አዕምሮን ወዳጅ ማድረግ ከሁሉ የሚልቅ ወዳጅነት ነው!
(እ.ብ.ይ.)
ዓለማዊው ወይም ውጫዊው ወዳጅነት እና ጓደኝነት ግላዊ ነው፡፡ ወዳጅነት ሁለት ወይም ሶስት ቢበዛ እስከአራት ድረስ የሚደርሱ ሠዎች እርስበርሳቸው የሚያቋቁሙት ፈቃዳዊ ውል ነው፡፡ ጓደኝነት ክፉንም ደጉንም፣ ሃሳቡንም ጭንቀቱንም የሚካፈሉበት መድረክ ነው፡፡
በዚህ ወዳጅነት ውስጥ ሚስጥር መጠበቅ ዋነኛው መስፈርት ነው፡፡ ‹‹አትንገር ብዬ ብነግረው፤ አትንገር ብሎ ነገረው›› የሚለው ብሂል ወዳጅነትን አፈር የሚያስግጥ፤ የሞቀ ጓደኝነት ላይ ውሃ የሚቸልስ ክህደት ነው፡፡ ወዳጅነት ሚስጥርን መጠበቅ ካልቻለ እውነተኛ ጓደኝነት አይሆንም፡፡ በዚህ ዘመን የምናየው አብዛኛው ወዳጅነት ግን እውነተኛ ጓደኝነትን የማይገልፅ ተግባቦት ብቻ ሆኗል፡፡ አንድ ሠው ወዳጅነቱን ለማስፋት ሲል ብዙ ሠዎችን ጓደኛ ያደርጋል፡፡ ለሠው ከብዙ ሠዎች ጋር መግባባቱ ክፋት ባይኖረውም የልብን የሚያዋዩት ሠው ግን አንድ አልያም ሁለት ወዳጅ ግድ ይለዋል፡፡ እውነተኛ ወዳጅ የውስጥን የሚተነፍሱለት፣ ጭንቀትንና ጥበትን ተካፍሎ አዲስ የተስፋ መንገድ የሚያሳይ፤ እንዲሁም አብሮ አዝኖ አብሮ የሚደሠት የልብ ጓደኛ ነው፡፡
አርስጣጢሊስ ‹‹ለሁሉም ጓደኛ የሆነ ለማንም ጓደኛ መሆን አይችልም፡፡›› ይለናል፡፡ እውነት አለው! ከብዙ ሠዎች ጋር በስራ፣ በጉርብትና፣ በዝምድና፣ በተለያዩ ጉዳዮች መግባባትና ማሕበራዊ ሕይወትን መካፈል ደስ የሚያሠኝ ቢሆንም ወዳጅነት ግን በጥቂት ሠዎች ብቻ የሚመሠረት ማሕበራዊ ውል ነው፡፡
የሠው ወዳጅ መልካም ቢሆንም የአዕምሮ ወዳጅ ግን ከሁሉ ይልቃል፡፡ የገዛ አዕምሮን ወዳጅ ማድረግ፣ ከህሊና ጋር ጓደኛ መሆን፣ ከልቦናችን ጋር አለመጣላት ከወዳጆች ሁሉ የበለጠ ወዳጅነት ነው፡፡ አዕምሮን መቅረፅ፣ በአዕምሮ መንገድ መመላለስ፣ ሕሊናን ማርቀቅ፣ ናላን ማጫወት፣ ልቦናን ማትጋት ከሠው ልጅ የሚጠበቅ ትልቅ ተጋድሎ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ተጋዳላይ የምንሆነው ከውጫዊው ሕይወታችን ጋር ነው፡፡
እርግጥ ነው ለመኖር መስራት ይጠበቅብናል፤ ሆዳችንን ለመሙላት መውጣት መውረድ ግድ ይለናል፡፡ ሆኖም ግን አዕምሮን ማስደሰት፣ ሕሊናን ማጥገብ፣ ልቦናን ማርካት እንዳለብንም መዘንጋት የለብንም፡፡ ነፍስያችን የሚደሠተው፣ መንፈሳችን ሐሴት የሚያደርገው ከአዕምሯችን ጋር ተግባብተን እውነተኛ ወዳጅ ስንሆን ብቻ ነው፡፡ የስጋ ፍላጎትን መሙላት ጊዜያዊ ደስታ ሲሠጥ የአዕምሮን ፈቃድ መሙላት ግን የማይነጥፍ ደስታን ያጎናፅፋል፡፡ በሕይወታችን ታላቁን ፍስሃ የምናገኘው ሕሊናችንን አርቅቀን ልባዊ መሻታችንን ስንሞላ ነው፡፡ ስጋ ደንድኖ ሕሊና ቢቀጥን ደስታ አይገኝም፡፡ ቦርጫችን ገፍቶ አዕምሯችን ቢራብ እውነተኛ እርካታ እውን አይሆንም፡፡ ምግባራችን፣ ተግባራችን፣ የሕይወት ምልልሳችን ትርጉም ያለው የሚሆነው ከውስጣችን ጋር ተግባብተን፣ ሕሊናችንን ስለን፣ ከአዕምሯችን ጋር ወዳጅ ስንሆን ብቻ ነው፡፡
ብዙ ሠው ከራሱ ጋር ተጣልቷል፡፡ ግብ ግቡ ቀላል አይደለም፡፡ ገላጋይ የማይፈታው ነው፡፡ ገላጋዩም፣ አስታራቂው ሽማግሌም ሌላ ሳይሆን ራሱና ራሱ ብቻ ነው፡፡ ከራሱ ጋር እርቅ የማይፈፅምና ከሕሊናው ጋር ወዳጅ የማይሆን መጨረሻው አያምርም፡፡ ከአዕምሮው ጋር ፀብ የገባ ሠው ራሱንና ጨርቁን ይጥላል፡፡ በየመንገዱ የምናያቸው የአዕምሮ ሕመምተኞች ከአዕምሯቸው ጋር ጦርነት ገጥመው በሽንፈት እጅ የሠጡ ናቸው፡፡ የአዕምሮውን ሠላም ማስጠበቅ የማይችል ሠው መጨረሻው ከራሱ ጋር መጋጨት ነው፡፡ የዚህም ዋና ምክንያቱ ከአዕምሮው ጋር ወዳጅነት መፍጠር ባለመቻሉ ነው፡፡ ሕሊናውን ከመስማት ይልቅ ዓይቶ ባላየ፣ ሠምቶ ባልሠማ በመሆኑ ነው፡፡ አብዛኛው ሠው ከሌሎች ሠዎች ጋር መወዳጀትን እንጂ ከራሱ ጋር መግባባትን ይዘነጋዋል፡፡ ከራሱ ያልተግባባ ከሌላው ጋር እንዴት ይግባባል??? ከሌላው ጋር ወዳጅ ለመሆን ከራስ ጋር መወዳጀት ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት፡፡ ከውጫዊ ዓለም ጋር ተግባብቶ ለመኖር ከውስጣችን ዓለም ጋር መዋሃድ ግድ ይለናል፡፡
ወዳጄ ሆይ…. አዕምሮን ወዳጅ ማድረግ ከሁሉ የሚልቅ ወዳጅነት ነው! ወዳጅ በማብዛት እውነተኛ ወዳጅነት አይገኝም፡፡ ከራስ ጋር መወዳጀት ግን ከሁሉ የሚበልጥ ዓላማ ያለው ተግባር ነው፡፡ ከራሱ ጋር ወዳጅ የሆነ ከሌላ ሠው ጋር ወዳጅ ሆኖ ፀንቶ ለመቆየት አይከብደውም፡፡ ከራሳቸው ጋር ሳይወዳጁ ወዳጅ የሚያንጋጉ ሠዎች የወዳጃቸውን ሚስጥርና ገበና አደባባይ ያወጣሉ፡፡ ወዳጅነት ልክ፣ ገደብ፣ ወሰንና ድንበር አለውና የጓደኝነት ሚዛኑን በማስተዋል እንያዝ የዛሬው መልዕክት ነው፡፡ ከራስ ጋር መግባባት፣ ከራስ ጋር እርቅ መፈፀም የመግባባትና የእርቆች ሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ከአዕምሮ ጋር መወዳጀት የወዳጅነት ቁንጮ ነው፡፡
ወዳጄ ሆይ ቀድመህ ከራስህ ጋር ታረቅ፤ ቀጥለህ አዕምሮህን ወዳጅ አድርግ! በመጨረሻም ከዓለሙ ጋር ተስማምተህ መኖር የሚያስችልህ ዕውቀትና ልምድን ታገኛለህ! አዲዮስ!
‹‹ከሕሊናህ ጋር ተጨዋወት!
አዕምሮህን ተወዳጀው!
ጠላት አርገኸው!
እንዳይፈጅህ!
እንዳትፈጀው፡፡››
ቸር ወዳጅነት!
ቸር ጊዜ!
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️

ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም!
(እ.ብ.ይ.)
ማንም ሰው ከእውቀት ጋር አልተወለደም፡፡ ሰው ሲወለድ እውቀት የሚያመነጭበትን አዕምሮ ይዞ ነው የተወለደው እንጂ ጥበበኛ ሆኖ አልተወለደም፡፡ ጥበብ ከማሰብ ብዛት፣ ከምርምር፣ ከጥናት፣ ከንባብ የሚገኝ ነው፡፡ ዕውቀት በቅን አስተሳሰብ፣ በበጎ ሕሊና፣ በአዕምሮ ድካም፣ በማሰብ ሂደት፣ የተለያዩ ሃሳቦችን በማስተናገድ የሚመጣ ነው፡፡ እናቱ ሆድ ውስጥ ሆኖ ሁሉን ያወቀ የሰው ልጅ የለም፡፡ ሁሉም ዕውቀትና ጥበብ፤ ክሂልና ልዩ ሃሳብ የተገኘው በመማር፣ በልምምድና በትጋት ነው፡፡
የሰው ልጅ ሲወለድ ማሰቢያ ማሽን ተገጥሞለት ነው የተወለደው፡፡ ይሄ ማሽን የማይታክት፣ የማይደክም፣ የማይሰለች፣ በቀንም ሆነ በሌት ዕረፍት የሌለው፣ መቼም ከስራው የማይዛነፍ ነው፡፡ ሰው ጤንነት ጎድሎት ቢያብድ እንኳን አዕምሮ የእብድ ሃሳብ ከማመላለስና ከመከወን አያርፍም፡፡ አዕምሮ የረባም ሆነ ያልረባን ሃሳብን እንደግብዓት ተጠቅሞ ውጤቱን የሚሰጥ ልዩ ማሽን ነው፡፡ ጥሩ ውጤት ለማግኘት ግን ጥሩ ግብዓት መስጠት ግድ ይላል፡፡ የስንዴ እህል ወፍጮ ቤት ወስዶ የጤፍ ዱቄት መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ የሰጠነውን አሳምሮ የሚሰጥ ነው ውዱ ሐብታችን (Give and take ነው ጨዋታው)፡፡ ያልሰጠነውን አይሰራም፤ የሰጠነው እንክርዳዱንም ቢሆን እህል አድርጎ አያወጣም፡፡
የአዕምሮ ጥሬ እቃ ሃሳብ ነው፡፡ ቁልፉ ደግሞ ማሰብ ነው፡፡ ማሰብና ሃሳብ ደግሞ በአሳቢው ይወሰናል፡፡ የአዕምሮ ቁልፉ ያለው በአዕምሮው ባለቤት በግለሰቡ እጅ ላይ ነው፡፡ ይሄ ቁልፍ ነው ሰውን በሞራል፣ በስብዕና፣ በምግባር ከፍም ዝቅም የሚያደርገው፡፡ ግለሰባዊ የሃሳብ ልዩነት የመጣው የአዕምሮ ምርቱ የተለያየ በመሆኑ ነው፡፡ የተለያየ አዕምሮ እንደአስተሳሰቡና እንደሃሳቡ ይለያያል፡፡ የሃሳብ ልዩነቱ እንዳጠቃቀማችን ይወሰናል፡፡ አዕምሮውን በርግዶ የመክፈትም ሆነ ጠርቅሞ የመዝጋት ፈቃዱ ያለው እያንዳንዱ ግለሰብ ላይ ነው፡፡ አዕምሮ እንዲያስብ ማሳሰብ ያለበት ግለሰቡ ነው፡፡ ጥልቅ አሳቢ ሰው የአዕምሮውን ቁልፍ ለመጠቀም የሚፍጨረጨር ነውና፡፡
አዕምሯዊ ብልጽግና የሃብት ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ በሃሳብ ሳይሰለጥኑ፣ በማሰብ ሳይዘምኑ፣ በቅን አስተሳሰብ ከፍ ሳይሉ ውስጣዊ ብልጽግና አይገኝም፡፡ መርማሪ ሕሊና፣ አመዛዛኝ ልቦና፣ የነቃ አዕምሮ ባለቤት መሆን የሚቻለው በሃሳብ መበልፀግ ሲቻል ነው፡፡ በማሰብ የጠለቀ፣ በሃሳብ የረቀቀ፣ በበጎ ስራ የከበረ አዕምሮ የበለፀገ ነው፡፡ በማሰቡ ሃይል፣ በሃሳቡ ጥልቀት የሚመካ ደግሞ በሃሳብ ይበለፅጋል፡፡ በዚህ ዘመን የሚያስፈልገን የበለፀገ አዕምሮ እንጂ ስሙ ብልፅግና የሆነ ፓርቲ አይደለም፡፡ ፓርቲ የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ አባላቱ ሳይበለፅጉ የፓርቲያቸው ስም ብልጽግና ቢሆን ስምና ግብር ለየቅል ይሆናል፡፡ ስሙ ይቆየን፤ ግብሩ ይቅደመን!
አዕምሮ የሌሎች ሐብቶች ሁሉ ምንጭ ቢሆንም ሰው ሐብት ፍለጋ ከአዕምሮው ኮብልሎ የውጪውን ዓለም ነው የሚያማትረው፡፡ ራሱን የዘነጋ መቼም ቢሆን ከአዕምሮው ጋር ተስማምቶ መኖር አይችልም፡፡ ከራሳችን ጋር መጣላት የምንጀምረው የራሳችንን ሐብት ዘንግተን ሌላ ሐብት ፍለጋ መባከን ስንጀምር ነው፡፡ ያሰብነው ዓለማዊ ሐብት በእጅ ቢገባ እንኳን ያለአዕምሮ አይደላደልም፡፡ በማሰብ ያልተዘጋጀ አዕምሮ እንግዳ ነገር ሲገጥመው መልስ ለመስጠት ደመነፍሱን ይጠቀማል፤ ስሜቱን ያስቀድማል፡፡ ሰው አይደለም ለቁሳዊ ሐብቱ ቀርቶ ለመንፈሳዊ ሐብቱ ጭምር አዕምሮውን መጠቀሙ ግድ ይለዋል፡፡ የደስታና ሐዘን፣ የእርካታና ርሃብ መሰረቱ አዕምሮ ነውና፡፡ ሰላምም ሆነ ጦርነት በዓለማችን ላይ የሚከሰተው አዕምሮን ከማሰራት እና ካለማሰራት ነው፡፡ ነገር ግን የተሰጠን ሐብት ድንቅ ቢሆንም አብዛኞቻችን የሚደነቁ ስራዎችን ያልሰራነው አዕምሯችንን ባለመበልጸጉ ነው፡፡
አዎ በዚህ ዘመን ድንቁን አዕምሮ በበቂና በብቃት የሚጠቀምበት ሰው እምብዛም ነው፡፡ ጥቂት ሰዎች በተለያየ ዘመን ተነስተው አዕምሯቸውን በሙላት ተጠቅመዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው የአለምን አካሄድ የሚቀይር ችግር ፈቺ ሃሳቦችንና ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረው ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡ አዕምሮን በሙላት መጠቀም ከራስ አልፎ ለዓለምም ያስተርፋል፡፡ አይደለም ለሰፊው ዓለም ቀርቶ ለአንድ ሰው እንኳን መትረፍ ደስታው ምን ያህል እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡
ወዳጄ ሆይ.... ከሁሉ ከሁሉ የአዕምሮ መክሊትህን በሙላት ተጠቀም፡፡ አምላክ የሰጠህ ተጠቅመህ እንድታተርፍበት እንጂ ቀብረህ እንድታባክነው አይደለም፡፡ አውቀህ ባትወለድም በንባብ፣ በምርምርና በማሰብ ሃይል እውቀትና ጥበብን በእጅህ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ያገኘኸውን አዕምሯዊ ሀብት ደግሞ ለዓለም አስቀርተህ ወደማይቀረው መሄድ ትችላለህ፡፡ አዕምሮህን በሙላት መጠቀም ስትጀምር ከመምሰል ዓለም ወጥተህ በመሆን ውቅያኖስ ውስጥ ትዋኛለህ፡፡ መሆን እንጂ መምሰልና ማስመሰል የሌለበት ህይወት የምትጎናፀፈው አዕምሮህ ሲበለፅግ ብቻ ነው፡፡ ከፓርቲህ በፊት አዕምሮህን አበልፅግ፡፡ ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም፡፡
‹‹በማሰብ ያልሰለጠነ፣
በሃሳብ ያልዘመነ፣
በሕሊና ያላደገ፣
በቅንነት ያልበለፀገ፣
መክሊቱን ቀበረ፣
አዕምሮውን ከሰረ፡፡››
ቸር የአዕምሮ ብልጽግና!

ሦስቱ ልጆች እና ጥቅል በትሮቹ፤
====================
በአንድ ወቅት አንድ አዛውንት ከሶስት ወንድ ልጆቹ ጋር በአንድ መንደር ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ ሦስቱም ልጆች ታታሪ ሠራተኞች ነበሩ ፡፡ ነገር ግን ሁል ጊዜ እርስ በርሳቸው ይጣሉ ነበር፡፡ አዛውንቱ አባታቸው አንድ ሊያደርጋቸው ብዙ ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡ የመንደሩ ነዋሪዎች ልፋታቸውን እና ጥረታቸውን ቢያደንቁም በጸባቸው ላይ ይዘባበቱባቸው ነበር፡፡
በእንዲህ ያለ ሁኔታ ዓመታት አለፉ። እናም አዛውንቱ አባታቸው ሕመም ገጠመው፡፡ ልጆቹ አንድ ሆነው እንዲቀጥሉ በተደጋጋሚ ነግሯቸው የነበረ ቢሆንም ግን አልሰሙትም፡፡ ስለዚህ ልዩነቶቻቸውን ረስተው አንድነት እንዲኖራቸው ተግባራዊ ትምህርት ሊያስተምራቸው ወሰነ፡፡ እናም ልጆቹን ጠራቸው ፡፡ እንዲህም አላቸው፦ “አንድ ጥቅል እስር ዱላ እሰጣችኋለሁ እያንዳንዱን ዱላ ለይታችሁ ለሁለት ለሁለት ትሰብሩታላችሁ፡፡ ዱላውን በፍጥነት የሚሰብረው የበለጠ ሽልማት ያገኛል" ልጆቹም ተስማሙ፡፡ አዛውንቱም ለእያንዳንዳቸው የ10 ዱላ ጥቅል ሰጣቸው እና እያንዳንዱን ዱላ ወደ ሁለት እንዲከፍሉ ጠየቃቸው፡፡ ዱላዎቹን በደቂቃዎች ውስጥ ሰበሩ፡፡ ልጆቹ በድጋሜ ማን ቀድሞ እንደመጣ እንደገና በመካከላቸው መጨቃጨቅ ጀመሩ ፡፡
ሽማግሌው “ውድ ልጆቼ ጨዋታው አልተጠናቀቀም አሁን ለእያንዳንዳችሁ ሌላ ጥቅል ዱላ እሰጣችኋለሁ፣ ዱላዎቹን ለያይታችሁ ሳይሆን እንደ ጥቅል መስበር አለባችሁ” አላቸው፡፡
ልጆቹም ተስማምተው የዱላውን ጥቅል ለመስበር ሞከሩ፡፡ ምንም እንኳን የተቻላቸውን ሁሉ ቢሞክሩም ጥቅሉን መስበር አልቻሉም፡፡ የተሰጣቸውን ሥራም በአግባቡ መፈጸም አልቻሉም ፡፡ ሦስቱም ልጆች እንዳልቻሉ ለአባታቸው ሪፖርት አደረጉ፡፡
አዛውንቱ አባታቸውም: - “ውድ ልጆቼ ፣ አያችሁ! ዱላዎችን በነጠላ በቀላሉ ወደ ቁርጥራጭ መቀየር ትችላላችሁ፣ ግን ጥቅሉን መስበር አልቻላችሁም! ስለዚህ አንድ ሆነህ ከቀጠልክ ማንም ሰው ምንም ጉዳት ሊያደርስብህ አይችልም ፡፡ ከወንድሞቻችሁ ጋር ሁል ጊዜ ጠብ ትሆናላችሁ፣ ማንም ሰው በቀላሉ ሊያሸንፋችሁ ይችላል፡፡ አንድነት በመካከላችሁ እጠይቃለሁ፡፡
በመጨረሻም ሦስቱ ልጆች የአንድነትን ኃይል በመረዳት ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሁሉም አብረው እንደሚቆዩ ለአባታቸው ቃል ገቡ፡፡
አንድነት ጥንካሬ ነው

በእንግሊዝ እድሜያቸው ከ18 እስከ 65 በሆኑ ሴቶች ላይ በተሰራው አንድ ጥናት ምንም አይነት ሚስጥር ቢሆን ከ10 ሴቶች አራቱ ሚስጥር መጠበቅ እንደማይችሉ ተመልክቷል፡፡ አርባ አምስት በመቶ (45%) የሚሆኑት በልባቸው የሚያስጨንቃቸውን ሚስጥር ለመገላገል ሲሉ የሚያወጡት ሲሆን ኋላ ላይ ግ ን እንደሚጸጽታቸው ተናግረዋል፡፡ ግማሽ ያህሉም ሚስጥር ላለመጠበቃቸው አልኮል መጠጣትን እንደምክን ያት አቅርበዋል፡፡ ሴቶቹ እንዳሉት ሚስጥሩን ለባሎቻቸው፣ ለፍቅር ጓደኞቻቸው፣ ለእናቶቻቸውና በጣም ምርጥ ለሚሉት ሰው ነው የሚናገሩት፡፡
በዚሁ ጥናት ላይ 83 በመቶ (83%) የሚሆኑት ራሳቸውን ታማኝ አድርገው ቆጥረዋል፡፡ በዚህም ከአራት ሶስቱ ጓደኞቻቸውን በፍጹም እንዳልበደሉ ወይም እንዳልካዱ ይናገራሉ፡፡ በጥናቱ ሌላው አስገራሚ ነገር ሴቶች በሳምንት ቢያንስ ሶስት ሐሜቶችን እንደሚሰሙ ተናግረዋል፡፡ ምንም ሆነ ምን ሴቶች ሚስጥር መያዝ የሚችሉት እስከ 47 ሰዓት (ሁለት ቀን) ብቻ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል፡፡
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
በዚሁ ጥናት ላይ 83 በመቶ (83%) የሚሆኑት ራሳቸውን ታማኝ አድርገው ቆጥረዋል፡፡ በዚህም ከአራት ሶስቱ ጓደኞቻቸውን በፍጹም እንዳልበደሉ ወይም እንዳልካዱ ይናገራሉ፡፡ በጥናቱ ሌላው አስገራሚ ነገር ሴቶች በሳምንት ቢያንስ ሶስት ሐሜቶችን እንደሚሰሙ ተናግረዋል፡፡ ምንም ሆነ ምን ሴቶች ሚስጥር መያዝ የሚችሉት እስከ 47 ሰዓት (ሁለት ቀን) ብቻ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል፡፡
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
7 ነገሮችን አስታውስ!
1. ከሕልምህ እንጂ ከሰዎች ኋላ አትሂድ፣
2. ራስህን አፍቅርና ሌላው ይከተልሃል፣
3. የማድነቅ ስሜትህን ፍጹም አትተዉ፣
4. ከምታውቀው በላይ ትችላለህ፣
5. በሕይወት መፀፀት የለም፤ ትምህርት መውሰድ እንጂ፣
6. ብቸኛው ወሰን ራስህ ነህ፣
7. ሕይወት ከመቅፅበት ትጠፋለች።
ስለሆነም ሕይወትን ኑር!
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
1. ከሕልምህ እንጂ ከሰዎች ኋላ አትሂድ፣
2. ራስህን አፍቅርና ሌላው ይከተልሃል፣
3. የማድነቅ ስሜትህን ፍጹም አትተዉ፣
4. ከምታውቀው በላይ ትችላለህ፣
5. በሕይወት መፀፀት የለም፤ ትምህርት መውሰድ እንጂ፣
6. ብቸኛው ወሰን ራስህ ነህ፣
7. ሕይወት ከመቅፅበት ትጠፋለች።
ስለሆነም ሕይወትን ኑር!
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
የራስን የማጋነን አባዜ
👉ለፍተን ያገኘነው ነገር እና በስጦታ ያገኘነው ነገር ልዩነት የሚፈጥርብን ለምንድነው? ስለገንዘብ ነው እማወራው። አብዛኛዎቻችን 2ሚሊዮን ብር ሎተሪ ቢወጣልን የምንጠቀምበት መንገድ የተለየ ነው። ቤት እንገዛለን ወይም እንዝናናበታለን ዱባይ ወይ ፓሪስ ቲኬት ቆርጠን አሪፍ የመዝናኛ ፓርክ ውስጥ እናሳልፋለን። ምን አገባን ገንዘቡ ቢያልቅ ለፍተን አላመጣነው። በአለም ላይ በተደረገ ጥናት ሎተሪ የሚደርሳቸው ሰዎች ስለገንዘቡ ግድ እንደማይሰጣቸው እና የትም ቢጠፋ ምንም እንደማይመስላቸው አረጋግጠዋል። ሎተሪ የደረሳቸውን ሰዎችም ህይወት ሲመረመር ተመልሰው የነበሩበት ላይ ተገኝተዋል።
👉ነገር ግን በተመሳሳይ 2ሚሊየን ብር ለፍታችሁ ብታገኙት ምን ታደርጋላችሁ? ወይ ባንክ ታስቀምጣላችሁ ወይ የሆነ ስራ ላይ ታፈሱታላችሁ ወይም ደግሞ ትቆጥቡታላችሁ። ሮልፍ ዶብሊ እንደዚህ ሲል ይጠይቃል ፦ ለፍታችሁ ያመጣችሁትም 2 ሚሊዮን ብር በስጦታ የተበረከተላችሁም 2 ሚሊዮን ብር አንድ ነው። ለፍታችሁ ስላመጣችሁት የሚቀየር ብር የለም ይላል።
👉ይሄ ነገር ብዙዎቻችን ላይ ይሰራል በበአል ቀን በልደት ቀን የምናገኛቸውን ብሮች ቤተሰብ የሚሰጠንንም ብር የትም ለማጥፋት ግድ አይሰጠንም። ይህ የራስን የማግነን አባዜ ኪሳራ ውስጥ ይጥለናል። በነገራችን ላይ እኛ ለፍተን ከምናመጣው ብር በላይ በስጦታ እና በተለያዩ የበአል ዝግጅቶች ላይ የምናገኛቸው ብሮች ብዙ ናቸው። እናም ገንዘብን መቆጠብ እና በትክክለኛ ቦታ ላይ ማዋል አግባብ ነው። ለፍታችሁ አመጣችሁትም ሳትለፉ ብር ብር ነው። ስለሆነም በትክክለኛው እና አግባብ በሆነው ቦታ ላይ አስቀምጡት። መልካም ምሽት እወዳችሁዋለው❤️

ሁለቱ ሰካራሞች
👉ሁለት ሰካራም ቀዛፊዎች ለሊት መድረስ ያለባቸው ቦታ ቢኖርም ትንሽ ለማረፍ ብለው ከአንድ መጠጥ ቤት ገብተው መጠጣት ጀመሩ እናም እንደመስከር ሲያደርጋቸው ተነስተው ጉዞ ለመጀመር ወደ ጀልባቸው አመሩ እናም መቅዘፊያቸውን አንስተው ውሀውን ቢከፍሉትም ካሉበት መንቀሳቀስ አልቻሉም። ቡዙ ሰአት ቀዘፉ ነገር ግን ካሉበት አልተንቀሳቀሱም። እሚደርሱበት አላቸው መንገዳቸውን ያውቁታል ጀልባውም አላቸው ነገር ግን አንድ ነገር ዘንግተው ነበር ጀልባዋ የታሰረችበትን ገመድ መፍታት።
👉አብዛኛዎቻችሁ ወጣቶች እንደነዚህ ናችሁ። አላማ አላችሁ፣ መሄጃችሁን ታውቃላችሁ፣ ህልማችሁም ተገልጦላችሁዋል። ነገር ግን ካላችሁበት እንዳትንቀሳቀሱ ያደረጋችሁ የሆነ ነገር አለ። ፀባያችሁ ፣ ልማዳችሁ ፣ ቤተሰብ ፣ አጉል ጉዋደኛ ፣ ሱስ፣ ሴሰኝ ነት። የተለያዩ ነገሮች አሉ። አለማን ብቻ ማወቅ ወዳሰብነው አያደርሰንም። አላማህን ለማስፈፀም እና ወዳሰብከው ለመድረስ መክፈል ያለብህን ዋጋ ሁሉ መክፈል ይኖርብሀል። ለአዚያ እንደነዚህ ሰካራሞች ትሆናለህ። ጀልባ ኖሮህ ምትሄድበትን አውቀህ ፣ መቅዘፊያ ኖሮህ ፣ ውሀው የተረጋጋ ሆኖ ነገር ግን የጀልባዋን ማሰሪያ ባለመፍታትህ ብቻ ትቆማለህ። ስለዚህ የያዘህ ምንድነው? ልቀቀው። ቤተሠብም ይሁን ጓደኛ ወይም ፍቅረኛ ብቻ ማንም ይሁን ካሰብከው አላማ እና ግብ እሚያስቆምህ መሰናክል ከሆነ ህይወት ላይ ምን ይሰራል ? እውነቴን ነው።።
👉የማላደርገውን አልነግራችሁም። ማንም በኔ ህይወት ላይ ዋጋ የሌለው መስሎ ከተሠማኝ እና ከምሄድበት የሚያስቀረኝ ከሆነ እቆርጠዋለው። ብዙዎቹንም ቆርጫቸዋለው። ከምወዳቸው ጀምሮ። ስለዚህ አላማዬን ሁሌም አሳድደዋለው እናም እይዘዋለው። የራቀኝ ቢመስለኝም ከትላንትናዬ አንድ እርምጃ እንደቀረብኩት አስባለው።ዛሬ ላይ የፈለኩበት ቦታ ባልደርስም ከትላንትናዬ አንድ እርምጃ እንደቀረብኩት አውቃለው። የፈጀውን ይፈጃል እንጂ እደርስበታለው። ምክንያቱም ብዙ ዋጋ ከፍዬበታለው ጀልባዬን እያሰረ ያስቸገረኝን ዛሬ ላይ ሚጠቅም የመሠለኝን ነገር ነገዬን እማያሳየኝን ሁሉ በጥሼዋለው። ነገም እየበጠስኩ እሄዳለው።
👉አንተ ከምቾትህ ሳትወርድ ነው አቃተኝ እምትለው ስለዚህ ውጣ ከምቾትህ።

ቋንቋችን “ጊዜ” ይባላል!
አንድን ሰው ከልባችሁ የምታከብሩት ከሆነ ቀላሉ መመዘኛ የዚያን ሰው ሰዓት ወይም ጊዜ የማክበራችሁና ያለማክበራችሁ ጉዳይ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ለዚያ ሰው ስትሰጡት ያንን ሰው እንደምታከብሩት መልእክትን እያስተላለፋችሁ ነው፡፡ ገንዘብ፣ ቁሳቁስና የመሳሰሉት ነገሮቻችሁን ለማንም ሰው ልትሰጡ ትችላላችሁ፣ ጊዜያችሁን (በተለይም የተጣበበውን) ግን ለሚከበርና ለመወደድ ሰው ነው የምትሰጡት፡፡
አንድ ስራ በትክክል ከተከናወነ ወሳኝ የሆነ ጥቅም እንዳለው ስታምኑ ስራውን በሰዓቱ ጀምራችሁ በሰዓቱ ታጠናቅቁታላችሁ፡፡ ስለሆነም፣ ግድ ከማይሰጣችሁ ስራ ጊዜን እየወሰዳችሁ ለምታከብሩትና ጥቅም ላለው ታውሉታላችሁ፡፡
ማሰተካከያ ልናደርግበት የሚገባን ቀውሰ ያለው እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፡፡ የአብዛኛዎቻችን የግንኙነት ቀውሶች፣ በስራ ስኬታማ ያለመሆንና የመሳሰሉት ቀውሶች መነሻቸው ለምንወደውና ለእኛ ወሳኝ ለሆነ ሰውም ሆነ ስራ ተገቢውን ጊዜ አለመመደብና አለመስጠት ነው፡፡ ይህ ቀውስ ብዙ ጠቃሚ የሆኑ ሰዎችንና ስራዎችን ከእጃችን እንዲወሰዱ ያደርገናል፡፡
ይህንን አትርሱ፣ ማንኛውም ሰው ሆነ ስራ እኛ ተገቢውን ጊዜና ትኩረት ካልሰጠነው ተገቢውን ጊዜና ትኩረት የሚሰጡት ሰዎች “ላፍ” አድርገው ይወስዱታል፡፡
ጊዜያችሁን ለምትወዱት፣ ለምታከብሩትና ቅድሚያ ለምትሰጡት ሰው ስትሰጡ ተገቢውን ምላሽ ታገኛላችሁ፡፡ ተገቢውን ምላሽ ካላገኛችሁ ደግሞ ግንኙነታችሁን እንደገና ማጤንና ማስተካከያ ማድረግ የግድ ነው፡፡
ዋጋ ለምትሰጡት ስራም ቢሆን ጊዜ ስትሰጡት ስራው ውጤትን በመስጠት ይመልስላችኋል፡፡ ስራው ጊዜያችሁን እየወሰደ ውጤት የማይሰጣችሁም ከሆነ ደግሞ ስራው እንደገና ሊቃኝ ይገባዋል፡፡
ለዚህ ነው “ጊዜ” የመግባቢያ ቋንቋ ነው የምንለው፡፡@mihret_debebe

👉 ሚስትህን የዘወትር ልብሱዋን ለብሳ እንጂ ተብለጭልጫ አትምረጣት። ለምን መሰለህ በዚህ በወጣትነት ጊዜያችን ላይ ለፍቅር የምንመርጣቸውን አካላት በቤታችን ሳይሆን በአደባባይ ነው እምናያቸው። እናም በአደባባይ ሁላችንም አምረን እና ተውበን ነው የምንወጣው። በቤታችን ውስጥ ግን በፓንትም ልንቀመጥ እንችላለን። ሁሌም ቢሆን የኔ የምትላት ወይም የኔ የምትይው ፍቅረኛሽን በአደባባይ ባለው ማንነቱ ሳይሆን እቤት ውስጥ ባለው እሱነቱ ምረጭው። በአደባባይ የሚያስከብርሽ ሆኖ በቤት ውስጥ የሚያንቋሽሽ ፍቅረኛ ከሆነ ያለሽ ህይወትሽ የተበላሸ ይሆናል። አንድ ነገር ማወቅ አለባችሁ አሁን እና ነገ ፈፅሞ አንድ አይደለም። ምን ማለት መሰላችሁ ዛሬ በአደባባይ በማንነቱ ያከበራችሁ ባላችሁ በቤቱ የተለየ ነው እሚሆነው።
👉የሚስትህን ሞያ ለማወቅ እናቲቱን ተመልከት ይባላል አይደል። ምን ማለት መሰለህ ሁሉም እሚገለጠው በጓዳ ቤት ውስጥ ስለሆነ ነው። ሁሌም የኔ ከምትሉት የፍቅር አጋራችሁ ጋር ግልፅ ሆናችሁ ተነጋገሩ። ለምን እንዳፈቀራችሁ። ስለ ፀባያችሁ ስለ ቤት ማንነታችሁ ስለእያንዳንዱ ድካማችሁ እና ጥንካሬያችሁ ተወያዩ ምክንያቱም ነገአችሁን ለማሳመር የምትፈልጉ ከሆነ የግድ ያስፈልጋችሁዋልና ነው።
👉አብዛኛውን ጊዜ ፍቅረኛዬን መጠየቅ እምፈልጋቸው ጥያቄዎች አሉ ነገር ግን እንዳይቀየመኝ እና እንዳይደብረው እንዳላስከፋው ስል ዝም እላለው ይሉኛል። እንደዚህ አይነት የአይምሮ መሸማቀቅ በፍቅረኞቻችሁ ፊት ማስተናገድ አይገባችሁም አግባብም አይደለም። ስለዚህም ሲባል ይህንን በማስተካከል ስለፍቅራችሁ ስለ ድካማችሁ አውሩ። እወዳችሁዋለው መልካም ቀን🙏
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
👉የሚስትህን ሞያ ለማወቅ እናቲቱን ተመልከት ይባላል አይደል። ምን ማለት መሰለህ ሁሉም እሚገለጠው በጓዳ ቤት ውስጥ ስለሆነ ነው። ሁሌም የኔ ከምትሉት የፍቅር አጋራችሁ ጋር ግልፅ ሆናችሁ ተነጋገሩ። ለምን እንዳፈቀራችሁ። ስለ ፀባያችሁ ስለ ቤት ማንነታችሁ ስለእያንዳንዱ ድካማችሁ እና ጥንካሬያችሁ ተወያዩ ምክንያቱም ነገአችሁን ለማሳመር የምትፈልጉ ከሆነ የግድ ያስፈልጋችሁዋልና ነው።
👉አብዛኛውን ጊዜ ፍቅረኛዬን መጠየቅ እምፈልጋቸው ጥያቄዎች አሉ ነገር ግን እንዳይቀየመኝ እና እንዳይደብረው እንዳላስከፋው ስል ዝም እላለው ይሉኛል። እንደዚህ አይነት የአይምሮ መሸማቀቅ በፍቅረኞቻችሁ ፊት ማስተናገድ አይገባችሁም አግባብም አይደለም። ስለዚህም ሲባል ይህንን በማስተካከል ስለፍቅራችሁ ስለ ድካማችሁ አውሩ። እወዳችሁዋለው መልካም ቀን🙏
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
💎ለነገሮች ብቁ አይደለሁም ብለህ አትሽሽ፡፡ሳትሞክር ብቁ መሆን አታውቅም፡፡
ደጋግመህ ሞክር!አሸናፊነት የሚገኘው ባለመውደቅ ሳይሆን ወድቆ በመነሳት በመሞከር ነው፡፡
ጀግኖች ሁሉ ወድቀዋል ግን ተነስተው የአለማችንን ታሪክ ቀይረዋል።
ተመልከት ከዚህ ሰው የበለጠ ምን ምስክር ይኖራል ኒክ የማይሰራው የለም በመሞከሩ አለምን ሁሌም ያስደምማል።
አንተስ/አንቺስ ምን አለ በውስጥሽ/ህ ?💎
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
ደጋግመህ ሞክር!አሸናፊነት የሚገኘው ባለመውደቅ ሳይሆን ወድቆ በመነሳት በመሞከር ነው፡፡
ጀግኖች ሁሉ ወድቀዋል ግን ተነስተው የአለማችንን ታሪክ ቀይረዋል።
ተመልከት ከዚህ ሰው የበለጠ ምን ምስክር ይኖራል ኒክ የማይሰራው የለም በመሞከሩ አለምን ሁሌም ያስደምማል።
አንተስ/አንቺስ ምን አለ በውስጥሽ/ህ ?💎
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
#ምክር •••••••
✅በጣም ብዙ የምትናገር ከሆነ ፤ ትዋሻለህ።
✅በጣም ብዙ የምታስብ ከሆነ ፤ ድብርት ውስጥ ትገባለህ።
✅ በጣም ብዙ የምታለቅስ ከሆነ ፤ የአይን እይታህን ታጣዋለህ።
✅ በጣም ብዙ የምታፈቅር ከሆነ ፤ ማንነትህ ይጠፋል።
✅በጣም ብዙ ስለሰዎች የምታስብ ከሆነ ፤ ዋጋህን ሰዎች እያጡት ይመጣሉ።
✅ በጣም ብዙ የምትጫወት ከሆነ ፤ አብዛኛውን ጊዜ ማንም ከቁምነገር አይቆጥርህም።
✅በጣም ብዙ የምታምን ከሆነ ፤ በሰዎች ትካዳለህ።
✅በጣም ብዙ የምትሰራ ከሆነ ፤ በውጥረት ትሞታለህ።
✅ በጣም ብዙ የምትመገብ ከሆነ ፤ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ውስጥ ትገባለህ።
✅በጣም ብዙ እንቅልፍ የምትተኛ ከሆነ ፤ ስራ ፈት ትሆናለህ።
✅በጣም ብዙ ገንዘብ የምታባክን ከሆነ ፤ የወደፊት ነገር ምንም አይኖርህም።
✅ በጣም ብዙ ሜክፕ የምትጠቀም ከሆነ ፤ የአንተን ውበት እያጣኋው ትመጣለህ።
✅ በጣም ብዙ ነገር የምትመለከት ከሆነ ፤ ትኩረትህን እያጣኸው ትመጣለህ ።
✅በጣም ብዙ ስለ ህይወት የምታስብና የምታሳድድ ከሆነ ፣ ሁሉንም ነገርህን ታጣለህ።
🔰 በጣም ብዙ ነገር የምትጠብቅ ከሆነ ፤ በጣም ትከፋለህ። በጣም ብዙ አትሁን ምክንያቱም ያ በጣም ብዙ ነገር ብዙ ይጎዳሀልና።

♦ልብ በሉ የሰው ልጅ ብቸኛ ነው የሚባለው ከፈጣሪ ሲርቅ ብቻ ነው ...
✳ በዙሪያህ ሰው ያጣህ ቀን ራስህን ወዳጅ የሌለው ብቸኛ ሰው አርገህ በፍፁም እንዳትጨነቅ ፤ ሰው ብቸኛ ነው የሚባለው ከፈጣሪው ሲርቅ ነውና ፤
ወዳጄ አንተ እንደ መፃጉ ሰው የለኝም ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ይሆናል ግን አስተውል " አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም" ተብሎ ተፅፏል ።
ትናንት አጃቢ የበዛልህ ሰው ነበርክ ዛሬ ግን ብቻህን ቁመህ ይሆናል በዚህም ብዙ አትደነቅ ከክርስቶስ እጅ እንጀራ እና አሳ በበረከት ሲበሉ የነበሩ ሰዎች መች በመከራው ጊዜ በቀራንዮ አደባባይ ከርእሱ ጋር ቆሙ ታዲያ ሕይወት ለሰጣቸውና ምግበ ነብስ ምግበ ሥጋ ለሆነላቸው ለክርስቶስ ያልሆኑ ሰወች እንዴት ለእኔ አልሆኑም ብለህ ትገረማለህ ?
አይንህን ገልጠህ ልብህን ከፍተህ አስተውል #ሰው ማለት ሸንበቆ ነው ከተደገፍከው ይሰበራል ተሰብሮ እንኳ አይተውህም ስለተደገፍከኝ ነው የተሰበርኩት ብሎ ስባሪውን አሹሎ ውስጥህ ድረስ ይወጋሀል ፤ እናም ወዳጄ በጆሮህ ሳይሆን በልብህ ስማኝ ዘመድ ወይም ታማኝ ጓደኛ ላይኖርህ ይችላል ግን ከሁሉ በላይ ሆኖ ሁሉን የሚገዛ #አልፋና_ኦሜጋ ኋለኛው እና መጨረሻው እኔ ነኝ ያለው አንተን ከፍ አርጎ የሚሾምህ ፈጣሪ ስላለህ ወዳጅ አዝማድ ስለማጣትህ በፍፁም እንዳትጨነቅ ዮሴፍን ወንድሞቹ በግፍ ሸጠውት ወደ ግብፅ ሲወርድ ማንም ሰው አልነበረውም #ፈጣሪ ግን በጲጥፋራ ቤት በባዕድ ሀገር ገዥ አድርጎ ሾሞታል ።
በዚ እኔና አንተም ባለንበት ዘመንም ዛሬም ድረስ በሰዎች ተንኮል ብዙዎች ይሸጣሉ ፣ ይገፋሉ ፣ ይሰደዳሉ ፈጣሪ ደግሞ በፍቅሩ ገዝቶ መገፋትህን ገፍቶ በምድሩ ይሰበስብሀል እናም ወዳጄ ጊዜን አይቶ የማይከዳ ዘመን የማይለውጠው ምንጊዜም ሰው ለሌላቸው ቀድሞ የሚደርስና ስላንተ ካንተና ከሰወች በላይ የሚጨነቅልህ የነብስህ ጌታ የሆነው ዘላለማዊው ፈጣሪ አለህና ስጋህን አይተው ለሚቀርቡህና ለሚርቁህ ስጋ ለባሽ ፈራሽ ሰወች ስለማጣትህ በጭራሽ የሰናፍጯን ቅንጣት ታክል ጭንቀት እንዳይገባህ በሱ በፈጠረህ ብቻ የሰናፍጯን ቅንጣት ታክል እመን ያኔ ብቻህን ሆነህ እልፍ ትሆናለህና ።
ሼርርርር።።።።።

💚💛❤#Good__night 💚💛❤
* ስኬታማ ሰወች ከንፈር ላይ #ሁለት ነገር ይስተዋላል !
1ኛው ↩«#ዝምታ» ሲሆን
2ኛው ↩ «#ፈገግታ» ነው።
ስኳርና ጨው አንድ ላይ አደባልቀህ መሬቱ ላይ ብታስቀምጥ ጕንዳኖች ጨውን ትተው ስኳሩን ልሰውት ይሄዳሉ።
✔ ወደጆቼ ሆይ እናንተም ህይወታችሁን የሚያጣፍጥላችሁን ሰው ምረጡና ጣፋጭ ኑሮን ኑሩ።
✔ ግብህ ጋ መድረስ ከተሳነህ ግብህ እንጅ ተስፋህ አይቀየርም።
✔ ዛፎች ቅጠሎቻቸውን እንጅ ስሮቻቸውን አይቀይሩም።
✔ክብር መስጠት ላለብህ ጉዳዮች ላይ ክብር ስጥ።
✔ ቀለል ማድረግና አንዳንዴም ማለፍ ላለብህ ጉዳዮች ላይ ጊዜህን አታባክን።
#ልብ ይበሉ አዳዲስ መፃፅፎች በየ ሰዓቱ ከፈለጉ
ፔጁን ሼር፣፣ 🏆

ለማሰብ እንፈራገጥ!
የትም አገር ብትሄዱ ያልነቃ ሕዝብ መሆን ከባድ ነው። ሕዝብ ለማሰብ ካልተፈራገጠ ከሰል ነው። [የሚሆነው] ከሰል ወጥ ይሰራልጂ ከሚሰራው ወጥ የሚደርሰው(የሚያገኘው) ነገር የለውም!
ለማሰብ ያልተፈራገጠ ሕዝብ ያጨበጭባል ለምን? እንደሚያጨበጭብ አያቅም ይኖራል ለምን? እንደሚኖር አያውቅም ለማሰብ እንፈራገጥ!

አንዳንድ አስቀያሚ የሕይወት ዕውነቶች
◄▸► ◄▸► ◄▸◄ ◄▸◄ ◄▸ ◄▸ ◄▸
1. አንዳንድ ጓደኞችህ እና ዘመዶችህ ውድቀትህን እና መውደቅህንን በድብቅ እየጠበቁ ናቸው። አንዳንዶች መልካም እየተመኙልህ ሊሆን ይችላል። እና ፣ ጥሩ ስትሰራ ማየት ይፈልጋሉ ።ነገር ግን፣ ከእነሱ የተሻለ እየሰራህ ከሆነ እሱን ላይፈልጉ ይችላል። ስለዚህ ምንም አይነት ነገር ቢደርስብህ መጥፎ ጊዜህን ከጓደኞችህ ወይም ከዘመዶችህ ጋር ቢሆንም በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አታካፍል።
2. ወላጆችህ ካልሆኑ በስተቀር ሕይወትህ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማንም አያስብም። ትግላችሁን ለራሳችሁ አድርጉ እና በህይወት ውስጥ ግፉ። ሰዎች በማማረርህን በአቤቱታህን ሰልችተዋል ነገርግን ለአንተ ላለመናገር መርጠዋል።
3. ብዙ ሰዎች አይለውጡም ግን ያስመስላሉ። ብዙዎች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ይከዱሃል። ነገር ግን ፣ በፍቅር በመውደቅ ወይም ሰዎችን በማመን እራስዎን አይወቅሱ ዝም ብለህ ቀጥል።
4. ሁልጊዜ የምትፈልገውን አታገኝም እና የምትጸልይላቸው አብዛኛዎቹ ነገሮች አይፈጸሙም። ነገር ግን ይህ ከመጸለይ ሊያግድዎት አይገባም ምክንያቱም ጸሎት ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ይሰራል።
5. ደስታ ለዘላለም አይቆይም ሀዘንም ለዘላለም አይቆይም። ሕይወት ለእርስዎ ምንም ያህል ከባድ ወይም ጥሩ ቢሆንም ፣ ለዘላለም እንደማይሆን ያስታውሱ። ደስታ በሀዘን እና ጭንቀትን ይተካል። በተጨማሪም ሀዘን እና ጭንቀት በደስታን ይተካሉ። ይህንን ቀደም ብለው ባወቁ መጠን ህይወትዎ የተሻለ እና ያነሰ ጭንቀት ይሆናል።
6. የቱንም ያህል ቆራጥ፣ ትኩረት ወይም ደፋር ብትሆን ሕይወት በእርግጠኝነት ይሰብርሀል። በህይወት ውስጥ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ትወድቃለህ እና ትበሳጫለህ። የእርስዎ እቅዶች፣ ህልሞች እና ምኞቶች አንዳንድ ጊዜ አይሰሩም። ግን መንቀሳቀስዎን ይቀጥሉ እና የተሻሉ ቀናት እየመጡ መሆኑን ልብ ይበሉ።
7. ሁሉም ሰው ስለ ምንም ስለማያውቀው ነገር አስተያየት አግኝቷል እና ብዙ አላዋቂዎች ሲሆኑ, ብዙ አስተያየቶች ይኖራቸዋል, ምክንያቱም ገደቦች ሁል ጊዜ የሚጣሉት በእውቀት ክፍተቶች ነው።
8. ስሜቶች ከተቆጣጠሩትህ አንተነትህን ቀድመህ አተሀል። ስሜትህ ጠላትዎ ሊሆኑህ ይችላል,። ለስሜት ራስህን ከሰጠህ, እራስህን ታጣለህ, ምክንያቱም ሰውነት ሁል ጊዜ አእምሮን ስለሚከተል።
9. ትልቅ ውሸት ከተናገርክ እና ብትደግመው ሰዎች በመጨረሻ ያምኑታል። ፖለቲከኞችን ጠይቋቸው የተሻለ ይነግሩዎታል።
10. የቱንም ያህል ጠንካራ ብትሆን ደካማ እንድትሆን የሚያደርግህ ሰው አለ።
ተጨማሪ ፅሁፎችን ለማግኘት ቴሌግራምችንን ይጓብኙ ብዙ ይማራሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

መልካም ስራ የክፉ ቀን ስንቅ ይሆናል!
---ጎጆሽ ይሻላል ንብረትሽ
ውብአለም ተመለሺ---------
የአበበ መለሰ - እውነተኛ ገጠመኝ
ትልቅ ሰውዬ ናቸው። በናዝሬት አንድ መዝናኛ በር ላይ ቆመው "ልጆቼ ሀገሬ መግቢያ አጥቼ ነው አግዙኝ" እያሉ ይማፀናሉ።
......
በቦታው የነበረው በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ታላቅ ስም ያለው የዜማው ምንጭ አበበ መለሰ ይህንን የሰውየውን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ። በርግጠኝነት ይህንን ድምፅ ያውቀዋል።
.......
እናም ለማረጋገጥ እርዳታ ይጠይቁ የነበሩትን ሰውዬ አተኩሮ እያያቸው አባቴ ምን ሆነው ነው ሲል ጠየቃቸው። ሰውየውም ለአንድ ጉዳይ ከሚኖሩበት ቦታ መጥተው አሁን መመለሻ አጥተው እንደተቸገሩ ነገሩት።
.........
አበበ አሁን ማን እንደሆኑ እርግጠኛ ሆነ። ይህ ድምፅ የአያ ትርፌ ድምፅ ነው። ወንበር ስቦ ካስቀመጣቸው በኋላ ይጠይቃቸው ጀመር ።
አባቴ፦ ስምዎት አያ ትርፌ ነው አይደል?
አዎ አሉ
ጎጃም ውስጥ የጁቤ አይደል የሚኖሩት?
ልክ ነህ ልጄ
እኔ አበበ እባላለሁ። ከብዙ አመታት በፊት እርሶ ቤት እመጣ ነበር።
አያ ትርፌ አላስታወሱትም ።
አበበ ግን በደንብ አውቋቸዋል።
እኚህ አሁን ከሀገራቸው ወጥተው መመለሻ በማጣት ሲለምኑ ያገኛቸው ሰው የያኔው የጮማው፣ የቅቤው፣ የእርጎውና የማሩ ጌታ አያ ትርፌ ናቸው። እኚህ ሰው አደለም ለራሳቸው ለሰውም ይተርፉ የነበሩ ሲሆኑ አበበንም ጥብስ ከጥሬ እያበሉ ለወራት እንግዳቸው አድርገውት ነበር።
....
ከብዙ አመታት በፊት በ1974 ዓ.ም ላይ የአሁኑ ታዋቂ የያኔው ወጣት አበበ መለሰ የገጠሩን ህብረተሰብ ለማስተማርና ለመርዳት ሲባል ታውጆ በነበረው ዘመቻ ምክንያት ጎጃም ውስጥ የምትገኝ የጁቤ የምትባል የገጠር ከተማ ዘምቶ እያለ ነበር እኚህን ሰው የሚያውቃቸው።
.....
አያ ትርፌን የዛኔ ሲያውቃቸው የሞላ ኑሮ ያላቸው ወጣት ከምትባል ሚስታቸው ጋር በፍቅር የሚኖሩ ሰው ወዳጅ ሰው በልቶ የሚጠግብ የማይመስላቸው ነበሩ ።
....
ዛሬ ሀገራቸው መግቢያ አጥተው በችግር ከስተው እና ጠቁረው ፊቱ ቆመው ሲለምኑ ድንገት ያገኛቸው አያትርፌ ያኔ ወዛቸው የሞላ ፡ ደስተኛ ትዳር ፡ ውብ የሆነች ሚስት የነበራቸው ፡ የተከበሩ አባወራ ነበሩ።
......
አበበ ሰውየውን አጠገቡ አስቀምጦ የትና መቼ ያውቃቸው እንደነበር ነገራቸው።
ለመሆኑ ለምን መጥተው ነው
አይ ታሪኩ ብዙ ነው ልጄ ብለው ይነግሩት ጀመር ፡ አያ ትርፌን ከቀዬያቸው አርቆ ፡ ለችግር የዳረጋቸው የሚወዷት ሚስታቸው ድንገት ከቤት መጥፋት ነበር።
......
ድንገት አንድ ቀን ከእርሻ ውለው ቤት ሲመለሱ ፡ ያቺ ምድጃውን ለኩሳ ፡ ቡና አቅርባ ፡ ቤቱን አሙቃ ትጠብቃቸው የነበረች ሚስታቸው ውባለም የለችም ።
.....
ትመጣለች ብለው ጠበቋት ።
.....
ውባለም ርቃ ሄዳለች ።
.........
ካሁን አሁን ከዛሬ ነገ ትመለሳለች ብለው በር በሩን የሚያዩት አያ ትርፌ የውባለም ወጦ መቅረት እውን ቢሆንባቸው እሳቸውም በራቸውን ዘግተው ፍለጋ ወጡ።
...........
አዲስ አበባ ታየች ሲባል አዲስ አበባ ሄደው ውባለሜን አያችሁ ወይ ሲሉ በከንቱ ደከሙ።
....
ሀረር ታየች አሏቸው
......
አያትርፌ ፡ ውቧ ሚስታቸው ውባለም ታይታለች ወደተባለበት ሀረር ተጓዙ።
....
ሀረርም የለችም።
......
በዚህ መሀልም እህልና ከብቶቻቸውን ሽጠው የያዙት ገንዘብ አለቀ።
እንደምንም አዳማ ደረሱ።
...
የሞላ ኑሮ የነበራቸውን እኛ የተከበሩ ሰው ችግር አሸንፎ የሰው ፊት እንዲያዩ አደረጋቸው።
.....
በዚህ ሁኔታ ልጆቼ ሀገሬ መግቢያ አጥቼ ነው እያሉ ሲለምኑ ከአመታት በፊት መልካም ካደረጉለት ከአበበ መለሰ ጋር ተገናኙ።
....
አቤ ይህንን አሳዛኝ ታሪክ ከሰማ በኋላ አያትርፌን ሳንቲም ሰጥቶ አልሸኛቸውም።
ይዟቸው ያረፈበት ቦታ ሄደ። ተጎሳቁለው የነበሩት አያ ትርፌ ፡ ሻወር ወሰዱ ፡ ልብሳቸው በአዲስ ተቀየረ።
....
ድንገት ሳያስቡት በማያውቁት ሰውና ከተማ ውስጥ አይዞት አባቴ የሚል ሰው አገኙ። በአንድ ወቅት ያደረጉት መልካም ስራ ስንቅ ሆኖ፡ ከዚህ መልካም ሰው ጋር አገናኛቸው።
አበበ መለሰ አያ ትርፌን በዚህ ሁኔታ ካስተናገደ በኋላ፡ የትራንስፖርት ብቻ ሳይሆን ኑሯቸውንም ሊደጉም የሚችል ብዙ ገንዘብ ሰጥቶ ልብሳቸውን ቀያይሮ፡ ወደሀገራቸው ሸኛቸው።
..........
አበበ መለሰ አያ ትርፌን ወደ ሀገራቸው ከሸኘ በኋላም የሳቸው ነገር ከውስጡ ሊጠፋ አልቻለም። እና ይህንን አሳዛኝ የአያ ትርፌንና የውባለምን የፍቅር ታሪክ በዜማ ለመስራት ተነሳ።
እናም ሙዚቃ ለመስራት አብሮት አዳማ የነበረው ድምጻዊ ቴዲ ታደሰ እንዲዘፍነው አንድ ዜማ ሰራ።
.....
ይህ ከቴዲ ታደሰ ተወዳጅ ስራዎች መሀከል አንዱ የሆነው ውባለም ናፈቅሽኝ የሚለው ዜማ የተሰራው በዚህ ሙድ ነበር።
ሆኖም ይህንን ዜማ የሰራው አቤ፡ ግጥሙን እንዲሰራ ለይልምሽ ሰጠው።
ይህ ዜማ ሲወጣ አበበ መለሰ አሁንም በውስጡ ያለው፡ የአያትርፌና የውባለም ነገር በግጥሙ እንዳልተገለፀ ተሰማው። ምክንያቱም አያ ትርፌንም፡ ውባለምንም በአካል የሚያውቀው እሱ ነው።
ሌላ ስራ ለመስራት አሰበ ።
እናም ኤፍሬም ታምሩ ውባለም ተመለሽ(ጎጆሽ ይሻላል) የሚለውን ስራ ግጥሙንና ዜማውን ሰርቶ ሰጠው።
እንግዲህ በፊት በፊት ሙዚቃ የሚሰራው በዚህ መሳይ ጥልቅ ስሜቶች ነበር።
........
የፍቅርን ሀያልነትና ፡መልካም ስራ አንድ ቀን ሊከፍል የሚችል መሆኑን የሚያሳይ ህያው ታሪክ ።
ምንጭ ©W.T እንደፃፈው
ሀቅ እና ድንቅ