Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
✨ ELOHE PICTURE
🅲🅻🅸🅲🅺 🅷🅴🆁🅴
ይህን ይጫኑት
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ Lᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ
🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗⏰
https://www.tgoop.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ እና ሕሊናህ እንዲረጋጋ ሁል ጊዜ በደልህን ተናዘዝ ። ነገር ግን ውድ እርሱ እንዳትመለስ ተጠንቀቅ ።
አቡነ ቄርሎስ ስደተኛ
🅲🅻🅸🅲🅺 🅷🅴🆁🅴
ይህን ይጫኑት
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ Lᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ
🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗⏰
https://www.tgoop.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
✨ ELOHE PICTURE
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው
መዝ118:26

"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?
"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡
እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?
አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።
እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት መጽሐፍ)

Telegram
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
የሰሙነ ሕማማት ሰኞ
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡
በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦
ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ የውጭ ቃላት አሉ ቀጥታ ሳይተረጓሙ ከዕብራይስጥ፣ቅብጥ፤ግሪክ ቃላት ይገኛሉ።
ኪርዬ ኤሌይሶን/ኪርያላይሶን/
ኪርዬ ማለት እግዚኦ ሲሆን ኪርያ ሲሆን ግን እግዝእትነ ይሆናል ኪርያላይሶን የምንለው በተለምዶ ነው እንጂ መባል ያለበት ኪርዬ ኤሌይሶን ነው ትርጉሙም አቤቱ ማረን ማለት ነው።
እብኖዲ ማለት አምላክ ማለት ነው።
ናይናን ማለት ማረን ይቅር በለን ማለት ነው።
ታኦስ የግሪክ ቃል ሲሆን ጌታ አምላክ ማለት ነው።
ማስያስ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ መሲሕ ማለት ነው
ትስቡጣ ማለት ዴስፖታ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ደግ ገዥ ማለት ነው።
ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው።
ክርስቶስ ማለት መሲሕ ማለት ነው።
አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው።
በሰሙነ ሕማማት የሚባሉ ቀለሞች እንደ ሌላው ጊዜ ወጥ ከግዕዝ የመጡ አይደሉም ይልቁንሙ ከዕብራይስጥ ፣ ከሮማይስጥ ፣ ከግሪክ የተውጣጡ ናቸው።
ቅዱስ ያሬድ ይህንን ያደረገበት ምስጢር ጲላጦስ ጌታን ካሰቀለ በኋላ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ የሚለውን ቃል በእነዚህ ቋንቋዎች ጽፎ በትራፈ መስቀሉ ላይ ጠርቆት ነበርና ያንን ለማስታወስ ነው።

ከማግሥተ ሆሣዕና በኃላ ዕለተ ረቡዕ
ሰሞነ ህማማት
እለተ ረቡዕ
በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላት እንደ ተገለጸው በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ተግባራት ተፈጽመዋል፤
አንደኛ የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
ሁለተኛ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
ሦስተኛ ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹‹ሲኒሃ ድርየም›› ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት
የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለ ነበር ‹‹ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡
ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (ዐቃቤ ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡ ‹‹ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤›› በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹አዛኝ ቅቤ አንጓች›› እንደሚባለው ነበር፡፡ ይሁዳ፣ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም ነበረ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ (ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮)፡፡
የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ዅሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ ‹‹ገንዘብ የኃጢአት ሥር ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡
ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ኾነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይኾን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ኾነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን

👍2
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
https://www.tgoop.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk

Forwarded from ማኅቶት Wave

+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? +
ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት::
"ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39
ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ::
"ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ::
ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20)
እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም?
ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ?
"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር::
የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23)
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን?
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ::
"ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም::
ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13)
ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ::
ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ::
አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር::
የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን::

🌿በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።🌿
ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሠላም።
🔆ልደታ ለማርያም🔆
💠{ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን }💠
🕯መዝ 86÷1🕯
እመቤታችን ልደቷ እንደእንግዳ ደራሽ እንደውኃ ፈሳሽ ሆኖ ሳይነገር ሳይታወቅ ሳይጠበቅ የመጣ አይደለም፤ እንደልጇ ሁሉ አበው ሲሿት በምሳሌ ጥላነት ሲያዩዋት፣ ነቢያቱ ሲተነበዩላት ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚኝ በማለት ሰሎሞንሞ እቴ ሙሽራዬ እያለ በትንቢት መነጽርነት ሲያናገራት የነበረች ናት እንጂ ።
አስቀድሞ ለአዳም በገባለት ቃልኪዳን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኃለው በማለት እርሱ ይወለድባት ዘንድ ያላት የመረጣት የአዳም የልጅ ልጅ እንደምትወለድና ከእርሷም እንደሚወለድ ነግሮታል።
ከዚህ በጎላ እና በተረዳ ግን ነቢዩ ኢሳይያስ "ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓዐርግ ጽጌ እምኔሃ" ... ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከግንዱ ይወጣል ... በማለት በትር ብሎ በትረ አሮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእሴይ ሥር ከዳዊት እንደምትወለድና ከእርሷም ጽጌ የተባለ ክርስቶስ እንደሚወለድ ተናግሯል።
የእመቤታችን ልደት ሊቁ "መኑ ይእቲ እንተ ትሔውጽ ከመጎኅ ያላት" ... ይህች እንደማለዳ ፀሐይ ያለች ማናት ... በማለት የገለጣት ለአማናዊው ፀሐይ ጎኅ፤ ለአማናዊው ወንጌል ንዑስ ወንጌል የሆነች የእመቤታችን ልደቷ ለልደተ ክርስቶስ ጎኅ ሆኖልን፤ በእርሷ መወለድ የእርሱን ሰው ሆኖ መወለድ እውን ሆኖልን ያረጋገጥንበት ነው።
ደራሲም ድንግል በልደቷ ለአዳምና ለልጆቹ ከመርገሙ መዳኛ ስለመሆኗ እንዲህ ብሎ ይጠቅሳል :-
ማርያም ድንግል በልደትኪ መጠነ አቅሙ፤
አዳም ይዌድስኪ ምስለ ደቂቀ ኩሎሙ፤
እስመ ለአዳም ብኪ ተስእረ መርገሙ።
🕯መልክአ ልደታ🕯
የእመቤታችን ልደት ከአምስቱ ልደታት አንዱ የሆነው እንደ ልደተ አቤል ያለ ይኸውም ከእናትና ከአባት የሚወለዱት ልደት ነው። ልደቷም መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን... መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው.. በማለት ቅዱስ ደዊት "አድባር ቅዱሳን" ብሎ ከገለጣቸው በምድር ከተነሱት ሁሉ በግብራቸው በጽድቃቸው በትሩፋት በክብር እንደ ተራራ ከፍ ብለው ከሚታዩት ከተነሱት ከታላላቅ ቅዱሳን ወገን ነው።🌱ታሪክ በእንተ ልደተ ማርያም🌱
ጰጥሪቃና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ቅዱሳን ባለጸጋ ለእንሶቻቸው የወርቅ ጉትቻ እስኪያረጉ ድረስ ሁሉ የተትረፈረፋቸው ሰዎች ነበሩ። እነርሱም መካን በመሆናቸው ያዝኑ ነበር። አብዝተውም እግዚአብሔርን ለመኑት ጠየቁትም በኋላም ሕልምን አዩ።
ሕልሙንም ሕልም ፈቺ ዘንድ ሔደው ፍቺውን ጠየቁት። እርሱም ነጭ ጥጃ መልኳ ደምግባቷ ያማረ ምግባሯ የተወደደ ሴት ልጅ ናት። እንዲህ አይነቷ እሷን የምትመስል እየወለደች ትሔዳለች፤ የመጨረሻዋ ጥጃ ጨረቃ መውለዷም ከሰማይ ዝቅ ከምድር እና ከፍጥረታት ወገን ግን ከፍ ያለች ልጅ ናት የፀሐዩ ነገር ግን አልተገለጠልኝም አላቸው። እነርሱም ይህንኑ ሰምተው ሄዱ። ሄኤማንን ወለዱ። ሄኤሜን ዴርዴንን፣ ዴርዴን ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሔርሜላን ወለደች። ሔርሜላና ማጣትም የጌታ አያቱ የምትሆን ሐናን ወለዱ።
💠ኢያቄም እና ሐና
ከነገሥታቱ ከይሁዳ ወገን የሚሆን ኢያቄም ቀለዮጳ የሚባል አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር። እርሱም ከካህናቱ ከነገደ ሌዊ የምትወለደውን ሐናን አገባ። እነርሱም የተቀደሱ ደጋግ ነበሩ። በደቂቀ እሥራኤል ዘንድም አብዝተው መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀንም ከደቂቀ እሥራኤል ወገን የሆነ ሮቤል የተባለ ሰው መጣና " በእኛ ፊት መሥዋዕትን ታቀርብ ዘንድ አይገባም፤ በእሥራኤል መካከል ዘር የለህምና" አለው። አይሁድ እና ካህናቱም ልጅ ስለሌላቸው ይንቋቸው ይጠሏቸው፤ መሥዋዕታቸውንም ለመቀበል እምቢ ይሉ ነበር።
ኢያቄምም ፈጽሞ አዘነና ስእለቴን እስኪሰጠኝ ወደእኔና ወደሚስቴም እስኪያይ ድረስ አልመገብም አልጠጣምም ብሎ ሱባኤ ለመያዝ ወደ ገዳም /በረሓ ወጣ። ሰባቱ ሰማያት እንደመጋረጃ ተገልጠው ነጭ ወፍ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ በራእይ አየ።
ታላቁ የፋሲካ በዓል በደረሰ ጊዜ አንዲት የመንደሩ ሴት ወደሐና መጥታ ለምን ታዝኛለሽ? ራስሽንስ ለምን ትጎጃለሽ? በዓል ስለደረሰ መምህሬ የሰጠኝን ይህንን ልብስ ልበሺ ልብሱ የነገሥታት ልብስ ነውና አንቺ ትለብሽው ዘንድ ይገባሻል አለቻት።
ሐና ግን አዝና ነበርና ብቸኛ በመሆኔ፣ ልጅም ስለሌለኝ ኀዘንተኛ ነኝና ያማረ ልብስን አለብስም፤ ደግሞም ማን እንደሰጠሽ በምን አውቃለሁ? እኔንም ከኃጢአትሽ ልትጨምሪኝ ነውን? አለቻት። ሴቲቱም በምላሹ ተናዳ እግዚአብሔር ማኅጸንሽን በመዝጋቱ ደግ አድርጓል አለቻት።
ሐናም ከቀድሞው አብልጣ አዘነች። ፈጥና ተነስታም ወደቤተ መቅደስ ሔደች። አእዋፋትንም ከልጆቻቸው ጋር ባየች ጊዜ አንስሳት አራዊት ልጆች አላቸው፤ ምድር እንኳን ፍሬ አላት ለእኔ ግን ልጅ የለኝም፤ ለሁሉ ልጅ አለውና ለእነርሱ ልጅን የሰጠህ ወደእኔ ተመልከት ልጅንም ስጠኝ ብላ እያለቀሰች ትጠይቅ ነበር።
⚜ቅድስት ሐና ሆይ እግዚአብሔርስ አንቺን ሳይመለከት ቀርቶ አይደለም። ከተናገረው ቀን ሳያጓድል ይመጣ ይወርድ ይወለድ ዘንድ ያለበትን ጊዜ እየጠበቀ ነበር እንጂ። እነሆም ቀኑ ደረሰ እግዚአብሔርም ወደአንቺ አየ ስእለትሽን ሰማ ልመናሽንም ተቀበለ ልጅንም ሰጠሽ፤ በአንቺም ዘንድ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም "ነጸረ አብ እምሰማይ ወኢረክበ ዘከማኪ" ያላትን ከፍጡራን መካከል አምሳያ የሚተካከል የሌላትን አንድያ እናቱን አገኘ።
ቅድስት ሐናም ነጭ ርግብ መጥታ በራሷ ላይ ተቀምጣ ከራሷ ላይም ወርዳ በጆሮዋ ገብታ በማሕፀኗ ስትተኛ በራእይ ተመለከተች። እነሆም በሐምሌ 30 ቀን የጌታ መልአክ (ቅዱስ ገብርኤል) ከሰማይ ወርዶ በፊቷ ቆመ፤ ጸሎትሽ ተሰምቷል ልምናሽንም ተቀብሏል ትፀንሻለሽ አላት። እርሷም ልጅን ከሰጠኝስ እስከ ዘመኑ ፍጻሜው ድረስ እንዲያገለግል ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ አለች። መልአኩም ወደ ኢያቄምም ሔዶ ይህንን ብሥራቱን አበሠረው።ኢያቄምም ተደስቶ ሁለት በጎችንና 12 ላሞችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።
አንድ ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ንጽሕት ብጽእት ድንግል ማርያምም ነሐሴ 7 ቀን በብሥራተ መልአከ በንጹሕ መኝታ ተጸነሰች። ስለ ጽንሰቷም የብሕንሳው ሊቀጳጳስ አባ ኅርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ .... ድንግል ሆይ ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነሽ አይደለሽም በሕግ በንጹሕ መኝታ ከኢያቄምና ከሐና ተወለድሽ እንጂ... በማለት ንጹሕ ከሆነ አልጋ ንጹሕ ከሆነ መኝታ መገኘቷን ይናገራል። ጠቢቡ ሰሎሞንም.. ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ምንም ነውር የለብሽም።.. (መኃ 4፥7) ብሎ ከማኅጸን ጀምሮ ጥንተ አብሶ እንደሌለባት ያስረዳናል።#ተአምረ_ማርያም_እምማኅፀነ_ሐና

ሐናና ኢያቄም ይባረኩ ዘንድ ወደ ቤተመቅደስ ሔዱ። ዘካርያስም መልአኩ ለሐና እንዲነግራት ያዘዘውን ልትባረክ ስትመጣ ይነግራት ጀመረ።"ሐና የምነግርሽን ነገር ስሚ፤ በልቦናሽም ጠብቂው ከዚህ በኋላ ከባልሽ ከኢያቄም ጋር አትተኚ፤ በማኅጸንሽ ያለው ፍሬ ለእግዚአብሔር ንጹሕ መሥዋዕት ነውና። ይኸውም በዚያን ዘመን ሙሴ የተመለከተው ዕጽ ነው። በውስጡም እሳት ይነድ ነበር፤ ፍሬውንም አላቃጠለውም፤ ይኽም በበረሓው ድንኳን ውስጥ ያስቀመጡትን የወርቅ መሶብ፣ ከሰማይ የወረደ፣ ለዓለሙ ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ የተሰወረ መና ያለበት ነው። ዛሬም ለእግዚአብሔር የተቀደሰና ንጹሕ ቁርባንን እስከምትወልጂ ድረስ (ከጉድፍ) ከጉስቁልና ትጠበቂ ዘንድ አዝዝሻለው። ሥራውንም ለዓለሙ ሁሉ ለልጅ ልጅ ይናገራሉ አላት።" ሐናም ይኽን ነገር በልቧ እየጠበቀች በረከትን ተቀብላ ወደቤቷ ሔደች።
ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም በሐና መጽነስ ተደስተው ይጎበኟቸው ነበር። ከእነዚህም መካከል ሀና ቤርሳቤህ የተባለች የአጎቷ የአርሳባን ልጅ ተደንቃ ማኅጸኗን ስትዳስሳት አይኗ በርቶላታል።
ሌላም ሐና የምትወደው ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ በሞተ ጊዜ ተግንዞ ወደተኛበት ሄዳ የአልጋውን ሸንኮር ይዞ በምታለቅስበት ወቅት ጥላዋ ቢያርፍበት ከተኛበት ተነስቶ .. ሰማይንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱ የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ ይሁን .. አላት፤ አይሁድም ደንግጠው ምን አይተህ እንዲህ አልክ? አሉት።
እርሱም "ከዚህ ከሐና ማኅጸን የምትወለደው ሕጻን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ እርሷ ናት" አለ በዚህም አይሁድ በማኅጸን ባለች ጽንሷ እንዲህ ካደረገች በእኛ ልትሰለጥን አይደለምን ብለው በምቀኝነት ተነሳሱባት። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው።#ጊዜ_ልደት_በደብረ ሊባኖስ
ሐናና ኢያቄምም በደብረ ሊባኖስ እያሉ ግንቦት 1 ቀን ሐና እመቤታችንን ወለደች። ቅዱስ ያሬድም ይህንን በማሰብ ...ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ፤ ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐየ። ኢያቄምና ሀና ሰማይን ወለዱ፤ ሰማይቱም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን አወጣችልን ... አለ።
ስለ ጊዜ ልደቷም ሲናገር "በእንተ ልደታ ለማርያም አድባር ኮኑ ኅብስተ ሕይወት ወእምዕጸወ ገዳምኒ ፈረዩ አስካለ በረከት" .. ድንግል ማርያም ስትወለድ ድንጋዮቹ ተራሮቹ ሁሉ የሕይወት እንጀራ (ምግብ) ሆኑ እጽዋትም ሁሉ የሕይወት ፍሬ አፈሩ በማለት ይገልጽልናል።
ሐናና ኢያቄምስ ወላጅነታችሁ ድንቅ ነው። በእውነት በመጽሐፍስ መካን የነበሩ ብዙ ደጋግ ቅዱሳን የተባረከ ልጅን ወልደዋል። እናንተ ግን ለፍጥረተ ዓለም በጸጋ፤ ለፈጣሪ ደግሞ በግብር እናት የምትሆንን ልጅ ወልዳቹሃልና። ለእናንተ ልጅ ናት ለኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድያ እናቱ ናት።
አብርሃምና ሣራ ብሩክ ዘር የሚሆን ይስሐቅን ወለዱ፤ ሐናና ኢያቄም ግን የምድርን አሕዛብ ይባርክ ዘንድ አምላክ የሚወለድባትን ዘር ለዓለም ሰጡ።
ሐና አልቅሳ ለእሥራኤል መስፍን ለቤተ መቅደስም አገልጋይ የሚሆን ሳሙኤልን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን ለአማናዊው ድኅነት መፈጸሚያ የሆነች ቤተመቅደስን ወለዱ።
ራሔል አልቅሳ ያዕቆብንና ዘሩን ከምድራዊ ረኃብ ከጊዜያዊ ሞት ለጊዜው የሚቤዣቸውን ዮሴፍን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን አዳምን ከነልጆቹ ከዘለዓለማዊው ሞት አንስቶ ለዘለዓለማዊ ድኅነት በማብቃት የሚቤዣቸውን ክርስቶስን የምታስገኘውን፤ እርሷም በፍቅሯ እየጠራች ስለኃጢአታቸውም ምሕረትን እየለመነች የምታድናቸውን መድኃኒት ወለዱ።
ሐናና ኢያቄምስ ከዚህ በፊት ከነበሩት ወላጆች ሁሉ ከበሩ፤ በክብር በሞገስም ከፍ ከፍ አሉ ለአምላክ አያቱ ሆነዋልና፤ ዘርን በማስቀረት ረድኤቱን በማድረግ ለአዳምና ለልጆቹ ሲሰጥ ለነበረ አምላክ እናቱን ስጦታ/መባዕ አድርጋችሁ ሰጥታቹሃልና። ይኸውም መባዕ ቅድሚያ ብቸኛ እናት ልትሆነው የምትችለውን (እስከ እርጅና ያለልጅ የቀራችሁበትን ጊዜ በእምነት ታግሳችሁ ከሌላ ሳትሄዱ) በመውለዳችሁ፤ ሁለተኛም ለእርሱ አገልጋይ ሆና ነየ አመቱ ለእግዚእነ ... እኔ ለጌታ ባሪያው ነኝ .. የምትል ለታላቂቱ አገልግሎት (ለድኅነተ አዳም) የተመረጠች ልጅን ስለሰጣችሁ ነው።
"ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፤ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና (ሃይማኖት) ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።"
🕯መኃ 4፥8🕯
ጠቢቡ ሰሎሞን በትንቢት መነጽር ልደቷን ተመልክቶ በሊባኖስ እንደምትወለድ በሳኔር በተመሰለ ከኢያቄም በኤርሞንም በተመሰለች ከሐናም እንደምትወለድ፤ የአንበሶች የነብሮች ተራራ በማለት ከሁለቱ ኃያላን ከቤተ መንግሥት እና ከቤተ ክህነት ወገን እንደምትወለድ ተናግሯል።
የእመቤታችን ልደት የተከናወነው በደጅ፤ ከፍ ባለ ተራራ ላይ ነው። በዚህ መወለዷም የእርሷ ልደት ለዓለም ሁሉ ጥንተ መድኃኒት መሆኑና ለሁሉ የተሰጠች ስጦታ መሆኑን ለማመልከት ነው።
በስደት ላይ ያለ ሰው የላመ የተዘጋጀ ምግብ የለውምና ሐናና ኢያቄም ንፍሮ እየበሉ እመቤታችንን በደብረ ሊባኖስ መውለዳቸውን በማሰብ በዓሉን ከደጅ ወጥተን ንፍሮ በመብላት እናከብረዋለን። በበዓሉም ምዕመናን ለከርሞ ብንደርስ በማለት ብጽዓት/ ስእለት ይሳላሉ። ዕለቱን ከኪዳን ከማኅሌት ከቅዳሴው በመሳተፍ፣ ቅዱስ ቁርባኑን በመቀበል፣ ጸበል በመጠጣት በመጠመቅ፣ የእመቤታችንን የምስጋና መጻሕፍትን በተለይም መልክአ ልደቷን በማድረስ፣ በመመጽወት የታመሙትን የታሰሩትን በመጠየቅ ማክበር ይገባናል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ዋቢ መጻሕፍት
1.መጽሐፍ ቅዱስ የ፳፻ ዕትም
2.ድርሳነ ማርያም
3. መኃልይ መኃልይ ዘሰሎሞን ማብራሪያ በመጋቤ ሐዲስ ስቡሐ አዳምጤ
4. መዝሙረ ዳዊት ትርጓሜ ትንሳኤ ዘጉባኤ እትም
5.የእመቤታችን በዓላት በመ/ር ተስፋሁን ነጋሽና መ/ር ኤርምያስ ወ/ኪሮስ

https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0

ግንቦት ፲ /10/
በዚችም ቀን አብርሃም ፀራቢ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ
የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ ተማረና በብዙ የሚጋደል ነበር። ድንጋይ በመጥረብ የውሀ መሔጃ ይሰራ ነበር። በአንዲት ዕለትም በሌሊት ሲጸልይ የዚችን ዓለምና በውስጧ ያለው ሁሉ ኃላፊ መሆኑን አሰበ።
የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ ስም ምስክር ሆኖ መሞትን ወደደ። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶት ጽና አትፍራ አንተ ጠላቶችህን ድል አድርገህ የሰማዕትነትን አክሊል ትቀበላለህና አለው ።
ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ወደ ተጠመቀባት ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ በሥዕሉ ፊት ቁሞ ጸለየ። በርሱም ዘንድ ሰውነቱን አደራ አስጠበቀ ወደ መኰንኑም ወጥቶ ክርስቲያን እንደ ሆነ ታመነ። ያንጊዜም ከከባዶች እንጨቶች ጋራ የኋሊት አሥረው ከረኃብና ከጽምዕ ጋራ ከፀሐይ ውስጥ ጣሉት። መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ጌታችን ተገለጠለት። ሰላምታም ሰጠው ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግም ቃል ኪዳን ሰጠው።
ከዚህ በኋላም መኰንኑ ራሱን እንዲቆርጡት አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ራሱ እኔ ክርስቲያን ነኝ እያለች ሦስት ጊዜ በተራራው ላይ በረረች ሃምሳ ምዕራፍ ያህልም ሒዳ ከባሕርወደቀች።
ከዚህም በኋላ ሆዱን ሰንጥቀው ባሩድና ሙጫ ዘይትን መልተው ከእሳት ውስጥ ጣሉት። እሳቱ ግን ምንም አልነካውም ከዚህም በኋላ በየጥቂቱ ከትፈው በእንቅብ አድርገው ከባሕር ውስጥ ጣሉት። በእግዚአብሔርም ፈቃድ ከራሱ ጋራ አንድ ሆኖ እንደ ቀድሞው እስና በሚባል አገር በባሕሩ ወደብ ታየ ምእመናንም ወስደው በታላቅ ክብር ቀበሩት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
❤2
Forwarded from ማኅቶት Wave
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0
https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0
https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0
መልካም ዕድል!!!
https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0
https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0
https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0
Forwarded from ማኅቶት Wave
🎬 ምን አይነት የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ፊልም እና ጥቅሶች ይፈልጋሉ❓️
🎬 JOIN አዳምና ሔዋን ሙሉ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN አቡነ ተክለሃይማኖት ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN ጠቢቡ ሰለሞን ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የሃያል ሳምሶን ሙሉ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የአባ ጳውሊ መንፈሳዊ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN ቅድስት አርሴማ ሙሉ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የነብዩ ቅዱስ ሙሴ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN አባ ኖብ ሙሉ መንፈሳዊ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 Join Elohe picture
✅ እንደ ምርጫው መርጠው ይ🀄️ላ🀄️ሉ ✅