Telegram Web
እንዳትቀሩ
እሁድ ታህሳስ 11
ከ 8.00 ጀምሮ

ትባረኩበታላችሁ
እንዴት የፍቅር ጥያቄ እናቅርብ ||
4 ክርስቲያናዊ መንገዶች

1.እሷ እስክትጠይቅህ አትጠብቅ
- እንደምትወዳት እርግጠኛ ከሆንክ እና እሷም ለአንተ ያላትን ስሜት በተለያየ መንገድ አሳይታህ ከሆነ አንተ ቀድመህ ብትጠይቅ መልካም ነው።[ ሴት ልጅ የፍቅር ጥያቄ ማቅረብ የለባትም እያልኩ አይደለም ]
- ከምትወዳት ሴት ጋር የመኖር ፍላጎቱ ካለህ የመጠየቅ ሐላፊነት እንዳለብህ አትዘንጋ።[ እሷ እስክትጠይቀኝ ልጠብቅ ካልክ ረጅም ጊዜ ሊፈጅብህ ይችላል ሲቀጥል ቀድሞ የነበረህን የመጠየቅ እድል ልታጣ ትችላለህ።]
- አስተውል እምቢ ልትባልም ትችላለህ ስለዚህ እሺ ብትልህም እምቢ ብትልህም ሀላፊነት ለመውሰድ ራስህን ዝግጁ አድርግ።

2. አትሟዘዝ ወይም አታስፈራራ
- እየተቅለሰለስክ ስሜትህን በሙሉ መዘርገፍ ተገቢ አይደለም።[ ይህ ለእሷ ነፃነት አይሰጣትም]
- አንዳንድ ሰው ሊያለቅስ ሁላ ይችላል ይህ ደግሞ እጅግ መጥፎ ነው። በዚህ ጊዜ እሺ ብትልህ እንኳን በዋናነት አሳዝነሀት እንጂ ወዳህ ላይሆን ይችላል።
- አንዳንዴ እንደ ጥሩ ጓደኛ አብራችሁ ከቆያችሁ እና ያን ጓደኝነት ወደ ፍቅር ሲቀየር ሙሉ ስሜትህን በአንዴ ብትዘረግፍ ችግር ላይኖረው ይችላል ምክንያቱም አስቀድማ ስለምታውቅህ ግን እንዳታለቅስ።
- ሌላው ከመሟዘዝ በተቃራኒው በጣም ብዙ ነገር በማለት ማስፈራራት ተገቢ አይደለም። ይህም ነፃነት አይሰጣትም ይረብሻታል።
- በህልሜ አይቼ ፣ አገልጋይ ተናግሮኝ የሚሉ ነገሮችን ፈፅሞ አትግለፅ ምናልባት አይተህ እንኳን ቢሆን ማለት ነው።[ በዚህ ጊዜ እሺ ብትልህ እንኳን ፈርታ እንጂ ወዳህ ላይሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ሁለታችሁንም ይጎዳችኋል።]

3. በዙርያዋ ላሉ የእኔ ለምትላቸው ሰዎች አክብሮት ይኑርህ
- ከወንዶች በበለጠ ለማህበራዊ መስተጋብር ሴቶች ትልቅ ትኩረት ይሰጣሉ።
- ከቤተሰቦቿ ከጓደኞቿ ጋር የሆነ ያክል መቀራረብ ቢኖርህ መልካም ነው።[ እሷ ዋጋ ከምትሰጣቸው ነገሮች ዋጋ መስጠትህ እሷ በተራዋ ለአንተ ዋጋ እንድትሰጥህ ይረዳሃል።]
- ይህን ማድረግ ያለብህ ስለሆንክ እንጂ እሷን ለማግኘት ማስመሰል የለብህም።[ ሴቶች ስታስመስል ጠንቅቆ የማወቅ ጥበብ አላቸው። ]

4. ራስህን በመሆን እና ትክክለኛ አላማ ይዘህ ጠይቅ
- ውሸትን መሰረት አድርገህ ፈፅሞ የፍቅር ቀጠሮ አትጀምር።
- የእጮኝነት ግቡ ትዳር እንደሆነ ጠንቅቀህ በማወቅ ጉዞ ጀምር።
- መፅሐፍ ቅዱስ ከሚለው አትጨምር አትቀንስ። [ ከአህዛብ ጋር እንዳንጋባ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ]
(ወደ ዕብራውያን ምዕ. 4)
----------
12፤ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤

13፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።


መልካም ቀን❤️🤍💙
#share #HENONSTUDIO #subscribe Protestant Mezmur “የመልካም መጀመሪያ"…
Henon Studio OFFICIAL
▯▷ ● የመልካም መጀመሪያ ● ◁▯
🎙 Yidnekachew Nibret
💽 New Live Worship Song
Duration: 8:36 Min
📥 Size: 8.09MB

ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ
━━━━━━⊱ ♻️ ⊰━━━━━━
SHARE || @DAILY_VERSE
━━━━━━⊱ ♻️ ⊰━━━━━━
መዝሙር 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
² ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።
³ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
⁴ ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥ ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው።
⁵ ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
⁶ እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።
👍👍👌ምርጥ ባህሪያማ ማንነት 👍👍

★. ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

★. አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር
ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን

★. ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት

★. ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

★. ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

★. አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

★. በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

★. የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናገር

★. ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

★. ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

★. ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

★. የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

@proverbs_christians_tube
"ፕሮስኪኒዮ"
(Proscuno)
ስለ አምልኮ ጥልቅ የሆነ ትርጓሜ ካላቸው የግሪክ ቃላት አንዱ ሲሆን ትርጓሜውም፦
🤲 የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን እጅ ወይንም 🦶 እግር መሳም ማለት ነው።
ምሳሌ፦ ውሻ ባለቤቱ ጋር ሲመጣ የባለቤቱን እግር ይልሳል... እላዩ ላይ ይጠመጠማል... የማይሆነው ነገር የለም...🐕 ለምን ሲባል ጌታው ነዋ የሚያኖረው፣ የሚያበላውና የሚያጠጣው እርሱ እስካ ድረስ እንደሚኖር ስለሚያውቅ ነው።
🙏 በተመሳሳይ መልኩ አምልኮ ማለት በእግዚአብሔር ፊት በዚህ መረዳት እንደዛ መሆን ማለት ነው።

💎ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ 💎
ፍቅር ምንድን ነው?

1. ፍቅር ማለት አንዱ ሌላውን ለመርዳት. መሞከር ማለት ነው!!
- ፍቅር ማለት መስዋዕት መሆን ማለት ነው!!

2. ፍቅር ማለት መልካም ማለት ነው!!
√ ክፋት በፍቅር አለም ፈፅሞ የለም::

3. ፍቅር ማለት መልካም ቃላትን መለዋወጥ ማለት ነው!!
√ ፍቅር የሀጢዐትን ብዛት ይሸፍናል::
- 1ኛ ጴጥ. 4:8

4. ፍቅር ማለት በፍቅር(በትዳር) አጋር መካከል ያለ የይቅር ባይነት መንፈስ ነው::
√ ቂምን አይይዝም ብድር አይመልስም::
- 1ኛ ቆሮ 13:14-17

5. ፍቅር ማለት አንዱ ራሱን ለሌላው አሳልፎ መስጠትና መስዋዕት መሆን ማለት ነው!!

6. ፍቅር አንዱ ለሌላው ፈገግ ብሎ ደስታ ማሳየት ነው!!

7. ፍቅር ማለት አንዱ ሌላውን ማሞገስና ማመስገን ማለት ነው::

8. ፍቅር ማለት ስሜት ብቻ ሳይሆን አንዱ ለሌላው መልካም ነገሮችን ማሰብና ማድረግ ነው::
√ ፍቅር በስራ ይገለጣል!!
√ የባልና ሚስት ዋና ሀብታቸውና ንብረታቸው ወይም ቀሪ ገንዘባቸው በሞት እስኪለያዩ ድረስ የሚኖረው ፍቅር ነው!!

9. ፍቅር በጋብቻ ውስጥ ሆኖ አንዱ ሌላውን በግብረ ስጋ ግንኙነት ማስደሰትንም ያካትታል!
√ የግብረ ስጋ ግንኙነት ግን ፈፅሞ የፍቅር መለኪያ አይደለም::

10. ፍቅር ማለት አንዱ ሌላውን መታገስና ተስፋ አለመቁረጥ ነው::
√ ፍቅር ወደፊትም ተስፋ ያደርጋል!!


#ሼር
@proverbs_christians_tube
#Repost


(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3 )
------------
2፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።

3፤ ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፤
2024/11/17 05:12:25
Back to Top
HTML Embed Code: