Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
756 - Telegram Web
Telegram Web
እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+"+ ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ +"+

=>ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::

+ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐመድ ተከታዮች) ናቸው:: 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::

+በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::

+በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::

+መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::

+ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው:: ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::

+"+ ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ +"+

=>አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን): በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::

+ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::

+ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::

+በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::

+በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::

+ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ:: "አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::

+"+ ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ +"+

=>አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::

+በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::

+ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::

+መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::

+"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ኅዳር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
2.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
3.ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
4.አባ አበጊዶ ዘትግራይ
5.ታላቁ አባ ዘካርያስ
6.ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#የንስሐ_ጸሎት

  🥀አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ አዳምን ከሲኦል ፣ ኖህን ከውሃ ጥፋት ፣ ይስሃቅን ከመታረድ ፣ እስራኤልን ከፈርኦን ፣ ዳዊትን ካሳኦል ፣ ኤልያስን ከኤልዛቤል ፣ መርዶክዮስን ከሀማ ፣ ሰልስቱን ደቂቅን ከእቶን እሳት ፤ ያዳንክ አምላክ ሆይ እኔንም ባሪያህን ከመከራ ስጋ ከመካራ ነፍስ አድነኝ  ። በዚህ አለም ስኖር ከርሃብ ፣ ከጥማት ፣ ከመሰደድ ፣ ከመንገላታት ፣ በኃይለኞችና በጨካኞች እጅ ከመውደቅ አድነኝ ፤ ለንሰሐ ሞት አብቃኝ ፤ የሗላ ቤቴን አሳምርልኝ ፤ ከዳግም ሞት አድነኝ አሜን!

      🥀አቤቱ አምላኬ ሆይ ኢዮብን ከቁስል ፣ አላዛርን ከመቃብር ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም ፣ ዮናስን ከአሳነባሪ ፣ ምናሴን ከብረት ቀፎ  ፣ ሙሴን ከዳታንና ከአቤሮን ፣ አሮንን ከደቂቀ ቆሬ ያዳንክ አምላክ ሆይ እኔንም ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ አድነኝ ፤ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ዳንኤልን አእፈ አናብስት ፣ ሶስናን ከእደ ረበናት ፣ ሎጥን ከሰዶምና ከገሞራ  ፣ ዲቦራን ከሲሳራ ፣ ያእቆብን ከወንድሞቹ ፣ ሶምሶምን ከእርግውና ወደ ውርዝውና የመለስክ ፤ የበለአምን አህያ ያናገርክ እኔንም ባርያህን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ሰውረኝ ፤ በንፅህና ሆኜ ቅዱስ ስጋህን እና ክቡር ደምህን እየተቀበልኩኝ ለመኖር ፍቀድልኝ ከዚህ አለም እሾህና አሜኬላ አድነኝ አሜን!

    🥀 አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሰባ ነገስታት ፣ ጦቢትን ከአይን ህመም ፣ ብሩክ ታዊትን ከአፍ ደራጎን  ፣እግዚሃርያን ከመቶሎሚ ፣ የአትናስያን ሞት ወደ ህይወት የመለስክ ፣ በላኤሰብን የማርክ ፤ አክሊለ እሾህን ያጠለክ ፣ በቅድመ አይሁድ እስራትና ግርፋት ለአለም ቤዛነትን የተቀበልክ ፣ በፆረ መስቀል በፍኖተ አምስት ጊዜ የወደቅህ ፣ በፊትህም በኃላህም ምራቀ አይሁድን የተቀበልክ ፣ በቀራንዮ በእለተ አርብ ደምህን ያፈሰስክ ስጋህን የቆረስክ ፣ ህማማተ መስቀልን የተቀበልክ ፣

የእውሩን አይን ያበራክ ፣ ለምፃሙን ያነፃክ ፣ ጎባጣውን ያቀናክ ፣ ዲዳን ያናገርክ ፣ አንካሳን የፈታህ ፣ ባህርን ያናወፅክ ፣ ፴፰ አመት በአልጋ ቁራኝነት የነበረውን መፃጉን ያዳንክ ፣ ያመኑብህን የማትጥል ፣ ሰማይና ምድርን በቃልህ ያቆምክ ፣ መአልቱን በሌሊት በጋውን በክረት የምታፈራርቅ ፣ አካልህ የማይዳሰስ ቃልህ የማይገሰፅ ፣ መንግስትህ አያልፍ ፣ ከተሾምክ ያልተሻርክ የማትሻር ፣ ከተወለድክ የማታረጅ ያላረጀክ ፣ ከአለም በፊት የተገኘህ አለምን አሳልፈህ ለዘለአለም የምትኖር አልፋና ኡሜጋ ኤልሻዳይ አዶናይ ፀባኦት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከክፋት ወደ በጎነት መልሰኝ ፤ ሀይል መዊእ ለዳዊት የሰጠህ ለእኔም ስጠኝ እድሜ ለማቱሳላ ፣ ፅድቅ ለቅዱስ ላሊበላ የሰጠህ ለእኔም እድሜ ለንሰሐ ፅድቅ ለፍሰሀ ስጠኝ ፤ መልአከ ጠባቂዬን አበርታልኝ ከሰውና ከእግዚአብሔር  የሚስማማ ምግባርን ስጠኝ ፤ በተወለድኩበት አገር ክፋን ነገር አታሳየኝ ፤ የመላእክት የሰማእታት የፃድቃን የነቢያት የሐዋርያትና የምእመናን የደብርን የገዳማትን የእፅነ የእንስሳትን የአእሩግን የህፃናትን የንጉስን የመስተጋድል ልመና ፀሎት የተቀበልክ አምላክ የእኔንም ልመና ፀሎት ስማኝ ተቀበለኝ  ። "መሐረኒ እመከራ ስጋ  እመከራ ነፍስ ዓለም ለዓለም አሜን !!!
ናሁ ሰማን(Nahu seman)
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_3 #ርዕስ ፦ ጉዞ ወደ ጥብርያዶስ ➯ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ዘመድ የኬፋዝ ንጉሥ ወደ አለበት ወደ ጥብርያዶስ ሄዱ፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስ እንደ ሚያሳድዳት ዘመዷ ለሆነው ንጉሥ ነገረችው:: "ንጉሡም ሄሮድስ የሚያሳድድሽ ለምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቃት።" "ይህን ሕፃን ለመግደል ስለሚፈልግ ነው አለችው::" ንጉሡም እመቤታችንን "ከዚህ ከእኔ ቤት ተቀመጪ አላት።" ቤተሰቦቹንም…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_4

#ርዕስተአምረ ማርያም በምድረ ጋዛ

➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲዘዋወሩ #ጋዛ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በጋዛ የሚኖሩ ሰዎች እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡ ዮሴፍ በጋዛ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲሀ አላቸው። "በአገራችሁ ውሃ የለምን?" የጋዛ ሰዎችም እንዲህ አሉ "በሀገራችን ውሃ የለም ውሃ የምንቀዳበት ቦታ ርቀት በእግር 27 ቀን ይወስዳል፡፡ 27 ቀን ተጉዘን በግመል ጭነን አምጥተን ትንሽ ትንሽ እንጠጣለን አሉት።" የጋዛ ሰዎች ክፉዎች ስለሆኑ እንዲህ አሉ እንጂ በሀገራቸው ውሃ የሌለ ሆኖ አይደለም፡፡ የጋዛ ሰዎች ውሃ ከቀዱ በኋላ የውሃውን ጉድጓድ ዝግባ በተባለ ታላቅ እንጨት ይገጥሙታል፡፡ መንገደኞች ውሃ ሲጠይቋቸው ወይም ሲለምንዋቸው ውሃ የለንም ይላሉ፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሕይወት ይሆን ዘንድ የፈጠረውን ውሃ የሚከለክሉ ጨካኞች ነበሩ፡፡

➯የውሃ ልመናው ያልተሳካለት ዮሴፍ እመቤታችንን እንዲህ አላት፡፡ በዚህ ሀገር የምንጠጣው ውሃ የለም፡፡ እመቤታችንም አተር የአሚወቁ የሚያበራዩ! ሰዎችን አየች። አተር ወደ ሚወቁት ሰዎች እንሂድና አተር ስጡን እንበላቸው አለችው ዮሴፍን እመቤታችን የጋዛን ሰዎች ጭካኔና ርኅራኄ ማወቅ ፈልጋለች ፡ አተር ወደሚያበራዩት / ወደሚወቁት ሰዎች ሄደው "ይህን ሕፃን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለራው ትንሽ አተር ስጡት ብለው ለመንዋቸው። የጋዛ ሰዎች ውሃ እያላቸው ውሃ የለንም እንዳሉ ሁሉ የአተሩን ልመናም አልተቀበለትም። ይልቁንም "ይህ የምታዩት አተር ሳይሆን ድንጋይ ነው" በማለት ቀለዱባቸው።"

➯ከዚህ በኋላ ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን "እንደቃላችሁ ይሁንላችሁ በያቸው አላት፡፡" እመቤታችንም "እንደቃላችሁ ይሁን አለቻቸው።" ወዲያው የሚወቁት አተር ድንጋይ ሆነ፡፡ ውሃ እያላቸው ውሃ የለንም ስላሉ ውሃቸውም ደረቀ። አገራቸውም እህልን ዕፅዋትን የማያበቅል ደረቅ ሆነ። ምንጊዜም ቢሆን ለከፉ ሰዎች የተንኮላቸው ዋጋ ይከፈላቸዋል፡፡

➯ኢየሱስ ክረስቶስ ወንጌልን በሚያስተምርበት ጊዜ ተንኮለኞች በተንኮላቸው እንደሚጠፉ እንዲህ ሲል ተናግሯል ፡ "ወራት ይመጣብሻልና ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኩሉም ያስጨንቁሻል" (ሉቃ 19፥43-44) ኢየሱስ ክርስቶስን ግብዞች ፈሪሳውያን ስለአሉባት ከተማ የተነገረ ቃል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን ሰቅለው የገደሉ የአይሁድ ከተማ ኢየሩሳሌም ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በ10 ዘመን በሮማውያን ጠፍታለች።


#ክፍል_አምስት_ይቀጥላል.....
የህዳር ወር አመታዊ በዓላት

ህዳር 1 - ዕንቁ ልደታ - ቅዳሴ ቤቷ- ቀበና በኮከበ ጽዕባ ትምህርት ቤት አጠገብ ባለው ቅያስ(ኮብል) ወደ ላይ መውጣት

ህዳር 3 - በዓታ ማርያም (ዘንዶ አስራ) - ቅዳሴ ቤቷ -ቦሌ አራብሳ

ህዳር 6 - ቁስቋም ማርያም -ወደ ደብረ ቁስቋም የገቡበት መታሰቢያ ዕለት

ህዳር 7 - ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቅዳሴ ቤቱ

ህዳር 8 - አርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል ) - በ4 ኪሎ ባለወልድ ቤተክርስቲያን

- በጣፎ አባ ኪሮስ ቤተክርስቲያን

ህዳር 11 - ቅድስት ሐና - በዓለ እረፍቷ

ሰኞ ህዳር 12 - ቅዱስ ሚካኤል - በዓለ ሲመት(የተሾመበት)

ህዳር 13 - እግዚአብሔር አብ - እልፍ አእላፍ መላእክት የተሾሙት

ህዳር 15 - ቅዱስ ሚናስ - በዓለ እረፍቱ - በድሬ ዳሌ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ጣፎ አባ ኪሮስ አለፍ እንዳሉ ድሬ መገንጠያ አዲሱ መንገድ ብላችሁ የድሬዳሌ ትራንስፖርት መያዝ ከዛ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ብላችሁ ጠይቁ

ህዳር 21 - ፂዮን ማርያም

ህዳር 22 - ፉሪ ቅዱስ ዑራኤል - ቅዳሴ ቤቱ - በሀይሌ ጋርመንት ወደ ገላን በሚወስደው መንገድ ሰፈራን አለፍ እንዳሉ አዲስ የሚሰራው ኮንዶሚኒየምን ዝቅ ብለው

ህዳር 24 - ሃያራቱ ካህናተ ሰማይ(ሱራፌል) - በቦሌ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን

- አቡነ ተክለሃይማኖት - 25ተኛ ሆነው የሥላሴ መንበር ያጠኑበት መታሰቢያ ዕለት

ህዳር 25 - ቅዱስ መርቆሬዎስ - በዓለ እረፍቱ - በጎፋ መብራት ሀይል ቅዱስ መርቆርዮስ ቤተክርስቲያን በካሳንቺስ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን በአዲሱ ገበያ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን

ህዳር 26 - አቡነ ሃብተማርያም - በዓለ እረፍታቸው

ህዳር 29 - አቡነ እጨጌ ዮሐንስ -በዓለ ልደታቸው - በወይራ ሰፈር

ቸር ያገናኘን አሜን !!!
እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አባ ዮሐኒ" እና "ቅዱስ ለንጊኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

(በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ትግራይ ውስጥ የሚገኘው አስደናቂው የጻድቁ ገዳም ነው)

+"+ ታላቁ አባ ዮሐኒ +"+

=>በምድረ ኢትዮዽያ ዝናቸው ከወጣና ቀደምት ከሚባሉ ጻድቃን አንዱ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ("ኒ" ጠብቆ ይነበብ) ነው:: አበው ሊቃውንት የቅዱሱን ታሪክና ገድል ገና በልጅነት ስለ ነገሩን አንረሳውም:: እጅግ ጣፋጭ ዜና ሕይወት ያለው አባት ነውና:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ቅዱስ አፄ ካሌብ ነግሦ ሳለ: አንድ ቅዱስ ሰው ከግብጽ ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: እኒህ ሰው "አሞኒ ዘናሕሶ" ይባላሉ:: ቅዱሱ ዓለምን ላለማየት ቃል ገብተው በትግራይ በርሃ ይጋደሉ ነበር::

+በዘመኑ አፄ ካሌብ የናግራን (የመን) ክርስቲያኖችን ለመታደግ ዘመቻ አድርጎ ነበር:: ታዲያ አንድ የንጉሡ ወታደር ወደ ዘመቻ ሲሔድ ሚስቱን ይጠብቅለት ዘንድ ትንሽ ወንድሙን አደራ ይለዋል:: ወንድሙ ግን አደራውን ትቶ የትልቅ ወንድሙን ሚስት አስገድዶ ይደርስባትና ትጸንሳለች::

+ከዘመቻ የተመለሱት ከ1 ዓመት በሁዋላ ነውና ሚስቱን ምጥ ላይ ያገኛት ወታደር ደነገጠ:: ተቆጣ:: የጸነሰችው ከእርሱ እንዳልሆነ ያውቃልና ምጥ ላይ ሆና ሊያዝንላት አልፈለገም::

+ለገልጋይ አስቸግሮ ሚስቱን ይደበድባት ገባ:: በዚህ ምጥ: በዚህ ዱላ ነፍሷን ከሥጋዋ ሊለየው የደረሰችው ያቺ ሴት ግን "ወንድማማችን አላጋድልም" ብላ ቻለችው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ያን ግብጻዊ ባሕታዊ (አባ አሞኒን) አምጥቶ ከሰዎቹ በር ላይ አቆመው::

+"ከእሱ ነው በይ" አላት:: እርሷም "ከዚያ ባሕታዊ ነው" ብላ ተናገረች:: ወታደሩ ባሏም በቁጣ ወጥቶ ቅዱስ አሞኒን በዱላ ስብርብር እስኪል ድረስ ደበደበው:: ልጁ ልክ ሲወለድም ከእናቱ ነጥቆ ለባሕታዊው አሳቅፎ አባረረው::

+ቅዱስ አሞኒም ሕጻኑን አቅፎ ወደ ተምቤን በርሃ አካባቢ ወሰደው:: ግን ምን ምግብ: ምን ልብስ: ምን መኝታ እንደሚሰጠው ጨንቆት ጻድቁ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜም ቅዱስ መልአክ የጸጋ ምንጣፍን አነጠፈለት::

+ጆፌ አሞራ መጥቶ ክንፉን ሲያለብሰው አጋዘን መጥታ ጡት አጠባችው:: በዚህ የተደነቀው ቅዱስ አሞኒ ሕጻኑን "ዮሐኒ" ሲል ስም አወጣለት:: ትርጉሙም "ወልደ አራዊት - ወላጆችህ (አሳዳጊዎችህ) አራዊት ናቸው" እንደ ማለት ነው::

+ሕጻኑ ዮሐኒ በዚህ መንገድ ከአሞኒና ከአራዊቱ ጋር አደገ:: 5 ዓመት በሞላው ጊዜም ትምሕርተ ሃይማኖትን: የቅድስና ሕይወትን ተማረ:: ልክ እንደ መንፈሳዊ አባቱ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: ግን እርሱ ከእርሱ: ከአሞኒና ከአራዊቱ በቀር ሌላ ፍጥረት: ዓለም (ብዙ ሰዎች) መኖራቸውን አያውቅም::

+12 ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ክህነት ይገባዋል ብሎ መንፈስ ቅዱስ ስላሳሰባቸው ቅዱሱ አሞኒ ዮሐኒን ወደ ዻዻሱ ወሰዱት:: መንገድ ላይም ቅዱስ ዮሐኒ ወጣት ሴቶች ተሰብሰበው ሲጫወቱ ተመልክቶ "አባ! እነዚህ ጸጉራቸው የረዘመ: ደረታቸው ወደ ፊት የወጣ ፍጥረቶች ምንድን ናቸው?" ሲል ጠየቀ::

+አባ አሞኒም "ልጄ! እነዚህ ሴቶች ናቸው:: ግን ለእንደ እኔና አንተ ያሉ የበርሃ ሰዎች አይሆኑምና አትቅረባቸው" አለው:: ቅዱስ ዮሐኒ መልሶ "አባቴ! ድንገት ቢመጡብኝ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀ:: አባ አሞኒም "ልጄ! ከዘለዓለም ርስት ከምትነቀል ሩጠህ ብታመልጥ ይሻላል" አለው::

+ከ6 ዓመታት በሁዋላ (ዮሐኒ 18 ዓመት ሲሞላው ማለት ነው) ቅዱስ አሞኒ ኅዳር 5 ቀን ዐረፈ:: ለ14 ዓመታትም ቅዱስ ዮሐኒ ከአራዊትና አባ አበይዶን ከመሰሉ አባቶች ጋር ኖረ:: ከንጽሕናው የተነሳም ቅዱሳን መላእክት ያነጋግሩት ነበር::

+ስም አጠራሩ በምድረ ትግራይ ሲወጣ ወላጅ እናቱ በሕይወት ነበረችና ሰማች:: የአካባቢዋን ሴቶች ሰብስባም ልትገናኘው ወዳለበት ተራራ ገሰገሰች:: ወደ ተራራው ደርሳ ስትጠራው ቅዱሱ ተመለከታት::

+ወዲያው ትዝ ያለው አባቱ ቅዱስ አሞኒ "ሴት ስታይ ሩጥ" ያለው ነውና እግሩን አንስቶ ሮጠ:: እናቱ ስትከተለው: እርሱ ሲሮጥ ከገደሉ ጫፍ ደረሰ:: ወደ ሁዋላ ሲመለከት ሊደርሱበት ነው::

+በስመ ሥላሴ ፊቱን አማትቦ ወደ ገደሉ ተወረወረ:: በዚህ ጊዜ ግን መንፈሳዊ ክንፍ ተሰጥቶት ተሰወረ:: ቅዱስ መልአክም ብሔረ ሕያዋን አስገብቶታል:: ይህንን ታሪክ ሲያደንቁ አበው እንዲህ ብለዋል::

"ሰላም ዕብል ለዘኮነ ሱቱፈ::
ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ::
እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንትኒ ኢያትረፈ::
ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ::
ወከመ ክንፎሙ አብቆለ አክናፈ::" (አርኬ)

+"+ ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት +"+

=>ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22)

+ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ አሞኛል ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ::

+በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ወደ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::

+ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::

+ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::

+ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት: ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::

+በመጨረሻ በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት:: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽቅድ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: አይሁድም አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

< አስተርዮተ ርዕሱ >

=>ይሕች ዕለት አስተርዮተ ርዕሱ ትባላለች:: እርሱን ከገደሉ በሁዋላ አይሁድ ራሱን ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው ጥለዋት ነበር:: የእርሱን ሰማዕትነት ያየች አንዲት ክርስቲያንም ከለቅሶ ብዛት ዐይኗ ቢጠፋ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች::

+ወዲያው ግን ሕጻን ልጇ ሞተባትና ሐዘኗ ከልኩ አለፈ::
ለአንዲት እናት ዐይንንና ልጅን በአንዴ ማጣት እጅግ ጭንቅ ነው:: በሌሊት ግን ቅዱስ ለንጊኖስ በራዕይ ተገልጦ ደስታ ነገራት::+ "ልጅሽ በገነት ሐሴትን ያደርጋል:: አንቺ ግን ራሴን ከተቀበረችበት አውጪ" አላት:: ወደ ጠቆማት ቦታ በመሪ ስትቆፍር ብርሃን ወጥቶ ዐይኗ በራላት:: በታላቅ ሐሴትም ቅድስት ራሱን ወደ ሃገሯ ወስዳታለች::
ናሁ ሰማን(Nahu seman)
እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አባ ዮሐኒ" እና "ቅዱስ ለንጊኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ (በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ትግራይ ውስጥ የሚገኘው አስደናቂው የጻድቁ ገዳም ነው) +"+ ታላቁ አባ ዮሐኒ +"+ =>በምድረ ኢትዮዽያ ዝናቸው ከወጣና ቀደምት ከሚባሉ ጻድቃን አንዱ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ("ኒ" ጠብቆ ይነበብ) ነው:: አበው ሊቃውንት የቅዱሱን ታሪክና ገድል ገና በልጅነት ስለ ነገሩን…
=>አምላከ ቅዱሳን የቀደምቶቻችንን የዋህነት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ታላቁ ቅዱስ ዮሐኒ (ዘትግራይ)
2.አባ አሞኒ ዘናሕሶ
3.ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
4.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ

=>+"+ ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል:: ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ: እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል:: +"+ (ዮሐ. 19:33)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ታሪክ ላላችሁ እንሆ ይኸው
👇👇👇👇👇👇👇👇

አንድ በምሽት አቅጣጫ የጠፋበት መርከብ ከሩቅ ያየ ሰው ወደ እቤቱ ገብቶ ሻማ ይለኩሳል

ሻማውም ለምን ለኮስከኝ ቢለው ሰውዬው ‹‹አቅጣጫ የጠፋው መርከብ ከሩቅ ያታየኛል
ለሱ በእሳት ልጠቁመው ነው ይለዋል ሻማውም ‹‹ታዲያ እኔ ሻማ ነኝ እንዴት ከሩቅ እታያለሁ›› ቢል ሰውዬውም መለሰ ‹‹ሻማዬ ሆይ አንተ ብቻ የቻልከውን ብራ›› አለውና ይዞት ይወጣና ብዙ ደረቅ እንጨቶችን እንደ ዳመራ ከቆለለ ቦሃላ በሻማው እሳት እንጨቶቹን ለኮሰ ብርሃኑም ብዙ ሆነ
ያኔ መርከቡም ተመልክቶ መጣ

ሰውዬውም ለሻማው እንዲህ አለው ‹‹ሻማዬ ሆይ አየህ አንተ በቻልካት መጠን ስለበራህ ያንተን ብርሀን ተቀብለው የሚያደማምቁ ብዙዎች አሉ›› አለው፡፡


እንግዲህ እንዲህ ነው የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ

‹‹የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ ደግነት
እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል››

እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን
አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡

ተወዳጆች ጥሩ ምሽት  ይሁንላችሁ!
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ 🌹በዓለ ደብረ ቁስቁዋም🌹 ✞✞✞

✞✞✞ የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ: በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

*የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::

+"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?"

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: )

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ድንግል ማርያም ከርጉም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነው::

+በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች:: በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች::
"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ)

+ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች:: ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሙ: አክሱም: ደብር ዓባይ: ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች:: በጣና ገዳማትም: በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሽዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::

+ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች:: በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች:: ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች:: ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::

+እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቁዋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል:: ሐሴትንም አድርገዋል::

+ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቁዋም ታንጻ ተቀድሳለች:: የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: አስከትሎ ወረደ::

+የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው: ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል::

+ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው:-
"እመ ኀሎኩ በጐይዮቱ ውእተ መዋዕለ:
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ:
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ:
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኀበ ተተክለ:
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ::" እንዳሉ:: (ሰቆቃወ ድንግል)
እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል::

+ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ:: የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና::

"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ:
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ" ልንልም ይገባል::

+" 🌷አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ🌷 "+

+ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::

+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ::

+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው /ሲያጠምቁዋቸው 'ጽጌ ድንግል' አሏቸው:: ሲመነኩሱም 'ጽጌ ብርሃን' ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::

+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርግው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: ጻድቁ ያረፉት ጥቅምት 27 ሲሆን ዛሬ የቃል ኪዳን በዓላቸው ነው::

✞✞✞ ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም (ሚጠታ ለማርያም)
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅድስት ሰሎሜ ቡርክት
4.ቅዱስ ዮሳ (ወልደ ዮሴፍ)
5.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
6.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
7.አባ ፊልክስ ዘሮሜ
ናሁ ሰማን(Nahu seman)
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞ ✞✞✞ 🌹በዓለ ደብረ ቁስቁዋም🌹 ✞✞✞ ✞✞✞ የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ…
=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

++"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኗን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ናሁ ሰማን(Nahu seman)
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_4 #ርዕስ ፦ ተአምረ ማርያም በምድረ ጋዛ ➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲዘዋወሩ #ጋዛ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በጋዛ የሚኖሩ ሰዎች እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡ ዮሴፍ በጋዛ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲሀ አላቸው። "በአገራችሁ ውሃ የለምን?" የጋዛ ሰዎችም እንዲህ አሉ "በሀገራችን ውሃ የለም ውሃ የምንቀዳበት ቦታ ርቀት በእግር 27 ቀን ይወስዳል፡፡…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_5

#ርዕስ ፦ ጉዞ ወደ ምድረ ግብፅ

➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ወደ ምድረ ግብጽ ሲጓዙ ሦስት ቀን ጫካ ውስጥ ሰነበቱ። በጣም ተራቡ፣ ተጠሙ። በበረሃ በረሀብና በውሃ ጥም እንዳይሞቱ እመቤታችን ጸለየች። ወዲያው የተሠራ ማዕድ የተዘጋጀ ምግብ መጣላቸው በልተው ጠገቡ። ከዚህ በኋላ #ኢንፍሎን ወደተባለ አገር ሄዱና #ርግባዳ ከተባለ ሰው ቤት ተቀመጡ። ብዙ ሰዎች ዕውቀት ፈልገው ወደ እመቤታችን ይመጡ ነበር። እመቤታችን ከጥበበኞች ከእስራኤል ሀገር ስለመጣች ብዙ ጥያቄዎችን ይጠይቋት ነበር። እመቤታችንም ብዙ ምሳሌ እየመሰለች ጥያቄዎቻቸውን ስትመልስላቸው እያደነቁ ይሄዱ ነበር።

➯ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዚያች ሀገረ ገዥ ሞተ። ቤተሰቦቹ መጥተው ለእመቤታችን ነገርዋት፡፡ እመቤታችን ስትሄድ ሞቶ አገኘችው፡፡ የሚያለቀሱትን ሰዎች "ዝም በሉ አለቻቸው።" አልቃሾቹ ዝም አሉ። በቀኝ እጅዋ ይዛ "በእግዚአብሔር ስም ተነስ አለችው።" የሞተው ሀገረ ገዥ ሕያው ሆኖ ተነሣ ለልቅሶ የተሰበሰቡት ሰዎች የጣዖቶቻቸውን ስም የመጥራት አጵሎንና አርዳሚስ ሰው ተመስለው መጡ አሉ። እመቤታችንም "እናንተ የምትሏቸው ጣዖታት አይደለሁም። ከይሁዳ ምድር ተሰድጄ የመጣሁ ሰው ነኝ" ካለቻቸው በኋላ የሞተውን ሰው ማስነሣት የሚቻለው እግዚአብሔር መሆኑን እንዲያውቁና በእግዚአብሔር፡ እንዲያምኑ፡ አስተማረቻቸው።

➯በሀገራቸው ውስጥ የሚኖሩ በሽተኞችን እየፈወሰችላቸው ጥቂት ወራት ተቀመጠች። ምድራችውን ውሃ አፈለቀችላቸውና፡ "በዚህ ተፈወሱ አለቻቸው።" የታመመ ሰውም ሆነ እንስሳ አመቤታችን ባፈለቀችው ውሃ ሲታጠብ ይፈወስ ነበር፡፡

➯ከዚህ በኋላ #ራፋን ወደተባለ ሀገር ሄዱ፡፡ የራፋን ሰዎች መለከት እየነፉ ወጥተው እመቤታችንን ዮሴፍንና ሰሎሜን በድንጋይ ቀጠቀጧቸው፡፡ እነዮሴፍም ከዚያ ሀገር ወጥተው ሄዱ፡፡ በአረብ #አንፃር_ቄድሮስ ከተባለ አገር ደረሱ፡፡ በተቃራኒው የሚጾሙ የሚጸልዩ ደጋግ ሰዎችን አገኙ። ሀገሩም በጣም ደስ የሚያሰኝ ልምላሜ የተሞላበት ሀገር ነበር፡፡ #በቄድሮስ 8ወር ተቀመጡ፡፡ ዮሴፍም እመቤታችንን "ሁሉን ነገር ትተን ከዚህ ሀገር እንቀመጥ አላት።" ሀገር ለሀገር ዋሻ ለዋሻ መንከራተቱን ትተን እንረፍ ማለቱ ነው፡፡ እመቤታችንም "ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እዚህ መቀመጥ አንችልም" አለችው ዮሴፍን፡፡

➯በዚያች ሌሊት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ እመቤታችንን ከዚህ አገር ውጪ አላት፡፡ ከዚያች አገር ወጥተው ወደ #ደብረ_አሞር ሄዱ፡፡ የተለያየ ደዌ የያዛቸው ሰዎች ወጥተው ተቀበሏቸው። እመቤታችን ሁሉንም ፈወሰቻቸው እነዮሴፍ በደብረ አሞር በዙ ጊዜ
ተቀመጡ፡፡

➯በደብረ አሞር ወጥተው ሲሄዱ #ሌላውዳ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በዚያም ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው አገኙ። ርኩስ መንፈስ ከያዘው 70 ዓመት አልፎታል፡፡ ሰውየው አይተኛም ሥጋውን በድንጋይ ይቦጫጭቃል በሰንሰለትም ሲታሰር ሰንሰለቱን ይሰባብራል። እመቤታችንን ባያት ጊዜ "ይቅር በይኝ" ብሎ ከእግሯ ስር ወደቀ፡፡ እመቤታችንም ርኩሱን መንፈስ "በእግዚአብሔረ ስም ውጣ አለችው፡፡" ርኩሱ መንፈስ ወጣ፡፡ ርኩሱ መንፈስ ጦጣ ይመስል ነበር፡፡ ክፉ አራዊት የርኩሳን መናፍስት መገለጫዎች ናቸው። #ዮሐንስም በእባብና በዘንዶ ዲያብሎስን ሲገልጸው እንዲህ ይላል፡፡ "«ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ»" (ራዕይ 12፥9) ርኩሱ መንፈስ የወጣለት ሰው አልለይም ብሎ እየሰገደ እመቤታችንን ተከተላት። እመቤታችንም "ወደ ዘመዶችህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ነገር ንገር" አለችው፡፡

➯እመቤታችን የተለያዩ ተአምራትን እንደምታደርግ በአካባቢው ተሰማ፡፡ አንድ ሆዱን የነፋው ሀገረ ገዢ መጥቶ "ፈውሺኝ" አላት፡፡ እመቤታችንም "በልጄ እመን ትድናለህ" አለችው፡፡ እርሱም "አምናለሁ" አለ። ከሆዱም እባብ ወጣለት፣ ከበሽታው ተፈወሰ፡፡ እነዮሴፍን ዘጠኝ ወር ያህል ከቤቱ አስቀመጣቸው፡፡

➯ከዘጠኝ ወር በኋላ ከቤቱ ወጥተው ሲሄዱ #ሌበ የሚባል ባሕር ካለበት ሀገር ደረሱ፡፡ የዚያ ሀገር ሰዎች በጅራፍ እየገረፉ አባረሯቸው፡፡ እነዮሴፍ #ቤልቤል ከሚባል ዛፍ ስር አደሩ፡፡ ነገር ግን መልአክ ወርዶ በሰረገላ ወስዶ ካሳደዷቸው ሰዎች ሀገር መካከል አስቀመጣቸው።

➯እመቤታችንም ከእንቅልፏ በነቃች ጊዜ ያደሩበት ሀገር በጅራፍ እየገረፉ ያሳደዷቸው ሰዎች ሀገር እንደሆነ አወቀች። እመቤታችንም የቅናቱ ጅራፍ ተመልሶ እንዳይመጣ ወደ እግዚአብሔር አጥብቃ ጸለየች፡፡ በጅራፍ የገረፍዋቸው ሰዎችም ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለወጠው ውሻ ሆኑ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ሰዎች የሚቀጣበት መሣሪያው የተለያየ ነው፡፡ አእምሮ ያለውን ሰው አእምሮ የሌለው እንስሳ ያደርገዋል፡፡ ይህ አይነት ቅጣት በጣም የሚታበዩ ሰዎች የሚቀጡበት ነው።

➯የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በትዕቢቱ ምክንያት ወደ አውሬነት ተለውጦ ቤተ መንግሥቱን ለቆ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ሰባት ዓመት ኖርዋል፡፡ (ዳንኤል 4፥28-34፡፡)


#ክፍል_ስድስት_ይቀጥላል
እንኩዋን ለቅዱስ "ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ "*+

=>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-

+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት - ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ (ደራጎን) ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) ደረሰ::

+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ "የሰማዕታት አለቃቸው" : "ፀሐይና የንጋት ኮከብ" በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ::
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ::" እንዲል መጽሐፍ::

+ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::

=>ይህቺ ዕለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያል ቅዳሴ ቤቱ ናት:: እርሱ በ390ዎቹ አካባቢ ሰማዕት ከሆነ ከጥቂጥ ዓመታት በሁዋላ በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው በዚህች ቀን ቀድሰዋታል::

+ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነውና አንዷን እንመልከት:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት (ነገሥታት) መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::

+በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::

+ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::

+እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7 ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::

=>አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::

+"+ ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ +"+

=>በቤተ ክርስቲያን "ጊዮርጊስ" የሚባሉ ብዙ ቅዱሳን አሉ:: ከልዳዊው ቀጥሎም ይህንን ግብጻዊ ሰማዕት እንጠቅሳለን:: ስሙ ጊዮርጊስ የተባለውም በታላቁ ሰማዕት አማላጅነት ስለ ተገኘ ነው::

+አባቱ ኅዳር 7 ቀን የሊቀ ሰማዕታትን ቅዳሴ ቤት ሊያከብር ሒዶ ስለተማጸኑ የሚስቱ ማሕጸን ተከፍቶለት ልጅ ወልዷል:: ስሙንም ጊዮርጊስ ብሎታል:: ባደገም ጊዜ እጅግ ብርቱ ክርስቲያን ሆነ::

+የግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብርታቱ ምንድን ነው ቢሉ:-ንጹሕ አምልኮቱ ጾምና: ጸሎቱ: በጐ ምጽዋቱ ነው:: "ስም ይመርሕ ኀበ ግብር - ስም ወደ ተግባር ይመራል" እንዲሉ አበው የሰማዕቱን ስም ይዞ እሱም ይሔው እድል ገጠመው::

+በአጋጣሚ ወላጆቹ ሲሞቱ የሚኖረው ከከተማው መኮንን ቤት ነበር:: ምክንያቱም የመኮንኑ ሚስት እህቱ ናትና:: ችግሩ ግን መኮንኑ አርማንዮስ ጣዖት አምላኪ: በዚያ ላይ ጨካኝ መሆኑ ነው::

+አንድ ቀን ግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመኮንኑን ሴት ልጅ ወደ በርሃ ወስዶ የደብረ ቁስቁዋም መነኮሳትን ዝማሬ አሰማት:: ክርስትናንም አስተማራት:: ይህንን የሰማው መኮንኑ ግን በብስጭት ቅዱስ ጊዮርጊስንና የራሱን ሴት ልጅ በአደባባይ አሰይፏቸዋል:: የክብርን አክሊልም ተቀዳጅተዋል::

+"+ ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ +"+

=>እነዚህ ቅዱሳን እናትና ልጅ ናቸው:: ዘኖብያ እናቱ ስትሆን ዘኖቢስ ደግሞ ወጣት ልጇ ነው:: የቅዱሳኑ ሃገር ደግሞ ተበይስ ትባላለች:: በዘመነ ሰማዕታት ድንቅ በሆነ ሕይወታቸውና ተአምራቸው እንደ ኮከብ አብርተዋል:: ከ5 ጊዜ በላይም ከተደገሰላቸው የሞት ወጥመድ በእግዚአብሔር ኃይል አምልጠዋል::

+ " ክርስትናችን አንክድም: ከክርስቶስ ፍቅር አንለይም በማለታቸው:-

1.ልብሳቸውን ገፈው: በዓየር ላይ ሰቅለው: ደማቸው እስኪንጠፈጠፍ ገረፏቸው:: በክርስቶስ ኃይል ተረፉ::

2.የእንጨት መስቀሎችን አሰርተው በአደባባይ ቸንክረው ሰቀሏቸው:: ከዚህም ዳኑ::

3.. 2 ወንበሮች ላይ ችንካሮችን ተክለው በዚያ ላይ አስቀመጧቸው:: አሁንም በፈጣሪ ኃይል ዳኑ::

4.ጥልቅ ጉድጉዋድ ተቆፍሮ: እሳትም ነዶ በዚያ ውስጥ ተጨመሩ:: ቅዱስ መልአክ ግን ወርዶ አጠፋላቸው::

5.አንዴ ደግሞ በቤት (በውሽባ ቤት) እሳት ነዶ በውስጥ ተጨመሩና ተዘጋባቸው:: እግዚአብሔር ግን ከዚህም ታደጋቸው:: ስለ ክብራቸውም ቅዱስ መልአክ ወርዶ እነሱን አክብሮ: መኮንኑን ዙፋኑን አሸክሞ በአደባባይ አዙሮታል::

+አንዴም ጋን አሸክሞ በሁዋላቸው አስከትሎታል:: በነዚህ ሁሉ ድንቆች ብዙ ሕዝብ እያመነ በሰማዕትነት ሙቷል:: በመጨረሻ በዚህ ቀን ዘኖብያና ዘኖቢስ ሲሰየፉ መብረቅ ወርዶ 54 አሕዛብን ገድሏል:: በዚህም መኮንኑ ተገርሞ በክርስቶስ አምኗል::

+"+ አባ ሚናስ ዘተመይ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት ደግሞ ጣዕመ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው በተክሊል አጋቡት:: ወደ ሙሽራይቱ ገብቶም "እህቴ! ይህ ዓለም ኃላፊ ነውና ለምን በድንግልና አንኖርም?" አላት::

+እርሷም በደስታ "ይሁን" አለችው:: ለበርካታ ዓመታትም ቀን ቀን ሥራቸውን ሲሠሩ: እንግዳ ሲቀበሉ ይውላሉ:: ሌሊት ደግሞ ወገባቸውን ታጥቀው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ያድራሉ::

+ከዓመታት የቅድስና ሕይወት በሁዋላም ቅዱስ ሚናስ ሚስቱን አስፈቅዶ በርሃ ገብቷል:: በተጋድሎ ሳለም እግዚአብሔር ለእረኝነት መርጦት: ተመይ በምትባል የግብጽ አውራጃ ላይ ዽዽስናን ተሹሟል:: በዚያም እስካረጀ ድረስ ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::

=>እንደ ደመና የከበቡን የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ በቸርነቱ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
ናሁ ሰማን(Nahu seman)
እንኩዋን ለቅዱስ "ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +*" ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ "*+ =>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:- +ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ…
=>ኅዳር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
3.ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ (ሰማዕታት)
4.ቅዱስ ሚናስ ዘተመይ
5.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ዮሐንስ (ጻድቃን ወሰማዕት)
6.አባ ናሕርው ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ:: በመጋዝ ተሰነጠቁ:: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:35-38)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
እንኳን አደረሰን


"ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም።"
(ስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ)
ገድለ ቅዱሳን

ወላጆቹ ስሙን በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰየሙለት።
በንጹሕ አምልኮት የኖረ
በጾምና: ጸሎት የኖረ
በጐ ምጽዋት የሚወድ
  የእስክንድርያ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከበረከቱ ይክፈለን::
+የግብጽ አረማውያን ገዢዎች እንደ ትልቅ ሥራ የሚያዩት አድባራትን ማቃጠል: ገዳማትን መመዝበር ነውና እርሱም ለዚሁ ሥራ ተነሳ:: ሠራዊትን አስከትቶ በሠረገላው ተጭኖ ወደ አንድ ገዳም ደረሰ:: ልክ የገዳሙን መሬት ሲረግጥ ግን በአንዴ ልቡናው ተሰበረ::+ሠራዊቱን ወደ ከተማ አሰናብቶ እርሱ ብቻውንወደ ገዳሙ ዘለቀ:: ወደ አበ ምኔቱም ቀርቦ ሰገደላቸውና እንዲያጠምቁት ተማጸናቸው:: እርሳቸውም አስተምረው አጠመቁት:: በዚያውም መንኖ መነኮሰ::

+ለዘመናትም በጠባቡ መንገድ ተጋድሎ ከጸጋ (ከብቃት) ደረሰ:: በአካባቢው ሰውና እንስሳትን የፈጀውን ዘንዶም ባሪያ አድርጐ ለ10 ዓመታት ገዝቶታል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በዚህ ቀን ዐርፏል::

=>አምላከ ቅዱሳን መላእክት እነርሱን ለረድኤት ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)
2.ቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት
3.አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ
4.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል)
5.ቅድስት እግዚእ ክብራ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
3.አቡነ ኪሮስ
4.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
5.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ በዙፋኑም መካከል: በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በሁዋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት እንስሶች ነበሩ:: ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል:: ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል:: ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው:: አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል:: አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሏቸው:: +"+ (ራዕይ. 4:6)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#ህዳር_8 #አርባዕቱ_እንስሳ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ህዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣

🔵👉 እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

🔶👉 የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

🔷👉 የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

🔴👉 ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

🔵👉 የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

👉 ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

🔵👉 በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

🔴👉 እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

🔷👉 ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

🔷👉 ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

🔵👉 በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

🔴👉 ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው።

🔷👉 ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

🔵👉 ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ
 
አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን ሰዐሉ በእንቲአነ
( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )  

🔷👉 ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
     አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።

🔷👉ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
🔷ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
🔷ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
🔷ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን

🔴የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።
ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን

🔴አንድም አርባዕቱ እንስሳት
በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ።
    
          🔵#አርባዕቱ_እንስሳት #በእመቤታችን_ድንግል_ማርያም_ይመሰላሉ። እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ ፤  ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና ።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
      ህዳር 8/2017 ዓ.ም

“ምን ፍሬ አፈራን?” ይለናል አባታችን ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡፡


“ልጆቼ! እስኪ ፍቀዱልኝና ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ ብዙውን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ትመላለሳላችሁ፡፡ መልካም ነው፡፡ ግን ምን ለውጥ አመጣችሁ? ምን ፍሬ አፈራችሁ? ታገለግላላችሁን? ከአገልግሎታችሁ ምን ረብሕ አገኛችሁ? ጥቅምን ካገኛችሁ በእውነት ምልልሳችሁ የጥበበኛ ምልልስ ነበር ማለት ነው፡፡ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ወንጌላውያን እንዲህ እያስተማሩን ሳለ የማንለወጥ ከሆነ ግን የእስከ አሁን ምልልሳችን የአይሁድ ምልልስ ነበር ማለት ነው፡፡

  አይሁዳውያን ሕገ ኦሪትን የተሰጠቻቸው ኃጢአታቸውን በእርሷ መስታወትነት አይተው ንስሐ እንዲገቡባት ነበር፡፡ እነርሱ ግን የንስሐ ፍሬ ሳያፈሩባት እንዲሁ ይመኩባት ነበር፡፡ ስለሆነም ለሕይወት የተሰጠቻቸው ሕግ ሞት ሆና አገኟት፡፡ እኛም እንዲህ ለኵነኔ ያይደለ ለጽድቅ የተሰጠችን ወንጌል ፍሬ የማናፈራበት ከሆነ ከአይሁዳውያን የባሰ ቅጣት ትፈርድብናለች፡፡ እስኪ ምሳሌ መስዬ ላስረዳችሁ፡፡ አንድ የሚታገል ሰው (wrestler) በየጊዜው ተጋጣሚውን እንደምን ማሸነፍ እንዳለበት ልምምድ የሚያደርግ ከሆነ ክህሎቱ ይዳብራል፡፡ ተጋጣሚውም በቀላሉ ማሸነፍ ይቻሏል፡፡ በየጊዜው ራሱን የሚያሻሽል (Update የሚያደርግ) ሐኪም ጐበዝ አዋቂና ሕመምተኞችን በአግባቡ የሚረዳ ይሆናል፡፡

በየቀኑ ቃሉ የሚነገረን እኛስ ምን ለውጥ አመጣን? ምን ፍሬ አፈራን? እየተናገርኩ ያለሁት ለአንድ ዓመት ብቻ በቤተ ክርስቲያን የቆዩትን ምእመናን አይደለም፡፡ እየተናገርኩ ያለሁት ከልጅነታችን አንሥተን በቤቱ ለምንመላለስ እንጂ፡፡ ይህን ያህል ዘመን በቤቱ እየተመላለስን ፍሬ ካላፈራን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን ብንመጣ ምን ጥቅም አለው? አባቶቻችን አብያተ ክርስቲያናት ያነጹልን ለምንድነው? ዝም ብለን እንድንሰባሰብ ነውን? እንደዚህማ በገበያ ቦታም መሰባሰብ አንችላለን፡፡ አበው አብያተ ክርስቲያናትን ያነጹለን ቃሉን እንድንማር፣ በተማርነው ቃልም የንስሐ ፍሬ እንድናፈራ፣ ሥጋ ወደሙን እንድንቀበል፣ እርስ በእርሳችን እንድንተራረም እንጂ ለሌላ ዓላማ አይደለም፡፡ ታድያ ምን ፍሬ አፈራን? …”

ከ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሓፍ
††† እንኳን ለአበው ቅዱሳን "318ቱ ሊቃውንት" ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ጉባኤ ኒቅያ †††

††† በዚህች ዕለት (ኅዳር 9 ቀን) በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::

እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:-
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)
4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)
5.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)
7.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)
8.ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ:
ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)
9.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)

ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው::

በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ነው ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው::

በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር::

ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ::

ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል::

ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት
ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው::

ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ
እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::

ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከ2ቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውነት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት:: በጉባኤው መጨረሻም:-
1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ::
2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ::
3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ::
4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ::
5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ::

ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን
ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል::

††† በየዘመኑም ዐርፈው ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን:
መምሕሮቻችን:
መሠረቶቻችን:
ብርሃኖቻችን:
ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
4.አባ ይስሐቅ ሊቀ ጳጳሳት
5.ሊቁ አካለ ወልድ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
3.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
4.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
5.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

††† "እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል:: ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" †††
(ማቴ. ፲፰፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በኒቅያ ጉባኤ ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው ድንቅ አባት ነው በእውነት  አንክሮ ይገባል!!)::"
     <<<ከበረከቱ ይክፈለን።>>>
የሰናፍጭ ቅንጣት [ማቴ. 13÷31]
ታላቅነትን በታናሽነት ሰውራ የያዘች እንከን የለሽ፤ ዙሪያዋን ቢመለከቷት ነቅ የማይገኝባት አስደናቂ ፍጥረት ናት፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በምሳሌ ካስተማረባቸው መንገዶች አንዱ ሰናፍጭ ነው፡፡ ስትዘራ ታናሽነቷ ስትበቅል ግን ታላቅነቷ የገዘፈ ምስጢር ያለው በመሆኑ ለዚህ ተመርጣለች በመጽሐፍ እንደተባለ ሰናፍጭ ስትዘራ እጅግ ታናሽናት ስትበቅል ግን ባለብዙ ቅርንጫፍ እስከመሆን ደርሳ ታላቅ ትሆናለች ከታላቅነቷ የተነሳ እጅግ ብዙ አእዋፍ መጥተው መጠጊያ እንደሚያደርጓትም አብሮ ተገልጿል አሁን ታናሽነቷን በታላቅነት መሰወር ችላለችና ብዙዎችን ልታስገርም ትችላለች፡፡

ይህ ምሳሌ ታላቅነትን በታናሽነት ሰውራ ይዛ የኖረችውን የክርስቶስ ቤተ ክርሰቲያን ነው እንጅ ሌላ ምንን ያመለክታል? የሰናፍጭ ቅንጣት ብሎ የጠራት አካሉ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ምክንያቱም እንደ ሰናፍጭ ሁሉ ሲዘራት ትንሽ ነበረች፡፡ በመቶ ሃያ ቤተሰብ ብቻ የተዘራች ዘር ናት፡፡ የእግዚአብሔርን ምስጢር ልብ አድርጉ ኦሪትን ሲመሰርት እንዲህ ነበርን? በሙሴ ምክንያት በስድስት መቶ ሺህ ሕዝብ መካከል የሠራት አይደለምን? ወንጌልን ግን እንዲህ አይደለም ከመቶ ሃያ በማይበልጡ ሰዎች መካከል ሠራት እንጅ፡፡ ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ የጥቂቶች ብቻ መሆኑን ሲያሳየን ይህን አደረገ፡፡

ሰናፍጭ ካደገች በኋላ ለብዙዎች መጠጊያ እስኪሆን ድረስ ብዙ ቅርንጫፍ እንድታወጣ ቤተ ክርስቲያንም የዓለም መጠጊያ የሰው ልጆች መጠለያ ናት፡፡ ኦሪት በብዙዎች መካከል የተሰበከች ብትሆንም ቅሉ ቅርንጫፏ ከቤተ እስራኤል ወጥቶ ለሞዓብና ለአሞን ስንኳን መጠጊያ ሊሆን አልቻለም፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ቅርንጫፏ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሶ ሰማያውያኑንና መሬታውያኑን ባንድ ማስጠለል ይችላል ሙታን ሳይቀር መጠለያቸው ቤተክርስቲያን ናት እንጅ ሌላ ምን አላቸው፡፡ ከዚህም የተነሳ "ሰናይ ለብዕሲ መቅበርቱ ውስተ ርስቱ፤ ለሰው በርስቱ ቦታ መቀበሩ መልካም ነው" እያሉ ሥጋቸውን በቤተክርስቲያን ነፍሳቸውን በገነት እንዲያኖርላቸው ይማጸናሉ፡፡

ቤተ ክርስቲያን እንደ ሰናፍጭ ካልቀመሷት በቀር ጣዕሟ የማይታወቅ ታናሽ የምትመስል የሰናፍጭ ቅንጣት ናት ለቀመሷት ሁሉ ደግሞ ጣዕሟ በአፍ ሳይሆን በልብ የሚመላለስ ከደዌ የሚፈውስ ነውና ቀርባችሁ ጣዕመ ስብከቷን፣ ጣዕመ ዜማዋን፤ ጣዕመ ቅዳሴዋን እንድትቀምሱ አደራ እላችኋለሁ፡፡ ከዚሁሉ ጋራ ርስታችሁ ናትና ከአባቶቻችሁ በጥንቃቄ እንደ ተረከባችሁ ለቀጣዩ ትውልድ እስክታስረክቡ ድረስ የተጋችሁ እንድትሆኑና የጀመራችሁን መንፈሳዊ ተጋድሎ በትጋት እንድትፈጽሙ መንፈስ ቅዱስን ዳኛ አድርጌ አሳስባችኋለሁ፡፡

ኃያሉ አምላክ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሀገራችን ኢትዮጵያን አንድነት የኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተ ክርስቲያናችንን ዕድገት ለዘለዓለሙ ይባርክ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
2024/11/18 05:55:32
Back to Top
HTML Embed Code: