ትምህርት ሚኒስቴር ከሁዋዌና ሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር የሚያዘጋጀው የአይሲቲ ውድድር አበረታች መሆኑ ተገለጸ።
ከሁዋዌ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ፍጻሜ ለተወዳደሩ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።
ሽልማቱ የተበረከተው የሁዋዌ የ2024/25 አይሲቲ የውድድር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ ባስተላለፉት መልእክት ውድድሩ ለተማሪዎች የስራ እድልን በማመቻቸት እና የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን ከማጎልበት አኳያ ሰፊ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ዘላለም አክለውም ሁዋዌ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተማሪዎችን ክህሎት ለማዳበር እያደረገ ላለው አበርክቶ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን መሠል ጥረቶችን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጠናክሮ ማስቀጠል የሚገባ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የሁዋዌ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኢትዬጵያ ሚስተር ሊሚንግየ በበኩላቸው ውድድሩ ለወጣቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
@moeofficial

የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።
ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et
➡️ በቴሌግራም : https://www.tgoop.com/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

Forwarded from Piassa Tech ™ (Zēus)
የትምህርት ሚኒስቴር ከራሽያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
---------------------------//---------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር ከራሽያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።
የተፈረመው ስምምነት ሰነድ በእኩልነት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና ውጤታማነት መርህ ላይ በመመስረት ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተመላክቷል።

#ጥቆማ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።
ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።
የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።
ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።
የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 08/2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ነው።
ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።

#WolloUniversity
በ2017 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ያለፋችሁ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 13 እና 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
- የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ።
የተመደባችሁበትን ግቢ ለማወቅ 👇
Telegeram Bot: @WU_Registrar_bot
Website: https://tinyurl.com/wu-Registrar-s

#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ፈተና ለመፈተን እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰማ።
ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘን ፈተና ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ " የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም " ብለዋል።
አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።
ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

#JimmaUniversity
በ2017ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ
· ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ ምዝገባችሁ በመጪው ህዳር 19 እና 20/2017 በዩኒቨርስቲው በተመደባችሁባቸው ካምፓሶች ማለትም የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ከሴክሽን 1-26) እና ግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ (ከሴክሽን 27- 31) እንዲሁም የሶሻል ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ደግሞ በዋናው ግቢ እንደሚካሄድ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።
👉ማሳሰቢያ
1. በ2017ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ በRemedial ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ግዜያችሁ በቀጣይ ማስታወቂያ የሚገለጽ መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን፡፡
2. በ2016ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ የRemedial ፕሮግራም ትምህርታችሁን የተከታተላችሁ ተማሪዎች በመጪው ቅርብ ቀናት https://portal.ju.edu.et ላይ የመለያ ቁጥራችሁን በማስገባት አጠቃላይ ውጤታችሁን ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ላለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባችሁ ከላይ በተጠቀሰው ቀናት በተመሳሳይ የሚፈጸም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
3. አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ሴክሽን እና ካምፓስ ከተወሰኑ ቀናት በ3.4 https://portal.ju.edu.et ላይ ስለሚለቀቅ የአድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ነባር የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ደግሞ ይህንን መረጃ የመለያ ቁጥራችሁን (ID No) በማስገባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ፤
በጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡
በዩኒቨርሲቲዉ ሴቶች፣ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት “በጋራ ጎበዞቹን እንሸልም”በሚል መርሃ ቃል በተዘጋጀዉ መርሃ ግብር ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ ተገኝተዉ ባደረጉት ንግግር ተሸላሚዎቹ በብዙ ልፋት ዉጤታማ ሆነዉ ለሽልማት መብቃታቸዉ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች ባገኙት ዉጤት ሳይዘናጉ ጠንክረዉ በመስራት የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸዉም መክረዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ም/ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር ገመቺስ ፊሌ በበኩላቸዉ፤የላቀ ዉጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎችን ማበረታታት ሌሎች ተማሪዎችንም ለዉጤታማነት የሚያተጋ በመሆኑ የማበረታታት ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በዛሬዉ ዕለት 3.25 እና ከዛ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡ 536 ሴት ተማሪዎች እና 3.85 እና ከዛ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡ 136 ወንድ ተማሪዎች በድማሩ ስድስት መቶ ሰባ ሁለት/672/ ተማሪዎች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

[በ40 ምንጭና በተለያዩ አካባቢዎች በሰማይ ላይ እየነደደ የሚጓዘው ምን ይኾን?
የዛሬውን እንግዳ ክስተት በተመለከተ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ካጋሩት ሳይንሳዊ እና ሃይማኖታዊ ምልከታ ሳይንሳዊውን እንደሚከተለው እነሆ👇
💥 ዛሬ ጥር 1/ 2017 ዓ.ም. በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የታየ በሰማይ እየተቀጣጠለ የሚኼድ በጣም በርካታ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በውስጥ መሥመር እየተላኩልኝ ነበርና ምልከታዬን ለማስቀመጥ እሞክራለኹ።
💥 ከሰማይ ላይ አብርተው ስለሚታዩ ስለሚወድቁ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አካላት መረዳት ግድ ይላል።
የተፈጥሮ የሕዋ ዐለቶችን አስቀድመን እንመልከት፦
1. አስትሮይድ
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትዮር
4. ሜትሮይት
መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት መረዳት ያስፈልጋል፡-
1. አስትሮይድ
💥 በዋነኛነት በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው የአስትሮይድ ቀበቶ ውስጥ የሚገኙት ዐለታማ ሥሪትነት ያላቸው አካላት ናቸው። መጠናቸውን ለመረዳት ለምሳሌ አስትሮይድ ቬስታ መጠኑ 329 ማይል (530 ኪሎ ሜትር) ዲያሜትር ያለው ሲኾን ከታናናሾቹ ውስጥ ከ33 ጫማ (10 ሜትር) በታች የኾኑም ይገኙበታል። የኹሉም አስትሮይድ አጠቃላይ ክብደት ግን ከምድር ጨረቃ ያነሰ ነው።
👉 በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ኤፕሪል 13/ 2029 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ከምድር በላይ 30,600 ኪሎ ሜትር (19,000 ማይል) ርቀት ላይ የሚያልፍ ሲኾን ቢሊዮኖች በዐይናቸው ያዩታል። መሬትን የመመታት ዕድሉ 2.7 ፐርሰንት ብቻ ነው። (አንድሮሜዳ ክፍል 2 ገጽ 388 - 394 )
2. ሜትዮራይድ
💥 ሜትዮራይዶች በሕዋ ያሉ ትናንሽ ዐለቶች ሲኾኑ መጠናቸው ከከሸዋ ቅንጣት እስከ 1 ሜትር አካባቢ ይደርሳሉ። አንዳንድ ሜትዮራይድ ዐለቶች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብረታ ብረት ወይም የድንጋይ እና የብረት ውሕዶች ናቸው። ሜትዮራይድ ብዙ ጊዜ ከአስትሮይድ ወይም ከኮሜት ወይም ከሌሎች ፕላኔቶች ጭምር የሚመጡ ናቸው። በአጠቃላይ ሜትዮራይድ ስንል ገና በሕዋ ላይ ያሉትን ነው።
3. ሚትየር
💥 ከላይ እንዳየነው ሜትዮራይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ወይም ወደ ሌላ ፕላኔት በከፍተኛ ፍጥነት ሲገቡ እና ሲቃጠሉ ሚትዮር ይባላሉ። በሌላ አጠራር “ተወርዋሪ ኮከቦች” ብለን የምንጠራቸው ሲኾን አንዳንድ ጊዜ ሜትየሮች ከቬኑስ የበለጠ ብሩህ ኾነው ሊታዩ ይችላሉ። ያን ጊዜ “የእሳት ኳሶች” ተብለው ይጠራሉ። ብዙ ተወርዋሪ ከዋክብት በአንድ ላይ በሰዓታት ሲታዩ "ሜትየር ሻወር" በመባል ይታወቃሉ።
4. ሜትሮይት
💥 ሳይቃጠል የምድርን ከባቢ አየር ዐልፎ በምድር ላይ የሚያርፍ የሜትሮይድ ቁራጭ መጠሪያ ነው። በሰዓት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ በኃይለኛ ግፊት ወድቆ ሲበታተን ብሩህ ነበልባል ይመስላል።
ሜትሮይትስ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላሉ፡-
1) ድንጋያማ ሜትሮይትስ (በዋነኛነት ከሲልኬት) ማዕድናት የተውጣጡ ናቸው)፣
2) የብረት ሜትሮዮይትስ (በአብዛኛው ከብረት-ኒኬል ውሕዶች የተውጣጡ ናቸው)
3) ድንጋያማ ብረት ሜትሮይትስ (በግምት እኩል መጠን ያላቸው የሲሊኬት ማዕድናት እና ብረት ኒኬል ይዘዋል)
👉 ሜትሮይቶች ሲታዩ የምድር ዐለቶችን ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚያብረቀርቅ ሊመስል የሚችል የተቃጠለ ውጫዊ ክፍል አላቸው። ይኸውም በከባቢ አየር ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሜትሮይት ውጫዊ ገጽታ ሲቀልጥ የሚፈጠር ነው።
👉በምድር ላይ ከ 50,000 በላይ ሜትሮይትስ ተገኝተዋል.
ከእነዚህ ውስጥ 99.8% የሚሆኑት ከአስትሮይድ የሚመጡ ናቸው።
👉 በየቀኑ 48.5 ቶን የሜትሮይት ቁስ አካል ወደ ምድር ይወድቃል። ይህም በዓመት 17,000 ሚቴዮራይትስ እንደማለት ነው። አብዛኛው ግን በከባቢ አየር ውስጥ ተንኖ ተወርዋሪ ኮከብ ይኾናል።
👉 በቅርብ የተከሰቱ አደገኛ ከሚባሉት የሜትሮይትስ ክስተቶች ውስጥ ኹለቱን በማንሣት ጽሑፌን ልቋጭ፦
1ኛ) በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ሜትሮይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ የገባው እኤአ በ1908 ሲኾን የቱንጉስካ ክስተት በመባል ይታወቃል። ይህ ሜትዮር በሩሲያ በሳይቤሪያ ላይ የተከሰተ ሲኾን ምድሩን ሳይመታ በፊት በአየር ላይ ጥቂት ማይል ርቀት ላይ ፈነዳ።
👉 የፍንዳታው ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ስፋት ባለው ክልል ውስጥ ዛፎችን ለማውደም የሚያስችል ኃይለኛ ነበር። ሜትዮሩ 120 ጫማ (37 ሜትር) ስፋት ያለው እና 220 ሚሊዮን ፓውንድ (100 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበረ። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ አጋዘኖች ሲሞቱ ነገር ግን ማንም ሰው በፍንዳታው መሞቱን የሚያሳይ ቀጥተኛ መረጃ የለም።
2ኛ) እ.ኤ.አ. በ 2013 በቼልያቢንስክ ሩሲያ ሰማይ ላይ ቤትን የሚያህል ሜትሮይድ በሰከንድ ከ11 ማይል (18 ኪሎ ሜትር) በላይ ወደ ከባቢ አየር በመግባት ከመሬት በላይ 14 ማይል (23 ኪሎ ሜትር) ላይ ፈነዳ። ፍንዳታው ወደ 440,000 ቶን የሚገመተውን የቲኤንቲ ኃይል በመልቀቁ ከ200 ስኩዌር ማይል (518 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) በላይ መስኮቶችን የሰባበረ እና ሕንፃዎችን ያበላሽ አስደንጋጭ ኹኔታን ፈጠረ። በፍንዳታው ይልቁኑ በመስታወት ስብርባሪ ከ1,600 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
💥 ሌላው በሰማይ እየተቃጠሉ ሲሄዱ ሊታዪ የሚችሉት ሰው ሠራሽ ነገሮች
👉 ከአሁን በኋላ የማይሠሩ በጠፈር ውስጥ ያሉ ሰው ሠራሽ ነገሮች Space debris, space junk, orbital debris በመባል ይታወቃሉ።
ለምሳሌ፡-
👉 የድሮ ሳተላይቶች
👉 የሮኬት ክፍልፋዮች
👉 የፈነዱ ወይም የተጋጩ ተሽከርካሪዎች ወይም የተቆራረጡ ቁርጥራጮች ይገኙበታል።
👉 ከጠፈር ተልእኮ በኋላ የተጣሉ ቁሶች ናቸው።
💥 በግምት ከ10 ሴንቲ ሜትር በላይ ከ36,500 በላይ ቁሶች ሲኖሩ፤ ከ1-10 ሴ.ሜ በላይ 1 ሚሊዮን ቁርጥራጮች እና ከ1 130 ሚሊዮን የሚጠጉ ትናንሽ ቁርጥራጮች ይገኛሉ።
ሊያመጡ የሚችሉት አደጋዎች፡-
1) የሚሠሩ ሳተላይቶችን፣ ዐለም ዐቀፍ የጠፈር ጣቢያ (አይኤስኤስ) ወይም የጠፈር መንኮራኩሮችን በመግጨት ሊጎዳ ይችላል።
👉 አንዳንድ ቁርጥራጮች ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ ከገቡ መሬት ላይ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
👉 ለምሳሌ ሰኞ ታኅሣሥ 21/ 2017 ወይም December 30, 2024, በኬንያ፣ ሙኩኩ መንደር ውስጥ ከሮኬት የመለያያ ቀለበት በመባል የሚታወቅ አንድ ትልቅ ብረታማ ነገር የተከሰከሰ ሲኾን ቀለበቱ በግምት 2.5 ሜትር ዲያሜትር እና 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል። እንደ እድል ሆኖ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰም።
✍️
የዛሬውን እንግዳ ክስተት በተመለከተ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ካጋሩት ሳይንሳዊ እና ሃይማኖታዊ ምልከታ ሳይንሳዊውን እንደሚከተለው እነሆ👇
የተፈጥሮ የሕዋ ዐለቶችን አስቀድመን እንመልከት፦
1. አስትሮይድ
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትዮር
4. ሜትሮይት
መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት መረዳት ያስፈልጋል፡-
1. አስትሮይድ
👉 በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ኤፕሪል 13/ 2029 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ከምድር በላይ 30,600 ኪሎ ሜትር (19,000 ማይል) ርቀት ላይ የሚያልፍ ሲኾን ቢሊዮኖች በዐይናቸው ያዩታል። መሬትን የመመታት ዕድሉ 2.7 ፐርሰንት ብቻ ነው። (አንድሮሜዳ ክፍል 2 ገጽ 388 - 394 )
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትየር
4. ሜትሮይት
ሜትሮይትስ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላሉ፡-
1) ድንጋያማ ሜትሮይትስ (በዋነኛነት ከሲልኬት) ማዕድናት የተውጣጡ ናቸው)፣
2) የብረት ሜትሮዮይትስ (በአብዛኛው ከብረት-ኒኬል ውሕዶች የተውጣጡ ናቸው)
3) ድንጋያማ ብረት ሜትሮይትስ (በግምት እኩል መጠን ያላቸው የሲሊኬት ማዕድናት እና ብረት ኒኬል ይዘዋል)
👉 ሜትሮይቶች ሲታዩ የምድር ዐለቶችን ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚያብረቀርቅ ሊመስል የሚችል የተቃጠለ ውጫዊ ክፍል አላቸው። ይኸውም በከባቢ አየር ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሜትሮይት ውጫዊ ገጽታ ሲቀልጥ የሚፈጠር ነው።
👉በምድር ላይ ከ 50,000 በላይ ሜትሮይትስ ተገኝተዋል.
ከእነዚህ ውስጥ 99.8% የሚሆኑት ከአስትሮይድ የሚመጡ ናቸው።
👉 በየቀኑ 48.5 ቶን የሜትሮይት ቁስ አካል ወደ ምድር ይወድቃል። ይህም በዓመት 17,000 ሚቴዮራይትስ እንደማለት ነው። አብዛኛው ግን በከባቢ አየር ውስጥ ተንኖ ተወርዋሪ ኮከብ ይኾናል።
👉 በቅርብ የተከሰቱ አደገኛ ከሚባሉት የሜትሮይትስ ክስተቶች ውስጥ ኹለቱን በማንሣት ጽሑፌን ልቋጭ፦
1ኛ) በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ሜትሮይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ የገባው እኤአ በ1908 ሲኾን የቱንጉስካ ክስተት በመባል ይታወቃል። ይህ ሜትዮር በሩሲያ በሳይቤሪያ ላይ የተከሰተ ሲኾን ምድሩን ሳይመታ በፊት በአየር ላይ ጥቂት ማይል ርቀት ላይ ፈነዳ።
👉 የፍንዳታው ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ስፋት ባለው ክልል ውስጥ ዛፎችን ለማውደም የሚያስችል ኃይለኛ ነበር። ሜትዮሩ 120 ጫማ (37 ሜትር) ስፋት ያለው እና 220 ሚሊዮን ፓውንድ (100 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበረ። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ አጋዘኖች ሲሞቱ ነገር ግን ማንም ሰው በፍንዳታው መሞቱን የሚያሳይ ቀጥተኛ መረጃ የለም።
2ኛ) እ.ኤ.አ. በ 2013 በቼልያቢንስክ ሩሲያ ሰማይ ላይ ቤትን የሚያህል ሜትሮይድ በሰከንድ ከ11 ማይል (18 ኪሎ ሜትር) በላይ ወደ ከባቢ አየር በመግባት ከመሬት በላይ 14 ማይል (23 ኪሎ ሜትር) ላይ ፈነዳ። ፍንዳታው ወደ 440,000 ቶን የሚገመተውን የቲኤንቲ ኃይል በመልቀቁ ከ200 ስኩዌር ማይል (518 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) በላይ መስኮቶችን የሰባበረ እና ሕንፃዎችን ያበላሽ አስደንጋጭ ኹኔታን ፈጠረ። በፍንዳታው ይልቁኑ በመስታወት ስብርባሪ ከ1,600 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
👉 ከአሁን በኋላ የማይሠሩ በጠፈር ውስጥ ያሉ ሰው ሠራሽ ነገሮች Space debris, space junk, orbital debris በመባል ይታወቃሉ።
ለምሳሌ፡-
👉 የድሮ ሳተላይቶች
👉 የሮኬት ክፍልፋዮች
👉 የፈነዱ ወይም የተጋጩ ተሽከርካሪዎች ወይም የተቆራረጡ ቁርጥራጮች ይገኙበታል።
👉 ከጠፈር ተልእኮ በኋላ የተጣሉ ቁሶች ናቸው።
ሊያመጡ የሚችሉት አደጋዎች፡-
1) የሚሠሩ ሳተላይቶችን፣ ዐለም ዐቀፍ የጠፈር ጣቢያ (አይኤስኤስ) ወይም የጠፈር መንኮራኩሮችን በመግጨት ሊጎዳ ይችላል።
👉 አንዳንድ ቁርጥራጮች ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ ከገቡ መሬት ላይ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
👉 ለምሳሌ ሰኞ ታኅሣሥ 21/ 2017 ወይም December 30, 2024, በኬንያ፣ ሙኩኩ መንደር ውስጥ ከሮኬት የመለያያ ቀለበት በመባል የሚታወቅ አንድ ትልቅ ብረታማ ነገር የተከሰከሰ ሲኾን ቀለበቱ በግምት 2.5 ሜትር ዲያሜትር እና 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል። እንደ እድል ሆኖ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰም።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM