"አለማወቅ ስህተት አህደለም።ስህተትም ስህተት አይሆንም።አይሆንምም ብሎ ማመንም እራሱ ስህተት ነው።"
እንዲህ ያለው ወዳጄ ልክ ነው።አለማወቅ ስህተት ከሆነ ሁሉም ፍጡር ካለማወቅ ሰፈር ተሰዶ የመጣ ነው።ጨለማ የወረሰውና ይነገሰበት የሰው ልጅ ከብርሀን አፀድ ዘልቆ ለመታየት የግዜ ጥርቅም ያስፈልገዋል።እነዚህን ግዜያት ደግሞ ለማወቅ ያልቋመጠበት ሂሊና ካለው፣እንደቃጭል የሚቅጨለጨል ባዶ ጭንቅላት ከሆነ የሸከመው፣በትናንቱ ዛሬን የሚኖር ከሆነ የዚ ሰው አለማወቅ ስህተት ነው።አለማወቅ ስህተት የማይሆነው የስሜት ህዋሶቹ ስንት እንደሆኑ ለይቶና ጥቅማቸውን ከተገነዘበበት ቀን ጀምሮ ካለው ግዜ በፊት የሱ አለማወቅ ስህተት አህደለም።
ስህተትም ስህተት አይደለም።1+1=2 የሚለውን ለማወቅ ሞክረን ብንሳሳት ስህተታችን የኛ ስህተት ሊሆን አይችልም።የኛ ስህተት አለማወቃችንን ነው የሚጠቁመው።ስህተት የሚባለው አእምሮአችን ለማወቅ ጥሮና ጠርጎ እንዲሁም ለነገሩ ተመሳሳይ ፍንጭ ካወቀና ከተረዳ በሆላ ቢሳሳት እውነት ነው ስህተታችን ነው ብለን እንቀበላለን።ነገር ግን ቁዝምዝም ወዳ ፍየል ወዲ ሀኖ ለፍየሎ ስብራት የኛ አእምሮ ተሳስተሀል ልንለው አይገባም።
ስህተትን እራሱ ስህተት አይሆንም ብለን ልናምንም አይገባም።👍 የሰው ግን ተመቸኝ ነብይ ነው እንዴ😜 በአንተ እሳቤ ልክ ነው ብለህ ያመንክበት ሎጂክ በኔ ደግሞ ልክ ላይሆን ይችላል።ዶሮ ነው ብለህ ያሳየህኝን ለኔ NO ብዬ ይሄ ሰጎ ነው ልልህ እችላለው።ደግሞም ባቆሜ ስለፀናው ደረቅ፣የማይገባህ፣አህያ አትበለኝ።ካልክማ እኔ እንደውም ካንተ አይነቱ እውቀት ሳይሆን ድርቀት ነው የሚጠበቀው ብዬህ ልሄድብህ እችላለው።
አዎን! ይቺ አለም ከመለኮታዊ መፅሀፍ ስር ካላየናት ሁላችንም ልክ ነን።ልክ አይደለህም ለሚለን ሂሊናችን አምኖ ካልተቀበለው በቀር ሆላ ልንቆጭበት እንችላለን።የኔ ሀሳብ፤የኔ ብቻ ሀምንለው ነገር በዚ ምድር የለም።ያንተ ሀሳብ ልክ ነው የኔ ሀሳብ ልክ አይደለም የምንለው አንፃራዊ እንጂ ሌላ አይሆንም።ሀአንድ ነገር ብይን የሚገኘው።ሊለወጥ ሊሻር ሊበለጥ ሊደለዝ ሊሰለች ከማይችል አንድ ነገር ኖሮን የኔና ያንተን ሀሳብ ከሱ ጋር ተፋርደን በምናገኘው ፍርድ ነው እንግዲ የኔ ልክ ያንተ ስህተት የምንለው።
ከዛ ውጭ የምንፋረድበት ነገር ሁሉ የሚሻር፣የሚለወጥ በመሆኑ ፈራጅ አይሆነልም።ለምን ብትሉ ነገ የኛ ሀሳብ እራሱ ግዜ አግኝቶ ፈራጅ ሊሆን ይችላልና። ስለዚህ ፈራጅ በለለበት ልክ ነኝ ማለቱ ልክ አይሆንምና ሁላችንም ልክ ነን።ሁላችንም ስህተት ነን።
ላስታሀትዎ 👇
@Abdelhakim42

የፈላስፋው ጥመት...
፨፨፨
የጠርጣሪነት ፍልስፍና (scepticism) ጀማሪ እንደሆነ የሚታመንለት የጥንቱ ፈላስፋ ፊሮ አንድ ቀን ጥበብን ያካፍላቸው ዘንድ ወደጋበዙት ሰዎች በማለዳ አመራ። በቦታው ሲደርስ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ተሰብስቦ ሲጠብቀው ተመለከተና ወደተዘጋጀለት የከፍታ ቦታ በዕርጋታ ወጥቶ ቆመ። ፊሮ ትምህርቱን ከመጀመሩ በፊት ጥያቄ ወረወረ፦
<<ዛሬ እዚህ የተሰበሰባችሁት ከእኔ ልትማሩ ነው?>> ተማሪዎቹ በአንድ ድምፅ አዎንታቸውን ገለፁ።
<<እንግዲያውስ ስለምን እንደማስተምር ታውቃላችሁ ማለት ነዋ?>> አለ ፊሮ።
<<ኧረ ምንም አናውቅም>> አሉ ተማሪዎቹ አሁንም በአንድ ድምፅ።
<<ስለምን እንደማስተምር ካላወቃችሁማ ዝም ብዬ ማውራት አልፈልግም>> አለና ከመድረኩ ወርዶ ወደ ቤቱ አመራ።
በነጋታው አሁንም በዚያው ቦታ ህዝቡ ተሰብስቦ ይጠብቀው ጀመር። ፊሮም መጣና በእርጋታ ወደ መድረኩ ወጣ።
<<ዛሬስ ስለምን እንደማስተምር አውቃችኋልና?>> በማለት ጠየቀ።
የተሰበሰበው ህዝብ በአንድ ቃል አዎንታቸውን ገለፁ።
ፊሮም <<ካወቃችሁትማ ወደ ቤቴ ልሂድ....>> በማለት ከከፍታው ላይ ወረደ።
በሚቀጥለው ቀን ወደ ቦታው ሲያመራ አሁንም ህዝቡ ተሰብስቦ እየጠበቀው ነው። የዚያን ቀን ግን ህዝቡ መልሳቸውን አዘጋጅተው ነበር የጠበቁት።
ፊሮም ወደ ከፍታው ከወጣ በኋላ፦<<ዛሬስ ስለምን እንደማስተምር ታውቃላችሁ..?>> አለ።
ህዝቡም፦<<ግማሾቻችን እናውቃለን፤ግማሾቻችን ደግሞ አናውቅም...>> አሉት።
ፊሮም፦<<እንግዲያውስ ግማሾቻችሁ የምታውቁት፤ ለግማሾቹ የማያውቁት ንገሯቸው!..>>
ምንጭ ፦ ጥበብ ከጲላጦስ
፨፨፨
፨ አሁን በእናንተ አረዳድ በፈላስፋው ላይ ነው ወይስ በተከታዮቹ ላይ ነው የሚፈረደው...?
ለሀሳብ አሥተያየትዎ
👇👇👇
@SSR60 ወይም
@abdu23 ላይ ይጠቀሙ !!!!
@phillosophy @phillosophy

እንደስነ_ልቦነ አሁን ላለበት የአንድ ሰው ባህሪ ትልቁን ገፀ ባሕሪ የሚጫወተው ባከባቢው የሚደረሱ ድርሰናት ናቸው ይላሉ።
@Abdelhakim42
@Abdelhakim42
ይሄውልህ
ዘላለማዊነት በፍልስፍና ሲመዘን
/ክፍል ፩/
📜📖📖📜
በፍልስፍናው ዓለም አንቱ ተብለው ታላቅ ከበሬታ እስከዛሬ ከሚቸራቸው ፈላስፎች አንዱ ፕሌቶ ነው ። " ከሞት በኋላ ሕይወት አለና ተፅናና " ቢሉት " እኔ ዘላለማዊ የምሆነው ገነት በመግባት ሳይሆን ምድር ላይ ትቼው በምሄደው ሥራዬ ነው " አለ ።
📖📖📖
ብዙዎች ከሞት በኋላ ሕይወት " በመኖሩ " ይፅናናሉ ። አንዳንዶች ደግሞ የለም ዘላለማዊ ሕይወት ብሎ ነገር የለም ይላሉ ፤ እንዲያውም በእንዲህ ዓይነቱ ሐሳብ ይሳለቃሉ ። ፊሮ የተባለው ፈላስፋ ደግሞ " እኔ የዘላለም ሕይወት ከሞትኩ በኋላ የማገኝ ከሆነ ውሻዬ ለምን ይቀርበታል? " ይላል " እንዲያውም በዘላለም ሕይወት መለኪያ ውሻዬ እንደ እኔ እያታልልም ፣ አይክድም ፣ አይሰርቅም ፣ አይዋሽም...ወዘተ..ስለዚህ ከእኔ ይልቅ በብዙ መመዘኛ ውሻዬ ለዘላለማዊ ሕይወት የተገባ ነው " ብሏል ።
📖📖📖
ብ ዙዎቹ ፈላስፎች የዘላለም ሕይወት አሊያም ከሞት በኋላ ሕይወት የሚለው ሃሳብ መሠረቱ ሕንድ እንደሆነ ይናገራሉ ። ቱስካሮራ የተባሉ የሕንድ ጎሳዎች " አንድ ሰው ሲሞት ሟቹ መልካም ሰው ከሆነ ወደ አንድ የመንፈስ ዓለም ይወሰዳል ፤ በዚያም የአደን አውሬ ታድኖ የማያልቅበት ዓለም ውስጥ ይገባል " ሲሉ " ሟቹ ክፉ ከነበር ደግሞ ምግብ ከሌለበት እባብ ከሚርመሰመስበት ዓለም ውስጥ ይወድቃል " የሚል ነው እምነታቸው ።
፧
ከዚያ ቀጥሎ ግብፆች ይነሳሉ ። ጥንታዊ ግብፃውያን እዚህ የምንኖርበት ቤት ወደፊት (ከሞት በኋላ) ከሚጠብቀን ቤት ጋር ሲነፃፀር እንደ ትንሽ ጎጆ ነው ይላሉ ። ( ይኸ እንግዲህ አሁን በጎጆ ውስጥ የሚኖርን ሰው አይመለከትም ) !
📖📖📖
ከሞት በኋላ ሕይወት አለ የሚለው አስተሳሰብ ምንጭ ናቸው ተብለው የሚታመኑት ሕንዶች በሌላው የእምነት ክፍላቸው ደግሞ " ከሞትክ በኋላ ነፍስህ በሌላ ዓለም በድሎት ፣ ወይም በችግር ራሷን ችላ አትኖርም ፣ ነገር ግን እንደ ሰራኸው ሥራ በሌላ ፍጡር አካው ውስጥ ትገባለች እንጂ " ይላሉ ።

<< ቀስትህን እስከመጨረሻው ካልሳብከው ዒላማው ውስጥ ሄዶ እስከመጨረሻው አይገባም፤ ዕውቀትን የሚሻም ተማሪ እስከመጨረሻው የሚተጋ ብቻ ነው... >>
/ ሜንሲየስ /
ለማወቅ ጉጉት ያለን ሰዎች እንኖራለን እስከመጨረሻው ማወቅ የምንፈልግ ግን ጥቂቶች ነን...ዕውቀት ገደብ የለውም በእርግጥ ግን ማወቅ ለፈለግነው ነገር ጊዜአችንን ትኩረታችንን እና ሙሉ አቅማችንን የምንሰጠው ስንቶቻችን ነን...? ባብዛኛው እኛ እናቀዋለን የምንለው ነገር ላይ እራሱ ከውስጡ ማወቅ የፈለግነውን ያህል ብቻ እየያዝን ሌላውን መሬት እየጣልን አይመስላችሁም የምንጓዘው...?
፧
እራሳችንን የሰጠንለት እውቀት የትኛው ነው...?
እናውቀዋለን የምንለውንስ ምን ያህል የራሳችን አድርገንዋል...?
የጥያቄ ጋጋታን ያስከተልኩባችሁ አለምክንያት አይደለም...አበው " አንድን ነገር በከፊል ከማወቅ ጭራሹኑ አለማወቅ ይሻላል " ይላሉ ይህንን ፍልስፍናቸውንም ታላቁ ጀርመናዊ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼም ይጋራቸዋል...እንዲህ ሲል.." Its better to know nothing than half knowing many ting "... ሲል ታድያ በዚህ ዙርያ የኛ እይታስ ምን ይሆን...?
ራስን መጠየቅ ይቀድማልና እስቲ ከራሳችን ጋር እንወያይበት...!!

" ትክክለኛ እውቀት ማለት የራስን የድንቁርና መጠን አልያም ስፋት ማወቅ ነው። "
/ ኮንፊሽየስ /
ዕውቀት ውጪያዊ የሆነና ከውጪ የምንቃርመው የሚመስለን ብዙዎቻችን ነን...ግን የእውቀት ባለቤት እኛው ነን...'የሰው ልጅ የሚማረው #የጠፋበትን አእምሮ ለማስመለስ ነው' የምትል የቆየች አባባል አለች...እውቀትን እና የእውቀትን ፍለጋ ይሄ በሚገባ የሚገልጸው ይመስላል ።
፧
፨ መረጃ የእውቀት ግብአት ቢሆን እንጂ በራሱ እውቀት አይሆንም...ምክንያቱም መረጃ ማለት ከውጪ የምትሰበስበው ውጫዊ ነገር ነውና...ትምህርት ማለት ልክ ያንቀላፋ አዕምሮን እንደማንቃት ነው። ይህ ማለት ግን አንቀላፍተን ተፈጥረናል ማለት አይደለም...ማሰብ እንደምትችል ያወቅህ እና ያሰብህ ሰዓት የሁሉም ነገር መነሻው ያንተ አእምሮ እንደሆነ ትደርስበታለህ ። ማይምነትን ልትፈራው እንጂ ልትጠላው አይገባም...ማይምነትህ መነሻህ ነውና ማይምነትህን ካላወቅህም ወደማወቅ መንገድ አትጀምርምና።
፧
፨ ስንጠቀልለው "የራስህን የድንቁርና መጠን ስታውቅ ያኔ ትክክለኛ እውቀት ይኖርሃል" ሲል ኮንፊሺየስ ያስቀመጠው በተለይ ቁንፅል መረጃን እና እውቀትን ያደባለቁ ሰዎች ፤ ወይም የራሳቸው ማይምነት ወደ እውቀት የመራቸው መሆኑን የዘነጉ ሰዎች ወይም በሌላ አገላለፅ ጥራዝ ነጠቅ ወሬን እንደ ጥልቅ እውቀት ቆጥረው ሰው ላይ የንቀት እና የስድብ አጀብ የሚያወርዱትን አዋቂ መሳዮች መጀመርያ የራሳችሁን ድንቁርና እውቁት ሲላቸው ነው ።
ምንጭ ፦ Philosophical Megazines
Via ከፍልስፍና አለም

" የህመም ስሜት የማይሰማው ማንነት የደነዘዘና መታመሙን እንኳ ሳያውቀው የሚያልቅለት ማንነት ነው "
(ዶክተር ኢዮብ ማሞ)
ምክረ መጽሐፍ...
፨፨፨
፨ ሙሉ መፍትሄ ማንም ሰው ጋር እንደሌለ እወቅ ፨
በአለም ላይ ላለው ችግር በሙሉ ሙሉ መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል ሙሉ ብቃት ያለው አንድም ሰው የለም። ለአንዱ ያስቸገረው ለሌላው ቀለል ብሎ ይገኛል። ምዕራባውያን የሚቸገሩባቸው እኛ አፍሪካውያን ግን ከምንም የማንቆጥራቸው በርካታ ሁኔታዎች አሉ። በተቃራኒውም ለእነሱ የቀለሉ ለእኛ ደግሞ ያስቸገሩን ብዙ ሁኔታዎች አሉን። ይህንን ነጥብ ወደ ግልህ ስታወርደው እውነታው አይለወጥም። ይህንን እውነታ በሚገባ መገንዘብ በአካባቢህ ላሉ ችግሮች ሁሉ የመፍትሄ ሃሳብ አንተ ጋር ብቻ እንደሌለ ወደ ማስተዋል ትመጣ ይሆናል። ውጤቱ ፦ ይህንና ያንን ለመለወጥ ከመሯሯጥ በፊት ትኩረትን ራስን መለወጥ ላይ ማድረግ።
፧
፨ የመፍትሄው እንጂ የችግሩ አካል አትሁን ፨
በእያንዳንዱ ሕብረተሰብ ውስጥ ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። የችግሩ አካል የሆኑና የመፍትሄው አካል የሆኑ። የችግሩ አካል የምንላቸው ሰዎች፣ በአንድ ጎኑ ለተከሰቱት ችግሮች መንስኤ የሆኑትን ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ያለውን ችግር በማጋነን ሃሳብ ከመስጠት ያለፈ ነገር የማያደርጉ ናቸው። የችግሩ አካል ለመሆን የግድ ችግር ፈጣሪ መሆን የለብንም። ችግርን ማራገብ፣ ተወቃሽን መፈለግ፣ መፍትሄ እንደሌለ ማውራትና የመሳሰሉት አጉል አመለካከቶች ሁሉ አንድን ሰው የመፍትሄው አካል ከመሆን ይልቅ የችግሩ አካል እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው ዝንባሌዎች ናቸው ።
(ትኩረት....ገጽ 145)
፨ አለመመቸትን አትሽሸው ፨
የአለማችንን ሁኔታ በመሸሽ የሚኖሩ ሰዎች ምንም ነገር የማይገነቡ ሰዎች ናቸው። አንዳንድ ሰዎች የማይመችን ሁኔታ በመሸሽ ነው የሚኖሩት። ወደ አንድ ስራ ይገባሉ፣ ትንሽ ከሰሩ በኋላ የመጀመርያው የማይመች ሁኔታ እንደተከሰተ ጥለው ይሄዳሉ። መስራትና መኖር ስላለባቸው ብዙም ሳይቆዩ ሌላኛው መስሪያ ቤት ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል። ችግር የሌለበት የማህበራዊ ህይወት እንደሌለም በዚያም ቦታ እንደገና ማየት ይጀምራሉ። እንዲህ እያሉ ከአንዱ ስራ ወደ ሌላው፣ ከአንዱ ሰፈር ወደ ሌላኛው፣ ከአንዱ ወዳጅነት ወደ ሌላኛው በመዘዋወር በዚህ አለም ላይ ተፈልጎ የማይገኝን ከችግር ነፃ ሁኔታ ሲፈልጉ እድሜያቸውን ይፈጃሉ።
፧
፨ ምቾትን አትመነው ፨
አንድ ሰው ወደ ሃኪም ሄዶ ሙሉ ስለሆነ ጤንነቱ ሲነግረው፣ "ጤናማ ከመሆኔ የተነሳ ቢቆነጥጡኝ እንኳ አያመኝም" ቢለው ሃኪሙ በቀጥታ ከፍተኛ ምርመራን ነው የሚያዝለት። የህመም ስሜት የማይሰማው ማንነት የደነዘዘና መታመሙን እንኳ ሳያውቀው የሚያልቅለት ማንነት ነውና። ምንም እንከን የማይገኝለትን ሁኔታ ሲፈልግ የሚኖር ሰው ያንን ሁኔታ በፍጹም እንደማያገኘው ሁሉ፣ "ሁሉም ተመችቶኛል፣ ምንም ችግር የለብኝም" የሚል ሰውም ከተጠራቀመና የኋላ ኋላ አጥፊ ከሆነ ችግር አያመልጥም። ችግርና አለመመቸት የራሱ ተጽእኖ እንዳለው ሁሉ ምንም አይነት አለመመቸት የሌለው ሁኔታም የራሱ የሆነ መዘዝ አለው።
(ትኩረት...ገጽ 149-150)
፨፨፨፨
ምንጭ ፦ ትኩረት/Focus
ዶክተር ኢዮብ ማሞ
...ትኩረት...መነበብ ያለበት መጽሐፍ ነው ብታነቡት ስል እጋብዛለሁ መልካም ቀን...!

የዛሬው የመጽሐፍ ግብዣችን...
ሱፊዝም
📚📚📚
ሱፊዝም መሰረቱ የእስልምና ሐይማኖት ይሁን እንጂ በተከታዮቹ ዘንድ ሁሉም ሀይማኖት እኩል እና ወደ አንዱ ፈጣሪ የመድረሻው የተለያዩ መንገዶች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡‹‹ የእኛ ስራ ፈጣሪን ማፍቀር ፣በዚህም ማንነቱን እና ምንነቱን በምድራዊ ህይወታችን መግለጥ ነው›› የሚሉን ሱፊዎች ከዚህ ተሻግረን ስለገነት እና ሲኦል መጨነቅ በፈጣሪ ስራ ጣልቃ እንደ መግባት ይቆጠራል፡፡›› ይላሉ ፡፡
ይህ የሱፊዎች አስተምህሮት ሁሉምንም ሐይማኖቶች የሚስማማ አስተምህሮቶች እንዳሉት ሁሉ ለእያንዳንዳችን መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ እድገታችንን የሚያበለጽግ የህይወት ቅመሞች አሉት ፡፡ ሲፊዝም መጽሀፉ ቀልድ ፤ ወግ እና ተረት አስመስሎ ብዙ ቁም ነገሮችን በመያዙ ሙሉ በሙሉ ብወደውም ከዚህ በታች ባለው ርዕስ የተካተተው መልዕክት ግን በጣም አስተምሮኛል፡፡
፧
‹‹ፈጣሪ የሰጠህን ተፈጥሮ ሰው እንዲያስተምርህ አትሰሻ››
አንድ ቀን የሱፊው ሩሚ ደቀ መዝሙራቸውን በከፍተኛ ሀዘን ተውጦ ተመለከቱት እና ምን እንደሆነ ይጠይቁታል ፡፡ ደቀ መዝሙሩም የቁዘማውን ምክንያት ለመመህሩ ከነገሩ በኃላ ቁዘማቸውን መቀጠላቸውን ሲመለከቱ፡
‹‹ ወዳጄ የልብን ሀዘን የፈጣሪ የማንነቱ ብርሀን የሚገባበት ሽንቁር ነውና አትጥላው፡፡›› የሚል መጽናኛ ነገረውት አለፉ፡፡ በሱፊዎች እምነት ከደስታ ይልቅ ሀዘን ፈጣሪን የመቅረቢያው መንገድ ነው፡፡እንዲውም ሀዘን ፈጣሪን ለማዎቅ ካልተጠቀምንበት ፈጽሞ መወገድ ይገባዋል ይላሉ፡፡ ይህንን ከህይወት እውነታም በመነሳት ሲያረጋግጡልን ‹‹ አንድ ነገር በማጣትህ ለሀዘንህ ምክንያት ቢሆን እንኳን በሌላ መንገድ ወደ አንተ ተመልሶ መምጣቱን እርግጠኛ ሁን›› በማለት ነው ፡፡
፧
አንድ ሰው እውነተኛ ደስታውን መግለጽ የሚችለው መቼ ነው? በማለት በደቀመዝሙራቸው የተጠየቁት ሩሚ እንዲህ መለሱለት ይባላል፡፡‹‹ሀዘን ሲጋጥምክ ደስተኛ ሆነክ ደንስ ፡የችግር ሰንሰለት ዙሪህ ሲጠመጠም ደንስ፡ ከሰዎች ጋር ግጭት የምትገባበት ሁኔታ ሲጋጥምክ ደስታህን ምርጫ አድርገህ ደንስ፣በመውደቅህ ደንስ ፣በመከራህ ደንስ፣በነጻነትህ ደንስ …..ይህን ማድረግ ስትችል ብቻ በእውቀት የነቃህ እና የፈጣሪ ብርሀን የበራልክ መሆኑን ታሳያለክ›› አሉት፡፡
በሌላ ጊዜ ደቀ መዙሙሩ እንዲህ ጠየቀ ፡፡ ፈጣሪን ማመስገን እፈልጋለሁ እና እንዴት ማመስገን እንደሚገባኝ ያስተምሩኝ;
ሩሚ ጠየቁት፡ የወፎች ዝማሬ ሰምተህ ታውቃለህ?
ደቀ መዝመሩ ፡ በሚገባ መመህር ሆይ ዘወትር ማለዳ እሰማለሁ፡፡
ሩሚም፡ ዎፎች ስለድምጻቸው ማማር የሚጨነቁ ይመስልሀል?
ደቀመዝሙሩም ፡ በፍጹም መምህር ሆይ ሲል መለሰ
ሩሚም ፡ አየህ ፈጣሪን እንዴት ማመስገን እንዳለብኝ የተማርኩት ከወፎች ዝማሬ ነው ፡፡ ወፎች የማለዳ ዝማሬን በተፈጥሮ የተቀበሉት እና ይህንኑ የሚፈጽሙ ፍጡሮች ናቸው፡፡ስለድምጻቸው ማማርም ሆነ ማስጠላት አይጨነቁም፡፡እኔም ፈጣሪዮን ለማመስገን የተቀበልኩት ድምጽ ከበቂ በላይ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ምስጋናዬን ሳቀርብ ሰዎች ምን ይሉኛል ወይም ሰዎች ይተቹኛል ብየ አላስብም ፡፡ እናም ፈጣሪ የሰጠህን ሰው መልሶ እንዲያስተምርክ አትሻ››በማለት አሰናበቱት ፡፡
📖📖📖
ምንጭ 📖 ሱፊዝም
✍ ከጲላጦስ( ሀይለጊወርጊስ ማሞ )
ኅትመት ፦ 2007ዓ.ም
፨ አንብቡት ቆንጆ መጽሐፍ ነው...
Credit to ፦ Seido Bob
@phillosophy @phillosophy @phillosophy

1. "ማሰብ አቁም ፥ የችግርህ ሁሉ ማቆሚያ እዚያ ላይ ነው !!
ማሰብ እንግዲህ መልኩና አይነቱ ብዙ እንደመሆኑ መጠን " # የነፍስ ሃሳብ #" ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ይሆናል ። እኛም በዋነኛነት ለአሁኑ ጉዞአችን እሱኑ እየያዝን ብንመለከት የማሰብን አታካች መንገድ ለመዝለቅ የሚያስችለን ይሆናል። ቀዳሚው "# ማሰብ " ስለነገ አብዝቶ በማሰብ የተጠመዱትን ይመለከታል ። የነገ ሃሳብና ይህም ሃሳብ የሚፈጥረው ጭንቀት እንዴት የሂዎት መገለጫችን እንደሚሆን ቀጣይዋን ወግ እንመልከት እና ወደ ጠለቀው ሚስጥር እንሻገራለን ።
ምንም እንኳን ሸክርፔር " መልካምና መጥፎ የሚባል ነገር የለም ፥ ነገር ግን ሃሳባችን እንደዛ ያደርገዋል፡ " ይበለን እንጅ የሰው ልጅ መላክም እና መጥፎ ሃሳብን የመምረጥ መብት ግን አስቦ እንዲወስን እንደተሰጠው አንዘነጋም ፡፡ የትኛውንም ሃሳብ በምርጫችን እናስብ ይህ ሃሳብ ግን ውሎ አድሮ በሂዎታችን እውን መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ከሩቅ ምስራቅ ሃገራት ያገኘናት ወግ ይህንኑ የምታሳይ ናት፡፡
በምድር ላይ ከሚሳቡ የትላትል ዘሮች አንዱና አስደናቂ አፈጣጠር የሚታይበት #መቶ እግር # የሚሉት ነው። ይህ ትል አስደናቂነቱ መቶ እግር ብቻ የታደለ መሆኑ አይደለም፡፡ ከዚያ በላይ ግን እኒዚህን መቶ እግሮች በንድ ጊዜ አንቀሳቅሶ ሲራመድ አንዳች ግራ መጋባትም ሆነ መደናቀፍ አጋጥሞት አያውቅም ። ይሁንና አንድ ማለዳ ይህ መቶ እግር እንደተለመደው በአትክልቱ ስፍራ እግሩን ሲያፍታታ የተመለከተች አንዲት ጥንቸል"በጣን ይደንቃል ! ይህ ትል በቅጽበት ችግር ውስጥ በግባቱ አይቀርም ። ይህን ሁሉ እግር ይዞ ሲራመድ እንዴት ግራ አይጋባም ?? ለመሆኑ የትኛውን ከየትኛው አስቀድሞ መራመድስ እንዳለበትስ እንዴት ያስታውሳል ? " በማለት ማሰብ ጀመረች ። በፍጥነትም ወደ መቶ እግሩ በመቅረብ " ወዳጄ እኔ በፍልስፍናዊ አስተሳሰብ የተያዝኩና እውነትንም በመጠየቅ የተጠመድኩ ተማሪ ነኝ" በማለት ራሷን አስተዋወቀች ፡፡
"መቶ እድርም " መልካም ነው ታዲያ ምን ልርዳሽ ? አለ ። በዚህ ጊዜ ጥንቸል በማቅማማት " እኔ እንኳን ስለዚህ እግሮችህ አስበህ ታውቅ እንደሆነ ልጠይቅህ ፈልጌ ነው ፥ ለመሆኑ መቶ እግሮችህን በአንድ ጊዜ አንቀሳቅሰህ ለመራመድ የቻልከው እንዴት ነው ? " ስትል ጠየቀችው ።
በዚህ ጊዜ መቶ እግር " ስለዚህ ነገር ፈጽሞ አስቤው አላውቅም ነበር ፥ እንዲሁን ሌላ እንደ እኔ አይነት መቶ እግርም ይህን አስቦት እንደማያውቅ እርግጠኛ ነኝ ። በእምነት መጽሃፋችንም ስለዚህ ጉዳይ የተባለ ነገር እንደሌለ አውቃለሁ ። እግራችንን ግን ያለ አንዳች ችግር ስንጠቀምበት ኖረናል ። ይሁንና ጥያቄሽ ተገቢና ላስብበት የሚገባ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ። ከእንግዲህ የኔ ሃሳብ በዋናነት ስለ እግሬ ይሆናል " አላት ።
ይሁንና " መቶ እግር " ይህንን ተናግሮ ጉዞውን ለመቀጠል ሲሞክር አንዱ እግር ከሌላው እየተጋጨ መውደቅ ጀመረ ። በዚህ ጊዜ በጣም በመናደድ ወደ ጥንቸሏ ዞሮ " እባክሽን ይህን ፍልስፍናዊ ጥያቄሽን ከእንግዲህ ለየትኛውም መቶ እግር እንዳታነሽ ። እነሆ ጥያቄሽ አንድ ጊዜ ወደ አእምሮየ በመግባቱ እያንዳንዱን እርምጃ ለመራመድ እግሮቸን ሳንቀሳቅስ በቅድሚያ እሱን ማሰብ ግድ ሆኖብኛል ። ከዚህ ቦሃላ የኔ ሃሳብ ያንችን ጥያቄ በመርሳት ላይ የተጠመደ ይሆናል ። አእምሮየ መርሳት ካልቻለ ግን መራመድ አበቃልኝ " በማለት መቶ እግር እየወደቀ ፥ እየተነሳ ጉዞውን ቀጠለ ።
የሰው ልጅ የሃሳቡ ውጤት ነው ፡፡
ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ( 2)
ገጽ 24 - 26
እና ምን ለማለት ነው ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በሂዎታችን ገብተው ማሰብ የማንፈልገውን እያሳሰቡ የምፈልገውን ነገር ሊያሳጡን ይችላሉና ፥ ማሰብ ስለሚገባን ብቻ እናስብ !
ይቀጥላል
ለማንኛውም ሃሳብ አስተያየታቹ
👇👇👇👇
@SSR60

ፍልሥፍናና የህይወት እውነታ
Notes_200102_045735_65d.pdf
ከላይኛው የቀጠለ ሃሪፍ ነገር ነው አውርዳቹ አንብቡት
እያነበባቹ ስለሆነ ከልብ እናመሰግናለን
ሃሳብ አስተያየታቹ አይለየን ብለናል
@SSR60 👈👈 ብታደሱን ለማስተካከል ይረዳናል እና የዘወትር ትብብራቹ አይለየን 🤙🙏🙏🙏

1. "ማሰብ አቁም ፥ የችግርህ ሁሉ ማቆሚያ እዚያ ላይ ነው !! (2)
አሁን ላነሳው የምፈልገው ሃሳብ ደግሞ ሌላው ሰው ለእኛ የሚያስበውን "ሃሳብ" በማወቅ ፍላጎት ይገለጻል ። በምድራዊ ህይዎታችን ዙሪያ የምናገኛቸውን ሰዎች ስለእኛ ምን እንደሚያስቡ ከግምት ባለፈ እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ያስቸግራል ። እናም የዘወትር ሃሳባችን ከመልካሙ ነገር ይልቅ በከፋው ገጠመኛችን የተጠመደ ሆኖ እንደ አስጨናቂ ህልም በየቅጽበቱ የሚያባንን መከራ ይሆንብናል ። ሂዎት ከተቸረችው የአበባ ገጸ በረከት ይልቅ ለአእምሯችን ቅርብ የሚሆንብን እሾሁ ነው ። ስለ አበባው ማንስ ግድ ይለዋል ?? ፡፡ ከወዳጅህ ይልቅ ጠላትህን ማሰብ ትልቁ ስራህ ነው ። የአእምሮህን የእስከዛሬ ድርጊት ለአፍታ መለስ ብለህ በትግስት ብታስበው የምትወዳቸውን ሳይሆን የምጠላቸውን በማሰብ የቱን ያክል ተጠምዶ እንደኖረ መረዳት ትችል ነበር ። የሰው ልጅ አእምሮ መርሳትን ጸጋው አድርጎ ቢቀበለውም ይህ ጸጋ ግን ለወዳጆቹ እንጅ ለጠላቶቹ እንደማይሆንም መረሳት የማያሻው ለዚህ ነው ። አእምሮውን ለመልካም ያዘጋጀ በአንጻሩ ውበትን ለመመልከት ፥ ከአበባው በረከትም ለመቋደስ የሚቸግረው አይሆንም ። አእምሮ በተቀደደለት የሃሳብ ቦይ ሲፈስ እንዲሁ የሂዎት ልምዱን ከተዋበው ገጠመኙ እየሰበሰበ መጓዝ ከቻለ ዙሪያውን በውበት ይከበባል !! ። ለዚህ ደሞ ብቸኛው መፍትሄ የአእምሮን የሃሳብ አቅጣጫ ለመቀየር መወሰን ይሆናል ። እዚህ ላይ ቀጣይዋን ወግ ለሃሳባችን ማጠያከሪያ አድርገን እናምጣት >
በአንድ የአይሁድ ምኩራብ የተከሰተ ታሪክ ነው ። ምኩራቡን አይሁድ እንደገዳም የሚጠቀሙበት ሲሆን የዚህ ምኩራብ ሊቀ ካህን ደግሞ በባህሪው እጅግ ቁጡና ኮምጫጫ ነበር ። በዚያ ገዳም ውስጥ ኑሯቸውን የመሰረቱ ሁለት ጓደኛሞች ዘወትር ሳይለያዩ የሚፈጽሙት አልድ ልማድ ቢኖር ከአትክልቱ ስፍራ እግራቸውን መጓዝ ነው ። በማለዳ ለአንድ ሰኣት ፥ ምሽት ላይ እንዲሁ ለአንድ ሰአት ይህንን የእግር ጉዞ ሳያቋርጡና ሳይለያዩ ለረጅም ጊዜ የሚፈጽሙት እነዚህ ሁለት ወጣቶች የቀረውን ጊዜያቸውን ደግሞ የእምነት መጽሃፍትን በማጥናትና በመማር እንዲሁም ሌሎች የገዳሙን ስራዎች ሲከውኑ ያሳልፉ ነበር ፡፡ ይሁንና እነዚህ ሁለት ወጣቶች ዘወትር በአእምሯቸው እየተመላለሰ የኒያስስባቸው አንድ ጉዳይ ነበር ፡፡ ይሄውም " በአትክልት ስፍራው እግራቸውን ሲያፍታቱ ሲጋራ ማጨስ እንዲፈቀድልን ሊቀ ካህኑን እንዴት እንጠይቀው ? " የሚለው ነው ። ሁለቱን ጓደኛሞች በሲጋራ ሱስ የተጠመዱ ቢሆንም በዛ ገባም ውስጥ በተቀደሰው የአይሁድ ምኩራብ ይህን ድርጊት መፈጸም ቀርቶ ማሰብም ትልቅ ወንጀል እንደነበር ያውቁታል።
ምንም እንኳን እጅን በአንበሳ አፍ የመክተት ያህል አስፈሪ ቢሆንም ወጣቶቹ የሱስ ስቃዩን መቋቋም ባለመቻላቸው ሊቀ ካህኑን ለየብቻ እየሄዱ ለማስፈቀድ ወሰኑ ። " እንደምታውቀው ሊቀ ካህኑ አደገኛ ሰው ነው ፥ ምን እንደሚለን እንግዲህ ፈጣሪ ያውቃል " ተባባሉ ።
በቀጣዩ ቀን አንድኛው እንባው ባይኑ ቀርሮ ተቆጥቶና አዝኖ ከምኩራብ ሲወጣ ጓደኛው በአትክልት ስፍራው እግሩን እያፍታታ በአበቦች መአዛም እየተዝናና ሲጋራውን ሲያጨስ ተመለከተው ። " አምላኬ ሆይ ! ሊቀ ካህኑን ሳትጠይቅ ሲጃራ ማጨስ ጀመርክ ? " በማለት አፈጠጠበት ።
ጓደኛው ግን ፈገግ ብሎ " የለም !! ተይቂያለሁ " አለው ።
በዚህ ጊዜ አንደኛው ጥልቅ ሃዘን ተሰማው ፥ ምን አይነት ሰው ነው ? እኔ አሁን ገብቸ ስጠይቀው እኮ በጩኸትና በስድብ ነው ያባረረኝ ። ምን እንዳለኝ ታውካለህ ? " ይህ ቦታ እኮ ገሃነም አይደለም ! ሲጃራ ማጨስ የምትፈልግ ከሆነ ገሃነም ሄደህ አጭስ " በማለት አባረረኝ ፥ ለመሆኑ ለአንተ እንዴት ለፈቅድልህ ቻለ ? " በማለት ተየቀው ።
ጓደኛውም ፈገግ ብሎ " መጀመሪያ ምን ብለህ እንደጠየከው ልትነግረኝ ትችላለህ ? " በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መለሰ ።
እሱም " የእኔ ጥያቄ ከዚህ ጋር ምን ያገናኘዋል ? " አለው
ጓደኛውም " እሱን ቦሃላ እነግርካለሁ በቅድሚያ ግን ምን ብለህ እንደጠየከው ማወቅ እፈልጋለሁ" አለው
" በቀላሉ ላስረዳው ፈልጌ በቀን ሁለት ሰአት ያክል የጸሎት ጊዜ እንዳለን ታውቃለህ . . . . . በእነዚህ ሰአታት ከአትክልቱ ስፍራ እንድንሄት የተፈቀደ ነው ፥ ስለዚህ እየጸለይኩ ሲጋራየን ማጨስ እችላለሁ " በማለት ነበር የጠየኩት አለው ።
በዚህ ጊዜ ጓደኛው "አየህ ! ሃዳብህ በሊቀ ካህኑ ፍርሃት ተይዟል እና አጠያየቅህንም እንዲሁ በተሳሳተ መልክ አቀረብከው ። እኔ ግን በሃሳቤ ስለ ሊቀ ካህኑ አስቀድሜ የወሰንኩት ነገር ቢኖር ሲጃራ ማጨሴን እንደማይቃወም ስለነበረ ጥያቄየን በዚህ ሃሳብ መሰረት አቀረብኩለት " ጌታዮ!! ሲጃራ በማጨስበት ጊዜ መጸለይ እችላለሁን ??" አልኩት ። እሱም ተደስቶ " በሚገባ እንጅ . . . .በማንኛውም ጊዜ ፈጣሪህን ማሰብ የተገባ ነው " በማለት ፈቀደልኝ ብሎ እየሳቀ ወደ ሲጋራ ማጨሱ ተመለሰ ።
ጥበብ ቅጽ ( 2 )
ገጽ 29 - 31
ሃይለጊዮርጊስ ማሞ
ማንኛውም ሰው የሃሳቡን ፍሬ እንደሚበላ ምንም ጥርጥር የለውምና አእምሯችን የሚወልዳቸውን ሃሳቦች በሚገባ ማጤን እና የተሻለውን መርጦ መጓዝ የተሻለ ነገን እንድንኖር ያደርገናል ባይ ነኝ

"ዕውነትን ማወቅ ትልቅ ጥረት ይጠይቃል። ዕውነትን መናገር ደግሞ ትልቅ ድፍረት፣ ዕውነትን ለመኖር ከሁሉ የሚበልጥ መስዕዋትነት ያስከፍላል። ምክንያቱም ዕውነትን ለመረዳት ብሩህ ልቦና፣ ለመናገር ንፁህ ህሊና፣ ለመኖር ደግሞ የሰውን ሁለንተና ይጠይቃል።"
® ዶክተር ምህረትደበበ
® ዶክተር ምህረትደበበ
የፈላስፋው ፍርድ
"የሰው ልጅ #ለተፈጥሯዊው_ሕግ የሚገዛበትን አዕምሮ #በዓለማዊው_ሕግ በከለው"
/ ላኦ-ዙ /
📚📚📚
.....ላዎ-ዙ በመላዋ ቻይና ጠቢብ ለመሆኑ በተመሰከረለት ዘመን ላይ ቆሞ ነበር ። ይኸን የሰማው የቻይና ንጉስ ላኦ-ዙን አስጠርቶ በታላቅ ትህትና ከተቀበለው በኋላ ..."እባክህ!የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ እንድትሆን እለምንሀለሁ?"ሲል የሹመት ጥያቄ አቀረበለት ።
፨ ላኦ-ዙ ግን "ንጉስ ሆይ! ተሳስተሀል!ለዚህ ቦታ የሚሆን ትክክለኛው ሰው እኔ አይደለሁም ፤ ልቅርብህ...ሌላ ሰው ፈልግ!" አለው ።
ንጉሱ ግን የላዎ-ዙን እምቢታ መቀበል ቀርቶ መስማት እንደማይፈልግ ነገረው፦"ከአንተ በቀር ማንንም ሰው በዚህ ወንበር ላይ ማስቀመጥ አይቻልምና የሰጠሁህን ሥልጣን ግድ መቀበል አለብህ"ሲል ወተወተው ።
፧
፨ ላዎ-ዙም፦ "እንግዲ አልሰማህም የምትል ከሆነ በመጀመሪያው ቀን ችሎት የምፈፅመውን ስትመለከት መሳሳትህ ይገባሀል ። ከትህትና በመነጨ ወይም ለአንተ ካለኝ አክብሮት ለቦታው የምገባ አለመሆኔን ነገርኩህ እንጂ ፣ እውነቱ ግን መንግስትህ የዘረጋው ሥርዓት የተሳሳተ መሆኑን ማወቄ ነው!እናም በቦታው ላይ ወይ እኔ እኖራለው ፤ ወይም ደግሞ የአንተ ህግና ሥርዓት። ፣ እንዲሁም እሱን የሚከተለው ሕዝብህ ይኖራል"በማለት ሥልጣኑን ለመቀበል ተስማማ ።
፨ ላዎ-ዙ ጊዜ ሳያባክን በነጋታው ችሎት ተቀመጠ ። ተከሻሱ ሰው በቻይና ዝነኛ ከነበረ ሀብታም ብዙ ገንዘብ ዘርፏል ተብሎ ከፊቱ ቀረበ። ላዎ-ዙ የተከሳሹን ወንጀል አድምጦ ሲያበቃ ፍርድ ሰጠ ። "ከሳሽም ተከሳሽም እያንዳንዳቸው በስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ፈርጃለሁ"።
፧
ከሳሽ የሰማውን ማመን አልቻለም ። ምናልባት ላኦ-ዙ ክሱ አልገባው ይሆናል ፤ አልያም እርጅና እየተጫጫነው ስለሆነ መርሳት ጀምሮት ይሆናል ፥ ወይም ደግሞ ለስራው አዲስ ስለሆነ ...ብቻ አስቦ ሲጨርስ ፈገግ ብሎ፦"ክቡር ዳኛ!ምን እያሉ ነው? ገንዘቤን የተዘረፍኩት እኮ እኔ ነኝ ፤ ይሄ ምን አይነት ፍርድ ነው? ሀብቴን ተዘርፌ እንዴት እንደገና ከዘረፈህ ሰው ጋር አብረህ ወህኒ ውረድ እባላለው ? ግዴለም የሆነ ቦታ አልገባዎትምና ያልተገባ ፍርድዎን ያስተካክሉልኝ!"
፨ላዎ-ዙ ፈገግ ብሎ ምክንያቱን አስረዳው፦"ይልቁንስ ያልገባህ አንተ ነህ!ያልተገባ ፍርድ የሰጠሁ መስሎህ ከታየህ ምናልባት ያልተገባ ፍርድ የሰጠሁትም ገንዘብህን ዘርፏል በተባለው ሰው ላይ ነው ። የአንተ ወህኒ መውረድ ግን ከሌባው በላይ የተገባ ሆኖ አግኝቼዋለው ። ምክንያቱም አንተ የበዛ ሀብት ለራስህ ያከማቸኽው ፥ ሌላው ሰው ማግኘት የሚገባውን እያሳጣህ ነው...ብዙዎች በችግር የሚማቅቁባት በዚህች ሀገር አንተ ገንዘብ በገንዘብ ላይ ታከማቻለህ ። ለምን ይሆን? አየህ! የአንተ ከልክ ያለፈ ስግብግብ ባህሪህ እነዚህን ሌቦች ፈጠረ! ስለሆነም ሌባው በድርጊቱ ፤ አንተ ደግሞ ሌባ በመፍጠርህ እኩል ፍርድ ይገባችኋል ! የመጀመሪያው ወንጀል ፈጣሪ ግን አንተ ነህ ።
፧
ላዎ-ዙ፦"የሰውን ልጅ ዓለማዊው እውቀትና ሕግ ሳይሆን የተፈጥሮ ሕግ ሊገዛው ይገባዋል" የሚለው ለዚህ ይመስላል ። ይህ ከላይ የተሰጠው ፍርድ መለስ ብለን ብንቃኝ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በውስጡ ያስቀመጠችውን የእኩልነት ፣ የመፋቀር ፣ የመተሳሰብ ፡ባህሪይ እንዲጥል ያደረገው ራስ ወዳድነት በመስፈኑ ነው ። የራስ ወዳድነት ምንጩ ደግሞ ይህንን ስሜቱን የሚጠብቅለት ሰው ሰራሽ ሕግ መፈጠሩ ነው ። ሀብትን ለማንም ሳታካፍል ማከማቸት እንደምትችል እርግጠኛ ያደረገህ ማንም እንደማይወስድብህ የሚጠብቅልህ ሰው ሰራሽ ሕግ መኖሩ ነው ። ለዚያም ነው "የሰው ልጅ ለተፈጥሯዊው ሕግ የሚገዛበትን አዕምሮ በዓለማዊው ሕግ በከለው/corrupt አደረገው" የሚለን ላዎ-ዙ ።
📚📚📚
ምንጭ ፦ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ-ፍትህ መፅሔት ቁ.57(የተወሰደ)

ተሸካሚ በሌለበት ሸክም የለም...!!
፨፨፨
<< አንድ ነገር የሚታየው በሌላ አካል ለመታየት ስለሚችል ሳይሆን ነገር ግን ሌላ አካል ስላየው ነገሩ ሊታይ ቻለ፤ ወይም አንድ ነገር ተመሪ የሚሆነው መሪ ስላለው እንጂ ነገሩ ተመሪ ስለሆነ አይደለም። አንድ ነገር ሸክም የሆነው ተሸካሚ ስላለው እንጂ ነገሩ በራሱ ሸክም ሆኖ አይደለም። ይኽ ማለት አንድ ውጤት በራሱ ልቆ የወጣበት አካል ውጤቱ የራሱ ሳይሆን ምክንያት ስላለው ነው። ውጤት የሆነ ነገር በራሱ ውጤት አያመጣምና። ቅድስናም እንዲሁ ቅዱስ የሚሆነው አማልክት ስለሚወዱት እንጂ በራሱ ቅዱስ ስለሆነ አይደለም። >>
/ ሶቅራጥስ /

በእንተ ንባብ ወሐሜተ መጻሕፍት
✍️
ወዳጄ አንብብ
ከማንበብ አትቦዝን ስታነብ ጎደሎ ትሆናለህ ፤ ጎደሎነትህን ለመሙላት
ስትደክም ብዙ ታተርፋለህ። ፖለቲከኛው ለምትታገልለት ህዝብ ሐሳብ ከማመንጨት ሐሳብ
ወደ መሸጥ ታድጋለህ ።ካነበብህ በስሜትና በመላ በመሰለኝና በደሳለኝ ከመመራት ወጥተህ ለዓላማና ለመርህ የሚቆም አንተን ትሰራለህ። ስለሆነም
አንብብ በእውቀት ሞግት ምክንያታዊ ሁን በስሌት እንጅ በስሜት አትጩህ። በመጮህ እታገልለታለሁ
ለምትለው ህዝብ ቀርቶ ለራስህም ሳትሆን እንዳትቀር አንብብ ።
✔
ስታነብ ሐሜተኛ አትሆንም ብታማም መጽሐፍትን እንጅ ሰውን አይሆንም ።
ደግሞ መጽሐፍ ይታማሉ እንዴ ትለኝ እንደሆነ "እንዲህ አሉ" እያልክ መነጋገርያ መወያያ ታደርጋቸዋለህ እና ነው ። መጽሐፍትን ስታማ የምታውቀውን ታስታውሳለህ ፤ ተመስጦ ትጨምራለህ ፤ ሐሳብ ታፈልቃለህ ፤ ስትገፋም ትራቀቅባቸዋለህ ። ስለዚህ እያነበብክ መጽሐፍትን እማቸው።
✔
አንድ ምክር ልምከርህ አንብብ አንብብ አንብብ!! ግን መርጠህ
አንደምትመገብ መርጠህ አንብብ !! መጽሐፍ ይመረጣል ወይ ትለኝ እንደሁ አዎ ይመረጣል። በአንተ የመረዳት ልክና መጠን የተጻፉ መጻሕፍትን አንብብ የረቀቁብህን ከተሻሉት ጋር በሐሜት ፕሮግራምህ ትረዳቸዋለህ። ለሕጻን ወተት እንጅ አጥንት እንደማይሰጠው ሁሉ አንተም ቀድመህ ወተት መጻሕፍትን አንብባቸው በንባብ የዳበረ ጥርስ ስታበቅል ያኔ አጥንት መጻሕፍትን እየቆረጣጠምህ በየብልት በየብልቱ እየሰደርህ ለተራቡት የመመገብን አክሊል ትቀዳጃለህ። ከዚህ ውጭ ግን ሳታነብ ላውራ ብትል ፍሬከርስኪ ይሆንብሃል። ልጫወት ብትል ተደራሲህን ታዝጋለህ ልናገር ብትል እንቶፈንቶ ይሆንብሃል። ላስታርቅ ብትል አጣልተህ ትወጣለህ መጻሕፍት ግን ለዚህ ሁሉ ነገር መላ አላቸው። የዘመናት እውቀትን የትውልድ የካበተ መረዳትን ጠቅልለው አንዴ ያጎርሱሃል።
✔
እናም ግድየለም ስማኝ የመጻሕፍት ሐሜት ጉባኤ ስራ። መጽሐፍትን ማማት የምንጀምረው በትዕግስት እና አብዝተን ማንበብ ስንጀምር ነው። ያኔ የመጽሐፍቱ ደራሲ ፣ አርታኢውም ይሁን ማንኛውም በመጽሐፍት ዝግጅቱ ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው ሳይኖር ስለ መጽሐፍቱ አንስተን ራስችን ጠያቂ ፣ መላሽ ፣ ተሟጋች እያደረግን አንዱን መጽሐፍ ከሌላው ጋር እናፋጫለን ከሌሎች መጻሐፍት እያጣቀስንም እናስታርቃለን እናመሰጥራለን ያኔ መጽሐፍትን ማማት ጀምረናል ማለት ነው ።
መጻሕፍትን ማማት ስንጀምር እንራቀቃለን ቀድሞ ያልነበረን ሐሳብ ይፈልቃል ፤ ሞጋቾችም እንሆናለን ፤ ያኔ የሰው ሐሜት ትዝ አይለንም ።
ወዳጄ ይህኔ ሙግትህ ከደራሲ እከሌ ወይም ሚስተር (x) ጋር ሳይሆን ከመጽሐፍቱ ጋር ይሆናል፤ ከነበርክበት ከፍ ትላለህ። ይህን ጊዜ ብዙ ድምፅ አይኖርህም አንተ ከሌሎች ጋር እኩል
አትጮህም ግራ ቀኝ ፊት እና ኃላ ትመለከታለህ ፤ ምክንያታዊ ትሆን እና ሚዛንህ ምጡን (balanced ) ይሆናል። ብዙ አትጮህም አንዴ ስትጮህ ግን ጩኸትህ የኢያሪኮን ቅጥር ከመሰረቱ የማፍረስ አቅም ይኖረዋል። እንዲሁ በዘፈቀደ ተነስቶ ማድነቅ ፤ ተንስቶ ማውረድ ፣ ተነስቶ ከፍ ዝቅ
ማድረቅ ይቀራል ለሁሉም ምክንያታዊ እይታ ይኖርኸል ። በቃ ትጠበብበታለህ
ምክንያቱም አንተ መጽሐፍት ማማት ጀምረኸል (ከማንበብ አልፈኸል ማለት
ነው) ።
✔
መጽሐፍቱን ስታማቸው ተከታይህ ይቀንሳል ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ሰዎች ሰውን በማማት የተጠመዱ ናቸው ። የሚጮኹት እንጅ ዝም የሚሉት አዋቂዎች አይመስሏቸውም ። አንተ በምክንያት ስትጮህ አብሮህ የሚጮህ አይጠፋም ፤ በምክንያት ስትደግፍ እና ስትቃወም ግን ከአብዛኛው ሰው ልብ ትርቃለህ ምክንያቱም አንተ ምክንያታዊ ነህ ። በዚህ ሰዓት ሐሳብ ጨማቀ መፍትሔ አፍላቂ አንተ ብቻ ትሆናለህ ሌላው ጥቅሙ ለአብዮት ቀን ብቻ ነው። የምትሸጠው ሐሳብ ሀገርን ይገነባል ለምን ካልከኝ መጽሐፍቱን
አምተኸቸዋላ ፤ እነርሱም ሐሳባቸውን ሰጥተውኸል። ወይ እንደ ቶማስ ሙር በልብወለድ እንግሊዝን ያክል ገናና ሃገር ትሰራለህ አሊያም እንደ ክቡር ዶክተር ሃዲስ ዓለማየሁ በክታብህ የፍቅር ወግ አስመስለህ ፀረ ፊውዳል ዘመቻህን ታጧጡፋለህ ካልሆነም እንደ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ ምስጢራዊነትን ትሰብካለህ ተፈጥሮን መንከባከብ እንዲገባ ትመክራለህ።
ወይም እንደ ሉሌ መላኩ እንደ ሪቻርድ ፓንክረስት እንደ አሥረስ የኔሰው እንደ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ታሪክን ከመሀል ለሚጀምሩት ከምንጩ እየቀዳህ የታሪክን አግቦ ለድኩማኑ ታስተምርበታለህ።
✔
አንባቢ ዘፋኝ ብትሆን ሙዚቃህም ለዛ አለው አዝማሪነትህም ጥዑም ነው። ታሪክን እያወሳህ ስለ ሕዝብ አንድነት ትጠበባለህ። ካላነበብህ ግን ሙዚቃህ የከበሮና የማሲንቆ የክራርና የጊታር የእቃቃ ጨዋታ ብቻ ከመሆን አይዘልም።
✔
አንባቢ ከሆንህ ፊልም ልስራ ብትል ሃገራዊ ጥበባትንና ምስጢራትን የስክሪፕትህ ማድመቂያ አድርገህ እያዋዛህ ሰው ሃገሩን እንዲረዳ እሱነቱን እንዲያውቅ ታደርግበታለህ። ሃይማኖታዊ ነቆቻችንን የባህል ዝንፈቶቻችንን ፖለቲካዊ ነውሮቻችንን ሃገራዊ ውድቀቶቻችንን እና ማኅበረሰባዊ ድክመቶቻችንን እየነቀስህ ሐሳብ ጨማቂ መፍትሔ አፍላቂ ሆነህ አርትን ትጠበብበታለህ ለሰው ልጅ እንዲገባም አድርገህ ጥበብን ትሰፋዋለህ። ከዚህ ውጭ ግን ካላነበብህ ፊልምህ ሁለት ጓደኛሞችን አፋቅሮ ከማጋባት ያለፈ ሚና አይኖረውም።
እናም በመረዳት እናንብብ።
ሰናይ ቀን።
🍌
✍️ተጽሕፈ በዘአቦላ ወበታዖርያ

ወንጀለኛው
(ካህሊል ጂብራን)
፨፨፨
አንድ በርሀብ የተጎዳ፣ ፈርጣማ ሰውነት ያለው ወጣት በእግረኛ መንገድ ላይ ተቀምጦ እጆቹን በመዘርጋት ረሃብና ሃፍረት እየሸነቆጡት በሚያሳዝን ዜማ ይለምናል። ምሽት ላይ ከናፍሮቹ እና ጉሮሮው ደረቁበት። እጁ ግን እንደሆዱ ባዶ ነበር። ከተቀመጠበት ተነስቶ ከከተማ ወጣና በአንድ የዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ በምሬት ያነባ ጀመር። ከዚያም ረሃብ ውስጡን እየሞረሞረው ግራ የተጋቡ አይኖቹን ወደ ሰማይ ላካቸውና እንዲህ አለ፤ <<ጌታዬ ሆይ፣ ወደ አንድ ሃብታም ሄጄ ስራ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት። እሱ ግን ቡትቶዬን አይቶ ፊቱን አዞረብኝ። የአንድ ትምህርት ቤት በር አንኳኳሁ፣ ግን ባዶ እጄን ነበርና ችላ ተባልኩ። ቁራሽ ዳቦ የሚያስገኝልን የትኛውንም አይነት ስረ ሞከርኩ፣ ይሄ ሁሉ ግን ከንቱ ነበር። ተስፋ በመቁረጥ እንዲመፀውቱኝ ለመንኩ፣ መፅዋቾቹ ግን ተመለከቱኝና <ጠንካራና ሰነፍ ነው፤ መለመን አልነበረበትም> አሉኝ... <<ጌታዬ ሆይ፣ እናቴ የወለደችኝ በአንተ ፍቃድ ነው። አሁን መጨረሻው ከመድረሱ በፊት ምድር ወደ አንተ እንድመለስ ፈቅዳልኛለች።>>
፧
ይሄን ጊዜ ፊቱ ተለዋወጠ። ብድግ አለና አይኖቹን በቁርጠኝነት አጉረጠረጣቸው። ከአንዱ የዛፍ ቅርንጫፍ ወፍራም አርጩሜ ቆርጦ ወደ ከተማዋ በመቀሰር ጮኾ ተናገረ። <<ያለኝን ድምፅ ሁሉ አጠራቅሜ ዳቦ ስጡኝ ብያችሁ ነበር። እናንተ ግን ችላ አላችሁኝ። አሁን በጉልበቴ አገኘዋለሁ! በፍቅር እና በርህራሄ ስም ለምኜያችኋለሁ፤ ስብዕና ግን ዋጋ አልነበረውም። አሁን በርኩስ መንፈስ ስም አገኘዋለሁ!>>
ዓመታት ሲያልፉ ወጣቱ ዘራፊ፣ ነፍሰ-ገዳይ እና የነፍስ አጥፊ ሆነ፣ የተቃወሙትን ሁሉ ያጠፋል፤ ጉልበቱን በመጠቀም ብዙ ሃብት ሰበሰበ። ከግብረ-አበሮቹ አድናቆትን አገኘ፣ በሌሎች ሌቦች ተከበረ፣ በህዝቡ ዘንድ ደግሞ ተፈሪ ሆነ።
፧
ሃብቱና በጉልበቱ ያገኘው ተፈሪነቱ፣ አሚሩ የከተማዋ ባለስልጣን አድርጎ እንዲሾመው አበቃው- ብልህነት የጎደላቸው አገረ-ገዢዎች አሳዛኝ ሥራ። ከዚያ በኋላ ስርቆት ህጋዊ ስራ ሆነ፤ ጭቆና በስልጣን ይደገፍ ጀመር፤ ደካሞችን ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሆነ እናም ዙፋኖች ይፈሩና ይከበሩ ጀመር።
#ስለዚህ ስግብግብነት ነካ ያደረገው ስብዕና አይናፋሮችን ወንጀለኛ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ደግሞ ነፍሰ-ገዳይ ያደርጋል፤ ስግብግብነት የጎበኘው ስብዕና ያድግና መልሶ ስብዕናን አንድ ሺ እጥፍ ጊዜ ያጠፋዋል!
፨፨፨
ምንጭ ፦ እንባ እና ሳቅ(Tears and Laughter)
ደራሲ ፦ ካህሊል ጂብራን
ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ
...ዋጋ የነሱት(ያሳጡት)ነገር ዋጋ ያስከፍላል...!
ለማንኛውም ሃሳብ አስተያየትዎ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/SSR60

ሰላም ሰላም ውድ የቻናላችን ተከታዮች ሁሌም ለናንተ ምርጥ ምርጡን ለማድረስ እንተጋለን ፡ ፡ ሰሞኑን ለተፈጠረው ክፍተት ይቅርታ እየጠየቅን 🙏🙏 ። ለቀጣይ ስራችን የናንተ አስተያየት ወሳኝ ነው እና አስተያየቶታችሁን ትቸሩን ዘንድ እንጠይቃለን ።
አድሚኖቹ
ከላይ የተያያዘው ሊንክ ለናንተ ይጠቅማል ያልነው ምርት የመጽሃፍት መደብር ነው እና ተቀላቅለው የመጽሃፍት እጥረተዎን ያስወግዱ!!!

ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!:
"• ታዋቂ በግ ከመሆን ብቸኛ አንበሳ መሆን ይሻላል፡፡
• የተለየ ሰዉ መሆን ይቻላል፡፡
• የሚወደድ ሰዉ መሆንና ዋጋ ያለዉ ሰዉ መሆን ልዩነት አለዉ፡፡ ብዙ ሰዎች ሊወዱህ ይችላሉ ግን ብዙዎቹ ዋጋ አይሰጡህም፡፡ ስለዚህ ዋጋ ያለዉ ሰዉ ሁን!
• አንድን ሰዉ ሁል ጊዜ እንዲያስታዉስህ አትስገድደዉ፡፡ ዝም ብለህ አንተ ሳትኖር እንዴት እንደሚኖር ታዘበዉ፡፡
• ህይወት አንተ የምትፈልገዉን ሰዉ ለክታ አትሰጥህም፡፡የሚረዳህ ፣ የሚጎዳህ ፣ የሚወድህ ፣ ጥሎህ የሚሄድ እንዲሁም ትልቅ እንድትሆን መንገዱን የሚያመቻችልህን አስፈላጊ ሰዉ ግን ትሰጥሃለች፡፡
• ማንኛዉም አዛ የሚያደርግህ ነገር ካለ እሱ ነገር ትእግስት እንዲኖርህ እያስተማረህ ነዉ፡፡
ጥሎህ የሔደ ማንኛዉም ሰዉ በሁለት እግሮችህ ቆመህ በራስህ እንድትሄድ እያስተማረህ ነዉ፤
ማንኛዉም የሚያናድድህ ነገር ይቅርታንና ደግነትን እያስተማረህ ነዉ፡፡
ማንኛዉም ባንተ ላይ ሃይል ያለዉ ነገር የራስህን ጉልበትና ሃይል እንድትቆጣጠር እያስተማረህ ነዉ፡፡
ማንኛዉም የምትጠላዉ ነገር ያለቅድመ ሁኔታ እንድትወድ እያስተማረህ ነዉ፡፡
ማንኛዉም የምትፈራዉ ነገር ፍርሃትህን አሸንፈህ እንድትራመድ እያስተማረህ ነዉ፡፡
መቆጣጠር የማትችለዉ ነገር ሲደርስብህ ከእጅህ እንድትለቀዉ እያስተማረህ ነዉ፡፡
• በህይወትህ ያለዉ አስቸጋሪ ሁኔታ አንተን ለማጥፋት የተሰራ ሳይሆን ዉስጥህ ያለዉን እምቅ አቅምና ችሎታ እንድትረዳ የሚያግዝህ ነዉ፡፡ ችግሮችህ ከነሱ በላይ ችግር እንደሆንክባቸዉ ይወቁ!
• እርካታ ያለዉ ህይወት ስኬታማ ከሆነ ህይወት ይሻሻላል፡፡ ምክንያቱም ስኬትህ በሌሎች ሰዎች ሲለካ እርካታህ ግን በራስህ ነፍስ ፣ አእምሮና ልብ ይለካል፡፡
• ትላልቅ ነገሮች በምቾት የሚገኙ አይደሉም፡፡
• ሃላፊነት ዉሰድ፡፡ ካሸነፍክ ደስተኛ ትሆናለህ፤ ከተሸነፍክ ደግሞ ብልህ ትሆናለህ፡፡
• ነገሮችን ሁልጊዜ ሰዉ ሳያጨበጭብልህ በትክክል መስራት ከባድ ነዉ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ለራስህ አጨብጭብለት ፣ የራስህ ደጋፊ እራስህ መሆን ይኖርብሃል፡፡
• እዉነተኛ ሀብታም ለመሆን ባንክ ቡክህ ዉስጥ ያለዉ የገንዘብ ብዛት ሳይሆን ልብህ ዉስጥ ያለዉ ማንነት ይወስናል፡፡
• በግልህ ቺክ ጥበስ ፣ በግልህ አፍቅር ፣ በግልህ ደስተኛ ሁን ፣ በግልህ ኑር ፣ በዚህ መንገድ እየሄድክ ኪሳራህንና እራስህን መጠገን በግልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡
• ፍቅር ፣ ሀብትና ስኬትን አታሳድድ፡፡ ይልቁንም ከትላንቱ የተሻለ ማንነትን ገንባ ፣ ከዛማ እራሳቸዉ ያሳድዱሃል!
• በሃሳብ የምንሰቃየዉ በእዉነታዉ ከምንሰቃየዉ ይበልጣል፡፡
• አንዳንድ ቤተሰቦች ስኬታማ ለመሆን እርስ በርሳቸዉ መረዳዳት እንዳለባቸዉ ገና አልገባቸዉም፡፡
• ዋናዉ ችግራችን የሰአት ማነስ ሳይሆን የአቅጣጫ መጥፋት ነዉ፡፡ ሁላችንም 24 ሰአት ተሰጥቶናል፡፡
• አንዳንድ ጊዜ ስኬታማ የምትሆንባትን አንዷን አመት ለማግኘት ሌላ አስር አመት ሊፈጅብህ ይችላል፡፡
• በህይወትህ ዋናዉን ሃላፊነት የሚወስደዉ እራስህ ብቻ ነህ፡፡
• በምድር ላይ ስትኖር ባደረከዉ ስራ ልክ ይከፈልሃል!"
❤😍 የዲያሪ ላይ ጥቅሶች ❤️😍