Telegram Web
​​ሱባዔና ሥርዓቱ
ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ

ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡

ሱባዔ ምንድን ነው?

ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡

ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ሱባዔ መቼ ተጀመረ?

ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ሲል ቃልን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ አራት/፡፡

በቀጣይ ሱባዔ ምንድን ነው ጥቅሙ?
​​ሱባዔ ለምን?
የሰው ልጅ፤ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡

በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ.7.22-25፡፡

ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ /ሱባዔ/ ይገባል፡፡

እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡

ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው? በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡

ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡

አኃው ለተልእኮ በወጡበት አንዱን ድቀት አግኝቶት ያድሯል፡፡ በነጋው ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ አለው፡፡እኔም እንዲሁ አግኝቶኛል፤ ይልቁንስ ሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደ ቀደመው ኾነን እንኖራለን ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡

ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢገብረ እኁከል፤ ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡

ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባት ቀን/ እንደ ጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡

ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡


ሱባኤ ለመግባት መደረግ ያለበት ዝግጅት
ክፍል ሦስት

ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት ኣስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት ኣስፈላጊ ነው፡፡

ቅድመ ዝግጅት

ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/ በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኣንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት ኣለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡

ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሓ ኣባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በኣባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ ኣባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኣንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሓ ኣባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡
@menefesawinet
ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ ኣቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው ኣንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዓቅምንና ችሎታን ኣገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡

ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በኣብዛኛው ሱባዔ የሚገባው ኣጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን ኣለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በኣጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሓራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በኣጽዋማት ወቅት ብዙ ኣባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከኣባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ ኣይያዝም» የሚል ኣቋም ለመያዝ ኣይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ካጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግልናል ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ ኣያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና ኣድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡

በክፍል 4 :- በሱባዔ ጊዜ ምን እናድርግ?
@menefesawinet

​​ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/

በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡

በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡

በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሓራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢኣቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡

በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡

ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/

ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡

ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማጸን መጽናት ይኖርብናል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@menefesawinet
#ተወዳጁ_ልጅሽ_እንዲመግበኝ_ትለምኝልኝ_ዘንድ_እማጸንሻለሁ

እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ እርሱም የልዑል ልጅ ይባላል አለሽ።

በተቀደሰው ስሙ ኅሊናዬን ልቡናዬን እንዲቀድስ ትለምኝው ዘንድ እማጸንሻለሁ። ንጽሕት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የሕይወት ቃል ከአንቺ ሰው ይሆን ዘንድ በሥጋ ከአንቺ ይወለድ ዘንድ የተገባሽ የመድኃኒት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ከአንቺ በመዋሐዱም እኛ ዳንን። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በእናታቸው ማሕፀን ሕፃናትን የሚስላቸው ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ሁሉን የፈጠረው በማሕፀንሽ የተቀረጸብሽ የብርሃን እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ። ረቂቅ ድንቅ ምሥጢርን ዓለምንም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውን እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ። በመንፈሳዊ ልደት ይወልደኝ ዘንድ ወደ እርሱ ዓለምና አዳኝ ወደ ሆነች ዕውቀት ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እለምንሻለሁ፣ አማጸንሻለሁ።

የሕይወት መገኛ የነገሥታት ንጉሥ የባለሥልጣናቱ ባለሥልጣን የአምላኮችን አምላክ በበረት ያስተኛሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። አዳኝ ስለሆነው ስለስምሽ እንዲረዳኝ ትለምኝልኝ ዘንድም ወደ አንቺ እለምናለሁ፤ እማልዳለሁም። በማየቱ አዳምንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ነጻ ያወጣውን በክንድሽ የታቀፍሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ።

በረቂቅ መመልከቱ እንዲመግበኝ ከሰይጣን መሰናክልም እንዲያድነኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤ እማጸንሽማለሁ። ዓለማትን ሁሉ ለሚመግበው ጡትሽን ያጠባሽው የመድኃኒት እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ፤ የሰማይ ኃይላት የሚመገቡትም ከእርሱ ነው። ነፍሴን በፈቃዱ ከጸጋው ይመግባት ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ።

እመቤቴ ድግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ እንደ ፍጹም ፈቃዱ እንዲመግበኝ በየጊዜው በየሰዐቱ አማላጅ ሁኚኝ። ይህችም ወደ እርሱ የምትለምኝውን ልመና የተመላች መጽሐፍ ናት ። የለመንሁትን ሁሉ እርሱ ያደርግልሻልና። ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። ሰላምን ስለሰጠሽ ስለ አብ ከአንቺ ስለተወለደው አንቺንም ስለተዋሐደው ከአንቺም ሰው ስለሆነው ስለወልድ፣ ስለቀደሰሽ፣ ከሦስቱ ቅዱስ ለአንዱ ማደሪያ ለመሆን እስከሚገባሽ ድረስ ስላነጻሽ ስለመንፈስቅዱስም እለምንሻለሁ። አገልጋይሽን ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ። ለዘለዓለሙ አሜን።

#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ
(Deacon Birhanu Admass የተረጎመው
@menefesawinet
​​✞ ​​ጽንሰተ ማርያም ድንግል ✞

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው
ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም

      ክፍል አንድ [፩]

በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ነሐሴ ሰባት ቀን ከሚዘከሩ በዓላት መካከል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅንሰት አንደኛው ነው፡፡ በዓሉን ለመዘከር ያህልም የእመቤታችንን የመፀነስ ታሪክ በአጭሩ እናስታውሳችሁ፤

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ አያቶች ቴክታ እና በጥሪቃ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለ ጠጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካኖች ነበሩ፡፡ ዘራቸውን ባለመተካታቸውና ሀብታቸውን የሚወርስ ልጅ ባለማግኘታቸውም ያዝኑ፣ ይተክዙ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በጥሪቃ ሚስቱ ቴክታን ጠርቶ "አንቺ መካን፤ እኔ መካን፡፡ይህ ዅሉ ገንዘብ ለማን ይኾናል?"አላት፡፡ ቴክታም "እግዚአብሔር ከእኔ ልጅ ባይሰጥህ ከሌላ ይሰጥህ ይኾናል ሌላ ሚስት አግብተህ ልጅ አትወልድምን?"አለችው፡፡ እርሱም "ይህንስ እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል "አላት፡፡ በዚህ አኳኋን እያዘኑ ሲኖሩ አንድ ቀን ነጭ እንቦሳ (ጥጃ) ከበረታቸው ስትወጣ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ልጅ ስትደርስና ስድስተኛዪቱ እንቦሳም ጨረቃን፣ ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ ራእይ አዩ፡፡ ራእያቸውን ለሕልም ተርጓሚ ሲነግሩም "የጨረቃዪቱ ትርጕም ከፍጡራን በላይ የምትኾን ልጅ እንደምታገኙ የሚያመለክት ነው የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጠልኝም፡፡እንደ ነቢይ፣ እንደ ንጉሥ ያለ ይኾናል፤›› አላቸው፡፡ እነርሱም ይህን ሲሰሙ "ጊዜ ይተርጕመው ብለው" ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ ለዘር ሊያበቃቸው ፈቅዷልና መካኗ ቴክታ ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ‹ሄኤሜን› አለቻት፡፡ ትርጕሙም "ስእለቴን (ምኞቴን) አገኘሁ" ማለት ነው፡፡ ሄኤሜንም ለዓቅመ ሔዋን ስትደርስ ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለዱ፡፡ ለሐናም ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ እነርሱም እንደ በጥሪቃና ቴክታ መካኖች ኾኑ፡፡

በእስራኤላውያን ባህል መካንነት የእርግማን ምልክት ተደርጎ ይቈጠር ነበርና ሐና እና ኢያቄም ብዙ ዘለፋና ሽሙጥ ይደርስባቸው ነበር፡፡ በአንድ ወቅት መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደስ ሔዱ፡፡ የዘመኑ ሊቀ ካህናት ሮቤል መካን መኾናቸውን ያውቅ ነበርና "እናንተማ "ብዙ ተባዙ"ብሎ እግዚአብሔር ለአዳም የነገረውን ቃል ያስቀረባችሁ ርጉማን አይደላችሁምን? እግዚአብሔር ቢጠላችሁ እንጂ ቢወዳችሁማ ልጅ ይሰጣችሁ አልነበረምን?" ብሎ መሥዋዕታቸውን ሳይቀበላቸው ቀረ፡፡

አንድም ከአዕሩገ እስራኤል (ከአረጋውያን እስራኤላውያን) የተወለዱ ሰዎች የሚመገቡትን ተረፈ መሥዋዕት እንዳይመገቡ ከለከላቸው፡፡ በዚህ እያዘኑ ሲመለሱ ከመንገድ ላይ ከልጆቻቸው ጋር የሚጫወቱ ርግቦችንና አብበው ያፈሩ ዕፀዋትን ሐና ተመለከተች፡፡ እርሷም "ርግቦችን በባሕርያቸው መራባት እንዲችሉ፤ ዕፀዋትንም አብበው እንዲያፈሩ የምታደርግ ጌታ እኔን ለምን ልጅ ነሳኸኝ?"ብላ አዘነች።

ከቤታቸው ሲደርሱም "እግዚአብሔር ልጅ ቢሰጠን ወንድ ከኾነ ለቤተ እግዚአብሔር ምንጣፍአንጣፊ፣ መጋረጃ ጋራጅ ኾኖ ሲያገለግል ይኑር፤ ሴት ብትኾንም መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ስታገለግል ትኑር" ብለው ተሳሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ሐምሌ ፴ ቀን ኹለቱም ራእይ አዩ፡፡
ሐና "በሕልሜ ፀምር (መጋረጃ) ሲያስታጥቁህ፤ በትርህ አፍርታ ፍጥረት ዅሉ ሲመገባት አየሁ" ብላ ያየቸውን ራእይ ለኢያቄም ነገረችው፡፡ ኢያቄምም "ጸዓዳ ርግብ ሰባቱን ሰማያትሰንጥቃ መጥታ በራስሽ ላይ ስታርፍ፣ በቀኝ ጆሮሽ ገብታ በማኅፀንሽ ስታድር አየሁ"ብሎ ያየውን ራእይ ለሐና ነገራት፡፡ ወደ ሕልም ተርጓሚ ሔደው ትርጕሙን ሲጠይቁም "ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ "አላቸው። እነርሱም "አንተ አልፈታኸውም፤ ጊዜ ይፍታው" ብለው ተመለሱ፡፡ በሌላ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ "ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሎ የሕልሙን ትርጕም ትክክለኛነት ነግሯቸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ብሉይ ኪዳን (ዓመተ ዓለም፣ ዓመተ ፍዳ) ተፈጽሞ የሐዲስ ኪዳን መግባት ሊበሠር፤ ጌታችንም ሊፀነስ ፲፬ ያህል ዓመታት ሲቀሩ በፈቃደ እግዚአብሔር ነሐሴ ፯ ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀንሳለች፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእናቷ በቅድስት ሐና ማኅፀን ሳለች ካደረገቻቸው ተአምራት መካከልም በርሴባ የምትባል ሴትን ዓይን ማብራቷ አንደኛው ነው፡፡ ይህቺ አንድ ዓይና ሴት (በርሴባ) "እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኘሽ መሰለኝ፤ ጡቶችሽ ጠቁረዋል፤ ከንፈሮችሽ አረዋል" ብላ የሐናን ማኅፀን በዳሰሰችበት እጇ ብታሻሸው ዓይኗ በርቶላታል፡፡

ይህንን አብነት አድርገውም እንደ እርሷ የሐናን ማኅፀን በመዳሰስ ብዙ ሕሙማን ከደዌያቸው ተፈውሰዋል፡፡ እንደዚሁም ሳምናስ የሚባል ልጅ በሞተ ጊዜ ሐና የአልጋውን ሸንኮር ይዛ ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ከሞት ተነሥቶ "ሰላም ለኪ ኦ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ፤ ሰማይና ምድርን የፈጠረው አምላክ አያቱ ሐና ሆይ! ሰላም ላንቺ ይኹን! ሰላምታ ይገባሻል!" በማለት ሕልም ተርጓሚ ያልፈታውን ራእይ በመተርጐም ከቅድስት ሐና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ ከእመቤታችን ደግሞ እውነተኛው ፀሐይ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንሚወለድ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡
@menefesawinet
​​ደብረ ታቦር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

           ክፍል አንድ [፩]

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊሊጶስ ቂሳርያ ለደቀመዛሙርቱ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቋቸው ነበር፡፡ እነርሱም "አንዳንዶች ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ቅዱስ ነውና ኤርሚያስ ነው ይሉሀል፤ አንዳንዶቹ ድንቅ የሆነ ልደትህንና የምታጠምቀውን አዲስ ጥምቀት አይተው መጥምቁ ዮሐንስ ነው ይሉሀል፤ ሌሎች ደግሞ ለአባቶችህ ቤት ያለህን ቅናት አይተው ኤልያስ ነው ይሉሃል" እያሉ መልሰውለት ነበር፡፡

ጌታችንም መልሶ፡- "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ብሎ ጠየቃቸው፡፡ የሐዋርያት አፈጉባዔ የሚሆን ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ" ብሎ መልሷል፡፡ ጌታም "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም (ምድራዊ መምህር) ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ" ብሎታል፡፡

ከዚህ በኋላ ጌታችን በኢየሩሳሌም ሊቃነ ካህናት፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ስለሚያደርሱበት መከራ ስለሚሞተው ሞት ይነግራቸው ጀመር፡፡ ሰይጣንም አስቀድሞ በቀዳሚት ሔዋን እንዳደረገው አሁንም በስምዖን ጴጥሮስ አንደበት ወዳጅ መስሎ "አይሆንም አይደረግም" በማለት መከራከር ጀመረ፡፡

ጌታችን ግን ጴጥሮስን አድርጎ ሰይጣንን ይገሥፀጸው ጀመር፡- "ጴጥሮስ ሆይ! የእኔ አመመጣጥ ለምን እንደሆነ አታስተውልምን? የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በቤተ ልሔም ተወልጄ ከሴቶች ለሚወለዱ ሕፃናት ሁሉ ደስታ እንደሆንኩላቸው አሁንም የእኔን እዚያ መውረድ እየተጠባበቁ የሚገኙትን ቅዱሳን ወደ ገነት እመልስ ዘንድ ወደ ሲዖል መሄድ አለብኝ፡፡ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን ይህን ሊያዩ ይመኛሉና፤ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ይናፍቃልና፡፡ ስለዚህ አያቸው ዘንድ መውረድ አለብኝ፤ እጎበኛቸው ዘንድ ልሞት ልሰቀል ይገባኛል፡፡ በእውነት ሰይጣን ካልሆነ በቀር የእኔን መሰቀል የሚቃወም የነፍሳትንም ነፃ መውጣት የማይናፍቅ ማን ነው? አንተ ጴጥሮስ! ይህን ሁሉ የምትለኝ ሰይጣን በአንተ ተመስሎ አንድም አንተው ራስህ ለእኔ ካለህ ፍቅር የተነሣ መሆኑን ብረዳም ጀሮህ ትንቢተ ነቢያትን ባይሰማ ይልቁንም ዓሣ ማጥመድን ብቻ ስለሚያውቅ ነውና ወግድ" አለው፡፡

ይህም በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ማለትም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ ክርስቶስ ባይሞት እንዴት ያለ ክብር እንደሚቀርባቸው ያሳያቸው ዘንድ ምስክርም እንዲሆኑ እነዚህን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ይዞ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖሱ መድኃኔዓለም ክብረ መንግሥቱን፣ ብርሃነ መለኮቱን ገልጠላቸው፡ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የምታከብረው ከዘጠኙ ዐበይት የጌታ በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡

በዚህ ዕለት ሕፃናት ጅራፋቸውን ገምደው እያስጮኹ ይጨፍራሉ፡፡ ይኸውም ጅራፍ ሲጮህ እንደሚያስደነግጥ ሁሉ ከጌታ ጋር የነበሩት ሦስቱ ደቀ መዛሙርትም አብ በደመና ሆኖ ሲናገር መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን የሚያስታውስ ነው፡፡

ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ ደቡብ በኵል 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ ከናዝሬት ከተማ በስተምሥራቅ፣ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ተራራው ከባሕር ወለል በላይ 572 ከፍታ አለው፡፡ ብዙ ሰዎች ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡

ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው?
መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ

ትንቢቱን ለመፈጸም ነው::
1⃣ ትንቢቱን ለመፈጸም
"ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ" እንዲል መዝ፹፰፥፲፪

2⃣ ምሳሌውን ለመፈጸም
ይህ ተራራ ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳ፬፥፮
ታሪኩም እንዲህ ነው፡፡ "የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር፡፡… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር" መሳ ፬፥፩-፫

ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ''ከፈተናው ጋር መውጫን መውጫን ደግሞ ያደርግላችኋል'' የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው ፩ቆሮ ፲፥፲፫

እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው፡፡

ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡

እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ "ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ" ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ፤ ጦርነቱም ሳይጀመር አለቀ፡፡

ምክንያቱም "እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ" መሳ፬፥፲፭

እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ፡፡ "በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ" ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር።
ዕብ ፲፩፥፴፪-፴፬

ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን (የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ ከዚህም በመነሣት ነው "በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው" የሚባለው ፡፡

ለምን ሶስቱን ሐዋርያት ይዞ ወጣ?

  ክፍል ሁለት ይቀጥላል.....
@menefesawinet
Forwarded from ተዋህዶ
የበገና መዝሙሮችና ቁጥሮቹን እንዴት ላግኝ?🤔
በገና ምንድነው?🤔
አገልግሎቱስ?🤔
ከበገና ደርዳሪ ምን ይጠበቃል?🤔
መንፈሳዊ ጥቅሙስ ምንድነው ?🤔
ሁሉኑም በአንድ ያገኛሉ ይቀላቀሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ነሐሴ ፲፮ ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለእመቤታችን
#ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የትንሳኤና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ #🌷ዕርገተ_ድንግል_ማርያም🌷 +"+

=>ይሕች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት:: ምክንያቱም
የድንግል ማርያም ሥጋዋ ተነስቶ ዐርጐባታልና:: ድንግል
እመቤታችን ተነሳች: ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ:
እንደ ውሃ ፈሶ: ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም::
ጥንቱን በአምላክ ልቡና ታስቦ: ሁዋላም ትንቢት
ተነግሮለት ነው::

¤ታሪኩ: ነገሩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም
በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት
#እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::

¤ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና
መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ
"እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500
ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ #ንጽሕት_ዘር
ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
¤ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና
ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን
ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም
መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ
እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::

+"+ የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ +"+

*ከአዳም በሴት
*ከያሬድ በሔኖክ
*ከኖኅ በሴም
*ከአብርሃም በይስሐቅ
*ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
*ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ
ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::

¤ከሌዊ ደግሞ #በአሮን: #አልዓዛር: #ፊንሐስ:
#ቴክታና_በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::

¤አባታችን #አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት
#ወላዲተ_አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት
ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ
#ኢያቄም_ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7)
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ::
(#ቅዱስ_ቴዎዶጦስ_ዘዕንቆራ)

¤ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ
#ቤተ_መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12
ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና
እያገለገለች: እርሷን ደግሞ #መላእክተ_ብርሃን
እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ: ጽዋዕ ሰማያዊ
እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ ጻድቅ
#አረጋዊ_ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::

¤በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና
ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው::
ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር:
ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ::
(#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም #ለብሐዊ)

¤ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ:
እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14)
"#ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በናዝሬት ገሊላ ለ2
ዓመታት ቆዩ::

¤አርዌ ሔሮድስ "እገድላለሁ" ብሎ በተሳበት ወቅትም
ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም:
በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ
#ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር
ሲሆነው: ለርሷ ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር
ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::

¤በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን
እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች::

እርሷ 45 ዓመት: ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን
ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3
ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም
እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::

¤የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም
የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን
ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ
በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች::
ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::

¤ከልጇ #ዕርገት በሁዋላ #በጽርሐ_ጽዮን ሐዋርያትን
ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮን
ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች::
በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ:
ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና:
ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::

¤ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን #መድኃኒታችን
አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን
ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም
በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት
ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ:
ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ:
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል::

¤ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም
እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው
ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ:
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ:
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::

¤በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ
#ቅዱስ_ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ
እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር
አኑሯታል::

በዚያም #መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት
ቆይታለች::

¤#ቅዱስ_ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን
ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ
ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል
ማርያምን #ንጹሕ_ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም
#በጌሴማኒ ቀብረዋታል::

¤በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ #ትንሳኤ
ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ
#ቅዱስ_ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም
መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ
1 ቀን ሱባኤ ገቡ::

¤ለ2 ሳምንታት ቆይተው: በዚህች ቀንም ሁሉንም ወደ
ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ
የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ
ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን
ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ #ደብረ_ዘይት
ተመልሰዋል::

=>ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና #እመቤታችን:
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን:
ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
@menefesawinet
Forwarded from መዝሙር ግጥሞች ቤት (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ከ አየር ጤናም መነሻ አለ
#ከአያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል
# ከ አያት አደባባይ
# የካ ሚካኤል ና መገናኛ
#አዲሱ ገቢያ

0953125078 እደዉሉ
@DA121922 አናግሩኝ
Forwarded from Quality button
የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች ትወስድለት የነበረችው ሴት ማን ትባላለች?
+ ጊዮርጊስ ሆይ ከእኛ ወገን ነህን? +

ወደ አድዋ ከዘመተው ሕዝብ አብዛኛው ባዶ እግሩን ነበር:: ዳዊት ጎልያድን ሊዋጋ ሲወጣ ከያዛት በትር በቀር አብዛኛው ሰው መሣሪያ አልታጠቀም:: አብዛኛው ዘማች ባዶ እጁን የዘመተው ሁለት ነገር አስቦ ነው:: መሣሪያ ባይኖረውም በውጊያው መካከል ከጠላት ጦር መሣሪያ ነጥቄ እዋጋለሁ አለዚያም ከሚወድቁት ላይ መሣሪያ አንሥቼ እዋጋለሁ ብሎ ነበር:: በውጊያው ታንክ በጎራዴ እስከመማረክ ያደረሳቸውም ይህ ቆራጥነታቸው ነበር::
ለመንፈሳዊ ጥንካሬያቸው ደግሞ ምሥጢሩ አብራ የዘመተችው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት እና ንጉሡ በድንግል ማርያም ስም ምለው የሠጡት አደራ ነበር:: ለተገፉ የሚቆመው ሰማዕቱ ጊዮርጊስም በግፍ ባሕር አቁዋርጠው በደሃ ሕዝብ ላይ እሳት ከሚያዘንቡት ከአባቱ ዘመዶች ከሮማዊያን ጋር ሳይሆን እንደ ዳዊት በትር ይዘው በእግዚአብሔር ስም ከወጡት ባለማተቦች ጋር በምልጃው ተሰልፎ ዋለ::
በዚያች ዕለት አንድ ጣሊያናዊ ቅዱስ ጊዮርጊስን አግኝቶ ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን እንደጠየቀው "ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? " ብሎ ቢጠይቀው ኖሮ "እኔ አሁን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ ይልቅስ የቆምክባት መሬት ኢትዮጵያ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" ባለው ነበር::

የዐድዋ ዘማቾች ጾመኞች ነበሩ:: እንግሊዝም ጣሊያንም ሰይጣን ይመስል ኢትዮጵያን የተዋጉአት በዐቢይ ጾም ነበር:: "ወድቀህ ብትሰግድልኝ መንገድና ፎቅ እሰራልሃለሁ" ያለንን ጣሊያን አባቶቻችን "ሒድ አንተ ጣሊያን የራስህን እንጂ የእኔን አታስብምና" ብለው ድል ነሡት::
ዘማቾቹ የምግብ እጥረት ቢኖርም እንኩዋን ጾሙን ትተን ካልበላን አላሉም:: ድንገት መሞቴ አይቀር ብበላ ይሻለኛል ሳይሉ ተዋግተው ድል ተቀዳጁ:: እኛ በሰላም ጊዜ የምንተወውን ጾም እነርሱ በጦርነት ላይም ሆነው አልተዉትም:: በዚያ ድል  ሀገሪቱ ለዐርባ ዓመት ከጦርነት ስታርፍ ለዕድሜ ዘመንዋ ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዐረፈች::
ቅኝ ግዛት ብንገዛ ኖሮ ደሃ አንሆንም ነበር የሚል ሰው አይጠፋም:: ይህንን አሳብ የብዙ አፍሪካውያን ሀገራት ጆሮ አይስማው:: ዛሬ ነጻ ከወጡም በኁዋላ በባርነት ሕሊና የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው::
ብዙ በፈረንሳይ የተገዙ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዛሬም ድረስ በአደራ አስተዳደር በፈረንሳይ በእጅ አዙር ይተዳደራሉ:: በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ቅኝ ገዢዎቻቸውን ተወካይ ሁነኝ ብለው የሚልኩ ሀገራት አሉ::
ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት ጥቁሮች ሊስተናገዱ በተሰለፉበት ሱፐር ማርኬት አንድ ነጭ ከመጣ ሰልፍ ሳይይዝ ቅድሚያ ይስተናገዳል:: (በዓይኔ ያየሁት ነው)
ዛሬም ድረስ ብዙ አፍሪካዊያን ጥቁር በአስተሳሰብ ከነጭ በታች ነው ብለው ያምናሉ:: በዜኖ ፎቢያ የገዛ ወንድሞቻቸው አፍሪካውያንን የሚያሰቃዩ ደቡብ አፍሪካውያን ነጭ ሰፈር ግን ዝር አይሉም:: ሂሳብ ስታሰላ ሲያዩህ እንኩዋን አንተ ጥቁር ሆነህ እንዴት ያለ ካልኩሌተር መደመር ቻልክ የሚሉ ሰዎች ተፈጥረዋል::
በአውሮፓ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ስኬታማ የሆኑት ጥቁሮች እንኩዋን የቤተሰብ ስማቸው ላይ አያቶቻቸውን በባርነት የገዛው ነጭ ገዥ ስም አብሮ ስለሚለጠፍ የዕድሜ ልክ የበታችነት ይሰማቸዋል:: አባቶቻችን ከብዙ ጣጣ አድነውናል አሁን ራሳችን የምንፈጥረውን ችግር ቢያዩ ለማመን የሚቸገሩ የሚሆኑትም ዘር ሳይለዩ አብረው የተዋደቁት ጀግኖች ናቸው:: ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ቤሩታዊት ኢትዮጵያን ከዘረኝነትና ጥላቻ ደራጎን ይታደጋት ዘንድ የምንማጸንበት ጊዜ ነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 23 2012 ዓ ም
ወላይታ ሶዶ ኢትዮጵያ
ፎቶዎች :- ሊባኖስ ቤሩታዊትዋን ባዳነበት ሥፍራ እና ልዳ በቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ሥፍራ የተነሣሁት:: እናንተንም መቃብሩን ለመሣለም ያብቃችሁ::
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
https://www.tgoop.com/menefesawinet
የመነኮሳት መመኪያ፣ የምእመናን ሁሉ አባት፣ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ሐዲስ ሐዋርያ፣ አጋንንትን የሚያሳዱ ጣዖታትን የሚያርዱ፣ እልፍ አእላፋትን በወንጌል መረብ የሚያጠምዱ፣ በምድር ተወልደው እንደ መልአክ የኖሩ ጻድቁ አባታችን አባ ተክለ ሃይማኖት ያረፉበት እለት ዛሬ ነው።

እግዚአብሔር ለወንጌል አገልግሎት የቤታቸውን በር እንደ ተከፈተ ጥለው የወጡትን አባት፣ የገነትን ደጅ ወለል አድርጎ ከፍቶ በታላቅ ክብር የተቀበለበት እለት ነው።

እንኳን አደረሳችሁ!

                           አባ ጸሊ በእንቲአነ!

@menefesawinet
የ2017 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 5500+2017= 7517 ይህ ዓመተ ዓለም ይባላል።

🔷👉 የ2017 ዓ/ም ወንጌላዊውን ለማወቅ :-
ዓመተ ዓለሙን (7517) ለ4ቱ ወንጌላውያን በማከፈል
       7517፥ 4=1879 ደርሷቸው 1 ይቀራል።
     ይህ ማለት 7517 - 4 × 1879 = 1 ይሆናል።
              1879 መጠነ ራብዒት ይባላል።

🔴👉 ልብ በሉ ቀሪው 1 ከሆነ ዘመኑ ማቴዎስ፣ 2 ከሆነ ማርቆስ ፣ 3 ከሆነ ሉቃስ ፣ ያለምንም ቀሪ ከተካፈለ ዘመኑ ዮሐንስ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ በ2017 ዓ/ም ቀሪው 1 ስለሆነ ወንጌላዊው ማቴዎስ ይሆናል ማለት ነው።

🔷👉 የመስከረም መባቻ የሚውልበትን ዕለት ለማወቅ፦

👉 ዓመተ ዓለም ሲደመር መጠነ ራብዒት  
  7517+1879= 9396  ይህ ለ7ቱ ዕለታት ሲካፈል
       9396 ፥ 7 = 1342 ደርሶ ቀሪው 2 ነው።
    ይህ ማለት 9396 - 7 × 1342 = 2 ይሆናል።

🔴👉 ልብ በሉ ሲካፈል ያለምንም ቀሪ በዜሮ ከተካፈለ ቅዱስ ዮሐንስ ሰኞ ዕለት ይውላል፣ ቀሪው1 ከሆነ ማክሰኞ ፣ 2 ከሆነ ረቡዕ ፣ 3 ከሆነ ሐሙስ ፣ 4 ከሆነ ዓርብ ፣ 5 ከሆነ ቅዳሜ ፣ 6 ከሆነ እሑድ ቀን ይውላል።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም ቀሪው 2 ስለሆነ  የመስከረም መባቻ ረቡዕ ዕለት ይውላል ማለት ነው።

🔴👉 የዘመኑን ወንበር ለማግኘት፦

👉 ዓመተ ዓለሙን ለንዑስ ቀመሩ ማካፈል
        7517፥19 =395 ደርሶ 12 ይተርፋል።
            1 ለዘመን ትተን  11 ይቀራል።
🔷👉  ስለዚህ የ2017 ዓ/ም ወንበሩ 11 ይሆናል ማለት ነው።

🔴👉 የዘመኑን አበቅቴን ለማወቅ ፦

👉 365 -354= 11ይህ ጥንተ አበቅቴ ይባላል።
  ስለዚህ አበቅቴን ለማወቅ ፣ የዘመኑ ወንበር ሲባዛ   
  11x11=121 በአራት 30 ስንገድፍ  1 ይቀራል።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም አበቅቴ 1 ይሆናል ማለት ነው።

🔴👉 መጥቅዕን ለማወቅ ፦

👉 መጥቅዕን  ለማግኘት  ወንበሩን በንዑስ ቀመር አባዝቶ በ30 ገድፎ የሚገኘው ነው።
     11x19 = 209 በ6 ሠላሳ ሲገደፍ 29 ይቀራል።

🔴👉 ልብ በሉ መጥቅዕ ከ14  በላይ ከሆነ በመስከረም ፣ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ወር ላይ ይውላል። 14 ራሱ መጥቅዕ አይሆንም።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም መጥቅዕ 29 ይሆናል ማለት ነው።
እናም የ2017 ዓ/ም ከ14 በላይ 29 ስለሆነ በመስከረም ይውላል።

🔴👉 ልብ በሉ አበቅቴና መጥቅዕ ተደምሮ ከ30 አይበልጡም ፣ከ30 አያንሱም ሁልጊዜ 30 ይሆናሉ እንጂ።

🔴👉 ተውሳክ፦

👉 ተውሳክ ማለት፦ ጭማሬ ማለት ነው። እሱም በዓላቱንና አጽዋማቱን ለማወቅ ከመጥቅዕ ጋር እየተጨመረ የሚቆጠር ነውና። 3 ዓይነት ተውሳኮች አሉ። እነሱም ፦ የዕለታት ፣ የበዓላት እና የአጽዋማት ተውሳኮች ናቸው።

🔴👉 የዕለታት ተውሳኮችን ለማግኘት መጥቅዕ ከዋለበት ሳኒታ(ማግሥት) ጀምረን ነነዌ እስከ ዋለችበት ቀን ስንቆጥር ከ122-128 ቀናት ናቸው የሚሆኑት።

🔷👉 ከመጥቅዕ ማግሥት ነነዌ እስከ ዋለችበት ቀን እየቆጠሩ 125ቱን በ30 እየገደፉ ቀሪውን በመያዝ የዕለት ተውሳክ ይገኛል።
መጥቅዕ ከዕለታት ተውሳክ ጋር ተደምሮ ጾመ ነነዌን ያስገኛል።

የዕለት ተውሳክ በቅዳሜ ይጀምራል።
1. የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው
2. የእሑድ ተውሳክ 7 ነው።
3. የሰኞ ተውሳክ 6 ነው።
4. የማክሰኞ ተውሳክ 5 ነው።
5. የረቡዕ ተውሳክ 4 ነው።
6. የሐሙስ ተውሳክ 3 ነው።
7. የዓርብ ተውሳክ 2 ነው።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም የነነዌ ጾም መቼ እንደሚገባ ለማወቅ ከዚህ በታች ያለውን ፎርሙላ ይመልከቱ።

👉 በ2017 ዓ/ም መጥቅዕ የዋለው መስከረም 29 ቀን ነው። መስከረም 29 የሚውልበት ዕለት ረቡዕ ነው። የረቡዕ ተውሳክ 4 ነው። ስለሆነም 29+4=33 በአንድ 30 ሲገደፍ  3 ይቀራል።

🔷👉 ስለዚህ በ2017 ዓ/ም ጾመ ነነዌ  የካቲት 3 ቀን ትገባለች ማለት ነው። እሷም << መባጃ ሐመር>> ትባላለች። ከዚህ በኋላ መባጃ ሐመሩን ወይም የነነዌ የገባችበትን ቀን ከአጽዋማቱና በዓላቱ ጋር እየደመሩ ከ30 ያለፈውን በ30 እየገደፉ ቀሪውን የበዓሉን ወይም የአጽዋማቱን መግቢያ ማግኘት ይቻላል።

1. የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ነው። 14+3=17 ስለዚህ ዐቢይ ጾም የካቲት 17 ይገባል ማለት ነው።
2. የደብረ ዘይት ተውሳክ 11 ነው። 11+3=14 ። ስለዚህ መጋቢት 14 ደብረ ዘይት ይሆናል ማለት ነው።
3. የሆሣዕና ተውሳክ 2ነው ። 2+3=5።
ስለዚህ ሚያዝያ 5 ሆሣዕና ይሆናል ማለት ነው።
4. የስቅለት ተውሳክ 7 ነው። 7+3=10።
ስለዚህ ሚያዝያ 10 ስቅለት ይውላል ማለት ነው።
5. የትንሣኤ ተውሳክ 9 ነው ። 9+3=12 ። ስለዚህ ሚያዝያ 12 ትንሣኤ ይውላል ማለት ነው።
6. የርክበ ካህናት ተውሳክ 3 ነው። 3+3=6። ስለዚህ ርክበ ካህናት ግንቦት 6 ይውላል ማለት ነው።
7. የዕርገት ተውሳክ 18 ነው። 18+3=21። ስለዚህ ዕርገት ግንቦት 21 ቀን ይውላል ማለት ነው።
8. የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28 ነው። 28+3=31። ስለዚህ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 1ቀን ይውላል ማለት ነው።
9. የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ 29 ነው።
29+3=32 በ30 ሲገደፍ =2 ። ስለዚህ
ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 2 ይውላል ማለት ነው።
10. የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ነው። 1+3=4። ስለዚህ ጾመ ድኅነት ሰኔ 4 ቀን ይገባል ማለት ነው።
https:www.tgoop.com//menefesawinet
ጷግሜን_ለምን_እንጾማለን?

ጷግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

በመጠመቃችን_የምናገኘው_ጥቅም_ምንድን_ነው?

ጷግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል፡፡

#ጷግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያት_ይከፈታሉ ጸሎታችን በሙሉ ያርጋል፡፡

/ዩ ትዩብ ላይ የለቀኩትን ትምህርት በጽሑፍ ቃል በቃል አቅርቤላችኃለሁ/

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደሚታወቀው ወርኃ ጳግሜ፤ ኢትዮጲያን ብቸኛዋ ባለ አሥራ ሦስት ወራት ሀገር ያደርገች ልዩ ወር ናት፡፡ ታዲያ ይህችህ በሦስቱ ወንጌላውያን አምስት ፣ በዘመነ ዮሐንስ በአራት ዓመት ስድስት ቀን የምትሆነው ጳግሜ፣ ብዙ ምስጢር እና ልዩ ጥቅም የላት ወር ናት፡፡

ጳግሜን_ለምን_እንጾማለን?

የጳግሜ ወር በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የዓለም ፍጻሜ መታሰብያ ወር ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ ጳግሜ የዓመታት መሸጋገሪያ፤ ጨለማው የክረምት ወቅት፤ ወደ ማብቂያው እና የሚያልፍበት፤ እንደ ሆነ ሁሉ፤

ዳግም ምጽዓትም ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፤ ከጊዜያው ወደ ዘላለማዊ መሻጋገሪያ በመሆኑ ጳግሜ የእለተ ምጻት ምሳሌ የሆነችው፡፡ በዚህም ምክንያት የኦርቶዶክስ አማኞች የጳግሜን ወር በሱባኤ በጾም በጸሎት ያሳልፋሉ፡፡ በገዳም ያሉ አባቶች ጳግሜን በዝግ ሱባኤ ያሳልፋሉ፡፡

በእግርጥ ጳግሜ ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ባትካተትም፤ ጳግሜን በግዴታ ሳይሆን በውዴታ ብንጾም የበረታን ሱባኤ ብንይዝባት፣ የቻልን በታቅቦ ብናሳልፋት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡

አንደኛ በፈቃዳችን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በሱባኤ ብናሳልፍ ጸጋና በረከት ያሰጠናል፡፡ ሁለተኛው ጳግሜ የአዲስ ዓመት መቀበያ የዋዜማ ቀናት በመሆኗ፤ አዲሱን ዓመት በጾም፣ በጸሎት በሱባኤ ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት፣ የረድኤት ይሆንልናል፡፡

አዲሱን ዓመት በተለይም በዋዜማው በመዝናናት፣ በመጨፈር፣ በመጠጣት እና በመዘሞት ከምንቀበል፤ በጸሎት ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት ዓመት፣ ያሰብነው ያቀድነው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሳካበት ይሆናል፡፡

ቅድም እንዳልኩት የገዳም አባቶቻችን የጳግሜን ወር፤ መንፈሳዊ ጥቅም ስለሚያውቁ፤ በፈቃዳቸው በታላቅ ሱባኤ ሆነው ስለ ሀገር፣ ስለ መጪው አዲስ ዓመት መልካምነት ፈጣሪን ይማጸኑበታል፡፡ እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን እና፣ እነሱ የሄዱበትን መንገድ ተከትለን፤ እንደ እነሱ ልንጠቀም ያስፈልጋልና፤ ወርኃ ጳግሜን በጾም በጸሎት እና በሱባኤ ብናሳልፍ እንጠቀማለን፡፡

በተለይ በአሁኑ ጊዜ እኛም፣ ሀገራችንም ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንም የገጠመን ፈተና፣ እጅጉን ከባድ ነውና እግዚአብሔር እንዲታረቀን፣ ገጸ ምህረቱን እንዲመልስልን፣ ወረርሽኙን እንዲያጠፋልን፣ ለቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንና ለሀገራችን ጽኑ ሰላም እና አንድነት እንዲሰጥልን ወርኃ ጳግሜን እንደ በፊቱ በመብላት በመጠጣት ሳይሆን በጾም በጸሎት ብናሳልፍ ጥቅሙ ለእኛው ነው፡፡

ጳግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

እንደሚታወቀው ብዙዎቻችን ወርኃ ጳግሜን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜን የምንጠመቅበት ዋናው ምክንያት ከሊቀ መልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር የተያያዘ ነው፡፡  

በዚህ በጳግሜ ወር በዓለም ላይ ያሉ ውቅያኖሶች፣ ባህሮች፣ ወንዞች፣ ኩሬዎች ጸበሎች በአጠቃላይ ውሃዎች ሰማይ ተከፍቶ፣ በመላክእት የሚባረኩበት ስለሆነ፤ ጳግሜን የቻልን ጸበል ቦታ ሄደን፣ ወይም በአከባቢያችን ጸበል ካለ እዛም ሄደን፤ መሄድ ባይመቸን፣ ቤታችን ውስጥ ባለው ውኃ ብንጠመቅ እንባረክበታለን፣ ከበሽታችንም እንድንበታለን፡፡

በጳግሜ ጸበል፣ እንኳን የሰው በሽታ፤ በሽታ ያለው እህል፣ በሽታው ይለቀዋል፡፡  ገበሬው ከጳግሜ ወዲያ ነው የሚጠፋውንና የማይጠፋውን እህል የሚለየው፤ በተለይ ዘንጋዳ ጳግሜ ላይ ነው በደንብ የሚያስታውቀው፡፡

በአባባልም ‹‹ዘንጋዳ እና ቡዳ ከመስከረም ወዲያ›› ነው የሚያስታውቀው ይባላል፡፡ የሚገርመው አባቶቻችን ጳግሜ ሦስት ሌሊት ስድስት ሰዓት በተለይ ፏፏቴ ያለው ወንዝ፤ ውሃው ሲቆም ያዩታል፡፡

ቀድሞ አባቶቻን ይህንን ተአምር ለማየት ጳግሜ ሦስት ሌሊት በተለይ ፏፏቴ ያለበት፣ ትልቅ ወንዝ ዳር ሄደው ያድሩ ነበር፡፡ ውሃው ቀጥ ብሎ ሲቆም ሰማይ ሲከፈት ያዩ ነበር፡፡ ጳግሜን በተለይም ጳግሜ ሦስት፣ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በአሉ ስለሆነ፤

በዚህ ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ውሆችን የሚባርክበት፤ እና ለሰው ልጆች በፈጣሪው ጸጋ፤ ድህነት እና ፈውስ የሚያሰጥበት ቀን ስለሆነ ብንጠመቅ ከበሽታችን እንድናለን፡፡

በመጸሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል በምዕራ 5 ቁጥር 4 ላይ ‹‹አንዳንድ ጊዜ  የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ፣ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኃላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር›› ይላል፡፡

የጌታ መልአክ ‹‹ውኃውን ያናውጥ ነበር›› የተባለው፤ ከሰማይ ወርዶ ውኃውን ይባርከው ነበር ለማለት ነው፡፡ ውኃውም የሚናወጠው የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ሲባርከውና እና በመጠመቂያው፣ ለፈውስ ደጅ የሚጠኑት፣ ህሙማን ውሃው በመልአኩ መባረኩን የሚያውቁት ውኃው ሲናወጥ ነው፡፡

ዛሬም እንደ ቀድሞ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል፤ በዓለም ላይ ያሉትን ውሃዎች ሁሉ ስለሚባርካቸው፤ ብንጠመቅባቸው እንፈወሳለን፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቅዱሳን መላእክትም ውኃውን ይባርኩታል፡፡

ጳግሜ ሦስት ይህ ብቻ አይደለም ሊቀ መልአኩ ያስለመደን ነገር አለ፡፡ ይህም ሁል ጊዜ ጳግሜ ሦስት ሌሊት፣ ጠዋት፣ ከሰዓት አልያም ማምሻ ላይ ይዘንባል፡፡ ይህ ከሰማይ የሆነ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ጸበል ነው፡፡

በልጅነታችን ጳግሜ ሦስትን ‹‹ሩፋኤል አሳድገኝ›› እያልን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜ ሦስት በዘነበው ውኃ መጠመቅ ትልቅ መታደል እና ፈውስ ነው፡፡ በደዌ ይሰቃይ የነበረው ኢዮብም በዚህ ሳምንት ነው ተጠምቆ ነው የዳነው፡፡

የሚገርማችሁ በዚህ በከተማ ብዙም ስለማይታወቅ ነው እንጂ፤ በገጠር እና በክፍለ ሀገር የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነው ዝናብ በእቃ ይቀዳና ይቀመጣል፡፡ በተቀዳው ጸበል ቦሃቃው ይረጭበታል፣ በውሃው እህሉ ይቦካበታል፣ ቤቱ ደጁ ይረጭበታል፡፡

ይህም የሚሆነው የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነበው ውኃ የሰላቢ መንፈስን ስለሚያርቅ ነው፡፡ የሰላቢ መንፈስ ከቤታችን የእህል በረከት የሚያሳጣ፣ ለአንድ ወር ያሰብነውን ለሳምንት የማያዳርስ፣ ለዓመት ያልነው በሦስት ወር እንዲያልቅ የሚያደርግ፤ ክፉ መንፈስ ስላለ ይህን ያርቅልናል፣ በጸበሉ በረከት እህል አስቤዛውን ያበረክትልናል፡፡

እንደምታውቁት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ በመጀመሪያዋ እለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክት ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው

ቅዱስ ሩፋኤል ራማ ላይ ነው ከነ ሠራዊቱ ያረፈው ወይም የከተመው፡፡ በራማም መናብርት ተብለው ለሚጠሩት አሥሩ ነገድ አለቃ ወይም መሪ ሆኖ በእግዚአብሔር ተሹሟል፡፡ በኃላም መጋብያን በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ተሹሟል፡፡

ስለዚህ ጳግሜ ሦስት የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሲመት ወይም የሹመት በዓሉ ነው፡፡

ይህንንም እራሱ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በመጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 12 ቁጥር 15 ላይ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› በማለት ተናግሯል፡፡
የስሙንም ትርጉም ስንመለከት ‹‹ሩፋ›› ማለት ሐኪም ማለት ነው፡፡ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለትነው፡፡ ሌላው መልአከ ሰላም ወጥዒና ወይም የሰላም እና የጤና መልአክ ይባላል፡፡

የሰው ልጆችን ከተያዙበት ከተለያዩ በሽታውች በጸሎቱ፣ በአማልጅነቱ እንዲፈውስ ስልጣን እና ጸጋ የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው፡፡
ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለት መሆኑን ነብየ

እግዚአብሔር ቅዱስ ሄኖክ በመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 10 ቁጥር 13 ላይ ‹‹በበሽታ ሁሉ ላይ፣ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ፤ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› እንዲሁም እዛው መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 6 ቁጥር 3 ላይ

‹‹በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መልእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው››  በማለት እግዚአብሔር ለቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የወጣውን፤ ቁስል እና ደዌ፤ ይፈውስ ዘንድ ስልጣን እንደሰጠው፣ ሐኪም እንዳደረገው ነግሮናል፡፡

እንዲሁም ፈታሄ ማሕፀን ይባላል፡፡ እንኳን በምጥ የተያዙትን ሴቶች፣ እናቶች፤ ቀርቶ እንስሳት እንኳን ምጥ ሲፀናባቸው፣ ስሙን ከጠሩት ይፈታቸዋል፡፡ ይህ መልአክ በተለይ ለሴቶች እጅጉን ረዳታቸው ነው፡፡ ከፀነሱበት ጊዜ አንስቶ እስኪወልዱ አይለያቸውም፡፡

በተለይ በእርግዝናቸው ጊዜ ስሙን እየጠሩ፣ መልኩን እየጸለዩ፣ ጸበሉን እየጠጡ እየተዳበሱ፣ ከተማጸኑት ጭንቀታቸውን ያቀላል፣ በሰላም ያዋልዳቸዋል፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይሁንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ስለ ቅዱስ ሩፋኤል እንዲያሳውቃቸው፣ ክብሩን እንዲገልጽላቸው ጠየቁት፡፡ ጌታም ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሩፋኤልን እንደሚመጡ አዘዛቸው፡፡ እነሱም መጡ፡፡

ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ስለ ራሳቸው ከተናገሩ በኃላ ጌታም ቅዱስ ሩፋኤልን ‹‹ክብርህን ንገራው›› አለው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምስጢር ነገራቸው፡፡

በተለይም ስሙን ለሚጠሩ፣ መታሰብያውን ለሚያደርጉ፣ በጸሎቱ ለሚማጸኑ፣ እንደማይለያቸው፣ እንደሚረዳቸው፣ ክብር እንደሚያሰጣቸው ለሐዋርያት ነግሯቸው ወደ ሰማያት አርጓል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያትም በወቅቱ ወንጌልን ሲያስተምሩ፣ ስለ ቅዱስ ሩፋኤል ክብር እና በእሱ የሚገኘውን መልአካዊ እርዳታ፣ ለምዕመናኑ በደንብ አስተምረዋል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ልቦናን ደስ የሚያሰኝ፤ ባለ መድኃኒት ፈዋሽ፤ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው፤ በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ፤ የሰውንም ይሁን እንስሳን ማሕፀን የሚፈታ፤ አዋላጅ፣ ምጥን የሚያቀል፣ ታላቅ መልአክ ነውና እንጠቀምበት፡፡

ስለዚህ የቅዱስ ሩፋኤል ቀን የዘነበውን ዝናብ በዕቃ ቀድታችሁ አስቀምጡ፡፡ ያንንም ጸበል ቤታችሁን፣ ደጃችሁን፣ እንዲሁም የሥራ ቦታችሁን እርጩበት፣ እየቆጠባችሁ እህል ስታቦኩ አብኩበት ጠጡት ተጠመቁበት፡፡ ብዙ በረከት እና ፈውስ ታገኙበታላችሁ፡፡

እህል እና ገንዘብ የሚሰልብባችሁን የሰላቢ መንፈስ ያርቅላችኃል፡፡
ውጭ ሀገር ያላችው እህት ወንድሞቼ ጸበል መጠመቅ ስለማይመቻችሁ፤ ውኃ አቅርባችሁ፣ ያስለመዳችሁትን ጸሎት ውሃው ላይ ጸልያችሁ ‹‹አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል›› ባርክልኝ ብላችሁ ቤት ውስጥ ተጠመቁ ጠጡት፡፡

ጳግሜን መጠመቅ ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ የነበረ እና በየአመቱ ጳግሜን መጠመቅ የሚናፈቅ ጊዜ ስለሆነ ተጠቀሙበት፡፡ በዚሁ አጋጣሚ እኛም እንጦጦ ማርያም ጳግሜን የጸበል አገልግሎት ስለምንሰጥ መጥታችሁ መጠመቅ ትችላላችሁ፡፡

#ጳግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያትይከፈታሉ_ጸሎታችን_በሙሉ_ያርጋል፡፡

ጳግሜ ሦስት ርህወተ ሰማይ ይባላል፡፡ ርኅወተ ሰማይ ማለት የሰማይ መከፈት ማለት ነው፡፡ ይህም የሰማይ መስኮቶች ወይም ደጆች የሚከፈቱበት እለት ነው፡፡ ርኅወተ ሰማይ ወይም የሰማይ መከፈት ሲባል፤ በሰማይ መከፈት እና መዘጋት ኖሮበት ሳይሆን፤

ቅዱሳን መላእክት የሰውን ልጆች ጸሎት፣ ልመና፣ ያለ ከልካይ፤ ወደ እግዚብሔር የሚያሳርጉበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ እንዲሁም ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገበ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ ነው ርኅወተ ሰማይ የተባለው፡፡

በእርግጥ በንስሐ ሆኖ ለሚጸልይ ሰው ለእርሱ ሁሌም የሰማይ ደጅ የተከፈተ ነው፡፡ ከዓመት ተለይታ ጳግሜ ሦስት የሰማይ መስኮቶች፤ ወይም ደጆች በሙሉ ተከፍተው፣ የምዕመናን ጸሎት በተለየ ሁኔታ የሚያርግበት ጊዜ እንደ ሆነ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስትያንም ይነግሩናል፡፡

ስለዚህ በዚህም ቀን ማለትም ጳግሜ ሦስት ያስለመድናቸውን ጸሎቶች፤ አንዳንዶቻችንም ያቋረጥናቸውን ጸሎቶች፤ በርትተን ብንጸል ቅድመ እግዚብሔር ይደርሳል፡፡

በዚህችም ቀን የጸለይነውን ጸሎቶች፤ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅዱሳን መላእክት ቅድመ እግዚብአብሔር ያሳርጉልናል፡፡ በዚህችም እለት የእግዚአብሔር ምህረት እና ቸርነት ለሰው ልጆች የሚወርድበት ታላቅ እለት ነው፡፡

አባቶቻችን እንደሚነግሩን ከሆነ፤ ጳግሜ ሦስት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ፤ ያስለመዱትንና ሌሎችንም ጸሎቶች ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ እነሱ ማድረግ ባንችል፤ የበረታን ሌሊት ስድስት ሰዓት፤ የቻልን ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስተን ጸሎት ልንጸልይ ይገባናል፡፡

ጳግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደምታውቁት ያለንበት ጊዜ አጋንንት ተፈቶ የተለቀቀበት፣ ሰው በክፋት ከአጋንንት ያልተናነሰበት አንዳንዴም የሚበልጥበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ በተለይ ብዙ ምዕመናን በመተት በድግምት እድላቸው ተወስዶ፣ ሕይወታቸው ባዶ እየተደረገ ነው፡፡

አጋንንት ጎታቾች እና መተት መታቶች ጳግሜን በሰው ላይ የሚመትቱትን መተት የሚያድሱበት ስለሆነ ጸበል በርትተን ብንጠመቅ እድሳታቸው ይሽራል፣ መተታቸውም ይከሽፋል፡፡ ስለዚህ በዚህ በወርኃ ጳግሜ በመተት እና በድግምት የምትሰቃዩ ወገኖቼ በርትታችሁ ጸበል ተጠመቁ ጠጡ፡፡

ምክንያቱም ዓመቱን ሙሉ በእድላችን ሲመተት ወደ እና ሕይወት ሲጎተት የነበረው አጋንንት ጳግሜን በርትተን ከተጠመቅን አጋንንቱ አዲሱን አመት አይሻገርም፡፡

በተመተተብን መተት እና በበላነው ድግምት ውስጣችን በተለይ ሆዳችን፣ እንዲሁም መላ አካላታችን ላይ ደዌ ሆኖ የተቀመጠው አጋንንት ይለቀናል፣ ውስጣችን ያለው የደዌ መተት ይሻራል፡፡
እንዲሁም በአውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን በቅዱስ ዮሐንስ ስም አስታከው ዛር አንጋሾች፤ ለዛር ደም የሚያፈሱበት፣ የሚገብሩበት ጊዜ ነው፡፡

አዲሱን አመት ደም በማፍሰስ፣ ለዛር በመገበር ስለሚቀበሉ ጸበል መጠመቁ ከእዚህ ችግር እናመልጣለን፡፡ በተለይ ቤተሰባችሁ በቅዱስ ዮሐንስ የሽፋን ስም ‹‹ለዓውደ ዓመት ነው፣ ለአድባር ነው፣ አዲስን ዓመት ለመቀበት ነው፣ የእናት አባታችን የአያቶቻችን አምላክ እንዳይጣላን ነው፣

በአዲሱ ዓመት ጠላታችን ደሙ እንዲፈስ ነው፣ ደም የምናፈሰው የእኛን ጦስ ይዞ እንዲሄድ ነው›› በማለት ገብስማ፣ ወሰራ፣ ባለ ነጠላ ዶሮ፤ ነጭ፣ ቀይ በግ እያሉ ያረዱትን እንዳትበሉ፡፡

አውቃችሁ በዮሐንስ ስም ለዛር የተገበረለትን ብትበሉ በደም የገባውን ዛር፤ በጸበል ለማስወጣት ትቸገራላችሁ፡፡ በቤታችሁ፣ በአከባቢያችሁ እንደዚህ አይነት ክፉ ልማድ ካለ ተቃወሙ፣ ለማስተው ሞክሩ፡፡ የእነሱ እዳ ነው ነገ ለእናንተ የሚተርፈው፡፡

በተረፈ ይህችን ወርኃ ጳግሜን እንደ አባቶቻችን እንድንጠቀምባት አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል ይርዳን፡፡
https://www.tgoop.com/menefesawinet
💐🌻"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።🌻💐

           #መስከረም ፩ (1) ቀን።

እንኳን #ለርእሰ_ዐውደ_ዓመት_ለቅዱስ ዮሐንስ፤ #ከዘመነ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወደ_ዘመነ_ቅዱስ_ማቴዎስ አሸጋግሮ #እግዚአብሔር አምላክን በሰላምና በጤና አደረሰን።
                                                              #የተባረከ_የመስከረም_ወር_የግብፅና #የኢትዮጵያ_ዓመታት_ወሮች_ርእስ_ነው። የቀኑ ሰዓትም ከሌሊት ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው። ከዚህ በኋላ እያነሰ ይሔዳል። አሁንም በፍጹም ንጽሕና ታላቅ በዓልን አድርገን ልናከብር ይገባናል።

ይህች ዕለት ከሌሎች ዕለታት ተለይታ የተባረከች ናትና ከክፉ ሥራዎችም ሁሉ ተለይተን እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝባቸውን አዳዲስ የሆኑ በጎ ሥራዎችን እንሥራ። ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ "እነሆ የቀደሙት ሥራዎች አልፈው ሁሉ በክርስቶስ ሐዲስ ሆነ" እንዳለ። ይህም ከ #እግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ የጐላ የተረዳ ሆነ እርሱም በ #ክርስቶስ ልጅነትን በመስጠት ይቅርታውንና ቸርነቱን አደለን።

ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ #መንፈስ_ቅዱስ ስለርሱ ድኆችን በልብ ያዘኑ ሰዎችን ደስ አሰኛቸው ዘንድ ለተማረኩም ሰዎች ነፃ መውጣትን አስተምራቸው ዘንድ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ #እግዚአብሔር የወሰነውን ዘመን የተመረጠ እለው ዘንድ ፍዳ የሚደረግባትንም ቀን ደግ እላት ዘንድ ያዘኑትንም ሰዎች ደስ አሰኛቸው ዘንድ ላከኝ"።

ነቢዩ ዳዊትም ዳግመኛ እንዲህ አለ "የምሕረትህንም ዓመት እህል ትባርካለህ። ምድረ በዳዎችም ከበረከትህ ጠሎችን ይጠግባሉ። ምንጭ፦ የመስከረም 1 ስንክሳር።
@menefesawinet
“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ።" (ራእይ 21፥5)
#ውድ_የተዋህዶ ልጆች_የቻናሎቼ_ተከታዮች

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወደዘመነ ማቴዎስ  ወንጌላዊ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ::
ቀን እና ሌሊትን
ሳምንታትን እና ወራትን
አመታትን እና አዝማናትን እያፈራረቀ በዕድሜያችን ላይ ዕድሜን ጨምሮ ለአዲሱ ዘመን ያደረሰን ከዘመናት በፊት የነበረ ዘመናትንም አሳልፎ የሚኖር ለህላዌው ዘመን የማይቆጠርለት ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ስለማይነገር ስጦታው እስከዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን::
አዲሱ  አመት ዘመን የምንቀይርበት  ብቻ ሳይሆን እኛም ተቀይረን ለክብር የምንበቃበት ይሁንልን።
ብዙዎች ይቺን ቀን ለማየት ናፍቀው ያላዩ  በሞት የተጠሩ አሉ።
ብዙዎች በህመም በየ ሆስፒታሉ በየፀበሉ ያሉ አሉ።
በመከራ በስቃይ በችግር ውስጥ ያሉ አሉ እኛን ግን እግዚአብሔር  ነብዩ 'በቸርነትህ' አመታትን ታቀዳጃለህ'' (መዝ 65:11) ብሎ አንደተናገረው በስራችን ሳይሆን በቸርነቱ አዲሱን አመት ያሳየን ቸሩ አምላካችን የተመሰገነ ይሁን።

ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመርያው መልእክቱ ምዕራፍ 4-3 ላይ
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።”
ብሎ ባለፈው ዘመን ከኖርንበት የኃጢአት መንገድ እንድንመለስ ያስተምረናል::
እኛም ከክፋት፣ከተንኳል፣ከመከፋፈል በጠቃላይ ከክፉ ተግባር ርቀን እግዚአብሔርን የምናስደስትበት ዘመን ያድርግልን።
ዲ/ን ተረፈ ተስፋዬ ነኝ።
@ty1921
@webzema @menefesawinet @kinexebebe @yedawit_begena @amantaakoo @yeberhanljoche @esxifanose
#ሰው_ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

ከአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@menefesawinet
2024/09/25 12:42:46
Back to Top
HTML Embed Code: