Telegram Web
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል

አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል/2/

በመስቀል ተሰቅለህ መድኃኒት ሆነሃል
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል
ሳታቆስል በፍቅርህ ማርከኸን
ከፊት ቀድመህ በድል አስከተልከን
በደለኞች እኛ ሆነን ሳለ
አንተ ከፍለህ ክሳችን ተጣለ
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን
#አዝ
እንደሰማን እንዲሁ አይተናል
ማዳንህን ቀምሰን መስክረናል
የእግዚአብሔር በግ ቆስለህ የፈወስከን
ወደ ድንቁ ብርሃን ያሻገርከን
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን
#አዝ
አፅናንተኸን ሞትን አስተከዝከው
ወደ ጥልቁ እንዲወርድ አዘዝከው
ባንተ ፍቅር ምርኮ በዝቶልናል
ማማ ሆነህ ከፍ ከፍ ብለናል
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን
#አዝ
ስንሸሽህ እየተከተልከን
ልጆች አርገህ በክብር አስጌጥከን
ተቅበዝባዡን ሰብስበሃልና
ከማደሪያህ ይፈልቃል ምስጋና
ኪርያላይሶን ኪርያላሶን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
     🔸 @Z_TEWODROS

✍️Comment @Channel_admin09
%E1%8B%9D%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%89%A0%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D
<unknown>
ዝናው በአለም የተወራ

ዝናው በአለም የተወራ
ክብሩ በምድር የተፈራ
ምን ይሳነዋል ከቶ ለሱ
እልል በሉለት በቤተ መቅደሱ

ካህናቶቹ ጽድቅ የለበሱ
በደብረ ጽዮን በራ መቅደሱ
ወደ እሱ መጥቶ ሁሉ ተፈወሰ
ስሙን የያዘ ቀንቶት ተመለሰ

መንጦላይቱን በሳት የሰራ
የአርያም ጸሀይ ላለም አበራ
ቸር አምላካችን ስንለው ሰምቶ
ይታደገናል እጁን ዘርግቶ

ለሚቃወሙን ክንዱን ገለጠ
እኛን ለማዳን ሞትን መረጠ
ከድሀ ሰው ጋር ትሁት ይሆናል
ሀይለኞችንም ያንበረክካል

እግዚአብሔር ማን ነው ብለው ቢያሙት
እነ ፈርኦን ቢያቃልሉት
እረኛው ሙሴን ከኮሬብ ጠርቶ
አደቀቃቸው ክንዱን ዘርግቶ
Forwarded from ናሁ ሰማን(Nahu seman) (?)
የምንለወጠው ምን ስናደርግ ነው

በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደ በረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰ'ሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም !

“እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለኾነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ ፈጽመው ሊወገዱ እንደ ማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡

በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡
Forwarded from ናሁ ሰማን(Nahu seman) (?)
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር👏
Photo
❤️ ጼዴንያ ማርያም ❤️

መስከረም ፲ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምትወድና በሚቻላትም ሁሉ የምታገለግላት፣ ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ መነኮስ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አድረው በማግሥቱ ከቤቷ ሲወጡ ማርታ የሚሔዱበትን አገር በጠየቀቻቸው ጊዜ እርሳቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው ቅዱሳት መካናትን እንደሚሳለሙ ነገሯት፡፡ ማርታም ከእርሷ ገንዘብ ወስደው የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው ይዘውላት እንዲመጡ ለመነቻቸው፡፡ መነኵሴውም በራሳቸው ገንዘብ ሥዕሉን ገዝተው እንደሚያመጡላት ቃል ገቡላት፡፡
አባ ቴዎድሮስ ኢየሩሳሌም ደርሰው ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ሥዕሏን ሳይገዙ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ?›› የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰምተው ተመልሰው መልኳ ያማረና የተወደደ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ገዝተው በሐርና በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ይዘው እየተጓዙ ሳሉ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ሲደርሱ ወንበዴዎች ተነሱባቸው፡፡ ሊሸሹ ሲሉም ‹‹መንገድህን ሒድ›› የሚል ቃል ከሥዕሏ ወጣ መነኵሴውም መንገዳቸውን በሰላም ተጓዙ፡፡ ሁለተኛም አንበሳ ሊበላቸው በተነሣባቸው ጊዜ ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረላቸው፡፡
አባ ቴዎድሮስ ይህን ኹሉ ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜም ያቺን ሥዕል ለማርታ ከመስጠት ይልቅ ወደ አገራቸው ሊወስዷት ወደዱ፡፡ በመርከብ ተሳፍረው በሌላ አቅጣጫ ሲሔዱም ታላቅ ነፋስ ተነሥቶ ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያ ወሰዳቸው፡፡ ከመርከብም ወርደው ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ደረሱ፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን ለማርታ አልገለጡላትም፤ እርሷም አላወቀቻቸውም ነበር፡፡
በማግሥቱም ተሠውረው ወደ አገራቸው ሊሔዱ ሲሉ የቅፅሩ ደጃፍ ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ዋሉ፤ በመሸባቸው ጊዜም ወደ ማደሪያቸው ተመለሱ፡፡ ማታ ማታ በሩን ያዩታል፤ ነግቶ መሔድን ሲሹ ግን የበሩ መንገድ ይሠወርባቸዋል፡፡ እንዲህም ኾነው እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቆዩ፡፡ ማርታም ‹‹አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ኾነህ ነው?›› ሰትል ጠየቀቻችው፡፡ እርሳቸውም ከእመቤታችን ሥዕል የተደረገውን ተአምር ሁሉ ነገሯት፤ ራሳቸውንም ገለጡላትና ሥዕሏን ሰጧት፡፡ እርሷም የእመቤታችንን ሥዕል ተቀብላ የተጠቀለለችበትን ልብስ በፈታችው ጊዜ ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች፡፡ ከደስታዋ ብዛት የተነሣም የአባ ቴዎድሮስን እጃቸውንና እግራቸውን ሳመች፡፡ ሥዕሏም ቅዱስ ሉቃስ የሣላት ነበረች፡፡
ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር አኖረቻት፡፡ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት፡፡ በቀንና በሌሊትም የሚያበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች፤ ከመቅረዞች ውጭም የሐር መጋረጃን ጋረደች፡፡ ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፡፡ እኒያ መነኰስም እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገሉ ኖሩ፡፡
የሀገሩ ሊቀ ጳጳስም የእመቤታችን ሥዕል ሥጋ የለበሰች ሆና ባገኙና ተአምሯንም በተመለከቱ ጊዜ ከዚህ አምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ፡፡ ከሥዕሏ ከሚንጠባጠበው ቅባት ቀድተው ለበረከት ሲካፈሉም ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ መላ፡፡ ሥዕሊቱን ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜም ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፡፡ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያች አገር በጼዴንያ ትገኛለች፡፡
የሁሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን ትፈውሳለች፡፡ ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና በየዓመቱም መስከረም ፲ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን ከእመቤታችን ፴፫ቱ በዓላት ውስጥ አንዱ አድርጋ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የልጇ፣ የወዳጇ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት አይለየን፡፡

ምንጭ፡ መጽሐፍ ስንክሳር ዘወርኃ መስከረም  
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እመቤታችን በአንቺ ምልጃ
@ney_ney_emye_maryam
#እመቤታችን_በአንቺ_ምልጃ (በማየ ቃና)

እመቤታችን በአንቺ ምልጃ (2)
ድንግል ማርያም በአንቺ ምልጃ (2)
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና(2)

ለጌታችን ተአምር >>> በማየ ቃና
ተመርጣ ታድላ >>> በማየ ቃና
መጀመሪያ ኾነች >>> በማየ ቃና
ቃና ዘገሊላ >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ ---------------

ታውቋት ስላለችው >>> በማየ ቃና
ወይንኬ አልቦሙ >>> በማየ ቃና
ውኃ ወይን ሲሆን >>> በማየ ቃና
ኹሉ ዓዩ ሰሙ >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ -------------

አሳላፊዎቹ >>> በማየ ቃና
ግራ ቢገባቸው >>> በማየ ቃና
የድንግል ማርያም ልጅ >>> በማየ ቃና
ከጭንቅ አወጣቸው >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ --------------

እኛም እናምናለን >>> በማየ ቃና
በርሷ ትንብልና >>> በማየ ቃና
ስለ ቃልኪዳኗ >>> በማየ ቃና
ሁሉ እንደሚቀና >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ


መዝሙር: ቀሲስ እስክንድር ወ/ማርያም
እመኑ በርሱ - ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን (Official Audio)
እመኑ በእርሱ ድንቅ ያደርጋል ጌታ
በረዶ አዝንቦ ጠላት እየመታ
ውቅያኖስ ጥልቁን ፈጥኖ እያተነነ
ነገር ለወጠ ሁሉ በእርሱ ሆነ

እመኑ በእርሱ ተራራው ነደደ
„ „ „ „ ሸለቆው ታወከ
„ „ „ „ አለቱ ደቀቀ
„ „ „ „ የአህዛብ ጣኦታት
„ „ „ „ በፊቱ ረገፉ
„ „ „ „ በስሙ የታመኑ
„ „ „ „ ወጀቡን ቀዘፉ

እመኑ በእርሱ የማይነጋ ሌሊት
„ „ „ „ የማያልፍ ቀን አለ
„ „ „ „ ሁሉ ይቻለዋል
„ „ „ „ ጌታ መድኃኔዓለም
„ „ „ „ ፍቅር ነው ዘላለም
„ „ „ „ ደግ አባት ለልጁ
„ „ „ „ ሁሌ ተዘርግታ
„ „ „ „ ትኖራለች እጁ

እመኑ በእርሱ ሞገድ የማይሰብረው
„ „ „ „ ጽኑ መርከብ አለን
„ „ „ „ አንፈራም አንሰጋም
„ „ „ „ ከእርሱ ጋር እያለን
„ „ „ „ ጠላት ተሽንፏል
„ „ „ „ ሰይጣን አፍሯል ዛሬ
„ „ „ „ ወህኒው ይነዋወፅል
„ „ „ „ በታላቅ ዝማሬ

እመኑ በእርሱ ባዶ ነው አይሰራም
„ „ „ „ የጠላት ፉከራ
„ „ „ „ የማይተወን ጌታ
„ „ „ „ አለ ከእኛ ጋራ
„ „ „ „ እጅግ አትረፍርፎ
„ „ „ „ ፀጋ ከበዛልን
„ „ „ „ በሞት ጀርባ ቆመን
„ „ „ „ ገና እንዘምራለን

ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
◈ ለእኔ ያደረገው ◈
✞ ጋሜል - ዘ ኦርቶዶክስ ✞
✞ ለእኔ ያደረገው ✞

ለእኔ ያደረገው ሚካኤል ብዙ ነው [፪]
ከእግዚአብሔር ተልኮ ድንቅ ነገር አደረገልኝ
አፅናኝና እረዳት ሚካኤል ሆነልኝ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ታናሽ ብላቴና ስምክን የማይረሳ
ደግፈኝ ሚካኤል ስወድቅ እንድነሳ
ስምህን በልቤ ጽላት እጽፋለሁ
በክንፎችህ ጥላ ዛሬም ድረስ እላለሁ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ውለታህ እንዳይጠፋ ሁሌም ከሐሳቤ
ሚካኤል ሳልልህ ፍቅርህን ከልቤ
አንተነህ የዋህ መልአክት የእርግብ አምሳል
የብርሀን አክሊል ነህ ሚካኤል ኃያል

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ለእኔ ያለህን ፍቅር በዓይኔ አይቻለሁ
ውለታህን ሳስብ እጅግ አደንቃለሁ
በነፍስም በስጋም መታመኛዬ
የምትጥብቀኝ መከታ ጋሻዬ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ስወጣ ስገባ ከልሎ ከእንቅፋት
ሚካኤል ጠብቀኝ ከሚገጥመኝ ጥፋት
ደግ ነው ሚካኤል ፍቅሩ በዝቶልኛል
በዘመኔ ሁሉ እሱ ይረዳኛል

መዝሙር|
ሊቀ ልሳናት ዘማሪ ቸርነት ሰናይ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://www.tgoop.com/yemezmur_gexem
https://www.tgoop.com/yemezmur_gexem
https://www.tgoop.com/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Forwarded from ናሁ ሰማን(Nahu seman) (?)
+++ የዘመኑ ፈተና... +++

የራስ ጸጉሩን በመጠኑ ለመስተካከል አንድ ሰው ወደ ጸጉር ቤት ያመራል፡፡ የጸጉር ውበት ባለሙያውም ያለመጠን ብቅ ብቅ ያሉ የጸጉር ዘለላዎቹን ከማረም ጋር ጥቂት ጨዋታ ቢጤ ይጀምራሉ፡፡

  ጸጉር ቆራጭ- ወንድሜ በእግዚአብሔር መኖር ታምናለህን?

  ተቆራጭ- እንዴታ?! ምን ጥርጥር አለው፡፡

  ጸጉር ቆራጭ- እኔ ግን በእግዚአብሔር መኖር አላምንም፡፡ ያንተም እምነት ልክ እንደሆነ አላስብም፡፡ እስኪ አስተውል! ዓለምን እና በውስጧ የሚኖሩትን የፈጠረ በጎ ፣የፍጥረቱንም መጎዳት የማይሻ መልካም አምላክ ቢኖር ኖሮ ዓለም እንዲህ በጥፋት ባልታመሰች፡፡ አሁን ወደ ጎዳናው ብትወጣ አሳዳጊ አጥተው በደዌ ተይዘው በየሜዳው የተበተኑ ሕፃናትን፣ ጧሪ ያጡ አረጋውያንን ትመለከታለህ፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ነገር እያየህ ፈጣሪ አለ ብለህ ታምናለህ?

በዚህ ጊዜ ጸጉሩን የሚስተካከለው ሰው በዝምታ ተዋጠ፡፡ የተነሡት ማስረጃዎች ሁሉ የማይካዱ የአደባባይ ሐቆች እንደሆኑ ሲያስብ መልስ አጥቶ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጠመ፡፡ ፈጥኖ የእርሱን ሐሳብ መቀበልም አልፈለገም፡፡ የማይጨበጥ ምክንያት ይዞ በጉንጭ አልፋ ክርክር ሊሞግተውም አልወደደም፡፡ ብቻ የመረጠው ዝምታን ነበር፡፡ ዝም አለ!

እንዲህ ዝም እንዳለ ጸጉሩን ተስተካክሎ ጨርሶ ወጣ፡፡ የሚደንቀው ግን ወደ ወጣበት ጸጉር ቤት ድንገት ዘው ብሎ ገባ፡፡ ቀጥሎም ጸጉሩን ወዳስተካከለው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭ የለም!›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም በንግግሩ እየተገረመና በድንጋጤ እያየው ‹‹እንዴት? አንተ ራስህ የት ተቆርጠህ ነው እንዲህ የምትናገረው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ያም ደንበኛ ጸጉር ቆራጩን እጁን ይዞ ወደ ውጭ እያስወጣው፣ በጎዳናው ላይ የተንጨባረረ እና ያልጸዳ ጸጉር ወደ ነበረው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭማ የለም፡፡ ጸጉር ቆራጭ ቢኖር ኖሮ ይህ ምስኪን በተቆረጠ ነበር›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም እርማት ለመስጠት እየቸኮለ ‹‹ቆይ ቆይ ወንድሜ አትሳሳት፡፡ ጸጉር አስተካካይማ እኔ አለሁ፡፡ ይህ ሰው ጸጉሩ የተንጨባረረው እኔ ባለመኖሬ ሳይሆን እርሱ ወደ እኔ ስላልመጣ ነው›› እያለ መኖሩን ሊያሳምነው ሞከረ፡፡

ያም ጸጉር ተስተካካይ እንዲህ አለው ‹‹አዎ፤ የዚህ ሰው ጸጉር ያለ ልክ አድጎ የተንጨባረረውና አዳፋ የሆነው አንተ ባለሙያው ስለሌለህ ሳይሆን እርሱ ወደ አንተ ስላልመጣ ነው፡፡ ልክ እንደዚህ ደግሞ ዓለም ችግር ውስጥ የምትወድቀውና ክፉ ነገር የሚያጋጥማት ፍጹም በጎ የሆነ አምላክ ሰለሌለ ወይም የሚጠብቃት ቸር እረኛ ስላጣች ሳይሆን ዓለም ወደ ፈጣሪዋ ስላልመጣች፣ በንስሓም ወደ እርሱ ስላልቀረበች ነው።››

‹እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል›
2ኛ ዜና 15፡2

ወደ አምላካችን እንቅረብ!!!
Forwarded from ናሁ ሰማን(Nahu seman) (?)
#መስከረም_16_የደመራ_በዓል
#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 #ደመራ ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ያወቀችበት ዕለት ነው፡፡

🔷👉 ደመራ ማለት፤ ደመረ፣ ጨመረ፣ አንድ አደረገ፤ ከሚለው የግእዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን መቀላቀልን፣ መገናኘትን፣ መሰብሰብን፣ መጣመርን፣ መዋሐድን በአጠቃላይ ሱታፌን፣ አንድነትን እና ኅብረትን ያመለክታል፡፡

🔷👉 ጥንተ ታሪኩም፤ ክርስቶስ በሞተ ጊዜ የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በጌታ መካነ መቃብር ጎልጎታ ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት የኢየሩሳሌሙ ኤጲስ ቆጶስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገው እነርሱም ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠዋትና ማታ በጎልጎታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡

🔵👉 ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተአምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ መፈወስ ጀመሩ፤ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ሳባቸው፡፡

🔶👉 ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየተጣለበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆየ፡፡

🔷👉 በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጕዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትዕምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ /በዚህ ምልክት ድል ታደርጋለህ/›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡

🔴👉 የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡

🔷👉 በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው እርሱም ሦስት ተራሮችን ጠቆማትና ከሦስት ተራሮች የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ግን በእግዚብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡

🔴👉 ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ /አስደምረሽ/ ዕጣን አፍስሺበትና በእሳት አያይዥው የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጭሽ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡

በዚህችም ቀን የጌታችን መካነ መቃብር ላይም ቤተክርስቲያን የታነጸችበት ዕለት ይታሰባል።

#መስቀል_ መስከረም 17

🔷👉 ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት መስቀሉ እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽቦችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡
Forwarded from ናሁ ሰማን(Nahu seman) (?)
የቅዱስ እስጢፋኖስና የብራነ መስቀሉ ተወዳጅ መዝሙሮች


1,✧ሰማያት ተከፍተው
2,✧ጽጌ_ሃይማኖት
3,✧ ሰማዕታት
4,✧ከመ ትባርከነ
5,✧ኦ እስጢፋኖስ
6,✧ ቅዱስ እስጢፋኖስ ✧   
7,✧ እስጢፋኖስ
8,✧ ቅዱስ እስጢፋኖስ
9,✧ ቀዳሚ ሰማዕት
10,✞መድኃኒት ዕፀ ሕይወት
11,✞ እፀ መስቀል
12,✞ ደስ_ይበለን_እልል_በሉ
13,✞ በመስቀል ላይ ሆኖ
14, ✞ መስቀል ኃይላችን
15,✞  እሰይ እልል በሉ 
16,✞ ድል በቀራንዮ
17,✞ዕሌኒ ንግሥት
18,✞አለው  ሞገስ
19,✞ጸጋ ነሣእነ
20,✞ መስቀል ክብሬ ነው
21,✞መስቀል ብርሃን ነው
22,✞ መስቀል ተመርኩዘን
23,✞ መስቀል አበራ
24,✞ መስቀል ብርሃን
25,✟እሰይ አበራ መስቀሉ
26,✟መስቀል መስቀል

ስም(ርዕስ) በመንካት መዝሙሩን ከነ ግጥሙ ያግኙ

ከተመቻቹ share like በማድረግ ቤተሰብ ይሁን
 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯
⚡️Acorns ቦትን በስልኮት በመጠቀም ብቻ በወር 100,000ሺ ብር በላይ ተከፋይ ይሁኑ 💸

🎁የ Acorns ቦት ጋር ልክ እንደገቡ የ
1000ብር ስጦታ ያገኛሉ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ በየቀኑ የ 50ብር ቋሚ ክፍያ ያገኛሉ

🔗ይህ የእርሶ የመጋበዣ
link ነው ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ 👇👇
https://www.tgoop.com/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r06502170520
2024/09/30 00:00:09
Back to Top
HTML Embed Code: