ማለት አንድን ቀድሞ ማድረግ የማንችለውን ወይም የማንፈልገውን ነገር ራሳችንን በዲሲፕሊን በማስገደድ ከመደጋገማችን የተነሳ ላለማድረግ እስከማንችል ድረስ ስንለምደው ማለት ነው፡፡
በአንድ ነገር ዙሪያ ዲሲፕሊን እንደከምታዳብሩ ድረስ ከተለመደው አዙሪት አትወጡም፡፡ አንድን ዲሲፕሊን ደግሞ ልማድ እስከሚሆን ድረስ ካልደጋገማችሁት የጀመራችሁት ነገር ስለማይጸና ታቋርጡታላችሁ፡፡ ይህ ጀምሮ የማቋረጥ ሁኔታ ደግሞ የራስ-በራስ ምልከታችሁን፣ እንዲሁም ለራሳችሁ ያላችሁን አክብሮትና ግምት እጅጉን ያወርደዋል፡፡
በርቱና የዲሲፕሊንና የልማድ ሰው ለመሆን ስሩ!
መልካም ቀን!