Telegram Web
ስነ ልቦና ምንድን ነው? ስል ምን ያጠናል?
.
ሳይኮሎጂ  የሚለው ቃል ሳይኪ (ψυχή)  እና ሎጊያ (λογία) ከሚሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የተዋቀረ ነው። ሳይኪ "ነፍስ" ወይም "እስትንፋስ"ን ሲወክል ሎጎስ ማለት ደግሞ "ጥናት"ን ያመለክታል። ቃል በቃል ሳይኮሎጂ ማለት "ስለ ነፍስ የሚያጠና" የትምህርት ዘርፍ ማለት ነው።

ሰፋ አድርገን በዘመናዊ መነፅር ስናየው ሳይኮሎጂ ስለ ሰዎች (እንስሳትንም ሊያካትት ይችላል) ስሜት (emotion)፣ ባህርይ (behavior) እና አስተሳሰብ (cognition) የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ነው። የሰው ልጅ ሁለመና ብዙ ጊዜ በሶስቱ ነገሮች ይወሰናል (አንዱ ሌላው ላይ ተፅዕኖ ያደርሳል)። ዘርዘር አድርገን እንመልከተው፦

➊ Cognition (ሀሳብ): የተደበቀ የሰዎችኝ ሀሳብ፣ ዕቅድ፣ ማሰላሰል፣ ስልትና የችግር አፈታት ዘዴን ይጠቁማል።

➋ Behavior (ባህርይ)፡ የሀሳብ ተቃራኒ ሆኖ በግልፅ የሚታይ ድርጊትን ይወክላል (ለምሳሌ፦ አረማመድ፣ አበላል፣ አለባበስ፣ አካሄድ፣ መኮሳተር፣ ፈገግ ማለት...ወዘተ)።

➌ Emotion (ስሜት)። ሌላኛው የሳኮሎጂ የጥናት ማዕከል ስሜት ነው። ስሜት የሚሰሙንን ውስጣዊ ሁኔታ የሚገልጽ ነው (ለምሳሌ፦ ደስታ፣ ሀዘን፣ ንዴት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት...ወዘተ)።

የሰውን ልጅ ውድቀት፣ ስኬት፣ ጤናና ህመምን ለመረዳት ባህርይውን፣ አስተሳሰቡን እና ስሜቱን በጥልቀት መረዳት ያስፈልጋል። ሳይኮሎጂም የሚያደርገው ይሄንን ነው።

ቸር ሁኑልን!!!

@psychoet
23👍8👏2
ቀድሜ ባውቃቸው ኖሮ ያልኳቸው 10  ምክሮች 👌

♻️መዝናናት ማለት መጠጣት፣ ፓርቲ ማድረግ እና ከሰው ጋር መዋል ብቻ አይደለም። መዝናናት ማለት ብቻህን የምታሳልፋት ምሽት፣ መጽሐፍ ውስጥ ሰምጦ ማንበብ፣ ጥልቅ ውይይት ማድረግ、እርምጃ መውሰድ፣ ስነ-ጥበብ መፍጠር፣ ሙዚቃ መጫወት ወይም ስራህን መስራት ሊሆን ይችላል። መዝናናት ያንተ ነው፤ ትርጉሙን የምትሰጠው አንተው ራስህ ነህ።

♻️"እምቢ" ለማለት ብዙ ማብራሪያ መስጠት እንደሌለብህ እወቅና ልማድህ አድርገው።

♻️ለግል ድንበርህ/ወሰንህ ክብር የማይሰጥና የሚቀየምህ ሰው ካለ ችግሩ የራሱ ነው። በህይወትህ ውስጥ ልታስወግዳቸው ከምትችላቸው ሸክሞች ሁሉ ትልቁ ሸክም፣ ሌሎች ሰዎች ስለአንተ ያላቸው አስተያየት ነው።

♻️ጓደኛ ታፈራለህ፤ ታጣቸዋለህም። ስህተት ትሰራለህ፤ ታርማለህም። ትወድቃለህ፣ ትከሽፋለህ፣ ትማራለህ፣ ትገነዘባለህ፣ ከእውነታው ጋር ትጋጫለህ፣ በፍቅር ትወድቃለህ፣ ትጎዳለህም። ራስህን ታጣለህ፤ በመጨረሻም ትጠነክራለህ።

♻️99% የሚሆነው ጉዳት በአዕምሮህ ውስጥ በአንተና በአስተሳሰብህ የሚፈጠር ነው። 1% የሚሆነው ጉዳት ብቻ ነው በእውነተኛው ሁኔታና በውጤቱ የሚከሰተው።

♻️የአዕምሮ ምግብህን አሻሽል።

የአኗኗር ስርአትህ የምትመገበው ብቻ እንዳልሆነ ስትገነዘብ ሁሉም ነገር ይለወጣል። የአኗኗር ስርአትህ የምታየው፣ የምታነበው፣ የምትከታተላቸው ሰዎች እና አብረሃቸው ጊዜ የምታሳልፋቸው ጭምር ነው። ግብህ ጤናማ አዕምሮ እንዲኖርህ ከሆነ፣ ከአዕምሮ ምግብህ ላይ "ቆሻሻ ምግቦችን" ማስወገድ ጀምር።

♻️የምትወደውን ሰው ለመማረክ ብቻ አካላዊ ውበትህ ላይ ብዙ ጊዜ ከማጥፋት ይልቅ አዕምሮአዊ ውበትህን በማሳደግ ላይ አተኩር። ራስህን አስተምር፣ ተደጋጋሚ መርዛማ አስተሳሰቦችህን ተጋፈጣቸው፣ የበታችነት ስሜትህን አስተካክል እና በራስህ ደስተኛ መሆንን ተማር።

♻️ብዙውን ጊዜ ችግሩ ራሱ ችግር አይደለም፤ ችግሩ ስለ ችግሩ የምታስብበት መንገድ ነው። አብዛኛውን ችግሮችህን አስተሳሰብህን በማስተካከል ብቻ መፍታት ትችላለህ።

♻️ከማግባትህ በፊት፣ ስለ ገንዘብ አጠቃቀም፣ ስለ ልጅ አስተዳደግ፣ ልጆቻችሁ በምን አይነት እምነት ማደግ እንዳለባቸው፣ ስለ ልጅነት የስነ-ልቦና ጠባሳዎች፣ ስለ ወሲብ ያላችሁ ምልከታ、ስለ ገንዘብ ነክ ምልከታዎች፣ ስለ ቤተሰብ የጤና ታሪክ፣ ስለ ህልም ቤት፣ ስራና ትምህርት እንዲሁም አዕምሮአችሁ ውስጥ ስለሚመጡ ማናቸውም ነገሮች ተወያዩ።

ፍቅር ብቻውን በቂ አይደለም።

ልጆችህ አንተን ወላጅ በማግኘታቸው ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመፈወስ እንዳይገደዱ፣ ልጆች ከመውለድህ በፊት አንተ ከውስጥ ቁስሎችህ ተፈወስ።

♻️ራስህን ታጣለህ፤ በመጨረሻም ትጠነክራለህ። አስታውስ! እነዚህ የህይወትህ ምርጥ ዓመታት ናቸው። በነዚህ ዓመታት በመደሰት እና እነሱን በማበላሸት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት አለብህ።
©ተዋነይ

#ውብ #ቀን
@psychoet
20
ፅኑ ስብዕና (resilient personality)

....

የወርቅ ንፅህና በእሳት ተፈትኖ እንደሚለየው የሰው ልጅ ፅናትም በመከራ ውስጥ ነው ፍንትው ብሎ የሚወጣው። ለምሳሌ ሁለት ነጋዴዎች በተመሳሳይ ጊዜ ሊከስሩ ይችላሉ። ማንነታቸው ግን የሚወሰነው በደረሰባቸው ኪሳራ ሳይሆን ለኪሳራው በሰጡት ምላሽ ይሆናል። አንዱ ተስፋ ቆርጦ ድባቴ ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፣ ሌላው ደግሞ የተሻለ ለመስራት ሊነሳሳ ይችላል።

ለችግሩ እጅ የሰጠው የመጀመሪያው ሰው ደካማ የፅናት ስብዕና ያላቸው ሰዎች ምሳሌ ሲሆን፣ በችግሩ ያልተበገረው ሁለተኛው ሰው ግን የፅኑ ሰብዕና አይነተኛ ምሳሌ ተደርጎ ሊወሳ የሚችል ነው።

በዚህች አጭር ፅሁፍ የፅኑ ሰብዕና ምንነትና ጥቅሞች እንመለከታለን።

ፅኑ ስብዕና ምንድን ነው?

ፅኑ ስብዕና ማለት በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ተፈትኖ ማለፍ፣ ወድቆ የመነሳትና ችግሮችን ወደ ዕድል የመለወጥ ማንነት ነው። ለመሆኑ፣ የሰብዕናችን የፅናት ደረጃ ከፍ ያለ ወይ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዴት እንለያያለን? ቀጥሎ 6 ነጥቦችን አነሳለሁ፦

ሀ) ቀና አመለካከት (Optimism)

ለነገሮች ያላቸው አመለካከት ቀና ነው። ሁሌም ችግሮች ጊዜአዊ እንደሆኑና "ሁሉ ነገር ለበጎ ነው" የሚል አስተሳሰብ አላቸው።

ለ) ተጣጣፊነት (flexibility)

በታላቅ አውሎነፋስ ውስጥ ብዙ ዛፎች ተገንድሰው ሲወድቁ የዘንባባ ዛፍ 🌴ግን ያንን አውሎ ነፋስ ዝቅ ብሎ ያሳልፍና መልሶ ቀና ይላል። ፅኑ ስብዕና ያላቸው ሰዎችም ልክ እንደ ዘንባባ ለተለያዩ ችግሮች የተለያዩ ምላሾች በመስጠት ያልፉታል፤ መናገር ሲገባቸው ይናገራሉ፣ ዝም ማለት ሲኖርባቸው አያወሩም፣ አንድን ችግር ችክ ብለው በተመሳሳይ መንገድ ለመፍታት አይዳክሩም።

ሐ) አለማስመሰል (Genuine)

ፅኑ ሰዎች ያልሆኑትን መስለው መታየት አይፈልጉም፤ ደካማ ጎናቸውን ለመሸፋፈን አይሯሯጡም።  የሌላቸውን "አለኝ" ለማለት ለታይታ ሲሉ የተለያዩ ጭምብሎችን በማጥለቅ በማጥለቅና በማውለቅ አሳራቸውን አይበሉም።

መ) ተማሪነት

ለመንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ስኬትም ውድቀትም፣ ማጣትም ማግኘትም፣ ከፍታም ዝቅታም አንዳች ትምህርት ጥሎ ከማለፍ ውጪ አንዳች ጠባሳ አይተውባቸውም።

ረ) በሚቆጣጠሯቸው ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ

የፀና ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ማድረግ በሚችሉት ጉዳይ ላይ እንጂ ከእነርሱ ቁጥጥር ውጭ ባለ ነገር ላይ አቅማቸውን አይጨርሱም።

ሰ) ጠንካራ ማሕበራዊ ቁርኝት

ፅኑ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸው እንጂ ብቸኞች አይደሉም።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፅኑ ሰብእና ያላቸው ሰዎች ከሌላቸው አንፃር ሲታዩ ሲበዛ ስኬታማና የተሻለ የአዕምሮና የአካል ጤንነት ያላቸው ናቸው።

ስለዚህ፣ ሁላችንም አይናችን ከሚገጥሙን ተግዶቶች ላይ አንስተን የመውጫ መንገዶችን ብንመለከት፣ ከማለቃቀስ ይልቅ የማንቀይረውን የሕይወትን ሰንጣቃ ብንቀበልና በሁሉ ብንደሰት የስኬት መንገድ ላይ መሆናችን አያጠያይቅም
7👍6
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
1. ‹‹ እኔ ሃይማኖተኛ ነው የምለው የሌሎችን ስቃይ የሚረዳ ሠውን ነው፡፡ ››

2. ‹‹ በዓለም ላይ እውነተኛው ሠላም እንዲሠፍን ከፈለግን ልጆችን ስለሠላም ማስተማር መጀመር አለብን፡፡ ››

3. ‹‹ ዓለም ላይ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ሁን፡፡ ››

4. ‹‹ መንፈሳዊ ጥንካሬ ከማይበገር ውስጣዊ ፈቃድ እንጂ ጡንቻን በማሳበጥ አይመጣም፡፡ ››

5. ‹‹ ነፃነት የመሳሳት ነፃነትን ካላካተተ በራሱ ዋጋ የለውም፡፡ ››

6. ‹‹ ማንም ሠው እኔን ከራሴ ፈቃድ ውጪ ሊጎዳኝ አይችልም፡፡ ››

7. ‹‹ ፀሎት ጧቱን መክፈቻ ቁልፍና እና ማታውን ማጥበቂያ ብሎን ነው፡፡ ››

8. ‹‹ ራስህን ለማግኘት ምርጡ መንገድ በአንተ ውስጥ ያለውን የሌሎች ማንነት መጣል ነው፡፡ ››
9. ‹‹ እንዴት ማሠብ እንዳለባቸው የሚያውቁ ሠዎች መምህር አያስፈልጋቸውም፡፡ ››

10. ‹‹ለመሞት ተዘጋጅቻለሁ፣ ለመግደል ግን የምዘጋጅበት ምንም ምክንያት የለም።››

11. ‹‹ መልካም ሠው ሕይወት ላላቸው ነገሮች ሁሉ ወዳጅ ነው፡፡ ››

12. ‹‹ ዓይንን በዓይን የሚለው ህግ መጨረሻው ዓለምን በሙሉ አይነስውር ማድረግ ነው፡፡ ››

13. ‹‹ ደስታ ማለት የምታስበውን ነገር፣ የምትናገረውን ነገርና የምታደርገውን ነገር ከሌሎች ጋር በመስማማትና በመዋሃድ የምታመጣው ሲሆን ነው፡፡ ››

14. ‹‹ ደካሞች ይቅር አይሉም፡፡ ይቅር ማለት ወይም ይቅርታ ማድረግ የጠንካሮች መገለጫ ነው፡፡ ››

15. ‹‹ ራስህን ስለሆንክና ትክክል ስለሆንክ ብዙ ሠዎች በተለይም አላዋቂ የሆኑ ሠዎች ሊቀጡህ ወይም ሊጠሉህ ይፈልጋሉ፡፡ ለትክክለኛነትህ ይቅርታ አታድርግለት፡፡ ትክክል ከሆንክና ትክክል መሆንህን ካወቅክ ለአዕምሮህ ንገረው፡፡ ምንም እንኳን ከታናናሾቹ አንዱ ብትሆንም እውነት አሁንም እውነት ነው፡፡ ››

16. ‹‹ አንድ ግራም ተግባር ከብዙ ቶን ስብከት በላይ ዋጋ አለው፡፡ ››

17. ‹‹በዓለም ላይ የሰውን ስግብግብነት ለማሟላት ሳይሆን ለሰው ልጅ ፍላጎት የሚበቃ በቂ ነገር አለ።››

18. ‹‹ ሠው ማለት የአስተሳሰቦቹ ብዜት ነው፡፡ የሚያስበውን ነውና የሚሆነው፡፡››

19. ‹‹ ያለአንዳች ተግባር የትም መድረስ አትችልም፡፡ ››

20. ‹‹እውነተኛ ሀብት የሆነው የወርቅና የብር ቁርጥራጭ ሳይሆን ጤና ነው።››

የትኞቹን አባባሎች ወደዳችኋቸው? comment አድርጉልን

አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏
—————————————————
አስተማሪ ሃሳቦች የምናጋራባቸውን የማህበራዊ ገፆቻችንን በመከተል ቤተሰብ ሁኑ። ታተርፋላችሁ:-

© የህይወት ፍልስፍና
👍1910
ባይረዱህም አትሞትም…

ስራ መስራት ስትጀምር ከሚያጋጥሙህ ነገሮች መካከል አንዱ በማይገባ መልኩ ሰዎች ሊረዱህም ሆነ ሊገነዘቡ ይችላሉ። አንዳንድ ሰው ከስራህ አንፃር ሳይሆን ዝም ብለው ሊጠሉህም ይችላሉ። ይሄ አንተ ምንም አደረክ ምንም መጥላታቸውን ሆነ ክፉ ምልከታቸው አይተዎም። ችግሩ ያለው እነሱ ጋር ነው።

ሌላኛው ስራ ስትሰራ የሚያስቸግሩህ የቅርብ ሰዎች ናቸው፤ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ጉረቤት፣የትዳር አጋር፣
ፍቅረኛ፣ የልብ ጓደኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ህልምህ አለኝ ብለህ ስትነሳ ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቀም ብለው ያጣጥሉብሃል። አንዳንዴ የቅርቤ ከምትላቸው ሰዎች ይልቅ በሩቁ የሚያውቁ ሰዎች ለስራህ ቦታ ይኖራቸዋል። ይህም ቢሆንም አለመረዳታቸው አይገልክም። አልተረዱኝም፣ አልረዱኝም ብለህ ህልምህ መቼም
አታቁም።

እየተሰደብክ ነው የምትቀጥለው፤ እየተጠለህ ነው የምትቀጥለወ፤ እየተተቸህ ነው የምትቀጥለው፣ ቢሆንም ግን ጥሩ መስራት መቀጠል አለብህ፤ ህሊናህ የማያቆሽ ከሆነ፤ ከፈጣሪ ጋር የማያጋጭህ ከሆነ ስራህን መቀጠል ነው።

©ህልመኛው

🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት

ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
@psychoet
Join and follow our page
13👍4
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
በህይወት ውስጥ ሁልጊዜ ደስተኛ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

❤️ሁሉም ሰው ችግሮች አሉበት። አንተ ብቻ አይደለህም።
(ችግር የሌለበት ሰው የለም። በዚህም አንተ የተለየህ አይደለህም።)

❤️ ሁሉም ሰው ከባድ ጊዜያትን ያሳልፋል። ፈተና የማይገጥመው በሕይወት የሌለ ሰው ብቻ ነው።
(በህይወት እስካለህ ድረስ ውጣ ውረድ አይለይህም።)

❤️ እያንዳንዱ ችግር መፍትሔ አለው። የተሻለ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርጉ መንገዶችም አሉ።
(ተስፋ የሚቆረጥበት ምክንያት የለም፤ መውጫ መንገድ ሁሌም ይኖራል።)

❤️ስለራስህ የምታስበው ነገር ደስታህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ልዩ እና ጠቃሚ እንደሆንክ እመን። አሉታዊ ሀሳቦች እንዲቆጣጠሩህ አትፍቀድላቸው።
(ለራስህ ጥሩ አመለካከት ይኑርህ፤ ክፉ ሀሳብ ቦታ አትስጥ።)

❤️ሌሎች በሚሉት ነገር አትጨነቅ። አንዳንድ ሰዎች አንተን ለመጉዳት አስበው መጥፎ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ።
( የሰዎችን ሀሜትና አሉታዊ አስተያየት ችላ በል።)

❤️ደስተኛ ከሚያደርጉህና አዎንታዊ አመለካከት ካላቸው ሰዎች ጋር ጊዜህን አሳልፍ። በአንተ ወይም በውጣ ውረዶችህ ላይ ከሚሳለቁ ሰዎች ራቅ።
(ጥሩ ጓደኞችን ምረጥ፤ ከሚያሳንሱህና ከሚያሳዝኑህ ራቅ።)

❤️የትርፍ ጊዜህን እንደ ስፖርት፣ የተለያዩ ጨዋታዎች፣ ፊልም መመልከት ወይም በእንተርኔት መረጃዎችን ማሰስ (browsing) ለመሳሰሉ በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ ነገሮች (hobbies) ተጠቀምበት።
(የሚያዝናኑህንና አእምሮህን የሚያድሱ ነገሮችን አድርግ።)

❤️ገንዘብ ወይም የቅንጦት ዕቃዎች እንዲያስፈራሩህ አትፍቀድ። ዛሬ ድሃ የሆነ ሰው ነገ ሀብታም ሊሆን ይችላል። ለውጥ ሁልጊዜ የሚከሰት ነገር ነው።
(የቁሳቁስ ነገር የህይወት መለኪያ አይደለም፤ የዛሬ ሁኔታ ነገ ላይቀጥል ይችላል።)

❤️ሁኔታዎች የቱንም ያህል ቢከብዱ ተስፋ አትቁረጥ። በህይወት እስካለህ ድረስ ተስፋ አለ።
(ማብራሪያ፦ እስትንፋስ እስካለ ድረስ መፍትሔና የተሻለ ቀን አለ።)

❤️አዘውትረህ ጸልይ። አብዝቶ መጸለይ መልካም ነገሮች በፍጥነት ወደ አንተ እንዲመጡ ሊያግዝ ይችላል።
(ከፈጣሪ ጋር ያለህ ግንኙነት ውስጣዊ ሰላምና በረከት ያመጣል።)

❤️ደፋር ሁንና የምትፈልገውን ነገር ተከተል። ህይወት አደጋዎችን (risks) መጋፈጥን ይጠይቃል። እድሎችን ካልሞከርክ ወይም አደጋዎችን ካልወሰድክ በእውነት የምትፈልገውን ነገር ላታገኝ ትችላለህ። ለራስህ ታማኝ ሁን። አንተ የምታደርገውን ነገር ከአንተ በተሻለ ማንም ሊያደርገው አይችልም። አንተ ግሩም ነህ! ስለዚህ ሁሌም ራስህን ሁን። መልካም ህይወት ይኑርህ!

@psychoet
25👍2
1. ሰዎች እንዴት ሊይዙህ እንደሚገባ የምታስተምራቸው አንተው ነህ።
ሰዎች የሚያደርጉት አንተ የፈቀድክላቸውን ብቻ ነው። አንድ ሰው የሚያደርግብህን ነገር ካልወደድከው፣ እስከዛሬ ምን ስትቀበል እንደነበር እራስህን መርምር።

2. "አንዳንድ ጊዜ ለችግሩ ያለህ አረዳድ ነው የበለጠ ችግር የሚሆነው።"
አብዛኛው ስቃይ የሚመጣው እየሆነ ስላለው ነገር ለራስህ ከምትነግረው ታሪክ ነው። ክስተቱ በራሱ ገለልተኛ ነው።ህመሙን የሚፈጥረው ያንተ ትርጓሜ ነው።አመለካከትህን ቀይር፣ ልምድህንም ትቀይራለህ።

3. "የተጣበቅከው ምን ማድረግ እንዳለብህ ስላላወቅክ ሳይሆን፣ ምን ማድረግ እንዳለብህ እያወቅክ ለማድረግ ፈቃደኛ ስላልሆንክ ነው።"
ይህ አረፍተ ነገር የማመካኛ ጨዋታን ያቆማል።በጥልቅ ስታስብ፣ቀጣዩን እርምጃህን ታውቀዋለህ።

4. "የሌሎች ሰዎች ስለ አንተ ያላቸው አስተያየት ያንተ ጉዳይ አይደለም።"
ስለ አንተ ያላቸው ሀሳብ የሚኖረው በነሱ አይምሮ ውስጥ ነው፤ ባንተ ውስጥ አይደለም። ልትቆጣጠራቸውም ሆነ ልትቀይራቸው አትችልም። ህይወትህን የሚቀርጸው ብቸኛው አስተያየት ያንተ የራስህ ብቻ ነው።

5. "የምትሆነው በተደጋጋሚ የምትናገረውን ሳይሆን በተደጋጋሚ የምታደርገውን ነው።"
ይህ አረፍተ ነገር በሀሳብ እና በተግባር መካከል ያለውን ክፍተት ይደፍናል።ልማዶችህ በተግባር የሚታዩ ማንነቶችህ ናቸው። ማንነትህ የሚወሰነው በግብህ ሳይሆን በየዕለት ውሳኔዎችህ ነው።

6. "ለመግባት የምትፈራው ዋሻ የምትፈልገውን ሀብት ይዟል።"
የምትፈልገው ነገር ሁሉ ያለው የምትሸሸው ነገር ማዶ ላይ ነው። ያ አስቸጋሪ ውይይት። ያ አስፈሪ እድል። ያ ምቾት የማይሰጥ እድገት። ትልቁ ስኬትህ ከትልቁ ፍርሃትህ ጀርባ ተደብቋል።

7. "ካሳመመህ አካባቢ ሆነህ ልትድን አትችልም።"
አንዳንድ ጊዜ ችግሩ ያለው አንተ ጋር አይደለም፤ ካለህበት ቦታ ሊሆን ይችላል።መርዛማ ግንኙነቶች፣ አሉታዊ አካባቢዎች እና መጥፎ ልማዶች አንተ ስለፈለግክ ብቻ አይለወጡም።አንዳንድ ጊዜ ለማደግ ቦታ መልቀቅም ጥሩ አማራጭ ይሆናል።

8. "ለመጀመሪያው ሀሳብህ ተጠያቂ አይደለህም፤ ለሁለተኛው ሀሳብህና ለመጀመሪያው ተግባርህ ግን ተጠያቂ ነህ።"
በድንገት የሚመጣው ሀሳብህ ካለፈው ልምድህ የሚመነጭ ነው። ምላሽህ ግን ከምርጫህ የሚመጣ ነው።ወደ አእምሮህ ብልጭ የሚለውን ነገር መቆጣጠር አትችልም፤ ነገር ግን በዛ ሀሳብ ምን እንደምታደርግበት መቆጣጠር ትችላለህ።

9. "የምትፈልገው ነገር ሁሉ ያለው ከጽናት ማዶ ነው።"
ተሰጥኦ አይደለም። እድል አይደለም። ትውውቅም አይደለም። ጽናት ነው። በየቀኑ የሚደጋገሙ ትናንሽ ድርጊቶች ተጠራቅመው አስደናቂ ውጤቶችን ይፈጥራሉ። አብዛኛው ሰው ከስኬቱ አፍ ላይ ሆኖ ያቆማል።

"book 🌎

#ኢትዮጵያዊነት#
@psychoet
👍147
አንዲት እናት ግመልና እና ሕፃን ልጇ ከለምለም ዛፍ ሥር ተኝተው ነበር። ከዚያም ሕፃኑ ግመል "እኛ ግመሎች ለምን ቶሎ ቶሎ ውሃ አይጠማንም?" ብሎ ጠየቃት። እናትም "እኛ የበረሃ እንስሳት ስለሆንን በጣም ትንሽ ውሃ ይዘን እንድንኖር ውሃ ለማከማቸት የተዘጋጀ የሰውነት አካል አለን" አለችው።

ሕፃኑ ግመልም ለትንሽ ጊዜ አሰበና ፣ “እሺ… እግሮቻችን ለምን ረጃጅም እና ጠንካሮች ሆኑ?" አላት፤ እናትም "በረሃ ውስጥ ለመራመድ ታስበው የተፈጠሩ ናቸው" ብላ መለሰች። ሕፃኑ ለአፍታ ቆመና አስቦ አስቦ "ለምን የዐይን ሽፋኖቻችን ረዘሙ?"
እናትም "እነዚህ ረዣዥምና ወፍራም የዓይን ሽፋኖች ንፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ዓይኖቻችንን ከበረሃው አሸዋ ይከላከላሉ"አለችው።

ሕፃኑ ግመል በጣም አሳብ ያዘውና እያሰበ በዛው ተኛ። በነገታውም እናቱ ጋር ሄዶ እንዲህ አላት፤ "በረሃ ውስጥ ብንሆን ኖሮ ውሃ ለማጠራቀም የሚረዳ አካል አለን አላት በአፉ እየጠቆመ፤ እግሮቻችን በበረሃ ውስጥ ለመራመድ ተብለው የተሰሩ ናቸው እና የዓይን ሽፋኖቻችን ከበረሃ አሸዋ ዐይኖቻችንን ይጠብቃሉ" እናት በልጇ የማስታወስ ችሎታ ተገርማ ሳታበቃ፤ ልጇ ይሄን ጠየቃት " ግን እኮ እማ፤ እኛ ያለነው እጅግ ለምለም በሆነ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ ነው!"
***
ሞራል፡
ተሰጥኦዎ ጠቃሚ የሚሆነው የተገቢው ቦታ ላይ ከሆነ ብቻ ነው። ያለዛ ለምን ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል?
***

@Psychoet
12👍1
ስለ ስራ ቦታ የሚነገሩ መራራ እውነታዎች

① አለቃህ ጓደኛህ አይደለም።
ምንም ያህል ብትቀራረቡ፣ ሁልጊዜ የሙያ ወሰንን ማስቀመጥ ልመድ።

② ግድግዳ ጆሮ አለው።
በስራ ቦታ ሚስጥርህን ለማን እንደምታወራ ተጠንቀቅ። የሚያዳምጥ ጆሮ ወሬ የሚያቀባብል አፍም ሊሆን ይችላል።

③ ቀጣሪህ ትኩረት የሚያደርገው ውጤት ላይ ነው።
ስራውን እንዴት እንደምትሰራው ያንተ ፋንታ ነው። ምንም አይነት ሰበብ ተቀባይነት የለውም።

④ በቢሮ ውስጥ ስለሚሆነው ነገር ለአለቃው ወሬ የሚያቀብል አንድ ሰው ወይም ቡድን ሁሌም አይጠፋም።
የአንዳንድ ሰራተኞች መረጃ አቀባበል ከኦፊሴላዊው ስራ ያልፋል (እንዲህ አይነት ድርጊት በግልጽ በሚከለከልበት የስራ ባህል ካልሆነ በስተቀር)። ይህንን አስተውል።

⑤ ከፕሮጀክቶች ስትገለል፣ ሌላ ሰው ስራህን እንዲለማመድ ሲመደብ፣ ወይም ያለምንም በቂ ምክንያት ከቦታህ ስትወርድ፣
ይህ ምናልባት በቅርቡ ከስራ እንደምትሰናበት የሚጠቁም ምልክት ሊሆን ይችላል።

⑥ እስከቻልክ ድረስ የግል ህይወትህን ከስራ ባልደረቦችህ አርቅ።
ምናልባትም አንተ ሳታውቀው፣ በግልህ ላስመዘገብከው ትልቅ ስኬት በምርመራ ስር ልትሆን ትችላለህ።

⑦ አንዳንድ የስራ ባልደረቦችህ ላይወዱህ ይችላሉ።
ምክንያቱ ምናልባት አቋምህ፣ አለባበስህ፣ አነጋገርህ፣ ችሎታህ፣ በስራ ላይ ያለህ ስኬት፣ ወይም ለመረዳት በሚከብዱ ሌሎች ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፤ ይህ ደግሞ ችግር የለውም። ሁሉም ሰው ሊወድህ አይችልም፤ ይህንን ተቀበል።

⑧ ከቡድን አባላትህ፣ ከባልደረቦችህ ወይም ከአለቃህ የሚንጸባረቀውን የሰውነት እንቅስቃሴ፣ የድምፅ ቃና፣ ከፍታና ፍጥነት ልብ በል።
እነዚህ በግልጽ የማይነገሩ ነገሮችን ሊጠቁሙ ይችላሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ስሜቶች፣ መውደድና አለመውደድ የሚተላለፉት 38% በድምፅ ቃና፣ 55% በሰውነት እንቅስቃሴ ሲሆን፣ በቃላት የሚተላለፈው 7% ብቻ ነው።

⑨ ሁልጊዜም ስራውን በአግባቡ የሚሰራ፣ እውቅናና ምስጋና የሚያገኝ ያ "ልዩ ባልደረባ" አይጠፋም።
ይህ የንቀት ወይም የበታችነት ስሜት እንዲሰማህ አትፍቀድ። ይልቁንስ ያ ሰው ምንን በተለየ መንገድ እንደሚሰራ ተመልከት፣ እንዴት እንደሚሰራውም አስተውልና ተማር። የተሻለ ሰው ትሆናለህ። ለመማር ክፍት ሁን።

⑩ የስራ ቦታ አዎንታዊና ጠቃሚ ግንኙነቶችን ማበረታታት ቢገባውም፣
ዋናው አላማህ ስራህን ሰርቶ ወደ ቤት መሄድ መሆኑን አትርሳ።

እወዳችኋለሁ
ምንጭ ተዋናይ
👏105👍2
ኢንቴሊጄንስ /Intelligence/
ይህ ፅንሰ ሀሳብ በብዙ ምሁራን፣ ሳይንቲስቶች፣ ፈላስፎች፣ የስነ ልቡና ሊቃውንት፣ ሌሎችም፣ ሌሎችም ለመተንተን ተሞክሯል። ፅንሰ ሀሳቡ ከእውቀት፣ ክህሎት ፣ምክንያታዊነት፣ ግንዛቤ፣ አመለካከት፣ አስተውሎት፣ ዝንባሌ፣ ራእይ፣ አተናተን፣ ችግር ፈቺነት ወዘተ ጋር የተገናኘ በመሆኑ አንዱን ስለ ፅንሰ ሀሳቡ ሲይዙ ሌላው ስለሚያመልጣቸው ሁለንተናውን የፅንሰ ሀሳብ ፍቺ ያገኘና ያስቀመጠ አልተገኘም፣ ግን በብዙ መልኩ ተሞክሯል።

የሠው ልጅ የአእምሮ ውጤት ገራሚና አለማችንን ባያሌው የለወጠ፣ ያስተካከለ፣ ያኖረ፣ ያራመደ ፣ ያስዋበ ፣ የተነተነ፣ የተረዳ፣ ያጠና፣ በእጅጉ ለሠው ልጅ ኑሮና ሕይወት ያመቻቸ ነው። የሠው ልጆች እውቀትና ክህሎት የተለያዬ ነው። አንዱ በቀላሉ የሚረዳው ለሌላው ጉም እንደመጨበጥን ያህል ይከብዳል። ለምንድነው የእውቀትና ክህሎት ወዘተ ደረጃ /level of intelligence/ እንዲህ ሊለያይ የቻለው። አጥኚዎች በተለይም የሥነ ልቡና ሊቃውንት በአእምሮው በተከማቸው ግረይ ማተር ወይም እምቅ እውቀትና ክህሎት ወዘተ ክምችት ብዛትና ማነስ ነው ብለው ያምናሉ። በአእምሮው የግረይ ማተር ማነስና መብዛት የኢንተሊጀንስ ደረጃውን ለመረዳት እንደሚያስችልም ይረዳሉ።

ይህ የሠው ልጅ አእምሮ ወለድ የሆነ እምቅ ችሎታ እንዴት ሊታወቅ ይችላል ? ከበድ ያለ ጥያቄና እምቅ ችሎታን በየዘርፉ ያነገቡ ምሁራን /intellects/ ሳያርፉ ከመረመሩት፣ ከተረዱት፣ ካጠኑት፣ ከተነተኑትና ካሳወቁት በመነሳት ልኬቱን በጥቂቱ ማለት እንችላለን።

እስካሁን ኢንተሊጄንስን ለመለካት በውስጡ የያዛቸውን ፅንሰ ሀሳቦች ያካተተ በውጭኛው /knowledge,skill, reasoning, understandig, attitude, problem solving capacity, etc/ በማካተት ሁለንተናዊ የሆነ የእውቀትና ክህሎት ወዘተ ደረጃውን ለማወቅ በመጠኑም ቢሆን የሚያስችል IQ /Intelligence quotient/ የሚለውን መለኪያ በስምምነት ተቀብለዋል።

ኢንቴሊጄንስ ኮሸንት የሁለት ብስለት ደረጃዎች ሬሺዮ ነው። አንደኛው የሠው ልጅ በአለም የኖረበት እድሜ ሲሆን /chronological age/ ሌላው የአእምሮ እምቅ ችሎታው /mental age/ ነው።
እንግዲህ የነዚህ የሁለቱን ሬሺዮ ወስደን መቶኛውን ስናሠላ ነው የልኬት ጠቋሚውን የምናገኘው፣ እንደሚከተለውም ይቀመጣል።

IQ = m/c * 100

IQ = intelligent quotient
M= Mental age
C=Chronological age ይህ የልኬቱን ጠቋሚ ይሰጠናል ማለት ነው።
የአንድን ሠው ሜንታል ኤጅ ለመረዳት አእምሮ ፈታሽ ጥያቄዎች ይዘጋጃሉ ለምሳሌ እንደ አፕቲትዩድ ቴስት ያሉ። ጥያቄዎቹ በአእምሮ ውስጥ ያለውን እምቅ ችሎታ አጉልተው የሚያሳዩን ናቸው ለምሳሌ ቃላትን፣ ፅሑፎችን፣ ትንተናዎችን፣ የመገንዘብና የመረዳት ክህሎት / verbal- linguestic/ ካርታዎችን፣ ስእሎችን፣ የተቀረፁ ቢድዮዎችን፣ አቀማመጦችን፣ ከፍታ ዝቅታዎችን በአተኩሮት የመመልከት ብቃት / visual-spatial / ስሌትንና አመክኒዮን የመገንዘብ ደረጃ /logical- mathematical/ የአካል ክፍሎቻችንን ለምሳሌ አይንና እጅን ሌሎችንም የማናበብ ክህሎት ደረጃ / bodly - kinesthetic/ የራስን የውስጥ ክህሎት የመረዳት ደረጃ /intra personal/ ከሌላው ጋር በመናበብ አብሮነትን የመንተራስና የመጠቀም ደረጃ /inter personal /
እነዚህን ሁሉ የሚያካትት ብቃት ባላቸው ምሁራን የሚዘጋጅ ነው ይህ የአእምሮ ብቃት መለኪያ። ምሁር /intelect/ የዩኒቨርሲቲን ደጃፎች ረግጦ ለብ ለብ በማድረግ ዲግሪን የጫነ ከመሠላችሁ ተሳሰታችኋል። ምሁራን እነደ ቤቶቤን የሙዚቃዊ ክህሎትን የተካኑ፣ እንደ ሼክስፕርና ሊዮ ቶሊስቶይ በቤርባል- ሊንጉስትክ ጥበብ የትለቀለቁ፣ እንደነ ሶቅራጢስ ፍልስፍናዊ ክህሎታቸውን ከሳይንሳዊ ጥበብ ጋረ ያዋሀዱ፣ እንደነ ሊዮናርዶ ተፈጥሯዊ ክህሎታቸውን በመጠቀም በስፓሻል ክነ ጥበባዊ እምቅ ችሎታቸው የትዬሌለ የደረሡ ፣ እንደነ አይሳክ ኒውተን በፈጠራ የተካኑ ናቸው ። አለም አቀፋዊ አስተሳሰባቸውም እጅጉን የላቀ እጅጉን የመጠቀ።

ኢንቴሊጀንስ ኮሸንት እንደ ቦዲ ማስ እንዴክስ በቀላሉ ልንፈትሸው የምንችለው አይደለም፣ከበድ ያለና ብዙ ውጣ ውረድን የሚጠይቅ የእውቀትና ክህሎት ወዘተ ውጤት ነው።

ፅንሰ ሀሳቡ ስፋትና ጥልቀት ስላለው እንዳላሠለቻችሁ ሌላ ግዜ ብመለስበት ይሻላል፣ የልኬት ጠቋሚዎችን ጠቁሜ ፅሑፌን ልቋጭ።
እላይ በተሠጠው የስሌት ጠቋሚ መሠረተ ሀሳብ በመመርኮዝ የጥቆማ ውጤቶቹ የሚከተሉትን ያብራራሉ፦

ከ55 አስከ 69 ጥልቅ የአእምሮ ዘገምተኛነት / mild mental disability.

ከ 70- 84 መጠነኛ የአእምሮ ዘገምተኝነት / border line mental disability/

ከ85 -114 አማካይ እውቀትና ክህሎት ደረጃ /average intelligence /

ከ 115 - 129 ከአማካይ የላቀ እውቀትና ክህሎት ደረጃ / above average or bright /

ከ 130 - 144 መለስተኛ ተሠጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / moderately gifted /

ከ 145 - 159 ከፍተኛ ተሠጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / highly gifted /

ከ 160 - 179 በጣም ከፍተኛ ተሰጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / exceptionaly gifted /

ከ 180 በላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ ተሰጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / profoundly gifted /

ገራሚ ነው፣ ሁሉንም ደረጃዎች ያነገቡ የሠው ልጆች በአለማችን ሞልተው ተርፈዋል፣ አለምን ትጉሃኑ ወደ ሞባይል ቴክኖሎጂ ሲያሻግሯት አናሳዎችም ቁልቁል እየረገጧት ነው። ተንታኞች ብዙ ብዙ ይላሉ ስለ ሠው ልጅ አእምሮ ስፋትና ጥልቀት፣ ሁሉን መዘርዘር አይቻልም፣ ከበድም ይላል፣ ለያንዳንዱ ፅንሰ ሐሳብ ትንተና ትልቅ መፅሐፍ አይበቃም። እውቀት ፣ጥበብ፣ ክህሎት ፣ መረዳት፣ መተንተን፣ መፍትሔ ማመንጨት ሁሉም ወርቃዊና ብሩኅ አእምሮ ባላቸው የሠው ቅመሞች እየተተነተኑ ነው፣ እነደነዚህ ያሉ ምሁራን በክህሎታቸው ንዋይ ሰብሳቢዎችና በቁጭታ ተቺዎች ሳይሆኑ አንቂዎች፣ መካሪዎችና አስተማሪዎች ናቸው የተግባርም ሠዎች፣ ሳይጠቀሙ ጠቃሚዎች፣ የሕይወትን ጎዳናና መንገድ ተረጂዎች፣ አጥፊዎች ሳይሆኑ አልሚዎች፣ ታካቾች ሳይሆኑ ታታሪዎች። የነርሱ መኖር አለምን ያኖራታል ፣ይጠብቃታል። በአለም የኑክለር ቃታ ለመሳብና የሠውን ልጅ ከምድር ገፅ ለማጥፋት የሚቃጡትን ሸውራራና በትምክሂት የተወጠሩትን ፖለቲከኞች ይመክራሉ፣ ያስተምራሉ ይመልሳሉ። የአንድን ድርጊት ውጤት ቀድመው ይረዳሉ በአለማችን የተከማቹትን የኑክለር አረሮችን ሠውን ለማጥፋት እንዳይጠቀሙ በማሥጠንቀቂያ ደወላቸው ያሥጠነቅቃሉ። እስካሁን ተረጋግተን እንድንኖር አብቅተውናል የወደፊቱን እግዜር ይወቀው።
በስእሉ ሦሥት የአሜሪካ ፕሬዚዴንት የነበሩትን እናያለን ክሊንተን ከሦሥቱ ከፍተኛ የሌኬት ጠቋሚ የተጎናፀፈ ሲሆን ቡሽ መጨረሻ ነው፣ ኦባማ በሁለቱ መሐከል የሚገኝ። የወቅቱ ፕሬዚዴንትም IQ ቢታወቅ መልካም ነበር፣ አለምን ለማውጣትም ሆነ ለማውረድ ሥልጣን ስላለው።
👍4
የአለማችን ነገርና ዩኒቨርስን የሚያስሰው የሠው ልጅ አእምሮ ገራሚ ናቸው። የወደፊቱ የአለም ሁኔታ በምን ይቋጭ ይሆን? መፍረስና መደፍረስ፣ ወይንስ ማደግና መሻሻል ፣ አስገኚው ይወቀው ሁለተኛውን እንዲሆን ይርዳን።

ከFB መንደር የተገኘ

www.tgoop.com/psychoet
👍61
ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች አውቅ ከሆኑ የሳይኮሎጂ መፅሀፍቶች የተወሰደ እና ከሳይኮሎጂ ባለሞያዎች/አማካሪዎች የተገኘ መረጃ!

#ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን #ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

11. የአዲስ መረጃ ቤተሰቦች፣ ሼር ማድረግ ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኝ ስለሚያውቁ ቀናቸውን የሚጀምሩት የኛን መረጃ ሼር በማድረግ ነው፡፡

ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!

----------------------

ምንጭ - (ቶማስ እንደፃፈዉ፣ ፅሁፉ ከዶክተር አለ የተወሰደ)

🎡@🎡መልካም ቀን
    #Join   #Join     #Join
      🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
             🚗 www.tgoop.com/Psychoet👍
12👍4
የስብዕና መዛባት (Personality Disorders)


በዓለም ላይ ከሚኖሩ አጠቃላይ ህዝቦች ውስጥ ከ 1-20% የሚያህሉት ለተለያዩ ዓይነት የስብዕና መዛባት ችግሮች ተጋላጭ ናቸው፡፡ የስብዕና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስንል ወደ አእምሯችን የሚመጣው መንገድ ላይ ጨርቁን ጥሎ የሚሄደው፤ አማኑኤል ሆስፒታል የተኛችው ፤ ወይም ደግሞ ሰውን በአረመኔያዊ ሁኔታ ገድሎ እስርቤት ውስጥ በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቀው ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን  በዓለም ላይ በጣም በጥቂቱ ከ 25 ሰው አንዱ  ለተለያየ ዓይነት የስብዕና መዛባት ተጋላጭ ሲሆን፤ እነዚህ ሰዎች የቤተሰባችን አካል፤ ጎረቤት፤ ወይም ደግሞ የስራ ባልደረቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ለስብዕና መዛባት ዋና መንስኤዎች የትወልድ ሃረግ (Genettics)፤ በልጅነት ዕድሜ የሚደርስ አካላዊ፤ ወሲባዊና ስነልቦናዊ ጥቃት፤ እንዲሁም ያደግንበት ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው፡፡ የስብዕና መዛባት ያለባቸው ሰዎች በአጠቃላይ በሶስት ቡድን (Clusters) ይከፈላሉ፡፡

ቡድን ሀ የስብዕና መዛባቶች (Cluster A Personality Disorders)

1. በምክንያት ያልተደገፈ ጥርጥር እና ከመጠን ያለፈ ሰዎችን ያለማመን ችግር (Paranoid Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ የትዳር ጓደኛቸው ከሌላ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው ብለው ሊያምኑ ይችላሉ፡ ከአስር አመት በፊት ወልደው ያሳደጉትን ልጅ የእኔ አይደለም ብለው ሊክዱ ይችላሉ፤ ዙሪያ ገባውን ሁሉ በጥርጣሬ የሚመለከቱ እና ሰዎቸ በመሰረቱ አደገኞች ናቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው፤ ለእነዚህ ሰዎች በቅንነት የወረወራችሁት ሃሳብ እንደ ጥቃት ሊቆጠር ይችላል

2. ከውጪዉ ዓለም ወይም ከእውነታው ሸሽተው  በራሳቸው አለም (ሃሳብ) የሚኖሩ (Schizoid Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ዓለም አብዝተው የሚመሰጡ፤ በእውኑ ዓለም ተጨባጭ ያልሆኑ ሃሳቦችን የሚያልሙ ሲሆን ለማኅበራዊ ደንቦች ግድ የሌላቸውና ከሰዎች ጋር ስሜታዊ ትስስር ለመፍጠር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው

3. በአነጋጋራቸው፤ በባህሪያቸው፤ በአስተሳሰባቸው ላይ መዛባት ያለባቸው ሰዎች (Schizotypal Disorder):- 
እነዚህ ሰዎች ከሌሎቹ የስብዕና መዛባት ዓይነቶች በተለየ መልኩ በቀላሉ ችግር ውስጥ እንደሆኑ በአነጋገራቸው፤ ከተለመደው ወጣ ባለው ባህሪያቸው እንለያቸዋለን፡፡ ምንአልባትም በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ እንደ “እብድ” የምንቆጥራቸው አብዛኞቹ የእዚህ ስብዕና መዛባት ተጋላጮች ናቸው

ቡድን ለ የስብዕና መዛባቶች (Cluster B Personality Disorders)

1. ለማኅበረሰብ ህግና ደንቦች ግድ የሌላቸው (Antisocial Personality Dsiroder)፡-
ሌሎች ሰዎች ላይ ሆን ብለው አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት የሚያደርሱ፤ ርህራሄ የሌላቸው እና የሰዎችን ስሜት የማይረዱ፤ ባጠፉት ጥፋት መጸጸት የማይሰማቸው እና ከህይወት ተሞክሮ ትምህርት ወስደው ራሳቸውን ለማሻሻል የማይሞክሩ ናቸው:: ብዙ ጊዜ ጥቃት አድርሰው፤ወንጀል ፈጽመው ወደ ህግ ሲቀርቡ ብናያቸውም አብዛኞቹ ግን በረቀቀ መንገድ የሚንቀሳቀሱ፤ ከህግ ከለላ በቀላሉ የሚያመልጡና በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ሰዎች ናቸው

2. ስለራሳቸው ማንነት ማወቅ የተቸገሩ (Boarderline Personality Disorder):-
እነዚህ ሰዎች  አበዝተው ባዶነት፤ የስሜት አለመረጋጋትና ፍርሃት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ቁጡዎች፤ ራሳቸውን ለመጉዳትና ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የስብዕና መዛባት በልጅነታቸው የጾታ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ላይ የተለመደ ነው፡፡

3. በሰውነታቸው ያላቸውን መልካም ዋጋ የማይረዱ (Histrionic Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች የሌሎችን ትኩረት አብዝተው የሚሹ እና በዕቅዳቸው ሁሉ የሌሎችን አበረታችነት የሚጠብቁ ናቸው:: ሌላ ሰው ቀጥሉ ካላላቸው ምንም ዓይነት ውሳኔ ለመወሰን ይቸገራሉ፡፡ከመጠን በላይ ለውበታቸውና ለአለባበሳቸውም የሚጨነቁም ናቸው

4. ክፉ ሰዎች (Narcissistic Personality Disorder)፡-
ሲበዛ ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች፤ በነገሮች ሁሉ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሰሉና በጣም ተቆጣጣሪዎች ናቸው፡፡ የዚህ ስብዕና መዛባት ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሌሎችን የሚቀርቡት በሆነ መንገድ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ሲያስቡ ብቻ ነው፡፡ እነሱ የፈለጉት ነገር ካለሆነ ለበቀል የሚጋበዙ ፤ዓለም በእነሱ ዛቢያ ብቻ የምትሽከረከር የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

ቡድን ሐ የስብዕና መዛባቶች (Cluster C Personality Disorders)

1. ከማኅበራዊ ህይወት ራሳቸውን የሚያገሉ (Avoidant Personality Disorder)፡-
ሲበዛ የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው በዚህም ምክንያት ሰዎች ስለነሱ መጥፎውን እንደሚያወሩ የሚያስቡ፤ ሰዎች የወቀሷቸውና ያገለሏቸው የሚመስላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ራሳቸውን ከማኅበራዊ ህይወት ያገላሉ፡፡ ሰርግ እና ሃዘን ቤት መሄድ፤ ከጓደኞች ጋር ሻይ ቡና ማለት ያስጨንቃቸዋል፡፡

2. በሌሎች ሰዎች ላይ ሲበዛ ጥገኛ የሆኑ ሰዎች (Dependent personality Disorder)፡- በራሳቸው መተማመን የሌላቸው፤ በዕለት ተዕለት ኑሯቸው ውስጥ የሌሎችን ውሳኔ የሚጠብቁ፡ ሲበዛ ሽቁጥቁጥና ለሰው አጎብዳጅ የሆኑ ሰዎች ናቸው

3. ስህተት አልባ ህይወት ፈላጊዎች (Anankastic Personality Disorder)፡- ለህጎች ፤ ስርአቶች ፤ ዕቅዶች ሲበዛ አብዝተው የሚጨነቁ፡፡ ያቀዱት ጉዳይ ካልተፈጸመ ዕረፍት የሚነሳቸው፤የሚለብሱት ልብስ መዛነፍ ወይም አለመተኮስ ቀኑን ሙሉ የሚረብሻቸው ሰዎች ናቸው፡፡

(በሰብለወንጌል አይናለም)
@Zepsychologist


ከእነዚ በአንዱ አልያም የተለየ የአዕምሮ ሕመም አለብኝ ብለው ካሰቡ ( በዚህ የሚጠቃ የቅርብ ሰው ካለ) የስነልቡና አማካሪዎች ጋር እንዲሄዱ እመክራለሁ ፡፡ የስነልቦና ስልጠናም መውሰድ ከፈለጋችሁ 0912664084 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል ፡፡
13👍2
መልካም ዜና!

14ኛ ዙር የስብዕና ግንባታና የሳይኮሎጂ ስልጠና (Life Improvment Training)  ሀምሌ 8 ሊጀምር ነው።

ስልጠናው ላለፉት 6 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ተግባራዊ ስልጠና ነው።


🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ፈልጎ ማግኘት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን
🔖ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀት ማሸነፍና፣ ድብርትንና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ስራ ፈጠራና የገንዘብ አስተዳደር
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦናን መረዳት
📖የሥነልቡና ቀውስና መፍትሄዎች መረዳት


ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በስራ ቀናት (ከሰኞ - አርብ) በጠዋት በከሰአትና በማታ እንዲሁም ቅዳሜና እሑድ ይኖረናል።

በአንድ ፈረቃ ጥቂት ብቻ ቦታ ስለሆነ ያለን ቀድመው ይመዝገቡ።
ለመመዝገብ / መረጃ ለማግኘት 0960865151 ወይንም 0912664084 ይደውሉ።

🏠 አድራሻ :- ቦሌ ብራስ፣ መገናኛ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ዛሙ ፈርኒቸር ህንፃ ቁጥር 206


🖼🎁ለመለወጥ መወሰን እንጂ ሰበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!! ሕይወትዎን ለመቀየር አሁኑኑ ይወስኑ!
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

@psychoet
6
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
#ይሉኝታ
እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ

#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡

#የይሉኝታ_መንስኤዎች
✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት

✿በራስ መተማመን ማነስ

✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ

✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን

✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ

✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

#ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች

✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት

✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?

✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ

✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ

✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ

✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር

✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር

✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል

©zepsychology

ይሉኝታን ለማስወገድ ስልጠናዎቻችንን ለመውሰድ 0912664084 ይደውሉ
2
2025/07/08 15:39:57
Back to Top
HTML Embed Code: