Telegram Web
“ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ብንሆን ኖሮ እግዚአብሔር ኅሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ምሽት
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot
ታኅሣሥ 3

በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና ።

እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ ።

ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእነርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ ።

ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጻፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች ።

ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል ።

ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ ።

ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ።

ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች ። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ቀን
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✞የዕለተ ሰንበት የነፍስ ስንቃችን

✞ "ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።" (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18)

☞ "ሰይጣን ከቶ እንደ ጸሎት ማስታጎል የሚወደው የለም። ጸሎት ፍላጻ ነውና ዓይኑን ይወጋዋል። ከሚጸልይ ሰው አንደበት እሳት ወጥቶ ሰይጣንን ያቃጥለዋል። ሰይጣንም ስለዚህ ከበጎ ሥራ ሁሉ ጸሎትና ትጋትን ይጠላል"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (በአርጋኖነ ማርያም ዘሠሉስ)

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ቀን
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው። ሰው በልቦናው ቂምንና በቀልን ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ።»

        👐 መጽሐፈ ቅዳሴ 👐

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የዕለተ_ሰንበት
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በቅድሚያ እንኳን አደረሳችሁ እያልን ለጌታችን የልደት በዓል የሚሆኑ እጅግ ያማሩ ሥርዓት የጠበቁ ግርግሞች በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበናል ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን 0954996114
እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለልደት ታላቅ ክብር በዓል በሰላም አደርሳችሁ አደርሰን ።

ተክለ ሃይማኖት ማለት የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን አቡነ #ተክለሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ማለትም
አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል ።
ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው።

አባታችን ምልጃ ፀሎታቸው አይለየን

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_በዓል _ይሁንላችሁ ❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በቅድሚያ እንኳን አደረሳችሁ እያልን ለጌታችን የልደት በዓል የሚሆኑ እጅግ ያማሩ ሥርዓት የጠበቁ ግርግሞች በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበናል ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን 0954996114
ሰው ሆይ

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ!አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ20፥35)።አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ4፥4)

ሰው ሆይ!አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ?ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

ከአቡነሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ

አዘጋጅ :-በለጠከበደ (የጣፈጡልጅ)አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ማምሻ
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot

ወስብሐትለእግዚአብሔር
በዚህ ሊንክ በመግባት በቴሌ ብር እየተጫወታችሁ ከ10.000አስር ሺህ እስከ 100.000መቶ ሺህ ተሸለሙ  የገና ስጦታ ይቀበሉ

I am inviting you to download telebirr SuperApp, register and make a transaction to get reward. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index1230.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1722184804351104&inviterId=1271496726451209&language=en&campaignType=christmas&time=Jan-01-2025-Jan-07-2025
"ሂድና ውደዳት!"

በአንድወቅት አንድ ሰው ሚስቱ እንድትወደው ብዙ ነገር አድርጎ ስላልተሳካለት ሚስቱም ስላልወደደችው ተበሳጭቶ ወደሰባኪው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይሄዳል፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

"ሚስቴእንድትወደኝ ብዙ ለፋሁ ፤ ያላደረኩት ነገር የለም ፤ምንም ልትወደኝ አልቻለችም፡፡ እንድትወደኝ ማድረግ የምችለው በምን መንገድ ነው?"ሲል በሀዘን ተሰብሮ ይጠይቀውና የሚነገረውን ጥበባዊ መንገድ በጥንቃቄ ለመረዳት እዝነልቦናውን አዘጋጅቶ የአባቱን ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ የአንደበቱን ጥኡም ቃል ይጠባበቃል፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

ቅዱስዮሐንስ ግን የነገሩት በአጭሩ በሁለት ቃል ብቻ የተዋቀረ ነበር፡፡ "ሂድና ውደዳት!"
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

ሰውየው'ያልኩትን አልተረዳኝ ይሆን እንዴ?' እያለ እያሰበ ጥያቄውን ደግሞ አቀረበ።  "ሚስቴ አልወደኝ አለች ምንም ባደርግ ልትወደኝ አልቻለችም ነው ያልኩት" አለ በድጋሜ፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

"ሂድናውደዳት" አለው ሰባኪው በድጋሜ፡፡

አሁንም ለሶስተኛጊዜ ሰውየው "ልትወደኝ የሚገባት ሚስቴ አልወደደችኝም ነው ያልኩዎትኮ!"አለ፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

ሰባኪውምመልሶ "ሂድና ውደዳት!"አለው፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

በዚህጊዜ ሰውየው እርሱ እንደሚወዳት ለመናገር 'እኔማ...'ብሎ ጀምሮ ራሱን መፈተሽ ጀመረ፡፡ እሱ ውስጥ ያለው፣ እርሱ የሚወደው፣ የእርሱ ፍላጎት የእርሱን የራሱን በእርሷ መወደድ እንጅ እርሷን መውደድ አልነበረም፡፡ ጊዜውን ለመወደድ በመጣር ብቻ አሳልፎታል፤ ጥረቱ ሁሉ እንድትወደው እንጅ እንዲወዳት አልነበረም፡፡  አዘነ፡፡ እርሷን መውደድ ሲገባው ራሱን በርሷ ለማስወደድ ሲጥር ኖሯል፤ አልተሳካለትም፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

ፍቅርየሚመጣው በራሱ በፍቅር እንጅ በሌላው ሁሉ ጥረት አይደለም፡፡ በሌላ ጥረት የሚመጣ ሰው ሰራሽ "ፍቅር" ካለ ግን ፍቅሩ ሀሰተኛ ነው፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

ራስንከመውደድ አልፈን ራስን ወደማስወደድ ከመሄድ ይልቅ ሌላውን በመውደድ መወደድን አናጣውም፤ ፍቅር ሌላውን የሚወድ ከሆነ ፍቅርንማ እንደምን አይወድ!
👉 www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

እርሷንስትወዳት ፍቅሯን ታገኛለህ እንጅ ፍቅሯን ያለፍቅርህ አትሞክረው!አንዳንዶቻችን እኔ ላደረኩት ነገር ለምን አልተደነቅሁም ለምንስ አልተወደድኩም እንላለን። እንደዚህ ካልን ያደረግነውን ላደረግንለት ሳይሆን ለራሳችን ነው ማለት ነው ያደረግነው፤ ይህ ደግሞ የፍቅር ባህሪ አይደለም፡፡  እኛ ለሌሎች የሌለንን ፍቅርም ሌሎች ጋ ወደኛ መጠበቅ የለብንም፡፡ ለባለቤቴ ባደረኩላት ነገር ከእርሷ ምስጋናን የምሻ ከሆነና ካልተመሰገንኩ ከከፋኝ እኔ ከፍቅር የነፃሁ ምስኪን ነኝ፡፡  በርግጥ ሚስቴ ደስ ስትሰኝ ማየት ሊያስደስተኝ ይገባል፤ ይህ ማለት ግን እንደዋጋ አድርጌ ልወስደው ሳይሆን መደሰቷን ስለምመርጥላት ስለእርሷ ደስታ ስል ነው፡፡ ስለእኔ በደስታዋ መደሰት ያይደለ፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

"ሂድናውደዳት!"  የሁልጊዜም መርሃችን ልትሆን ይገባል፡፡ እንድትወደን ሳይሆን እንድንወዳት ስንወዳት የምር ትወደናለች፡፡ ስንወድ ከተወዳጁ በምንጠብቀው ነገር መመስረት የለብንም የፍቅራችን መሰረት መመስረት ያለበት ፍቅራችን ላይ እንጅ በሚጠበቅ በሌላ ፍቅርም ሆነ ሌላመሰረት ላይ መሆን የለበትም፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

አምላክእኛን ስለወደድነው አይደለም የወደደን፤ በራሱ ፍቅር ተመስርቶ ወደደን እንጅ፡፡ እኛም በራሳችን ፍቅር ተመስርተን ልንወደው ወይም ስለማይናድ በራሱ ፍቅር ተመስርተን ልንወደው ይገባል፡፡
👉  www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

ሰውላይ ግን መመስረቻው የሰው ፍቅር አይደለም፤ አያስተማምንም፡፡ በራስ ፍቅር መሠረት ላይ የተተከለች ፍቅር በራስ ይዞታ ላይ እንደተሰራች ቤት ናት፡፡ ማንም መጥቶ አያፈርሳትም፡፡ ወዳኝ ከምንዋደድ  ወድጃት ብንዋደድ ይሻለኛል፡፡ መሰረቱን ራሴ ላይ ራሴ ብይዘው!
👉 www.tgoop.com/mezgebehaymanot👈

አዘጋጅ:-በለጠከበደ (የጣፈጡልጅ)አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ቀን
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot

ወስብሐትለእግዚአብሔር
ዛሬ የምትችሉ አትቅሩ የሰንበት ግብዣችን ይህን መንፈሳዊ ማዕድ እንድትካፈሉ ነው

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ሰንበት
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" www.tgoop.com/mezgebehaymanot
+ከአእላፋት ማግስት+

Credit:ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው (@yohannes_getachew1)

''ይሄንስእል እያመለክሽ ነው ሳታገቢ የቆየሽው በጌታ በእየሱስ ስም መንፈስሽን ወጋሁት''

እናቴ ናት በጠዋት እንዲህ የምትለው። አሁንማ ገና እየደረሰ በመሆኑ፥ አእላፋት ዝማሬ ብቻ ሆኗል ወሬው እሱ ይረብሻታል።

ስለ እናቴ ትንሽ ላውራቹህ...

ኤልሳትባላለች። ሲበዛ ተጫዋች፥ ረጅም፥ በጣም ቀይ፥ ስትስቅ ጥርሷ የሚያምር፥ በዛ ላይ ዲምፕል ያላት ውብ ናት። አባቴ ደግሞ ሱራፌል ይባላል፤ ዲያቆን ነበር። በእርግጥ እኔ 16 አመቴ እያለ ነው የሞተው። ሰዎች ስለ እርሱ አውርተው አይጠግቡም። ሰው ቀና ብሎ የማያይ፥ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፥ ጸሎተኛ ነበር ፤ መምህሩ ሲቀሩ እርሱ ነበር ጉባኤ ዘርግቶ የሚያስተምረው። ሁሉም ነበር የሚወደው። እኔን ራሱ ውዳሴ ማርያም፥ ዳዊት፥ ቅዳሴ፥ ሰዓታት አስተምሮብኛል። '

'ሰበኔ...ሴት ሆንሽብኝ እንጂ አንቺን ዲያቆን ነበር የማደርግሽ'' የሁል ጊዜ ንግግሩ ነበር።

እናቴ አባቴ በእግዚአብሔር ላይ ያለው መተማመን ይገርማታል። እኔ ልክ 15 አመት ሲሆነኝ አባቴ በጠና ታመመ። የሳንባ ካንሰር ያዘው። ከቤት መውጣት ከበደው፤ ቀኑን ሙሉ የሚያሳልፈው አልጋ ላይ መጽሐፈ መነኮሳትን እያነበበ ነበር። ትንሽ ህመሙ ባስ ሲልበት ደግሞ መጽሐፉን ደረቱ ላይ አድርጎ ለሰአታት መተንፈስ የከብደው ነበር። ከእርሱ ህመም በኋላ ቤታችን ውስጥ ሳቅ የሚባል ጠፋ። እናቴ ቀይ ፊቷን ማድያት ወረሰው።

.......የሆነማክሰኞ ቀን ጠዋት ላይ ''ኡኡኡኡኡኡኡኡ'' የሚል ጩኸት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ። እናቴ ነበረች። ብርድ ልብሱን ከራሴ ላይ በስርአት ሳላወልቅ ሮጥኩኝ። ኤልሲ አባቴን አቅፋ ፥-

"ጌታዬ ጉድ አታድረገኝ ባክህ ጉድ አታድርገኝ"

"እማ አባቴ ምን ሆነ?"......እምባዬከየት እንደመጣ አላውቅም። ፊቴ ርሷል...

"የልጀነትፍቅሬ ኧረ ተው" ትላለች።

"እማ አባቴ ምን ሆኗል?!"

"ጉድአረከኝ!ብቻዬን ለማን ጥለከኝ!ኧረ ያላንተ አይሆንልኝም!ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ"

ጩኸታችንን የሰሙ ጎረቤቶቻችን ቤታችንን ሞሉት። በአንዴ ግማሹ ቲቪ ይሸፍናል፥ ግማሹ ስለ ድንኳን ያወራል......ራሴንሳትኩ፤ ስነቃ ቀብር ሊሄዱ ህዝብ መጥቷል። ቤቱ ውጪው ግጥም ብሏል። ያ ሁሉ ህዝብ አንድ አባቴን አልሆን አለኝ.....

አባቴካረፈ ጊዜ ጀምሮ ቤታችን የማይቀሩ የማይቀሩ 3 ሰዎች ነበሩ። እነዚህ የእናቴ የስራ ባልደረቦች ታዲያ በመጡ ቁጥር ለእናቴ እንፀልይልሽ ብለዋት ነው የሚሄዱት፤ የሆነ ቀን ላይ ከታናናሾቼ ጋር ጸሎት እያደረግን "ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ቤት ሃይማኖት ተቀይሯል!"አለችን።

"ወደምን?"አልን

"ጌታን ተቀብለናል!ነገ ትጠመቃላችሁ። አቁሙ አሁን!"

"እንዴኤልሲ!እኛ እኮ ልጅ እያለን ተጠምቀናል"

"አንቺ ልጅ!ተናገርኩ በቃ!"

"አልቀይርም!አባቴ ያስተማረኝ ያወረሰኝ ነው፤ አልቀይርም!"አልኩ።

ኤልሲም መልሳ "ነው?ከሆነ ከቤቴ ውጪ!እናንተም እንደዛ ነው?

ታናሽእህቴም አዎ አለች።

"ውጡ!ችግር እና ረሃብ ሲፈራረቅባችሁ ትመጡ የለ!"አለችን በቁጣ።

ስልኬን አንስቼ ለአያቴ ደወልኩ። አያቴ ብቻዋን የምትኖር፥ በጣም ትልቅ ጊቢ ያላት፥ እሱ ላይ ወደ 20 ምናምን ቤት ሰርታ የምታከራይ ሴት ናት። ስደውል ኑ ኧረ ኑ አለች

.........እናቴ ሃይማኖቷን ቀየረች። ሁሉንም እኛ ክፍል የነበረ ስእለ አድኅኖ አውጥታ አቃጠለች። የአባቴን ግን ከበዳት። የእርሱን ዳዊት፥ የጸሎት መጻሕፍት፥ ሁሉን ነገሩን በአንድ ላይ አድርጋ አንድ ክፍል ውስጥ ቆለፈችበት። እኛም አያታችን ጋር መኖር ቀጠልን።

---------------------------------------------------

እናቴን ሃይማኖቷን ያስቀየሯት ሰዎች Theology እንድትማር አደረጉና ፓስተር ሆነች ።

ዛሬ...

"እሺባክሽ...አእላፋት ምናምን እያላችሁ ነው ደግሞ በነጭ ልብስ ጣኦት ልታመልኩ"

"ተይ እንጂ እማዬ...የማይሆን አትናገሪ። ለምን ዛሬ አብረን አንሄድም?"

"ማን?እኔ?ሆሆሆሆሆሆሆሆ...ሥራ አልፈታሁም"

"ምን ችግር አለው?ከደበረሽ ቶሎ እንወጣለን።"

"ቆይይይይይ እሄዳለው። የምሄደው ግን እንዴት ልክ እንዳልሆናችሁ ላሳይሽ ነው!"

ሁላችንምለባብሰን ወጣን። በጊዜ ነበር የደረስነው፤ ቦሌ መድኃኔዓለም ሞልቷል። እንደምንም ብለን ፊት ተጠጋን። ዲያቆኑ "እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ" ይላል። ቁርጥ የአባቴን ድምፅ!ኤልሲ ደነገጠች። አባቴን ያየችው መስሏት ተንጠራርታ ፈለገችው፤ የለም። የሚፀየውን ጸሎት በግእዝም በአማርኛም ስታየው ቆየች። እምባዋ ይፈስ ጀመር። ጸሎቱ ተጠናቆ ነጫጭ የለበሱ ዘማሪያን መድረኩን ሞሉት። መዝሙር ቀጠለ። ቸሩ ሆይ የሚለው መዝሙር ዘማሪዎቹ መዘመር ጀመሩ። የአባቴ የሚወደው መዝሙር ነበር። የሲቃ ድምጽ አውጥታ አለቀሰች። አሳዘነችኝ ደስም አለኝ። መዝሙሩ አለቀ። በአባቶች ብራኬ ተጠናቀቀ። ኤልሲ ሙሉ ሰአት እያለቀሰች ነበር ።

"ኤልሲዬ በቃ አንቺ ሂጂ፥ እኛ እናስቀድሳለን።"

"ልምጣ?"

"የምርሽንነው?"

"አዎልምጣ"

"ነይ" ድንጋጤዬ ያስታውቃል።

ማህሌቱ አልቆ፥ ቅዳሴው አልቆ፥ ቤት ገባን። እኛ ቤት ከመጣሁ 10 አመት አልፎኝ ነበር። ያው ነው፥ ምንም አልተቀየረም። እናቴ ሮጣ ጸሎት ቤት ገባች። ሁሉ ነገሩ አባቴን አባቴን ይላል። ትልቅ የእመቤታችን ምስለ ስዕል ፊት ወድቃ አለቀሰች።

"ሰበኔ አሁን ገባኝ!ልቤ ተሰብሬ ሲያገኙኝ ዓለም ገደል ስትሆንብኝ አግኝተውኝ ነው!ልጆቼ ይቅር በሉኝ!በጎደለኝ በኩል ሲቆሙ ወዳጆች መሰሉኝ ......"

ተቃቅፈንተላቀስን። ምን ተረዳሁ መሰላችሁ?እግዚአብሔር ስራው Mysterious ነው። እንዲህ ነው ብለን Define የማይደረግ። ዛሬ ላይ ቤተሰቤ ሙሉ ሆኗል፤ እናቴም ወደ ክርስትና ለመመለስ ትምህርት ለመማር ከመምህሬ ጋር አገናኝቻለሁ። ከ 10 ዓመት ከብዙ ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ። እጆቼን ከፍ አድርጌ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ...

"የእኔንእምባ ያቆምክ እግዚአብሔር...እምባቸውን ለሚያወጡ ድረስ" ብዬ። "ሰላም ለናፈቁ ሁሉ ሰላም ስጥ። አባቴ የደከሙ ልቦችን አሳርፍ፥ ፈገግታን የናፈቁን ሁሉ ሳቅ አጥግብ፥ ለደስታ የተግደረደሩትን ሁሉ አላምዳቸው ...ባለቀሱበትቦታ እንባቸውን አብስ። ሁሉን ቻይ ሆይ፥ የመዳናቸውን ቀን አታርቅ።"

ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው (Instagram:- @yohannes_getachew1)
ጥር1 / 2017
አዲስ አበባ
Forwarded from ዘ-ተዋሕዶ ቦት
አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️

1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ   50  ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ   25  ብር ካርድ

➡️ ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇
2025/01/15 01:29:24
Back to Top
HTML Embed Code: