Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1275 - Telegram Web
Telegram Web
ትዳርና የወሊድ መቆጣጠሪያ ክፍል 5
......ባለቤቴ እና እኔ ኑሯችን ከእጅ ወደ አፍ ነው።እንኳን ልጅ ወልደን ማሳደግ ራሳችንንም ማኖር እየከበደን ነው።ስለዚህ ጥሩ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ የወሊድ መቆጣጠሪ እንጠቀማለን።ይህ አይፈቀድም ወይ...... የሚል ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይነሳል። በነገራችን ላይ የወሊድ መቆጣጠሪያ ካደረገች ሴት ጋር ሩካቤ ማድረግ ማለት በኮብል ስቶን ላይ ጤፍ እንደመዝራት ያለ ነው። ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ እንዲህ ይላል "ሚስቱ እንዳትወልድ መድኃኒትን ያደረገ ሰው ታላቅ በደልን በደለ" ይላል።መነኩሴ ሲመነኩስ ታላቅ የፍትወት ፈተና እንደሚያጋጥመው እውነት ነው። ስለዚህ ይህንን ለመዋጋት የስነ ልቡና ዝግጅት አድርጎ ነው የሚገባው።ወደ ትዳርም ሲገባ ልጅ እንደምትወልድ ቤት እንደምትሰራ በደንብ አስበህ የምትገባበት ነው።ስለዚህ ላለመውለድ የወሊድ መቆጣጠሪያን እንደ አማራጭ መያዝ ሳይሆን ብዙ ልጅ እንደምትወልድ አስበህ እንዴት እንደምታኖራቸው ማሰቡ ላይ ትኩረት ማድረግ የተሻለ ነው።

እንጂማ.... ሰው ፍትወት የማይነሳበት ቢሆን ኖሮ ሁሉም መነኩሴ በሆነ ነበር። ማስተዳደር አይሆንልኝም ካልክ አለማግባት እና መመንኮስ ነው።አይ ፍትወትን ማሸነፍ አልችልም ካልክ ደግሞ ልጆች ይወለዱ ለፍተህ ግረህ እየሰራህ አሳድጋቸው።በመነኮሳትምኮ ታላቅ የሆነ የፍትወት ፈተና አለባቸው።ነገር ግን በጾም በጸሎት ያለ እንቅልፍ በትጋህ ሌሊቱን ሙሉ በስግደት እያደሩ ፍትወቱን ለማጥፋት እስከ እለተ ሞታቸው ይታገሉታል። በትዳር ያለው ፈተና ደግሞ ልጅን ለማሳደግ ሙሉ ኃላፊነትን መሸከም ነው።ስለዚህ ይህንን ለማድረግ ደግሞ እስከ እለተ ሞትህ እየጣርክ እየሰራህ መኖር ነው።

ሌላው ግን የሰውን ልጅ የሚመግብ እግዚአብሔር መሆኑን መዘንጋት የለብንም።የሚያኖርም ነፍስን ከሥጋ የሚለይም እግዚአብሔር ብቻ ነው። ክረምትንና በጋን እያፈራረቀ የሰውን ልጅ የሚመግብ እግዚአብሔርን በፍጹም ልንጠራጠረው አይገባም።ትዳር በብዙ መንገድ ሊፈተን ይችላል።ስለዝህ አእምሯዊ የስነ ልቡና ዝግጅት አድርገን ነው ልንገባበት የሚገባው። እስከ መጨረሻው ላለመለያየት ልዩ ፍቅር እስከ ሞት ድረስ ሊኖረን ይገባል።
👍1
ትዳር እና አለመተማመን

አንዴ አባ ጳውሊ ሲሰራ ሲሰራ ውሎ ከሥራ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሚስቱን ከአገልጋያቸው ጋር አልጋ ላይ ተኝታ አገኛት።እና እርሱም ተረጋግቶ በቃ አንተም ለእርሷ መልካም ሁንላት አንቺም ለእርሱ መልካም ሁኝለት ብሎ መንኖ ገዳም ገባ ይባላል።በባልና በሚስት መካከል አለመተማመን ከነገሠ አደገኛ ነው።ባልና ሚስት አንድ አካል ስለሆኑ ፍጹም ግልጸኛ መሆን አለባቸው። ችግራቸውንም በግልጽ በመነጋገር መፍታት አለባቸው።እንዳው ቢቻል በባልና በሚስት ጉዳይ ሌላ ሦስተኛ አካል በጭራሽ ሊገባ አይገባም። እናትህም ትሁን አባትህም ይሁን አብሮ አደግ ጓደኛህም ይሁን ብቻ ማንም ቢሆን በእናንተ መካከል ሊገባ አይገባም።

ለምሳሌ እናትህ ሚስትህን ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ አገኘኋት ብላ ብትነግርህ ተረጋግተህ ሄደህ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝተሽ ሰዎች አየናት ብለውኛል ይህ ነገር እውነት ነወይ ብለህ ጠይቃት።አይ አይደለም ካለችህ ልታምናት የሚገባህ ሚስትህን ነው።አንተ እስካላየሀት ድረስ የሰው ነገር ሰምተህ ሚስትህን መጥላት አይገባም።ሌሎች ነግረውህ ሳይሆን በራስህ መንገድ አረጋግጠህ ጥፋተኛ ሆና ካገኘሀት ብቻ የራስህን ውሳኔ መወሰን እንጂ ሌላ ሰው በጭራሽ እንዳትሰማ ተጠንቀቅ።ሴትም ብትሆኝ እንዲሁ።በመካከላችሁ ምንም ዓይነት የጥርጣሬ ስሜት እንዳይገባ።

ውርጃ
ጽንስን ማስወረድ አይገባም።ጌታን ያጠመቀው እና ሴቶች ከወለዱት እርሱን የሚበልጠው የለም የተባለው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በጽንስ ደረጃ እያለ ነበር ለጌታችን የሰገደ።ሉቃ.1 ላይ አንፈርዐጸ እጓል በውስተ ከርሣ እንዲል። ስለዚህ ምንም እንኳ ከቤተሰብ ፈቃድ ውጭ ሥጋዊ ፈቃድ አነሳስቶን በሕገ ወጥ መንገድ ጸንሰን ብንገኝ ቤተሰብን ወይም የሰፈርህን ሰዎች ስድብ እና አሽሙር በመፍራት ጽንስ እንዳታስወርዱ። ላጠፋነው ጥፋት ይቅር ባይ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን ንሥሓ ገብተን ስድብን ተቋቁመን ልጁን ልናሳድገው ይገባል።
👍1
ከዝምታና ከመናገር የቱ ይሻላል?

አቀድም አእኲቶቶ ለእግዚአብሔር።
ዝምታ በግእዝ አርምሞ ይባላል።የቅድስና በር ነው።ከ10ሩ መዓርጋተ ቅድስና የመጀመሪያው አርምሞ ነው።በሌላ በኩል ተናገሩ ድንቅ ሥራውን በእውነት መስክሩ ይላል። ታዲያ መቼ በምን ጉዳይ የት ለምን እንናገር ዝምስ እንበል የሚለው ብዙ ጊዜ ያከራክራል።ጠቢቡ ሰሎሞን ቦ ጊዜ ለኩሉ ብሏል።ለመናገርም ጊዜ አለው ዝም ለማለትም ጊዜ አለው።

ዝምታን በሚመለከት እምተናግሮ ይኄይስ አርምሞ ከመናገር ዝም ማለት ይሻላል ሲባል።መናገርን በሚመለከት ደግሞ ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ይላሉ።የሆነ ሆኖ መቼ ዝም እንበል መቼስ እንናገር የሚለውን እንመልከት።

አርምሞ=ዝምታ
ዝምታ ነገርን በልብ የመያዝ ታላቅ ጥበብ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወንጌል ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ብሏል።የዝምታ አስፈላጊነት በነቢብ ወይም በንግግር ከሚሰሩ ኃጢአቶች ራስን ለማራቅ ነው። የነቀፋ የስድብ የሐሜት የውሸት የትምክህት የዘፈን የተርእዮ ሀሳብን የሚያንጸባርቁ ነገሮች ሲያጋጥሙን ከመናገር ይልቅ ዝም ማለት ይሻላል። ንግግርህ ለሰሚውም ለአንተም ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ወይም ሥጋዊ ጥቅምን የማይሰጥ ጉዳይ ከሆነ ባትናገረውና ዝም ብትል ይሻላል።

ተናግሮ=መናገር
የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ለመመስከር ለሌላውም ለማስተማር እና ለማሳወቅ የምንናገረው ነገር የጽድቅ መንገድ ነው።ወተዝያነው እምዕለት ዕለት አድኅኖቶ።በቀን በቀን የእግዚአብሔርን ማዳን ይነጋገሩ ነበር ተብሏል።አሁን ዘመናችን ከፍቶ እንጂ ቀድሞ አባቶቻችን እናቶቻችን ሲገናኙ ነገራተ እግዚአብሔርን ነበር የሚነጋገሩት። የቅዱሳንን ህይወት እያነሱ ይማማሩበት ነበር።ስለዚህ ሰሚው አካል ሰምቶ በመንፈሳዊ ወይም በዓለማዊ ረገድ ጥቅም የሚያገኝበት ከሆነ ተናገር።

ተናግረኽው በአንተ ላይ ከንቱ ውዳሴን ተርእዮን ትእቢትን የሚያመጣብህ ከሆነ መጀመሪያውንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ። ሰሚውን የሚያሳዝን የሚያናድድ የሚያበሳጭ ንግግር ከሆነ አለመናገር ነው።በሃይማኖት ጉዳይ ግን መናፍቁን ይከፋዋል ተብሎ ሃይማኖትን ከመመስከር ወደኋላ ማለት አይገባም።

ሌላው ግን በባልና በሚስት እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች አለመተማመን ሲሰፍን ተቀራርቦ መነጋገርና ባለን Resource መፍትሔ መስጠት ይገባል።ሌላው ግን አጥርተን በማናውቀው ጉዳይ ባንዘባርቅ መልካም ነው።ብንጠየቅ መልስ መስጠት የምንችለውን ጉዳይ ነው መናገር ያለብን።በሆይ ሆይ ከሌላ ሰው በሰማነው ጉዳይ ግን ዝም ብንል የምናተርፍ ይሆናል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
1👍1
ሞትን ስታስብ ምን ይሰማሀል?

ልክ ስትሞት በዚህ ምድር አለኝ የምትለው ነገር ሁሉ የአንተ ወዳለመሆን ይሸጋገራል።የለፋህበት የተጣላህበት ነገር ሁሉ ከንቱ ይቀራል። በዚህ ምድር ያሉት ሀብት ሥልጣን ክብር ጉልበት ዕውቀት እና የመሳሰሉት በዚህ ምድር እስካለህ ድረስ ብቻ የሚያገለግሉህ ናቸው።ስትሞት እነዚህ ሁሉ ምንም ናቸው።በእርግጥ እኒህን ነገሮች ከሞት በኋላ ለሚመጣው ሕይወት ካዋልካቸው ለነፍስህ ጥቅምን ይሰጣሉ።

ብዙ ቅዱሳን የዚችን ዓለም አጭርነት ተረድተው ንቀዋት በምናኔ በየጫካው በየፍርክታው በጾም በጸሎት ተወስነው ያሳልፏታል።ሞት አንዱ የሕይወታችን አካል ነው።ቀድሞ የነበሩ ሰዎች አሁን በሥጋ የሉም።ዓለምን አንቀጥቅጠው የገዙ ዝናቸው በዓለም የታወቀ ሰዎች አሁን የሉም ሞተዋል።

መጀመሪያውንም ካለመኖር ያመጣን እግዚአብሔር በሥጋ ወደ አለመኖር ይወስደናል።ሞት ሲታሰብ ይጨንቃል ምክንያቱም ሞተን ስላላየነው አናውቀውም።ሞት በዚህች ምድር ሳሉ ሥልጣናቸውን ጉልበታቸውን እውቀታቸውን ሀብታቸውን በአግባቡ ለመልካምነት ለተጠቀሙት ሰዎች ዕረፍት ነው። በተቃራኒው ሀብታቸውን ሥልጣናቸውን እውቀታቸውን ሌላውን ለመጉዳት ለተጠቀሙት ሰዎች ሁለት ሞት ነው።

ስለዚህ ሞትን ላለመፍራት ከፈለግህ በዚህች ምድር እስካለህ ድረስ ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቅ።3 ነገሮች ያስፈሩኛል ብሏል አንድ ሊቅ።እኒህም አለ፦
1ኛ ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
2ኛ ለፍርድ በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም
3ኛ ሲፈረድባት
ሁላችንም ካለመኖር እንድንኖር ያደረገን እግዚአብሔር ፊት እንቆማለን።ስለዚህ የእርሱን ረድኤት ጋሻ አድርገን በእርሱ ፊት ለመቆም የሚያበቃንን ስራ እንስራ።

እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቅር ይበለን።
👍5👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከ social media ያገኘሁት ድንቅ ምክር ስለሆነ አጋራኋችሁ🙏
🥰2👍1
"ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።" ራዕ 12፡1

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት አስተርዕዮ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!
🥰32
ጥበበኛው ሰው (ሁልጊዜ አስታውሱ)
 
ብዙ ሰዎች ወደ አንድ ጠቢብ ዘንድ በተደጋጋሚ እየሄዱ ተመሳሳይ ቅሬታዎችን እና ችግሮችን ይነግሩታል። በአንደኛው ቀን ግን ይህ ጠቢብ ሰው አንድ ቀልድ ነግራቸው እና ሰዎቹ ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይስቁ ጀመር ። ከሁለት ደቂቃዎች በኋላም ይህ ጠቢብ ሰው ያንኑ የቀድሞውን ቀልድ ደግሞ ነገራቸው። ጥቂቶች ብቻ ፈገግ አሉ። ለሦስተኛ ጊዜ መልሶ በነገራቸው ጊዜ ማንም ሰው የሳቀም የፈገገም አልነበረም። በዚህን ጊዜ ጥበበኛው ሰው ፈገግ እያለ እንዲህ አላቸው ። 
" በአንድ ቀልድ ደግማችሁ ደጋግማችሁ ልትስቁ አልቻላችሁም አትችሉምም ፤ ታዲያ ለምንድነው አንድ ዓይነት ለሆኑ ችግሮቻችሁ ደጋግማችሁ የምታለቅሱት " በማለት አስተምሮአቸዋል ።

ስለ ችግሮቻችሁ ደጋግማችሁ ማሰባችሁ እና ማዘናችሁ ጊዜን እና አቅማችሁን ማባከን ነው እና ስለመፍትሄው ማሰብ የተሻለ ነው ማለት ፈልጎ ይሆን?
👍74
ከኢየሱስ አንደበት

"ወንጌል ስለ ኢየሱስ ብቻ ነው" ያለ ማን ነው?
ተሳስቷል።
  የፍቅሩና ቤዛነቱ ምስክር የኾኑ ቅዱሳትና ቅዱሳን መታሰቢያቸው በወንጌል እንዲጻፍ ያዘዘ እርሱ ራሱ ኢየሱስ ነውና።

በዝሙት የኖረች አንዲት ሴት ነበረች። ማርያም ዘናይን/ኀጥእት ትባላለች።
የጌታችን ክርስቶስን የእጁን ተአምራት አላየችም። የቃሉን ትምህርት አልሰማችም። እንደወትሮዋ በመስታወት ፊት ቆማ ስትኳኳል፥ ውበቷን የሚያጠፋ ሞት ትዝ አላት።
ይቅርታና ምሕረት ለማግኘት ወደ መሐሪው ጌታ ፈጥና ኼደች። በስምዖን ፈሪሳዊ ቤት  አገኘችው።

"የረከሰ ነገርን የነካችኹ እጆቼ ሆይ፥
የጌታ ክርስቶስን እግር ትዳስሱ ዘንድ ታደላችኹ።" እያለች የጌታዋን እግር በዕንባ አጠበች።
ጌታችን ክርስቶስም "እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ አላት"

ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ ሲል አዘዛቸው።
“እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።”
ማቴዎስ 26፥13
በሰላም ሂጂ ያላት ጌታ፥ ዛሬ የካቲት ስድስት ወደ ጻድቃን ከተማ ወሰዳት።

ይኽች ማርያም፥ የአልዐዛር እኅት ማርያም ወይም ማርያም መግደላዊት አይደለችም።
👍2
ቁጣ ድል አይንሣህ

ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት። ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው፤ በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው፡፡ ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው፣ ከአንተም በተለየ ጊዜ የእሱን ነገር ተናገር፡፡ ከበጎ ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት፡፡

በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ሥራ ትስበዋለህ ታነቃቀዋለህ፡፡ አንተ ባመሰገንከው ምስጋና፣ አንተ ባከበርከው ክብር የተነሣ ያፍር ዘንድ እንዳመሰገንከው ያልሆነ እንደሆነ ያፍራል፤ እንዲህ የሆነ እንደሆነ ዘርአ ትሩፋትን ትዘራበታለህ፡፡

ነፍስህ ከለመደችው ባልንጀራህን ከማክበር የተነሣ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ ይቀርጻል፡፡ ፍጹም ትሕትናን ገንዘብ ታደርጋለህ ሳትጥር ብዙ ሥራ ትሠራልህ፡፡ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ አይደለም ነውር ያለበትም ቢሆን አክብረው እንጂ፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ አንተ ካከበርከው ክብር የተነሣ አፍሮ ካንተ ድኅነትን ያገኛል።

ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት፤ ጥበብም የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘን መራራት ናት። አንዱንስ እንኳን አትቈጣ፣ ተቈጥተህ አታሳዝነው፣ ቍጣ ድል አይንሳህ፡፡ ስለ ሃይማኖትም ቢሆን፣ ሥራው ክፉ ስለሆነም ቢሆን ሰው እንዳታማ ተጠበቅ እንጂ አትፍረድበት፡፡ በልዕልና ፊት አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ ዳኛ ክርስቶስ አለንና፡፡ ወደ በጎ ሥራም ልትመልሰውም ብትወድ እዘንለት፤ እያለቀስህ የለዘበ ነገር ንገረው፤ በቍጣ አትናደድበት፤ ጸብ ያለህ ይመስለዋል ፍቅር ውስጣዊ ቍጣን አይሻምና።

[ማር ይስሀቅ]
🥰31👍1
ተግሣጽ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ተከታታይ ትምህርት


                ተግሣጽ ፩

እሳተ ገሀነም ፈጽማ ታቃጥላለች። እሳት ስትሆን ብርሃን ግን የላትም። ከታላላቁም
ከጥቃቅኑም ኃጢአት ፈጽመን ልንርቅ ይገባናል። ኃጢአት ከመንግሥተ ሰማያት ይለያል።
ሕጉን ማፍረስ እግዚአብሔርን መስደብ ነው። ፍጡርን መንቀፍ ፈጣሪን መንቀፍ ነው።
ወንድሙን የሚያከብር እግዚአብሔርን ያከብራል። አንደበታችንን በበጎ ምክር ከክፉ ነገር
እንከልክል። ወንሚጥ ቃለ ፅርፈት ኀበ ሠናይ ቃል። ስድቡን ወደበጎ ነገር እንመልስ። ክብር ምስጋና ይግባውና ፈጣሪ ጌታ አንደበታችንን ልንሳደብበትና ሐሰት ልንናገርበት አልፈጠረልንም። እርሱን እናመሰግንበት ዘንድ ፈጠረልን እንጂ። የሚሰሙንን ሰዎች እውነት ነገር ተናግረን ደስ እናሰኛቸው ዘንድና ወደበጎ ፍቅር እንመልሳቸው ዘንድ ነው እንጂ። እገሌ ክፉ ነው ብትል ሐሜተኛ ተሳዳቢ ትባላለህ እንጂ የምትጠቀመው ነገር የለም። ቅንአት ከእግዚአብሔር ይለያል። ተሳዳቢ የሚጎዳ ራሱን ነው። የተሰደበ ሰው ግን ስድቡን ቢታገሥ
በሰው ሁሉ ዘንድ ፍቅርን መወደድን ያገኛል። ለሌሎች በጎ ሥራን የሚሠራ ሰው አስቀድሞ የሚጠቀም ራሱ ነው። መንግሥተ ሰማያት እጅግ ያማረች ናት። የገሀነምን የመከራውን ጽናት እንረዳ ዘንድ ይገባናል። ይኸውም ለዘለዓለም በእሳት ሲቃጠሉ መኖር ነው። በጨለማ መኖር ነው። ረዳት የሌለበት ጩኸት ሳያቋርጡ ጥርስ ሲያፋጩ መኖር ነው። ከሌባ ከወንበዴ ከነፍሰ ገዳይ ጋር በባሕረ እሳት ሰጥሞ መኖር ነው። እንዲህም ሆኖ መተያየት የለም። ከእኛ ጋራ እንደኛ ብዙ ሰዎች ሳሉ ብቻችንን ያለን ይመስለናል። ዘወትር ይህንን በልቡናችን ማሰብ ይገባናል። በወዲያኛው ዓለም ባለሟልነትን እናገኝ ዘንድ እንመጽውት። ቅን ኅሊናን ገንዘብ እናድርግ።

ይቀጥላል...
1👍1
ተግሣጽ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ተከታታይ ትምህርት


                    ተግሣጽ ፪

እግዚአብሔርን የምትወዱ እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተ እንዳንታበይ መሆን ይገባናል።
መከራን ልንታገሥ ይገባናል። ቀድመው የሞቱትን ሰዎች አስባቸው። ምንም ሳንይዝ ወደዚህ
ዓለም እንደመጣን ምንም ሳንይዝ ከዚህ ዓለም እንለያለን። አንተ ሰው የዚህን ዓለም ገንዘብ
በማግኘት ደስ አይበልህ። የዚህን ዓለም ገንዘብ ወንበዴዎች ቀምተው፣ ሌቦች ሰርቀው፣ ገዳዮች
ገድለው፣ ክፉ ሠሪዎች ክፉ ሠርተው፣ ዘማውያን ያገኙታል። የሚገባ ቁጣ አለ። ይኸውም ሕግ
ቢፈርስ ሕፃናት ከመማር ቢሰንፉ የተማሩትን ቢገድፉ ነው። ስለመንግሥተ ሰማያት ብለን
የምንቀናው ቅንአትም ተገቢ ቅንአት ነው። መመካት አይገባም እነጂ የሚገባ ከሆነ በብዕል
ያይደለ በድኽነት እንመካ። ድኽነታችንን አይተው በሚነቅፉን በሚንቁን ሰዎች አንዘን። ሀብትም
ድኅነትም በራሳቸው ክፉዎች አይደሉም። ካወቁባቸው ሁለቱም የጽድቅ ምክንያት ይሆናሉ።
ድኽነት ኩራትንና ትዕቢትን ያርቃል።
ሁለት ወንድማማቾች በአንድነት ይኖሩ ነበር። ከፍቅራቸው ጽናት የተነሣ አንዱ ለተራድኦ ወደ
ውጭ ወጥቶ ጥቂት የቆየ እንደሆነ ወንድሜን ምን አግኝቶት ይሆን እያለ ሲጨነቅ ይቆየው
ነበረ። ከዕለታት በአንድ ቀን በዓት ለመሥራት መሬት ሲቆፍሩ ድስት ሙሉ ወርቅ ተቀብሮ
አገኙ። በዚህ ምክንያት ሞታቸውን ይፈላለጉ ጀመር። አንዱ መድኃኒት አጠጣኝ ብዬ በጥብጦ
ሲያቀርብልኝ በሰይፍ አንገቱን እለዋለሁ ብሎ አሰበ። ሁለተኛውም መርዝ አጠጥቼ ገድዬ

ወርቁን ለብቻዬ አስቀራለሁ ብሎ አሰበ። ከዚህ በኋላ መድኃኒት አጠጣኝ አለው። መርዝ
ጨምሮ በጥብጦ አቀረበለት። እርሱም ያንን በሰይፍ አንገቱን ብሎ ገድሎ መርዙን ጠጥቶ
ሞተ። ሁለቱም ሙተው ወርቅ ብቻውን ቀርቷል። ገንዘብ ብናጣ በማጣታችን አንዘን። ብናጣም
ብናገኝም እግዚአብሔርን እናመስግነው እንጂ። ብናጣ አያውቁበትም እንጂ ብሎ ነው ብለን፣
ብናገኝ ሰጥተው መጽውተው ይጠቀሙበት እንጂ ብሎ ነው ብለን እናመስግነው።

ይቀጥላል...
👍31
"ፍቅርና ፍርሃት"

በሰው መካከል ያለ ቀረቤታ ሲጠነክርና ፍቅሩ ያደገ ሲመስል መከባበርና ሐፍረት እየቀነሰ ሊመጣ ይችላል። "አሁንማ መፈራራት አያስፈልግም"፣ "እንደ ስሜትህ መሆን ትችላለህ?" የሚሉ ቃላቶችን በጊዜው ለጠበቀው ወዳጅነታቸው መመሪያ ጥቅስ ሊያደርጉትም ይችላሉ።  ነገር ግን ጉዳዩ ለከቱን ያለፈ ቀን ይዞባቸው የሚመጣው የጠብ ጦስ እንዲህ በቀላሉ የሚመለስ አይደለም። ሁል ጊዜ በጸና ፍቅር ውስጥም ቢሆን መኖር ያለበት "ንጹሕ ፍርሃት እና ሐፍረት" አለ። እርሱ ደግሞ መከባበርን ያመጣል።

የእግዚአብሔርን ፍቅር በሚገባ ላልቀመሰ ሰው ከገጸ ምሕረቱ ይልቅ ገጸ መዓቱ ይጎላበታል። ስለዚህ ትእዛዛቱን ለመፈጸም የመጀመሪያ ምክንያት የሚሆነው "በሥጋዬ እንዳይቀስፈኝ፣ በነፍሴ እንዳያጠፋኝ" የሚለው ፍራቻው ነው። እንዲህ ያለውን ፍርሃት መጽሐፈ መነኰሳት "ፍርሃተ አግብርት"/"የባሮች ፍርሐት" ብሎ ይጠራዋል። ይህም እንደ እኛ ባሉ ጀማሪ ክርስቲያኖች ኅሊና ውስጥ የሚሯሯጥ ፍርሃት ነው። ፍቅሩን ለሚያስብ የበረታ ክርስቲያን ግን ባላደርግ እቀጣለሁ ብሎ ሳይሆን፣ ፈጣሪውን ስለሚወድ ብቻ ትእዛዙን ይፈጽማል።(ዮሐ 14)

ይሁን እንጂ ከፍቅር ላይ የደረሱም ቅዱሳን ቢሆኑ እግዚአብሔርን መፍራታቸው የማይቀር ነገር ነው። ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር መልሰው እርሱን እንዲዳፈሩት ምክንያት አይሆናቸውም። የቅዱሳኑ ፍርሃት ግን "ምን ያደርገኝ ይሆን" የሚል የባርያ ፍርሃት ሳይሆን፣ "እንዳያዝንብኝ፣ እንዳይከፋብኝ" ከሚለው ልጃዊ ፍቅር የመነጨ ነው።

በተጨማሪም የመለኰቱ ርቀት፣ የባሕርዪው ምልዓት በልብ ታስቦ የማይደረስበት መሆኑን ዐውቀው፣ በልባቸው ጉልበት እየራዱ አይመረመሬነቱን በአንክሮ ማድነቃቸው ነው "እግዚአብሔርን መፍራታቸው"።

ሐዋርያው "ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል" ይለናል።(1ኛ ዮሐ 4፥18) ምን ማለት ነው? ስለ የትኛው ፍርሃት እየተናገረ ይሆን? ቅዱስ ዮሐንስ የሚናገረው አንደኛ "ፍርሐተ አግብርት" ስለተባለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ እሳት ስለቱን እንዲሁም በሥጋ የሚመጣውን ስቃይ ተሰቅቆ እርሱን ከመካድ ስለሚያደርሰው "ጎጂ ፍርሃት" ነው።

በቀረው ግን ፍጹም ፍቅር ሥጋዊ ፍርሃትን እንጂ፣ እግዚአብሔርን መፍራትን ከውስጣችን አውጥቶ አይጥልም!
4👍1
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ
ሮሜ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
¹⁸ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
¹⁹ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
²⁰ ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
²¹ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
👍5🙏3
መዝሙር 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
⁸ የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
⁹ የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።
¹⁰ ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።
¹¹ ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
¹² ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
¹³ የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
¹⁴ አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።
2🙏2
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
የሰው ልጅ ሐይማኖቱን በመጽሐፍ እየጻፈ ክርታስ እየከረተሰ ሊኖር አልተፈጠረም፤ እርሱ እራሱ መጽሐፍ ነበረ፤ ግን እራሱን አዋርዶ እምነቱን ከወረቀት እራሱን ግን ለሰይጣን አጋልጦ የዲያብሎስ መጫወቻ ሆነ።

"ቅዱስ አባታችን ሄኖክ"

“ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።”
  — ያዕቆብ 1፥22

ቃሉን የምናነብ እና የምንሰማ ብቻ ከመሆን ይጠብቀን፤ የምናደርግ፤ የምንጠብቀውም ጭምር ያድርግልን እንጂ።
2025/07/08 18:22:51
Back to Top
HTML Embed Code: