✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ግንቦት 1 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ቅዱስ ናትናኤል +"+
+በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት
መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ
ሐዋርያ ነው::
+ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ
ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን
ይታወቃል ቢሉ
እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ
እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ
በቅርጫት ውስጥ
አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው
ነበር::
+ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል::
በባልንጀሮቹ
ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ
ስላደገ): አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::
ምሑረ ኦሪት
ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር::
+በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል
የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ
የጠራበት አንዱ
ምክንያትም ይሔው ነው::
+ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ
ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም
ይተክዝ
ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን
አውቆ በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል::
+ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን
ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት
ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል
አመስግኖታል::
+ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር
ምስጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ
ቅዱስም ሰክሮ ብዙ
አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ
ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::
+የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ
ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ
ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ
አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል::
በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል::
በገድለ
ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው
በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች
በመጨረሻ
ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::
❖እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን
ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን::
ከበረከቱም አይለየን::
=>ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ
3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት
4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
4.ቅድስት እንባ መሪና
5.ቅድስት ክርስጢና
=>+"+ ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልዾስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ' አለው:: +"+ (ዮሐ. 1:48-51)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

✝ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ
🗓 ግንቦት 16 የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
🌕 ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
📝 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ፡ በገሊላ አካባቢ አድጐ፡ ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል።
💡ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል።
📝 ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ። ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው።
📝 ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል። ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው። ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል።
📝3 መልዕክታት፡ ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል። ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል። ከእሳት እስከ ስለት፡ እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል። እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል።
ቅዱሱ በኤፌሶን
📝ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል። ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ።
📝ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ። ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው። በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች። ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ። ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ።
💡ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ። እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም። በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው። 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ። እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ።
📝አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ። 1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው። 2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው። ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች።
📝ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ። እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ። ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው። ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ።
📝የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ። ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው።
📝ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ። ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው። መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ። በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ። ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው።
💡በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ። እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን፡ ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው። በስመ ሥላሴ አጥምቆ፡ ካህናትን ሹሞ፡ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል። በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል። ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች።
📝ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው። በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች። አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት።
📝ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል። ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው። በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት፡ በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል። ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል።
የፍቅር ሐዋርያ
📝ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች። ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል። በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር።
💡በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል፦ "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል:: ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ፦ "ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፡ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ)
📝ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው፡ እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር። እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና።
📝ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል። ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል።
📝ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው። ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው፡ ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ፦
"በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ፡
ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት።

📝ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው።
📝ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት።
📝እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው፦
1. ወንጌላዊ
2. ሐዋርያ
3. ሰማዕት ዘእንበለ ደም
4. አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
5. ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
6. ወልደ ነጐድጓድ
7. ደቀ መለኮት ወምሥጢር
8. ፍቁረ እግዚእ
9. ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
10. ቁጹረ ገጽ
11. ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
12. ንስር ሠራሪ
13. ልዑለ ስብከት
14. ምድራዊው መልዐክ
15. ዓምደ ብርሃን
16. ሐዋርያ ትንቢት
17. ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
18. ኮከበ ከዋክብት
🤲 በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር። ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን። 🤲
🗓 ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ)
3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት)
🗓 ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ
(የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
7.አባ ዳንኤል ጻድቅ
📖"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፡ የእናቱም እህት፡ የቀለዮዻም ሚስት ማርያም፡ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን፡ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት። ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።"
(ዮሐ. 19:25)
✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨

🌿እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
✝በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
♱ቅዱስ ኤዺፋንዮስ
📝ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው።
💡ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው። ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ። በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ። ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው።
📝ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ።
📝ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር።
💡አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ።
📝ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ። በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ።
📝 እግዚአብሔርም ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች።
📝ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ406 ዓ.ም. ዐርፏል:: እድሜውም 96 ዓመት ያህል ነበር።
🤲አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን!
🗓 ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)
2. ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ
3. አባ ሉክያኖስ ጻድቅ
4. ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ
🗓 ወርኀዊ በዓላት
1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4. አባ ገሪማ ዘመደራ
5. አባ ዸላሞን ፈላሢ
6. አባ ለትጹን የዋህ
📖"የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል። እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው። እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም። ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም። ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ።'' (1ቆሮ. 9:25)

እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
በዓለ ዸራቅሊጦስ
ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,978 ዓመታት
በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን::
♱ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል
*ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ:
*በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ:
*በኅቱም ድንግልና ተወልዶ:
*ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ:
*በ30 ዘመኑ ተጠምቆ:
*ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ:
*በፈቃዱ ሙቶ:
*በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ:
*በአርባኛው ቀን ያርጋል::
+ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው
ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው::
+እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ
በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ
ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ
በአምሳለ እሳት አደረባቸው::
+ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው
ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም
ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ::
+ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል
አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም
አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል::
"ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ:
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ:
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ::
+በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:-
1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-"
*እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና
ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን
ነውና::
2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-"
*አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት
የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ
ተመስርታለች::
♱ አባ ገዐርጊ
=>በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር።
ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ።እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ።
ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው።
አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም።
ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ።
በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት።
ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ።
ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች።
እሊህ ቅድሳንም ለመነኰሰኘሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኃላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ።ከእርሱ በኃላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን።
=>በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
=>አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን::
=>ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት
2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ
3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
=>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው
አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ::
ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ
ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም
መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ
ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4)

✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+✝+ አባ ዓቢየ እግዚእ +✝+
❖ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን
የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ:: (እንደ ወትሮው ሁሉ) ከተማዋ ውስጥ ጅብና እባብን
የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ
ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ?
☞ መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን
እገምታለሁ:: (ምክንያቱም ሆኖ አያውቅማ!)
+ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን
ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ
አይጠፉባቸውም::
"ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና
ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ
በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: (ሁሉም የሃገራችን ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው)
+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ
ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው
'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ
መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው"
ማለት ነው::
+ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ
ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ
ከሐዲስ ጠነቀቁ::
ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ
እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል::
+በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ
በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን
አግኝተዋል::
በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ
ይበሉ ነበር::
+ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ
ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን
አፍርተዋል::
ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ
አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ
ስብከታቸው ነው::
+አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት
ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10
ነውና ተከዜ
እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ
ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-
አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው
ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ::
+ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ
ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000
በላይ
አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም
ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር)
ይከበራል::
+ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና
አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ
ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት
ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::
+በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት
ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ
ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም
ስለ ሕዝቡ ለመኑ::
+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ
የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት
አይሠለጥኑባቸውም::
በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው
ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል::
+ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ
ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል::
ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው
እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ
ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ
ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ19) ይቅርና
በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት 19) ለንግስ የሚመጣው
ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል::
+አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት
በቅድስና ኑረው: 3 ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን
ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም
ተቀብለው: በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል::
የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው::
+<< ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ
ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ
ዓለም:: አሜን:: >>+
+<< ከበዙ ተአምራቱ አንዱን >>+
=>ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን
(መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ!
የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም
በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው
ሰጧት::
+ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና
"ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል)
ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም
"በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት::
+ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ
(ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው
ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ::
ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና::
+ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ
ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ!
የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም
እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ::
+"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ
ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን
በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም'
አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና::
+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል
ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ
ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)
¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . .
ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44)
+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን
'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ
ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ::
"እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ
ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው
ለጻድቁ ሰገዱ::
=>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን
ለዓለመ ዓለም:: አሜን::
❖አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ
ይሠውርልን::
❖ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር
ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ)
3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ)
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ (7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ)
5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ)
6.አባ ይስሐቅ ገዳማዊ
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ
4፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ

††† እንኳን ለመናኙ ንጉሥ ቅዱስ አፄ ካሌብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† መናኙ ንጉሥ ካሌብ †††
††† ቅዱሱን ንጉሥ አፄ ካሌብን በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በትልቁ ያከብሩታል:: ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አክሱም አካባቢ ካልሆነ ከነ ስም አጠራሩ እንኳ እየተዘነጋ ይመስለኛል::
ነገር ግን ውለታው : ምናኔውና ቅድስናው የማይረሳ ነውና እንኳን በእምነት የሚመስሉን ይቅርና የማይመስሉን ምሥራቅ ኦርቶዶክሶችና ካቶሊኮች ዓመታዊ በዓሉን በወርኀ ጥቅምት ያከብራሉ::
ከአክሱም ነገሥታት በኃይሉም ሆነ በሃይማኖታዊ ቅድስናው አፄ ካሌብ ዋናው ነው:: ቅዱሱ የነገሠው በ485 ዓ/ም አካባቢ ሲሆን እስከ 515 ዓ/ም ድረስ በዙፋኑ ላይ ቆይቷል:: ከመልካም ትዳሩ አፄ ገብረ መስቀልን ጨምሮ ልጆችን ወልዷል::
††† ስለ ቅዱስ አፄ ካሌብ እስኪ እነዚህን ነገሮች ብቻ እናንሳ:-
1.በንግሥና ዙፋን ከመቀመጡ በፊት የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ጠንቅቆ ተምሯል::
2.ሃይማኖቱ የጠራና እጅግ የሚደነቅ ነበር:: በእርሱ ዘመን ሃይማኖት ለነገሥታቱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ነበር:: እርሱ ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ አምልኳል::
3.ለእመቤታችንና ለቸር ልጇ የነበረው ጥልቅ ፍቅር የተገለጠና የሚያስቀና ነበር::
4.ገና በዙፋኑ ሳለ ጸሎትን ያዘወትር ነበር::
5.ዛሬም ድረስ ሁሉም ክርስቲያኖች የማይረሱትን መንፈሳዊ ቅንዓትን አሳይቷል::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
*በወቅቱ ዐመፀኛው የአይሁድ መሪ ፊንሐስ በሃገረ ናግራን (የአሁኗ የመን) ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖችን ክርስቶስን ካዱ በሚል ጨፈጨፋቸው::
ከተማዋንም ለአርባ ቀናት በእሳት አነደዳት:: ዜናው በመላው ዓለም ሲሰማ በርካቶቹ ቢያዝኑም የተረፉትን ለመታደግ የሞከረ አልነበረም::
ቅዱስ አፄ ካሌብ ግን የሆነውን ሲሰማ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በግንባሩ ሰገደ:: ወደ ፈጣሪም ጸለየ:- "ጌታዬ ሆይ! የክርስቲያኖችን ደም እመልስ ዘንድ እርዳኝ? እኔ በጦሬ ብዛት አልመካም:: እኔ ተሸንፌ ክርስትና ከሚናቅ እዚሁ ግደለኝ" ብሎ በበርሃ ላሉ መነኮሳት እንዲጸልዩ ላከባቸው::
ጊዜ ሳያጠፋ በመርከብና በፈረስ : በበቅሎና በግመል ናግራን (የመን) ደረሰ:: ፊንሐስን ገድሎ ሠራዊቱንም ማርኮ ክርስቲያኖችን ነጻ አወጣ:: ደምና እንባቸውንም አበሰ:: አብያተ መቅደሶችን አንጾላቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ::
ወዲያው እንደተመለሰ ወደ አክሱም ጽዮን ገብቶ "ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረክልኝ የምሰጥህ ሰውነቴን እንጂ ሐብቴን አይደለም" ብሎ መንግስቱን ለልጁ ገብረ መስቀል አውርሶ ከዙፋኑ ወጣ:: የወርቅ አክሊሉን ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ እርሱ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ መነነ::
(በፎቶው ላይ የምታዩት አፄ ቅዱስ ካሌብ የመነነበት : አክሱም አካባቢ የሚገኝ የአባ ጰንጠሌዎን ገዳም ነው)
ከዚሕች ዓለም ከአንዲት ረዋት (ኩባያ) : ከአንዲት ሰሌንና ከአንዲት ቀሚስ በቀር የወሰደው አልነበረም:: ከዚያም በበዓቱ ውስጥ በጾምና በጸሎት ተወስኖ አንድም ሰው ሳያይ በሰባ ዓመቱ (በ529 ዓ/ም) ዐርፏል:: ጌታችንም በሰማይ ክብርን አጐናጽፎታል::
††† ለቅዱስ አፄ ካሌብ የተለመነ አምላክ ለእኛም ይለመነን:: በጻድቁም ጸሎት ከመከራ ይሠውረን::
††† ግንቦት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አፄ ካሌብ (መናኙ ንጉሠ ኢትዮጵያ)
2.ቅዱስ አሞንዮስ ገዳማዊ (ታላቁ አሞኒ ዘቶና)
3.ቅድስት ሳድዥ የዋሂት
4.አባ ሖር ጻድቅ
5.አባ ዳርማ ገዳማዊ
6.ቅዱስ ዘካርያስ አንጾኪያዊ
7.አባ በትረ ወንጌል ዘደብረ ሊባኖስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
††† "አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል::
በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል::
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::
የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም::
በበጐ በረከት ደርሰህለታልና::
ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ::
ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም::
ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ::
በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው::" †††
(መዝ. ፳፥፩-፭)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖✝ ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝ቅዱስ እንድራኒቆስ +"+✝
=>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ
ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው::
ጌታችን በመዋዕለ
ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር
ደምሮ አስተምሮታል::
+ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት
ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር::
ይሕ የተፈጸመ ገና
መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20)
+ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10
ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት
ተቀብሏል:: እንደ
ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን
ሰብኳል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት
አምላኩን
አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ
እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ
መልዕክቱ
16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው::
+ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ
ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል
አብርተዋል:: እጅግ ብዙ
መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው
ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት
ቤቶችን አፍርሰው
አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል::
በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል::
+ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን
ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ
በዚሕች ቀን
አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር
ገንዞ ቀብሮታል::
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+
=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ
የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
+ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር
የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ
(ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ
ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ
ገስጾታል:: በዚህም
ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል::
እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት
ቀስፎታል::
❖የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ
ክብራቸውን ያድለን::
❖ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ደቅስዮስ
3፡ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5፡ አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
6፡ አባ ጳውሊ የዋህ
++"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ:
ደግሞም
ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ
ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና
ዮልዮስ) ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖✝ ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝ቅዱስ እንድራኒቆስ +"+✝
=>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ
ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው::
ጌታችን በመዋዕለ
ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር
ደምሮ አስተምሮታል::
+ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት
ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር::
ይሕ የተፈጸመ ገና
መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20)
+ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10
ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት
ተቀብሏል:: እንደ
ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን
ሰብኳል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት
አምላኩን
አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ
እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ
መልዕክቱ
16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው::
+ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ
ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል
አብርተዋል:: እጅግ ብዙ
መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው
ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት
ቤቶችን አፍርሰው
አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል::
በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል::
+ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን
ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ
በዚሕች ቀን
አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር
ገንዞ ቀብሮታል::
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+
=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ
የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
+ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር
የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ
(ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ
ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ
ገስጾታል:: በዚህም
ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል::
እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት
ቀስፎታል::
❖የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ
ክብራቸውን ያድለን::
❖ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ደቅስዮስ
3፡ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5፡ አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
6፡ አባ ጳውሊ የዋህ
++"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ:
ደግሞም
ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ
ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና
ዮልዮስ) ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝✝✝ በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: ✝✝✝
+✝" አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ "✝+
=>እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::
+ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::
+ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::
+ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::
+የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::
+ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::
*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)
*በ40 ቀናት : ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::
*በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም::
+በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::
"1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ:
2.ስለ ምናኔሕ:
3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ:
4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ:
5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ:
6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ:
7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"
+"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::
+ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}
=>አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)

✝✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝
+"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+
=>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::
+ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው::
+መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::
+ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)
+ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-
1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::
+ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::
+ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::
+ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::
+በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::
+በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::
+ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::
+በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::
+እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::
=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::
=>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ)
3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)

"✝" ግንቦት 26 "✝"
+*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+
=>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::
+እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::
+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::
+ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::
+አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::
+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::
+በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::
+በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::
+ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
+ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::
+በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::
+ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::
+ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::
+እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::
+ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}
<< ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! >>
=>+"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: +"+ (1ዼጥ. 5:3)

††† እንኩዋን ለበዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) በሰላም አደረሳችሁ †††
††† በዓለ ጰራቅሊጦስ (መንፈሰ ጽቅድ) †††
=>ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም
ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ➊➒➐➏ ዓመታት
በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን
እናስባለን::
††† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል
*ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ:
*በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ:
*በኅቱም ድንግልና ተወልዶ:
*ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ:
*በ30 ዘመኑ ተጠምቆ:
*ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ:
*በፈቃዱ ሙቶ:
*በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ:
*በአርባኛው ቀን ያርጋል::
+ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው
ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው::
+እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ
በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ
ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ
በአምሳለ እሳት አደረባቸው::
+ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው
ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም
ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ::
+ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል
አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም
አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል::
"ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ:
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ:
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ::
✝በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:-
1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-"
✝እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና::
2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-"
✝አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት
የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች::
✝የመንፈስ ቅዱስ ቸርነቱ፤ ምሕረቱ፤ ጸጋው ይደርብን

††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ †††
†††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:-
¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ
¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ
¤ጌታውን ያጠመቀና
¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:-
ነቢይ:
ሐዋርያ:
ሰማዕት:
ጻድቅ:
ገዳማዊ:
መጥምቀ መለኮት:
ጸያሔ ፍኖት:
ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች::
††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ †††
††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:-
¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
¤መናኔ ጥሪት የተባለ
¤በድንግልና ሕይወት የኖረ
¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው::
ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል::
ቅዱስ ዮሐንስ
¤ቁመቱ ልከኛ
¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ
¤የራሱ ጸጉር በወገቡ
¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ
¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር::
ቅዱስ ኤልሳዕ
¤በጣም ረዥም
¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ)
¤ቀጠን ያለ
¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር::
በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት::
ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት::
ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል::
በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል::
††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን::
†††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ)
3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ
†††ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
†††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው::
የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" †††
(ማቴ. 11:7-15)

††† ✝እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††✝
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አቡነ ተጠምቀ መድኅን †††
††† ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው #ወልደ_ክርስቶስና #ወለተ_ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ #ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ #ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ::
ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም::
ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ::
ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት:-
1.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል
2.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል
3.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና)
4."7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
††† ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ #ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል::
እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ #በጋሾላ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል::
††† ቅድስት ማርታ †††
††† እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች::
መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን (በበዓለ ልደት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት::
ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት::
ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ25 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች::
††† የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: †††
††† ሰኔ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ማርታ ተሐራሚት
2.አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
3.ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት
4.ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት
†††ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
††† "አልሞትም: በሕይወት እኖራለሁ እንጂ::
የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ::
መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ::
ለሞት ግን አልሠጠኝም::
የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ::
ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ::
ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት::
ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ::
ሰምተኸኛልና:
መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ::" ††† (መዝ. 117:17-22)

❖ ሰኔ ፬ ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁዋ ሰማዕት "ቅድስት ሶፍያ" እና ለቅዱስ "ዮሐንስ ዘሐራቅሊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" #ሶፍያ (SOPHIA) "*+
=>ሶፍያ ("ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ) በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር:: ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው:: በዚህ ስም የሚጠሩ አያሌ ቅዱሳት አንስት ሲኖሩ አንዷ ዛሬ ትከበራለች::
+*" ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት "*+
=>ቅድስቷ የተወለደችው በምሥራቅ ሮም ግዛት ውስጥ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ዘመኑ የጭንቅ : የመከራ በመሆኑ ሕዝቡ በስደት ይኖር ነበር::
+የቅድስት ሶፍያ ወላጆች ክርስቲያኖች ናቸውና በመልካሙ መንገድ በንጽሕና አሳድገዋታል:: ባለጠጐች በመሆናቸው አገልጋይ ቀጥረውላት : ያማረ ቤት ሰርተውላት በዚያ ትኖር ነበር:: ሁሉ ያላት ብትሆንም ሁሉን ንቃ በጾምና በጸሎት ትኖር ነበር::
+ለዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለከተማው መኮንን (ገዢ) ሊድሯት መሆኑን አወቀች:: ወደ ቤቷ ገብታ 100 ጊዜ ሰገደች:: ወደ ፈጣሪዋም ጸለየች:- "ጌታየ ሆይ! የዚህን ዓለም ቀንበር አታሸክመኝ:: አልችለውምና:: ያንተው ቀንበር ግን የፍቅር ነውና እችለዋለሁ" አለች::
+አገልጋዩዋን ጠርታ ብዙ ወይን አጠጥታት ልብስ ተቀያየሩ:: በሌሊትም ወጥታ ወደ በርሃ ሔደች:: ዓላማዋ ምናኔ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ግን ሌላ ነበር:: በመንገድ ብዙ ክርስቲያኖች በመከራ ብዛት ሲሰደዱ አገኘቻቸው:: እርሷ ስደትን አልመረጠችም::
+እያጠያየቀች "ሰው በላ" ከተባለው አረመኔ ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ ደረሰች:: በንጉሡ ፊት ቀርባ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" አለችው:: ንጉሡ ከመልኩዋ ማማርና ከድፍረቷ የተነሳ አደነቀ::
+ሊያባብላት: ሊያስፈራራትም ሞከረ:: ግን
አልተሳካለትም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው ጦር ባለው
የብረት ዘንግ
ደብድበዋታልና ደም አካባቢውን አለበሰው:: መሬት
ለመሬት እየጐተቱ እሥር ቤት ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ
ገብርኤል መጥቶ
ፈውሷት ሔደ::
+አንዴ በእሳት: አንዴም በስለት: ሌላ ጊዜም በግርፋት
አሰቃዩዋት:: ከሃይማኖቷ ግን ሊያነቃንቁዋት አልቻሉም::
በመጨረሻ አንገቷን እንድትሰየፍ ንጉሡ አዘዘ::
ወታደሮቹም ፈጸሙት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ
ቅድስት ሶፍያን
በክብር አሳረጋት:: "ስምሽን የጠራ: መታሰቢያሽን ያደረገ
ምሕረትን ያገኛል" አላት::
+"+ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ +"+
=>ቅዱሱ የነበረው በተመሳሳይ በዘመነ ሰማዕታት ነው::
አባቱ ዘካርያስ: እናቱ ኤልሳቤጥ: እርሱ ደግሞ ዮሐንስ
ይባላል:: የሚገርም መንፈሳዊ ግጥጥሞሽ ነው:: የቅዱሱ
ወላጆች የሃገረ ሐራቅሊ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ
የተመሰከረላቸው
ደጐች ነበሩ::
+ዘካርያስ አርፎ ዮሐንስ በመንበሩ የተቀመጠው ገና በ20
ዓመቱ ነበር:: በወቅቱ ከ2 አንዱን መምረጥ ነበረበት::
1.ለጣኦት ሰግዶ በምድራዊ ክብሩ መቀጠል
2.ወይ ደግሞ በክርስትናው መሞት
+ቅዱስ ዮሐንስ ግን ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ነውና
2 ከባባድ ነገሮችን ፈጸመ:: በመጀመሪያ በአካባቢው ያሉ
ጣዖት
ቤቶችን አወደመ:: ቀጥሎ ወደ ንጉሡ ሔዶ በመኩዋንንቱ
ፊት "ክርስቶስን የተውክ ሰነፍ" ብሎ ገሠጸው::
+ከዚህ በኋላ በቅዱሱ ላይ የተፈጸመው መከራ የሚነገር
አይደለም:: ያላደረጉት ነገር አልነበረም:: እሳቱ: ስለቱ:
ሰይፉ: መንኮራኩሩ . . . ከሁሉ የከፋው ግን ቆዳውን
ገፈው በእሳት ጠብሰውታል:: እርሱ ግን ስለ ሃይማኖቱ
ይሕንን
ሁሉ ታግሶ በዚህች ቅን አንገቱን ተሰይፏል::
=>አምላካችን እግዚአብሔር ግፍዐ ሰማዕታትን አስቦ
እኛን ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም
ይክፈለን::
=>ሰኔ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
3.ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት
4.ቅድስት ማርያ ሰማዕት
5.ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት)
6.ቅዱስ አሞን ሰማዕት
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2፡ ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
=>+"+ እንግዲሕ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ:
የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ
የምነግራችሁን
በብርሃን ተናገሩ:: በጀሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ
ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል
የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም
በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: +"+ (ማቴ.
10:26)

††† እንኳን ለኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ብሶይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ አባ ብሶይ ሰማዕት †††
††† ቅዱሱ አባታችን ከዘመነ ሰማዕታት ጣፋጭ ፍሬዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው::
††† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ ታግሕስጦስና ክሪስ የሚባሉ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በቀናው የጽድቅ ጐዳና ቢኖሩም ከጋብቻ በኋላ ለአሥራ ሰባት ዓመታት መውለድ አልቻሉም::
የአሥራ ሰባት ዓመት ልመናቸውን የተመለከተ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አበሰራቸው:: "ሕፃኑ ለሰማዕትነት ተመርጧልና ብሶይ በሉት" አላቸው:: ብሶይ በተወለደ በሰባት ዓመቱ ወላጆቹ ይማር ብለው ወደ ገዳም ወሰዱት:: በገዳም ውስጥ መጻሕፍትን አጥንቶ ዲቁናን ተሾመ:: ወደ ዓለም ተመለስ ቢሉትም እንቢ አለ::
ከባልንጀራው ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ለሃያ አንድ ዓመታት በድንግልና : በተጋድሎ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተሩ ኖሩ:: ቅዱስ ብሶይ ሃያ ስምንት ዓመት በሞላው ጊዜ መልአኩ የተናገረው የትንቢት ዘመን ደረሰ:: በርካታ ምዕመናን ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ታረዱ:: ወደ እሳትም ተጣሉ:: ሞትን የፈሩ ደግሞ በየዱር ገደሉ ተሰደዱ::
ቅዱስ ብሶይም በሚያውቁት ሰዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ:: ድንገት ከሰማይ ፍጡነ ረድኤት ወሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ደረሰለት:: "አይዞሕ! እኔ እስከ መጨረሻው ከአንተ ጋር ነኝ" አለው::
የጦር መኮንኑ ክርስቶስን እንዲክድ አባበለው:: ቅዱሱ ግን ጣዖታቱ የአጋንንት ማደሪያ መሆናቸውን በገሃድ ነገረው:: መኮንኑ ቢበሳጭ ወታደሮቹ እንዲጨምቁት አዘዘ:: ደሙ እየወረደ ገረፉት:: በፊትና በኋላ ብረት አድርገው ሥጋውን ጨፍልቀው እሥር ቤት ውስጥ ጣሉት:: ሊቀ መላእክት መጥቶ ዳስሶ አዳነው::
መኮንኑ እርሱን ማሰቃየት ደከመው:: የቅዱሳን ሕይወት ግርም ይላል:: ተገራፊው እያለ ገራፊው : ስቃዩን የሚቀበለው እያለ አሰቃዩ ይደክመዋል::
††† ይሕንን መሰለኝ አባ ጽጌ ድንግል:-
"እመዐዛ ጽጌኪ ድንግል ውስተ ዐውደ ስምዕ ዘሰክረ::
ውግረተ አዕባንኒ ይመስሎ ሐሰረ::
እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ" ያለው::
ቅዱስ ብሶይን ከአንዱ መኮንን ወደ ሌላው እያመላለሱ አሰቃዩት:: አካሉን ቆራረጡት:: ዓይኑን በጋለ ብረት አወጡት:: በምጣድ ቆሉት:: በጋን ውስጥ ቀቀሉት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ፍቅር የጸና ነውና ሁሉን ታገሰ:: በነዚሕ ሁሉ የስቃይ ዓመታት ቁራሽ ዳቦ እንኳ አላቀመሱትም:: በረሃብ ቀጡት እንጂ:: ለእርሱ ግን ምግቡ የክርስቶስ ስም ነበር::
በመጨረሻ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ አንገቱን በሰይፍ አስመታው:: ሥጋውንና የተቆረጠ አንገቱን ገንቦ (ጋን) ውስጥ ከቶ ጣለው:: የቅዱሱን አካል የያዘችው ጋን ግን በእግዚአብሔር ቸርነት : ማንም ሳይሸከማት ከመሬት ከፍ አለች:: ለሃያ ቀናት ተጉዛ ከሶርያ ግብጽ (ቦሃ) ደረሰች:: ክርስቲያኖች ተቀብለው ሲከፍቷት የቅዱስ ብሶይ ራሱና አንገቱ ተጣብቆ ተገኝቷል:: በክብርም አሳርፈውታል::
††† ቅዱስ ያዕቆብ †††
††† ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ (ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል::
በዚህም ምክንያት መከራን ተቀብሏል:: ታስሯል:: ተገርፏል:: እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል::
††† ቸር አምላክ ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሶይ እና ከቅዱስ ያዕቆብ በረከት ያሳትፈን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::
††† ሰኔ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ብሶይ (ኃያል ሰማዕት)
2.ቅድስት ማርታ ለባሲተ ክርስቶስ (በቅድስናዋ የተወደሰች : በስደት ያረፈች እናት ናት::)
3.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ
4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
5.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት
6.ቅዱስ መርቆሬዎስና ማኅበሩ (ሰማዕታት)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ : ወይስ ጭንቀት : ወይስ ስደት : ወይስ ራብ : ወይስ ራቁትነት : ወይስ ፍርሃት : ወይስ ሰይፍ ነውን?
"ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን" ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፰)

†††✝✝✝ እንኳን ለጻድቅና ሰማዕት አባ ቴዎድሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
†††✝✝✝ አባ ቴዎድሮስ †††✝✝✝
†††አባ ቴዎድሮስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ግብፃዊ አባት ነው:: ተወልዶ ባደገባት የእስክንድርያ ከተማ ብሉያትንና ሐዲሳት በወቅቱ ከነበሩ አበው ሊቃውንት ተምሯል:: ጊዜው ምንም መናፍቃን የበዙበት ቢሆን በዛው ልክ እነ ቅዱስ እለ እስክንድሮስና ቅዱስ አትናቴዎስን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና ከነሱ የሚገባውን ወስዷል::
አባ ቴዎድሮስ "አባ" ያሰኘው ሥራው:- ሲጀመር ገና በወጣትነቱ ድንግልናንና ምንኩስናን በመምረጡ ነበር:: ምንም እንኳ ሐብት ከእውቀት ጋር ቢስማማለትም ይሕ እርሱን ከምናኔ ሊያስቀረው አልቻለም:: ከከተማ ወጥቶ: በዓት ወስኖ በጾምና በጸሎት ተወሰነ::
በ340ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ግን በምዕመናን ላይ ከባድ ችግር ደረሰ:: የወቅቱ ነገሥታት በስመ ክርስቲያን አርዮሳውያን ነበሩና ሕዝቡን ማስገደድ: አንዳንዴም የአርዮስን እምነት ያልተቀበለውን ማስገደል ጀመሩ:: በዚህ ምክንያትም ታላቁ የኦርቶዶክስ ጠበቃ ቅዱስ አትናቴዎስን ከመንበሩ አሳደዱት:: በምትኩም አርዮሳዊ ሰው ዻዻስ ተብሎ ተሾመ:: ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ እውነተኛ እረኛ ያስፈለገው::
በበዓቱ የነበረው አባ ቴዎድሮስ አላቅማማም:: ቤተ ክርስቲያን ትፈልገዋለችና መጻሕፍትን ገልጾ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ምዕመናንን ያጸናቸው ጀመር:: መናፍቃኑን ተከራክሮ ምላሽ በማሳጣት ሕዝቡን ከኑፋቄ በመጠበቅ የሠራው ሥራ ሐዋርያዊ ቢያሰኘውም ለአርዮሳዊው ዻዻስ (ጊዮርጊስ ይባላል) ሊዋጥለት አልቻለም::
በቁጣ ወታደሮችን ልኮ አባ ቴዎድሮስን ተቆጣው:: እንዳያስተምርም ገሰጸው:: አባ ቴዎድሮስ ግን እሺ ባለማለቱ ግርፋት ታዘዘበት::
ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲገርፉት ረድኤተ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከዛ ሁሉ ግርፋት አንዲቷም አካሉ ላይ አላረፈችም:: በዚህ የተበሳጨው አርዮሳዊ ዻዻስ የአባ ቴዎድሮስን እጅና እግር ከፈረስ ጋሪ በኋላ አስረው በኮረኮንች መንገድ ላይ በፍጥነት እንዲያሮጧቸው አዘዘ::
ፈረሶቹ መሮጥ ሲጀምሩ የአባ ቴዎድሮስ አካሉ ይላላጥ ጀመር:: ትንሽ ቆይቶ ግን እጆቹ ተቆረጡ:: በኋላም ራሱ ከአንገቱ ተለይታ መንገድ ላይ ወደቀች:: አካሉ በሙሉ መሬት ላይ ተበታተነ:: እግዚአብሔር ቅድስት ነፍሱን ተቀብሎ አሳረጋት::
††† ለቅዱሱም 3 አክሊል ከሰማይ ወርዶለታል:-
1.ስለ ፍጹም ምናኔውና ድንግልናው
2.ስለ ሐዋርያዊ የወንጌል አገልግሎቱ
3.ስለ ሃይማኖቱ ደሙን አፍስሷልና
"እምአባልከ ተመቲራ ለእንተ ሠረረት ርዕስ:
እግዚአብሔር አስተቄጸላ በአክሊል ሠላስ" እንዳለ መጽሐፍ::
ምዕመናን ሥጋውን ሰብስበው በዝማሬና በማኅሌት በክብር ቀብረውታል::
††† አምላካችን ከቅዱሱ በረከት ይክፈለን::
††† ሰኔ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ቴዎድሮስ ሰማዕት
2.አባ ገብረ ክርስቶስ
3."40" ሰማዕታት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
††† "መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይህንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያሰረክባል:: ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም::" †††
(2ጢሞ. 4:7)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††✝✝✝

††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ †††
††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው : በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው::
ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር::
አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት : ገና በ3 ዓመቱ : እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ::
††† ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:-
1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ::
2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ::
3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው::
ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል::
ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን:: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው::
"እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል::
ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን : ዕጸበ ገዳምን : ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
††† በዘመኑም:-
1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል::
2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል::
3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል::
4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::
በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች::
††† አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን::
††† ሰኔ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ
2.ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው)
3."16,000" ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ)
4.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
††† "ይሕንን እዘዝና አስተምር :: በቃልና በኑሮ : በፍቅርም : በእምነትም : በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው:: እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር : ለማስተማርም ተጠንቀቅ::" †††
(1ጢሞ. 4:11)

††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ ዓበይት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::
††† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ ምድረ ግብጽ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኳን ለስደተኛ በቤቱ ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት ያውቀዋል::
††† ለዛም ነው ሊቁ በቅዳሴው:-
"አዘክሪ ድንግል ረሃበ ወጽምዐ : ምንዳቤ ወኀዘነ : ወኩሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ" ያለው::
ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት ድንግል እመቤታችን ውኃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች : ግን ጥርኝ እንኳ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች:: ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች ወስደውት ደረሰች::
ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውኃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች::
"በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ::
እምሰብአ ሃገር አልቦ ዘየአምራ ለጽድቅ::
ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀሐቡኒ በሕቅ::
ወአሕጎልኩ ለወልድየ አሳእኖ ዘወርቅ::" እንዳለ ደራሲ::
ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው ሕይወትነት ያለው ማይ (ጠበል) ፈለቀ:: ጌታችን : እመቤታችን: ዮሴፍና ሰሎሜ ከውኃው ጠጥተዋል::
ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ (መድኃኒት) : ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል::
"ከመ ኢይስተይዋ ሰብአ ሐገር ለይእቲ ማይ አምረራ::
ወለርኁቃንሰ ፈውሰ ወጥዕምተ ገብራ::" እንዳለ መጽሐፍ:: (ሰቆቃወ ድንግል)
ከመቶዎች ዓመታት በኋላም ጌታ ጠበል ያፈለቀበት : ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል:: ጠበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል::
††† የጠበል በዓል †††
†††ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች::
እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት (እምነት) : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ (በመታሸት) : በቅዱሳን አካል (በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .) ይፈውሳል::
እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል ( ይፈውሳል):: (2ነገ. 5:10, ሐዋ. 3:6, 5:15, 19:11)
††† ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: (ዮሐ. 5:1, 9:7)
††† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::
††† ሰኔ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት
2.የቅዱስ ውኃ (ጠበል) መታሠቢያ
3.ቅድስት ትምዳ እናታችን
4.ቅዱስ አውሎጊስ
5.አባ አትካሮን
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት)
††† "ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ::
ግርማው በእሥራኤል ላይ: ኃይሉም በደመናት ላይ ነው::
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::
የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን: ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል::
እግዚአብሔርም ይመስገን:::" †††
(መዝ. ፷፯፥፴፬)