Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1295 - Telegram Web
Telegram Web
📜"ለእኔ ሕይወት #ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" [ፊል 1፥21]

እነኾ ምሳሌ፦
በምንኩስና ይኖር የነበረ አባት ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ ገነት ሄደ። ከውጭም ቆሞ እንዲከፈትለት ደጁን ያንኳኳ ጀመር። ወዲያውም "ማን ነኽ?" የሚል ድምጽ ከውስጥ ሲወጣ ሰማ። መነኩሴውም "እኔ ነኝ" ሲል መለሰ። ይኹን እንጂ ያንኳኳው በር ግን ሊከፈትለት አልቻለም። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም  እንደ ገና  ተመልሶ ወደ ገነት በመምጣት ደጁን አንኳኳ። እንዳለፈውም ጊዜ ከውስጥ "ማን ነኽ?" የሚል ድምጽ ሰማ። እርሱም እንደ ለመደው "እኔ ነኝ" አለ። አኹንም በሩ ሳይከፈትለት ቀረ።

መነኩሴው በዚህ ተስፋ አልቆረጠም። ይኽ ከኾነ ከብዙ ዓመታት በኋላ እርሱም በመንፈሳዊው ጥበብ ጎልምሶ ተመልሶ ወደ ገነት ሄዶ በሩን አንኳኳ። እንደ ከዚኽ በፊቱም "ማን ነኽ?" የሚል ድምጽ ሰማ። ያም አባት የቀድሞው መልሱን ተወና "በእኔ ውስጥ የምትኖረው አንተ ነኽ" ሲል ለጠየቀው አካል መለሰ። በዚህ ጊዜ ተዘግቶ የነበረው በር ተከፈተለት ይባላል።

#ክርስትና ምንድር ነው? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ ማብራሪያዎች ሊሰጡ ይችላሉ። በአጭሩ ግን እንመልሰው ካልን፣ ክርስትና ማለት " #ክርስቶስ የሚያድርበት መቅደስ መሆን " ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲገልጽልን "እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም #ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል" ይለናል።(ገላ 2፥20) #ክርስቲያን ማለት "አንተ ማን ነኽ?" ተብሎ ሲጠየቅ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "በእኔ የሚኖር #ክርስቶስ ነው"፣ "አነ #ዘክርስቶስ" - "እኔ #የክርስቶስ ነኝ" ብሎ መመለስ የሚችል ነው።

#ጌታችን በወንጌል ለደቀ መዛሙርቱ "በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ" ሲል እንደ ተናገረ፣ እኛ #ለክርስቶስ መኖር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ይኖርብናል፤ እኛ #ለክርስቶስ ማደር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ያድርብናል። (ዮሐ 15፥4)

እንዲህ ያለውን ሕይወት የሚኖር እውነተኛ ክርስቲያን የሥጋን ሞት አይፈራም። ስለ ሃይማኖቱ መከራ መቀበልን አይሰቀቅም። #ክርስቶስን ከሚያሳጣው ሕይወት ይልቅ ወደ #ክርስቶስ የሚወስደውን ሞት ይመርጣል። ፈጣሪው ከሌለበት ምቾት ይልቅ ፈጣሪን ይዞ መሰቃየት ለእርሱ ያስደስተዋል።

ሰይፍ ይዘው በሚያስፈራሩትም ጨካኝ ወታደሮች ፊት "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" እያለ በሐሴት ይዘምራል። (ፊል 1፥21)

=======

በሰይፍ ለሚገድለው ወታደር በኩራት የልብሱን ኮሌታ ከፍ አድርጎ አንገቱን ስለ #ክርስቶስ በደስታ ለሰጠ፣ ለታላቁ ሐዋርያ #ለቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነት በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!

የአገልግሎቱ ድካም፣ በረከት በሁለችን ላይ ይደርብን!!!

✍️ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://www.tgoop.com/nshachannel
1
ገላትያ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።
¹⁷ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።
¹⁸ በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።
¹⁹ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥
²⁰ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥
²¹ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
²² የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
²³ እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።
²⁴ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።
²⁵ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።
²⁶ እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።

https://www.tgoop.com/nshachannel
1👍1
2025/07/14 12:34:50
Back to Top
HTML Embed Code: