ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም
❤4🙏1
ራስን መውቀስ
በአንድ ወቅት ምህረትን ለሰዉ ብታደርግ ምህረት ባላሰብከው ጊዜ ይደረግልሃል።
በመከራ ላይ ላለ ሰው ርህራሄ ብታደርግለት ከሰማዕታት እንደ አንዱ ትቆጠራ ለህ።
የሰደበህን ሰዉ ይቅር ብትለው ሀጢያትህ ይቅር የሚባልልህ ብቻ ሳይሆን የሰማይ አባትህ ልጅ መሆን ይቻልሃል።
ስለድኅነት ጥቂት እንኳን ብትጸልይ ድህነትን መፈጸም ይቻልሃል።
ራስህን ብትወቀስ ፣ራስህን ብትከስስ ፣ በእግዚአብሔርም ፊት በራስህ ላይ ብትፈርድ በተጸጸተ አዕምሮ ሆነህ ትጸድቃለህ።
ስለኃጢአትህ ብታዝን ብታለቅስም ሀዘንህ ከእርሱ የተሰወረ አይሆንም።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ስለኃጢአትህ ብታለቅስ ድህነትን ታገኛለህ።
እርሱም ለድህነትህ መንገድ ይሆነሃል።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️

👍8
+ አባ ይርማስ +
ዐቢይ ጾም ውስጥ ለአገልግሎት ወደ ወልድያ ሔጄ ነበር:: በረሃብና በጦርነት አለንጋ እየተገረፈ ዓመታትን ያሳለፈውንና በእሳት የተፈተነውን ሕዝበ ክርስቲያን ለቃለ ወንጌል ጉባኤ የሰበሰበው ይህ ዕለት በርካታ ልብ የሚነኩ ትምህርቶች ያገኘንበት ነበር:: ከሁሉ የሚደንቀው የጉባኤው ትንግርት ግን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ነበሩ::
ብፁዕነታቸውን የማውቃቸው ከጵጵስና በፊት በምንኩስናቸው ጊዜ ለአንድ አገልግሎት ታጭተው በአንድ ሊቀ ጳጳስ ጽሕፈት ቤት በተጠሩ ጊዜ እኔም በተመሳሳይ ምክንያት ተገኝቼ በነበረ ወቅት ነው:: በወቅቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁዋቸው እኚያ ትሑት መነኩሴ ወደ ውጪ ሀገር ለቋሚ አገልግሎት እንዲሔዱ ሲጠየቁ በትነውት ሊሔዱት የማይችሉት የወታደሮችና የፖሊሶች ጉባኤ እንዳላቸው ሲናገሩ ሰምቼያቸው ነበር:: በእርግጥም በዚህ ደረጃ ለነፍሳት የሚገደውን አባት በየሥፍራው እግዚአብሔር እንደሚያስቀምጥ በመጽሐፍ ያነበብኩትን በዓይኔ ሳይ በጣም ተደንቄ ነበር::
ከዓመታት በኋላ "በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ" የሚለው ቃል ተፈጽሞ ስለአንድ ጉባኤ የሚገዳቸውን ትሑት አባት ጳጳስ ሆነው ተሹመው ሳይ "ለቤተ ክርስቲያን ቅን መሪን የሚሠጥ" እግዚአብሔር አመሰገንሁ::
ብፁዕነታቸው ከጵጵስና በኋላ ምን እንደሠሩ እኔ ከምነግራችሁ ይልቅ "ዕድሜያቸውን ሳብ ያርግልኝ" ያለውን ሙስሊም ስሙት :-
"ወላሂ እኚ ቄሱ ማን ነበር ስማቸው እኛ ቄሱ ... ሙስሊም ክርስቲያን ሳይሉ ሕይወቱን ያተረፉት እኚያ ቄሱ .. እየለመኑ ሕይወቱን ያተረፉት ቄሱ ናቸው ... የወልድያ ቄስ የወልድያ ቄስ የኪዳነምሕረት ቄስ ... ይቅርታ አድርግልኝ አባ ይርማስ ይባላሉ ቄሱ"
ብፁዕነታቸው አባ ይርማስ በእርግጥም እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትነው በሠሩት የአባትነትና የእረኝነት ሥራ ምክንያት ከግለሰብነት ገዝፈው ተራራ ሆነዋል:: በነገራችን ላይ ወልድያ በስማቸው ተራራ ሰይማ "አቡነ ኤርምያስ ተራራ" ብላለች::
ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ ክፍተት ሳይሸሽጉ "ተቅዋማዊ እንክብካቤ ሳናገኝ እዚህ ቦታ ላይ ስለተቀመጥን አግዙን" በሚል ትሕትናን የተሞላ ንግግራቸው ራሳቸውን የሕዝብ አገልጋይ አድርገው ሰይመዋል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ለአንድ ክርስቲያን ዓለም ሀገረ ስብከቱ ነው:: ለአንድ ሊቀ ጳጳስ ግን ሀገረ ስብከቱ ዓለሙ ነው" ያለውን በተግባር እያሳዩ ካሉ ብፁዓን አባቶች አንዱ ናቸው::
በሀገረ ስብከታቸው እየሠሩት ያለው አብነት ትምህርትን ከዘመናዊ ትምህርት ያስተባበረ ግዙፍ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ከነገዋን ቤተ ክርስቲያን ሕልውና በትምህርት ዓለት ላይ የሚያጸና ድንቅ ፕሮጀክት ነው::
በብፁዕነታቸው ሀገረ ስብከት ቆይታችን ወቅት ያየሁት ሌላ ድንቅ ነገር ብፁዕነታቸው በሥራ የሚመሩትን ሀገረ ስብከት በአማካሪነትና በጸሎተ ቡራኬ የበላይ ሆነው አብረው የሚመሩ አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መኖራቸውን ማየታችን ነው::
ብዙ መጻሕፍትን የጻፉትና እጅግ ተወዳጅ ስብከቶቻቸውን ከበሳል ንግግሮቻቸው ጋር ከልጅነታችን ጀምሮ የምናነብና የምንሰማላቸው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በሕይወተ ሥጋ ሳሉ በዕርግና ምክንያት ሥራ እንዳይበደል ከእርሳቸው ጋር የሚሠሩ ወጣት ጳጳስ አስሹመው እርሳቸው በካበተ ልምዳቸውና መንፈሳዊ ዕውቀታቸው እያማከሩ ሥራውን በአዲስ ጉልበት እያፋጠኑት ነው::
ይህንን ሳይ ወደ ወልድያ የመጣሁት ለጉባኤ ሳይሆን ሙሴና ኢያሱን ፤ ኤልያስና ኤልሳዕን ፤ ዮሐንስና አብሮኮሮስን ፤ ጳውሎስና ጢሞቴዎስን ፤ ጴጥሮስና ቀሌምንጦስን በአካል አግኝቼ ቡራኬ ለመቀበል እንደሆነ ገባኝ:: ከሁለቱ አበው ጋር ባመሸንበትና ብዙ ሊጻፍ የሚችል ቁምነገር በተጨዋወትንበት ጊዜ ትሕትናን ፍቅርን ለቤተ ክርስቲያን ሕይወትን መሥጠትን በብዙ ያየሁበት ሌሊት ሲሆን የበረከት ሥጦታና ጸሎት ተቀብለን ስንወጣም ነፍስ አልቀረልንም ነበር::
ከዚህ በላይ ላስቀናችሁ አልፈልግም:: የሁለቱን አበው ቡራኬ የምትፈልጉ ሰዎች የፊታችን ሰኔ 25 እዚህ አዲስ አበባ ይመጣሉ::
አቡነ ቄርሎስ እንደ ኤልያስ "ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን" እያሉአችሁ ነውና ከብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ጋር እንደ ኤልሳዕ "መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ" በሉአቸው::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 17 2015 ዓ.ም.

❤5👍1
ወጣት ነህን?
ወጣት ነህን ወጣት በመሆንህ ገና ብዙ ዘመን አለኝ ዕድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን ተለክቶ የታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለህም አድርገህ አታስብ ‹‹የጌታ ቀን ድንገት እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና›› 1ኛ ተሰ5፤2 ስለዚህ ምክንያት የእድሜያችንን መጨረሻ አስቀድመን እንዳናውቀው አደረገ ከዛሬ ዕለት ጀምሮ በትጋት ዝግጅታችንን እንጀምር ዘንድ በለጋ ዕድሜያችን ሲቀጩ በየቀኑ አታይምን ስለዚህም አንዱ ሲመክር እንዲህ ብሏል “ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከዛሬ ነገ እመለሳለሁ እያልህ አትቁጠር” ሲራ 5፤8 ዛሬ ነገ እመለሳለሁ ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ፤ ስለዚህ ሽማግሌውም ይህንን ምክር ልብ ይበል ወጣቱም ይህንን ነገር ተረድቶ ተግባራዊ ያርግ ዘንድ ይሁን ወይስ በምቾትና ሁሉ ነገር ተሟልቶልህ የምትኖር እስካሁን ችግር የሚባል ደርሶብህ የማታውቅ ባለጸጋ ነህን እንዲህም ቢሆን ቅዱስ ጳውሎስ የሚለውን ስማው “ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል” 1ኛ ተሰ 5፤3 የዚህ ዓለም ነገሮች ሁሉ ተለዋዋጮች ናቸው እኛ በራሳችን የወደፊት ሕይወትና ሁኔታ ላይ ማዘዝ የምንችልና የሰለጠን አይደለንም ነገር ግን በጽድቅ ሥራ ላይ የሰለጠንን እንሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና››
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ ገጽ 134

❤3
"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"
[ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ]
አብዛኞቻችን ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር መሆኑን እናውቃለን። ግን ስንቶቻችን እንሆን ከምንወዳቸው ጋር ለመነጋገር የምንወደውን ያህል ከአምላክ ጋር ለማውራት የምንቸኩለው? ጸሎትን ስናደርግ ከመላእክት ጎን እንደቆምን የሚሰማን ስንቶቻችን እንሆን? መላእክትስ የእኛን ጸሎት ለማሳረግ እንደሚጠብቁን፣ የጸለይነው ጸሎት አርጎ መንበረ ጸባኦት እንደሚደርስ የምናስበው ስንቶቻችን ነን? በእውኑ ጸሎታችን እንደ አቤል ያለ ንጹሕ መስዋዕት ይሆን ወይስ እንደ ቃየል የተልከሰከሰ መስዋዕት፤ እንዲያ በችኮላ፡ በቸልተኝነት፡ ያለ ተመስጦ የጸለይነውን ጸሎት ያደረስነውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ፊት ልናቀርበው እንዴት እንሻለን? እኛ የትኛውን ነን? ጸሎት ሲያደርስ በእሳት ነበልባል እንደተከበበ በቅዱሳን መላእክቱ በቅዱሳን ነቢያቱ በቅዱሳን ሐዋርያቱ በቅዱሳን በቅዱሳኑ ሁሉ ፊት እንደቆምን፣ የምንጸልየውንም ጸሎት እንደሚሰሙን፣ የሚሰማን ስንቶቻችን እንሆን? “እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማስተዋል ዘምሩ።” መዝሙር 46፥7
በፍርሀት ፣ በተመስጦ ፣ ሆነን፦ “እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።” ሉቃስ 17፥21 እንዳለ፤ በእግዚአብሔር መንግስት መካከል እንደቆመ ሰው የማንሆነው እስከ መቼ ነው? “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል አለው።” ኢሳይያስ 38፥1 ተብሎ ብዙም ሳይቆይ "ኢሳይያስ 38² ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ ³ አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ። ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ። ⁴ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ ⁵ ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ።" የተባለው የእግዚአብሔርን ልብ በምታራራ ጸሎት ነውና በሉ ከእንግዲህ ቤታችንን በጸሎት እናስተካክል፤ ለእግዚአብሔር እንደተገባ አድርገን እናስተካክለው።
"1ኛ ጴጥሮስ፡ 1¹⁵-¹⁶ ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። ¹⁷ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።"

ከወደቀ ነገር ሥራን የሚሠራ አምላክ
(ዲ/ን ሕሊና በለጠ)
የተቀበረ (የተጣለ) ስንዴ እንዲበቅል የሚያደርግ እግዚአብሔር ከወደቀ ነገር ሥራን መሥራት ያውቅበታል። አበቃለት የተባለ ጉዳይ ላይ ሕይወት መዝራትን ይችላል። ብዙ ጊዜ "አከተመልኝ" ስንል እርሱ ሥራውን ይጀምራል። ምንም አይጠቅሙም የተባሉትን አንሥቶ መቀደስና ለዓለም እንዲተርፉ ማድረግ ያውቃል።
ቀለም አይዘልቅለትም የተባለው፣ በአገልጋዮቹ ዘንድ የተናቀው፣ የተጻፈን እንኳን ለመረዳት እንደሚያዳግተው ተደርጎ የሚታወቀው አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያምን ይደርሳል ብሎ ማን አሰበ? "የኢትዮጵያ ነገረ መለኮት" ሲባል ከቅዱስ ያሬድና ከአባ ጊዮርጊስ አስተምህሮ በላይ የሚነገርለት ሊቅን ማግኘት አይቻልም፤ ታዲያ እኚህ አበው በትምህርት የወደቁና ቀለም አይዘልቃቸውም የተባሉ አልነበሩምን? እግዚአብሔር ሲሠራ እንዲህ ነው። "ወደቁ፣ ቀለም አይዘልቃቸውም" የተባሉትን ለሺህ ዘመናት የማይዘለቅ ቀለምን እንዲያፈልቁ ያደርጋል።
የደረቀን በትር ማለምለም፣ በእኩለ ሌሊት መብራትን ማብራት፣ የሞተን ማስነሣት፣ በማዕበል ውስጥ ማንሳፈፍ፣ ደም ማየት ላቆመች እናት ልጅ መስጠት፣ በፍርስራሽ ውስጥ ማነጽ፣ በብስባሽ ውስጥ ማብቀል ለእርሱ (ከበጎ ፈቃዱ ጋር) ተግባሩ ነው። "የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል"። (2ሳሙ. 14:14)።
ወድቀው የተነሡትን እንዘርዝር ካልን ጊዜ አይበቃንም። ክርስቲያን ራሱ "ሰባቴ ይወድቃል፤ ሰባቴ ይነሣል" ይባል የለ!
ወድቆ መነሣት ብቻ ሳይሆን ሰዎች የጣሉትን እያነሡ የተነሡ ብዙዎች ናቸው። እግዚአብሔር የሚረዳን ለሰዎች ብርቅ የሆነውን ነገር በመስጠት ብቻ አይደለም፤ ሰዎች የናቁትንና የጣሉትን እየሰጠንም ጭምር እንጂ። እስራኤላውያን በእርሻዎቻቸው ሰብልን ሲሰበስቡ ቃርሚያን ሆን ብለው ለእንግዳና ለተቸገሩት፣ ለወፎችም ይተዋሉ እንጂ ጨርሰው አይቃርሙም። መጽሐፍ "የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ" የሚለው ለዚህ ነው። (ዘሌ.19:10)። ስለዚህ ሆን ብለው ከእህላቸው ይተዋሉ፤ ይጥላሉ። የተተወውን አንሥተው የሚነሡ አሉና። ሩት የቦኤዝን አዝመራ ስትቃርም የነበረው ስለዚህም ነው።
ለድሆች መጣል አንዱ የጽድቅ መንገድ ነው። ከአበው አስተምህሮ አንዱን እናንሣ። የላመ የጣመ የሚበላ አንድ ባዕለ ጸጋና የሚላስ የሚቀመስ የሌለው አንድ ምስኪን ደኻ ነበሩ። ከቀናት በአንዱ: ምስኪኑ ደኻ ወደ ባዕለ ጸጋው በመሔድ ይመጸውተው ዘንድ ይለምነዋል። ባዕለ ጸጋው ግን የልመናውን ድምጽ ሲሰማ ከመራራት ይልቅ ይረበሽና ሊያባርረው ይሞክራል። የኔ ቢጤው ግን ይህን ሳይረዳ ልመናውን ቀጠለ። በመሆኑም ባዕለ ጸጋው በብስጭት የሚወረውርበትን ነገር ሲፈልግ ሳይበላ ተረስቶ የደረቀ ዳቦን ያገኝና በዚያ የደረቀ ዳቦ ወርውሮ ይፈነክተዋል። ምስኪኑ ድኻ ግን ከተፈነከተበትና ከደማበት ድርጊት ይልቅ የርኃቡ ሕመም በልጦበት ነበርና በውኃ አርሶ ሊበላው ዳቦውን አንሥቶ እያመሰገነ ሔደ። ባዕለ ጸጋውም በቅድመ እግዚአብሔር በመላእክተ ጽልመት ቢከሰስም በዚህ ደኻና በመላእክተ ብርሃን ምስክርነት "ፈንክቷል" ሳይሆን "መጽውቷል" ተብሎ ይህ ድርጊቱ እንደ ጽድቅ ተቆጠረለት።
እንዴት ይደንቃል!? ቸርነቱ እንደ ባሕር ጥልቀት፣ ምሕረቱ እንደ ጠፈር ምጥቀት የሰፋው አምላካችን ከጣልነው ነገር ላይ እንኳን በጎውን ይፈልግልናል፤ መወርወራችንን ምጽዋት የሚባልበትን መንገድ ይፈልግልናል። እርሱ የሚምርበትን መንገድ ቢያሰፋውም እኛ የምንጠፋበትን መንገድ እያበዛን አመፅን እንጂ!
ከላይ ከተነሣው ታሪክ ጋር የሚመሳሰል አንድ ነገር በዚህ በማኅበራዊው ሚዲያ ሲዘዋወር ደንቆኝ ስመለከት ነበር። በእግር ኳሱ ዓለም እጅግ ታዋቂውና የፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን አጥቂና አንበል የሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከወራት በፊት ሀገሩ ከሰርቢያ ጋር ስትጫወት ባለቀ ሰዓት ጎል ያገባል። የጨዋታው የመሃል ዳኛ ጎሉን በስሕተት ይሽሯታል። በዚህም ምክንያት በጎሉ ትክክለኝነት እርግጠኛ የነበረው ተጨዋቹ ብስጭቱ ከቁጥጥሩ በላይ ሆነበት። በመሆኑም ክንዱ ላይ ያሠረውን የአንበልነት ምልክት አውጥቶ በንዴት ጣለውና ከሜዳ ወጣ።
ይህን የአምበልነት ምልክት አንድ ምስኪን ሰው አንሥቶት ከጊዜያት በኋላ ለጨረታ አቀረበው። በዚህም ከ75,000 ዶላር በላይ አገኘበት። የተጣለውን ያነሣው ይህ ልባም ሰው ግን ገንዘቡን በሙሉ ለአንዲት በአቅም ምክንያት በሕመም ትሰቃይ ለነበረችና ቀዶ ጥገናን ለማድረግ አቅም ላልነበራት የስድስት ወር ምስኪን ሕፃን ለገሰው። ሕፃኗም የተሳካ ቀዶ ጥገና ተደርጎላት ከሞት ተረፈች።
እግዚአብሔር ሥራን የሚሠራበት መንገድ ረቂቅ ነው። በሰው ተሰልቶ ሊደረስበት የሚችል አይደለም። አንዳንድ ጊዜ "ለምን ይህ ሆነ?" ብሎ ፈጣሪን ማማረር በደል ይሆን? እርሱ "ለምኑን" የሚመልስበት ጊዜም ምክንያትም አለውና። የሆነው ሁሉ እኛ ካመንን ለሚመጣው በጎ ነገር መነሻ ነው። ካመንን።
ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! ወደቅኩ ብለህ አትዘን። እንዲያውም ካመንክ እርሱ ሥራውን በወደቁት ላይ መሥራትን ያውቅበታል። ብትሞት እንኳን ትንሣኤ ያለው የሚሞት እንደ ሆነ አትርሳ። "ሁላችን እንሞታለን፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ ነን፤ እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወድድም፥ ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል" (2ሳሙ.14:14)። የተጣለ፣ የተናቀ ደረሰኝ ብለህም አትቆጭ፤ እመን እንጂ በተጣለ ነገር መነሻነት ማንገሥን እርሱ ያውቅበታል።
ወዳጄ ሆይ! የማይጠቅምህንም ስትጥል የሚያነሣው እንዳለ እያሰብክ ይሁን። ተለብሶ ያለቀው ልብስህ ለአንዳንዶች የክት ልብስ ነው። ተበልቶ የተረፈውና የሻገተው ምግብህ ለአንዳንዶች የበዓል ምግባቸው ነው። ተደርጎ ያለቀው ጫማህ ለብዙዎች የቅንጦት መኪናቸው ነው። ስለዚህ አለቃቀምህን ብቻ ሳይሆን አጣጣልህንም አስብበት።
የተጣለን የማይረሳ የወደቀን የሚያነሣ አምላክ በምሕረት ዓይኑ ያየን ዘንድ፣ ለዚያ የሚያበቃ ትንሽ እምነትን ያድለን!
ፎቶ:- የተጣለው የሮናልዶ የአምበልነት ምልክት ባነሣው ሰው እጅ።

👍6❤2
ስንክሳር ሠኔ 21 ቅዱስ ቶማስ
በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል።
ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ። ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን "ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሽሹ።" ብሎ መከራቸው።
ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል። ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት።
እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል። የሠራው ሥራ (መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው። በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?" ሲል ጠየቀ። ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ። ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና "ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ።" አለ። ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች።
ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው። እርሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ። ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን አምጡልኝ።" አለ። የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል 'የገደልኩሽ እኔ፤ የሚያስነሳሽ ግን ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።' ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው። እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች። ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል።
ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን።
ሠኔ ፳፩ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫.ቅዱሳን ሐዋርያት
፬.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፭.ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ
፮.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፯.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፰.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር (ሰማዕት)
፱.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ጳጳሳት
"ስለ ጽዮን ዝም አልልም።
..... አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ። የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ። በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።"(ኢሳ ፷፪፥፩-፫)
የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ፡ ፍቅሯ፡ ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

❤5👍3
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል?
የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ መናገር ያምረኛል፡፡...
ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት! ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች።
[ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ]
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል?
በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕትና እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡ የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ መናገር ያምረኛል፡፡...
ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት! ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች።
[ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ]
❤8🙏2🥰1
"አለሙም ምኞቱም ያልፋል"
ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ፤ ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።
ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ፤ ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም፤ በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ፤ መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም።
ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን፤ ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ።
ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው።
"ዓለም ሳትንቅህ በፊት ናቃት!!!"

❤4
✝ ምክረ አበው ✝
#ተግሳጽ ነፍስን በመልካም ምግባር ለማጠናከር ምክንያቷ ነውና ተግሳጽን ውደድ።
#በሌሎች ላይ እርማትን ከመሰንዘር በፊት የራሳችንን ስህተት ማረም ይጠቅማል ።
#አንዳንድ ስዎች ነጻነት የሚለውን ቃል የሚረዱት የወደዱትን ሁሉ የመፈጸም ፈቃድ አድርገው ነው። ሰዎች አብዝተው ራሳቸውን የኃጢአት ባሪያ እያደረጉ በመጡ መጠን ህጉን ለራሳቸው እንዲስማማ አድርገው ሊተረጉሙ ይዳዳቸዋል። እንዲህ አይነት ሰዎች ውጫዊ ነጻነትን የሚጠቀሙበት በተሳሳተ መንገድ ነው።
(ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ)
#ሞትን አትፍራ ሀጢአትን ፍራ።
#ስለ መተላለፋችን ምንም አይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር።
#አለም አንተን ሳትንቅህ አስቀድመህ ናቃት።
(ቅዱስ አትናቴዎስ)
@nshachannel @nshachannel
@nshachannel @nshachannel
@nshachannel @nshachannel
please share✝✝✝ORTHODOX

🥰3
በወንጌል የተባለውን አልሰማችሁምን?
¶ስጡ ይሰጣችኋል፤ አበድሩ፤ የማያረጀውን የማይጠፋውን በሰማይ ያበድራችኋልና፡፡
¶ዳግመኛም በመጽሐፍ ቃል በምድር ያላበደረ በሰማይ የሚያበድረው የለም፡፡
¶በምድር ማደሪያውን ያልፈለገ (ያላዘጋጀ) በሰማይም ማደሪያ አያገኝም፤ በምድር እያለ ያልራራ ሰው በፍርድ ቀን በሰማይ የሚራራለት የለም፡፡
¶በምድር በሕይወት እያለ ንስሐ ያልገባ(ያልተጸጸተ) ከሞተ በኋላ ንስሐን አያ ገኝም፡፡
¶ሰው ከስንፍናው የተነሣ በሕይወቱ መልካምን ባለማድረጉ ምንኛ ሰውነቱን አጠፋ(ጎዳ)፡፡
¶ካልተጠቀመ ዕለተ ሞቱንስ ካላወቀ፣ ገንዘቡንም ካልወሰደ ምን ይጠቅመዋል።
¶ነፍሱ በመፍራት፣ በመንቀጥቀጥ ራቁቷን ከሰማያዊው ከእግዚአብሔር ፊት
ትደርሳለችና።
¶መላእክትም ወደ ሚነድደው እሳት ይነጥቋታል፡፡
¶ይህችን ምድር (ዓለም) ሳታስረጀን እናስረጃት፡፡
¶ከእርሷ ወጥተናል(ተገኝተናል) ሁላችንም በመሬት የተደሰትነው ሁሉ ወደ እርሷ እንመለሳለንና ኃላፊ ናት፤ ሰነፍ፣ ምድራዊት ናት፡፡
¶እንደ ልብስ ታረጃለች እንደ ጥላ ታልፋለች ለዘለዓለሙ ኅልፈት የሌለባት ቤታችን ማደሪያችን በዚያ(በሰማይ) ናትና፡፡
ርቱዓ ሃይማኖት
ምንጭ፦ አምደ ሐይማኖት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

👍9❤1👏1
"በተፈጥሮዬ ደካማ ነኝ በሚል ሰበብ፤ ሴት ልጅ በገዛ ራሷ ላይ ስንፍናን ማንገሥ የለባትም!!!
ምክንያቱም ድክመት በሥጋ፥ ጥንካሬ ደግሞ በመንፈስ ናቸውና። ሴት ልጅ በተፈጥሮዋ የቅልጥፍና፣ የጥንካሬና የወሳኝነት ችሎታን የተላበሰች ናት። የሚጠበቅባትን ያመነችበትን ለመፈጸምና ራሷን ለተቀደሰ ሕይወት ለማስገዛት ምንም አያግዳትም። እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ከወንዶች እንደሚያይሉ የሚገልጹ ጽሑፎችን እናገኛለን። ስለዚህ ማንም ቢሆን፥
የሥጋ ስንፍናውን ወይም ዝለቱን ለቦዘኔነቱ እንደ ምክንያት ማቅረብ የለበትም።"
[ቅዱስ ጎርጎርዮስ]

👍4❤3🙏1
ራስን መንቀፍ
ራሱን የማይነቅፍ ሰው እርሱ ትክክል እንደሆነና እንዳልተሳሳተ አድርጎ ስለሚያስብ ምንም አይነት ስህተች ቢሰራ እንኳ ይቅርታ አይጠይቅም። ከወንድሙ ጋር ሲጋጭ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ራሱን አያነሣሣም። እርቁ እንዲመጣ የሚፈልገው ከሌላ ወገን ነውና። ግን ለምን? ይህን የሚያመጣው ማንነት ነው! ሌላው ቢቀር እኔነቱ ምንም አይነት ስህተት እንዳልሠራ አድር ስለሚያሳምነው ስህተቱንም በእግዚአብሔር ፊት እንኳ እይናዘዝም።
ራስን መንቀፍ የሚመጣው ከትሕትና ሲሆን ትሕትና ደግሞ ራስን ወደመካድ ይመራል። ትሑት ያልሆነ ሰው ራሱን አይነቅፋም አይኮንንም። ሁልጊዜ የሚነቅፈው ሆነ የሚኮንነው ሌሎችን ነው። እንዲህ ዓይነቱን ሰው ለምን ሌሎችን እንደሚነቅፍ ብትጠይቁት ይህን በማለታችሁ ብቻ እንኳ ይገሥጻችኋል።
አንድ ራሱን ምንጊዜም በዓለማዊ ዘዴዎች የማያጎላና የማያከብር ሰው ዋናውና ተቀዳሚው ዓላማው ራሱን ከስህተትና ከጥፋት ማንጻት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ሁልጊዜ ራሱን ይወቅሳል፣ ስህተቶቹን ይመረምራል፣ ለስህተቶቹም ማስተካከያ ይወስዳል፡፡
በአንድ ወቅት ጳጳሱ ቴዎፊለስ መነኮሳት አባቶች የሚኖቱበትን በአት ሲጎበኙ የዚያ ቦታ አስጎብኚ ለሆኑት መነኩሴ በዚህ ሳሉ ስለገኟቸው ቅዱስናዎች ሲጠይቋቸው “እመኑኝ አባቴ! ከሁሉም ነገር በላይ ራስን ከመውቀስ የሚበልጥ ቅድስና የለም!” በማለት መልሰውላቸዋል፡፡ ይህ አንድ ሰው ራሱን ብቻ እንጂ ሌሎች ሰዎችን፣ አካባቢውንና እግዚአብሔርን የማይወቅስበት መንፈሳዊ መንገድ ነው፡፡
ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የወቀሰ ሰው በወዲያኛው ዐለም ከመወቀስ ይድናል። ሰው ራሱን የሚወቅስበት ምክንያት ወደ ንሰሐ ለመቅረብ ነው። ንሰሐ ከገባ ደግሞ እግዚአብሔር ሐጢያቱን ይቅር ይለዋል። ራሱን ከማክበር አንጻር ራሱን የማይወቅስ ሰው ግን ሳይሻሻል በሐጢያት ውስጥ በመወቀስ ይኖራል።
ቅዱስ እንጦንስ “እኛ ራሳችን ከወቀስን ዳኛው በእኛ ይደሰታል።” ብሎ የተናገረው ምንኛ እውነት ነው! ከዚህ በመቀጠልም “እኛ ሐጢያቶቻችንን የምናስታውሳቸው ከሆነ እግዚአብሔር በንሰሐ ይረሳልናል፤ እኛ ሐጢያቶቻችንን የምንዘነጋቸው ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስታውሰናል፡፡” በማለት ተናግሯል።
ራስን መውቀስ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ ይረዳናል፡፡ ሰውን “አንተ ትክክል ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቼ የተሳሳትሁት እኔ ነኝ . . . ” በማለት ይቅርታ መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ቃላት የወንድምህን ቁጣ ሰለሚገቱት ይታረቅሃል፡፡ ይህን ሳታደርግ ራስህን ነጻ ለማውጣት የምትከራከር ከሆነ ግን ጠላት ስህተትህን ለማጋለጥ ማንም አይደርስበትም፡፡
ይህን አስመልክቶ ቅዱስ መቃርስ የተናገረው አባባል ምነኛ ድንቅ ነው! “ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ሳይወቅሱህ አንተ ራስህን ውቀስ!”
[አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ]

ወዳጄ ሆይ! የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡
አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡
ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ፡፡ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

👍3
"ከፊትህ አንድ መመሪያ አስቀምጥ፤ ይህም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ውስጥ የምትዋጋው ታላቁ ውጊያ፣ ከራስህ ጋር የምታደርገው ውጊያ ነው፤ ወደ ኅሊናህ የሚገባውን ማንኛውንም ዓይነት ክፉ ፍላጎት ተሸክመኸው አትዙር፤ ልትቆጠብ የማትችል ከኾነ ጉዳዩን ለጊዜው አራዝመው፤ ከዚህ በኋላ ጉዳዩን መላልሰህ ለማራዘም ራስህን አስገድደው፤ በማራዘም ውስጥ የእግዚአብሔር ጸጋ ስለሚጎበኝህ እርሱ ያጽናናሃል፤ ... በመንፈሳዊ ትጋትህ ውስጥ ቸልተኝነትህን፣ ግዴለሽነትህን እና ቁም ነገር ማጣትህን የሚገልጹ የተለያዩ ነገሮችን ወደ አንተ እንዲመጡ አትፍቀድ"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ፤
መንፈሳዊ መንገድ፤ ትርጒም በአያሌው ዘኢየሱስ፤ ፲፱፻፺፱(1999)ዓ.ም፤ ገጽ ፵፫/43)
ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ። ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን!!!

👏5👍1
‹‹መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው››
|must read|
መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ምትሐት ምስሎአቸው ታውከው በፍርሃት ጮኹ። ጌታችን ኢየሱስም ‹‹አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ አትፍሩ›› አላቸው፤ ቅድስ ጴጥሮስም መልሶ፥ አቤቱ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ›› አለው። እርሱም ‹‹ና›› አለው። ጴጥሮስም ከታንኳው ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ። ነገር ግን ነፋሱ በርትቶ ባየ ጊዜ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ወዲያውም ጌታችን ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘው ‹‹አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ?›› ብሎታል፡፡ መጠራጠር ያለመጽናት፣ ያለማመን ውጤት ነውና፡፡ (ማቴ. ፲፬፥፳፬-፴፩)
መጠራጠር ወደ ሰው ልቡና በቀላሉ ሊገባ ይቻላል፤ ከዚያ ሰው ግን በቀላሉ አይወጣም፡፡ መጠራጠር የሰውን ሰላምና የኅሊና ዕረፍት ያሳጣል፡፡
የእግዚአብሔርን ህልውና መጠራጠር
መጠራጠር በእግዚአብሔር ህልውና ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በአንድ ወቅት በዲያብሎስ የተጠነሰሰና በሰው ሕይወት ውስጥ ጣልቃ የሚገባ ረቂቅ ውጊያ ነው፡፡ ይህ የሚመጣውም በዚህ ዙሪያ የተጻፉ መጻሕፍትን ከማንበብ፣ እግዚአብሔር የለም ብለው ከሚያምኑ ሰዎች ጋር ከመወዳጀትና ከኅሊና በላይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከመፈላሰፍ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ውጊያ ከተለያዩ የፍልስፍና እና የሳይንስ የምርምር መስኮች ወይም ስለ ህዋና አፈጣጠሩ ከተጻፈ ታሪክ ወይም ደግሞ ታዋቂ ለመሆን ፈልገው ሰዎችን ከሚቃወሙ አካላት የሚመጣም ነው፡፡
ምናልባትም መጠራጠር የእግዚአብሔርን ህልውና ከመጠራጠር ላይነሣ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ርዳታውንና ጥበቃውን፤ ፍቅሩን እና ቃል ኪዳኑን ወይም የጸሎትን ጥቅም ተንተርሶ ይነሣል፡፡ ርብቃ እግዚአብሔር ያዕቆብን ለመባረክ የገባውን ቃል ኪዳን ስለ ተጠራጠረች ይስሐቅን ለማታለል ሰው ሰውኛውን የማታለል ዘዴ ተጠቅማለች፡፡ (ዘፍ. ፳፯፥፭-፲፯)
ዶግማን መጠራጠር
የዚህ መጠራጠር ውጤት የሚመጣው በሌሎች የእምነት ድርጅቶች አማካይነት ነው፡፡ የጸና እምነት የሌለው ሰው የእነርሱን ስብሰባ በመካፈል፣ የእነርሱን መጻሕፍት እና በራሪ ጽሑፎች በማንበብ የውጤቱ ተካፋይ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በጆህቫውያኖች መካከል ተገኝቶ ስብከት ሊያዳምጥ ይችላል፡፡ ወይም ኦርቶዶክሳውያን ባልሆኑ ሰዎች ስብከት ተጽዕኖ ሊደርስበት ይችላል፡፡ እነዚህን በማድረጉ ጥርጣሬ ወደዚህ ሰው ልብና ኅሊና ዘልቆ ይገባል፡፡
ሰው በእምነቱ በዓለት ላይ እንደ ተመሠረተ ቤት ጽኑ ሊሆን ይገባዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች የዶግማ ጥናት ስለሚከብድ ከመንፈሳዊነት የተራቆተ ነው በማለት ያስታሉ፡፡ ማጥናትን ካቆመ በኋላ ሰው ከአንድ አስቸጋሪ ጥያቄ ጋር ሲጋፈጥ መጠራጠር ውስጥ ይገባል፡፡ እኛ የምንመክረው ግን መንፈሳዊ፣ የዶግማ እና የሥነ መለኮት መጻሕፍትን እንዲያነብ ነው፡፡ (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፭)
ቅድስናን መጠራጠር
አንድ ሰው የጾም አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? የሥጋ ቅድስና ምን ዋጋ አለው? የመቆጠብ ጥቅም ምን ይፈይዳል? የድንግልና ጥቅሙስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ከእኛ ጸሎትን ሳይጠባበቅ የሚያድነን ከሆነ ጸሎት ማድረሱ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? በማለት በጥርጥሬ ሊሞላችሁ ይችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ሰው ‹‹የቅድስና ጥቅሞች ምንድን ናቸው? ተራ ተግባራት ወይም ሕግጋት ናቸው እኮ!! ሰው ደግሞ በሕግ አያጸድቅም!!›› ብሎ እስከመናገር ይደርሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ‹‹እስካመንህ ድረስ የወደድኸውን ማድረግ ስለምትችል ምንም ዓይነት ቅጣት አይደርስብህም! ሌላው ቢቀር ሰባት ጊዜ ብትወድቅ እንኳ ሰባት ጊዜ ልትነሣ ትችላህ›› በማለት ይናገራል፡፡
መጠራጠር ዘመናዊ የፈጠራ ግኝቶች ማለትም እንደ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ሲኒማና ሙዚቃን አስመልክቶ ተፈቅዷል ወይስ ተከልክሏል? በማለት ያጠራጥራል፡፡ በኅብረተሰቡ መካከል እንግዳና አዲስ የሆኑ ነገሮችን ማለትም እንደ እርግዝና መከላከያንና ከማኅፀን ውጪ ተገርዘው የሚወለዱ ልጆችን በማስመልከት ጥርጣሬ ሊያመጣ ይችላል፡፡ እንዲህ ያሉት ነገሮች እንደ መረዳትና እንደ ጥናት ጥልቀት እንጂ እንደ ፊደል ባይሆኑ መልካም ነው፡፡ ለምሳሌ ሲኒማ ሊፈቀድም ሆነ ሊከለከል የሚገባው ከሚሰጠው ጥቅምና ጉዳት አንጻር ተመዝኖ ነው፡፡ ቴሌቭዥን፣ ሬዲዮ፣ ተውኔት የምንጠቀምባቸው ለበጎ ነው ወይስ ለክፉ? ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡
አገልግሎትን መጠራጠር
አንድ አገልጋይ አገልግሎቱ ስኬታማ ነው? አገልግሎቱ መቀጠል ይሁን ወይስ ማቋረጥ እንዳለበት መወሰን አቅቶት አብዝቶ ይጠራጠራል፡፡ ፈጥኖ የሚደርሰውን ፍሬ ለማየት ከመጓጓት የተነሳ እንደነዚህ ዓይነት ጥርጣሬዎች በውስጡ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ፍሬውን ማየት ካልቻለ ግን የአገልግሎቱን ስኬታማነት ይጠራጠራል፡፡ ይህን አስመልክተን ከተክል አስተዳደግ ትምህርት ልንወስድ እንችላለን፡፡ አንድ ዘር ለማደግ፣ ለመጠንከርና ዛፍ ለመሆን ጊዜ ያስፈልገዋልና፡፡
የመጠራጠር መንሥኤዎች
የመጠራጠር መንሥኤዎች ከራስ የሚመጡ ውስጣዊ ወይም ውጪያዊ ናቸው፡፡ ወደሚያጸና መፍትሔ ለመድረስ እንችል ዘንድ እነዚህን መንሥኤዎች እንመለከታለን፡፡
አንዳንድ ጊዜ ግን ጥልቅ ሀሳብ ወደ ምክንያታዊነት ስለሚመራ የልብን ገራገርነት ያሳጣል፡፡ ከዚህ በኋላ ይህ ሰው መለኮታዊና መንፈሳዊ ምሥጢራትን በውሉን ሕሊናው አቅም ሊረዳቸው ስለሚናፈቅ ጥርጥር ውስጥ ይወድቃል፡፡ ብዙ ጊዜ ፈላስፎች ጥርጥሬ ውስጥ የሚወድቁት በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ፍርሃት
ብዙ ጊዜ ፍርሃት እና መጠራጠር አይነጣጠሉም፡፡ አንዱ ለሌላው ምክንያትም ውጤትም ሊሆን ይችላል፡፡ ፍርሃት ወደ መጠራጠር ይመራል፤ መጠራጠር ደግሞ ፍርሃትን ያስከትላል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በባሕር ላይ መራመድ ከጀመረ በኋላ ተጠራጠረ፤ መጠራጠሩ ፍርሃት አስከትሎበታል፡፡ ፍርሃቱ እየጨመረ ሲመጣም መስጠም ስለ ጀመረ ድምፁን አውጥቶ ጮኋል፡፡ (ማቴ. ፲፬፥፴)
የዲያብሎስ ውጊያዎች
መጠራጠር ከዲያብሎስ የሚቃጣ ጥንታዊ ውጊያ ነው፡፡ እርሱ በመጀመሪያ ቀደምት አባታችን ወደተከለከለችው ዛፍ በጥርጥር መርቷቸዋል፡፡ የመብላታቸውን ውጤትም እንዲጠራጠሩ አድርጓቸዋል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዲያብሎስ በጥርጥሬ ሊዋጋው ቢሞክርም ስላልቻለ ወድቋል፡፡ በመስቀል ላይ እያለም እንዲህ ብሎታል ‹‹…የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ…፡፡›› ዲያብሎስ ቅዱስ እንጦንስን በጥርጥር ከምንኩስና ለማራቅ ሞክሮ ነበር፡፡ ሰው በሞቱ አፋፍ ላይ እያለ እንኳ ዲያብሎስ ወደ ቅጣት ሊያስገባው ወደ መጠራጠር ይከተዋል፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፵)
ዲያብሎስ ዓለሙን እያሳተ ያለው ጥርጣሬን ከጥንት ጀመሮ ከማወቁም በላይ እንዴት በእነርሱ መዋጋት እንደሚችል በሚገባ ስሚያውቅ ነው፡፡ ስለሆነም በሁሉም ነገር ላይ ጥርጣሬን ይተክላል፤ እርሱ በእምነት ላይ እንኳ ጥርጣሬን ያመጣል፡፡ ሌላውን ለማደናር ከሌሎች ጋር ይወዳጃል፤ ሌላውን ደግሞ ያሳፍራል፤ መጠራጠር ከዲያብሎስ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢም ይመጣል፡፡
በሰዎች አሉባልታ የሚመጣ ጥርጣሬ
መግደላዊት ማርያም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከትንሣኤው በኋላ ብትመለከተውና እርሱም ቢያነጋግራት እንኳ አይሁድ በየሥፍራው በነዙት የተሳሳተ አሉባልታና ጥርጥሬ መካከል ራስዋን ስታገኝ ተጠራጥራ ነበር፡፡ (ዮሐ. ፳)

❤2