Telegram Web
የኛ ግጥም ና ታሪክ pinned «-ልብ ልብ' ይባል!!! በፀሎት ብርከካ ልባችን ሲረካ አንድ ብቻ በፆም በሁዳዴ ይመጣ ይሆን ገዴ? አቻ ላቻ ከጥምቀት ፀበሉ ተመላለስ ሲሉ እማር ብዬ እኔ አንድም ከመንፈስ በነጠላ ስጓዝ ያለኝም እብስ ብርከካ ስግደቴ ባዶ ልቤ ተሰዶ ሀሳብ ተንዶ እስከመቼ ንቀት እስከመች ልጅነት ሽልማት ስነጠቅ ትገባኝ ይሆን ህይወት? እንባ ከሳቹ ትርጉመ ልል ልብ ያላወራው ቃል ይቀላል ከምበታተን በደመነፍሴ ሰብስቤ…»
"ሶምሶማ ጦርነት"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከነጮች ጋር እየተማረ ቁጭ ብለው እየተጨዋወቱ ሳለ "በልጅነቴ ጫማ አላውቅም ነበር" ሲላቸው ነጮቹ ደነገጡ::

"ረጅሙን የትምህርት ዘመኔን በባዶ እግር ነው ያሳለፍኩት" አለ ::
ምን ቢሉት ጥሩ ነው "ለምን አትፅፈውም? ይሄ እኮ የሚደንቅ ነው ለብዙ ሰው::"
ለነርሱ የደነቃቸው ክስተት ለጌታቸው ኃይሌ ሀገር ግን የተለመደ ህይወት ነበር::

ለብዙ የሚደንቀው ነገር ለኛ ኑሮ መሆኑ ስላቅ ነው:: በዓመት ሦስቴ የምናከብረው ብቸኛ ብዓል ነው ውጊያ::

ለምንሰማው ከደከመን እዳው ላይ ላሉት ዳፋው ዳይ ለወደቁት ምንኛ ስቃይ ይሆን?

ዛሬም ተስፋ አለን እንባባል ይሆናል:: ግን ዋሾ ነን:: እንደሀገር ሁለት ስሜት አለቀቀንም
ያልወጣልን ብሶት እና
የማንወጣው እልህ::

እንደህዝብ ቁጡ እና ሆደ ባሻ ሆነናል::
ታክሲ ውስጥ ብሶት
ኪዎስክ ውስጥ ጠርሙስ መስበር ቱግ ባይ::
ሳንነካ ሁሉም የሚያጠቃን የሚመስለን
ሁሉም የሚንቀን የሚመስለን
ሳንጠየቅ ገና የይሆናል መልስ የምናዘጋጅ ደንባሮች ሆነናል::

እንደህዝብ ተቀያይመናል::
እንደግለሰብ ተጠላልተናል::

በየሶሻል ሚዲያው ላይ ያሉት ነገሮች ድምፃቸው ቤተስኪያን ደጅ ከሚጮህ የመዝሙር ሞንታርቦ በላይ ይሰማል:: (ለሁለት ደቂቃ Tiktokህን ስክሮል አርገህ ሞክረው::) ሁሉም እየጮኸ ነው::
-ዳንሱ በጩኸት
-ስብከቱ በጩኸት
-ሞቲቬሽኑ በጩኸት
-ምክሩ በጩኸት

እልህ+ብሶት = ( )

እንደሀገር ልጅነቴ በሀገሬ ቅያሜ ካለኝ ቆየሁ:: ተኳርፍናል::

በየቦታው ሄጄ ያየሁት ህዝብ የራሱ ብሶት የራሱን እልህ ሳይ ያስፈራል እላለሁ::

"....አስርጪብኝ የምነት ቀንጃ
ለስጋቴ አጣማጅ አቻ
ለጭንቀቴ መቀንቻ ....."
እንዳለ ጸጋዬ

እኛስ
አይደክምም ወይ እያስታመሙ መግደል?
አይደክምም ወይ እየገረፉ ማባበል?
አይደክምም ወይ እየሳቁ ምስጋት?
አይደክምም ወይ እያረፉ መዋጋት?
አይደክምም ወይ?
አይደክምም?
አይደክምም?
🥰እናቴ🥰

❤️የህይወት መሠረቴ❤️
❤️የምን ጊዜም ቤቴ❤️
❤️ሲከፋሽ አልወድም ስተክዢ አዎ❤️
❤️አለውልሽ ሁሌም ገና እጦርሻለው❤️
❤️ሲርበኝ አብልተሽ ሲጠማኝ አጠጥተሽ❤️
❤️ሲያመኝ አስታምመሽ❤️
❤️ዘጠኝ ወር በሆድሽ ይዘሺኝ❤️
❤️እግሬ እስኪራመድ በጀርባሽ አዝለሺኝ❤️
❤️ሁሌም ተንከባክበሽ❤️
❤️አጫውተሽ አዝናንተሽ❤️
❤️አይዞሽ አለውልሽ ❤️
❤️ልጄ ትይኛለሽ❤️
❤️እናቴ እናቴ የእኔ ውዷ እናቴ❤️
❤️መቼም አልተውሽም እስከለተ ሞቴ❤️

ገጣሚ: ዮርዳኖስ ዘውዱ
ለማንኛውም አስተያየት
👇
@Pswyb
"የማይወዱን ሰዎች ግን ምን አጠፉ?"
ኤልያስ ሽታኹን
(እዚህ እና እዚያ)
~ ~ ~ ~

አለመወደድ ምንድነው?

ሰላም እንደማትወድኝ የነገረችኝ እህቷ ናት:: ልብ በሉልኝ 14 አመቴ ነው::
"አትወድህም" አልችኝ::
አለመውደድ ምንድነው?

እውነት ለማዉራት ነገሩ በቅጡ ሳይገባኝ ማቃጠር ጀመርኩ እወደድ እንድሆን::
"ከዛስ" ብባል መልስ የለኝም::
ብቻ መጠላትን አለፈልግኩትም:: እንዲሁ::

"አትወድህም?" ድምፅ ይከተልኛል::
አለመወደድ ምንድነው?

-ጎረቤታችን እናትህን "አትወዳትም"

-እህቴ ቦይ ፍሬንዷ ተለያት
ለምን?
"አይወዳትም"

-ክበብ ውስጥ በጏደኛህ ስለምትቀናበት
"አይወድህም"

-የአባትህ ልጆች አንተን "አይወዱህም"

ምንድነው "አለመወደድ?"

በአንድ ወቅት
ሀገር ሆላንድ የምትኖር ቆንጆ ልጅ አውቅ ነበር::

ምቾት ወይም ደስታ ውስጥ ነበርኩ::

"ባልና ሚስት እንሁን" በቅንፍ ይቀመጥልኝ::
ተባባልን
ሆንን::
አመት ሊሞላን ወር ሲቀረን ተለያየን::
ለምን?
"ፍቅሬ አለቀ" አለችኝ
ለምንኳት-

ፍቅሯን ፈልጌ?

ወይስ ማጣት ፈርቼ?

ቆንጆ ስለሆነች?

ሌላ መያዝ ደክሞኝ?

እንጃ ብቻ ለምንኳት::

ወራት ደጅ ጠናሁ::

ቢከብዳት እኔ አልኩላት::

"አትወጅኝም" በድምፅ ጠየቅኳት::
በቴክስት "አዎ ፍቅር የለኝም" አልችኝ::
ለህሊናዬ ነገርኩት "አትወደኝም" ዘገነነኝ::
አንዲት ሴት እኔ እንደማልወዳት ሲሰማት እንደዚህ ነው? የምትሆነው?
ብርድ ብርድ? አይነት
ወንድ ሸንቶ ሲጨርስ የሰውነት መርገፍገፍ? አይነት
(ሴቶች እንደሚሰማቸው አላጣራሁም)
እንባ የለሽ ሀዘን? አይነት
መውጫ ያጣ እልህ እቃ ስበር ስበር? አይነት

ብቻ "አልወድህምን" ደጋገምኩት::
ታመምኩት::
ሰክኜ አየሁት::
ያለወደዱን ሰዎች ምንድነው ጥፋታቸው?
እንደወደዱ ማስመሰል እንጂ አለመውደድ ጥፋት አልመሰልኝም::
ምክክር ከራሴ
ጥፋቱ እንድወደድ ገፄን ቀይሬ ፀጋዬ ደልዬ ጭብጨባ መግዛቴ እንጂ::

በአንዳንዶች አልወደድም::

አለመወደድ ምንድነው?

ከኔ ጋር መቃረን?

ስለኔ ክፉ ማሰብ?

መንገዴ ላይ መሰናክል መመኘት?

ህልውናዬን አለመቀበል?

የምኖርበትን መስመር አለመቀበል?

ስህተቴን ብቻ ነጥሎ ማየት?

ቅናት ያመጣው መታወር?

ምንድነው አለመወደድ?
የኛ ግጥም ና ታሪክ pinned «"የማይወዱን ሰዎች ግን ምን አጠፉ?" ኤልያስ ሽታኹን (እዚህ እና እዚያ) ~ ~ ~ ~ አለመወደድ ምንድነው? ሰላም እንደማትወድኝ የነገረችኝ እህቷ ናት:: ልብ በሉልኝ 14 አመቴ ነው:: "አትወድህም" አልችኝ:: አለመውደድ ምንድነው? እውነት ለማዉራት ነገሩ በቅጡ ሳይገባኝ ማቃጠር ጀመርኩ እወደድ እንድሆን:: "ከዛስ" ብባል መልስ የለኝም:: ብቻ መጠላትን…»
"ቢጫ ሞት"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ቢጫ አበባ ቆርጠን አደይ ቀነጠስን
ለወረት ገላችን ተስፋ ነሠነሥን....

እንዲያው ይመስል በዓል
የውሸት ከነዓን
ሀሰት ወለደ ነዌ
የውሸት ነነዌ
ለሀሰት ወጋችን ለውሸት ማዕረግ
ስንት አደይ ስንት በግ?

እኛ
የማይጠብቀንን ወቅት እየጠበቅን
ተስፋን ሰበብ አርግን ስንቱን አረገፍን?
ጥያቄ?
ከስሩ ገንደሰን
ከግንዱ ቀንጠሰን ለኛ ተስፋ ያልነው
ለአደዩ ምንድነው?

ሞት::
#እማሆይን ፍለጋ#

#ለልባም ሴት#

"...የሚነገሩ ንግርቶች፣ የሚጠቀሱ ጥቅሶች ፣የሚተረቱ ተረቶችም ልትሰሚ፣ልትዘከሪም ትችያለሽ። በመልክሽ፣በወዘናሽ ተለክቶ ስም ሊሰጥሽ ይችላል።
ቃላቶችሽን አክብሪያቸው ኑሪላቸው ለጥሩ አድማጭ አዊያቸው አልያም ዝምታን ምረጪ ለችግሮቿ መፍትሄ፣ለሀዘኗ ደስታን የምትፈጥር ከጥላቻ በላይ ፍቅርን ሰባኪ የሆነች ሴት ብልህ ነች።"
ይላሉ እማሆይ
"ወላጅ ቆንጥጦ ከሚያስተምረው
እድሜ ፈትኖ ሚያስተምረው ትምህርት እጅጉን የላቀ ነው።
የሰው ልጅ ምን ያህል ውድ እንደሆነ ዋጋውን የሚያውቀው አካባቢው ላይ እሱን አሳታፊ አሉባልታ ስለተቸረ ሳይሆን ማን እንደሆነ እራሱን ያወቀ ጊዜ ነው
አጥፍቶ እርሱ ስህተቱን እንዳልሆነ የተረዳ ወቅት ነው እራሱን ያወቀው ልጄ ከተጠበብሽ ምታውቀውን ስለሚመክሩሽ ስለምታከብሪያቸው ጆሮ ስጫቸው ጠቢብ ሴት ምክር ሳይሆን አዲስ ሀሳብን መቃረም ነው ሚበጃት።(ካላት ላይ ለመጨመር)
በስመአብ ስትዪ ማማተብን ከራስሽ እንደምትጀምሪው
መውደድን ከራስሽ ጀምሪ እራስ ወዳድ ሳይሆን እራስሽን የምትወጂ ሁኚ ያን ጊዜ ነው ሰው ሁሉ ጀርባውን ቢያዞር ቋሚ ምትሆኚው። ምታደርገውን ምታውቅ በራሷ ምትተማመን ልባም ከራሷ አልፋም ሰውን መካሪ እንደሆንሽ አውቃለው ሰዉ ጎድቶ በሸሸ ጊዜ በምድር ስብእና እና እውነት በሰማይ ፈጣሪ ብቻ መፅናኛ ሚሆነው ሁለቱን አጥብቀሽ ጨብጪ" ብለውኝ ዉሀ ተጎንጭተው ለቁርስ ለአቢ ከተሰራው የበሶ ጭብጦ ላይ ሁለቴ ቆነጠሩ
ወዲያው አቢ 'እማሆይ' እያለ ቁና ቁና ተንፍሶ ወደ ቤት ዘለቀ ለእማሆይ ተልኮ መመለሡ ነው።
አልቃሻ እማሆይ ከአምስት አመቱ ጀምሮ ያሳድጉት የነበረ የቀዬው ህዝብ 'እማሆይ አሁንም አድጎ ይሄ ልጅ መንሰቅሰቁን አልተወም እንደው ወንድ መሆኑንስ እንጃ' ሲሏት በስተርጅና ብስል የሆነችው እማሆይ "ሳሳድገው በሚያዝንበት፣በሚከፋበት ጊዜ አልቅሰው ይውጣልህ ብዬው ነው ይላሉ።"አቤት ጥበብ! አቤት መሠልጠን! ያለቀሰ ሁሉ ከማልቀሱ በፊት ላለማልቀስ እንደጠነከረ ሰው አላወቀ... አዎ ያልቅስ ሀዘኑ ከውስጡ ታምቆ ንፁህ ስብእናውን በበቀል እንዳይ ተካው እንባ አማላጅ ይሁን እንባ ሻሪ ይሁን።እንባ ድክመት አይደለም ሀዘንን መሻሪያ ዘዴ እንጂ።
በሉ እማሆይ እንዳይረፍድብኝ ልነሳ አየመጣው አዮታለሁ ብዬ እግራቸውን ስሜ አንዳች ነገር የቀረኝ ይመስል እፊታቸው ተገተርኩኝ አይኔን አይተው የገባቸው ይመስል "ደህና ሁኚ ቸር ይመልስሽ ብለው ሸኙኝ።" አሁንም ቅር እንደተሰኘ እያንገራገርኩ ከመኖሪያቸው ወጣሁ እማሆይ ጠቢብ ናቸው አንሰላስዬ ያሳነሱብኝ ምርቃት ቢበዛ ሀሴትን ፈጥሮ ያወጉኝን እንዳልዘነጋው መሆኑ ተገለፀልኝ.......

###እማሆይን እንፈልግ አልያም ልቦናችን ላይ እንገንባቸው...###

ደራሲ : ማህሌት ገድለ ሚካኤል (NiZ)
ለዚህ ነው "ህይወትን" የማላምናት?

ለዚህ ነው "መኖር" "የሰው ስም ብቻ ነው" የምለው::

ለዚህ ነው "አለሁ" ማለት ነውር የሚመስለኝ::

ለዚህ ነው "ሳለን እንከባበር" እና " ሞትን እንቅደመው" የምለው::

እሳት ነው "ሞት" ያገኘውን ይበላል::

ጨለማ ነው "ሞት" ወደ-አለመተያየት ያስገባል::

"ሳይጨልምብን እንተያይ"

ኤልያስ ሽታኹን
የወደደ ፍቅሩን
ሸረሪትም ድሩን
እንደማያስነካ
እንዲዚያ ነኝ በቃ::

ወዶገባ ሆኖ ምርኮኛ ትካዜው
እንዲሳካ ብሎ
እውነቱን ሸጦ ነው አፍቃሪ ለጊዜው።

“እሺ” ቢል ቢዋረድ ቢናቅም ቢዘበት
"ምንም አያመጣም" ብለሽ አትሳቂበት::

ለወናፍ ዐፍ ሁሉ ቢሆን መዘበቻው
የመጣበት ቀን ግን
በፍቅሩ ልክ ነው የአፍቃሪ ጥላቻው።
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች (༒︎𝔚𝒊𝒏𝒊 ︎ 𝔚ʙℯ𝓃𝒶)
አጠር ያለ አስተማሪ መልዕክት

አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ እያለ
በመዓበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩውሰጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ  ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ,,,,,,,,ምግብ ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ

አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት
ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው ,,,,,,,እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ ፈጣሪውን ወቀሰ

እንዴት እዚህ ባህር ላይ ለብቻዬ ጥለከኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለኸኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ ብሎ አለቀሰ አማረረ,,,,,,,, ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ ,,,,,, የመርከቡ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት
ከዚያም ለመርከብ ሰዎች ጠየቃቸው !
እንዴት አገኛችሁኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣችሁ ?

አላቸው ,,,,, መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር ከዚያ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት። አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፈረስከው  ወደ ትልቁ ቤቴ ልትወሰደኝ ነው አለ

አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ፈጣሪንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ጊዜ መጠጋት
ያለብንን አንድዬን እንረሳለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን ።ያጣነውን የሰጠን እግዚአብሔርን አእምሯችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን እግዚአብሔርን እንደ ቅዱሳን በእምነት መፅናትን ያድለን አሜን

💚 @eotcy 💚
💛 @eorcy 💛
❤️ @eotcy ❤️
የኛ ግጥም ና ታሪክ pinned «አጠር ያለ አስተማሪ መልዕክት አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ እያለ በመዓበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩውሰጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ  ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ,,,,,,,,ምግብ ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል…»
🐘እንደ ዝሆን ድዳ አትሁን…‼️

የዝሆን ግልገል ከልደቱ ጀምሮ በትንሽ ቦታ ውስጥ እንዲሆን ይሰለጥናል። አሰልጣኙ መሬት ላይ በተተከለ እንጨት ላይ የትንሹን ዝሆን እግር በገመድ ያስረዋል። ይህም የትንሹ ዝሆን የምቾት ቀጠና ነው። ትንሹ ዝሆን በመጀመሪያ አከባቢ ገመዱን ለመበጠስ ይሞክራል። ገመዱ ግን ጠንካራ በመሆኑ ትንሹ ዝሆን ገመዱን መበጠስ እንደማይቻል ይማራል። በገመዱ ርዝመት በተለካ አካባቢ ብቻ ተወስኖ መኖር ይማራል።

ዝሆኑ በቀላሉ ገመዱን ለመበጠስ የሚችልበት እድሜ ላይ ሲደርስም ለመበጠስ አይሞክርም። ምክንያቱም ገና በልጅነቱ ገመዱን መበጠስ እንደማይችል ተምፘልና። በዚህ መንገድ ትልቁ ዝሆን በጣም በቀጭን ገመድ መታሰር ይችላል።

ምናልባት ይህ አንተን ይገልፅህ ይሆናል። ልክ ዝሆኑን ባሰረው እይነት ቀጭን ገመድ አሁንም በምቾት ቀጠናህ ውስጥ ታስረህ ይሆናል። እነዚህ ያሰሩህ ቀጫጭን ገመዶች ደግሞ በልጅነትህ የተቀበልካቸው እንቅፋት የሆኑ እምነቶችና ምስሎች ናቸው። ይህ የሚገልፅህ ከሆነ መልካም ዜና አለ። ይኸውም የምቾት ቀጠናህን መለወጥ ትችላለህ። እንዴት ለዚህ ሶስት የተለያዩ መንገዶች አሉ፤

1️⃣ የምትፈልገውን እንዲገኘህ፤ እንደ ስራህና ነገሮች በፈለግከው መነገድ እያሄዱልህ እንደ ሆኑ ማረጋገጫና አውንታዊ የራስ ጋር ንግግር መጠቀም ትችላለህ።
2️⃣ የምትፈልገውን ስታገኝ፤ ስትሰራና ስትሆን ያለ አዲስ አስገዳጅ ኃይል ውስጣዊ ምስል መፍጠር ትችላለህ።
3️⃣ በቀላሉ ባህርይህን መቀየር።

እነዚህ አቀራረቦች ከአሮጌው የምቾት ቀጠናህ ያወጡሀል።
....................

አንዳንዴ ሀሳባችን ወደ የት እንደሚሄድ አናውቀውም ለሆዳችን ቀን በቀን ምግብ እንደምንመግበው ሁሉ አዕምሮአችንም ከቀን ወደ ቀን ስልጠናዎች እንዲሁም ፍሬ ነገሮች ያስፈልጉታል ስንቶቻችን ነን እዚህ ምድር ላይ ለሆነ አላማ እንደተፈጠርን የምናውቀው?🧐 ስንቶቻችን ነን ስለተፈጠርን ብቻ እየኖርን ያለነው?🧐ስንቶቻችን ነን ህይወታችን ውስጥ የተሰጡንን ሴኮንዶች እየተጠቀምንባቸው ያለነው?🧐🧐🧐


ከምንም አይነት ነገር በፊት እራሳችን ላይ መስራት ያስፈልገናል። 😊😊😊

💥⚡️ልናማክርሽ እንፈልጋለን እንዲሁም እኔ ከአሁን ጀምሮ የእውነት የሚገባኝን ህይወት መኖር እንፈልጋለው ለምትሉ እህት ወንድሞቼ ከስር ባለው የቴሌግራም እንዲሁም ኢንስታ አካውንቴ inbox ልታናግሩኝ ትችላላቹ⚡️💥

Telegram...... @Nizan5
Instagram...... nizan9336

######growth######
######Life########
2025/02/05 08:04:38
Back to Top
HTML Embed Code: