Telegram Web
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአጋሮ ከተማ ላስገነባው የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ከቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት::
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዶሮ እና የእንስሳት ምርቶቹን በስካላይት ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው ዓውደ-ርዕይ በስፋት አቅርቧል::
**********************************************
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ

ኘራና ኤቨንትስ መቀመጫውን ሱዳን ካደረገው አጋሩ ኤክስፖ ቲም ጋር በመተባበር የዶሮ እና የእንስሳት ሀብት ዓውደ-ርዕይ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በስካላይላይት ሆቴል በይፋ መከፈቱ ይታወቃል፡፡

ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ በተገለጸው በዚህ ዓውደ-ርዕይ ላይ በተለይም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው ኤልፎራ አግሮ ኢንደስትሪስ የዶሮ እና የሥጋ ምርቶቹን በስፋት አቅርቧል፡፡

ዓውደ ርዕዩ ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።
11ኛው የዶሮ ኤክስፖ እና 7ኛው የእንስሳት ሀብት ዓውደርዕይ በወተት፣ በዶሮ እና የሥጋ እሴት ትስስር በመፍጠር፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በማስተዋወቅ፣ የእውቀት ሽግግርን በማምጣት እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዕድሎች ያስተዋውቃል ተብሎ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

በዚሁ የዶሮና የእንስሳት ሀብት ዓውደርዕዩ ላይ ከ10 ሀገራት እንዲሁም ከ 4 ሺህ በላይ የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት እና ባለሙያዎች ጋር የንግድ ግንኙነት የሚፈጥሩበት መድረክ ይሆናልም ተብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በ10 ዓመት የልማት ዕቅዱ የወተት ምርትን ወደ 11 ነጥብ 8 ቢልየን ሊትር፣
የሥጋ ምርትን ወደ 1 ነጥብ 7 ሚልየን ቶን፣
እንቁላል 5 ነጥብ 5 ቢልየን እንዲሁም
የዶሮ ሥጋ ምርትን 106 ሺህ ቶን ለማድረስ አቅዷል።
ይህም የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች የነፍስ ወከፍ ፍጆታን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድን ጨምሮ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና የመንግስት ኃላፊዎች በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቂያ መድረክ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
***************************************
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 19/2015
ዓ.ም አዲስ አበባ

የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን ለባለሀብቶች የሚያስተዋውቅ መድረክ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በተገኙበት የይርጋለምን የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን ለባለሃብቶች የማስተዋወቂያ የኢንቨስትመንት ፎረም በሀዋሳ እየተካሄደ ነው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መምሩ ሞኬ በ2014 ከፓርኩ የአቦካዶ ዘይት ለውጭ ገበያ መቅረቡን ተናግረዋል።

ፓርኩ በአሁኑ ወቅት እሴት የተጨመረባቸው የማር፣ የወተት ፣የቡናና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ለገበያ እንደሚያቀርብም ገልፀዋል።

እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገለጻ በፓርኩ 11 ባለሀብቶች ስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም ሶስቱ በሙሉ አቅማቸው በመስራት ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ናቸው።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0S4qzuyXwYc39NCW2RYf19JMFa7J2rw42zoDXPifvox7eTLVG3T7JD9MFQtJhZSoSl&id=100076612531374
photo_2022-10-30_19-23-48.jpg
151 KB
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የሎሊ ችፕስ ፋብሪካን ጎበኙ
*****
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት
22 ቀን 2015 ዓ.ም

አቶ መላኩ አለበል በይርጋለም ከተማ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን በሚያስተዋውቅ መድረክ ላይ ከነበራቸው ተሳትፎ በኋላ ነበር ጉብኝቱን ያደረጉት፡፡

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ እና የተቋሙ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አካለ ወልድ አድማሱ ፋብሪካውን ለሚኒስትሩ አስጎብኝተዋቸዋል፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሀዋሳ ከተማ ያስገነባውን የሎሊ የችፕስ ፋብሪካ ነሐሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ማስመረቁ ይታወሳል፡፡፡፡
ሎሊ ቺፕስ ፋብሪካ፡-
- የተገነባበት ቦታ ድንች ለማምረት አመቺና ተመራጭ ነው፡፡
-ለችፕስ ምርት እጅግ ተመራጭ የሆነን የድንች ዝርያ በግብዓትነት ይጠቀማል፡፡
-ፋብሪካውን ያስገነባው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባልና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሥር የሚገኘው ሀዋሳ-አግሪ ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ ይባላል፡፡
- እህት ኩባንያው የኤልፎራ እርሻና በድንች አምራችነቱ የታወቀው የአካባቢው አርሶ አደር ግብዓቱን በስፋት ያቀርቡለታል፡፡
-አሁን በስራ ላይ ያለው የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን በቅርቡ ምዕራፍ 2 እና 3 ስራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
- ፋብሪካው አሁን ላይ በቀን 360 ኩንታል ድንች ተጠቅሞ ቺፕስ የማምረት አቅም አለው፡፡
-በአሁኑ ሰዓት 6 ዓይነት ጣዕም ያላቸውን የችፕስ ምርቶች ማምረት የጀመረ ሲሆን በቅርቡ ተጨማሪ 5 ዓይነት ጣዕሞችን ለገበያ ያቀርባል፡፡
-በምዕራፍ አንድ ብቻ ለ242 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡
2024/09/27 16:24:38
Back to Top
HTML Embed Code: