Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
ጾሙ ከተጀመረም በኋላ ሕዝቡ ወደ አምላኩ እንዳይጮህ እና እንዳይጸልይ ለማወክ የሕዝብ አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ የመንግሥት ሹማምንት ሊያገለግሉት ኃላፊነት የተቀበሉበትን የሀገሪቱን ሕግ ጥሰው ምእመናን ልጆቻችን ጥቁር ለብሰው ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡና በመንግሥት ቢሮዎችም አገልግሎት እንዳያገኙ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና አንዳንድ በፌዴራል እና በከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጥቁር የለበሱ እና በሀዘን ላይ ያሉ ልጆቻችንን በማሠር ሲያንገላቱ በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዚህም ሹማምንት ስልጣናቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት እየተጠቀሙበት መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ንቀት እና ጥላቻ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡

ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡
ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር:: ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል፡፡

በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችው የ፫ ቀናት ጸሎትና ምህላ በአግባቡ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይን አስመልክቶ በየካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል፡፡

በመግለጫውም፡-
፩ኛ. በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ መልኩ ሰልፍ ተጠርቷል በማለት መጥቀሱ የቤተክርስቲያን የመጨረሻው አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸውን አካላት የእምነቱ ተከታይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መብት ያላቸው ሕጋዊ አካላትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች አድርጎ መጥራቱ አሁንም ላይ ማብራርያ ለመስጠት መሞከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ እና የሚያጠለሽ እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጦች ጠበቃ ሆኖ የሚከራከረው መንግሥት መሆኑን ጭምር ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንግሥት የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተሰጠ የተባለው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንን ሕጋዊ መብት የገፈፈ እና ሕገ ወጥ መግለጫ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፡፡
፪ኛ. ጉዳዩን የውጪ እና የውስጥ ጠላቶች የፈጠሩት ነው በማለት የተለመደውን ፖለቲካዊ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከርም ቤተክርስቲንያንም ሆነ ሕዝብን መናቅ በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ላለፉት ፬ ዓመታት በሀሰተኛ ትርክት ልጆቿ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መከራን ሲቀበሉ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት ችላ ያለፈችው የሀገር መሠረት እንዳይናጋ፣ ቅጥሯ እንዳይደፈር በማሰብና በሀገር አንድነት ላይ ባላት የማይናወጽ ጽኑ አቋም ምክንያት መሆኑን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጉዳዩ ግልፅ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሆኖ እያለና መፍትሄውም በመንግሥት እጅ የሚገኝ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የፖለቲካ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከር ችግሩን ያባብሰው እንደሆን እንጂ አይፈታውም፡፡

በሰሞኑም ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የምትመራ እና ልጆቿም ድምጽዋን አውቀው በአግባቡ የሚሰሟት መሆኑ እየታወቀ ሆነ ተብሎ ቃላት አጠቃቀሙ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የሀሰት እና ጸብ አጫሪ የሆኑ መልእክቶችን በአደባባይ የተለጠፉ መሆናቸውን ሲታይ ምን ያህል ጉዳዩን ላልተገባ ፖለቲካዊ ጥቅም እንደተፈለገ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ተለጠፈ የተባለውም ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነና ፈጽሞም ሊሆን የማይችል መሆኑን ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

፫ኛ. የትኛውም ሰልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማድረግ አይቻልም በማለት የተደረገው ክልከላን በተመለከተም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውስጥ መሠረታዊ መብት ሆኖ የተጠቀሰ እና በሕገ መንግሥቱም አንቀፅ ፴ ላይ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ መንግሥት ራሱ የሚመራበትን ሕገ መንግሥት ማክበርና ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከላይ የተጠቀሰው ከፍተኛ መከራና በደል ምክንያት ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ጸንታ የመጣችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእኛ በልጆቿ ዘመን ስትፈርስ ዝም ብሎ መመልከት በጭራሽ የሚታሰብ አይሆንም፡፡

ይህን በደላችንን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማሳወቅ እና መንግሥትም ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነትና አፈና ወጥቶ ሕግ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠራነው የየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ እንድናከናውን መፍቀድ አሊያም የጠየቅናቸውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ እና አንድ በአንድ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥም የሚደርስብንን ሞት፣ መከራና ስደት እኛ አባቶች ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጋር ደስ ብሎን የምንቀበለው እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት፣ ዝም የሚል አንደበትና የሚሸከም ኀሊና የማይኖረን መሆኑን በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡
መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡

መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

“እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ”
የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://www.tgoop.com/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo
➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
🕊🕊 ㅤ ❍ㅤ YAHWEH NSi ♡ ㅤ 🕊 ❍ㅤ 🕊

📡 "ያህዌህ ንሲ" የሚለው ቃል የዕብራይስጥ ቃል ሆኖ ትርጉሙ "እግዚአብሔር አላማዬ ነው" ማለት ነው !! እግዚአብሔር ዓላማህን በማድርግ የእግዚአብሄርን ቃል ፣መንፈሳዊ ትምህርት ፣ የቤተክርስትያን ታሪክ ትውፊት እና ሥርዓት ለምእመናን ማድረስ መባረክ ነው።

እንዲሁም እግዚአብሄር ዓላማችሁ አድርጋችሁ መንፈሳዊ ትምህርት ለምታስትላልፉ ሁላችሁ መምህራን፣ምእመናን በየቻናሎቻችሁ የተለያዩ አገልግሎቶችን የምታቀርቡ  ሰዎች በሙሉ በመጀመርያ ምስጋና ይገባችኋል።
ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።  500 members ካለው 5ሺ members ያሉ በጣም ብዙ ናቸው ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ #ከ5ሺ እስከ 50ሺ members የያዙ እና ከዛ በላይ  አባሎች የያዙ ቻናሎችን እያሳደግን እንገኛለን እና ያለን ቦታ የተወሰነ ሰለሆነ ሁላችሁም የቻናል ባሌቤቶች (Owners ) በተሎ እንድትመዘገቡ በትሕትና እናሳውቃለን ።

  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ያስመዝግቡ
                =  @YEmeAmlak_DnglMaryam_Ljoch_Bot         
                =  ♡@Azaheill
Tel      :-  +251943686155 📞 ያገኙናል !!
 
          የፕሮሞሽኑ ሰዓት የተመለከተ

የሳምንት ፕሮግራም  
                 ➱ ማክሰኞ
                   ➱ ሀሙስ                   
                     ➱ ቅዳሜ     
                        ➱ እሁድ                    

🔘 ሰአት ፦ ከምሽቱ 12:00 - ጧት 2:00

🔘 Resend ፦ ከምሽቱ 2:00 ላይ ይደርጋል !!

   የፕሮሞሽን ማስታወቅያዎች  በሰዓቱ እንለቃለን እንዲሁም
በሰዓቱ እንሰርዛለን !!
               
#ሰበር_ዜና
፨፨፨፨፨፨፧፨ ፨፨፨፨፨፨

ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ በመሾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት መካከል አንደኛው ዛሬ የካቲት 5/2015 ዓ.ም የይቅርታ ደብዳቤ ለማስገባት ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደሚገኙ ሰምተናል።

ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።

ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን
👇
https://www.youtube.com/channel/UCElyVBweer5T07XVECr_Nkg?sub_confirmation=1
ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአት ጉባኤ ጠርቶ አባቶች በመግባት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም ምዕመናን በትዕግስት የቅዱስ ሲኖዶስን ወሣኔ ብቻ እንድትጠብቁ ስንል እናሳስባለን!

ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን
ዘወረደ
========
«ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ 3፥13፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃል ኪዳን መሰረት “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ።  ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭  ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው ፡፡

ጾሙን የበረከት ያድርግልን!!

ቶኔቶር ሀገረ እግዚአብሔር አቢሲኒያ ኢትዮጵያ ናት።
👉 @tonetore
ከፕሮቴስታንት-ተሐድሶ መናፍ**ቃ*ን ጋር ስንነጋገር ገድላትን ለኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ መከራከሪያ አድርገን አናቅርብ፣ በሐዋርያውያን ትውፊታውያን አብያተ ክርስቲያናት ከጥንት ጀምሮ የመጣውን አስተምህሮ አብራርተን ማቅረብ የምንችልበትን ጊዜ በአግባቡ እንጠቀም ማለት ገድላት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት እና መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቡ ለመረዳት አያስፈልጉንም ማለት አይደለም። ነገር ግን ለመወዛገብ በር የማይከፍቱ በግእዝ ብቻ ሳይሆን በግሪክ፣ በላቲን፣ በእብራይስጥ ጭምር የተመሳከረ ቅጅ (edition) ያላቸው ጥንታውያን ድርሳናትን ጠቅሰን ሐዋርያዊውን ኦርቶዶክሳዊ እምነት ማሳየት በምንችልበት ሁኔታ ለምን እነርሱ በመረጡት ሜዳ ላይ እንከራከራለን ለማለት ነው። ስለ ገድላት ብዙ ማጥናት እና የታረሙ ቅጅዎችን ማዘጋጀቱ በጣም አስፈላጊ ሥራ ነው። በጥልቀት ብንመረምራቸው እጅግ ጥልቅ ትምህርቶች እንዳሉዋቸው ይታወቃል። ብዙ ረቂቅ (mystical) መለኮታዊ ሐሳቦችን ይዘዋል።  ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊውን አስተምህሮ ለማስረዳት በገድላት ላይ መመሥረትና ዋናውን ጉዳይ እዛ ላይ ያሉ ጉዳዮችን ለማብራራት ማዋል የአካሄድ ስሕተት (methodological fault) ይመስለኛል። በጊዜ ቅደም ተከተልም ስናየው ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ከአብዛኞቹ ገድላት ይቀድማል፤ ገድላት በዚያ አስተምህሮ አምነው የኖሩ ቅዱሳን ተጋድሎን የሚያሳዩ ናቸውና። በመሆኑም በ4ኛው መ/ክ/ዘመን በሁሉም ዓለም ተንሰራፍቶ የሚገኝን ትምህርት ትክክለኝነት ለማስረዳት በ14ኛው መ/ክ/ዘመን የተጻፈ የአንድ ቅዱስ አባትን ገድል ዋና መከራከሪያ አድርጎ ማቅረብ ጊዜን መገልበጥ (anachronism) ይሆናል።
ስለገድላት እና ተአምራት በራሳቸው ርእስ አድርጎ መነጋገርም መከራከርም ችግር የለውም። እነ ወንድም ዘማርያም ገድላትን እንዴት መመልከት እንዳለብን ያሳዩበት መንገድ መልካም ነው። የበለጠ ደግሞ የተለያዩ ቅጅዎች ተጠንተው መታረም የሚያስፈልጋቸውም አሉ። ዋናውን ነገረ-ሃይማኖታዊ ጉዳይ ለመሸፈን ክርክሩን ሁሉ ገድላት እና ተአምራት ላይ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት ስላሉ ያነን መፍቀድ የሚገባ አይመስለኝም።
አጠንክሬ መናገር የምፈልገው ከ*መና*ፍቃ*ን ጋር በሚደረጉ ክርክሮች ዋናውን ጉዳይ ገድላትን ተአምራትን ወደማብራራት አናድርገው ማለት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ዝቅ አድርገን እንይ ለማለት አይደለም፤ ሌሎች በዓላማ ስለሚጠቀሙባቸው እና ብዙዎቹ የተጣራና የተመሳከረ ቅጅ (edition) ስላልተሰራላቸው ጉዳዩ ከጥንት ጀምሮ ወደሚታወቁ ድርሳናት ቢወሰድ ይሻላል ለማለት እንጂ።

Bereket Azemeraw
👉 @tonetore
በደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት በፖርት ኤሊዛቤት ከተማ ከ120 በላይ የሚሆኑ ትውልደ ደቡብ አፍሪካዉያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ።

በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ የከንባታ፣ ሐዲያ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት በፖርት ኤሊዛቤት ከተማ ከ120 በላይ የሚሆኑ ትውልደ ደቡብ አፍሪካዉያንን አጥምቀው የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ አድርገዋል።
በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ለ15 ታዳጊ ትውልደ ደቡብ አፍሪካ ወጣቶች የዲቁና እና ለ3 ዲያቆናት የቅስና ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።

ዘገባው የተሚማ ነው።

👉 @behlateabew
በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርከነ
በእደ ገብሩ ቆሞስ፣ በእደ ገብሩ መምህር፣ በእደ ብፁዕ ሊቀጳጳስነ፣ በእደ ክቡር መምህር

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በልክ እና በመልክ የተሠራ ሥርዓተ አምልኮ አላት፤ ሦስት መዓርጋተ ክህነትም አላት
እነርሱም
1 ድቁና
2 ቅስና
3 ጵጵስና
ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው በፍጹም ትሕትና ሁነው የሚያገለግሉባቸው መደቦች አሏቸው። ወደሰፊው ዝርዝር ሳልገባ ወተነሣሁበት ርእስ ለመመለስ ላሳጥረው።
የዲያቆናት አገልግሎት ተልዕኮ እና ማስተማር
የቀሳውስት ማስተማር ማጥመቅ ማቁረብ መናዘዝ መባረክ
የጳጳሳት ማስተማር ማጥበቅ ማቁረቡ መናዘዝ መባረክ ሌሎችን መሾም ነው።
ምእመናን ደግሞ ተሠጥዎ አላቸው መቀበል ማለት ነው።
ቄሱ ወይም ጳጳሱ ሊለው ከሚገባው ቦታ ላይ መጽሐፉ ይበል ካህን/ይካ ይላል
ዲያቆኑ ሊለው የሚገባው ቦታ ላይ ይበል ዲያቆን/ይዲ ይላል።
ምእመናን በሚቀበሉበት ቦታ ላይ ይበሉ ሕዝብ/ይሕ ይላል።
አገልግሎቱ የሚመራው በዚህ ነው። አሁን አሁን ግን በከተሞች አካባቢ የምንሰማው ነገር መንፈሳዊ አገልግሎት መሆኑ ቀርቶ መሞጋገሻ አስመስሎታል።

አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርከነ፤
ትርጉም፦ በአገልጋዩ በካህኑ እጅ ይባርከን ዘንድ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ።
በሚለው ቦታላይ
አንዳንዱ ያልተጻፈውን በእደ ብፁዕ ሊቀጳጳስ ከመ ይባርከነ ይላል
ለጳጳሳቱኮ ገብረ እግዚአብሔር መባል ታላቅ ክብር ነው እነ ቅዱስ ጴጥሮስን እነ ቅዱስ ጳውሎስን ገብሩ ወሐዋርያሁ የምንል ሰዎች ገና በምድር ያሉ ጳጳሳትን ገብሩ ብንላቸው ያከብራቸዋል እንጂ አያዋርዳቸውም። እመቤታችንም ነየ አመተ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር አገልጋዩ እነሆኝ ነው ያለችው።
መጽሐፉም ይካ ይላል እንጂ ይጳ፣ ይቆ፣ ይመ አይልም።
ጳጳስም ቆሞስም ቄስም ካህናት ናቸው በእደ ገብሩ ካህን የሚለው ያጠቃልላቸዋል ስማቸው ነው።

ከጠለና ደግሞ በእደ ክቡር ቆሞስ ማለት ተጀመረ ይህንን ሳናስተካክል ዝም ስል ጊዜ ቀሳውስቱ አለቆች የኛስ ለምን ይቅርብን ብለው በእደ ክቡር መምህር ማስባል ጀምረዋል።
በመሠረቱ መምህር የሙያ ስም እንጂ የክህነት ስም አይደለም።
ስለዚህ እባካችሁ ዲያቆናቱም በእደ ገብሩ ካህን በሉ
አባቶችም በእደ ገብሩ ካህን መባል ታላቅ ክብር ስለሆነ ሌላ ነገር የሚጨማምሩ ልጇቻችሁን ገሥጿቸው።

መ/ር ኀይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ።

👉 @tonetore
👇 Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ!
👉 https://www.youtube.com/channel/UCElyVBweer5T07XVECr_Nkg
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።


ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦
1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የካቲት 12 ቀን "ኦነግ ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ  የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
   መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
           የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
                  አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
2025/01/22 09:13:43
Back to Top
HTML Embed Code: