† #ሐምሌ ²¹ #እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም : ቅዱስ ዑራኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
† ድንግል እመቤታችን እና ቅዱስ ዑራኤል፦ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዚህች ቀን ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል:-
1.ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቀድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች::
2.ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በአራቱም አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጓል::
3.ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ በኢትዮጵያ ወንዞች ላይ አፍስሷል::
4.ለብዙ ቅዱሳን (አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ) ጽዋዐ ልቡናን አጠጥቷል::
† ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን : ከቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከትን እግዚአብሔር ያድለን::

➣በሥራ ወይም በሌላ አጋጣሚ የዶሮ እርባታ ሥፍራዎችን፣ የቆዳ ፋብሪካዎችን፣ የእንስሳት እርባታና ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ቦታዎችን የመጎብኘት ሁኔታ አጋጥሞን ከሆነ መጥፎ ጠረኑ አፍንጫችንን እንድይዝ አስገድዶን ሊሆን ይችላል። በተለይም ራሳችንን እንደ ቀበጥ የከተማ ልጅ /City boy/ የምንቆጥር ከሆነ የመጥፎ ሽታውን ጠረን ለመቋቋም በጣም እንቸገራለን~እንዴውም "ኡፍፍፍፍ" እያልን እንጠየፋለን።
ወዳጄ ሆይ~ እየሸተተን ያለው ግን አዛባና የዶሮ ኩስ ሳይሆን የገንዘብ /ዶላር ሽታ ነው። it's the smell of money. በዓለማችን የዚህን አዛባና ኩስ ሽታን ተቋቁመው ጠንክረው በመሥራት ወደ ከፍተኛ የብልጽግና ማማ ላይ የተፈናጠጡ አያሌ ባለጸጎች እንዳሉ ፎርቢስ ላይ ማንበብ ወይም በዙሪያችን ያሉትን ጥቂት ባለጸጎች መመልከት በቂ ነው። በከተሞች መንገድ ላይ የተከመረ ቆሻሻን በማጽዳት፣ እንደ ችቦ ብርሀን በመፈንጠቅ የሥራ ባህልና ሞራል ለገነቡልን ክብር ልንሰጣቸው ይገባል።
ከእውነተኛ ሀብት ጀርባ ሁልጊዜ ትልቅ ድካም፣ ትልቅ ትዕግስት፣ መጥፎ ጠረን የተሞላ የሥራ ቦታን መታገስ፣ እንቅልፍ የሚያሳጣ ረጅም የሥራ ሰዓት፣ ጅማት የሚያዝል ጡንቻ የሚያሸማቅቅ አድካሚ ሥራ፣ አዕምሮ የሚያነሆልል እሳቤ የሚጠይቅ ተግባር፣ የእጅ መዳፍ የሚገሸልጥ፣ የእግር ተረከዝ የሚሰነጥቅ፣ ጥፍርን የሚቀረድድ አድካሚ ሥራ መሥራት፣ ወገብ የሚያንቀጠቅጥ ተጋድሎ መፈጸም የግድ ይላል። በእንዲህ ያለ ድካም የሚገኝ ገንዘብ የኅሊና እርካታ፣ የሞራል ልዕልና ከምቾት ጋር ያጎናጽፋል። እንዲህ ባለ ሁኔታ የሚገኝ ሀብት ባለ ጸጋ ያደርጋል። ባለጸግነት የሞራል ልዕልና ደግሞ ትጋትን፣ ቅንነትና እውነትን ትይዛለች። ገንዘብ በስርቆትና መሰል በማጭበርበር ተግባራትም ሊገኝ ይችል ይሆናል። በዚህ መልኩ የተገኘ ገንዘብ ሀብታም ያደርግ ይሆናል እንጅ ባለጸጋ አያደርግም።
በአገራችን ብዙ ሀብታሞች አሉ፤ ብዙ ባለጸጎች ግን የሉንም። ሀብታሞች ከባለጸጎች የሚለዩት ገንዘብ የሚያገኙት የሌሎችን በመቀማት፣ ጉልበት በመበዝበዝና እንዲሁም በማደህየት ሲሆን ባለጸጎች ግን ሀብትን በድካማቸው ይፈጥሩታል። ታላቁ የአሜሪካ የመኪና አምራች ኩባንያ ባለቤት ሚስተር ፎርድ ሥራውን የጀመረው አካፋና ዶማ በማምረት ነበር። ባለጸጎች ለሌሎች ይተርፋሉ እንጅ አይቀሙም።
ሀገራችን ባሳለፈቻቸው ሰላሳና አርባ ዓመታት የኢኮኖሚ ዕድገት ጭላንጭል ቢታይበትም በሞራልና በሕግ ባለመመራት ብዙ ባለ ሀብቶችን እንጅ ብዙ ባለጸጎችን አልታደለችም።
እነዚህ ድካምን ሳያዩ፣ ልፋትን ሳይቀምሱ ገንዘብ ያግበሰበሱ ባለሀብቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ከማናጋታቸው በላይ በወጣቱ ሥነልቦና ላይ የፈጠሩት ጠባሳ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ከጠባብ ወደ ሰፊ፣ ከውድቀት ወደ ስኬት፣ ከኮረኮንች መንገድ ወደ ደልዳላ ጉዞ፣ ከመሳሳት ወደ መታረም፣ በመጨረሻም ከማጣት ወደ ማግኘት ከአካልና ከአዕምሮ ብስለት ጋር እንደሚታደግ ለወጣቶች ያስተማራቸው አርዓያ የሚሆናቸው አልነበረም።
ትናንት ምንም ያልነበረው ሰው ድንገት ዛሬ በርካታ ሚሊዮን ብሮች፣ ብዙ ህንጻዎች፣ ቅንጡ ተሽከርካሪዎች፣ በርካታ ድርጅቶች እንዳሉት ይሰማሉ። በቃ የሀብት መንገድ አጭርና አቋራጭ ብቻ እንደሆነ፣ በድካም በጊዜ ሂደት መበልጸግ ሞኝነት እስኪመስላቸው ድረስ ስነ ልቦናቸውን የተጣመመ ሆኗል።
በጥቅሉ ከባለጸጎች ስኬት ጀርባ ብዙ የፈሰሰ ወዝ፣ የተንጠባጠበ ላብ፣ የተኮማተረ ጅማት፣ የታጠፈ አንጀት የተላጠ ትከሻ አለ። ከሀብታሞች ታሪክ ጀርባ ግን ቅሚያ፣ ጉልበት ብዝበዛ፣ ውንብድና እና ማጭበርበር አለ። ሀብት ከፈጠረው የቀላ ደረት፣ የወዛ ፊት ጀርባ የቆሸሸ ህሊና ሊኖር ይችላል።
ከህይወት ልምዴና ከመጽሀፉ ንባብ የተረዳሁት "የገንዘብ ሽታ ፍልስፍና" ነገር ቢኖር~ የንጹህ ገንዘብ ሽታ የከብት አዛባ፣ የዶሮ ኩስ ሽታ ነው። የእውነተኛ ገንዘብ ጠረን የጭቃ፣ የኬሚካል፣ የጭስ፣ ከሰውነት ድካም የሚመነጭ የላብ ጠረን ነው። አሁን ሲገባኝ ለካ መጥፎ ሽታ የከብቶች አዛባ አይደለም፣ የዶሮ ኩስም አይደለም፣ የድካም ላብ ጠረንም አይደለም። መጥፎ ሽታ ድህነት ነው። መጥፎ ጠረን የሰው እጅ ማየት፤ ተቸግሮ ከሠው ፊት መቆም ነው። መጥፎ ቅርናት ማለት ስንፍናና ስርቆት ነው። ክርፋት ማለት ውድ ሱፍና ካራባት ለብሶ እንደ አገር እርዳታ መቀበል ነው።
#ችቦ መጽሀፍ~ዘር፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሀይማኖት ቢለያየንም በዓለም ላይ ያለ ሁሉ የአንድ አዳምና ሄዋን ልጅ ነው። ትክክልና ስህተት /Right and wrong/ ለሁሉም ተመሳሳይ ነው። በሞራልና በዕምነት ጎዳና ላይ ከሚያሳስቱን ይልቅ የሚያርሙን ይበልጣሉ። ከሚያሰናክሉን ይልቅ የሚያርሙን ይልቃሉ። ከዛህ ረገድ ከያዝነው መርህ መንሸራተት እንደሌለብን በአጽንኦት ይነግረናል። "Take care your self! Do not slide down from your principles!"
መጥፎ በምንለው የአዛባ ሽታ፣ አስቀያሚ በምንለው የዶሮ ኩስ ጠረን ውስጥ ገንዘብ ይታፈሳል፣ ላብን በሚያንጠባጥብ ከባድ በምንለው ሥራ ውስጥ ወርቅና ዳይመንድ ይገኛል። ሽታውን ውደደው፣ ሽታው የገንዘብ /የዶላር ነው። it's the smell of money. Don't Worry!
እኔም ከዓመታት በፊት ቀለምና ቡርሽ አዋህጄ ስዕልና ጽሁፍ እየሰራሁ በነበረበት ወቅት የቅርብ ጓደኞቼ የቀለሙንና የማዋሀጃውን ኬሚካል ሽታ ይጠየፉት እንደነበረ አስታውሳለሁ። በበኩሌ የቀለሙን ሽታ ባልጠላውም የዶሮ ኩስ፣ የከብት ሽንትና አዛባ ባለበት ቦታ ሁሉ ሽታውን ለመቋቋም አፍንጫየን እይዝ ነበረ። ይሁን እንጅ ከጥልቅ መረዳት በኋላ መጥፎ ጠረን ባለበት የሥራ ቦታ ሁሉ አፍንጫን መያዝ ሳይሆን አብሮ የመስራት ጥልቅ ፍላጎት አደረብኝ።
"ችቦ"

ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ!
ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ!
(አሌክስ አብርሃም)
ፍቅር ብቻውን መልስ የሚሆንበት ጊዜ ላይ አይደለንም።
በማንም ላይ መፍረድ ከባድ ነው። ሲቸገሩ መርዳት አለመቻል ከሚፈጥረው ህመም ለመራቅ ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን እንርቃለን። ዓይናቸው ውስጥ ያለውን ስቃይ ላለማየት ዓይናችንን እንሰብራለን።የአቅማችንን መደገፍ እንኳን ከአቅም በላይ ሆኗል። የተወለድንበት እና ያደግንበት ስር የሰደደ አብሮነት፣ መረዳዳት አሁን እግር ከወርች ካሰረን ኑሮ ጋር አብሮ አልሄድ ብሎ አስጨንቆናል። ረስተነው ወደወዳጆቻችን መንገድ ከጀመርን ፣ልንደውል ስልክ ካነሳን በኋላ ባዶ አይናቸው እጃችሁ ከምን ቢለንስ ብለን ተመልሰናል። ከመሄዳችን በላይ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን አንደበታቸው ሳይሆን ኑሯቸው ሁኗል። የተጨነቀ መንፈስ፣ የተጨነቀ አየር። የማንንም እርዳታ የማይፈልጉ መንፈሰ ፅኑ ወዳጆቻችን ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነውባቸው በዓይናቸው ባዶ ኪሳችንን ሲቃኙ ብናይ መርዳቱ ቢቀር አንታዘባቸውም። "እንትናም ተቸገረ?" ብለን አናሾካሹክም። ይገባናል ሰው ወደገደል ቢወድቅ አዳነውም አላዳነውም አጠገቡ ያገኘውን ሳርም ይሁን ቅጠል በደመነፍስ ጨምድዶ እንደሚይዝ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።ልብሳችንን አንቀው የሚማፀኑን እኛም የሌሎችን ልብስ አንቀን መንጠልጠላችንን ያውቃሉ። የመያያዙ መጨረሻ፣ የገደሉ ጫፍ የት እንደሆነ ማን ያውቃል?! እጃችን እየዛለ ነው። ደመነፍስ ላይ ነን። ማንንም ለመዳን እንይዛለን በማንም እንያዛለን። ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ። ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።