✞አወድሰኝ ኤፍሬም✞
@Orthodox_Addis_Mezmur
✞አወድሰኝ ኤፍሬም✞
አወድሰኝ ኤፍሬም ብላ ጠየቀችው ድንግል እናታችን
ባርክኒ ብሎ ወገቡን ታጠቀ ኤፍሬም አባታችን
የልጄ በረከት ይደርብህ ብላው ጀመረ ምስጋና
ወደ ብርሃን ድንኳን ወደ ተከበረው ደራሲው ገባና
ልቡ ያዘነ አዳምን ሊያድን ጌታ ወደደ
ዳግሚት ሰማይ ማደሪያው ልትሆን እሱ ፈቀደ
የሰማይ ምስጢር በማህጸንሽ ተከናወነ
ከዘሩ ቀርተሽ በንጽሕናሽ የሰው ዘር ዳነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን(በየ አዝማች አለ።)
አዝ= = = = =
በሔዋን ምክንያት በለስዋን በልተን ገነት ቢዘጋ
በአንቺ እናትነት ዳግም ተዛመድን ከአምላካችንጋ
ትውልድ ሁሉ ስምሽን በክብር አመሰገነ
የሲዖል ቀንበር በላያችን ላይ ስላልተጫነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
አዝ= = = = =
የእዳ ደብዳቤ ተቀዳደደ የባርነቱ
አዳም ሔዋንም ከእስራታቸው ወጡ ተፈቱ
የሲዖል ጽልመት በልጅሽ ጠፍቶ ብርሃን ሆነ
እረፍት አገኘን የምሕረት ዓመት ባንቺ ዘመነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
አዝ= = = = =
ሙሴ በሲና ሳትቃጠይ ያየሽ ሐመልማል
እግዚአብሔር መርጦሽ በማህጸንሽ ዙፋኑን ተክሏል
የዲያብሎስን ጥበብ እንዲያፈርስ አምላክ ሰው ሆነ
በልጅሽ መሞት መዳናችንም ተከናወነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
እንኳን ለሶርያዊው አባ ኤፍሬም
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
አደረሰን አብልኮት
መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
@mazemurdabetara
አወድሰኝ ኤፍሬም ብላ ጠየቀችው ድንግል እናታችን
ባርክኒ ብሎ ወገቡን ታጠቀ ኤፍሬም አባታችን
የልጄ በረከት ይደርብህ ብላው ጀመረ ምስጋና
ወደ ብርሃን ድንኳን ወደ ተከበረው ደራሲው ገባና
ልቡ ያዘነ አዳምን ሊያድን ጌታ ወደደ
ዳግሚት ሰማይ ማደሪያው ልትሆን እሱ ፈቀደ
የሰማይ ምስጢር በማህጸንሽ ተከናወነ
ከዘሩ ቀርተሽ በንጽሕናሽ የሰው ዘር ዳነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን(በየ አዝማች አለ።)
አዝ= = = = =
በሔዋን ምክንያት በለስዋን በልተን ገነት ቢዘጋ
በአንቺ እናትነት ዳግም ተዛመድን ከአምላካችንጋ
ትውልድ ሁሉ ስምሽን በክብር አመሰገነ
የሲዖል ቀንበር በላያችን ላይ ስላልተጫነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
አዝ= = = = =
የእዳ ደብዳቤ ተቀዳደደ የባርነቱ
አዳም ሔዋንም ከእስራታቸው ወጡ ተፈቱ
የሲዖል ጽልመት በልጅሽ ጠፍቶ ብርሃን ሆነ
እረፍት አገኘን የምሕረት ዓመት ባንቺ ዘመነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
አዝ= = = = =
ሙሴ በሲና ሳትቃጠይ ያየሽ ሐመልማል
እግዚአብሔር መርጦሽ በማህጸንሽ ዙፋኑን ተክሏል
የዲያብሎስን ጥበብ እንዲያፈርስ አምላክ ሰው ሆነ
በልጅሽ መሞት መዳናችንም ተከናወነ
ሰዐሊ ለነ (፪)
እንኳን ለሶርያዊው አባ ኤፍሬም
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
አደረሰን አብልኮት
መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
@mazemurdabetara
✞ውበት ነሽ✞
@Orthodox_Addis_Mezmur
✞ውበት ነሽ ለቤቴ✞
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና (2)
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና(2)
በሃዘን ጠቋቁራ ተከፍታለች ገፄ
አጎንብሻለሁኝ አፍሬ በለምፄ (2)
ወልቋል ከራሴ ላይ የብርሃን ልብሴ
ሃብቴ አንች ብቻ ነሽ ያለሽን ሞገሴ (2)
አዝ= = = = =
ለአምላክ የማቀርበው አጣው በጎ ስራ
ነፍሴ ተጨነቀች በምግባሬ መርራ (2)
ጥላሸቱ በዝቶ ተዳፍኗል ጎጆዬ
ብርሃን የለውም ካልበራ ሻማዬ (2)
አዝ= = = = =
የምታመንበት አንዳች ነገር የለኝ
በነፍስም በስጋ ሁሉ የጎደለኝ (2)
እጠባበቃለሁ የእጅሽን በረከት
በቤቴ ላይ አርፎ እስክባረከበት (2)
አዝ= = = = =
የጓዳዬ ክብር የቅጥሬ ድምቀት ነሽ
አይኔን የምትሞይው በመቅረዜ በርተሽ(2)
የፅልመት ጭላንጭል ጠፍቷል የለም ዛሬ
የብርሃን እናት ስላለች በበሬ (2)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
@mazemurdabetara
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና (2)
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና(2)
በሃዘን ጠቋቁራ ተከፍታለች ገፄ
አጎንብሻለሁኝ አፍሬ በለምፄ (2)
ወልቋል ከራሴ ላይ የብርሃን ልብሴ
ሃብቴ አንች ብቻ ነሽ ያለሽን ሞገሴ (2)
አዝ= = = = =
ለአምላክ የማቀርበው አጣው በጎ ስራ
ነፍሴ ተጨነቀች በምግባሬ መርራ (2)
ጥላሸቱ በዝቶ ተዳፍኗል ጎጆዬ
ብርሃን የለውም ካልበራ ሻማዬ (2)
አዝ= = = = =
የምታመንበት አንዳች ነገር የለኝ
በነፍስም በስጋ ሁሉ የጎደለኝ (2)
እጠባበቃለሁ የእጅሽን በረከት
በቤቴ ላይ አርፎ እስክባረከበት (2)
አዝ= = = = =
የጓዳዬ ክብር የቅጥሬ ድምቀት ነሽ
አይኔን የምትሞይው በመቅረዜ በርተሽ(2)
የፅልመት ጭላንጭል ጠፍቷል የለም ዛሬ
የብርሃን እናት ስላለች በበሬ (2)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
@mazemurdabetara
[_አልጠቅምም_አትበል_]
ስለ ሌሎች መዳን ከማይጨነቅ ክርስቲያን በላይ ሰነፍ ሰው የለም፡፡ ወዳጄ “እኔ ድኻ ነኝና ይህን ማድረግ አልችልም” የምትል አትኹን፤ ባለ ኹለት ዲናሯ_ሴት ትወቅስሃለችና፡፡ ዳግመኛም “ወርቅም ብርም የለኝም” ብሎ የተናገረ ጴጥሮስ ይወቅሰሃልና፡፡
"ምናምንቴ ነኝ" አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው ጢሞቲዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡
[_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_]
@mazemurdabetara
ስለ ሌሎች መዳን ከማይጨነቅ ክርስቲያን በላይ ሰነፍ ሰው የለም፡፡ ወዳጄ “እኔ ድኻ ነኝና ይህን ማድረግ አልችልም” የምትል አትኹን፤ ባለ ኹለት ዲናሯ_ሴት ትወቅስሃለችና፡፡ ዳግመኛም “ወርቅም ብርም የለኝም” ብሎ የተናገረ ጴጥሮስ ይወቅሰሃልና፡፡
"ምናምንቴ ነኝ" አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው ጢሞቲዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡
[_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_]
@mazemurdabetara