ሰሞነኛ ሰው እና ልብ የለሾች ከመሆን ይሰውረን
🥰2
📖#ራእየ_ኒፎን📖
#በምድራዊ አሠራር አንድ ንጉሥ ለእርሱ ጠንክረው ስለተዋጉ የሚያከብራቸው አሉ፤ ብዙ ስጦታን አምጥተው ስላከበሩት የሚያከብራቸውም ይኖራሉ፡፡ ሌሎችን ደግሞ ምንም ባያደርጉለትም በፊቱ ሞገስ የሚያ ይኖራሉ፡፡ በእግዚአብሔርም ዘንድ እንዲሁ ነው፡፡ ስለ ተጋድሏቸው የሚያከብራቸው አሉ፡፡ አገልግሎታቸው የሚያከብራቸው አሉ፡፡ ከልባቸው ተፀፀተው ንስሐ ስለመግባታቸው የሚያከብራቸው ይኖራሉ፡፡ ከርኅራኄውና ከቸርነቱ ብዛት የቅዱሳኑን ጸሎትና ምልጃ ተቀብሎ የሚያከብራቸውም አሉ፡፡ በሌላም መልኩ በዚህ ነገር በሕይወታቸው የደረሰባቸውን ነገር ሁሉ ሳያማርሩ በምስጋና ስለ መቀበላቸው በመንግሥቱ መጽናናትን የሚያገኙ ይኖራሉ፡፡”
....የአገልግሎት ሹመት ፍቅረ እግዚአበሔር አሳድዳ ለያዘችው ሲሆን ደግ ነው፤ ፍሬም ይገኝበታል፡፡ ደጅ ጠንተው መማለጃ ሰጥተው የያዙት ሹመት ግን በተራው ሌላውን ደጅ ጥኑኝ መማለጃ አምጡልኝ ከሚል ውጪ መንፈሳዊ ሥራ ለመሥራት አያበቃም፡፡”
#ወንድምህ ከቆመበት ትቢያ ሥር ባለው ጥልቅ ውስጥ ራስህን በትሕትና ማቆየት ካልቻልክ፤ በኅሊናህ ራስህን በእግሩ ላይ ጣል፡፡

" ወንጌልን ለመጻፍ ለበረታው ክንድህና የአርያምን ኃይል ለተቀበለው ክርንህ ሰላም እላለው
ዮሐንስ ሆይ ለከንቱው የዓለም እንጀራ ስሽቀዳደም መንፈሳዊውን መብል አላገኘሁምና የተሰውረውን መብልና የብርሃን መጽሐፍ ስጠኝ "
መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ

❤1
የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች:
✟ከሞት ባሻገር✟
"በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልብ ወለድ "
ዕለቱ እጅግ ብሩሕ ዕለት ነበር፡፡ ለእኔ ደግሞ ታላቅ ዕለት! ለዛሬዋ ዕለት የደረስሁት ለብዙ ሰዎች ትምህርት ሊሆን በሚችል ውጣ ውረድ ውስጥ አልፌ ነው፡፡ የእኔ ሕይወት ለሌሎች ትምህርት ይሠጣል የምለው ‹‹በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን ሆኖ የሚያበራ›› ሕይወት ኖሮኝ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ምሕረት ከከበበው ግን የእኔ ዓይነቱ ኃጢአተኛም ታሪክ ለሌሎች ምሳሌ ይሆናል፡፡
አሁን ያለሁት በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ነው፡፡ ይህ ዕለት ከቁም ሞት ተነሥቼ በሕይወት መኖር የምጀምርበት ቀን ነው፡፡ በየደቂቃው ስለ አምላኬ ባሰብሁ ቁጥር የሚታየኝ ወሰን የሌለው ቸርነቱና ምሕረቱ ነው፡፡ አሁን አባ በእጃቸው ጀርባዬን መታ አድርገውኝ በአጠገቤ አለፉ፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ሊገቡ ነው መሰለኝ ቀጥታ ሔዱ፡፡
አሁን ሦስቴ ሰገዱ.... ቆመው መጸለይ ቀጠሉአባ ኖላዊ የቤተሰባችን የንስሓ አባት ናቸው፡፡ ጠይም ፣ እንደ ቁመታቸው ረዥም ጢም ያላቸው ፣ ፊታቸው አንዳች የሚያስፈራ ግርማ ያለው ፣ ፊታቸው ላይ ስሜታቸው የማይነበብ በመንፈሳዊ አቋማቸው የማያወላውሉ መነኩሴ ናቸው፡፡
ወደ ቤታችን መምጣት ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የንስሓ አባትነታቸው ለወላጆቼ እንጂ ለእኔ አልነበረም፡፡ በቤተሰባችን በጣም የተከበሩና የተፈሩ ናቸው፡፡ የቤተሰቦቼ ሀብት የማይደንቃቸው ፣ ስኅተት ካዩ የማያልፉ ስለነበሩ ሁላችንም እንፈራቸዋለን፡፡አልወዳቸውም ነበር ፤ እሳቸው ገና ከበር ሲገቡ ድምጻቸውን ስሰማ በረዥሙ ‹‹ኤ...ጭ›› እልና ዘልዬ ወደ መኝታ ክፍሌ እገባ ነበር፡፡ እሳቸው እያሉ ሙዚቃ ማዳመጥ ... ፊልም መመልከት ስለማይመቸኝ ገብቼ እመሽጋለሁ፡፡ ኳስ እያየሁ የመጡ ዕለትማ ለጥቂት ጎል እንደሳተ ተጫዋች ዘልዬ ልፈርጥ ምንም አይቀረኝ፡፡
‹ኤ.....ጭ› እላለሁ..ሲያናግሩኝ ብስጭት ይቀድመኝ ነበር ... በክርስትና ስሜ ሲጠሩኝ እበሳጫለሁ ... እንዳልሰማ እሆናለሁ ... እርግጥ ነው ‹‹የክርስትና ስም ጌታ በጎቼን በየስማቸው እጠራቸዋለሁ ያለውን በማሰብ የሚሠጥ ነው... ድሮ በግዝረት ጊዜ ስም ይወጣ እንደነበር ዛሬ በጥምቀት ጊዜ ስም ይወጣል...›› ብለው ሲያስተምሩ ሰምቼአለሁ... ግን በቃ እነጫነጫለሁ....ከሁሉ
የሚያበሳጨኝ ጥያቄ ሲጠይቁኝ ነው ....‹‹ኃይለ መስቀል.... ትምህርት እንዴት ይዞሃል? .... መቼ ነው የምትመረቀው?›› የሁልጊዜ ጥያቄያቸው ናት፡፡ እየተንጠራራሁ እመልሳለሁ...ከዚያ ያቺን የሁልጊዜ ምክራቸውን ይደግሙልኛል....
‹‹አይዞህ በርታ እግዚአብሔር የራቀን የሚያቀርብ አምላክ ነው... እሱ ይርዳህ.... አንተም ታዲያ ከደጁ አትቅር .... ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትስ ተድላን የቀመሰ ማን ነው? ይላል ጠቢቡ.... ባለቤቱም ቢሆን እስመ ዘእንበሌየሰ አልቦ ዘትክሉ ገቢረ ይላል ... ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም ሲል ነው.... ያለሱ ምንም ማድረግ አይቻልም.... ምንም...›› ይላሉ እጃቸውን አቧራ እንደሚያራግፍ ሰው አፈራርቀው እያማቱ....ደሜ ይፈላል.... አንድም ቀን ስለ እኔ ጉብዝና እንደሌላ ሰው አያዳንቁም .... ‹‹እግዚአብሔር የሌለበት እውቀት የትም አያደርስም...›› ሲሉኝ ነው የኖሩት... ብቻ አንዳች የበታችነት እንዲሰማኝ የሚያደርጉኝ ስለሆኑ አልወዳቸውም ነበር...
አንዳንድ ቀን የፍልስፍና ጥያቄ ጠይቄ ልፈታተናቸው ሞክሬም ነበር... እንደ ዋዛ የሚሰጡኝ መልስ ኩምሽሽ እያደረገኝ. ተውኩት....በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቄ ወደ ሥራው ዓለም ከተቀላቀልሁ በኋላ አባን ማናገር የበለጠ ሞት ሆኖ ይታየኝ ነበር... በምርቃቴ ቀን መጥተው እንኳን ያቺን የማትቀረዋን ‹‹ያለእርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትስ ተድላን የቀመሰ ማን ነው?...›› የምትል ቃል ነግረውኝ ነው
የሔዱት ... እሳቸው ሲናገሩ በሆዴ አብሬያቸው እያልኩ እዘብት ነበር.... ወይ ትዕቢትይህ ትዕቢት ግን መቋጫ አላጣም.... እሳቸውንም ... የሸሸሁትን ፈጣሪዬንም የማገኝበት አጋጣሚ ተፈጠረ...ከጥቂት ወራት በኋላ በተቀጠርሁበት ድርጅት የውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል ተሠጠኝ... እንኳን ምክንያት አግኝቶ ቀርቶ ወትሮውንም ለኃጢአት የፈጠነው እግሬ ለጭፈራና ለስካርና ለፈንጠዝያ ተነሣ.... በሰው ተከብቤ ሳብድ ሰነበትኩ...ደስታዬ ግን ብዙም አልቆየም ... ለጉዞው አስፈላጊ የነበረውን የጤና ምርመራ ሳደርግ... የደም ካንሰር እንዳለብኝ ተነገረኝ....
አዕምሮዬ ሊሸከመው የማይችለው ድንጋጤ ... ራሴን ስቼ ወደቅኩኝ.... ሐኪሙ በቀሪ ጊዜዬ በደስታ እንዳሳልፍ ... እንዳልጨነቅ ... ብዙ ምክር ሠጠኝ... ለጊዜው ቢያረጋጋኝም ምንም አልጠቀመኝም....እንዲያውም የበለጠ ተስፋ ቆረጥሁ....በደስታ ሲደበላለቅ የከረመው ቤታችን በአንድ ቀን መቃብር መሰለ... ወላጆቼና እኅቶቼ ልባቸው ተሰበረ... ራሴን ማጥፋት ተመኘሁ... ግን ደግሞ ዘገነነኝ....በየሔድኩበት የሚያውቁኝ ሁሉ ከንፈር እየመጠጡ አቆሰሉኝ.... ሳልሞት የሚገድለኝ ሰው በዛብኝ... ፈጽሞ ልረጋጋ አልቻልኩም...
ከሳምንት በኋላ የጉዞዬን መሰናከል ለማሳወቅ ወደ መሥሪያ ቤቴ ሔድኩኝ ... ወሬው ግን ቀድሞኝ ደርሷል... በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ... የእኔ የትምህርት ዕድል ለሌላ ሰው መሠጠቱ ተለጥፎ ጠበቀኝ...
አንድ ቀን ጠዋት አርፍጄ ተኝቼ ሳለ እናቴ ወደ መኝታ ክፍሌ መጣች...‹‹አንተ እንቅልፋም... በል ተነሥ ....አባ መጥተዋል.... ›› አለችኝ ...እማዬና አባዬ ኀዘናቸውን ዋጥ አድርገው በእኔ ፊት ደስተኛ ለመሆን ይጥራሉ...
ላለማስከፋት የሚያደርጉት ጥረት ግን የበለጠ ያስከፋኝ ጀመር... እንደ ልጅ አይቆጡኝም ... ብቻዬን ስሆን አሥር ጊዜ መጥተው ያዩኛል... ብቻ መታመሜን ሲያስታውሱኝ ይውላሉ... ጓደኞቼም እንዲሁ ናቸው... እንደ ጓደኛ የሚተርበኝ... የሚቀልድብኝ የለም... ያለ ጠባያቸው
በምለው ሁሉ መስማማት ... ያልኩትን ሁሉ እሺ ማለት ሆኗል ሥራቸው... አባ ኖላዊ ጠበል እየረጩ ወደ መኝታዬ መጡ... እሳቸው ብቻ አልተለወጡም... ፊታቸው ላይ የሚነበበው ያው የድሮው ገጽታቸው ነው ... ስሜት አልባና ኮስታራ ገጽታ... ‹‹... ኃይለ መስቀል.... እንደምን አለህ? ደህና ነህ ወይ?....›› አሉኝ እንደ ወትሮው...መታመሜን እያወቁ ደህና ነህ ወይ ለምን ይሉኛል?... ብዬ በስጨት አልኩና ... ‹‹አለሁ አባ›› አልኳቸው፡፡‹‹መኖርህንማ እያየሁ ነው ፤ እግዚአብሔር ይመስገን በል እንጂ...›› አሉኝ
በብስጭት ሳቅ ብዬ ‹‹... እግዚአብሔር ይመስገን በል ይሉኛል? ... ያለሁበትን ሁኔታ እያወቁ እንዴት እግዚአብሔርን እንዳመሰግን ይጠብቃሉ?›› አልኩኝ አባ ትንሽ ፈገግ አሉ ‹‹ለነገሩ ...እንኳን በችግር ጊዜ... በደስታስ ጊዜ መች አመስግነህ ታውቃለህ?...›› አሉ እየተከዙ‹‹ልጄ ... እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ... ከአንተው አፍ ልስማው...›› አሉኝ በእርጋታእንኳንስ ንገረኝ ተብዬ የሚሰማኝ ምን እንደሆነ የሚጠይቀኝ ሰው ካጣሁ ሰንብቼአለሁ... ስለዚህ ደስ አለኝ ... ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው የሆነውን ሁሉ ነገርኳቸው፡፡ ቅልል ሲለኝ ተሰማኝ .. አባበጥሞናአዳመጡኝ... ልሰማቸው የማልፈልጋቸው አባ ሰሚ ባጣሁበት ጊዜ አዳማጬ ሆኑ...ጥቂት ዝም ካሉ በኋላ መናገር ጀመሩ

Telegram
የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
◉ ይህ ገፅ የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ነባር እና አዳዲስ መጣጥፎች የምናጋራበት የVIDEO ትምህርቶቹን የምንለቅበት የቴሌግራም ገፃችን ነው። ነገር ግን እንድታቁልን የምንፈልገው ገፁ በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ሚመራ ገፅ አደለም።
❤2
‹‹አየህ ልጄ የሰው ልጅ ድክመቱ ሞቱን መዘንጋቱ ነው፡፡ በእንግድነት የምንኖርባትንይህቺን ምድር እንደ ዘላለም ቤታችን አድርገን ዕቅዳችንን ፣ ተስፋችንን
፣ ፍጻሜያችንን በእርስዋ ላይ አድርገን ስለምናስብ መሞት እንፈራለን፡፡ ይህ ሕመም በደምህ ላይ መኖሩን ስትሰማ የተሠጡህ ምክሮች ሁሉ ሊጽናኑህ ያልቻሉትም ከዚህች ምድር ያለፈ ተስፋን ስላልያዙ ነው፡፡አየህ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ ለበጎ የሚያደርግ አምላክ ነው፡፡ ሰውን ለማሰቃየት አይሻም፡፡
ቢቀጣን እንኳን የሚቀጣን ለእኛ ሲል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል›› ያለው ለዚህ አይደል እንዴ? እስካሁን የምትኖረው በኃጢአት ውስጥ ነበር፡፡ ስለ እግዚአብሔር መስማትና ማሰብ እንኳን አትፈልግም ነበር፡፡ ምድራዊ ጉዞህ ማቋረጫ የሌለው ፣ እውቀትህም ሁን ድል የሚነሣ ይመስልህ ነበር፡፡ አሁን ግን በምድራዊ ሩጫህ የማታመልጠው ፣ በእውቀትህም ድል የማትነሣው ሞት መኖሩን አወቅህ፡፡ አስተዋይ ከሆንህ ደግሞ ከዚህ ሞት በላይ የሆነ ሌላ ኃይል እንዳለም ትማርበታለህ፡፡ ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትስ ተድላን የቀመሰ ማን ነው? አለ ጠቢቡ፡፡ ልጄ የረሳኸው
እግዚአብሔር አልረሳህም፡፡ ወደ እርሱ እየሳበህ ነው፡፡›› ሳላስበው ዕንባዬ ወረደ ... ሲናገሩኝ የቀለድሁበት የእግዚአብሔር ቃል ለክፉ ቀን የሕመሜ ማስታገሻ መሀኑን መች አውቅ ነበር?ዞር ብለው አየት አደረጉኝና መልሰው ወደ ሩቅ እንደሚያይ ሰው ትክ ብለው በሌላ አቅጣጫ እያዩ መናገራቸውን ቀጠሉ‹‹ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው? አንተ በዚህ በሽታ ብትያዝም ባትያዝም መሞትህ የማይቀር ነገር ነው፡፡ አሁን ‹ሊሞት ነው› ብለው ለአንተ ከንፈር ከሚመጡልህ ሰዎች መካከል ከአንተ ቀድመው
የሚሞቱ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ አንተ ከእነርሱ የምትለየው የምትሞት መሆንህን የምታስታውስበትን ዕድል ፈጣሪ ሠጥቶሃል፡፡›› አሉ በእርጋታ፡፡ የሚናገሩት ሁሉ በቁስሌ ላይ ሲያርፍ ይሰማኝ ጀመር፡፡‹‹ኃይለ መስቀል የሰው ልጅ ሁሉ ዓይኑ መታወሩ አይገርምህም?›› አሉኝ ሳቅ እያሉ፡፡ ግራገባኝ
‹‹የሰው ልጅ አስተሳሰቡ በዓይኑ ከሚታየው ነገር አላልፍ ብሎ ዓይኑ ታውሯል፡፡ እምነት አለኝ የሚለው ክርስቲያን እንኳን ከሞት ባሻገር ስላለው ሕይወት ማሰብ ተስኖታል፡፡
የሰው ልጅ ሕይወት ከሞት በኋላ ነው፡፡ የምድር ላይ ቆይታችን ለሰማያዊው ኑሮ የምንዘጋጀበት ጊዜያዊ የድንኳን ኑሮ ነው፡፡ ሰው ግን ከዚህች ጊዜያዊ ምድር የሚለይበትን ሞት ይዘነጋል፡፡ ‹‹...ሞቱን ከመርሳቱ የተነሣ ቀብር ለመቅበር መቃብር ሥፍራ ላይ ቆሞ እንኳን እሱ እንደሚሞት ከማሰብ ይልቅ የረዥም ጊዜ ዕቅድ ያቅዳል፡፡ ብዙ ሰው በንግግሩ መካከል ‹ሺህ ዓመት አይኖር› እያለ ይፎክራል፡፡
በእርግጥ ለመቶ ዓመትስ መች ይኖራል? አይ ሰው ከንቱ››ራሳቸውን እየነቀነቁ የምጸት ሳቅ ሳቁ‹‹ለማንኛውም አንተ ዕድለኛ ነህ ፤ ሰው ሁሉ ለረሳው ሰማያዊ ጉዞ እንድትዘጋጅ እግዚአብሔር ቀስቅሶሃል፡፡››አባ ኖላዊ በዚህ አላበቁም ፤ ስለ ሰማያዊው ሕይወት በሰፊው አስተማሩኝ ... ከመኖሬ ይልቅ መሞቴን እንድናፍቅ አደረጉኝ... ከሥጋዊ ፈውስ ይልቅ የነፍስ ፈውስ እንደሚበልጥ አሳዩኝ... ያላየነውን የምናይባት ... ያልሰማነው የምንሰማባት ..የእግዚአብሔር መንግሥት በእውነት ሞትን ታስረሳለች...ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ጀመርሁ... የአባ ኖላዊ ምክርም አዲስ እንዳልሆነና ቤተ ክርስቲያን በየዕለቱ ስታስተምረው የምትውለው እንደሆነ ተረዳሁ፡፡
ከሕይወታችን ጋር አላገናዝበው ብለን ነው እንጂ ቤተ ክርስቲያን ስለሁሉም ነገር ሳትነግረን አልቀረችም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ‹ሕይወት› ብላ ስትናገር እኛ የምናስበው ስለ ምድራዊ ኑሮአችን ብቻ ነው፡፡ለውጪ ሀገር ጉዞ በምዘጋጅበት ወቅት ‹‹መንግሥተ ሰማያት ከምትወርስና ወደ ውጪ ሀገር ከምትሔድ›› ብላል ኖሮ የትኛውን እንደምመርጥ ሳስብ በራሴና በብዙዎቻችን ደካማአስተሳሰብ አፈርሁ :::
አንድ ጠዋት ቁጭ ብዬ መዝሙር ሳዳምጥ አባ ኖላዊ ወደ ቤት መጡ ፤ መስቀል
አሳለሙኝና ‹‹ምነው ብቻህን ቁጭ አልህሳ ሰው የለም እንዴ?›› ብለው ጠየቁኝ፡፡
‹‹መዝሙር እየሰማሁ ስለሆነ ብቸኝነቴን አልጠላሁትም አባ››
‹‹ዘፈን ከመስማት አውጥቶ ጆሮህን ለምስጋናው አቀናው አይደል! ተመስገን!!›› አሉ እጃቸውን ዘርግተው ወደላይ እያዩየምሰማው መዝሙር አልቆ ሌላ መዝሙር ጀመረ
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ቀጠለ ...
ዓለም አታላይ ነሽ
ዓለም ወረተኛ
ያንቺስ ዝምድና ይቅርብኛ
ዓለም ወረተኛ
ከአባ ጋር ተያይተን ሳቅን ፤ የትምህርት ዕድል ሲመጣልኝ አብረውኝ ሲፈነጥዙ
የከረሙት ጓደኞቼ በሙሉ መታመሜን ከሰሙ በኋላ ቀስ በቀስ እግራቸውን አሳጥረዋል፡፡
‹‹አባ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት›› አልኳቸው ፤ ቀና ብለው ተመለከቱኝ
‹‹እግዚአብሔር ግን እኔን ይቅር ይለኛል?››
‹‹ለምን ይቅር አይልህም?››
‹‹አባ ስለማያውቁኝ ነው፡፡ እኔ ሕይወቴ በጣም የተበላሸ ቆሻሻ ሰው ነኝ... ፈጣሪዬን ብዙ
አስቀይሜዋለሁ .. ዘብቼበታለሁ... ››
አቋረጡኝ ‹‹እስቲ እሱን አውልቅና ስጠኝ›› አሉኝ
አንገቴ ላይ ያለውን ወርቅ እያሳዩ... እማዬ ለምርቃቴ የሰጠችኝ ባለ ብዙ ግራም ሰንሰለት
የሚያክል ወርቅ ነው...አባ በእጃቸው ላይ ይዘው ተመለከቱት...
‹‹ኃይለ መስቀል ይኼን ወርቅ በመንገድ ላይ ድንገት ተፈትቶ ከጭቃ ውስጥ ቢወድቅብህ ...
ምን ታደርጋለህ?››‹‹አነሣዋለኋ አባ..››
‹‹ጭቃ ውስጥ ገብቶ ቢጨማለቅስ...?››
‹‹አነሣዋለሁ!›› ፈገግ አልኩ
‹‹የወደቀው ከመጸዳጃ ቤት የወጣ ቆሻሻ ውስጥ ቢሆንስ...?››
ከልቤ ሳቅኩኝ ... ‹‹አነሣዋለሁ አባ ... እየቀፈፈኝም ቢሆን አነሣዋለሁ›› አባ የሚያስቅ ነገር
እንኳን እየተናገሩ አለመሳቃቸው ይገርመኛል....
‹‹ለምን ልጄ ... የሚሸት ነገር ውስጥ ገብቶ እንዴት ታወጣዋለህ?... በእግር እንኳን ለመርገጥ
የምትጠየፈውን የመጸዳጃ ቤት ቆሻሻ ትነካለህ...››
‹‹እንዴ አባ ... ገንዘብ እኮ ነው የወጣበት... ግራሙን አያዩትም ... ወርቅ ደግሞ ተወድዷል እኮ ...›› ሳቅ እያልኩኝ
‹‹አንተ እኮ ለእግዚአብሔር ከወርቅ በላይ ነህ... ይህ ወርቅ የተገዛው በገንዘብ ነው...
እግዚአብሔር ግን አንተን የገዛህ በደሙ ነው... ምንም አይነት የኃጢአት ቆሻሻ ውስጥ
ብትዘፈቅ እጁን ሰድዶ ያወጣሃል... መልሶ ያጥብሃል... ወደ ቀደመ ቦታህም ወልውሎ
ይመልስሃል›› ... ትኩስ ዕንባ በፊቴ ላይ ወረደ ...
አሁን ያለሁት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው... ዛሬ የክርስቶስን ሥጋና ደም
የምቀበልባት ... ከኃጢአት ቁስል የምፈወስባት ዕለት ናት...
ቅዳሴው ተጀምሯል በጥሞና እየተከታተልሁ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቃል በልቤ ሲያርፍ ቁስሌንም ሲሽር ይሰማኝ ነበር
ዲያቆኑ ለጸሎት ተነሡ! እያለ ያውጃል፡፡ የአዋጁ ጥልቅ መልእክት ዘልቆ ተሰማኝ፡፡
በዚህ ዘመን ለሰው ልጅ ሊቀርብ የሚችለው አዋጅ ‹‹ለጸሎት ተነሡ ... በእግዚአብሔር ፊት ቁሙ ... ከኃጢአት እንቅልፍ ተነሥታችሁ ለይቅርታው ተዘጋጁ›› የሚል ነው፡፡ ሕዝቡ
‹‹አቤቱ ይቅር በለን›› አለ ... አዎ ይቅር በለን ከማለት ውጪ ምን ጸሎት አለ? ...

ቅዳሴው ተገባደደ ... የጌታችንን ሥጋና ደም ተቀበልን.. እኔ በክርስቶስ ክርስቶስም በእኔ ሊኖር በቃሁኝ...
ዲያቆኑ ጽዋውን ይዞ ቆሞ ያዜማል
‹‹የተቀደሰውን ሥጋ ወደሙን የተቀበልነውን እግዚአብሔርን እናመስግነው ... ለነፍሳችን ቁስል ፈውስ ይሁነን... ›› ማለት ጀመረ...
እኛም ‹‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ወደ ፈተና አታግባን›› እያልን መለስን፡፡
በሰማይ በአባትነቱ መንግሥቱን እስከምንወርስ ድረስ
ከፈተና ከኃጢአት እንዲጠብቀን ፈጣሪያችንን ለመንነው፡፡ በካህኑ እጅ ተባርከን ተሰናበተን
በምድር ያለች የሰማይ ደጅ ... የቁስላችንን መፈወሻ ... ቤተ ክርስቲያንን የሠጠንን አምላክ ከልቤ አመሰገንሁት... ያለ እረኛ ስላልተወን አመሰገንሁት..
አዎ ሞት ከእንግዲህ ሞት ለእኔ ክብር ነው ... ሰውነቴ ቢከሳ ... ሥጋዬ ቢጎዳ እግዚአብሔር በምድርና በምድራዊያን መካከል ውበቴን አርግፎ በሰማይ ሊስጌጠኝ መሆኑን ስለማውቅ ደስ ይለኛል...
በሥጋዬ መታመም ለነፍሴ ጤንነት እንደሆነ ስለማውቅ ደስ ይለኛል ... ጤንነት ሲሰማኝ ወደ ኃጢአት እንደምሮጥ አውቃለሁና በመታመሜ አልከፋም ... መጎሳቆሌ
እግዚአብሔር ከምታልፈው ዓለም ለይቶ ለማታልፈው መንግሥቱ ሊያዘጋጀ እንደሆነ አውቃለሁ ..
‹‹ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅከኝ ለመልካም ሆነልኝ››
መዝ. 118፡71"////
‹‹በአምጣነ ብዝኃ ጸጋሁ ያበውኣ ለነፍስ ውስተ ኩሎን ጻዕረ ምንዳቤያት ፤ ወያመጽእ ደዌ በእንተ ጥዒናሃ ለነፍስ››
(ስለ ጸጋው ብዛት ነፍስን ወደ ብዙ ችግርና መከራ ያስገባታል
ስለ ነፍስ ጤና በሥጋ ላይ በሽታን ያመጣል፡፡››
( የቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ)
https://www.tgoop.com/hinokhailes_spiritual_teachings

ለመቀላቀል 👆👆👆 ይጫኑ
ዲያቆኑ ጽዋውን ይዞ ቆሞ ያዜማል
‹‹የተቀደሰውን ሥጋ ወደሙን የተቀበልነውን እግዚአብሔርን እናመስግነው ... ለነፍሳችን ቁስል ፈውስ ይሁነን... ›› ማለት ጀመረ...
እኛም ‹‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ወደ ፈተና አታግባን›› እያልን መለስን፡፡
በሰማይ በአባትነቱ መንግሥቱን እስከምንወርስ ድረስ
ከፈተና ከኃጢአት እንዲጠብቀን ፈጣሪያችንን ለመንነው፡፡ በካህኑ እጅ ተባርከን ተሰናበተን
በምድር ያለች የሰማይ ደጅ ... የቁስላችንን መፈወሻ ... ቤተ ክርስቲያንን የሠጠንን አምላክ ከልቤ አመሰገንሁት... ያለ እረኛ ስላልተወን አመሰገንሁት..
አዎ ሞት ከእንግዲህ ሞት ለእኔ ክብር ነው ... ሰውነቴ ቢከሳ ... ሥጋዬ ቢጎዳ እግዚአብሔር በምድርና በምድራዊያን መካከል ውበቴን አርግፎ በሰማይ ሊስጌጠኝ መሆኑን ስለማውቅ ደስ ይለኛል...
በሥጋዬ መታመም ለነፍሴ ጤንነት እንደሆነ ስለማውቅ ደስ ይለኛል ... ጤንነት ሲሰማኝ ወደ ኃጢአት እንደምሮጥ አውቃለሁና በመታመሜ አልከፋም ... መጎሳቆሌ
እግዚአብሔር ከምታልፈው ዓለም ለይቶ ለማታልፈው መንግሥቱ ሊያዘጋጀ እንደሆነ አውቃለሁ ..
‹‹ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅከኝ ለመልካም ሆነልኝ››
መዝ. 118፡71"////
‹‹በአምጣነ ብዝኃ ጸጋሁ ያበውኣ ለነፍስ ውስተ ኩሎን ጻዕረ ምንዳቤያት ፤ ወያመጽእ ደዌ በእንተ ጥዒናሃ ለነፍስ››
(ስለ ጸጋው ብዛት ነፍስን ወደ ብዙ ችግርና መከራ ያስገባታል
ስለ ነፍስ ጤና በሥጋ ላይ በሽታን ያመጣል፡፡››
( የቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ)
https://www.tgoop.com/hinokhailes_spiritual_teachings
https://www.tgoop.com/hinokhailes_spiritual_teachings
ለመቀላቀል 👆👆👆 ይጫኑ
Telegram
የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
◉ ይህ ገፅ የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ነባር እና አዳዲስ መጣጥፎች የምናጋራበት የVIDEO ትምህርቶቹን የምንለቅበት የቴሌግራም ገፃችን ነው። ነገር ግን እንድታቁልን የምንፈልገው ገፁ በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ሚመራ ገፅ አደለም።
መጽሐፈ መነኮሳት [አንቀጽ 8]
እጠገናለሁ ብሎ መሰበር እንደማይመች ንስሓ እገባለሁ ብሎ ኃጢአት መሥራት አይገባም፡፡ኃጢአት በልዑል እግዚአብሔር ዘንድ የተጠላች የተናቀች ናት፡፡የኖኅ ዘመን ሰዎች እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ ኃጢአትን በማብዛታቸው ጠፉ፡፡ካህኑ ኤሊ ልጆቹ አፍኒና ፊንሐስ የእግዚአብሔርን ሥርዓት ሲያፈርሱ ባለመቆጣቱ ከሕጉ ይልቅ ልጆቹን በመውደዱ እርሱም ሞተ፡፡ ክፉ ሥራ ሠርተን እግዚአብሔርን አናሳዝነው፡፡

👍1
መጽሐፈ መነኮሳት [አንቀጽ 16]
የዝሙትን ጾር ሁል ጊዜ ድል የሚነሣ ሰው የብርሃን መጽሐፍ ይሰጠዋል፡፡ ወዳጆቼ ከሐኬት
እንጠበቅ ዘንድ ይገባናል፡፡ ሐኬት መከራን ይወልዳልና፡፡ የትዕቢት ጾር በተነሳብህ ጊዜ ከሁሉ
አንሳለሁ በል፡፡ ኃጢአቱን ለንስሓ አባቱ የሚናገር ሰው ሥርየትን (ይቅርታን) ያገኛል፡፡ ብፁዕ
ዘርኅቀ እምዓለም፡፡ ከዓለም የተለየ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ ሥጋዊ ተድላን ሁሉ መከራ
ይከተለዋል፡፡ የኅልፈት ምክንያት ካለበት ከሥጋዊ ደስታ ተጠበቅ፡፡ ታናሹን ኃጢአት ድል
ካልነሣህ በታላቁ ኃጢአት መሠልጠን አይቻልህም፡፡

መጽሐፈ መነኮሳት [አንቀጽ 22]
ስለበጎ ሥራ የሚቀበሏቸው መከራት እንደጸጋ እንደ ክብር ይወደዳሉ፡፡ መከራ ለመቀበል
የሚወድ ሰው አስቀድሞ እግዚአብሔር ያድነኛል ብሎ ይመን፡፡ ተምሬያለሁ አዋቂ ነኝ ከሚል
ሰው ያልተማረ በመከራ የተፈተነ ጨዋ ይሻላል፡፡ የምናገኘው ክብር በመከራችን ልክ ነው፡፡
ከመከራ በኋላ ጸጋ ክብር ይሰጣል፡፡ ስለታበይን ከሰይጣናት ዘንድ የሚመጣብን መከራም አለ፡፡
ይህም ክፉ ክፉ ነገር በሚያደርጉብን ሰዎች ይጥለናል፡፡ የሰው ትዕግሥቱ መከራውን
ያርቀዋል፡፡ ትዕግሥት የጸጋ ምክንያት ናት፡፡ እግዚአብሔርን የወደድክ ያህል በመንፈስ ቅዱስ
ደስ የሚልህ ደስታ ይበዛል፡፡ እግዚአብሔርን መከራውን ታግሠን በማመስገን እንለምነው።

መጽሐፈ መነኮሳት [አንቀጽ 7]
ደካማነትን መረዳት የትሩፋት መጀመሪያ ነው፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር ታድናለች፡፡ ሰው
አብዝቶ ሲጸልይ ልቡናው ትሑት ይሆናል፡፡ ፈጣሪ ትሑት ልቡና የጸለየውን ጸሎት አልቀበልም
አይልም፡፡ ልቡና በመከራ ትሑት ካልሆነ ትዕቢትን መተው አይቻለውም፡፡ ትሕትና መከራን
ያርቃል፡፡ ክብርን ያመጣል፡፡ ትዕቢትን ያርቃል፡፡ ሰው ትሑት በሆነ ጊዜ ይቅርታን ያገኛል፡፡
ጸሎት መዝገበ ረድኤት ናት፡፡ የረድኤት መገኛ ጸሎት ናት፡፡ ወነቅዐ መድኃኒት የድኅነት መገኛ
ናት፡፡ ከመከራ ማዕበል ሞገድ የምታድን ወደብ ናት፡፡ የድኩማን መጠጊያ ናት፡፡ የሕይወት
ተክል ናት፡፡ በጠላት ፊት የተቃጣች ፍላፃ ናት፡፡ ሰው በጸሎት ሀብታት ምሥጢራትን አእምሮ
መንፈሳዊን ገንዘብ ያደርጋል፡፡ እያመሰገኑ መጸለይ ደስ ያሰኛል፡፡ ሰው በልቡ ወደፈጣሪው
ሲቀርብ ፈጣሪም ጸጋውን ክብሩን ይሰጠዋል፡፡ ደግ ሰው የባሕርዩን ድካም ያውቃል፡፡ ድካሙን
የማያውቅ ሰው ትሕትናን አያገኝም፡፡ የጌታን አጋዥነት የሚሻ ሰው እነሆ የባሕርዩን ድካም
አወቀ፡፡ ሰው እግዚአብሔርን በሥራው ሁሉ ሊያመሰግን ይገባዋል፡፡ ሰው ሁሉ በራሱ መፍረድ
ይገባዋል፡፡

👍2❤1
መጽሐፈ መነኮሳት [አንቀጽ 9]
የደገኛይቱን ሀገር የመንግሥተ ሰማይን ምሥጢር ማሰብ መልካም ነው፡፡ አብዝቶ መብላት
አይገባም፡፡ ትሩፋትን ስንሠራ ጸጋ ይሰጠናል፡፡

ቅዱስ ሚካኤል - መልአከ ምክሩ
በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር ስለሚያደርገው የምክር ጉባኤ ተጽፏል። ይህ መለኮታዊ ምክር ( the devine council) እግዚአብሔር ስለሚያደርገው እና ስለፍርዱ ከተመረጡ ቅዱሳን ጋር የሚያደርገው ነው። ይህን የሚያደርገውም ከቅዱሳንም መርጦ ላከበራቸው ያለውን ክብር ያሳይ ዘንድ ከሥልጣኑ በጸጋ እያሳተፋቸው እንጂ ከእግዚአብሔር ፍርድ እና ምክር የሚጎድል ኖሮ እነርሱ ሊሞሉለት አይደለም።
የመጀመሪያው ይህን የተመረጡ ቅዱሳን ምክር የሚያሳይ ጥቅስ መዝ. 81/82 ነው፦ “እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።"
ሌላኛው ደግሞ "እግዚአብሔርን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች እግዚአብሔርን ማን ይመስለዋል? በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው፤" የሚለው ነው። (መዝ. 89፥6-7)
***
ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ምክሩ የሚባል የመላእክት አለቃ ሆኖ የዚህ መለኮታዊ ምክር አካል ስለሆነ ነው። 'ተሾመ' የሚለው ቃል ይህን መመረጥ ይገልጣል። ከሌሎች መላእክት በተለየ በዙፋን ላይ ተቀምጦ መሳሉም ለዚሁ ነው። ድንግል ማርያምም የዚህ ማኅበር አካል ነች። ቀድሞ የክርስቶስ ምሳሌ የሆነው ሰሎሞን ለእናቱ ያለውን ክብር ይገልጥ በጎኑ ዙፋን አስቀምጦ ያማክራት ነበር። (1ኛ ነገ. 2፥19) ዳዊትም "ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ ተናግሮላታል። (መዝ. 44/45፥9)
ሐዋርያትም እንዲሁ ናቸው፤ ጌታ በ12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ላይ ሲፈርዱ በዙፋን እንደሚቀመጡ መናገሩ የመለኮታዊው ምክር አካላት እንዳደረጋቸው ያሳያልና። (ማቴ. 19፥28)
ይህንም ነቢዩ ዳንኤል ቀድሞ ተናግሮታል፦ “ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።” (ዳን. 7፥9) ነቢዩ 'ዙፋኖች' ያለው እግዚአብሔር ብዙ ዙፋኖች ኑረውት ሳይሆን የተመረጡ ቅዱሳን የሚሳተፉበትን ከእግዚአብሔር ፍርድ ሲወጣ ቀድመው የሚያውቁ እና በባለሟልነት የሚማልዱ የቅዱሳን ጉባኤ ክብራቸውን ለማመልከት ነው።
በዚህ ሁሉ ታላቁ መልአክ ሚካኤል አለ! ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል! ከእግዚአብሔር የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው። ለጎስቋሎች ባሮችህ ለምንልን። አሜን።

👍4🙏1
❝አዎን አቤቱ አምላካችን አንተን ደስ ከማያሰኝኽ ሐሳብ እንለይ ዘንድ መለየቱን ስጠን....🙏❞
[ቅዳሴ እግዚእ]
መልካም ዕለተ ሰንበት ወበዓለእገዚአብሔር ወልድ!
https://www.tgoop.com/nshachannel
[ቅዳሴ እግዚእ]
መልካም ዕለተ ሰንበት ወበዓለእገዚአብሔር ወልድ!
https://www.tgoop.com/nshachannel
👍6🙏3
ራእየ ኒፎን
የይቅርታ ፏፏቴ የርኅራኄ ባለጠጋ የሆንክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትመልስ፤ ማረኝ፤ ይቅርም በለኝ፡፡
ጌታ ሆይ “አላውቅህም አትበለኝ!' ጌታ ሆይ እስከዛሬ የት ነበርክ?' ብለህም አትቆጣብኝ፡፡ በኃጢአት የቆሸሽሁ፧ በበደል እንደ ጢስ የጠቆርሁ፤ ሕግህን በመተላለፍ የበሰበስሁ፤ ፍቅርህን በመርሳት የተዋረድሁ፤ በርኵሰት የሽተትሁ፤ በዲያብሎስ ምክር የጠፋሁ፤ ሰዎች በሚሠሩት አስነዋሪ ሥራም ዋነኛ የሆንኩ የማልጠቅም ትቢያና ጉድፍ ልጅህን አትናቀኝ፤ ከፊትህም አፍሬ አልመለስ፡፡
መምህሬ ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ ራራልኝ፤ አድነኝም፡፡ ሰው ወዳጅ ሆይ “አንተ የኃጢአተኛን በንስሐ ከክፉ መንገዱ መመለሱን እንጂ መጥፋቱን እንደማትሻ' አውቃለሁና ተመልሰህ እስክትረዳኝና ምሕረትህን እስካገኝ አላርፍም፡፡"

ፍኖተ ሕይወት
ይህ ቻነል ለነፍሳችን ያለንን ግንዛቤ ለማሳደግ ብቻ የተከፈተ ቻናል ነው።በዚህ ቻናል ማንኛውንም አይነት መጽሐፍት መዝሙር እና ትምህርት ከፈለጉ በቻልነው ፍጥነት እናደርስዎታለን። ጥያቄ ካለዎት በኮሜንት መስጫ ሳጥን ላይ ያድርሱን።
👍4
📜"ለእኔ ሕይወት #ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" [ፊል 1፥21]
እነኾ ምሳሌ፦
በምንኩስና ይኖር የነበረ አባት ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ ገነት ሄደ። ከውጭም ቆሞ እንዲከፈትለት ደጁን ያንኳኳ ጀመር። ወዲያውም "ማን ነኽ?" የሚል ድምጽ ከውስጥ ሲወጣ ሰማ። መነኩሴውም "እኔ ነኝ" ሲል መለሰ። ይኹን እንጂ ያንኳኳው በር ግን ሊከፈትለት አልቻለም። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም እንደ ገና ተመልሶ ወደ ገነት በመምጣት ደጁን አንኳኳ። እንዳለፈውም ጊዜ ከውስጥ "ማን ነኽ?" የሚል ድምጽ ሰማ። እርሱም እንደ ለመደው "እኔ ነኝ" አለ። አኹንም በሩ ሳይከፈትለት ቀረ።
መነኩሴው በዚህ ተስፋ አልቆረጠም። ይኽ ከኾነ ከብዙ ዓመታት በኋላ እርሱም በመንፈሳዊው ጥበብ ጎልምሶ ተመልሶ ወደ ገነት ሄዶ በሩን አንኳኳ። እንደ ከዚኽ በፊቱም "ማን ነኽ?" የሚል ድምጽ ሰማ። ያም አባት የቀድሞው መልሱን ተወና "በእኔ ውስጥ የምትኖረው አንተ ነኽ" ሲል ለጠየቀው አካል መለሰ። በዚህ ጊዜ ተዘግቶ የነበረው በር ተከፈተለት ይባላል።
#ክርስትና ምንድር ነው? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ ማብራሪያዎች ሊሰጡ ይችላሉ። በአጭሩ ግን እንመልሰው ካልን፣ ክርስትና ማለት " #ክርስቶስ የሚያድርበት መቅደስ መሆን " ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲገልጽልን "እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም #ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል" ይለናል።(ገላ 2፥20) #ክርስቲያን ማለት "አንተ ማን ነኽ?" ተብሎ ሲጠየቅ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "በእኔ የሚኖር #ክርስቶስ ነው"፣ "አነ #ዘክርስቶስ" - "እኔ #የክርስቶስ ነኝ" ብሎ መመለስ የሚችል ነው።
#ጌታችን በወንጌል ለደቀ መዛሙርቱ "በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ" ሲል እንደ ተናገረ፣ እኛ #ለክርስቶስ መኖር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ይኖርብናል፤ እኛ #ለክርስቶስ ማደር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ያድርብናል። (ዮሐ 15፥4)
እንዲህ ያለውን ሕይወት የሚኖር እውነተኛ ክርስቲያን የሥጋን ሞት አይፈራም። ስለ ሃይማኖቱ መከራ መቀበልን አይሰቀቅም። #ክርስቶስን ከሚያሳጣው ሕይወት ይልቅ ወደ #ክርስቶስ የሚወስደውን ሞት ይመርጣል። ፈጣሪው ከሌለበት ምቾት ይልቅ ፈጣሪን ይዞ መሰቃየት ለእርሱ ያስደስተዋል።
ሰይፍ ይዘው በሚያስፈራሩትም ጨካኝ ወታደሮች ፊት "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" እያለ በሐሴት ይዘምራል። (ፊል 1፥21)
=======
በሰይፍ ለሚገድለው ወታደር በኩራት የልብሱን ኮሌታ ከፍ አድርጎ አንገቱን ስለ #ክርስቶስ በደስታ ለሰጠ፣ ለታላቁ ሐዋርያ #ለቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነት በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!
የአገልግሎቱ ድካም፣ በረከት በሁለችን ላይ ይደርብን!!!
✍️ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ገላትያ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።
¹⁷ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።
¹⁸ በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።
¹⁹ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥
²⁰ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥
²¹ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
²² የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
²³ እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።
²⁴ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።
²⁵ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።
²⁶ እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።

❤1👍1