Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1233 - Telegram Web
Telegram Web
+ በመንፈስ ታድሳችሁ ስትነሱ መሰናክል ለሚሆኗችሁ እንዲህ በሉ +

አውግስጢኖስ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው:: በቅዱስ አምብሮስ ስብከት ከተመለሰ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኩስና መንገድ ሔዶ እስከ ጵጵስና ደረሰ:: ይህንን የንስሓ ሕይወት መኖር ከጀመረ በኁዋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው::
ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ::
ይህች ሴትም እየሳቀች :-
አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች

እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :- "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላት::

ክርስትና የወደቀ የሚነሣበት የረከሰው የሚነጻበት ሕይወት ነው:: በዚህ መስመር ያለፉ ሁሉ ትናንትን እየተዉ ሌላ ማንነትን ይለብሳሉ:: ትልቁ ፈተና ሰዎች ተነሥተህ እያዩህም እንኩዋን መውደቅህን አለመርሳታቸው ነው:: ፈጣሪ "ከእንግዲህ አትበድል" ብሎ ይቅር ቢልህም ሰዎች ግን ይቅር አይሉህም:: "ድመት መንኩሳ ዓመልዋን አትረሳ" እያሉ እየተረቱ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ ይገፉሃል እንጂ እንድትለወጥ አይፈቅዱልህም::

ሳውል አሳዳጅ ነበረ ዛሬ ግን ሐዋርያ ነው:: ብዙ ክርስቲያኖች ግን እርሱን ለማመን ተቸግረው ነበር:: ከመመረጡ ጀምሮ "ኸረ እርሱ አይሆንም" ብለው ለፈጣሪ ምክር የሠጡም ነበሩ:: ከተመረጠ በኁዋላም ለመቀበል ተቸግረው ከሐዋርያት አሳንሰው ያዩት አልጠፉም:: እርሱም በትሕትና  "ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ቢልም : "ጭንጋፍ" ብሎ ራሱን ያለ ጊዜው ከሚወለድ ጽንስ ጋር አነጻጽሮ ዘግይቶ የተጠራ መሆኑን ቢናገርም ከሐዋርያት በምንም የማያንስ ሐዋርያ ነበረ:: እነርሱ በትናንት ማንነቱ ሊያዩት ቢሹም እርሱ ግን "እርሱ አልነበረም"  እርሱ መኖር አቁሞ በእርሱ ይኖር የነበረው ክርስቶስ ነበረ::

አንዳንድ ሰዎች የማያምኑህ ከክፋት ተመልሰህ መልካም ስትሆን ብቻ አይደለም::  በጣም መልካም ስትሆንላቸውም አያምኑህም:: ስታከብራቸው ምን አስቦ ነው? ብለው ይጠራጠራሉ:: መልካም ስታደርግላቸው "ምነው ደግነት አበዛሽ? ተንኮል አሰብሽ እንዴ? "ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው" "there is no free lunch” ብለው ሊሰጉ ይችላሉ:: መልካም የሚያደርግላቸውን ሁሉ ሊያርድ የሚያሰባቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሉ:: ፍቅር የትግል ስልት የሚመስላቸው ጨብጠውህ ጣታቸው እንዳልጎደለ የሚቆጥሩ ዓይነት ተጠራጣሪ ሰዎች አሉ::

ዮሴፍ የገጠመው ይህ ነበር:: በሃያ ብር ሸጠው ግብፅ ያወረዱት ወንድሞቹን ይቅር ብሎ በፍቅር ተቀበላቸው:: አባታቸውን ያዕቆብን አስመጥቶ በክብር በግብፅ እንዲኖሩ አደረጋቸው:: ከዓመታት በኁዋላ አረጋዊው ያዕቆብ ሞተ::
ይሄን ጊዜ የዮሴፍ ወንድሞች ድንገት ስብሰባ አደረጉ: "አባታችን ከሞተ በኁዋላ ቢበቀለንስ?!" ብለው ስጋታቸውን ተመካከሩ::
ስለዚህ ዶልተው መጡና እንዲህ አሉት :-
አባታችን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል ተናዝዞ ነበር:: እባክህን የወንድሞችህን በደል ይቅር በል:: (ዘፍ 50:15-21) ዮሴፍ ይኼን ሲሰማ አለቀሰ:: ይቅርታን አድርጎም አለመታመኑ አመመው::

እርሱ ለእነርሱ ድሮም ክፉ አልነበረም:: አሁን ደግሞ ላደረሱበት በደል እንኩዋን ፈጣሪውን የሚያመሰግን ሆኖአል:: "እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው" ነበር ያለው:: ምንም በደል ቢደርስበት እነርሱ አልተለወጡ ይሆናል እንጂ እርሱ ግን ትናንት የሚያውቁት ዮሴፍ አይደለም:: "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላቸው::

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

ታሪኮቹን እየደጋገምን የምናቀርበው አስተማሪ ስለሆኑ ነው። 🙏🙏
"ከሚዎዱሽ ወንዶች የሞተ አለ?"

► ጊዜው፥ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር የጀመረበት፣ሐዋርያት በምልዓት ያልተጠሩበት፣ የዮሐንስ መጥምቅ ትምህርት የተፈጸመበት ወቅት ነው።

በዚያ ዘመን በገሊላ ናይን(Nain) ከተማ ይኽ ከዚኽ ቀረሽ የማትባል 'የደም ገምቦ' መልከ መልካም ሴት ነበረች። ውበቷ የኀጢኣትም የገንዘብም 'ትርፍ' ኾኗት ብዙ ጊዜ ቆይታለች።

ከዕለታት አንድ ቀን እንደልማዷ በመስታዎት ፊት ቆማ ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጠጕሯ ውበቷን ተመለከተች። ነገር ግን የመስታወቱ ምልሰት ላይ ከፊት ያለው ውበቷን ያይደለ ሞቷንና ኀጢኣቷን የነፍሷንም ድካም ተመለከተች።

ይኽም ራስን በጥልቀት የማየት ጉዳይ በሥጋ ዐይን አይኾንም። መጽሐፍ "ወብነ ክልኤቲ አዕይንት ውሳጣውያት ህየንተ አዕይንት ሥጋውያት" ብሎ በነገረን በነፍስ ዐይን እንጂ በመስታዎቷ ፊት ቆማ በዘመን ፀሓይ ለሚረግፈው አበባነቷ እንዲኽ አለች፦

"ዘወትር ወደ ዝሙት የምትሮጡ እግሮቼ ኾይ ሞት በሚያሥራችኹ ጊዜ እንደምን ትኾናላችኹ? ልታመልጡ ትወዳላችኹ አይቻላችኹም፣ ባንተ ብዙ ያጣኹ አንደበቴ ኾይ፦ ትመልስለት ዘንድ የማይቻልኽ የዐለም ኹሉ ገዥ የሚኾን ሞት ዝም ባሰኘኽ ጊዜ እንደምን ትኾናለኽ?'' ከድምፅ አልባው ምስሏ ጋር እንዲኽ ስታለቅስ ቆይታ ከኀጢኣት ወደ ጽድቅ የሚመልሳትን ጌታ ልትፈልግ ወጣች።

ግን ደገሞ ባዶ እጇን መኼድ አልወደደችም። ሃድኖክ ወደሚባል ነጋዴ ኼዳ ውድ ሽቱ ለመግዛት ጠየቀችው። የዘወትር ፈገግታዋን በፊቷ ላይ ያጣው ነጋዴም

ጠየቃት። እንዲኽ ስትል መለሰችለት

እቀብረው ዘንድ እወዳለኹ፡፡"

"ማርያም! ምን ኾነሽ አዝነሻል? ከሚወዱሽ ወንዶች የሞተ አለን?" ብሎ "እወ ብዙኅ ኀጢኣትየ ሞተ ወእፈቅድ እቅብሮ፤ ብዙ ኀጢኣቴ ሞተ እቀብረው ዘንድ እወዳለኹ፡"


[ማስታወሻ፦ ይቺ ማርያም የአልዓዛር እኅት ማርያም ወይም መግደላዊት ማርያም አይደለችም።]

ጸሎታ ወበረከታ የሀሉ ምስሌነ።
👍4
👁  👁

በተስፋ፡መኖሩን፡ተውና፡ዛሬውኑ፡ወደ፡ስራ፡ግባ። በራስህ፡ላይ፡ለውጥ፡ልታመጣ፡የምትችለው፡ስትመኝ፡ብቻ፡ሳይሆን፡ስትሰራም፡ጭምር፡ነውና!
ወደ፡አክሽን፡ያልተለወጠ፡ምኞት፡ተራ፡ምኞት፡ብቻ፡ነው!
                                                         

  (ብሩክ የሺጥላ)
“እኔ ግን ክቡር ጳውሎስ
"የእግዚአብሔር ማደሪያ ነን"
እንዳለ “እኛስ የእግዚአብሔር ማደሪያወች ነን” ብየ ሳልበቃ ደፍሬ እናገራለሁ? እንዲህ ማደሪያወቹስ ከሆንን
ሰውነታችንን ማንፃት ይገባናል፡፡ እሱ ንፁህ እንደሆነ ወዶ
ያድርበት ዘንድ ፤ እሱ ክቡር እንደሆነ ማደሪያውን ሰውነታችንን እናከብረው ዘንድ በበጎ ስራ በከበረ ነገር እናስጌጠው ዘንድ ይገባናል፡፡ በዓለማዊ ሥራ ሁሉ ገንዘብ ያደርጓት ዘንድ በማይቻል በንፁህ ልቡና ፀሎትንና ፈቃዱን በመፈፀም ሰውነታችንን እናሰለጥነው ዘንድ ይገባል፡፡ የልዑል ክርስቶስ ብርሃን በነፍሳችን መልቶ ያድርባታልና። የጌትነቱ ብርሃን በልቡናችን ላይ ይስላልና ሰውነታችንን ማንፃት ሰውነታችንን ማክበር ይገባናል”

(ማር ይስሐቅ)

@nshachannel
🙏5👍21
የምወዳቸው መምህር በትረማርያም አበባው ከሚያስተምሩት በትቂቱ አካፍላችኋለሁ🙏

ሃይማኖትና ፍልስፍና ክፍል 1
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ስለ ሥላሴ ከመነጋገራችን በፊት መጀመሪያ የዚህች ዓለም ፈጣሪ አላት ወይስ የላትም።ፈጣሪ ላለመኖሩ ወይም ለመኖሩ ማረጋገጫችን ምንድን ነው?የሚለውን በዚህ ክፍል እንመልከት።በእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ፈጣሪ ስለራሱ መኖር ራሱ ነገረን እንጂ ሰው ተመራምሮ ሕልውናውን ማወቅ አይችልም እንላለን።እንግዲህ በእውቀት ሰብአዊ አይደረስበትም ስንል።በፍልስፍና ክፍል በተለይም Theoretical Philosophy ውስጥ ከሚጠኑ ክፍሎች አንዱ Gnosiology ነው።በእኛ ተቀራራቢ ትርጉም ሐተታ እውቀት ወይም ነገረ እውቀት ማለት ነው።በዚህ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ እሳቤዎች አሉ።

1ኛ Dogmatismየሚባለው ሲሆን።በዚህ እሳቤ ውስጥ አንድን ከውጭ ወይም ከውስጥ ስላለ ነገር የምናገኘው እውቀት ፍጹም ነው።የሰውም አእምሮ ፍጹም ነው ይላል።በ5ቱ የስሜት ሕዋሳት ያለው እምነት ታላቅ ነው።እነዚህንም የስሜት ሕዋሳት በመስታወት ይመስላቸዋል።አንድን ነገር በመስታወት ፊት ብናቆመው የሚያሳየን ነገር ያንኑ ነው።የስሜት ሕዋሳቶቻችንም ስለሆነ ነገር የሚያስገነዝቡን እውቀት ፍጹም ልክ ነው ብሎ ያስባል።በእውነቱ ይህ እሳቤ ግን የተሳሳተ ነው።የተሳሳተ ለመሆኑ መለኪያችን ምንድን ነው ቢባል የስሜት ሕዋሳችን የሚያሳየን በሙሉ እውነት ነው ካልን።አንድን ቀጥ ያለ ዱላ ከውሃ ውስጥ ስንከተው የተጣመመ ይመስለናል።ስለዚህ ሁኔታ የስሜት ህዋሳታችን ወይም እይታችን የተሳሳተ ነገር እንዳስተዋለ መረዳት አያዳግትም።

2ኛው Scepticism የሚባለው እሳቤ ሲሆን ይህ ደግሞ እውነትን ማግኘት ፈጽሞ አይቻልም የሚል የላይኛው ቲዎሪ ተቃራኒ ነው።እውነት እንደ የሰው ይለያያል።እውነት ማለት አንድ ሰው ለራሱ ትክክለኛ መስሎ የሚታየው ሀሳብ ነው።ስለዚህ እውነት የግል እንጂ የጋራ እውነት አትገኝም ለአንድ ነገር ራሱ 2 ተቃራኒ እውነቶች ሊኖሩት ይችላሉ።ለምሳሌ ዳገትን ስንወጣ ዳገት እንለዋለን ስንወርደው ደግሞ ያንኑ ቁልቁለት እንለዋለን ይላሉ።በስሜት ህዋሶቻችን የምናገኛቸው እውቀቶች ጉድለት አለባቸው።ከእኛው ራሱ በተለያየ ሁኔታ ስንሆን ለአንድ ነገር ቋሚ እውነት የለንም።ጤነኛ ስንሆን የጣመን ስንታመም ይመረናል።በህጻንነታችን የወደድነው አሁን ያስጠላናል።በአንዱ ሀገር የተወደደው በአንዱ ይጠላል።ስለዚህ ቋሚ እውነት ፈጽሞ የለም ይላሉ።እኛ ግን የስሜት ሕዋሳችን የሚነግረን ሁሉ 100 በ100 ልክ ነው አንልም።ቋሚ እውነትም ፈጽሞ የለም አንልም።እግዚአብሔር ቸር ስለሆነ ጥቂት እውቀትን ሰጥቶናል የጋራ እውነትም አለ ብለን እናምናለን ለምሳሌ የማር ጣፋጭነት የሬት መራራነት በመጽሐፍም የተጻፈ ነው።የፀሐይ ብሩህነት... ወዘተ የጋራ እውነታችን ነው።

3ኛ Pragmatism የሚባለው ነው።ይህ በቅርብ ዘመን የተፈለሰፈ እሳቤ ነው።ይህ ደግሞ እውነትን ከጥቅም ጋር አያይዞ የሚናገርና ጥቅም የተገኘበት ነገር በሙሉ እውነት ነው ብሎ ያስባል።እኛ ግን እውነት ከጥቅም ጋር ብቻ አይያያዝም እንላለን።

4ኛ Positivesim በዚህ እሳቤ ደግሞ ከዓለሙ ውስጥ ልናውቀው የሚቻለው በዙሪያችን ለሚገኘውና ለምናየው ግዙፍ ዓለም ብቻ እርግጠኞች ነን እንጂ ከዚህ ውጭ ላለው በሃይማኖት ስለሚነገረው ሰማያዊ ዓለም በቂ ማስረጃና ድጋፍ ስለሌለን ምንም የምናውቀው ነገር የለንም።ውሸት ነው።ማናቸውም በዚህ ዓለም የሚደረገው ሁሉ የሚካሄደው በተፈጥሮ ሕግ ነው ይላል።እኛ ግን አንድን ነገር እኛ ስላላየነውና ስላልተረዳነው የለም ማለት አንችልም።እውር ብርሃንን ስላላየ ብርሃን የለም አይባልም።

5ኛ Criticism የሚባለው ነው።የሰው አእምሮ እንደመስታወት ያየውን ወይም በ5ቱ የስሜት ህዋሳት የተረዳውን ብቻ ያደርጋል ይላል።እኛ ግን ከዚህ ውጭም ውሸትን መዋሸት ይችላል ዝም ብሎ ውጭ ያየውን ብቻ እንደመስታወት አያንጸባርቅም እንላለን።ስለዚህ እኛ ስለ እግዚአብሔር ስናወራ ራሱ ስለራሱ የነገረንን ይዘን እንጂ የስሜት ሕዋሶቻችን ያሳሰቡን ብቻ እውነት ነው አንልም።ከዚህ ውጭ የሆነ ጠንካራ እምነት ነገረ ሥላሴ እንድናውቅ
ይረዳናል።ስለዚህ እምነት ምንድን ነው የሚለውን ቀጣይ ክፍል
እናያለን ይቆየን

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 15 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
👍2🙏21
ምሥጢረ ሥላሴ
      
በብዙ ገጸ ንባብ አብ ወልድን ወልድየ ሲለው ወልድም አብን አቡየ ሲለው ይስተዋላል።ይህ አብነት የባሕርይ አብነት ነው።ይህ ወልድነት የባሕርይ ወልድነት ነው።አብ አብ ስለተባለ ከወልድ አይበልጥም።ወልድም ወልድ ስለተባለ ከአብ አይበልጥም።ከአብ ያለ እናት ተወለደ ስንልም እንዴት ተወለደ ለሚለው ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል ነው።አብ ወልድን ወለደ ስለተባለ ከወልድ ቀድሞ የነበረበት ዘመን አልነበረም።አሐቲ ቅድምናሆሙ ለሥላሴ ወዕሩያን እሙንቱ በቅድምና ይላልና።የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ቅድምና አንድ ነው።በዘመን አንዱ ከአንዱ አይበልጥም። በመፍጠር በማዋሐድ በማጽናት በማንጻት አንድ ናቸው።ምንም እንኳ አንዱን ጉዳይ ለአንዱ ሰጥቶ ቢናገር በአካላዊ ግብር ካልሆነ በስተቀር በሥልጣናዊ ግብር አንድ ናቸው።ይህንንም የሚያሳየን ጌታ ስለ ትንሳኤው።ንሥትዎ ለዝንቱ ቤተ መቅደስ ወበሠሉስ እለት አነስኦ... ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን
አስነሳዋለሁ ብሎ ይኽውም ስለ ሥጋው እንደሆነ ተጽፋል።ስለዚህ ወተንሣእኩ በሥልጣነ ባሕቲትየ ይላል።በራሴ ሥልጣን ተነሳሁ ይላል።በሌላ በኩል ደግሞ አብ አነሳው ይላል።በሌላ ገጸ ንባብ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አስነሳው
ይላል።ይሕ ሥልጣናዊ ግብር ስለሆነ ለአንዱ አካል አድሎ ቢናገርም በተገናዝቦ የሚሰሩት ስራ ነው።ተገናዝቦ የሌለበት አካላዊ ግብር ነው።አካላዊ ግብር የሚባለው የአብ መውለድ
ማስረጽ ነው።የወልድ መወለድ ነው።የመንፈስ ቅዱስ መስረጽ ነው።

ነገረ ሥላሴ ጥልቅ ስለሆነ መጻሕፍትን በማንበብ መምህራንን በመጠየቅ ልናሰፋው ይገባል።በምሥጢረ ሥላሴ የተነሱ ብዙ መናፍቃን አሉ።ሦስቱ አካላት ለየራሳቸው ናቸው ያሉ ነበሩ።ይህ ግን ስህተት ነው የሚያገናዝባቸው መለኮት አለና።እንደሰባልዮስ አንድ ገጽ ያሉም አሉ።ነገር ግን እፌኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ መንፈሰ ጽድቅ ካልዐ ዘይወጽእ እም አብ ብሎ።ካልዐ ብሎ በአካል ሦስት መሆናቸውን ስለሚያስረዳ።ጉዳዩ ፈራሽ ሆኖ ይገኛል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 15 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
1
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 1
እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በገነት ካኖረው በኋላ አዳም ሊያደርገው የሚገባውን ነገር ነግሮታል ይኽውም ከእጸ በለስ እንዳይበላ ነው።ምሥጢሩ ጾም ነው።በዚህ ጉዳይ ሦስት ነገሮችን እናስተውላለን ሕግ ምርጫ እና ነጻነትን።ሕግ ፈጣሪ ለአዳም የሰጠው ነው።ነጻነት ደግሞ ሰው የሚጠቅመውንና ይሻለኛል ያለውን ለመምረጥ የተሰጠ በአእምሮ የሚመራ
ነው።ምርጫ ደግሞ ነጻነትን ተጠቅሞ የሚመርጡት ነው።አዳም እጸ በለስን ቢበላ የሞት ሞትን እንደሚሞት ነግሮታል።ሞት ማለት ነፍስ ከሥጋ መለየት ማለት ነው።የሞት ሞት ማለት ደግሞ ከእግዚአብሔር መለየት ነው።አዳም ግን ነጻነቱን ተጠቅሞ እጸበለስን በላ።ከበላ በኋላ ልጅነቱን አጣ ልጅነት ማለት ክብር ማለት ነው።ይኽውም የጸጋ ክብር ነው።የጸጋ ማለትም ከእግዚአብሔር የተሰጠ ማለት ነው።ጸጋውን ወይም ልጅነቱን ካጣ በኋላ ግን እግዚአብሔርን በመበደሉ አእምሮው ወደ ጸጸት ተመለሰ።እግዚአብሔርም የአእምሮውን መመለስ አይቶ ባጠፋው ጥፋት ፈታሒ በጽድቅ በእውነት ፈራጅ ነውና 5500 ዘመን ቀጥቶ ደግሞም መሐሪ ነውና በቸርነቱ ተወልዶ ስለእርሱ ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መልሶታል።ስለዚህ ነገረ ልደት የእግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለው ጥልቅ ፍቅር የተገለጸበት ሰውና መላእክት አንድ ላይ ያመሰገኑበት ትልቅ ምሥጢር ነው።አምላክ ሰው የሆነበት ሰውም አምላክ የሆነበት ትልቁ ምሥጢር እኛን ከስቃይ አድኖ ወደ ዘላለም እረፍት ለመመለስ መሆኑን ስናስብ የጌታችን ፍቅር ምን ይረቅ ብለን አድንቀን አድንቀን አድንቀን ግን ስለማንጠግብ ዕፁብኬ ዕፁብ ውእቱ
እስመ ለዕፁብ ትርጓሜ አልቦቱ ብለን እናቆማለን።ሊቃውንቱም ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ እያሉ ገልጸውታል።እንግዲህ የልደት ምስጢሩ ሰው አምላክ ሆነ አምላክ ሰው ሆነ የሚለው።ምን ሆነ ስንል ተወለደ። የት ተወለደ ስንል በቤተልሔም ተወለደ።መቼ ተወለደ ስንል የዛሬ 2013 ዓመት ወደኋላ ስንቆጥር በምናገኘው ዓመት ታኅሣስ 29 ቀን።ለምን ተወለደ ስንል አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ
ነው።የተወለደው ማን ነው ስንል እግዚአብሔር።እግዚአብሔር ማለት አምላክ ፈጣሬ ሰማያት ወምድር ማለት ነው።ከማን ተወለደ ስንል ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት ተወለደ እንላለን።የተወለደው እግዚአብሔር ከሆነ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ያለ ረቂቅ ሁሉን ቻይ ነው።ዓለምን የፈጠረ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረ ነው።ሰው ደግሞ ውስን የተፈጠረ ድኩም ነው።ስለዚህ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ስንል ምን ማለታችን ነው ቢሉ።እንበለ ውላጤ ያለመለወጥ
ነው።ይህም ማለት አምላክ ወይም ፈጣሪ ተለውጦ ሰው ፍጡር ሆነ ማለት አይደለም።አምላክ አምላክነቱንና የአምላክነቱን ግብር ሳይለቅ ምልዐቱን ርቀቱን ሳይለቅ በሥጋ ገዘፈ ዘመን ተቆጠረለት የሚዳስሰ የሚጨበጥ የሚታመም ሆነ።ሰውም ውሰንነቱን ሳይለቅ በመለኮት ረቀቀ ዘመን የማይቆጠርለት ሆነ መላ ማለት ነው።ሲጠቃለል ወልድ ዋህድ በተዋሕዶ ከበረ ማለት ነው።ይህንን ምሥጢር በመተው እነ ፎጢኖስ የክርስቶስ ህልውና ከማርያም ወዲህ ነው ብለው ክደዋል።ግን ራሱ ጌታ አብርሃም ሳይወለድ ነበርኩ ባለው ቃል ይረታሉ።እምቅድመ ይትወለድ አብርሀም ሀሎኩ አነ እንዲል።ቅዱስ ኤፍሬም በሃይማኖተ አበው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው ይላል።ድንግል ማርያምን የፈጠረ ጌታ ከድንግል ማርያም ተወለደ።አርዮስ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ አብ እርሱን ፈጠረ እርሱ ደግሞ ፍጥረታትን ፈጠረ ብሎ ካደ።ነገር ግን ዮሐ.1፥3 ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም ባለው ይረታል።ጌታ ሊወለድ 24 ቀን ሲቀረው ማለትም ከታኅሣሥ 5 ጀምሮ ቤተልሔምን በመላእክት በተለየ አስጠብቋታል።እነሆ ድንግል ትጸንሳለች
ወንድ ልጅም ትወልዳለች ያለው የኢሳይያስ ትንቢት ታኅሣስ 29 ተፈጸመ።ኢሳ.7፥14

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ጥቅምት 15 2013 ዓ.ም
መ/ር በትረማርያም አበባው
ኢትዮጵያ
👍41
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 2
በልደት ወይም በሥጋዌ ዙሪያ የተነሱ መናፍቃን ብዙ ናቸው።
1ኛ ሰባልዮስ፦ይህ መናፍቅ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ገጽ ናቸው ያለ እና በ220 ዓ.ም አካባቢ የነበረ መናፍቅ ነው።ይህ መናፍቅ ጌታችን የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስን ይልክላችሁ ዘንድ እኔ አብን እለምንላችኋለሁ ባለው የወንጌል ቃል ይረታል።

2ኛ ከ310-390 ዓ.ም አካባቢ የነበረው አቡሊናርዮስ የተባለ መናፍቅ ነው።ክርስቶስ ልብና ነፍስ የለውም።በልቡና በነፍሱ ምትክ መለኮቱ አለ ያለ መናፍቅ ነው።ይህ ደግሞ በዮሐ.10፥17 ነፍሴ እስከ ሞት ተጨነቀች ባለው ይረታል።ነፍሴ ያለው መለኮትን ነው እንዳይል መለኮት አይጨነቅምና በዚህ ይረታል።በተጨማሪም ጌታ ተፈጸመ አለ
ራሱን አዘነበለ።ነፍሱም ተለየች ባለው ይረታል።ነፍሱ መለኮቱ ከሆነች መለኮት የሌለበት ቦታ የለምና ሞተ ማለት ትርጉም አይሰጥምና በዚህ ይረታል።

3ኛ ንስጥሮስ ወልድ ከነቢያት እንደ አንዱ ነው አለ።ይህ መናፍቅ ከ351-451 ዓ.ም አካባቢ የነበረ መናፍቅ ነው።ንስጥሮስ ግን ዮሐንስ መጥምቅ በተናገረው ቃል ይረታል ይኽውም "ከእኔ በፊት ያለው እርሱ ከእኔ በኋላ ይመጣል" ይመጽእ እምድኅሬየ ዘሀሎ እምቅድሜየ ባለው ይረታል።እንደነቢያት እግዚአብሔር በጸጋ ያደረበት ቢሆን ኖሮ ከዮሐንስ በፊት ሊኖር አይችልምና።ከዮሐንስ በፊት የነበረው
ከዮሐንስ በኋላ የተወለደው የባሕርይ አምላክ መሆኑን ይናገርበታልና በዚህ ይረታል።

4ኛ አርጌንስ ይህኛው ደግሞ ከወልድ አብ ከመንፈስ ቅዱስ ወልድ ይበልጣል ከመላእክት መንፈስቅዱስ ይበልጣል ብሎ ያበላለጠ ነው።ነገር ግን እኔና አብ አንድ ነን ባለው አምላካዊ ቃል ይረታል።ከእኔ አብ ይበልጣል ይል የለምን ቢሉ ሕማም የሚስማማው ሥጋን ስለለበሰ ከአብ ብቻ አይደለም ከመላእክትም ጥቂት አሳነስከው ተብሎ ተጽፏልና ስለ ሥጋ እንግዳነት ተናገረ ከተዋሕዶ በፊት የነበረውን የአዳምን ባህርይ ማለቱ እንጂ ከተዋሕዶ በኋላስ በሥልጣን በፈቃድ አንድ ናቸው መበላለጥ የለም።

5ኛ አርሲስ ወይም አርሲሳን የሚባሉ መናፍቃን ደግሞ ጌታ ነፍሳትን ለማዳን ሥጋውም ወደ ሲኦል ሄዷል ብለዋል።ነገር ግን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን እንደገነዙት ስለሚናገር በዚህ
ይረታሉ።

6ኛ መነናውያን ከ216 እስከ 270 ዓ.ም አካባቢ የነበሩ መናፍቃን ናቸው።የክርስቶስ ሥጋ ምትሐት ነው የሚሉ ናቸው።ምትሐት ማለ እንደ ጥላ ያለ የማይዳሰስ ማለት ነው።ነገር ግን ታመመ ተሰቀለ ስለሚልባቸው ጥላ ወይም ምትሐት ደግሞ አይታመምምና በዚህ ይረታሉ።

7ኛ ልዮን የተወለደው ኢየሱስ አንድ አካል ሁለት ባህርይ ሁለት ፈቃድ ነው።መለኮት የመለኮትን ስራ ይሰራል ሥጋም የሥጋን ስራ ይሰራል ያለ መናፍቅ ነው።የሚያድን መለኮት ነው ይል ነበረ።ይህ ከሆነ ሐዋርያት በመርከብ ሲሄዱ አድነን ብለው ሥጋን ቀስቅሰውታል።መለኮት ብቻ የመለኮትን ስራ ይሰራል ከተባለ መለኮት አይተኛምና ለምን ቀሰቀሱት ፈቃዳቸውን አይቶ
አያድናቸውም ነበርን።ይህንና ይህን በመሰለ ኃይለ ቃል ይረታል።

8ኛ አውጣኪ የክርስቶስ ሥጋ የማይደክም የማይታመም ነው ያለ መናፍቅ ነው ነገር ግን ዮሐ.4፣6 ወደኪሞ እግዚእ ኢየሱስ በሐዊረ ፍኖት ነበረ ህየ ባለው ይረታል።

የኛ ትምህርት ግን ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ።ሰው የሆነው
አምላክ ነው አምላክም የሆነው ሰው ነው።ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ከሁለት አካል አንድ አካል አዳምን ለማዳን ሰው የሆነ ከድንግል ማርያም የተወለደው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
ብለን እናስተምራለን።


ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 15 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
2👍1
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 3

ጌታ ከሰማየ ሰማያት ወረደ እንላለን ነገር ግን ወረደ የሚባለው በሁሉ ቦታ የሌለ ነው ይህ ነገር እንዴት ነው ቢሉ።ወረደ ሰው ሆነ ተዋሐደ ተብሎ ነው የሚተረጎም።ምክንያቱም ከሰማይ ወረደ ካልን በምድር የለም ኖሯል እንዴ ያሰኛል።እግዚአብሔር ደግሞ በሁሉ ቦታ ያለ ነውና።ወረደ፥ኮነ፣ኀደረ ሲል ብታገኘው ተዋሐደ ሰው ሆነ ተብሎ እንደሚተረጎም አስተውል።በሃይማኖተ አበው ላይ መላእክት ከቦታ ወደ ቦታ እንደሚሄዱት ከሰማይ የመጣ አይደለም መላእክትስ ከሰማይ ወደ ምድር ሲላኩ ከሰማይ ይታጣሉ ከምድር ይገኛሉ።ከምድር ወደ ሰማይ ሲያርጉ ከምድር ይታጣሉ ከሰማይ ይገኛሉ ጌታ ግን ከሰማየ ሰማያት ወረደ ስንል ብትሰማ እንደ መላእክት ከዚያ ሲመጣ ከዚህ የሚገኝ ከዚያ የሚታጣ አይደለም ሰው ሲሆን ምልአቱንም አልለቀቀም እንጂ ይላል።አኮ ዘፈለሰ እመካን ውስተ መካን ከመ መላእክት እስመ እሙንቱ ይትኃጥኡ እመካኖሙ ሶበ ይትፌነው ለመልእክት ውእቱሰ ነስአ ሥጋ እንዘ ምሉእ ውእቱ በኩለሄ እንዲል ነው።የጌታ ልደት ሁለት ነው።አንደኛው ቀዳማዊ ልደት የሚባለው ሲሆን ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ
የተወለደው ነው።ሁለተኛው ከድንግል ማርያም የተወለደው ልደት ነው።እመቤታችን የወለደችው ከአብ የተወለደውን በሥጋ ነው።ስለዚህም ሥጋ በመለኮት ወልደ አብ ተባለ።ቃል ደግሞ በሥጋ ወልደ ማርያም ተባለ።ያው አንዱ ኢየሱስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ተባለ።ድንግል ወለደት ዘኢዚአሃ መለኮተ በዘዚአሃ ሥጋ አብኒ ወለደ ዘኢዚአሁ ሥጋ በዘዚአሁ መለኮት
ይላል።ምን ማለት አብ የእርሱ ያልሆነውን ሥጋ በመለኮት ወለደው።ድንግልም የእርሷ ያልሆነውን መለኮት በሥጋ ወለደችው።ስለዚህ እርሱ ብርሃን እንደተባለ እርሷ እመ ብርሃን እርሱ አምላክ እንደሆነ እርሷ እመ አምላክ ተባለች።ሃይ.አበ 35፤17 ላይ በምድር አባት በሰማይ እናት የለውም
ብሏል።በቀዳማዊ ልደቱ ከአብ ያለ እናት ተወለደ።በደኃራዊ ልደቱ ከድንግል ማርያም ያለ አባት ተወለደ።ድንግል ማርያምም በድንግልና እንደጸናች ሃይ.አበ.53፥2 ወነበረት ድንግል በድንግልና ከመ ቀዳሚ ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ይላል።አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው አልሆኑም ሰው የሆነው በተለየ አካሉ ወልድ ነው።ሃይ.አበ 90፥18 አብ ወመንፈስ ቅዱስ ኢተሠገው ወኢኮኑ ሰብአ ይላል።እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው
ይኩነኒ ባለችበት ቅጽበት ነው።ሰው ሆነ የምንለውም ከዚያ ጀምረን ነው።

ጌታ ሰው ሲሆን የሥጋ ገንዘብ ለቃል የቃል ገንዘብ ለሥጋ ሆነ ይህንንም ቅዱስ ቄርሎስ እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል ብሎ በድርሳኑ ገልጾልናል።ሃይ.አበ 26 ላይ
ሥጋ ወዘአልቦቱ ሥጋ ተደመሩ ኅቡረ በከዊነ አሐዱ ሕላዌ ወበአሐዱ ገጽ ወአሐዱ አካል ይላል ምን ማለት ነው።ሥጋ እና መለኮት በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆኑ ማለት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 15 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
👏21👍1🙏1
"ወንድምህ ኃጢአት ሲሰራ ብታየው ተው በለው፤ ሥጋው ድል ነስቶት ነው እንጂ ሲዖልን ወዶ ኃጢአት የሚሠራ የለምና"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
3👍2
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 4
እንግዲህ ሃይ.አበ 90፥18 ላይ አብና መንፈስ ቅዱስ ሰው አልሆኑም ብለናል።አምላክ ሰው ሆነ ካልን አብና መንፈስ ቅዱስ አምላክ አይደሉምን? አምላክ ሰው ከሆነ አብ መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆኑ አያሰኝምን የሚል ጥያቄ በአእምሯችን ሊመጣብን ይችላል።ስለዚህ በዚህ ክፍል ይህንን ለማስረዳት እንሞክራለን።ይህንን ለመረዳት ምሥጢረ ሥላሴ መረዳት ይገባል። እግዚአብሔር አንድ ነው።ይህን ዓለም የፈጠረ እግዚአብሔር በመለኮት አንድ በአካል 3 ነው።ለአብ የራሱ የሆነ
ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ፍጹም አካል አለው።ለወልድ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ፍጹም አካል አለው።ለመንፈስ ቅዱስም
ፍጹም መልክ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው።አብ በአካሉ በሁሉ ያለ የመላ ነው።ወልድም በሁሉ ያለ የመላ ነው።መንፈስ ቅዱስም በሁሉ ያለ በሁሉ የመላ ነው።እንግዲህ እንዲህ ከሆነ
ተደራርበው ነው የሚኖሩት ማለት ነው ወይስ እንዴት ነው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል።አብ ካለበት ቦታ ላይ በሙሉ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አሉ።በሥላሴም ተዋሕዶ አለ ሥላሴ በተዋሕዶ ወተዋሕዶ በሥላሴ ይላል ሃይማኖተ አበው።የሥላሴ አንድነት በሕልውና ነው።ምሥጢረ ሥላሴ ታላቁ ምሥጢር ያለው ኩነት ላይ ነው።አብ ልብ ወልድ ቃል መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ይባላል።በአብ ልብነት ያስባሉ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ።ይህ ኩነት እንደ አካላት ተከፍሎ የለበትም።ሥላሴን በተዋሕዶ የሚያገናዘብ ይህ ነው።ቃል ሥጋ ኮነ ይላል ዮሐ.1፥14 ቃል ሰው ሲሆን ከአብ ሳይለይ ነው የተባለው በኩነታት ተከፍሎ
ስለሌባቸው ነው።ከአብ ሳይለይ በተለየ አካሉ ሰው ሆነ ስንልም እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው።የፀሐይ ብርሃን እና ሙቀቱ አይለያይም ብርሃኑ ባለበት ሙቀቱ አለ ይህም ማለት ብርሃን ከሙቀት ተከፍሎ የለበትም ማለት ነው።ነገር ግን ተለይቶ ከዓይናችን ጋር ተዋሕዶ እንድናይ የሚያደርገን ብርሃኑ እንጂ ሙቀቱ
አይደለም።ይህንን እንዴት እንረዳዋለን ቢሉ።ሙቀትማ በጨለማ ጊዜም ኑሮ ግን እንድናይ አይረዳንምና ነው።ስለዚህ አብና መንፈስ ቅዱስ ሰው አልሆኑም ሰው የሆነ በተለየ አካሉ ነው ማለት ይህ ነው።ስለዚህ እንዲህ ከሆነ ደግሞ አብና መንፈስ ቅዱስን ከመለኮትነት አላወጣናቸውም ማለት ነው።አንድ
የሚሆኑ በሕልውና በመለኮት ነው እንጂ በአካል አይደለምና በተለየ አካሉ ሰው ሆነ ስንል በምልዓት አብ ካለበት ሁሉ
የሚኖረው ወልድ ምልአቱን ሳይለቅ ሰው ሆነ እንላለን።ሥላሴ በሕልውና አንድ ናቸው ያልነው ምስጢር ሰው ሲሆን
አልፈረሰም።መፍጠር ማዋሐድ እና የመሰሉ ግብሮች የሥላሴ የአንድነት ግብራቸው ወይም ሥልጣናዊ ግብራቸው ነውና።አብ አዋሐደው ወልድ አዋሐደው መንፈስ ቅዱስ አዋሐደው ቢል አንድ ነው።ብዙ ጊዜ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ ተገኘች ሲል።ግብረ አብ ግብረ ወልድ ቢል ያው ነው።አካላዊ ግብር ግን አይፋለስም።አካላዊ ግብር የሚባለውም የአብ መውለድ ማስረጽ የወልድ መወለድ የመንፈስ ቅዱስ መስረጽ ነው።አብ አጸናት መንፈስ ቅዱስ አነጻት ሲል ብታይ ማንጻት የመንፈስ
ቅዱስ ብቻ ማጽናት የአብ ብቻ አይምሰልህ።ስልጣናዊ ግብር ስለሆነ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አጸናት አብ ወልድ አነጻት ቢልም ያው ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 16 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
3
Audio
የጽዮን ደጆች ቅኔ ተሞሉ
ለድንግል ክብር እልል እያሉ
አንደነጭ እንቁ የሚያበራ
አልፈናል/አርፈናል ስሟን ስንጠራ/2/

ሀይልን በሚያደደርገው ለተወዳጅ ስምሽ
የዜማ እቃችንን አነሳን ልጆችሽ
ማሕተመ ቡራኬሽ በልባችን አለ
አፋችን ማርያም ሲል ጭንቃችን ቀለለ
           
         /አዝ=====

የምስጋና ጥበብ የቅኔ ሀብት ጸጋ
ከደጃፍሽ መጥተን ገዛን ያለዋጋ
ጥልቁን ለቀነዋል በትከሻሽ ሆነን
ጽዮንን በእልልታ በዜማ ሸፍነን
          
        /አዝ=====

ጠቢባን ምክራቸው ታየ ተሰውሮ
ሚስጢር ተገለጠ በህጻናት አእምሮ
ቤተልሔም ሰማች የብስራቱን ዜማ
ፍቅር ተለቀመ ከእግዚአብሔር ከተማ
            
         /አዝ=====

ከአሸናፊው ልጅሽ ከክርስቶስ ጋራ
አንደዘበት ወጣን የሞትን ተራራ
ፍሬሽን ቀመሰነው ልቦናችን ረጋ
ሰላም ነው ከእንግዲህ አንኖረም ስንሰጋ
👍5🥰2🤔1
እግዚአብሔር ብቻውን የተወው ሰው የለም።

መምህር እዮብ ይመኑ
👍3
ምርቃኑ ይድረሳችሁ " እርግማን ጥፋቱ ይራቅላችሁ🙏🙏
🙏8
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 5

ስለ ዘመነ ልደት ነቢያት አስቀድመው በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ከመንፈስ ቅዱስ ያገኙትን ተናግረዋል።ነቢያት ብቻ አይደሉም ጠንቋዮችም ተናግረዋል።ጥንቁልናንማ እግዚአብሔር ይጠላ የለምን ቢባል አዎ ይጠላል።ነገር ግን ለካዱትም ለተጠራጠሩትም ለአመኑትም ዝናምን የሚያዘንም ፀሐይን
የሚያወጣ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ትንቢቱንም በክፉዎች አድሮ ሊያናግር ይችላል።ይህም ቸርነቱን ያስረዳናል።ለምሳሌ በቀያፋ አድሮ ይህ ሁሉ ሰው ከሚሞት አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል ብሎ ትንቢት አናግሮታል።በለዓም ጠንቋይ ነበረ ነገር ግን ኮከብ ይሰርቅ እምያእቆብ ወያአትት ኃጢአተ ዓለም ብሎ ትንቢት ተናግሯል።ከያእቆብ ዘር ኮከብ ይወጣል የዓለምን ኃጢአትም ያስወግዳል ብሎ ትንቢት ተናግሯል።ቅዱሳን ነቢያትም
በየበኩላቸው ተናግረዋል ኢሳ.7፥14 እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ብሎ በድንግልና እንደምትወልደው ተናግሯል።ቅዱስ ዳዊት ይቤሎ እግዚእ ለእግዚእየ ንበር
በየማንየ ብሎ ሰው አምላክ ሆነ የሚለውን ምሥጢር ተናግሯል።በምሳሌም ሙሴ ሐመልማልና ነበልባል ተዋህደው አይቷል ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ.1፣1 በብዙ ምሳሌ እንደነገራቸው ገልጾልናል።ዳንኤል መቅደስ ትትሐነጽ እስከ ክርስቶስ ንጉሥ ወእምዝ ትትመዘበር ብሎ ተነበየ። የነቢያትን
ትንቢት ለመፈጸም ጌታ ሰው ሆነ የምንለው ስለዚህ ነው።ሕዝቅኤል በተዘጋ የምስራቅ ደጃፍ እና በንጉሥ አምሳል የእመቤታችንና የጌታ ነገር ተገለጸለት።ይህንን አይተው ኆኅትሰ
ድንግል ይእቲ ብለው እነ ቅዱስ ኤፍሬም ተረጎሙት።ነቢያተ ጽድቅ እንዳሉ ሁሉ ነቢያተ ሐሰትም በብሉይ ነበሩ።ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ነው ያሉትን ነቢያተ ሐሰት ደግሞ ከልባቸው አፍልቀው ከሰይጣን ሰምተው አይደለም ይሉ ነበር።በዘመናችንም እንዲህ ዓይነት የሐሰት ነቢያት ሊኖሩ ስለሚችሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛንነት መምህራንን በመጠየቅ እውነተኛውን ትንቢት ማወቅ አለብን።በጠቅላላ በብሉይ ስለ ጌታ መወለድ የተነገሩ ብዙ ምሳሌዎች
ብዙ ትንቢቶች አሉ።እነዚህን ትንቢቶች አይሁድ ሳይቀሩ ያውቋቸው ስለነበር ለሄሮድስ የሚወለድበትን ጊዜ ከነ ቦታው
ነግረውት ጌታን እገድላለሁ ብሎ 14 እልፍ ሕጻናትን አስገድሏል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 16 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
🙏2
2025/07/09 09:37:11
Back to Top
HTML Embed Code: