tgoop.com/ohtube/64
Last Update:
ከስፓኒሽ ፍሉ እና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉት የ104 ዓመቱ አሜሪካዊ ከኮሮና ቫይረስ በሽታ አገገሙ።
ከስፓኒሽ ፍሉ እና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉት ቢል ላፕሺስ የተባሉ የ104 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ አሁን ደግሞ በኮቪድ-19 በሽታ ከተያዙ በኋላ ማገገማቸው ተነግሯል።
ግለሰቡ ምናልባትም ከኮቪድ-19 ያገገሙ በዓለም ላይ በዕድሜ ትልቁ ሰው ሳይሆኑ አይቀርም ነው የተባለው።
ላፕሺስ የሁለት ዓመት ሕፃን ሳሉ የተከሰተው ስፓኒሽ ፍሉ እየተባለ የሚጠራው ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ፣ በወቅቱ ከ50 እስከ 100 ሚሊዮን የሚደርሱ የዓለም ሕዝቦችን መፍጀቱ ይነገራል።
እኚህ የዕድሜ ባለፀጋ እ.አ.አ በ1943 ወደ አሜሪካ ሠራዊት መግባታቸው እና በሁለተኛው የዓለም ጦረነት ላይ ማሳተፋቸውም ተወስቷል።
እ.አ.አ በ1916 በአሜሪካዋ ኦሬጎን ከተማ ሳሌም በተባለ አካባቢ የተወለዱት ቢል ላፕሺስ፣ ከሦስት ሳምንታት በፊት በተደረገላቸው ምርመራ ነበር የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው።
ከእርሳቸው ጋር ተመርምረው ቫይረሱ የተገኘባቸው ዕድሜያቸው በ90ዎቹ ውስጥ የሆነ ሌላኛው ግለሰብ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
ቢል ላፕሺስ ከሚኖሩበት ኤድዋርድ ሲ ኦልዎርዝ የአረጋዊያን መኖሪያ ቤት ውስጥ እስካሁን 16 በኮቪድ-19 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስምንቱ ማገገማቸው፣ አንዱ የቫይረሱን ምልክት ማሳየት ማቆሙ፣ ሁለቱ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ እና ሁለቱ ደግሞ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
ላፕሺስ ግን እ.አ.አ በ1918 ከተሰተው ስፓኒሽ ፍሉ እና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት (እ.አ.አ 1933-45) ተርፈው አሁን ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ በኋላ አገግመው በትላንትናው ዕለት 104ኛ ዓመት ልደታቸውን ለማክበር በቅተዋል ሲል ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
#via_EBC
www.tgoop.com/ohtube
BY OH TUBE

Share with your friend now:
tgoop.com/ohtube/64