"""""""PRECIOUS """""""""
Its not affection that called me to you
I ain't expecting any avail from you.
That one thing makes me wanna live
That sucky feeling i feel eveytime you say goodbye and leave
Something that made me realize life is worth to strive
The thing that forces me to take you as my beloved wife
The cause i got stronger
Believing in fantacies even more harder
The sole reason for my existence
Why i'm still strong w'out confidence
All b/c of your PRECIOUS SMILE!
Written by: Yesusra
@poemers @poemers @poemers
@poemers @poemers @poemers
Its not affection that called me to you
I ain't expecting any avail from you.
That one thing makes me wanna live
That sucky feeling i feel eveytime you say goodbye and leave
Something that made me realize life is worth to strive
The thing that forces me to take you as my beloved wife
The cause i got stronger
Believing in fantacies even more harder
The sole reason for my existence
Why i'm still strong w'out confidence
All b/c of your PRECIOUS SMILE!
Written by: Yesusra
@poemers @poemers @poemers
@poemers @poemers @poemers
Forwarded from тнσυgнт°ραι𝔫тιиg 🎞️ (Haileab Atsede)
world giving index ranking (የ አለም ለጋስ ህዝቦች ደረጃ)
በ አለም ዙሪያ በ 142 ሀገሮች የተሰራ ጥናት ነው። ጥናቱ በዋናነት 3 ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው። 1, ለተለያዩ ተቋሞች ገንዘብ መለገስ 2, የነፃ አገልግሎት መስጠት(volunteer) 3, የማያውቁትን ሰው በመርዳት ላይ ያደረገ ነው።
ታዲያ ሀገራችን ከ 142 ሀገሮች ውስጥ በ 38ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። Indonesia በአንደኝነት ስትመራ Kenya እና Singapore በሁለትና በ ሦስት ይከተላሉ።
ታዲያ ይሄን ነገር ለምን ዛሬ ለማውራት ፈለኩ መሰላቹ። በ አንድ ወቅት በ አዲስ አበባ በተደረገ ጥናት በ ቀን እስከ 2 ሚሊዮን ብር ለ የኔ ብጤ ይሰጣል። በወር ወደ 60 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደማለት ነው። የተለያዩ በአላት በሚኖሩበት ጊዜ ደግሞ ንግስ ሲኖር እስከ 8 ሚሊዮን ብር ለ የኔ ብጤ ይሰጣል እንግዲህ ይሄ በ አዲሳባ ብቻ ነው ፣ አጠቃላይ እንደ ኢትዮጵያ ስንት ሊሰጥ እንደሚችል አስቡት?
ሀገራችን ላይ የጥገኝነት መጠን(Dependency rate) አንድ ሰው 7 ሰው ነው የሚያስተዳድረው። ይሄ አንድ ሰው ሲሞት ሰባት ሰው ጎዳና ይወጣል እንደማለት ነው።
ታዲያ አሁን ላይ ከ የትኛውም ወቅት በላይ ብዙ የኔ ብጤ ብዙ ተፈናቃይ በበዛበት ጊዜ ይሄ ሁሉ ሰው በሰው ምፅዋት በሚኖርበት ወቅት እንዴት እንደዚህ ደረጃችን ዝቅ አለ? ቀላል ነው መልሱ የነሱ መስጠት በተቋም ደረጃና በ ተቀናጀ መልኩ ነው የሚከናወነው ። መስጠታቸው መዋቅራዊና በሚታይ መልኩ ነው ቀኝ እጅህ ሲሰጥ ግራ እጅህ አይመልከት የሚል ነገር የለም በግልፅ ይረዳሉ ለተቋም ይለግሳሉ እና የኛም ተቋማዊ መስጠት ቢሆን ስንተኛ ልንሆን እንደምንችል ማሰብ ነው።
ምን ልል ፈልጌ ነው ያው ቸግሮኛል በግልፅ እርዱኝ ደረጃችን ከፍ ይበል😊
የ አፀደ
በ አለም ዙሪያ በ 142 ሀገሮች የተሰራ ጥናት ነው። ጥናቱ በዋናነት 3 ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው። 1, ለተለያዩ ተቋሞች ገንዘብ መለገስ 2, የነፃ አገልግሎት መስጠት(volunteer) 3, የማያውቁትን ሰው በመርዳት ላይ ያደረገ ነው።
ታዲያ ሀገራችን ከ 142 ሀገሮች ውስጥ በ 38ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። Indonesia በአንደኝነት ስትመራ Kenya እና Singapore በሁለትና በ ሦስት ይከተላሉ።
ታዲያ ይሄን ነገር ለምን ዛሬ ለማውራት ፈለኩ መሰላቹ። በ አንድ ወቅት በ አዲስ አበባ በተደረገ ጥናት በ ቀን እስከ 2 ሚሊዮን ብር ለ የኔ ብጤ ይሰጣል። በወር ወደ 60 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደማለት ነው። የተለያዩ በአላት በሚኖሩበት ጊዜ ደግሞ ንግስ ሲኖር እስከ 8 ሚሊዮን ብር ለ የኔ ብጤ ይሰጣል እንግዲህ ይሄ በ አዲሳባ ብቻ ነው ፣ አጠቃላይ እንደ ኢትዮጵያ ስንት ሊሰጥ እንደሚችል አስቡት?
ሀገራችን ላይ የጥገኝነት መጠን(Dependency rate) አንድ ሰው 7 ሰው ነው የሚያስተዳድረው። ይሄ አንድ ሰው ሲሞት ሰባት ሰው ጎዳና ይወጣል እንደማለት ነው።
ታዲያ አሁን ላይ ከ የትኛውም ወቅት በላይ ብዙ የኔ ብጤ ብዙ ተፈናቃይ በበዛበት ጊዜ ይሄ ሁሉ ሰው በሰው ምፅዋት በሚኖርበት ወቅት እንዴት እንደዚህ ደረጃችን ዝቅ አለ? ቀላል ነው መልሱ የነሱ መስጠት በተቋም ደረጃና በ ተቀናጀ መልኩ ነው የሚከናወነው ። መስጠታቸው መዋቅራዊና በሚታይ መልኩ ነው ቀኝ እጅህ ሲሰጥ ግራ እጅህ አይመልከት የሚል ነገር የለም በግልፅ ይረዳሉ ለተቋም ይለግሳሉ እና የኛም ተቋማዊ መስጠት ቢሆን ስንተኛ ልንሆን እንደምንችል ማሰብ ነው።
ምን ልል ፈልጌ ነው ያው ቸግሮኛል በግልፅ እርዱኝ ደረጃችን ከፍ ይበል😊
የ አፀደ
በድሮ ዘመን በንጉስ ጊዜ ነው አሉ
የዛኔ ውታፍ ነቃይ የሚባሉ አሉ ስራቸው ምን መሰላቹ ነገስታቱ እና ሹማምንቱ ከመቀመጫቸው ሲነሱ ቀሚሳቸው ወይ ልብሳቸው ቂጣቻው ላይ ሲወተፍ ከመቀመጫቸው ላይ በመሳብ የሚነቅሉ ናቸው።
እና አሁንም አሉ ይባላል አንዳንዶቹ ካድሬ የተቀሩት ፓርላማ ውስጥ ነው የሚሰሩት አሉ😂
ስራ አይናቅም ወገን እየበረታን
የዛኔ ውታፍ ነቃይ የሚባሉ አሉ ስራቸው ምን መሰላቹ ነገስታቱ እና ሹማምንቱ ከመቀመጫቸው ሲነሱ ቀሚሳቸው ወይ ልብሳቸው ቂጣቻው ላይ ሲወተፍ ከመቀመጫቸው ላይ በመሳብ የሚነቅሉ ናቸው።
እና አሁንም አሉ ይባላል አንዳንዶቹ ካድሬ የተቀሩት ፓርላማ ውስጥ ነው የሚሰሩት አሉ😂
ስራ አይናቅም ወገን እየበረታን
*JAB TAK HAI JAAN*
.
.
Tumhari diwwani haso koo,
Tumhari pyaar kaa muskan koo,
Tumhari haathoka ishq,
Din se din tak,
Pel se pel tak,
pyaar karoonga!
Jab tak hai jaan(*2)
..........................................................
The smile and sadness you got
On the light philtrum of yours,
S/th that makes me feel like youth,
I will always love it!
Jab tak hai jaan(*2)
.....................................................
ከዚህ ወድያ አልወድሽም፣
የለም እወድሻለው ገና፤
ማፍቀር አጭር ቢሆንም፣
መርሳት ረጅም ነውና፤ (')
Jab tak hai jaan(*2)
...............................................
(')... የበዕውቀቱ ግጥም ነች።
...............................................
@poemers @poemers @poemers @poemers @poemers @poemers
.
.
Tumhari diwwani haso koo,
Tumhari pyaar kaa muskan koo,
Tumhari haathoka ishq,
Din se din tak,
Pel se pel tak,
pyaar karoonga!
Jab tak hai jaan(*2)
..........................................................
The smile and sadness you got
On the light philtrum of yours,
S/th that makes me feel like youth,
I will always love it!
Jab tak hai jaan(*2)
.....................................................
ከዚህ ወድያ አልወድሽም፣
የለም እወድሻለው ገና፤
ማፍቀር አጭር ቢሆንም፣
መርሳት ረጅም ነውና፤ (')
Jab tak hai jaan(*2)
...............................................
(')... የበዕውቀቱ ግጥም ነች።
...............................................
@poemers @poemers @poemers @poemers @poemers @poemers
ዎከም ኢዘየክ
ወግ አዋቂ በኃይሉ ገ/መድህን አንድ የመፅሐፍ ምርቃት ላይ ምን አሉ:-
ካይሮ መግቢያ ላይ ዎከም ኢዘየክ የሚል በ አረብኛ የተፃፈ ፅሑፍ አለ ምን ማለት መሠላቹ ሀሳቡ ወደኛ ሲተረጎም ለምሳሌ በሆነ ባለህ ነገር ስትኮራ አንተ ያለህ ነገር ሌሎች ብዙ ሰው እንዳላቸው አስታውስ። ለምሳሌ በመልክሽ ስትኮሪ ካንቺ የበላለጡ እንዳሉ ከዚህ በፊትም እንደነበሩ አስታውሺ ፣ አንተም በ ፕሮፌሰርነትህ ስትኮራ ብዙ ሌሎች እንዳሉ እስከዛሬም ብዙ ኖረው እንዳለፉ አስታውስ።
እና ከዳር ሆነህ ያለህን ነገር እያሰብክ ተገንጥለህ ከምትኮራ ቀለል አርገህ ሌሎቹን ሳትንቅ ጠጋ ብለህ የበኩልህን አስተዋፆ አበርክት ተጫወት ተዝናና!!
እናም ዎከም ኢዘየክ ፖለቲከኞች እና ፊደል በመቁጠራቹ ያልቆጠሩት ለሚያንስባቹ ፊደል ቆጣሪዎች ፣ ገንዘብ ኖሯቹ የሌለው ለሚያንስባቹ
ወግ አዋቂ በኃይሉ ገ/መድህን አንድ የመፅሐፍ ምርቃት ላይ ምን አሉ:-
ካይሮ መግቢያ ላይ ዎከም ኢዘየክ የሚል በ አረብኛ የተፃፈ ፅሑፍ አለ ምን ማለት መሠላቹ ሀሳቡ ወደኛ ሲተረጎም ለምሳሌ በሆነ ባለህ ነገር ስትኮራ አንተ ያለህ ነገር ሌሎች ብዙ ሰው እንዳላቸው አስታውስ። ለምሳሌ በመልክሽ ስትኮሪ ካንቺ የበላለጡ እንዳሉ ከዚህ በፊትም እንደነበሩ አስታውሺ ፣ አንተም በ ፕሮፌሰርነትህ ስትኮራ ብዙ ሌሎች እንዳሉ እስከዛሬም ብዙ ኖረው እንዳለፉ አስታውስ።
እና ከዳር ሆነህ ያለህን ነገር እያሰብክ ተገንጥለህ ከምትኮራ ቀለል አርገህ ሌሎቹን ሳትንቅ ጠጋ ብለህ የበኩልህን አስተዋፆ አበርክት ተጫወት ተዝናና!!
እናም ዎከም ኢዘየክ ፖለቲከኞች እና ፊደል በመቁጠራቹ ያልቆጠሩት ለሚያንስባቹ ፊደል ቆጣሪዎች ፣ ገንዘብ ኖሯቹ የሌለው ለሚያንስባቹ
Forwarded from тнσυgнт°ραι𝔫тιиg 🎞️
አንዱ ሸሁ ጋር ሄዶ
"ያ ሼህ ዘላለም መኖር እፈልጋለሁ?" አላቸው
ሸህየው:- "ዘላለም መኖር ከፈለግክ አግባ" አሉት
ሰውዬው:- "እንዴ ካገባሁ ዘላለም እኖራለሁ?"
ሸህየው:-"አይ ዘላለም የመኖር ሀሳብህን ትለውጣለህ"
🗣 አለማየሁ ገላጋይ
"ያ ሼህ ዘላለም መኖር እፈልጋለሁ?" አላቸው
ሸህየው:- "ዘላለም መኖር ከፈለግክ አግባ" አሉት
ሰውዬው:- "እንዴ ካገባሁ ዘላለም እኖራለሁ?"
ሸህየው:-"አይ ዘላለም የመኖር ሀሳብህን ትለውጣለህ"
🗣 አለማየሁ ገላጋይ
Social Media Burnout
Psychological Burnout ማለት በስሜት ፣ በ አካል እና በ አዕምሮ ለነገሮች የምንሰጠው ግብረ መልስ መዳከም ወይም መዛል ነው።
በኑሮ ፣ በፍቅር ማጣት ፣ የህይወት ትርጉም በማጣት..... Burnout ያደረጉትን ቤታቸው ይቁጠራቸው።
@ourrthought
ይመስለኛል ሦስተኛ አመት የሁለተኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሆነን ነው ስለ Psychological Burnout የተማርነው።
Psychological Burnout ማለት በስሜት ፣ በ አካል እና በ አዕምሮ ለነገሮች የምንሰጠው ግብረ መልስ መዳከም ወይም መዛል ነው።
ታዲያ ይህ ነገር ብዙ ጊዜ በ አዳዲስ አማካራዎች (counselor) የሆኑ ሰዎች ላይ ይበዛል። ብዙ ጊዜ የ ስነ ልቦና (psychology) አማካሪዎች የሚያጋጥማቸው ጉዳይ ነው። ይህም የሚከሰተው ብዙ ሰዐታቸውን የሰዎችን ችግርና የህይወት ፈተና ሲሰሙ ቆይተው የሰሙትን የደንበኛቸውን ጉዳይ በጣም በማሰላሰልና ጉዳዩን ቤታቸውም ጭምር ይዘውት በመሄድ ህይወታቸውን ከስራቸው መለየት ያቅታቸዋል። መደበኛ ህይወታቸውን ለመምራት እስኪቸገሩ ድረስ የሰሙት ከባባድ ሁኔታ ሰላም ይነሳቸዋል በዚህ ጊዜ ድብርት መረበሽ መጨነቅ ይመጣባቸዋል ስራቸውን ሳይዘልቁ ይተውታል ማለት ነው።
ታዲያ ይህን Psychological Burnout ለመቋቋም አማካሪዎች የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ከነዛ ውስጥ ዋነኛው መቋቋሚያ መንገድ የሰሙትን የ ደንበኛቸውን (client) ከባድ ታሪክ የ ሰውየውን ስም እና ማንነት ሳይገልፁ ከ ስራ አጋሮቻቸው ጋር በመወያየት ሸክማቸውን ማቅለል። ለምሳሌ የሆነ ደምበኛዬ እያሉ ወይ ስም እየቀየሩ ጉዳዩን ማውራት ስም መጥቀስ አይቻልም ምክንያቱም to keep confidentiality rule የ ደምበኛን ምስጢር አሳልፎ መስጠጥ አይቻልምና ነው። ሌላው ዘዴ የስራ ህይወትንና የግል ህይወትን መለየት ነው። ስራ ላይ ሲኮን ስራን ብቻ ማሰብ ከስራ ሲዎጡ የስራን ጉዳይ ጠረጴዛ ላይ ትቶ መውጣት ወደ ቤት ይዞ አለመሄድ እንደ ማለት ነው።
ታዲያ አሁን አሁን የ ሶሻል ሚዲያ ዘመን ሰውን ለ Burnout እየዳረገው ያለ ይመስለኛል። በጣም ከባባድ ለጆሮ የሚከብዱ ዜናዎችን ላይክና ኮመንት ለመሸቀል ሱሉ እንደ ቀልድ ይለቁታል። ታዲያ እንደ ድንገት social media ላይ ስትዘዋወር አስደንጋጭ ነገር ትሰማለህ ትታመማለህ ከ አቅም በላይ የሆነ የሰው ሸክም ትሰማለህ ከዛን ቡኋላ ስታብሰለስለው ውለህ ታድራለህ። አንዳንዶቹ የሚለቁልህ አሳዛኝ ዜና ከነ ምስሉ በመሆኑ በቶሎ ከዛ ሀዘን ለማገገም(recovery) ለማድረግ ትቸገራለህ። ጉዳዩን ለጓደኛህ ተነጋግረህ እንዳይቀልህ እሱም ከመብሰልሰል ውጪ የሚያደርግልህ የሙያዊ እገዛ አይኖርም ታዲያ በማትፈታው ጉዳይ ትታመማለህ።
በ ማህበራዊ ሚዲያ የምታያቸው ተደጋጋሚ ጉዳዮች ሲበዙ ላንተ ግልፅ ባልሆነ መንገድ ህይወት ያስጠላሀል ስራ ይደብርሀል አንተ ግን ምክንያቱን ላትረዳው ትችላለህ ለምን እንደ ደበረህ እንደውም በራስህ ህይወት የተደበርክ ሁላ ነው የሚመስልህ። እስቲ ከ social media ለ አንድ ሳምንት ምንም ዜና ሳትሰማ ልዩነቱን ተመልከተው የዛኔ ምን ያክል እንደሆነ ታየዋለህ ጉዳቱን።
በኑሮ ፣ በፍቅር ማጣት ፣ የህይወት ትርጉም በማጣት..... Burnout ያደረጉትን ቤታቸው ይቁጠራቸው።
@ourrthought
Forwarded from ሀሳቦቻችን (Haileab Atsede)
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጣም እያስተዋልኩት የመጣውት ነገር ቢኖር ሰዎች የ ስነ ልቦና ህመሞችን (Disorder) አለብኝ የማለት ነገር ነው።
Disorder በመጀመሪያ ምንድነው? የሚለውን ሲገለፅ አዕምሮ እና አካል በመደበኛ መስራት ያለባቸውን ተግባራት ባጋጠመን ቀውስ ምክንያት ድርጊቱን ማከናወን ሲያቅተው እንደማለት ነው።
ታዲያ ከ 360 በላይ Disorders አሉ። ከነዚህ ውስጥ ግን ከባባድ የምንላቸው ከ 10 አይበልጡም። የተቀሩት ቀለል ያሉ እና መካከለኛ የ አዕምሮ መታወኮች ናቸው። አንዳንዴ ከነዚህ ከ 360 መካከል ካሉት ውስጥ አውጥተህ Disorder አለብኝ ብትል ከኛ ሀገር ከኑሮ ደረጃ አንፃር እንደ ቅንጦት ሊታይብህ ይችላል። አንዳንዴም ከቤተሰብህ ወይም ከጊዜ ብዛት ያዳበርካቸው ባህሪያቶች እንደ Disorder ሊታይብህ ይችላል።
ታዲያ ለማንሳት የፈለኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተዘወተረ የመጣው ነገር እኔኮ እንትን ዲሶርደር አለብኝ እያለ ያለ ምንም የ ሳይኮሎጂ ወይ ሳይካትሪስት ከ ብዙ social media ካያቸው ወይ ካነበባቸው ነገር ብቻ ከመነሳት እነዚህን disorder ለራሱ አድርጎ ቁጭ ይላል። ድባቴ (Depression) ለምሳሌ በጣም ከባድ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ የ ዲስኦርደር አይነት ነው። ግን ብዙ ሰዎች ከ ድብርት ጋር በማምታታት ከ Google መዳኒቶችን በማመሳከር ያለ ማረጋገጫ ይወስዳሉ። ይሄ ነገሩን ካለመረዳት የሚመጣ ትልቅ ቀውስ ነው።
Disorder ለመሆኑን ለመለየት በቀላሉ ለመለየት ቢከብድም ቢያንስ ነገሩ ከኛ ጋር የቆየበትን የጊዜ ርዝማኔ ማጤን አለብን ለምሳሌ የ ዕንቅልፍ መዛባት ቢኖርብን sleeping disorder(insomnia) ቢኖርብን እሱ መሆኑን ለመለየት ቢያንስ እንቅልፍ እየተቸገርን እስከ ከ 3 እስከ 6 ወር ድረስ መቆየት አለብን። ሌላው አንድ ዲሶርደር አለብን ለማለት አንድ ምልክት ብቻ ሳይሆን ጉዳዩን የሚያስረግጡልን እስከ ሦስት ምልክቶች ድረስ ማየት ይጠበቅብናል ሲቀጥል ደሞ በመደበኛ ህይወታችን ላይ ምላሽ መስጠት እስኪከብደን ድረስ ህወታችንን መምራት እንዳንችል ሲያደርገን ነው። ከዛ ውጭ የ ስሜት መቀየር ሲያጋጥመን ወይ ለ አንድ ሳምንት ከደበረን ዲስኦርደር ሆኖብናል ማለት አይደለም። እና ለስሜት ማስታገሻ ወይም pain killer ከመዋጣችን በፊት ሌሎችንም ከማድረግ በፊት ከበፊት ህወታችን አንፃር አሁን ላይ የነበረንን የስሜት መዋዠቆች ካጋጠሙን ወደ psychiatrist ወይም psychologist ጋር ለመታየት እንሞክር።
የትኛውም የ ዲስኦርደር አይነት በህክምና መዳን የሚችል ነው።
@ourrthought
Forwarded from ሀሳቦቻችን (Haileab Atsede)
ጋዜጠኛው ፦" ጋሽ ስብሃት "
ስብሀት ፦ " ለበይክ "
ጋዜጠኛው፦ " አንተ ኮ ታዋቂ ደራሲ ነህ ለምንድነው የግል መኪና የሌለህ?"
አንገቱን አቀርቅሮ ለትንሽ ደቂቃ ቆየ
ስብሀት፦'' ምን አገባህ "
"እንዳልልህ አሳዘንከኝ ጥያቄህ የዋህነት ይነበብበታል ግን እንካ ልንገርህ....ከንቲባና ደራሲ በእግሩ ነው መሄድ ያለበት። በህዝብ መሃል መሹለክለክ ፤ ትንፋሹን መተንፈስ ፤ ለቅሶዉን ማልቀስ ፤ ሲያስነጥሰው ማስነጠስ ፤ ደስታውን መደሰት ወዘተ....።
እነሱን እየፃፍኩ እነሱን እየኖርኩ ጉሮሮዬን እደፍናለው ከንቲባም ስለነሱ እያወራ ይሰነብታል ሁለታችንም እሚያኖረን ህዝብ ነው። ታድያ ይሄን ማግኘት የምትችለው በእግርህ ስትሄድ ነው። አንተንስ በእግሬ ባልሄድ አገኝህ ነበር?" ጨረሰ።
ባሁን ጊዜ ከንቲባ በግሩ ያለፈበት ሰፈር ጭንቀቱ አይጣል ነው። ባያዩን ሆኗል ፀሎቱ ለምን ቀጣዩ እጣው ግልፅ ነው።
@ourrthought
20250403_193306
Your recordings
ርዕስ :- መዋቲነት
ዝግጅት :- ፍሉይ አለም
ምንጭ :- ፍልስፍና ከ ሶቅራጠስ እስከ ዘርዐያቆብ
ዝግጅት :- ፍሉይ አለም
ምንጭ :- ፍልስፍና ከ ሶቅራጠስ እስከ ዘርዐያቆብ
Forwarded from ሀሳቦቻችን (Haileab Atsede)
የስነ ልቦና አማካሪዎች (Psychologist) ደንበኞቻቸውን በሚያማክሩበት ወቅት የሚጠቀሙትን ዘዴዎ ላካፍላቹ።
አሁን አሁን ሰዎች በተለያዩ ምክንያት ቶሎ የመከፋትና የማዘን ነገር እየበዛ መጥቷል እና የሆነ ሰው ጓደኛህ ወይ ቤተሰብህ ሊሆን ይችላል ማንኛውንም ችግር ይሆናል ወይ ያለበትን ጉዳይ ሲያዋይህ ይህን አድርግ :-
1.
አትውቀሳቸው/ አትፍረድባቸው (Don't judge) :- በቻልከው አቅም አትፍረድባቸው። አንዴ ገብተውበታልና እንዴት እንዲ ታደርጋለህ? ምን አይነት ሰው ነህ? አትበሏቸው። ማንም ሰው ችግርን ፈልጎ አይመርጥም ፡ በቃ ምንም አትበላቸው ፀጥ በላቸው ካልሆነ የምትፈርድባቸው ከሆነ ድጋሜ ችግራቸውን ሊያዋዩህ አይመጡም። አለም ሁሉ ይፈርድባቸዋል ታዲያ ቢያንስ አንተ ለየት በልላቸዋ። ለዛ ነው ሰዎች ብዙ ጊዜ ለማንም የማይናገሩት ጉዳይ ለ ንስሀ አባታቸው መንገር የሚቀላቸው ለምን ብትል በጥፋታየው አይወቅሷቸውም።
2.
ማዳመጥ (Active Listening) :- አንዳንድ ሰዎች ገና ችግርህን ለመናገር እኔኮ እንደዚ ሆኜ ስትላቸው ወይኔ የኔን ብታይ ምን ልትል ነው? ብለው ችግራቸውን መቀባጠር ይጀምራሉ አንተም የሆድህን ጉድ በሆድህ ይዘ ትመለሳለህ። እና አዳማጭ ሁን በቃ አንዳንዴ ሰዎች የሚያዳምጣቸውን ብቻ የሚፈልጉበት ጊዜ አለ። እንድትመክራቸውም አይፈልጉም የሆነ ጊዜያቶች አሉ ጭንቀቱ ሊያፈነዳቸው ደርሶ ሸክማቸውን ማቅለል ብቻ ነው የሚፈልጉት። አንተም ዝም ብለህ አድምጥ አትምከራቸውም ሰምተህ ዝም እነሱም ቅልል ይላቸዋል። የማዳመጥ ችሎታህ እንዲጨምር ረጃጅም የ YouTube podcast ተመልከት የማዳመጥ ችሎታህ ይጨምርልሀል።
ታዲያ በምታዳምጥበት ጊዜ እየሰማኸው እንደሆነ እንዲያውቅ በመሀል በመሀል ጭንቅላትህን ማነቃነቅ (nodding) እና "አሀ" ማለት በየመሀሉ የዛኔ መስማትህን ሲያውቁ ይበረታታሉ።
3.
ሸክማቸውን እንዳንተ ሸክም ማየት (Empathy) :- ይሄ ደሞ እራስህን በነሱ ባሉበት ቦታ ተክተህ ማሰብ ነው። እኔ በነሱ ቦታ ብሆን ወይ የኔ ቤተሰብ ወይ ፍቅረኛ ቢሆኑስ ምን ማድረግ እችል ነበር? ብለህ ማሰብ ነው። ይሄ ቢያንስ ፈራጅነትህን ይቀንስልሀል።
እኔ ይሄን ለማወቅ መካነ አዕምሮ (University) ገብቼ ነው የተማርኩት። ለምትኖሩበትም ህይወት ይጠቅማቹሀል እና ተግብሯት።
የቀሩ ጥበቦችን በሌላ ጊዜ ፅፍላቹሀለሁ።
@ourrthought
Forwarded from ሀሳቦቻችን (Haileab Atsede)
የቀለም ስነ ልቦና (Color Psychology)
ለምንድነው ሀኪም ቤት ስሄድ ነጭ ቀለም የሚቀባው? ብለህ ታውቃለህ ወይም ስጋ ቤት? የተለያዩ የንግድ ተቋማት የሚጠቀሙትን ቀለም ለምን መረጡት ብለህስ ታውቃለህ? እንዲያ ቀለሙ ስላማረ ብቻ የሚቀቡት ከመሰለህ ተሳስተሀል ወዳጄ። እያንዳንዱ ትልልቅ ንግድ ተቋም የምታያቸው ድርጅቶች በዚህ በቀለም ስነ ልቦና ነው የሚመሩት። ሁሉም ቀለም የራሱ የሆነ ስነ ልቦና (psychology) አለው።
የ ቀለም ስነ ልቦና(color psychology) ምንድነው እንዴትስ ነው ባህሪያችን ላይ ተፅዕኖ ያለው የሚለውን እንመልከት።
ቀለም በጣም ትርጉም እንዳላቸውና ተፅዕኖ እንደሚያደርጉብን እና ባላሰብነው ሁኔታ (unconsciously) እንዴት ተፅዕኖ ያደርጉብናል የሚለውን neurological psychologist ሲመራመሩበት ቆይተዋል። ለምሳሌ ቃለ መጠይቅ (interview) ቢኖርብህና ቡርቱካንማ ቀለም ያለው ልብስ አድርገህ ብትሄድ ሀሳብህን እንዲቀበሉትና ካንተ ሀሳብ ጋር እንዲስማሙ የማድረግ ዕድሉ ሰፊ ነው። ለምሳሌ በ ሀኪም ቤት ነጭ ቀለም እና ነጭ ጋወን ያደረጉ ሀኪሞች ነው የምታየው ምክንያቱ ለምን መሰለህ ነጭ ቀለም ከ ንፅህና እና ከሰላም ጋር ነው ቁርኝነቱ እና ታመህ ሀኪምህ ነጭ ለብሶ ሲመጣ ውስጥህ የመዝናናት እና የመፍታታት ነገር ይሰማሀል ከህመምህ በላይ ወደ ውጪኛው አከባቢህ ትክረትህን እንድታደርግና በሽታው እንዳይሰማህ ይረዳሀል። እንዲሁም ነርስህ ሰማያዊ ልብስ ለብሳስትመጣ ሌላ የሚሰማህ ነገር አለ። ሰማያዊ ቀለምን አዕምሮዋችን የሚረዳው ከመረጋጋት እና ከታማኝነት አንፃር ነው። ዋና ቀለም ከሚባለው ስስጥም አንዱ ነው። በዛ ላይ ተፈጥሮን ይወክላል ከሰማይ ጋር ቁርኝነት አለው። እንዲሁም ቀይ ቀለም ከድርጊት ጋር ከድፍረትና ቆራጥነት ጋር የተያያዘ ቀለም ነው። ለምን ይመስልሀል ዘመን ባንክን በቀይ ያሽቆጠቆጡልህ ቀለም አጥተው ነው የሚመስል? እንዳልኩህ ነው። ዘመን ባንክ ስልህ ቆራጥነት ጀግንነት ሀብት ወደ አዕምሮህ ይሄዳል ይሄም ከቀይ ቀለም ጋር ግንኙነቱ ጥብቅ ነው።
ስለዚህ አሁን ላይ ለምንድነው ከተማውን ግራጫ ለመቀባት የፈለጉት? የሚለውን እንመለከታለን። አሁን ላይ አዲስ አበባ ፎቁ ፡ ሰፈሩ ፡ መንደሩ ሁሉ በሚባል ደረጃ በግራጫ ቀለም ለምን እንዲጥለቀለቅ ተፈለገ? እንደው ለውበት ነው የሚመስልህ? ተሳስተሀል ምንም አይነት ነገር ሲወሰን ያለ ምክንያት አይደረገም በብዙ ጥናት ነው የሚወስኑት ፡ ላንተ ግን የሚታይህ ያው ለውበት የሚለው ነገር ወይ ደሞ ዘመናዊነት ነው የሚመስልህ። ስለዚህ የግራጫን ቀለም ስነ ልቦና ለማወቅ ፅሑፍና ቪዲዮ ሳገላብጥ ያገኘሁትን አስደንጋጭ ወይ አስገራሚ ሳይኮሎጂ ላካፍላቹ።
በመጀመሪያ ዋና ዋና (primary color) የሚባሉት በዋናነት አራት ናቸው። አረንጓዴ, ቀይ, ሰማያዊ እና ቢጫ ናቸው። እኚ ቀለሞች ሁሉም ከተፈጥሮ ጋር ይቆራኛሉ አረንጓዴ ልምላሜ ፡ ቢጫ ከአደይ ከተስፋ ከፀሐይ መውጣት ፡ ቀይም ከፀሀይ መግባት ፅጌሬዳን እንዲሁም ሰማያዊ ባህርን ሰማይን ይወክላሉ። ሌሎቹ እነዚህ ሲደባለቁ የሚሰጡት ስብጥር ቀለም ናቸው።
ታዲያ ግራጭ ቀለም ውልደቱ ከየት ነው አትልም አረ በል ወገን ፡ ግራጫ ማለት ነጨ ያልሆነ ጥቁርም ያልሆነ በሁለቱ መሀል የሚወላውል ማንነቱ ግራ የገባው ቀለም ነው። ፍዝ ቀለም ነው። በ ስነ ልቦናው (psychology) አጠራር ፡ ምንም አስተዋፅኦ የሌለው(non contributor or zero involvemnt) ከንቱ ቀለም የሚባል አይነት ነው። እንዳልኩሁ ግራ የገባው ማንነት አልባ ከመሆኑ የተነሳ ግራጫ ቀለም ብቻ የተቀባበት አከባቢ ብትሄድ የ መጨነቅ ፡ የመደበር የ መቀርዘዝ እንዲሁም ዝጋታም (mute) ነው የምትሆነው። ሀገር አማን ብለህ ከቤት ደስ ብሎህ እየፈነጠዝክ ወጥተህ አራት ኪሎ ታክሲ መያዧ ጋር ትንሽ እንደቆምክ ድብርት እና ጭንቀት ሳታስበው ይፈናጠጥብህል አንተ የሚመስልህ በራስህ ጉዳይ የተደበርክ ነው ግን እንዳይመስልህ የግራጫው ተፅእኖም ሊሆን እንደሚችል መሆኑን ማሰብ አለብህ። ታዲያ ይሄን ባጋጣሚ የሚያደርጉት ይመስልሀል? ወዳጄ እንደዛ ከመሰለህ ሞኝ ነህ ማለት ነው። ግራጫ በብዛ ቁጥር ቅርዝዝና ጀዝባ ነው የምትሆነው። እንደውም መራገም ስትፈልግ አቦ ህይወትህን ግራጫ ያድርግብህ ብትለው ከባድ ዕርግማን በለው ምክንያቱም ግራጫ ጭንቀት : ድብርት ፡ መከፋት ነው። ግራጫ ቀለም ብቻ ያለበተ ሰፈር ብትሄድ እናቱ ገበያ እንደሄደችበት ልጅ አልቅስ አልቅስ ነው የሚልህ ከፍቶህ። እንዲሁም አረንጓዴ የሚቀቡትን እረጃጅም ቆርቆሮ ከተማው ላይ ስታይ ልምላሜ ብቻ አይምሰልህ አያይዘህ እንድታስብ የሚፈለጉ ነገሮች አሉ ለዛ ነው በኮሪደር ልማት ትንሽ ብትንሸራሸር ቤትህ ፈርሶ የተተከለው ዛፍ ሳይሆን ሀገራችን ዕድገት ነው ትውስ ብሎህ ፀሐዩ መንግስታችን የምትለው ተፅዕኖ ከባድ ነው።
Google company ፊት ለፊቱ ላይ ስትገባ (Dash board) ላይ ያሉትን Google የሚለውን ስሙን ቀለም በመቀየሩ ብቻ ገቢውን በቢሊየን ነው የጨመረው። እንዲሁም coca cola ጠርሙሱን በቀይ በማድረጉ ደንበኞቹን ጨምሯል። ለምሳሌ እነ አሜሪካ ከባባድ ወንጀል የሚሰሩ ሰዎችን ነጭ በነጭ ክፍል ከነጭ አገልጋና ልብስ ጋር ነበር የሚያስሯቸው ለምን? አትልም ከጊዜ በኋላ ያን ነጭ ከማየት ብዛት አይነ ስውር እንዲሆኑ በማሰብ ነው። ታዲያ እያንዳንዱ ቀለም አዕምሮዋችን ላይ እና ስሜታችን ላይ እንዲሁም በውሳኔያችን እና በምርጫችን ላይ ተፅዕኖ አላቸው። በ አከባቢህ እንዲሁም በየቦታው የምታየው የቀለም አይነት ፀባይህ ላይና አስተሳሰብህ ላይ የራሱን አሻራ ያሳርፋል።
ቢያንስ ለዚህ ነገር ንቁ በሆንን ቁጥር ከተፅዕኖ ለመውጣትና ንቁ (conscious) ለመሆን ይረዳናል። ማወቅ ይጠቅማልና አከባቢያችሁን እወቁ። ድብርትህ ያንተ ላይሆን ይችላል ምናልባት ከውጪ የሚለገስህ እንደሆነም አስብ።
@ourrthought
Forwarded from ሀሳቦቻችን (Haileab Atsede)
አነቃቂ ተናጋሪዎች(Motivational speakers) ለምን እንደማይመቹኝ ከ psychology አንፃር በምክንያት ላስረዳ:-
የ ስነ ልቦና አማካሪዎች (psychologist or counselor) በዋናነት ለምን ተቋቋሙ ወይ ደሞ ትልቁ ግባቸው ምንድነው? ብለን ብንጠይቅ እንደ መጨረሻ ግባቸው የሚወስዱት የሚያተኩሩት ሁለት መሠረታዊ ነገሮችን እናገኛለን።
1. የመጀመሪያው አላማ አንድ በችግር ውስጥ ያለን ግለሰብ በ አከባቢው ካለ ሀብት(resource) ጋር ማገናኘት ነው። በዙሪያው ያሉትን እሱን ሊደግፉትና ሊረዱት ከሚችሉት ነገሮች ጋር ማገናኘት ወይ ደሞ እንዲገነዘብ ማድረግ እንደማለት ነው። ለምሳሌ እኔኮ ብቸኛ ነኝ ሰው የለኝም የሚል ሰውዬ ቢኖር ሰውየውን ቤተሰቦቹን ፡ ጓደኞቹን ፡ ጎረቤቱን አከባቢውን እንዲገነዘብን ማድረግ ከተገነዘበም በኋላ ሌላ ጊዜ ችግር ቢያጋጥመው እነዚህን ሀብቶች ተጠቅሞ በራሱ ችግሩን እንዲፈታ ማድረግ ነው።
2. ግለሰቡ የራሱ የችግር ፈቺ (self counselor) እንዲሆን ማድረግ ነው። ችግር በመጣበት ጊዜ ነገሮችን በራሱ መንገድ እንዲፈታ የማስቻል ጥበብ ነው። ለትንሹም ለትልቁም ጉዳይ አማካሪዎች ጋር ሳይመጣ ችግርን የመፍታትና የመቋቋም ዘዴ በራሱ መንግድ የሚዘረጋበትን ዘላቂ መንግድ መዘርጋት ነው።
በዚህ መሠረት ካየነው ግቡ የዘላቂ መፍትሄ እንጂ ጊዜያዊ ነገር ላይ ያተኮረ እንደሆነ እንረዳለን። ከዚህም ጋር ተያይዞ ካነሳን አይቀር የስነ ልቦና አማካሪዎች 100% ከችግርህ እንድቶጣ ላያደርጉህ ይችላሉ። 80% የሚሆነውንም መፍትሄ ከራስህ ሀሳብ የሚመነጭ እንጂ እነሱ ይሄን አድርግ ይሄን አድርግ አይሉህም ግን ያለኽበትን ችግር እንድትረዳውና መፍትሄውን በራስህ እንድታመነጭ ነው የሚረዱህ። የተቀረው 20% ደግሞ ከችግሩ ጋር ተላምደህ በማይጎዳህ ሁኔታ የምትኖርበትን መንገድ ይዘረጉልሀል። እንጂ የግድ ሁሉም ችግር ተቀርፎ 0% ሆኖልህ ትመለሳለህ ማለት አይደለም። ለምሳሌ ከፍተኛ የፍርሀቻ ችግር ቢኖርብህ ከፍራቻህ እንድትላቀቅ ሳይሆን ከፍራቻህ ጋር በዘዴ ማዋሀድ እና ፍራቻ የሚፈጥርብህን ተፅዕኖ በመቀነስ ከራስህ ጋር የማዋሀድ ስራ ነው ማለት ነው።
ይሄ ሁሉ ሆኖ ሳለ አነቃቂ ንግግር አድራጊዎች ወይ ደሞ self help የሚባሉት ግን ከዚህ በተቃራኒው ሁሌ ለችግርህ ሁሉ መፍትሄውን ከነሱ እንድትቀበል ጥገኛ የሚያደርጉህ ሰዎች ናቸው። ለእያንዳንዱ ነገር መፍትሄ ፍለጋ እንሱ ጋር አንድትማትር እንጂ የችግርህ ፈቺ እንድትሆን አይፈልጉም ያን ካደረጉ ነፃ ወተህ ገቢያቸውን ታሳጣቸዋለህ። ሌላው ደሞ ዘላቂ መፍትሄ በፍፁም አይሰጡህም አሁን ያለህበትን ሁኔታ ብቻ በማነቃቃት ሂፕኖታይዝ በማድረግ አደንዝዘው ወደ ቤትህ ይልኩሀል እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ሲያምርህ ይቅር ሁሌም ቢሆን መማተር አለብህ ሽንቴን ልሽና? ምግብ ልብላ? ልብስ ላድርግ የሚለውን ሁላ ሳይቀር የጥገኝነትን ጫፍ ያሳዩሀል ያለነሱ ከንቱና ደካማ እንደሆንክ ያሳምኑሀል ብቻህን ቀሽም እንደሆንክ ግን ከነሱ ጋር ገነትን እንደምታይ ይሰብኩሀል።
መፍትሄውን በራስህ መንገድ እንድታመነጭ ሳይሆን እነሱ በራሳቸውና በሚመስላቸው መንገድ መፍትሄ ይሰጡሀል እንደዚ አድርግ ይሄን ማድረግ አለብህ ይሄ አይገባህም ብለው የራሳቸውን ቅዠት ይጭኑብሀል አንተም ግራ እንደተጋባህ በሰው ምክርና ሀሳብ በሬ ሆይ በሬ ሆይ እንደሚሉት መጨረሻህ የከፋ ይሆናል።
ለስንፍናህ ለብርታት የሚያነቃቃ ነገር ከውጪ የምትፈልግ ከሆነ መፍትሄው ሲደናገርህ ትኖራለህ። ከችግርህ በላይ የሚያነቃቃ ነገር ከየትም የለም።
@ourrthought