ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።እግዚአብሔርን ትተህ በመከራህ ላይ ብታፈጥ አንዳች ጥቅም የለውም።ካስተዋልከው ጨለማም ውበት አለው።ከካባ ይልቅ ደማቅ ነው።እሾህም አበባ አለው። ክፉ ሰውም አንድ ጥሩ ነገር አለው። ልብ አድርግ ለክረምት በጋ፣ለሊትም ቀን አለው።ላንተም ጊዜ አለህ።ጊዜን የሚሰጥህ ራሱ ጊዜ ሳይሆን የጊዜ ባለቤት እግዚአብሔር እንደሆነ እመንና ጠብቅ።
❤14👍2
[ † እንኳን ለድንግልና ሰማዕት አርሴማ ቅድስት ወዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። † ]
[ መስከረም ፳፱ [ 29 ] ]
" ሰማዕቷ ግን ፦ " ከሰማያትና ከምድር ንጉሥ ከእግዚአብሔር አምላኬ ትለየኝ ዘንድ የወደድክ ሰነፍ ንጉሥ ሆይ ! የሰይጣን መልአክተኛና የጥፋት ልጅ ፤ የይሁዳ ወገን ከእኔ ምን ትሻለህ ? ከወደድክስ በእጅህ ሰማዕት እሆን ዘንድ እወዳለሁ" አለችው፡፡ ...... እጅግ ስላፈረ አስገረፋት ፣ አሰቃያት ፣ ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት፡፡ "
🕊
" ሰማዕታት የዚችን አለም ጣዕም ናቁ ፤ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ፤ ስለመንግስተ ሠማያት መራራ ሞትን ታገሡ፡፡ "
[ ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ]
የእናታችን የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ፤ የወንጌላዊውም የቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ ፣ ቃል ኪዳንና በረከት ከሁላችን ጋር ጸንቶ ይኑር።

🙏3👍1
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ፍጡራንን ሁሉ አልፈህ ብትሔድ ! ]
--------------------------------------------------
" አሁንም እንደ አእምሮአችን ድካም መጠን የእግዚአብሔርን ጌትነቱን ማወቅን ልንነግራችሁ ይገባናል፡፡ ከምሳሌዎች ሁሉ የራቀ ነውና፡፡ የሰማይን ምጥቀት የውቅያኖስን ጥልቅነት ለማወቅ ለመረዳት ይቻለናልን ? ከፍጡራን ጥቂት መርምሮ ማወቅ የማይቻለን ከሆነ እግዚአብሔርን መርምሮ ወደ ማወቅ መድረስ እንደምን ይቻለናል ? [ ሲራ.፩፥፪ ]
አሁንም ነገርን አሳጥረን ይህን ክፍል እንፈጽም፡፡ ለፍጥረት ሁሉ ለማይመረመረው ለእግዚአብሔር ዕውቀትን ሁሉ እንተው። መላእክት የመላእክት አለቆች ሁሉ በየወገናቸው በየነገዳቸው በየመዐርጋቸው ከፍጡራን ሁሉ ጋር አንድ ወገን ሆነው ፤ በአንድነት ቢሰበሰቡ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ከማወቅ ወገን ጥቂት ያገኙ ዘንድ አይችሉምና።
እግዚአብሔርን ማወቅን ልንገልጽልህ ፤ አንተም ለራስህ ልትመረምር ከወደድክ ፤ ሥጋዊ ደማዊ ግብርን ሁሉ ከአንተ አርቅ። ከምድራዊ ሥራ ራቅ ፤ ከዓለማዊ ግብርም ተለይ ፤ ሰማያዊ ነገርን አስብ፡፡ የሰዓቶችን ፤ የከዋክብትን ብርሃን' ፈጥኖ መለወጡን ዕወቅ በምድር ያሉ ፍጡራንንም ሁሉ ተው። የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትን ሥርዓታቸውን ዕወቅ ፤ ከሁሉ የሚያስደንቅ ክበባቸውን ፥ ከሁሉ የሚበልጥ ብርሃናቸውን ሁሉ ዕወቅ።
ይህንን ሁሉ መርምረህ ከተረዳህ በኋላ በሰማይ ያለውን መመርመር ቢቻልህ ከመንፈሳውያን ሠራዊት ፥ ከሰማያውያን መላእክት ፥ ከሊቃነ መላእክት ፥ ከመናብርትና ከሥልጣናት ፤ ከአጋእዝትና ከኃይላት ፥ ከሊቃናትና ከመኳንንት መዐርግ የተነሣ በዚያ ቦታ ወዳለው ብርሃን በልቡናህ ብቻ አስተውል።
ከዚህ በኋላ እሊህን ፍጡራንን ሁሉ አልፈህ ብትሔድ ልቡናህም እሊህን ማለፍ ቢቻለው ከፍጡራን ሁሉ በላይ ያለ ኪሩብ ወደ አለበት ወደ አርያም ዐይነ ልቡናህን አቅንተህ ብታይ የማይታመም የማይደከም ፤ ፈጽሞ መለወጥ የሌለበትን የመለኮትን ባሕርይ በዐዋቂ በንጹሕ ልቡና አስተውል። [መዝ.፻፴፱(፻፴፰)፥፩-፲፬ ፤ ማቴ.፭፥፯ ፤ ፪.ቆሮ.፲፥፩-፭ ፤ ራእ.፬፥፩–፬] "
[ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

❤5
†
[ የትሕርምት ሕይወት ! ]
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !
[ " እስከ ፍጻሜ መጽናትን በተመለከተ ! ... " ]
------------------------------------------------
" በትሕርምት ሕይወት ውስጥ ሊኖር የሚወድ ሰው ቢኖር ሁሌም በንቃትና በታላቅ ትዕግሥት ሊመላለስ ይገባዋል እንጂ በድንገት ተነሥቶ ወደዚህ ሕይወት በመግባት ያለ ስልት ሊዋጋ አይገባውም፡፡ ያለበለዚያ ወደ ተስፋ መቁረጥ ይደርሳል፡፡ እንዲህ ዓይነት ፈተናዎች እንደሚመጡብህ አውቀህ ትጠቀምበት ዘንድ ከተማርከው ትምህርት በተጨማሪ ይህን ምክር እንደሰጠሁ ልብ በል፡፡
ስለዚህ ወዳጄ ሆይ የተማርከውን አስተውል ዛሬ በጅማሬህ እነዚህን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሜ ማለፍ ይቻለኛል ባልከው ቃልህ ነገ እንድትገኝ ተጠንቀቅ፡፡ ምክንያቱም ከአንደበትህ የሚወጣውን እያንዳንዱን ቃል በእግዚአብሔር ፊት ስለ አንተ የሚቆመው ጠባቂ መልአክህ ያደምጠዋልና፡፡
ስለዚህ ወዳጄ ሆይ ያለ ፈቃድህ የሚያስገድድህ አካል እንደሌለ ልብ በል፡፡ ከልብህ ለመታዘዝ ከቆረጥህ የማታደርገውን አደርገዋለው ብለህ ሐሰት አትናገር፡፡ ሐሰትን የሚናገረውን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፈዋልና፡፡ "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]

👍5❤1
[ የትሕርምት ሕይወት ! ]
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !
[ “ ለቃሉም ታዛዥ ሁን !" ]
------------------------------------------------
" ወዳጄ ሆይ ! በሙሉ ልብህ መዝሙራትን ለመድገምና ቅዱሳት መጻሕፍት ለማንበብ ትጋ፡፡ ሕፃን ከእናቱ ጡት የተነሣ እንዲፋፋ እንዲሁ ነፍስህ ከቃሉ ወተት ጠጥታ ትፋፋ ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር በማንበብ ትጋ፡፡
ከእነርሱ የመልካም ሥነ ምግባርን ዋጋ ትረዳለህ ፤ ለነፍስህም ደስታና ሐሴት ትሰጣታለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ ! የዋህ ፣ ታዛዥና ትሑት ሁን፡፡ እንደ ሕፃናት የዋህ ከሆንህ እርሱን መከተልና ፈቃዱን መፈጸም ይቻልሃል። በበአትህ [በመኖሪያህ በቤትህ] ሆነህ አርምሞን ገንዘብህ አድርገህ ኑር፡፡ ብዙ ከመናገር ተከልክለህ አርምሞን ውደድ፡፡ በልብህ ግን ወደ አምላክህ ጸልይ ለቃሉም ታዛዥ ሁን ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሰውነትህ ቅድስናን ገንዘብ ታደርግ ዘንድ በጌጠኛ ልብስ ሥጋህን አታስጊጣት፡፡
ባለጸጋ ዘመድ ስላለህም ራስህን አታስታብይ፡፡ ሊመካ የሚወድ በእግዚአብሔር ይመካ ይላልና፡፡ ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር የሰው ሁሉ ክብር እንደ ምድር አበባ ነውና፡፡ ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል የእግዚአብሔር ቃል ግን ለዘለዓለም ይኖራል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ! በጌታችን ሆኜ ሌላ ተጨማሪ መመሪያን እሰጣችኋለሁ፡፡ እርሱን ፈጽማችሁ ከተገኛችሁ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ደስ ያሰኛችኋል፡፡
ከንቱ የሆነውን ሕይወት ክደህ ወደ ቅዱሳን ሕብረት ከገባህ በኋላ ማኅበሩን ጥለህ ትወጣ ዘንድ የጠላት ዲያብሎስን ምክር አትስማ፡፡
በፍጹም ትሕትና ሆነህ ሥራህን ጀምር፡፡ ከጠላትህ የተነሣብህን ፈተና እንደ በቀቀን መልሰህ አታስተጋባው። ብፁዓን ከሆኑት ቍጥር ትሆን ዘንድ ታጋሽ ሁን፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው ፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና፡፡” [ያዕ.፩፥፲፪] "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
❤7👍2
“ሰይጣን ለብዙ ሰዓት ስለ እግዚአብሔር እንድናወራ ሊፈቅድ ይችላል በፍጹም ግን እግዚአብሔርን እንድናዋራው አይፈቅድም፡፡''
[አባ ብሾይ ካሜል]
[አባ ብሾይ ካሜል]
👍16❤2
"ሁላችንም የራሳችን ሕይወት ሰዓሊዎች ነን ገበታው ነፍሳችን ነው ፤ ቀለሙ ደግሞ ምግባራችን ነው። ልንስለው የሚገባው ደግሞ ክርስቶስን ነው።"
[ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ]
[ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ]
❤17
ኢሳይያስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ ከአንተ በቀር ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤ ነገር ግን በአንተ ብቻ ስምህን እናስባለን።
¹⁴ እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፤ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፤ ስለዚህ አንተ ጐብኝተሃቸዋል አጥፍተሃቸውማል፥ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ምንምን አድርገሃል።
¹⁵ ሕዝብን አበዛህ፥ አቤቱ፥ ሕዝብን አበዛህ፤ አንተም ተከበርህ፥ የአገሪቱንም ዳርቻ ሁሉ አሰፋህ።
¹⁶ አቤቱ፥ በመከራ ጊዜ ፈለጉህ፥ በገሰጽሃቸውም ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።
¹⁷ የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትጨነቅና በምጥ እንደምትጮኽ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ በፊትህ ሆነናል።
¹⁸ እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፤ በምድርም ደኅንነት አላደረግነም፤ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ።
¹⁹ ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።
²⁰ ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን በኋላህ ዝጋ፤ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።
ውድ ኦርቶዶክሳውያን ሆይ ቸል ሳትሉ የራሳችሁን ጸሎት ሳትንቁ ስለ ሃይማኖታችን ስለ ሀገራችን ጸልዩ፤ “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።”
— ማቴዎስ 7፥7 ይላል እግዚአብሔር። ስለዚህ ተወዳጆች በጦርነት ምጥ ለተጨነቀች እምነታችን ሀገራችን ጸሎት አድርጉ! ሰይጣንን የማያደማ ጸሎት የለም። በርቱ🙏🙏

👍3❤1
+ አምናለሁ እና አላምንም +
ልጁ የታመመበት አባት ነው:: ጌታን "ቢቻልህስ ልጄን ፈውስልኝ" አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡ አለው።
ይህን ጊዜ ሰውዬው "ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው፡ አለ" ማር. 9:24
የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው"
ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም?
ያምናል እንዳንል "አለማመኔን" ይላል ፤ አያምንም እንዳንል "አምናለሁ" ይላል:: የቸገረ ነገር ነው? ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: እኔ አላዋቂው ግን "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው" የሚለውን ቃል እየደጋገምኩት ቀረሁ::
እያመኑ አለማመን እንዴት ያለ ነው? ብዬ መላልሼ ሳጤነው ግን ሰውዬው የእኔኑ ድክመት እየተናገረ እንደሆነ ገባኝ::
አምናለሁ እላለሁ:: በእርግጥም በፈጣሪ መኖር አምናለሁ:: ሁሉን እንደሚችልም አምናለሁ::
ግን ደግሞ በእርሱ ታምኜ አላውቅምና በሥራዬ እክደዋለሁ:: ኑሮዬ "በሥራቸው ይክዱታል" ከተባሉት የሚመደብ ነው:: (ቲቶ 1:16) አቅዋሜ የማመን ኑሮዬ ያለማመን ነውና አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ብል ለእኔ የሚገባ ጸሎት ነው::
ወረደ ተወለደ ተጠመቀ ተሰቀለ ሞተ ተነሣ ዐረገ ብዬ አምናለሁ:: በትሕትና መውረድን ፣ በንስሓ መወለድን ፣ በታናሽ እጅ ዝቅ ብሎ ጽድቅን መፈጸምን ፣ መከራን በትዕግሥት መቀበልን ፣ ከመከራ ሞት ወዲያ ተነሥቶ በክብር ከፍ ማለትን ግን እኔ ሕይወት ላይ አላውቀውም:: የምተርከው ክርስቶስ እንጂ የሚተረክ ክርስትና የለኝም:: ስለዚህ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በልኬ የተሰፋ ጸሎት ነው::
መች በዚህ ያበቃል::
እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው::
ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢአት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው ሥጋ በሐሜት የምበላ ነኝና እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳሁ እላለሁ::
እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው::
ቆሜ የማደርሰው ጸሎትስ አለኝ:: ግን ልቤ ሠላሳ ቦታ ደርሶ ይመለሳል:: የምጸልየው ማናገር የማልፈልገውን ሰው በግድ የማናግር ያህል የግብር ይውጣ እንጂ ነፍሴ እርሱን ሽታ አይደለምና እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው እላለሁ::
እሰግዳለሁ አለመስገዴን እርዳውስ?
ላቤ እስኪወርድ ሰግጄ አውቃለሁ:: ልቤ ግን አንዴ አልሰገደም::
ጌታ ሆይ እመጸውታለሁ አለመመጽወቴን እርዳው:: እዘምራለሁ አለመዘመሬን እርዳው:: አስቀድሳለሁ አለማስቀደሴን እርዳው:: እማራለሁ አለመማሬን እርዳው:: ሆኜ ያልሆንሁትን አድርጌ ያላደርግሁትን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና እርዳኝ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

🙏7👍1
Forwarded from የሕይወት መዓዛ ዘመሠረተ ሕይወት
ከብጹዕ አቡነ ሺኖዳ አንደበት
"አስታውስ"
† ደካማነትህን አስታውስ ፣ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡
† የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል፡፡ በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል፡፡
† የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ ፡፡ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡
✝ ሞት እንዳለ አስታውስ ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ፡፡ ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡˝ መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ፡፡
† በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና፡፡
† ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ ፡፡ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ "በዋጋ ተገዝታችኋልና" 1ኛ ቆሮ.6:20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡
† በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ ፡፡
† በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ ፡፡ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ፡፡
† በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ ፡፡ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና፡፡
† ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ፡፡
† የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ ፡፡ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል፡፡
† የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፡፡ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን፡፡ ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡
(ብፁዕ ኣቡነ ሺኖዳ)
https://www.tgoop.com/yehiwot_meaza

🥰5👍1
+++ "እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር ጉዞ" +++
ጌታችን ስለ በጎ ባልንጀራ ተጠይቆ ለዚያ መልስ እንዲሆን በሰጠው ምሳሌ ላይ ያሉት ሁለቱ ሰዎች (ካህኑና ሌዋዊው) ያስገርማሉ። እነዚህ ሰዎች በመቅደሱ የሚያገለግሉ ሲሆኑ ቆስሎ የወደቀውን ታማሚ ያዩት ካህኑ የመቅደስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ ሌዋዊው ደግሞ ገና ለአገልግሎት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄድ ሳይሆን አይቀርም።(ሉቃ 10፥30-35) ከቤተ መቅደስ የወጣውም ወደ ቤተ መቅደስ የሚሄደውም ያን በሽተኛ አይቶ ገለል ብሎት አለፈ።
ለምን? ከመቅደስ የወጣው ለእግዚአብሔር የሚገባውን አገልግሎት ጨርሻለሁ ብሎ ስላሰበ፣ ወደ መቅደስ የሚሄደው ደግሞ የወደቀውን ሲረዳ የምስጋና ሰዓቱ እንዳይታጎልበት ሰግቶ እንደ ሆነስ? ማን ያውቃል?!
ብቻ "ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁ ለእኔ አደረጋችሁ" በማለት የተናገረውንና ከታማሚው ጋር ያለውን እግዚአብሔር መንገድ ላይ ጥለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ።
እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር መሄድ የሚሉት ፈሊጥ ምን ዓይነት ይሆን?
ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ወይም ከቤተ መቅደስ ስንመለስ ስንት ጊዜ እግዚአብሔርን ገለል ብለን አልፈነው ሄድን?
ዲያቆን አቤል ካሳሁን

Telegram
Dn Abel Kassahun Mekuria
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።
ይወዳጁን
ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL
ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_
ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW

🥰2
🍃🍃🍃
ቅዱስ ዮሐንስ - ድንግልን ተቀብሎ የወሰደ ሐዋርያ
ድንግልን በስጦታነት የተቀበለው ፣ ተቀብሎም ወደ ቤቱ የወሰዳት ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ ነው፡፡ ዮሐንስ ጌታ የሚወደው እርሱም ጌታን የሚወድ ሐዋርያ ነው፡፡ ከሌሎቹም ሐዋርያት ይልቅ ለጌታ ፍቅሩ የጸና ስለ ነበር ፣ ጌታም እርሱን ይወደው ስለ ነበር ፍቁረ እግዚእ - የጌታ ወዳጅ ተባለ፡፡ ለዚህም ነው … “የሚወደውን ደቀ መዝሙሩን” ተብሎ የተነገረለት፡፡ ታዲያ ጌታ ለምን እመቤታችንን ለዮሐንስ ሰጠ? ለምን የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ለሰጠውና ብፁዕ ነህ ብሎ ላመሰገነው ለጴጥሮስ አልሰጠውም? (ማቴ.16፡17-19)፡፡ እርሱስ ቢሆን ጌታን መውደዱን “እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” ብሎ የሚመሰክር አይደለምን? (ዮሐ.21፡15-17)፡፡ ቅዱስ ሥጋውን ከመስቀል አውርደው ለገነዙት ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስስ ለምን አልሰጣቸውም? ለሌሎቹ ሐዋርያትስ ለምን አልሰጣቸውም? ድንግልን ይወስዷት ዘንድ ቤት የላቸውምን? አይደለም፡፡…
ዮሐንስ የሚሰጠውን ስጦታ ለመጠበቅ ከሌሎቹ ሐዋርያት ይልቅ ብቁ ስለነበርም ድንግልን ለመቀበል በመስቀሉ ሥር እንዲገኝ እግዚአብሔር ፈቀደ፡፡ ሐዋርያት በጌታ መከራ ሞት ጊዜ አይሁድን ፈርተው እንደ ሸሹ ከዮሐንስ በቀር በእመቤታችን ሞትም ጊዜ አይሁድን ፈርተው ከጌቴሴማኒ የሚሸሹ ናቸውና ድንግልን እንደ ፍቁረ እግዚእ ለመቀበል አልቻሉም፡፡ ራሱን የሰጣቸውን ጌታ በቀራንዮ ጥለውት እንደ ሔዱ ሁሉ ከመስቀሉ ሥር የምትሰጣቸውን እመቤታችንንም በጌቴሴማኒ ጥለው የሚሔዱ ናቸውና በቀራንዮም በጌቴሴማኒም ለሚጸና ለዮሐንስ ተሰጠች፡፡…
…በርግጥ በዮሐንስ በኩል ድንግል ለተጠቀሱትም ላልተጠቀሱትም ለሁሉም ተሰጥታለች፡፡ ነገር ግን በዮሐንስ በኩል እንዲሆን ዮሐንስን የመረጠበት የተለየ ምክንያት አለው፡፡ ከማይመረመረው ከመለኮታዊው ምክንያቱ ባሻገር ዮሐንስን ከላይ እንደገለፅነው ይወደው ነበር፡፡ እመቤታችንን በስጦታነት ለመቀበል በጌታ መወደድ ያስፈልጋል፡፡ ማርያም ማርያም ለማለት በክርስቶስ መወደድ ያሻል፡፡ ድንግል ታማልዳለች ብሎ ምልጃዋን ለመቀበል በመድኃኔዓለም መወደድ ግድ ነው፡፡ ስሟ ሲጠራ ፊታቸው የሚጠቁር ሰዎች ምንም እንኳን እርሱ እንደሰው ቢወዳቸውም በተሳሳተ መንገድ ውስጥ ናቸውና እንደ ዮሐንስ ስላልተወደዱ ድንግልን ለመቀበል ብቁ አይደሉም፡፡ ጴጥሮስ እንዳለው ቆይተው “እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” የሚሉ እንኳን ቢሆኑ መከራ ሞቱ በጾም ሲታሰብ ፣ ሕማማቱ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ሲዘከርና ቤተ ክርስቲያን ስሟ ሲጠራ ጴጥሮስ “የምትሉትን ሰው አላውቀውም” ብሎ ገና ዶሮ ሳይጮህ ነገር በሚጸናባት ቁጥር ሦስት ጊዜ እንደ ካደ እነርሱም “የምትሉትን ሃይማኖት አናውቅም ፣ የምትሉትን ጾምና ሥርዐት አናውቅም” ብለው በጽናት ክደዋልና መስቀሉ ሥር ተገኝተው “እነኋት እናትህ” ሊባሉ አልቻሉም፡፡ (ማር.14፡71)፡፡…
…ጌታ በመስቀል ላይ እመቤታችንን ለዮሐንስ ከመስጠቱ በፊት ዮሐንስን ለእመቤታችን ሰጥቶ ነበር፡፡ አንድ ሰው ድንግልን ለመቀበል አስቀድሞ ራሱ ለድንግል መሰጠት አለበት፡፡ ለውዳሴዋ ፣ ለብፅዕትነቷ ፣ ለንጽህናዋ ፣ ለድንግልናዋ ፣ ለቅድስናዋ መጀመሪያ ራሱን መስጠትና ማስገዛት ይኖርበታል፡፡ ዮሐንስን መምሰል ያስፈልገዋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድርሳነ ማርያም ማንን ለድንግል እንደሚሰጥ ሲገልፅ የሚከተለውን ብሏል፤
“በኢየሩሳሌም ትነግሺ ዘንድ ነይ፡፡ መታሰቢያሽን የሚያደርግ በቃሉ የማይዋሽ ፣ መጽሐፍሽን የጻፈ ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ፡፡ ለአንቺም ይሆን ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡”
“…አንድ ሰው ራሱ ለእርሷ ለመሰጠት ሲበቃ ከዚያ በኋላ እርሷን ለመቀበል የሚችል ዕደ-ልቡና ይኖረዋል፡፡…
…ድንግልን ለመቀበል መሰጠት ያስፈልጋል፤ እመቤታችንን ለመቀበል ሞት በመጣ ጊዜ ከክር ይልቅ አንገትን የምታስቀድም በ”እንኩ” ባይ ፍቅር ፣ በቅዱስ ጥብዐትና በሰማያዊ ተስፋ የሠለጠነች የክርስትና እምነትን መሰነቅ ግድ ነው፡፡ ድንግልን ለመቀበል ቤትን ማዘጋጀት ሳይሆን እንደ ዮሐንስ የተወደደች ሃይማኖትን ይዞ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ ድንግል በዮሐንስ በኩል ለሁሉ እንደ ተሰጠች በተወደደች ሃይማኖት በኩል እንጂ በሌላ በምንም በኩል አትሰጥም፡፡ …
…ከዚህ በተጨማሪም ጌታ የሚወዳት እናቱን በመስቀል ላይ ሳለ ነፍሱን ከሥጋው በፈቃዱ ከመለየቱ በፊት ሊያያት እንደወደደ እመቤታችንም በሞቷ ጊዜ ነፍሷ ከሥጋዋ ከመለየቱ በፊት ልጇ በመስቀሉ ሥር ልጅሽ ይሁን ብሎ የሰጣትን ውድ የመንፈስ ልጇን ፣ ስጦታዋን - ዮሐንስን ልታየው ወዳ ነበር፡፡ እንዲህ ብላም ጸለየች፤
“‘በሰማይ የምትኖር ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ጸሎቴን ልመናዬን ስማኝ፣ ታናሹ ዮሐንስንም ላክልኝ፣ አይቼው እደሰት ዘንድ እወዳለሁና፤ ዳግመኛም ወንድሞችህ ሐዋርያትን ሁሉ ላክልኝ፤ በሰጠኸኝ ጸጋም አምናለሁ፤ እንደምትሰማኝ በአንተ ዘንድ የፈለግሁትን ሁሉ እንደምትሰጠኝ አምናለሁ’ እያለች ጸለየች፡፡”
ከ'የመሰጠት ሕይወት' መጽሐፍ ፣ ከገጽ 71-92 ድረስ ከሚገኘው በጥቂቱ የተወሰደ
[ዲ/ን ሕሊና በለጠ]

👏1
አንድን ወጣኒ ባሕታዊን እንደ መከረው
አንድ ያልተማረ ባሕታዊ ወደ በረሃ ሄዶ ብቻውን ተቀመጠ፡፡ ሰይጣንም መጥቶ "ምነው በዚህ በረሃ ብቻህን?" አለው፡፡ እርሱም ፦ "እጸድቅ ብዬ" አለው ፤ ዝም ብሎት ሄደ፡፡ ሁለተኛም ሄዶ "ምነው ብቻህን?" አለው፡፡ ያ ባሕታዊም ፦ "ክርስቶስን ባገኘው ብዬ" አለው ፤ ሰይጣኑም "የአሁኑ ይባስ!" ብሎት ሄደ፡፡ አባ መቃርስ ነገሩ ተገለጠለትና ወደዚህ ባሕታዊ ዘንድ ሄዶ ፦ "ከአንተ ዘንድ ሰው አልመጣምን?" አለው፡፡ እርሱም ዝም አለው፡፡ ግድ ብሎ ንገረኝ ባለው ጊዜ ፦ "አዎን ፣ መጥቶ ነበር" አለው፡፡ "ምን አለህ?" አለው፡፡ "ብቻህን ለምን ተቀምጠሃል?" አለኝ ፣ እጸድቅ ብዬ አልሁት ፣ ዝም ብሎኝ ሄደ፡፡ ሁለተኛም መጥቶ "ምነው ብቻህን?" አለኝ ፣ እኔም ክርስቶስን ባገኘው ብዬ አልኩት ፣ እርሱም "የአሁኑ ይባስ!" ብሎኝ ሄደ አለው፡፡
መቃርስም ፦ "ምነው እንዲህ ማለትህ የምትጸድቅና ክርስቶስን የምታገኝ አንተ ብቻ ነህን? በዓለሙ ያለ ሁሉ ክርስቶስን የማያገኝና የማይጸድቅ ሆኖ ነውን? ከአሁን በኋላ ተመልሶ የመጣ እንደ ሆነ ፦ ግብሩ የከፋ ውሻን አስረው ለብቻው እንደሚያስቀምጡት እኔም ጠባዬ ቢከፋ ግብሬ ከሰው ባይስማማ ከዚህ መጥቼ ተቀምጫለሁ በለው እንጂ እንዲህ አትበለው" አለው፡፡ ዲያብሎስም እንደ ልማዱ እንደገና መጣ፡፡ ያ ወጣኒም መቃርስ እንደ ነገረው መለሰለት፡፡ ዲያብሎስም "ይህን ያደረገ መቃሪ ነው እንጂ አንተ አይደለህም" ብሎት ሄዷል፡፡
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና በረከቱ አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

🥰3👍2
የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ሔር
(ቸር አገልጋይ) የተሰኘው ሲሆን ይህንን ስያሜ ያገኘበትም ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ሔር ወገብር ምእመን ገብር ዘአስመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው፡፡ ገብርሔር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡
የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብርኄር
ምስባክ መዝ. 39÷8
"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"
ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ።
ወንጌል
ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄደ፤ ነግዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታዉን ወርቅ ቀበረ፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ ተቈጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና፡- አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ ብሎ አምስት መክሊት አስረከበ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጥቶ፡- አቤቱ÷ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን አተረፈሁ አለ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ አሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለውም መጣና እንዲህ አለ፡- አቤቱ÷ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ÷ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ÷ መክሊትህ፡፡ ጌታውም መልሶ አለው፡- አንተ ክፉና ሰነፍ አገልጋይ÷ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ÷ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡

❤2👍1
ከዚያ የቆሙትንም እንዲህ አላቸው፤ ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን÷ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት፡፡
ዲያቆን (ምንባብ)
2ኛ ጢሞ.2÷1-15 ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡ ወደ ሰልፍ የሚሄድ÷ አለቃውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ነው እንጂ የዚህን ዓለም ኑሮ አያስብምና፡፡ የሚታገልም ቢሆን እንደ ሕጉ ካልታገለ አክሊልን አያገኝም፡፡ የሚደክም አራሽም አስቀድሞ ፍሬውን ሊያገኝ ግድ ነው፡፡ ያልሁህን አስተውል፤ እግዚአብሔርም በሁሉ ነገር ጥበብን ይስጥህ፡፡
በወንጌል እንደምሰብከው÷ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስበው፡፡ ስለ እርሱም እንደ ወንጀለኛ አስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም፡፡ ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ሕይወትና የዘለዓለም ክብር በሰማያት ያገኙ ዘንድ÷ ስለ ተመረጡት ሰዎች በሁሉ ነገር እታገሣለሁ፡፡ ነገሩ እውነት ነው፤ ከእርሱ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፡፡ ብንታገሥም ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው ግን እርሱም ይክደናል፡፡ ባናምነውም እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን መካድ አይቻለውምና፡፡

👍1🥰1
እንግዲህ ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ÷ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይጠቅም÷ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና፡፡የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት አቃንቶ ሲያስተምር እንደማያፍር ሰራተኛ ሆነህ ፣ራስህን የተመረጠ አድርገህ ለእግዚአብሔር ታቀርብ ዘንድ ትጋ።
ንፍቅ ዲያቆን (ምንባብ)
1ኛ ጴጥ.5÷1-11 እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡ ለመንጋዉ ምሳሌ ሁኑ እንጂ ሕዝቡን በኀይል አትግዙ፡፡ የእረኞችም አለቃ በተገለጠ ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡ እንዲሁ እናንተ ጐልማሶች ሆይ÷ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ልበሷት፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳልና፤ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትን ግን ያከብራቸዋል፡፡
እንግዲህ በጐበኛችሁ ጊዜ ከፍ ከፍ ያደርጋችሁ ዘንድ ከጸናችው ከእግዚአብሔር ክንድ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡ እንግዲህ ዐዋቂዎች ሁኑ፤ ትጉም፤ ጠላታችሁ ጋኔን የሚውጠውን ፈልጎ÷ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና፡፡ እርሱንም በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት፤ እንዲህም ያለ መከራ በዓለም በአሉ ወንድሞቻችሁ ሁሉ እንደሚፈጸም ዕወቁ፤ ፍቅርንም አጽንታችሁ ያዙአት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ልባሞችም ያደርጋችኋል፡፡ለእርሱ ክብርና ኅይል እስከ ዘለአለም ይሁን፤አሜን።
የሐዋ.1÷6-8 እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"

Forwarded from ፍኖተ ሕይወት
በተመሳሳይ ኃጢአት እየወደቅሁ ተቸገርኩኝ፤
ምን ላድርግ?
ክፍል፦1
#አንድ ሰው “ምን ላድርግ?” ብሎ ሲጠይቅ መንፈሳዊ ሕይወትን መፈለጉ ማሳያ ነው፡፡
አንድ ክርስቲያን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” የሚል ጥያቄ ካነሣ ለማደግ መፈለጉን፣ መንፈሳዊ መፍትሔ መሻቱን፣ እግዚአብሔር እንደሚረዳው በማያጠያይቅ መንገድ ማመኑን ያመለክታል፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ፣ ቀራጮች እንዲኹም ጭፍሮች እየመጡ፡- “ምን እናድርግ?” ይሉት ነበር /ሉቃ 3፡10-14/፡፡ ስለጠየቁም “ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ” ብሏቸዋል /ማቴ 3፡8/፡፡
ሐዋርያት ሲያስተምሩ፡- “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” ያሉት የገባቸው ናቸው /ሐዋ.2፡37/፡፡ ስለዚኽ ምንም ደካሞች ብንኾንም ድካማችንን ከእኛ የሚያርቀው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር “በርሱ ቃል እታነፃለኁ፤ እመከራለሁ” ብሎ “ምን ላድርግ?” ብሎ መጠየቅ ታላቅነት፣ አንድም ትሕትና፣ አንድም የመንፈሳዊ ሕይወት ፍላጎትን የሚያሳይ ነውና ኹል ጊዜ ጠያቂዎች ለካህናት፣ ለቤተ ክርስቲያን መምህራን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” ብለው ሲጠይቁ ሊበረታቱ ይገባቸዋል፡፡
ጥያቄው የብዙ ሰዎች ጥያቄ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ፡- “ሰው ኾኖ የማይበድል እንጨት ኾኖ የማይጤስ” እንዲሉ እንደየኑሮአችን ደረጃ፣ እንደየሥራችን ዓይነት ይለያይ እንደኾነ እንጂ ክርስትና ሕይወታችን ስንመላለስ አንድ ከሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ ኃጢአት የሚስማማን መኾኑ ነው፡፡ በርግጥም “ምን እናድርግ?”
#የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ማወቅ- አንድ
ሰው የሚወድቅበት ሀጥያት ሌላኛው ሰው የማይወድቅበትና ትኩረት የማይሰጠው ሊኾን ይችላል፡፡
ከዚኽ አንጻር “በተመሳሳይ ኃጢአት ደጋግሜ እወድቃለኁ” ያልነው ኃጢአት ምንድነው? እየተደጋገመ ያስቸገረን ምንድነው? ከምንም በፊት የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን አጢኑት፡፡ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ከለዩ በኋላ ለዚያ ከሚዳርጉን ቦታዎች፣ ወይም ጓደኞች፣ ወይም ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ወደምንወድቅበት ኃጢአት የሚገፋፉ ኹኔታዎችን፣ ቦታዎችን ወይም ጓደኛን በአጠቃላይ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መራቅ ያስፈልጋል፡፡ “ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ኾነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ኾነህ ትገኛለህ” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት /መዝ.18፡26/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም “አትሳቱ፤ ክፉ ባለንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” ይላል /1ኛ ቆሮ15፡33/፡፡ በዚኽ መሠረት ጠያቂያችን ብቻ ሳይኾኑ ኹላችንም ኃጢአትን ደጋግመን የምንሠራው በኹኔታዎች ተጽዕኖ ነው? ወይስ በጓደኞች ግፊት? ወይስ በምንሰማው፣ በምናየው፣ በምንዳስሰው ተጽዕኖ? ይኽን በአግባቡ ከለየን በኋላ ከምንጩ ለማድረቅ ለዚያ ከሚዳርጉ ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ ይኽን ስናደርግም ከምንም በፊት ኅሊናን ማሳመን ይጠይቃል፡፡ በመቀጠልም አካላዊ ውሳኔ መስጠትን ነው፡፡ ለኃጢአት በሚዳርግ ቦታ ተቀምጠን “በፍጹም አይነካኝም፤ አይደርስብኝም” ማለት መመጻደቅ ነው፡፡ ሰይጣንም እኛን ለመጣል አያርፍምና የምንወድቅበትንም መንገድ ያዘጋጃልናል በኅሊናም በአካልም ከዚያ መሸሽ ያስፈልጋል፡፡
የጴጢፋራ ሚስት ዮሴፍን ለክፉ ሥራ ስትከጅለው ቆሞ አልተሟገተም፤ ጥሏት ሸሸ እንጂ /ዘፍ.39/፡፡ ስለዚኽ ለተደጋጋሚ ኃጢአት ከሚዳርጉንና ከሚገፋፉን ነገሮች “እችለዋለኁ፤ እቋቋሟዋለኁ” ብሎ መመጻደቅ ሳይኾን መሸሽ ካለብን መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ እንደየኹኔታው በይበልጥም ከክፉ ቦታዎች፣ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ ኃጢአቱ በሥጋም በነፍስም ጎጂ እንደኾነ ማስተዋል፡፡ ይኽ በተመሳሳይ እየወደቅንበት ያለው ኃጢአት በሥጋም ጭምር የሚጎዳን ይኾናል፡፡
ከክርስትና ሕይወት ባሻገር ስብእናን የሚያጎድፍ፣ ጤናን የሚያውክ ሊኾን ይችላል፡፡ ከዚኽ አንጻር የዚኽ ጉዳት በጥልቀት ማስተዋል ያስፈልጋል፤ ጉዳቱን ማሰብ ለመጠንቀቅ ይረዳልና፡፡

🥰1
Forwarded from ፍኖተ ሕይወት
በተመሳሳይ ኃጢአት እየወደቅሁ ተቸገርኩኝ፤
ምን ላድርግ ?
ክፍል፦ ሁለት
#ከንስሐ አባታችን፣ ከመምህራን እንዲኹም ከመጻሕፍት ትምህርት ማግኘት የእድገት በደረጃ ነው፡፡ በአንድ ጀምበርም ለውጥ ላይመጣ ይችላል፡፡ በመኾኑም በሒደት ያንን የመተው መስመር ውስጥ እንድንጠነክር ከዚኽ ኹኔታም ፈጽመን ለመራቅ በራሳችን ጉልበት ብቻ አንችልም፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናልና /ዮሐ15፡5/፡፡ በዚኽም መሠረት ከመምህራን የምንሰማው የእግዚአብሔር ቃል፣ ከመጻሕፍት የምናገኘው፣ ከመምህረ ንስሐም በጸሎትና በምክር የምናገኘው ሐሳብ ያ እያጠቃንና እየጣለን ያለውን እንዲኹም የምንደጋግመውን ኃጢአት ለማስወገድ ኃይል ይኾነናል፡፡
#መንፈሳዊ ተግባራትን ማዘውተር፡፡ እንግዲኽ እንደየ ክስተቱ ለየትኛውም የኃጢአት ተግባር መንፈሳዊ ሕይወት፣ መንፈሳዊ ተግባር ድል መንሻው ነው። ይኽም “እንዲኽ ያለውን ክፉ መንፈስ ያለ ጾም ያለ ጸሎት ከእናንተ አይወጣም” እንዳለ /ማር.9፡29/ ጾምን፣ ጸሎትን፣ ንስሐን የሕይወታችን መሠረት ማድረግ ነው፡፡ መተውን መለማመድ፡፡ ይኽም ማለት ጠቢቡ ሰለሞን “ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” እንዳለ /ምሳ 23፡17/ “እስኪ ዛሬ ተቆጥቤ ልዋል” ብሎ መወሰን ማለት ነው፡፡
ከዚያ ከምንጠላው ግን ደግሞ እየወደቅንበት ካለው ስሕተት ተቆጥበን ከዋልን ማታ ላይ ተመስገን ብሎ ጸልዮ ማደር ነው፡፡ ነገም ሲነጋ “ዛሬም እንዲኹ እንደ ትናንትናው መንፈሳዊ መንገድና ሒደት ልዋል፡፡ ዛሬም እንዲኽ ካለው ተግባር ፍጹም ተቆጥቤ መዋል አለብኝ፡፡ ደግሞም እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያስችለኛል፡፡ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ኹሉን እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያበራታኛል” ስንልና ዕለት ዕለት ኹኔታውን እየኰነንነው፣ እያወገዝነው፣ “በዚያ መንፈስ ዛሬ አልውልም፡፡ ይልቁንም በመንፈሳዊ
መንገድና በጥንካሬ እውላለኁ” ብለን ስንወስን ያን ውሳኔአችንን እያደነቅን ስለተደረገልን ጥንካሬም ተመስገን እያልን ልምምድ ማድረግ ይቻላል፡፡ ደጋግመን የምንሠራው ኃጢአት እጅግ ብዙ ዘመናት ከእኛ ጋር የቆየ ሊኾን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ኃይል በላይ የኾነ ኃጢአት የለም፡፡ ዋናው የእኛ ውሳኔ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የምንታለለው እዚኽ ጋር ነው፡፡ ለመተው እንፈልጋለን፤ ለመተው ግን በተግባር አንወስንም፡፡
ንስሐ መግባት የማይፈልግ ሰው የለም፤ በተግባር ወስኖ የሚገባ ግን ጥቂት ነው፡፡ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ መኖር የማይፈልግ ክርስቲያን አይኖርም፡፡ ብዙዎች መቁረብ ይፈልጋሉ፤ ወስነው የሚቆርቡት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ከዝሙት ኃጢአት መራቅ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ዝሙትን የሚያበረታቱ ማስታወቂያዎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ምስሎችን እንዲኹም የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ዘፈኖችን እንዲኹም ጽሑፎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ንግግሮችን ሲከታተሉ ይገኛሉ፡፡ እነዚኽን ሰዎች ስናያቸው በውስጣቸው ከዚያ ኃጢአት የመራቅ ፍላጎት አለ፤ ተግባሩ ላይ ግን ከዚያ የሚያሸሻቸው አይደለም፡፡
ለዚኽም ነው ጌታ “ብዙዎች ይፈልጋሉ፤ አይችሉምም” ያለው /ሉቃ13፡24/፡፡
ስለዚኽ ከኃጢአት መራቅ የሚፈልግ ሰው የመተው ልምምድን አኹንኑ መጀመር አለበት፡፡ “ዛሬ ዘፈን አላዳምጥም፡፡ ዛሬን በዚኽ ምትክ መዝሙር አዳምጣለኁ” ብሎ መለማመድ አለበት፡፡ በዚኽ ውሳኔው ጸንቶም ዛሬን ይውላል፤ ያድራልም። ሌሎች ነገሮችም እንደዚኽ ናቸው፡፡ የመጠጥ ልምድ ያለው ሰው “ዛሬ አልጠጣም፤ ዛሬ በምጠጣበት ሰዓት እዚኽ ቦታ እሔዳለኁ፡፡ እዚያ ሒጄ እውላለሁ ። "በበጎ ነገር አሳልፈዋለኁ” ሲል ዛሬን ይውላል፡፡ ማታ ላይ ሲመሽ “ለካ ይቻላል፡፡ ለካስ እኔ ከበረታኁ እግዚአብሔር ያስችለኛል” የሚለውን በኅሊናው ያሳምናል፡፡ ነገሮችን የመተው ልምምድ በተግባር ማሳየት ማለት ይኸው ነው፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያ ያስቸግረን የነበረው ተደጋጋሚ ኃጢአት ታሪክ ይኾናል፤ ለሌላ ሰው መካሪ ኾነን ራሳችንን በለውጥ ቦታ ላይ እናገኘዋለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦መቅረዝ ዘተዋሕዶ

❤4