Telegram Web
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በመዓድን ዘርፉ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ለሀገር እድገት ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡
**********************************************
ድርጅቱ በዘርፉ ያሉ ምርትና አገልግሎቶቹን ለህዝቡ አቅርቧል፡፡
(ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም)

"Mintex” ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2022 በሚሊኒየም አዳራሽ ዛሬ ተከፍቷል፡፡

 ዝግጅቱም በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ተጀምሯል፡፡

 ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ፕሮግራሙን በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት እንደነዚህ አይነት መድረኮች የገበያ ትስስር በመፍጠር ፣ በቴክኖሎጂ ልውውጥ እና በመሳሰሉት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል፡፡

 የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከማዕድን ዘርፉ የምታገኘው 1 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው ብለዋል::

ይህን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታም በሚቀጥሉት 10 እና 15 አመታት ወደ 17 በመቶ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 እንግዶቹ ከመክፈቻ ንግግራቸው በኋላ በዘርፉ የቀረቡ ምርትና አገልግሎቶችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የመጀመሪያ ጉብኝታቸውንም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ላይ አድርገዋል፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02KKfFmKmaHUJwHDrGpRTPcmYkTMNBXoy3xg7unDPwMbJnMdCFNm9LcbKqKDnKL3bkl&id=100076612531374
 
የፕሮግራም ጥቆማ
*********************
ከምንወዳቸው የETV መዝናኛ ፕሮግራሞች መካከል በሪያሊቴ ሾው ፎርማት የሚቀርበው ውሎ አዳር አንዱ ነው፡፡
በአንጋፋዋና ተወዳጇ ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ የተዘጋጀና በኤልፎራ አግሮ ኢንደስትሪ ዶሮ እርባታ እና የእንቁላል ምርት ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ለቀጣይ እሁድ ህዳር 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ በETV መዝናኛ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡
የፕሮግራሙን ስፖት (ማስታወቂያ) ሊንከ አስቀምጠናል፡፡
ፕሮግራሙን ሲተላለፍ ጠብቀው እንዲከታተሉም ጋብዘንዎታል፡፡ https://youtu.be/XAjkJC4-bEQ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፕሮግራም ጥቆማ
*********************
ከምንወዳቸው የETV መዝናኛ ፕሮግራሞች መካከል በሪያሊቴ ሾው ፎርማት የሚቀርበው ውሎ አዳር አንዱ ነው፡፡
በአንጋፋዋና ተወዳጇ ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ የተዘጋጀና በኤልፎራ አግሮ ኢንደስትሪ ዶሮ እርባታ እና የእንቁላል ምርት ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ለቀጣይ እሁድ ህዳር 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ በETV መዝናኛ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡
የፕሮግራሙን ስፖት (ማስታወቂያ) ሊንከ አስቀምጠናል፡፡
ፕሮግራሙን ሲተላለፍ ጠብቀው እንዲከታተሉም ጋብዘንዎታል፡፡ https://youtu.be/XAjkJC4-bEQ
2024/09/27 13:51:41
Back to Top
HTML Embed Code: