Telegram Web
ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo.
🔴 እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል ? |...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል?
             
Size:-82.9MB
Length:-1:38:35

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo.
ቅድስት ቤተክርስቲያን ጠርታ ትሸልመው በቆብ እና በማዕረግ ስም ከመክበስበስ ውጭ ስራ ፈተው ያሉት ሰባክያን እና መነኮሳት አኬ ! የማንቂያ ደውል ነው።

በተረፈ የስምን ካባ የለበሳችሁ እና የእርሱ ከእናንተ መግነን አሳስቧችሁ አሁን ወዬ ወዬ የምትሉ የአውደ ምህረቱ መልክ ሰሪዎች እረፉ ! በነገራችን ላይ አንብቡ መማርም አይጎዳም ተማሩ !

ከሐሜት ትርቁ ዘንድ

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo.
ድካሙን ተረድተን በፍቅር ቃል እናርመው!
...................................
አኬና ጓደኞቹ በቲክቶክ ያስነሱት የወንጌል አቢዮት ቀላል የሚባል አይደለም። ቤተክርስቲያን የሆነችውን ሳይሆን ባልሆነችው በሚዲያ የሚከሷት፣የሚወቅሷት ቀላል አልነበሩም። ዛሬ በቀላሉ ይኼን ማድረግ አይችሉም።
ምክንያቱም እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው የቤተክርስቲያንን እውነተኛ መልክ የሚገልጡ፤ እውነተኛ ትምህርቷንም የሚያስረዱ ቀላል የማይባሉ ልጆች በፕላትፎርሙ አሏትና።

አገልግሎት ደግሞ ይህ ነው። ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለሁሉ በሁሉ ቦታ መድረስ። ነፍሳትን ከእሳት ነጥቆ ወደ ክርስቶስ የፍቅሩ ጥላ ማድረስ። እነ አኬ በዚህ ረገድ የተሻለ ስራ እየሰሩ ነው። አቀራረባቸው የዘመኑን ወጣት የተረዳ ነው።

አሁን ላይ ትልቅ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ፈተና የሆነው በመንፈሳዊ እውቀት መታበይ ብዙም አይታይባቸውም። መንፈሳዊ እውቀት የምናውቀው ብቻ ሳይሆን የምንኖረው በሕይወት የሚገለጥ ነው። የምናስተምረው የምንኖረው ነው እንጂ የተማርነው እውቀት ብቻ አይደለም።

መንፈሳዊ እውቀት ሊቅ ለመባል ሳይሆን ቅዱስ ለመሆን ነው የምንማረው።

የምናስተምረው ይህንን እውነት ነው። ነገር ግን በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ድካም ይኖራል።
የደከመውን ማበርታት እንጂ ገፍቶ መጣል ግን ከእኛ አይጠበቅም። በወንድማችን አክሊል አገልግሎት እጅግ ከሚኮሩ ወንድሞች አንዱ ነኝ።
እጅግ ትልቅ ስራ የሰራ፤እየሰራም ያለ ብርቱ ወጣት ነው። የሚበረታታ የእቅበተ እምነት ሥራ እየሰራ የሚገኝ ወንድም ነው። የእቅበተ እምነት ሥራ ለአንድ አካል የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም። ሁሉም እንደ ጸጋው ሊወጣው የሚገባ ተግባር እንጂ። በዘመነ ተሐድሶ ከፍተኛ የእቅበተ እምነት ሥራ ሲሰሩ የነበሩ የሰ/ት ቤት ወጣቶች ናቸው። የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዝምታን በመረጡበት ጊዜ እንኳን ሳይቀር።ይህ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። አሁንም እነዚህ ልጆች ማበረታታት እንጂ ሌላ ስም በመስጠት ለማሸማቀቅ መሞከር አጅግ ትክክል ያልሆነ ተግባር ነው።

ይህ ማለት ግን ምንም ስሕተት የለም ማለት አይደለም። በብዙ ወንድሞች የተገለጹ እኔም የምቀበላቸው መታረም ያለባቸው ስሕተቶች አሉ።
ያውም የመሠረታዊ ትምህርት። ነገር ግን በፍቅር ቀርቦ ማረም፤ በጸሎት ማገዝ ፤ለውጪ ጎታች ለውስጥ ገፊ አሳልፎ አለመስጠት፤
ሰድቦ ለሰዳቢ ፣ነቅፎ ለነቃፊ አለማድረስ ይገባል።

አክሊልና የአክሊልን ሀሳብ ለይቶ መነጋገር ያስፈልጋል። በርኅራኄ ፣በፍቅርና በሚያንጽ ቃል ሊያርም የሚገባው ነገሮ እንዲታረም መሞከር እንጂ ከክርስቲያናዊ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ እጅግ ኦርቶዶክሳዊነት በሚያሳይ መልኩ ሳይሆን በስድብና " ልክ አስገባሃለው " አይነት ጽንፍ የረገጠ፤ግለሰቡ ላይ ያተኮረ፤ድካሙንና ልፋቱን የዘነጋ አካሄድ እንድናጣው ያደርገን ካልሆነ በቀር እንዲታረም አያደርገውም።

የእውቀት ትከሻ መለካካት የሚመስሉ ቤተክርስቲያንን የዘነጉ ድርጊቶች እኛንና ትምህርታችንን የሚከተሉ ምእመናን ዘንድ ትዝብት ውስጥ ከመጣሉም ባሻገር ፤የምናስተምረውን የማንኖር " ጠላትህ ውደድ " ብለን የምንሰብክ ወንድማችንን የምናሳድድ ሆነን መቅረባችን ነውና እራሳችን እንታዘብ።

ለአኬም እንዘንለት፣እንጸልይለት፤ ብርታቱን ሳንዘነጋ ከድካሙ እንዲበረታ እናግዘው።
ይህ ከሆነ ለእኛ የታዩን ስሕተቶቹ የማየት እድሉ ይኖረዋል። ወንድማችንን አዳነው ማለት ይህ ነውና።

አኬን እንደ ወንድም እንውደደው። ሀሳቦቹን ደግሞ እንዲያርም እናግዘው እንጂ አንግፋው።

የሚያንጽ የፍቅር ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችን ከቶ አይውጣ።

✍️ የኤፍሬም ዕይታዎች
ሐዋርያት የሰበኩሽ
ሰማዕታት የሞቱልሽ
ጻድቃንም የከበሩብሽ
ተዋሕዶ ርትዕት ነሽ

ሰላም ተዋህዶ ሰላም ኦርቶዶክስ
የአትናትዮስ ሀውልቱ የዲዎስቆሮስ
የአዳም መመኪያ የሄዋን ሀገር
አንቺ አይደለሽም ሆይ የቅዱሳን ክብር

@ortodoxtewahedo
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚

#ጽናት

በጎ ሥራን አጽንቶ ከያዙት እግዚአብሔርን ያስገኛል፡፡ ሰይጣን የሚንቀው በጎ ሥራ የለምና የጀመራችሁትን በጎ ሥራ አጽንታችሁ ያዙ፡፡

#ኦርቶዶክሳዊያንን
👉 @ortodoxtewahedo ይጋብዙ፤

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ስለ ድንግል ብሎ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ስለ_ድንግል_ብሎ

ስለ ድንግል ብሎ ኢትዮጵያን ይጎብኛት
ድሮስ ከአምላክ በቀር ይህች አገር ምን አላት
በሠራዊት ብዛት መች ትጠበቃለች
በቅዱሳን ጸሎት እሳት ካልታጠረች(፪)

ዓለም ሸምቆባት አህዛብ ይስቃል
በልጆችሽ ዕንባ አውሬው ይቀልዳል
ታልቅ ሕዝብ መሆኑን ማን በነገራቸው
ከዘመናት በፊት አምላክ የጎበኘው(፪)
#አዝ
እውነተኛ ዕንባ ፈለቀ ከምድር
በፍጡራን ዋይታ ፍጹም ብትማረር
ዕንባና ደማችን ተደባልቆ ፈሷል
አምላክ ቅጣት ይብቃን አሁን ይቅር በለን(፪)
#አዝ
ቅዱሳንን መንቀፍ ወገኔ ተውና
ይልቅ ስለነሱ የጽድቅ ጎዳና
በረድኤታቸው በክብራቸው ጥላ
እንከተላቸው ከፍቅራቸው ኋላ(፪)

ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

"ኢትዮጵያ እጆቿን
ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች"
መዝ ፷፯፥፴፩

✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

@ortodoxtewahedo

✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
#ቅበላ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
                         አሜን

#ቅበላ #ምንድን #ነው

ቅበላ ማለት የጾም ዋዜማ፣ ጾም ከመግባቱ በፊት ቀደም ብሎ ያለው፤ ቀን ወይም ሰሞን ማለት ነው፡፡

በአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት ሰንበታት፣ አጽዋማትና በዓላት በዋዜማው በጸሎት (በምኅላ)፣ በመዝሙር፣ በትምህርት ወዘተ... ልዩ አቀባበል ይደረግላቸዋል።

🔘ለምሳሌ

አይሁድ ሰንበትን (ቅዳሜ) ሲያከብሩ በዋዜማው አቀባበል ያደርጉላታል፤ ዓርብ ፀሐይ ሲገባ ካህኑ ደውል ይደውላሉ፤ አሊያም በቤት ያለ የቤቱ አባወራ የሰንበት መግቢያ ሰዓት መቃረቡን ድምጽ በማሰማት ያሳውቃል።

በአካባቢው ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፤ በአንድ ላይ ሆነው ወደ ፀሐይ መውጫ ይሰግዳሉ፤ ጸሎት ይደረጋል፡፡

ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል አሥርቱ ቃላት ሌሎችም ንባባት ይደገማሉ፤  ማብራት ተይዞ “ዕለተ ሰንበት እንኳን ደህና መጣሽ” ብለው ያከብሯታል፡፡

ከሦስት ሰዓት በኋላ እራት ይበላሉ፤ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፤ አይሁድ (በሀገራችን ቤተ እስራኤላዊያንም ) የፋሲካን በዓል ከማክበራቸው በፊት የሰባት ቀን ጾም ይጾማሉ፤ በዋዜማው (ቅበላ) ይሆናል።

ከግብጽ ባርነት ነጻ ስለመውጣታቸው እንደተጠቀሰው ለፋሲካ ጾም አቀባበል ያደርጋሉ፤ ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች ወስደው በወሩ እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቀው የእስራኤል ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ያርዱታል፡፡
📖ዘጸ 12፥5

ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት መቃኑና ጉበኑን ይቀቡታል፤ በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይበላሉ ከመራራ ቅጠል ጋር ይበሉታል ጥሬውንና በውኃም የበሰለውን አይበሉም፤… የቀረ ቢኖር በእሳት ያቃጥላሉ፤ ያልቦካ ቂጣ ይበላሉ፤ ይህንን አድርገው መጻሕፍት ያነባሉ፣ጸሎት ያደረጋሉ።

በጾማቸው ወቅት ተጠንቅቀው ጾመው ይጨርሱና የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፤ ይህ ሁሉ ለሀዲስ ኪዳን ምሳሌ ነበር፤ ጾሙን የመሠረተልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ የፋሲካው በግም እርሱ ነው፤ ነጻ ያወጣንም ከዲያቢሎስ አገዛዝ ነው ቅበላ በተለይ የነነዌ ጾም እንዳለቀ ዐቢይ ጾም /ጾመ ሁዳዴ መስከረም አንድ ቀን በታወጀው መሠረት ቀናት ሲቀረው መናንንያን ካህናትና ምእመናን ጾሙን ለመቀበል የተለያዩ ዝግጅቶች ያደረጋሉ፡፡

ጾሙ አባ ዲዮስቆሮስ ስለ ዐቢይ ጾም ታላቅነት “ከመ እንተ ብእሲ ለጸዊም በውስተ ገዳም ኃደረ፤ እምኀበ ዲያብሎስ ተመከረ በኃይለ መለኮቱ መኳንንተ ጽልመት ሠዓረ፤ እንደ ሰው ሆኖ ለመጾም 40 መዓልት 40 ሌሊት በገዳመ ቆሮንቶስ ኖረ፤ ከዲያብሎስ ዘንድ በሦስት አርእስተ ኃጣውዕ ተፈተነ፤ ድል ይነሣልን ዘንድ 5500 መቶ ዘመን ሰልጥነው የኖሩትንና የጨለማ ገዥ የሆኑትን ሠራዊተ ዲያብሎስን በጌትነቱ ሻረልን”

እንዳለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት አድረገን በመጾም በዚህ ዓለም ስንኖር ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስን ድል ለማድረግ፣በጾሙ በረከት ጸጋና መንፈሳዊ ኃይል ለማግኘት እንድንበቃ የምናደርገው የዝግጅት ሰሞን ነው፡፡

በቅበላ ሰሞን አባቶቻችን በየገዳማቱና አድባራቱ ለቤተ እግዚአብሔር መገልገያ የሚሆኑ ንዋያትንና መብዓ ያዘጋጃሉ፤ ስምንቱን የዐቢይ ጾም የሱባዔ ሳምንታት የሚያሳልፉበትን ቦታ ይመርጣሉ፡፡

ለጸሎት የሚያግዟቸውን መጻሕፍት ያዘጋጃሉ፤ በጾም፣ በጸሎት፣ በምጽዋት ለማሳለፍ ዕቅድ ያወጣሉ፤ ጥሉላት (የእንስሳትና የዓሣ ሥጋ፣ የእንስሳት ውጤቶች) ምግቦችን ካስፈለጋቸው ለህሊናቸው ዕረፍት ለመስጠት በመጠኑ ይመገባሉ ጾመው ለማበርከትና ዋጋ ለማግኘት።

በከተማና በገጠር የሚገኙ ምእመናንም ጧፍ፣ ዕጣን፣ ዘቢብ፣ አልባሳት ሲገዙ ይሰነብታል፤ አልፎ አልፎም ጾሙን በንጹህ ህሊና ለመጀመር ከአበ ነብሳቸው ጋር ይወያያሉ።

"ወኢትፍራሕ ተጋንዮ በእንተ ኃጢአተከ ኃጢአትህን ለማመን ለመናገር አትፍራ፡” እንዳለ 📖ሲራክ 3፥18

የበደሉ ማሩኝታ የተጣሉም ይቅርታ ይጠይቃሉ፤ ነግቶ ለኪዳን፣ ቀኑን ለቅዳሴና ለሠርክ ጸሎት ለማወል ያቅዳሉ፡፡

መዝሙር ቤቶችም የበገናና ዘለሰኛ መዝሙራትን ያሰማሉ፤ ዛሬ ዛሬ ግን ቅበላ ሲባል በአብዛኛው አዕምሮ የሚከሰተው ከሰባው አርዶና አወራርዶ አሊያም ልኳንዳ ቤት ተሰልፎና ታድሞ፣ ጥሉላት ምግቦችን በዓይነት አሰልፎ፣ ጠጅ (አልኮል) ተጎንጭቶ፣ ከመጠን ያለፈ ደስታ ፈጥሮ ጾሙን መቀበል ሆኗል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም በመልእክቱ " በመጠን ኑሩ ንቁም ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና”
📖1ኛ ጴጥ 5፥8

እንዳለው ከመጠን ያለፈ ማንኛውም ደርጊት ለፈተና ብሎም በዲያቢሎስ ሊያስማርከን ይችላል፤ አንድ መምህር ሲያስተምር የሰማሁት ሴትየዋ በቅበላ ብዙ የጥሉላት ምግቦችን አዘጋጅታ ስትመገብ ሰንብታ ጾሙ ሲገባ ምግቡ ሳያልቅ ይቀራል፤ አላስችል ብሏት በጾሙ የመጀመረያ ሳምንት የተረፈውን ምግብ ትመገባለች፡፡

ይህችን እናት የህሊና ወቀሳ እረፍት ነሳት ለአበ ነብሷ(ለንስሀ አባቷ) መንገር ጥሩ አማራጭ እንደሆነ ተረድታ ያደረገችውን ነገረቻቸው፤ አበ ነብሷም አስተምረው ቀሪውን ጾም በተገቢው ሁኔታ እንድትጾም መክረው ይሸኟታል።

ጾሙ ሊያልቅ ሲቃረብ "ክፉ ባልንጀርነት መልካም አመል ያጠፋል” እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ከማይጾሙ ጓደኞቿ ጋር በመዋሏ የጥሉላት ምግብ ትመገባለች፤ አሁንም ከህሊና ወቀሳ መዳን ስላልቻለች ለአበ ነብሷ ለመናገር ወስና ነገረቻቸው፡፡

አበ ነብሷም የሴትየዋን ስም ጠርተው "ምነው ጾሙ ሲገባ አላስገባ አሁን ሊወጣ ሲል አላስወጣ አልሽ፤ አሏት ይባላል፡፡

ጾም አቀባበል የሚደረግለት መንፈሳዊነትን ባለቀቀ መልኩ በመጠኑ ሲሆን፤ በመጾማችን ድል የምናደርግበት በመንፈስ የምናድግበት የቤተክርስቲያን ልጅነታችንን የምናረጋግጥበት (ቀኖናና ሥርዓቷን ስለምንጠብቅ)  ይሆናል፤ ስለዚህ ዝግጅታችን ምን ይሁን ጾሙን ተቀብለን፤ ጾመን፣ ጸልየን፣ መጽውተን ሰግደን ዋጋ እንድናገኝ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡


         ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                  ይቆየን 

#ኦርቶዶክሳዊያንን

  👉 @ortodoxtewahedo ይጋብዙ፤
16 ❤️

እንጦጦ ሀመረኖህ ኪዳነ ምህረት

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#የካቲት_16_ኪዳነ ምህረት

ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡

ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡

እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡

ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ስም ቀል እገባልሻለው ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል።

በዚህም የተነሳ እመቤታችን እኛን በምልጃዋ የምታስምርበተ ፣ ጥያቄያችንን የምታስመልስበት ፣ እንቆቅልሻችንን የምታስፈታበት የምህረት ኪዳን የካቲት 16 ተቀብላለች እና ኪዳነ ምህረት እንላታለን ።


💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
#የካቲት_16_ኪዳነ ምህረት

ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡

ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡

እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡

ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ስም ቀል እገባልሻለው ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል።

በዚህም የተነሳ እመቤታችን እኛን በምልጃዋ የምታስምርበተ ፣ ጥያቄያችንን የምታስመልስበት ፣ እንቆቅልሻችንን የምታስፈታበት የምህረት ኪዳን የካቲት 16 ተቀብላለች እና ኪዳነ ምህረት እንላታለን ።

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
"ምድር ሁሉ በቁጣው ደመና ስትጋረድ የምህረት ኪዳን ቀስት ሆነሽ በመካከል የቆምሽ ድንግል ሆይ ፀጋውንና ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን ።"

🙏💚💛❤️

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
"እስመ ትቤ ለዓለም አሐንጽ ምሕረተ
በሰማይ ጸንዓ ጽድቅከ
ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩይንየ።"
            -መዝሙር 88፥2-4

"እንዲህ ብለሃልና። ምሕረት ለዘላለም ይመሠረታል፥ እውነትህም በሰማይ ይጸናል።
ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥"
        
         -መዝሙር 88(89)፥2-4

እንኳን አደረሰን አደረሳቹ

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
✝️7ቱ ኪዳናት✝️

ሰባቱ ኪዳናት "ተካየደ" ማለት "ተስማማ : ተማማለ" እንደ ማለት ሲሆን "ኪዳን" በቁሙ "ውል : ስምምነት" እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው:: እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጓል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: :: "ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ" "ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3)

#1 ኪዳነ አዳም አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው:: እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1) አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)

#2ኪዳነ ኖኅ ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች:: ከመርከቡ ከወጣ በኋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12) 

#3 ኪዳነ መልከ ጼዴቅ መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን ያስታኩት ነበር:: እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)

#4 ኪዳነ አብርሃም ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርህ አሕዛብ ይባረካሉ" አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)

#5 ኪዳነ ሙሴ ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ: የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)

#6 ኪዳነ ዳዊት ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሽህም" ብሎ ሲምልለት እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)

#7 ኪዳነ ምሕረት በብሉይ ኪዳን የነበሩ ስድስቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማኅጸን አደረ:: በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ ለአለም ቤዛ የሆነበት ነው ።

@ortodoxtewahedo
Forwarded from ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈ (👑 ናኦልዮጵያ ኢዮባዊ 👒)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔴 እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል ? |...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል?
             
Size:-82.9MB
Length:-1:38:35

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
🛑 || ብቻችንን አንችልም || እጅግ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ብቻችንን አንችልም
             
Size:-59.4MB
Length:-1:04:12

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
2025/02/22 10:11:29
Back to Top
HTML Embed Code: