#UK
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ መጥተው ስለሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እና ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ከከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሰልጣናት ጋር ውይይት አድርገው የነበሩት የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ፤ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም እና ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እንዲደርስ ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነት አጥብቀው እንደሚደግፉ አሳውቀዋል።
ቪኪ ፎርድ ፥ የትግራይ ባለስልጣናት ተኩስ በማቆም እና ከአፋር በመውጣት ምላሽ መስጠት አለባቸው ብለዋል።
የታየው ቁርጠኝነት በተግባር ሰብዓዊ እርዳታ ወደመላክ መተርጎም አለበት ያሉት ሚኒስትሯ ይህንንም የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለመደገፍ ዝግጁ ነው ሲሉ አብስረዋል።
ህወሓት ባወጣው መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም ዝግጁ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ከያዛቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች ለቆ ስለመውጣት ያለው ነገር የለም።

#Tigray
የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆመ መወሰኑ ይታወቃል።
ከመንግስት ውሳኔ በኃላም ከትግራይ ክልል በኩል በጎ ምላሽ መኖሩ ለበርካታ ወራት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እና ከክልሉ ውጭ ላሉ ቤተሰቦች በጎ ተስፋን ያጫረ እንደሆነ ይታመናል።
ነገር ግን ከዚህ በፊት የመከላከያ ኃይል ባለበት ፀንቶ ይቆያል ከሚለው ውሳኔ በምን ይለያል የሚል ጥያቄ የሚነሳ ሲሆን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፦
" የመጀመሪያው ወደ ትግራይ አካባቢ አልገባም አለ እንጂ የተለያዩ ትንኮሳዎች ካሉ አፀፋ አልመልስም አላለም።
የተለያዩ አካባቢዎች ላይ አደጋዎች ሊኖሩ ይችላሉ ብሎ በሰጋ በየትኛውም ጊዜ እርምጃ ከመውሰድ የሚያግድ ነገር አልነበረም።
የአሁኑ ግን ለበረራዎች ደህንነት ሲባል፣ የህወሓት ሚሊሻም በተለያየ መልክ ስጋት ውስጥ ገብቶ መንገዱን እንዳይዘጋው የትኛውም አይነት ግጭት ከማድረግ እቆጠባለሁ ነው ያለው " ሲሉ አስረድተዋል።
ከውሳኔው በኃላ እርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል የሚደረግ ጥረት በተመለከተ ዶ/ር ለገሰ፥
"...በሳምንት እስከ3 ጊዜ ይካሄድ የነበረ በረራ አሁን መጠኑን የመጨመር አንዱ ነው።
ሌላው ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የገንዘብ ፍሰት ጋር የተያያዘ የታገዱ ነበሩ እነሱ በተወሰነ ደረጃ የመጨመር እንቅስቃሴ ነው። ገደቦች ነበሩ ገደቦቹን የማሻሻል ስራ ይሰራል " ብለዋል።
ሌላው ፥ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታው መቀላጠፍ የህወሓት ኃይሎች በጉልበት ከያዛቸው አካባቢዎች ለቀው እንደሚወጡና ዋናውን የ " አብዓላ ኮሪደር " መስመርን እንዲከፍቱ ጠይቋል፤ ከያዙት ቦታ ባይለቁ ለሚለው ጥያቄ ዶ/ር ለገሰ " እሱን በሂደት ብናየው ይሻላል ከአሁኑ መገመት ተገቢ አይሆንም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#Update
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 18 የሚያካሂደውን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ዛሬ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምራል።
በዛሬው ዕለት በነበረው የጉባኤው ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና ንግግር አድርገዋል።
ፕ/ር መረራ በንግግራቸው " በሀገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የኦሮሞ ወጣት (ቄሮና ቀሬዎች ) የደም ዋጋ ከፍሎበታል። ብዙዎችን አጥተንበታል " ብለዋል።
" ለውጡ መጥቶ አዲስ መንግስት ተመስርቶ ወንድሞቻችን ወደ ሚኒሊክ ቤተመንግስት ሲገቡ ትንሽ ስራቸው አሳስቦኝ በግፋ በለው ባይሄዱ አልኩኝ " ያሉት ፕ/ር መረራ " በዚያ በግፋ በለው መንገድ በመሄዳቸው በእነዚህ አራት ዓመታት ሀገራችንንም ሆነ ህዝባችንን ብሎም ፓርቲያችንን ከፍተኛ ዋጋ አስከፍለዋል " ሲሉ ተደምጠዋል።
" ከምንም በላይ ደግሞ ምርጫውን ያለ ብሄራዊ መግባባት ብናደርግ ሰላም እና መረጋጋትን እድገት እና ብልፅግናን ብሎም ዴሞክራሲን አያመጣም በፈጣሪ ስም ወደ ብሄራዊ መግባባት እንሂድ ብለን ጠይቀን ነበር " ብለዋል።
" ነገር ግን በእንቢተኝነት ተሄደበት ውጤቱ ደግሞ የምታዩት ነው ፤ ኃይል በእጃቸው ያለው አይሆንም እኛ በቀድሞ ህግ መሰረት ነው የምንሄደው ብለው ምርጫ አካሄዱ ያ ደግሞ ጦርነት መዘዘ " ሲሉ ተናግረዋል።
ፕ/ር መረራ " ጦርነቱ እንዳይጀመር ተማፅነናል " ያሉ ሲሆን " ከተጀመረም እንዳይቀጥል በተደጋጋሚ ነው የጠየቅነው አሁን ያ ሁሉ ህይወትና ንብረት ወድሞ ወደእርቅ ተመጥቷል " ብለዋል።
ፕሮፌሰሩ ፤ 2014 ዓ/ም ላይ ከተካሄደው ምርጫ ተገፍተው መውጣታቸውን ገልፀው የፓርቲያቸው ጥያቄ የነበረው እውነተኛ የምርጫ ቦርድ ፣ ምህዳሩ የሰፋ የፖለቲካ ስርዓት እንደነበር አስረድተዋል።
የሃጫሉን ህልፈት ተከትሎ የፓርቲው አባላት እና አመራሮች ወደ እስር ቤት መታጎራቸውን ፤ ከ206 ፅህፈት ቤቶችም 203ቱን መዘጋታቸውን ይህን ተከትሎ ተገፍተው ከምርጫ መውጣታቸውን ገልፀዋል።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፤ በትግራይ ምርጫ እንዳልተካሄደና በኦሮሚያም አንድ ፓርቲ ከራሱ ጋር መወዳደሩን አንስተዋል።
በመጨረሻ ፕሮፌሰር መረራ " ሰሞኑን መንግስት ከህወሓት ጋር ጦርነቱን አቁሞ ወደ ብሄራዊ መግባባት እንሂድ እየተባለ ነው የሚገኘው የኛዎቹስ ? ኦነግ ሸኔ የተባሉትን በአንድ ወር እናጠፋለን እያሉ ነው በጦርነቱ ማንም ያሸንፍ ማን የኦሮሞ ህዝብ ግን የከፋ ዋጋን ያስከፍለዋል በፈጣሪ ስም አስቡበት በሏቸው። " ሲሉ ተደምጠዋል።
ፓርቲያቸው ለሰላም በሚደረገው ትግል፣ ለሀቀኛ ዴሞክራሲ በሚደረገው ትግል፣ ይሄን ሀገር ለመለወጥ እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ትግል ውስጥ የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

🌧 ኢትዮጵያ - ሶማሌ ክልል 🌧
" በሶማሌ ክልል አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መዝነብ ጀምሯል " - የሶማሌ ክልል መንግሥት
የሶማሌ ክልል መንግስት ዛሬ አመሻሽ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የድርቁ ጉዳይ አንዱ ነው።
ክልሉ በመግለጫው ላይ ፤ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ህዝብና እንስሳትን ለመታደግ በሰራው ስራ ድርቁን መቋቋም መቻሉን ገልጿል።
ከክልሉ መንግሥትና ህዝብ ጎን በመሆን ድጋፍ እና ትብብር ያደረጉ አካላት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን በማንሳትም ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል።
አሁን የድርቅ አደጋ ጊዜ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ያሳወቀው የሶማሌ ክልል መንግስት በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መጣል በመጀመሩ፣ ድርቁን ለመቋቋም እንደተሰራው አሁንም በድህረ ድርቁ እና በዚህ መሸጋገሪያ ወቅት ጠንካራ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን አሳውቋል።
በክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መዝነብ በመጀመሩ በአጠቃላይ ከሚጥለው ዝናብ በድርቁ የተጎዱ ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም በዝናቡ ምክንያት በወንዞችና ተፋሰስ አከባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች፣ ወረርሽኝና ተዛማጅ ጉዳዮች ለመከላከል ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የተሰሩ መሆኑን ገልጿል።

#Harari
ለቀጣይ ሶስት ወራት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራዮችን ማስወጣት ተከለከለ።
በዛሬው ዕለት የሐረሪ ክልል መስተዳድር ም/ ቤት ባካሄደው ውይይት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራዮችን ከተከራዩት ቤት ማስወጣትን የሚከለክለው ደንብ መርምሮ ማፅደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።
ምክር ቤቱ ደንቡን ያፀደቀው በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለመቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ብላል።
አዋጁ ለሶስት ወራት እንደሚቆይና የ " ንግድ ቦታ ኪራይን " እንደማያካትት ተገልጿል።

አቡበከር ናስር ወዴት ያቀናል
የአለም ዋንጫ
ተጠባቂ ዝውውሮች
የጨዋታ ውጤቶች እና ሌሎችም ያልተሰሙ አዳዳስ የስፖርት ዜናዎች
የyoutube channel ላይ ይከታተሉን
https://youtu.be/52bQiDuJk9E
የአለም ዋንጫ
ተጠባቂ ዝውውሮች
የጨዋታ ውጤቶች እና ሌሎችም ያልተሰሙ አዳዳስ የስፖርት ዜናዎች
የyoutube channel ላይ ይከታተሉን
https://youtu.be/52bQiDuJk9E
YouTube
ቃል ስፖርት ዜና 67