ጥቋቁር ገፆች
(ከገሃዱ አለም ታሪክ-ለትውስታ)
.
"ህይወት ትውስታ ናት፤
ከተረሳህ ትሞታለህ"
.
.
<< <ብዙ ቀን ተማሪዎቼን በደንብ ያላስተማርኳቸው ሲመስለኝ ህሊናዬ አያርፍም እንደምልሽ አስታወስሽ?.... በዛ ሁሉ ጨለማ ህይወትና አሁን የምኖረው ህይወት መሃል ያለው ብቸኛ ልዩነት.... ብቸኛ የደስታ ጭማሪ ህሊናዬ ማረፉ ስለሆነ ነው። እነሱ የሆነ ነገር ሲማሩ.... እንኳንም ያንን ሁሉ አለፍኩት፤ እንኳንም እዚ ጋር ለመቆም ታገልኩ እላለሁ። የመጀመሪያ ብዙ የምለውን ገንዘብ መቀበል የጀመርኩት እዚ ጊቢ ስገባ ነው.... ግን ከህሊናዬ ሰላም ውጪ የትኛውም ገንዘብ በየቀኑ ለማወጣው ጥረት የሚመጥን ሆኖ አይደለም የምቀጥለው። መምህር መሆን ቀላል አይደለም.... በየምሽቱ ለቀጣዩ ቀን መዘጋጀት ይጠይቃል። እኔን ስትሆኚ ደግሞ.... በየምሽቱ እንዴት ሰው ፊት እንደምትስቂ፣ እንዴት የራስሽን ችግር ለራስሽ ደብቀሽ ደስተኛና ባለ ተስፋ እንደምትመስዪ ማስመሰልንም ጭምር መለማመድ ይጠይቃል ምክኒያቱም ወትሮውን ደስተኛና ተግባቢ መሆን ቀርቶ የመኖር ተስፋ ያለው ሰው አይደለሁም።
.... የአእምሮ እጢ በሽተኛ ነኝ። አልጠበቅሽም አይደል? አንዳንዴ ክፉኛ ይነስረኛል.... ሀኪሞች በተኛህበት ደም አፍኖህ ልትሞት ትችላለህ እሰኪሉኝ ድረስ አደገኛ እጢ አለብኝ። ይድናል ወይ? አይድንም። እጢ እንዳለብኝ ያወኩት በ 14 አመቴ ነበር.... እሱም ነስር ሲበዛብኝ ሀኪም ቤት ራሴ ሄጄ በተመረመርኩ ጊዜ። የ 14 አመት ልጅ፣ መድሃኒት እንዴት እንደምገዛ.... ቀጠሮ እንዴት እንደምይዝ ምናምን ገና በወጉ ሳላውቀው ከፊቴ የተቀመጠው ዶክተር "ልትሞት ነው" ይለኛል። ለዚህኛው ግድ የለሽነታቸው ወላጆቼን መቼም ይቅር አልላቸውም። ተገደው ሊሆን ይችላል ለኔ ግድ ያልነበራቸው ግን.... እኔንጃ፤ ከዚ በኋላ ይቅር የሚል ልብ የለኝም። ዶክተሮች.... ወይ ደስተኛ በመሆን እድሜህን ታራዝማለህ፣ ወይ ራስህን በማስጨነቅና በመጠበብ ሞትህን ታፋጥናለህ ብለውኛል... ተፈልጎ የሚታዘን ይመስል። ብቸኛ ደስተኛ ቦታዬ ግን ይሄ ነው። በህይወቴ የፈለኩት አንድ ነገር.... "ጎበዝ!" መባል ነበር፤ ከወላጆቼ ለሰራሁት አንድ ነገር እንኳን ማበረታቻ ማየት.... ግን አልሆነም። እስካሁንም ካለኝ ነገር ላይ መስዋትነት በመክፈል ላይ ብቻ ነኝ። ግን እዚ መጥቼ ተማሪዎቼ "እንወድሃለን.... ገብቶናል" ሲሉኝ ለኔ ከዚ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ የቤተሰብነት ስሜት ይሰማኛል። ሁሌ "ደስተኛ ናቹ? ወዳቹኛል? ትንሽ ነገርም ቢሆን ገብቷቿል?" እያልኩ ማጨናንቃቸው ለዚ ነው። ተጨማሪ አንድ ቀን ለመኖር። ከንግዲህ ልሄድ ነው... ከ 1 ወር በኋላ.... ይሄን ሁሉ የማስረዳሽም ስለምሄድ ለውጥ አያመጣም በሚል ከጠቀመሽ ነው> >>
የንግግራችን ማብቂያ ባይሆንም ጭብጡ ነበር። ከዚ በኋላ እንደማልረሳውና.... ለራሱ ባይሆንም ለሌሎች ከተሞክሮው ትምህርት እንዲሆን መኖር እንዲቀጥል መነጋገራችንን አስታውሳለሁ-ከአመት በፊት። ከ800 በላይ መፅሀፎች አሉት.... "ረሀቤን ለማስታገስ ስል መፅሃፎቼን ሽጫለሁ" ሲል ከቀመሳቸው ክፉ ቀናቶች ሁሉ ይሄኛው እንደመረረው ፊቱ ላይ ይንፀባረቅ ነበር። ለዛም መሰለኝ ለኔ ለማስታወሻነት መፅሀፍ መስጠቱን የመረጠው። ውስጡ የተፃፈበት ትንሽ ማስታወሻ "በዚች ምድር ላይ ማንኛውም ጥቁረት፤ ነጩ ልብሽን እንዳያቆሽሸው ከመመኘት ጋር"... ከሚል ፅሁፍ ስር "ህይወት ትውስታ ናት፤ ከተረሳህ ትሞታለህ" የሚል ጥቅስ የታከለበት ነበር። የሚሞተው በእጢ የተመረዘ አካል ሲቀበር ሳይሆን ከትውስታ የተፋቀ ትዝታ ሲደመሰስ ነው ማለቱ ነው። እኔም ሁሌም በህይወት ይኖር ዘንድ ያካፈለኝን ቁምነገሮች ከወረቀት አሰፈርኩ...
.
.
ተፈፀመ
@Re_Ya_Zan

.....እነዛ.... በጉጉት ተጠባብቀን ያየናቸውን ፊልሞች እኮ አፈላልጌ ደግሜ አየኋቸው። አህህህህ..... ልጅነታችንን ይሸታሉ! ደብዝዘዋል ብቻ ብልህ እንዳታምነኝ.... አለም ከጥቁርና ነጭ ቀረፃ በተላቀቀ ማግስት ነበር እንዴ የታደምናቸው አስባሉኝ እንጂ። ደግሞ እንዳዲስ ምን ቢገርመኝ ጥሩ ነው?..... ለካ በዘመናችን ወጣት ጎረምሳና ኮረዳ ቆመው መሳሳቃቸው ያስቆጣ ነበር.... የወደደ ፍቅሩን ለመግለፅ ለቀናናናት ይጨነቅ ነበር.... ለካ ቀሚስ ከጉልበት በማለፉ ጭኖች እስኪቀሉ ተገርፈዋል.... በመፅሃፍ ገፆች መሃል የተረሳ አእላፍ ፅጌሬዳም ከትዝታው ጋር እንዳበበ ኖሯል....
.
.
.....ለካ.....ለካ ደግሞ እድሜ ታስሮ አይቀመጥ ነገር ያፈተልካል.... ዘመንም እንደ ሰው ስጋ ለብሶ ይናፈቃል.... በትናንት ውስጥ ወዳለች አንድ እውነተኛ ቀን መመለሻው እንዴት ይሆን ውዴ?... እንጃ.... ብቻ.... ከነ ሙሉ ክፉ ደጉ ያ የኖርንበት ደብዛዛ ጊዜ ቀና ነበር።

እለተ ጁምዓ
አዲሱ ጀምበር፣ ህይወታችንን ያስጀመርንበት ነብዩሏህ አደም ነፍሳቸው ህይወት የተዘራበት የኛ የሰው ልጆች ታሪክ አንድ ብሎ የጀመረበት አዲስ ምዕራፍ ሆነ። ይህ ሁሉ ለመከሰት ግን አንድ ጀምበር በቂው ነበር። ለረጅም ጊዜ ወደ ተግባር ለማምጣት በማሰብም ሆነ ባለማሰብ ሲጠነሰስ የኖረ ነገርን ወደ ክስተት ለመለወጥ እንደ ሂደቱ አዳጋች አይደለም። እንዲሆን ከተወሰነ ቡሃላ ሁኖ ለማየት ምናልባት ሰከንዶች በቂ ይሆናሉ። የህይወት ዙረትም ልክ እለተ ጁምዓ ከብዙ ሂደት ቡሃላ ብዙ ክስተቶችን እንዳስተናገደች ሁሉ፣ ህይወታችንም በአንድ ጀምበር ብዙ ክስተትን ያስተናግል። ይከሰት ይሆን ብለን የሰጋነው፣ አይከሰትም ብለን በጭፍን ያመንነው ሁሉ ወደሆነ ምስቅልቅል ይለወጣል። አንዳንዴ ሁሉም አዲስ ጀምበር የሚናፈቅ አይሆንም። ትናንት እንዳይከሰት ስንፈራው የነበረው በስጋት ቀጠናችን ውስጥ ሲመላለስ የኖረውን ሀሳብ ዛሬ እውን ሆኖ እንደ ተለምዷዊ የአኗኗር ዘይቢያችን እየኖርነው ይሆናል። እዚህ አዲስ ጀምበር ላይ አንድ ቀን ስንቆም ከክስተቱ አስደንጋጭነት በላይ የሚከብደው ጭንቅላታችን ሲሰራ የኖረው እንዳይከሰት በመፍራትና በመጠንቀቅ እንጂ ቢከሰት ምን ማድረግ እንዳለበት በመስራት ላይ አለመሆኑ ነው። ያኔ መላ ቢስ ሁነን እንቀራለን። አዲስ ምዕራፍን ከህይወት ገፅ ላይ ከፍቶ የሚፅፉበትን ነገር አለማወቅ እጅግ በጣም ፈታኝ ክስተት ነው። ነገሩን ይበልጥ የሚያከብደው ደግሞ የሚፃፈውን ካለማወቅ በላይ ገፁን ለመሙላት ዝግጁ የሆኑ ችግሮች መብዛታቸው ነው። የሚናፈቅ ጀምበር እንዳለ ሁሉ የሚያስፈራና የሚጨንቅ ጀምበር በየህይወታችን ውስጥ እየተፈራረቀ ይገኛል። ህይወት የሁለቱ ጀምበር ጥምረት ነውና።
@Re_Ya_zan

....እስኪ ደግሞ... ደግመን ከተቀማመጥን አይቀር ስለዛ የጌታህ ተዐምር እናውራ.... ስለዛ ስሜት ነው የማወራው..... "ሰው" ከመባላችን ውጪ ምናችንም ከማይገናኝ ሌላ ፍጡር ጋር ለብቻችን ለመኖር ድፍረት ስለሚሰጠን ስለዛ የብቸኝነት ስሜት..... ከተወለድን ጀምሮ ጥበቃን፣ ደስታን፣ ምክርን... ለመኖር አስፈላጊ ያልነውን ሁሉ ሲሰጠን ከኖረው አካል (ቤተሰብ) ጨክኖ የመውጣትን ድፍረት ስለሚሰጠን ስለዛ የጉድለት ስሜት.... በእውነቱም የራህማኑ አፈጣጠር ድንቅ ነው።
.....ማለት.... እሷኮ እንዴት እንደምታስደስታት ቀርቶ እንዴት መልስ ልትሰጣት እንደሚገባ ያልደረስክበት ውስብስብ ፍጥረት ናት። አንዳንዴ ስሜት የሌለህ ሁሉ ይመስላታል.... እንዴት እንደምታሳያትም ግራ ይገባሃል.... እሷ የተሰጣትን ያህል የቃላት ግርታ እንዳልገራልህ ታውቀዋለህ... ታውቀዋለችም እኮ.... ሆኖም አልተረዳኸኝም በሚል ታኮርፋለች። ነገሮችን በማይገባህ መልኩ ታወሳስባቸዋለች.... እስኪ አሁን ዛሬ ከአንደበትህ የወጣው "አንቺን ደስ እንዳለሽ" ሚኒሊክ ልጅ እያሉ ከሞተው የአክስቷ ባል ውሻ ጋር ምን አገናኘው?.... እምባዋ ቅርብ ነው.... ድንዳኔ በሞላው አለምህ ውስጥ ትንሽዬ ብርጭቆ ናት.... እንዴትም ብታነሳው በጠነከሩ ጡንቻዎችህ እንዳይሰበር ትሰጋለህ። ውስጧ የሰፈሩ ልዩ የፈጣሪዋ ኒዕማዎች አንተ ጋር የሉም.... ያማታል.... ያነጫንጫታል.... ልታጠጋጋው የምትሞክረው የትኛውም አይነት ህመም እያስረዳችህ ካለችው ህመም ጋር አይገጥምም.... ትጨነቃለህ። ስስ ናት.... ግን ደግሞ አንዳንዴ ልታስበው ከምትችለው በላይ የህመም መቋቋም አቅሟ ያስደንቅሃል... ሰው እንዴት ዘይትና እሳትን ይደፍራል?... ትንሽ ከመሆኗም ጋር አለቃ ናት... በጉልበቷ ሳይሆን በማሳዘኗ የፈለገችውን ስታስደርግህ ራስህን ታገኘዋለህ። አንዳንዴ አፍቃሪ ናት.... ሲላት ደግሞ የምታሳያት ፍቅር ሁሉ የሚያንገሸግሻት ራስወዳድ። "የሷን ስሜትና ንግግሮች ከመፍታት ለወፍ ማትስ ማስጠናት ይቀላል" ታስብልሃለች። ሳትወስዳት በፊት ይሄን ሁሉ ታውቅም ነበር...... ግን ታስፈልገኛለች ብለህ ያባትህን ቤት ትተህ ለሷ ጎጆ ለመቀለስ ስትወስን.... እዛ ጋር ይሄን ያዘናጋህ የጌታህ አንድ ተዐምር ነበር።
.....እስኪ አስቢው.... እሱኮ ምንም ነገር ብታስረጂው አንቺ በፈለግሽው መጠን የማይረዳሽ የሆነ አራት ማእዘን ኸልቅ እኮ ነው። ሰው እንዴት ዳቦ ግዛ ሲሉት ዳቦ ብቻ ገዝቶ ይመጣል?.... እንዴት ያ የተለመደው አቀማመጥሽ ሲቀየር እንደከፋሽ፣ የሆነ ትኩረት፣ የሆነ ፍቅር እንዳስፈለገሽ ወዲያው አይገባውም?.... ለአንድ ሰአት ተኩል አንዲትን ኳስ ሲያሳድድ ያልደከመው.... ለግማሽ ሰዐት የምታስረጂውን ትኩረት ሰጥቶ ማዳመጥ እዳ ይሆንበታል። ያንቺ አርቆ አሳቢነትና ፈትፍቶ ማስረዳት ለሱ ጭቅጭቅ ነው። አንዳንዴ.... ትንሽ ነገር ያስደስተዋል። የሆነ... ባለ በሌለ አቅምሽ ከቀያየርሽውን የሳሎን ቅርፅ ይልቅ ሩዋንዳ ውስጥ ያለ፣ ማንም ግድ የማይሰጠው ፖሊሲ መቀየር አጀንዳ ሆኖ ያስቦርቀዋል። አንዳንዴ ደግሞ ከሱፍራ ሙሉ ምግብ የአንዱ ጨው ማነስ ያስደነፋዋል። ለሱ ህይወት ጥቁርና ነጭ ቀላል ናት.... የምለብሰው የለኝም ስትዪው አደምና ሃዋ ዱንያ ላይ ሳይገናኙ በፊት የገዛልሽን ቀሚስ ይጠራል። ሳይነግርሽ ለሱ አሁንም ቆንጆ እና የሚወድሽ እንደሆንሽ እንድትረጂው ይጠብቃል.... ትናንት ነግሮሽ፣ ጠዋት ቢደግመው... ሲመሽ ቢሰልሰው ያልቅበታል እንዴ?... "በቃ ያን በሚያክል የጡንቻ ስብስብ ውስጥ ሁለት የአእምሮ ሴል ነው ያለው ማለት ነው?" ያስብልሻል። ሳትሄጂ በፊት ታውቂም ነበር...ግን ያስፈልገኛል ብለሽ ከናትሽ ቤት ወተሽ ወደጎጆው ልትከትሚ ስትወስኚ.... እዛ ጋር ይሄን ያዘናጋሽ የጌታሽ አንድ ተዐምር ነበር።
وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًۭا لِّتَسْكُنُوٓا۟ إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةًۭ وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَءَايَٰتٍۢ لِّقَوْمٍۢ يَتَفَكَّرُونَ
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡
(30 : 21)
....ጀባሩ ታላላቅ ተዐምራቶቹን ከጠቀሰበት ቅደም ተከተል መሃል ከራሳችን ለራሳችን ጥንዶች የተፈጠሩን መሆኑን ስለመጥቀሱ ነው የማወራው። በእርግጥም የሱ ተዐምር ሆኖ ጎዶሎነት፣ መሞላላት የሚያስፈልገን መሆናችንን የሚያስገነዝበን ያ ስሜት ባይኖር ይሄን ውሳኔ ባልደፈርን ነበር። ችግሩ ይሄ አደፋፍሮ ያስገባን ስሜት በተሟጠጠ ጊዜ፤ ራህማኑ እንዳዘዘን አንዳችን የአንዳችን ሰኪና መሆናችን በቀረ ጊዜ፤ ፍቅር እና እዝነት ሚዛናቸውን ጠብቀው መተካካት ባቆሙ ጊዜ.... ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው ሁሉም በአንዴ እንዳዲስ ዱብዳ ይሆናል። ለያዥ ለመካሪ አስቸግረን የገባንበትን ትዳር ወር ተስተካክሎ ሳያልፍ ካልወጣሁ ብሎ መጋደሉ ከመብዛቱ ጋር... እስኪ መነሻችንን አንዴ ደግመን እንፈትሸው። በእውነት ጠቃሚ ኡማ የሚያፈራ ትዳር የመመስረት ትክክለኛ ወንድነት ላይ ደርሰህና ተዘጋጅተህ፤ ወይስ ትዳር ሲባል ያቺ ተቃራኒ ፍጡር እስከዛሬ ጠብቃ ያቆየችው አካል የግልህ ሊሆን እንደሆነ በማሰብ ለሚከንፈው ሃሳብህ በመሸነፍ የወሰድከው እብደት ነበር?.... ብልሃትሽን፣ ትእግስትሽን፣ ውበትሽን አላህ ለወደደው ቤት ተጠቅመሽ የሞቀ የኢማን አለም ልትፈጥሪ ዝግጁ ሆነሽ፤ ወይስ እስከዛሬ ከመነካት ቀርቶ ከመታየት በተጠበቅሽው ልክ ከፍጥረትሽ ተቃራኒ የሆኑ ጠንካራ ክንዶች መሃል ለመታቀፍ የምትፍጨረጨረው ልብሽ አሳስታሽ?.... ከምን አንፃር ዝግጁነት እንደሚለካ ለመጪው የቤት ስራ ይሁነንና... ብቻ ራሳችንን አለም በፈሰሰበት የትዳር ቦይ ተከትለን ተንቧቡተን በሌላኛው ጎን የፍቺ ውድቀታቸው ላይ ሲፈሱ የምንከተል ሆነን እንዳናገኘው ሰከን እንበል። ወላሁል ሙስተዐን።

....ለማስታወስ ያህል...
.
.
....መስታወትሽ ዋሽቶሻል፣ አስቀያሚ አይደለሽም። ገና የሚስማማሽን የመዋብ ምርጫሽን በመፈለግ ላይ ብቻ ነሽ። መስታወትሽ ዋሽቶሻል፣ የአለም ቆንጆ አይደለሽም። አይተሽ ካልጠገብሽው መልክሽ በላይ የተዋበን ሌላ የፈጣሪሽን ስራ ስላልደረስሽበት ብቻ ነው።
.
....አልችልም አትበይ.... ከማብሰሉም፣ ከጥልፉም፣ ከማንበቡም፣ ከፅዳቱም የማትታማዋን አንቺን እስክታገኛት አትቦዝኚ። ሁሉንም እችላለሁ አትበይ.... ጌታሽ የሚያስከብርሽን አሳውቆ ፈጥሮሻልና ያለ ቦታሽ ተፎካክረሽ አላዋቂ አትሰኚ።
.
....አላረጀሽም.... ነገሽ የማያስችልሽን አእላፍ ሸክም ዛሬ አንፏቀሽው እደሪ። ገና ልጅ አይደለሽም.... ከሚፈስ የእድሜ ጅረት ጋር ትናንቴን ካልደገምኩ በሚል ስትታገይ ራስሽን አታድክሚ።
.
....ውበትሽን መሃከለኛነት ላይ ፈልጊው። በመወደድና ባለመወደድ መሃል የሰላም ጎጆ ይኑርሽ። በመሄድና በመቅረት መሃል ልብሽ ሚዛን ይርገጥ። በዝምታና በጨዋታ መሃል አስታራቂ ዳኛ ሁኚ። አንገት ለማቅናትና ለመድፋትም ተራ ስጪ። እህቴ ሆይ.... አለም ለአስተዋይ ሴት ልዩ ዙፋን አላት።

ነገሮችን ያለ ቦታቸው ፈልገህ ታውቃለህ?.... እኔ አውቃለሁ። አባቴን ብዙ ጊዜ ልጅ እያለን አንጠልጥሏቸው በሚገባቸው ፌስታሎች ውስጥ ፈልጌ አጥቼዋለሁ። አባትነት እንደዛ አይነት ነገር ነው.... ሁሉም የዩሱፉ ያዕቁብ አይሆንም፤ ስስቱን ቶሎ አታውቅበትም። አልያም ደግሞ... ፊቱን ያን ያህል የምትመረምርበት ጊዜም አይኖርህም... ምክኒያቱም ብዙ ራቶችህ ላይ ሳትተኛ ባለመድረሱ አትተዋወቁም። ወሳኝ ቀኖችህ ላይ እንኳን በታዳሚያን መሃል ፈልገህ አታገኘውም። ግን ልክ.... የህይወት ናዳ ላይህ ላይ ሊከመር ሲሞክር የሆነ የሚጠብቅህ ዳመና ነገር እንዳለ ልብ ብለህ ቀና ያልክ ቀን... ያኔ የተሳሳተ ቦታ ላይ ስትፈልግ እንደኖርክ ይገባሃል። ሆኖም ማስተዋል እስኪመጣ አንተም ሳታውቀው ሌላ ጎጆ ውስጥ ሌላ ተፈላጊ ሆነሃልና አሁንም የጋራ ጊዜ ማሳለፍ ቀጠሮ ላይ ይቀራል። ግን ተራ ተቀያይራቹ.... ከሱ ይልቅ ባንተ ጊዜ ማጣት መገናኘታቹ ሲቀንስ፣ ደግህን ሲያዩ በኩራት ትከሻህን የደገፉ እኚያ ክንዶች እገዛህን መሻት ሲጀምሩ፣ ጉዳትህን ሲያዩ የሚከስሉ እኚያ ቆዳዎች ከተሸበሸቡ መሰንበታቸውን ስታስተውል... ያኔ ነገሮች ወደ ማረፋፈዱ ከዞሩ ቆይተዋል።
.....እኔን ከጠየቅከኝ.... አባትህን በፍቅር ቃላት ጎርፍ መሃል አቅፎ የሚያባብል ክንድ የመጠበቅ አይነት እየፈለግከው ከሆነ ብዙ ትጠብቃለህ። አባትነት ዱዳ ነው... ቋንቋውን እንድታውቅለት ይፈልጋል። ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ እውር ነው... እናትነትን በመረዳትህ ብቻ ይረካል። አባትነት... ስለመከበሩ ነው፣ በዙሪያህ ያሉት እንዲያከብሩት ባደረግከው ልክ ያስከብርሃል። እንዲፈሩት ባደረግከው ልክ ያስጠብቅሃል። ብስጩነቱ መብዛቱን አትቁጠርበት እልሃለው.... ከጎንህ አለመገኘቱን አትይበት። ፍላጎቶቹን በድርቅናህ አትፎካከርበት። በእጁ ላይ ከምንም የማትቆጠር ደካማ ነገር ቢያመጣም ውደድለት። የከለለህ ዳመና በህይወትህ ሙሉ ሊከተልህ የታደለ ዘላቂ እንዳልሆነ ስትረዳ.... ያኔ እስከዛሬ ከምንም የቆጠርከው ትንሹም ትልቁም የሚናፈቅ የፍለጋህ መልስ እንደነበር ይገለፅልሃል። መልካም እድል።

በዘመናችን ግራ ከገባቸው አረዳዶች መሃል የሶሻል ሚድያ "የግል" ትርጉም ይመስለኛል። እንደ አንድ ሙስሊም በጥሩ ማዘዝና ከክፉ መከልከል (ስርዓቱን ከጠበቀ አገላለፅ ጋር) ግዴታችን መሆኑ እንዳለ ሆኖ፣ አንዳንዴ የተቀባዩ አካል ገርበብ ያለ ወላዋይ አቀባበል ያስደነግጣል። ለምሳሌ፤ ሱና እየሆነ ከመጣው ለሰርግ ብቻ ሂጃብ ማውለቅ ባህላችን ጋር.... ከሂጃቡ አለመለበስ፣ ሙሉ ሰርጉ ተቀርፆ ሚድያ ላይ ሲቸበቸብ መታየቱ አስደንጋጭ ሆኖ ሳለ... የሙስሊም ወንድም/እህትነት ምክራቹን ስትለግሱ የሙሽሮች "በግል ህይወታችን አይመለከታቹም" ይበልጥ ጥያቄ ይፈጥራል። ትንሽ የተዘነጋው ነገር... ገመናህን አንዴ ሚድያ ላይ እንዲወጣ በር ከከፈትክ በኋላ "የግል ህይወት" የሚባል ነገር የለም አኺ.... ከጅምሩም ገመናዬ ገመናቹ፣ ሚስቴ ሚስታችሁ ብለህ ስትጋብዘን እንደሚመለከተን አምነህበት አይደል? ባይሆንማ ትናንት ማታ የተገባበዛቹት ራት፣ ሰርፕራይዝ መደራረጋቹ፣ ከእንቅልፋቹ እንዴት እንደተነሳቹ ከኛ ህይወት ጋር ምን አገናኝቶት አጋራኸን?
....የማንንም የሶሻል ሚድያ መብት በመጋፋት አይነት ሳይሆን ሲወደዱ ብቻ የጋራ፣ ሲነቀፉ የግል የሚሆነውን "ህይወታችንን" ስትሻማን ቅር ስለሚል ነው። እንደኔ እንደኔ.... ቢጥምም ቢመርም ካካፈልከኝ አይቀር በገዛ "ሚስታችን ቀሚስ"፣ በገዛ "ልጃችን ባህሪ"፣ በገዛ "መኝታችን ዲዛይን"፣ በገዛ "ውሏችን ፍሰት" የተሰማኝን ከማካፈል ወደኋላ አልልም። ምናልባት ያኔ... ለየትኛው ሰላም፣ መብቃቃት እና ጣፋጭ ኑሮ ሲባል ከአይኖች ደበቅ ማለትን እንደታዘዝን ከመረዳት ጋር፣ "የግል" ምንነት ይገለፅልን ይሆናል። ራህማኑ ወደሱ የሚያቃርቡን ነገሮች ላይ መስራትን ይወፍቀን።

....የሆነ ጥሩ ቀን ላይ ደግሞ... መውደድ... ከፍቅር ቃላት ውጪ የሚገለፅበት ብዙ መንገድ እንዳለው ድንገት ብልጭ ይልልሃል። አለም ስለተስማማበት የተግባር አገላለፅ ሳይሆን... ከቃላት መካከልም በቦታቸው ተብለው፣ በኋላ ላይ ልብ ስትላቸው ከሌላው ልቀው ስለሚገኙት ነው የምልህ። ለምሳሌ... የእናትህን "ጨርሰህ ካልበላህ ወየውልህ!" አይነት... የአባትህን "የት ነው ያመሸኸው?" አይነት... ከተግሳፅ ውጪም ሌሎች ውስጣቸው መውደድን የደበቁ አገላለፆች... አንዳንዴ "ይቅርታ"ን... አንዳንዴ "እወድሃለው"ን ተክተው እንዳሳደጉህ ትዝ ይልህና ፈገግ ትላለህ።
....ከሁሉም ደግሞ... ጉዳዩ የአኽላቅ ተምሳሌት የሆኑት ተወዳጅ ሀቢብ ስለመረጡት አገላለፅ ሲሆን ሚዛኑ ፍፁም ሌላ ታሪክ ይሆናል። እናታችን ዓኢሻ (ረ.0) ጋር ከሚቆዩባቸው ቀናት በአንዱ እንግድነት ከመጡ ሶሃቦቻቸው ጋር ተቀማምጠው ሳለ፣ ከሚስቶቻቸው አንዷ በአንድ አገልጋይ ወደሳቸው ምግብ ወዳስላከችበት ወደዛ ቀን እንሳፈር። ዓኢሻ በድርጊቱ ተበሳጭታ የአገልጋዩዋን እጅ ትመታታለች፣ ምግቡም ከነ ሰሃኑ መሬት ላይ ወድቆ ይሰበራል። ታዲያ እንደማንኛውም አባወራ ያዙኝ ልቀቁኝ በሚያስብለው በዚ አጋጣሚ ላይ ሃቢቡና ቀለል አድርገው "እናታቹ ቀንታ ነው" በሚል ፈገግ በሚያደርግ ማስተባበያ ሸፍነውላት፣ ምግቡንም በምግብ፣ ሰሃኑንንም በሰሃን እንዳስተኩ ይነገራል። "እናታቹ ቀንታ ነው"... ምን አይነት ሰኪና... ምን ያለ ሂክማ ነው! አላልክም?... የማን ጭንቅላት ላይ እንዲ ሁሉን በአንድ የያዘ አገላለፅ ይመጣል? አንድም ንዴቷ እሳቸውን የመውደድ መሆኑን ሲረዱላት የሷን መውደድን.... አንድም እንግዶቹ ስሟን ይዘው እንዳይሄዱ ሲሰትሯት የሳቸውን መውደድን.... "ስለምወድሽ መውደድሽን ተረድቼ አልፌልሻለሁ" አይነት.... ማንስ ቢወዳቸው፣ ቢቀናባቸው መች ይገርማል?.... "በሳቸው ውስጥ መልካም መከተል (ምሳሌ) አለላችሁ" የተባልነውን ልዩ ሰው መከተልን.... ካስተማሩን ብዙ ብዙውን መተግበርን ራህማኑ ይወፍቀን።

ንጋት...
ሲነጋ አይኖች ሲከፈቱ፣ አዲስ ቀን ብቅ ያለ ይመስላል። ነገር ግን ንጋት ሁሌ አዲስ ተስፋ አይደለም። የትናንቱን ኮተት ሰብስቦ የሚመለስ፣ ፀሀይ መውጣቷ ብቻ የሚለየው ዳግማው ትናንትም ይሆናል። እድሜያችንም የነዚህ ቀናት ጥርቅም ነው። ዳግማዊ ትናንቶች በየቀኑ ሲደጋገሙ ህይወታችን ወጥ ይሆናል። ዛሬዎችን ማጣት ህይወትን ይበልጥ አሰልችና የሚያስመርሩ ያደቸዋል። በነዚህ ቀናት ስናልፍ አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ አዳዲስ ንጋቶች፣ አዲስ ቅርፅ ያለው ዛሬን ሲሰጡን ትላልቅ የደስታ ቀናት እናልፋለን። የደስታ ቀናችንንም አንድ ብለን ከቆጠርናቸው ብዙ ዳግማዊ ትናንቶች ጋ ደምረን አንድ እርምጃ እንደተንቀሳቀስን ሁሉ.... ዳግም ወደቆጠራ ተመልሰን ሁለት እንላለን። እድሚያችንም ይበልጥ ያጥርብናል። ብዙ የተቃጠለ እድሜም እንዳለ ይሰማናል። ዳግማዊ ትናንቶችን መደምሰስ ባንችልም ግን ከትናንቱ የተወሰነ ልዩነት ለማምጣት ብለን እስካልተነሳን ድረስ አዳዲስ ዛሬዎች ይበልጥ እየራቁን ይመጣሉ። ስለዚህ ቢያንስ ትናንትን ከዳግማዊ ትናንት ለመለየት የቀኑን አጀማመራችንን እንለውጠው ወይንም አጨራረሳችንን። አንድን ቀን ሁለቴ ላለመኖር ያክል ብቻ…

መንገዶች በመድረሻቸው ይለካሉ.... መድረሻህ የሚገባው ከሆነ መንገድህ ሩቅ አይደለም፣ ደስ የሚል ተሞክሮ ነው.... አድካሚ አይደለም እውቀት ያጀበው እድገት ነው። መድረሻህ ተራ ከሆነ መንገድህ ቅርብ ቢሆንም ብክነት ነው.... ልፋትህ ቀላል ቢሆንም ባዶ ነው። ለዛም ይመስለኛል ለአኼራ ስንኖር ነገ እንደምንሞት፣ ለ ዱንያ ስንሰራ ገና ጊዜ እንዳለን መኖርን የተመከርነው። ብቻ...... ጀነት ለመግባት የሚበቃ ስንቅን ለመሸከፍ የዱንያ ቆይታችን በመርዘሙ አድክሞ አያውቅም.... ከደከመን ከመድረሻው ነው።
@Re_Ya_zan
@Re_Ya_zan
በምድር ላይ ባለህ ቆይታም ከመልካሞች ጋር ተወዳጅ...እነርሱ ከመካከላቸዉ በጠፋህ ጊዜ ፈላጊዎችህ ናቸዉ፣ መንገድ ስተህ ባዩህ ጊዜም ይመልሱሃል፣ በተዘናጋህ ጊዜ ያነቁሃል፣ በራቅካቸዉ ልክም ይናፍቃሉ፣ ከጌታቸዉ ጋር በተንሾካሾኩም ቁጥር ስምህን አይረሱም...🤍
@Re_Ya_zan
@Re_Ya_zan
እድሜ
ልጅነት የተለየ አለም አለው። ደስታ፣ ጨዋታ፣ መቦረቅ፣ መደባደብ… ከኛ ከትልቆቹ አለም እጅግ ይለያል። በጣም ጣፋጭ የማይገኝ የሚናፍቅ ጊዜ ነው "ኧረ ልጆች ልጆች እንጫወት በጣም፣ ከእንግዲህ ልጅነት ተመልሶ አይመጣም…" እያልን ትርጉሙን ሳናውቀው እየዘመርን ቦረቅንበት። ትልቅ መሆን እንደተመኘን ነፃነት ያለው እየመሰለን እየጓጓንለትም አደግን። ነገር ግን ስናድግ ትልቅነት እንዳሰብነው የሚናፈቅ አለም ሁኖ አላገኘነውም። ልጅ ሁነን እጃችን ላይ ትንሽ ነገር ከቧጨረን ሳምንቱን እንደ ህመምተኛ እጄን ነካብኝ፣ አያስበላኝም፣ አያስተኛኝም ብለን እንዳልቀበጥን ሁሉ፣ አሁን መች እንደቆሰለ ራሱ የማናውቀው ብዙ ቁስል ሰውነታችንን ሞልቶታል። መች እንደቆረጥነው ሳናውቅ ረጥቦን ስንመለከተው እየደማ እንደሆነ የምናውቅባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም። በማደግ ውስጥ አለመታመም ኑሮ ወይስ የውስጣችን ህመም በዝቶ ይሆን ሲቆስል የማትታወቀን ባይገባኝም ትልቅነት ግን የሚያጓጓ ጊዜ አልነበረም።
በትልቅነት ውስጥ አዕምሯችን ይበሰልም አይብሰልም ሀላፊነቶችን የመወጣት ግዴታ ይኖርብናል። አሁን ላይ እያንዳንዱ ጥቃቅን ስህተት "ልጅ ናት አታውቅም" ተብሎ አይታለፍልንም። "ትልቅ አልደለች እንዴ?!" ብሎ ተቆጪው ወቃሹ ብዙ ነው። የስኬት መንገዶች ላይ ድሮ ልጅ እያለን የማናውቀውን "ምቀኛ" የሚባል ቃል እንማራለን። በየምንገዱ ማልቀስ ላገኙት ሁሉ መዘርገፍ የማያዋጣ ነገር ይሆናል። ድሮ ልጅ ስለሆንን "እንዳያስቡ!" ተብለን የተደብቅናቸውን ችግርና ፈተና የሚባሉ ነገሮችን በተግባር እንማራለን። ከዛም ትልቅነት ያስጠላናል፣ የምንነፋረቅበት እቅፍ ይናፍቀናል። ወደ ልጅነት መመለስን ብንሻም በምኞት ውስጥ ስንዋልል ቁሞ የሚጠብቅ እድሜ የለንም። ከኋላችን እርጅና ያሳድደናል አሁን ከምንኖረው የባሰ የሆነ እድሜ። ቁጭ ብሎ ወጣትነትን እያስታወሱ ራሳችንን የምንወቅስበት እድሜ። መለስ ብለን ስናስበው ብንመለስበት ብዙ ማሳካት የምንችልበት እንደሆነ እንዲሰማን የሚያደርግ፣ አሁን ብዙ ያደከመንን ፈተና "ለዚህ ነው?" ብሎ የሚያስንቅ እድሜ ወደፊት ይጠብቀናል። ምኞት ብቻ ሁነን መስሪያ ጉልበቱን የምናጣበት፣ ለነገ ብለን የገፋነው ሁሉ ተጠራቅሞ የሚጠብቅብን፣ አንገፋው ወደፊት የለን…አንሰራው አቅሙ የለን… እንዲሁ ሁነን እንባክናለን። ከዛም ለምን ወጣትነት ላይ ፈተና እና ችግር እንደሚበዛ ይገለጥልናል። የተሻለ የእርጅና ዘመን ላይ መኖር እንችል ነበር። ነገር ግን ነጋችንን ሳናቅድ ኑረነዋልና ያተረፍነው ነገር ምን እንደሆነ አይገባንም። ከዛም ዳግም ለምን ወጣትነቴን ሳልጠቀምበት የሚል ቁጭት እናስከትላለን። ይህን የሚያውቁ አዛውንቶችም በቻሉት መጠን ሊመክሩን ይጥራሉ። ሁሉም ባለፈበት እንድናልፍ አይመኝልንም። ትንሽ የሚንቀሳቀስ ወጣት ሲያዩ ይደሰታሉ። ሁሉም ወጣቱን ህዝብ ይፈልገዋል፣ ለስኬት አስፈላጊ እንደሁነ ስለሚያውቅ ያለፈውን እድል ወጣቱን ተጠቅሞ እንዲሳካለት ይለፋል። ምክንያቱም አስቦበትም ይሁን ሳያስብበት ሀላፊነትን የተሸከመው ወጣት እሱ ብቻ እንደሚያሳካው የሚያውቁት እድሜውን ያለፉት ብቻ ናቸውና። እናማ… ህመሙ፣ ችግሩ፣ ሀላፉነቱ ቢበዛም ሁሉን ችሎ ትልቅ ቦታ የሚደርሰው የወጣትነት ሀይል ያለው ብቻ ነውና ችለን ነጋችንን መገንባት ትልቁ ስኬታችን ነው። የእድሜያችን ፈተና ይህ ስለሆነ!

ማናችን እንሆን...ከወንጀል የጠራነው በየትኛው መንገድ ይሆን መልካም ሰሪ ብቻ የሆነው በይፋም ሆነ በድብቅ ስንት ወንጀሎችን እንሰራለን...ነገር ግን የኛ ሩህሩና አዛኝ የሆነው አላህ ወደ እሱ በቀረብን ቁጥር ሁሉንም ወንጀላችንን ይምረናል እንደ ሰው ድጋሚ ሳያነሳ ወንጀላችንን ሁሉንም በምህረቱ ያልፍልናል ታዲያ ይሄን የመሰለ ጌታችንን ማመፅ እንዴት ቀላል ሆነ...?
.
.
@Re_Ya_zan
.
.
@Re_Ya_zan
እየደከምክ ግን ላለመውደቅ በመፍጨርጨር ውስጥ ሳለህ የማይደርስልህ፣ የማያስተውልህ ወዳጅ የወደቅክ ቀን ሊያስተዛዝንህ ብቅ ይላል። የመውደቅ እንጂ ይዞ የመቆየት ህመም የሚያም አይመስለው ይሁን አሊያ ስትወርድ አንድኛውን አላቅስሐለሁ ብሎ ይሁን ብለህ ጠርጥር። እንጂ መውረድህ እፎይታ ሰጥቶት ከንፈር ይመጥልኛል ስትል አትጠርጥር።
አውቃለሁ እያነባህ የደስታ የሚመስላቸው ሰዎች እንዳሉ፤ እየታገልክ ቀና ያልከውን ከኩራት የሚመድቡት እንዳሉ ይገባኛል። ያለፍከው መከራ ልብህን እንደወንፊት አሳስቶ ቶሎ እንደሚከፋህም።
ግን....
መታገልህን የሚረዳ፣ በቁም ውስጥህ እየተበላ እንደሆነ የሚያየው አሏህ አይበቃህም? ሊፈርድብህ ሳይሆን ሊሰማህ የተዘጋጀው አሏህ፤ ብስራቱን ሊሰድልህ ጥቂት ትቀርበው ዘንድ አንተን መጠበቁ አይበቃም ?
ትንሽ ታገስ። የተስፋን ክር የያዝክበቱ እጅህ ከጌታው የሆነን መረዳት እስኪያገኝ ድረስ ታጋሽ ሁን!

....አንድ የጌታሽ ዱንያ ላይ፣ ሁለቴ መጣን እንል ዘንድ ለትዝታ....
.
.
"ስካር
ከምሽቱ 6:07
<ኧረ ልጅቷ ዛሬ በጤናዋም አይደለች! ምን ነክቷት ነው።> ቅድም ጀምራ የምትስቀውን እንስት ግራ በመጋባት ውስጥ ያይዋታል። ስተፈልግ ደሞ እየሳቀች ታለቅሳለች። በአፏ አንድ ነገርን ከመደጋገም ውጭ ለሚጠይቋት ጥያቄ ምንም መልስ አልሰጥ ብላቸዋለች። <ሰክራ ነው> ብለው ጥለዋት ሄዱ። ከማንም በፊት ለድሮ ሚስጥረኛዋ ጨረቃ መናገር ነበረባትና እነሱ ከመሄዳቸው ወደ ሚስጥረኛዋ እየተመከተች መናገር ጀመረች።
< ሰማሻቸው ጨረቃዬ! ሰከረች አሉኮ ሃሃሃሃ ለነገሩ ምን ይበሉ እኔን ያሰከረኝ ነገር መች ገብቷቸው። ልክ ናቸዋ ሰክሪያለሁኮ፣ ግን ጠጥቼ አይደለም የሰከርኩት። እያሳቀ የሚያስለቅሰኝ ስካር የደስታ ስካር ነው። ለካ ደስታም ያሰክራል። ታውቂያለሽ! እስከዛሬ ተናድጄ፣ ታምሜ፣ አዝኜ፣ ተከፍቼ፣ ናፍቄ ነበር እንቅልፍ የማጣው ዛሬ ግን በተለየ ሁኔታ በደስታ ሰክሬ ነው።> ፈገግታ ምስልን የተላበሰችው ጨረቃ እሷም በደስታዋ የተደሰተች ትመስላለች። ንግግሯን ቀጠለች < ጨረቃ ግን አልገረመሽም! ብዙ ነገር በአንዴ እንደዚህ ብስራት በብስራት ሲሆን? በራስሽ ብስራት በጣም ተደስተሽ ደስታሽን የምታካፍያቸው ሁሉ ሲደሰቱ ስታዪ ደሞ ምን ያክል ደስታሽ እንደሚጨምር። ከዛም ደሞ እንሱን ያስደሰታቸውን ሲያካፍሉሽ፣ በነሱ ደስታ ስትደሰቺ ሱብሃንንን… ታውቂለሽ በአንድ ወቅት ለኔ ቅርብ የሆነው ወንድሜ "ችግሮች ጫፍ ሲነኩ መፈቻቸው ይቃረባል" ብሎኝ ነበር። ከቀናት በፊትኮ በዚሁ ሰአት ጭንቄን ላሰማሽ ተቀምጬ ነበር። የአሁኑ ደስታዬ ደሞ በቃ ጭንቅ ውስጥ ማለፍ ምንም አንዳልነበር ያሳየኛል። እና እንደዚህ ሁኖ በደስታ ብሰክር ይፈረዳል ወይ? ለካ አንዳንዴም ከማዘን ይልቅ የኢላሂ ባሪያ በመሆን ብቻ መደሰትም የሚገባ ነው። > ምላሽ ሳትጠብቅ እየተፍለቀለቀች ከተቀመጠችበት ተሳች። ከማንም በፊት ምስጋና ለሚገባው ጌታ መስገጃዋ ላይ ተደፍታ ልታመሰግነው!
" ألهم لك الحمدْ كما ينبغي لجلال وجهك و لعظيم سلطانك "
ረቡዕ 19/12/13"
@Re_Ya_Zan
🚨SERIOUS ACTION NEEDED FROM ALL RIGHT NOW🚨
This channel has appeared in YouTube called B Quranic Songs that combines music with the Holy Quran. Whoever can report this channel should do so until it is closed.
REPORT THIS HERETIC CHANNEL THAT DISTORTS THE QURAN! ⚠️‼️
ارجوا التبليغ عن هؤلاء الزنادقه قندره عليهم
https://youtube.com/@quranicsongs?si=-YXoOKuPtmGj1RdO

Because they got alot of report on the above channal they proceed to this new one. We will not stop reporting untill they stop mocking by our Quran‼️‼️‼️
Report their YouTube channel ⚠️
https://youtube.com/@officialquranicsongs?si=et-vaE3gi_LD1-yE
And here their telegram channal👇
https://www.tgoop.com/QuranicSongs

Forwarded from HURQAN
በ ህይወትሽ የትኛው የህይወትሽ ክፍል ቢደገም ትደግሚያለሽ?ብባል ድጋሚ እንኳን ሳላስብ 'አስራ ሁለተኛ ክፍልን!" ምል ይመስለኛል😊
በጣም ሰነፍ ነበርኩ ብያችኋለው? ብቻ ሰነፍ ነበርኩ ( አሁንም!😂) እና ለ ኢንትራንስ እንድናጠና ሚዘጉልን ጊዜያት እንዴት ያለ ቆንጆ የ እንቅልፍ እና የ ወሬ ሰአት ሆኖልኝ እንደነበር! ልናጠና ተሰብስበን ስናወራ ቀኑ እልቅ!... አጥንቶ እንደዋለ ሰው ቤት ገብቼ እራቴን በልቼ ለጥ!.....ግን ይሄ ምቾት ብዙ አልዘለቀም። በሌላ በኩል የ dicipline ማስተርስ ያላቸው ጓደኞቼ በየት ያስተኙኝ?😑 ቤት ድረስ እየመጡ እየጎተቱ ላይብረሪ! ወለም ዘለም የለም። ብቻ ከወሬው ፣ ከዝላዩ እና ከማይረሱ ትዝታዎቹ ጋር እንደዛሬም ነገር ባለመክረሩ በ አላህ ራህመት + በ ጓደኞቼ ፅናት በጥሩ ውጤት ግቢ ገባው።
ባለፎ የዘንድሮዎቹን አግኝቼ "እናንተ ላይ ከፍቷል ጊዜው መቼም.. እንዴት ነው ጥናት?" ስላቸው እኩል ሳቁና
"ትተነዋል ባክሽ" አሉኝ።የዛን ቀን ፊታቸው ላይ ያየሁት ተስፋ መቁረጥ አስደንጋጭ ነበር።already ቀድመው እንደሚወድቁ አምነው ተቀብለውታል።ደሞ ገና 11 ላይ 12 ሲወድቁ ምን እንደሚሰሩ ከሚያወሩ ለጋ ወጣቶች ጋር ማውራት ሲያስጠላ ወላሂ!!
ግን "ለዚህ ምክንያቱ ማንም ይሁን ማን መወቃቀሱን ትተን ዳይ ወደ መፍትሄ!" ያለው ሁርቃን(hurqan) ተቋም ፤ አምና በ አመርቂ ውጤት 12ተኛ ክፍልን አገባደው ወደ አንጋፋው አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተቀላቀሉ ተማሪዎችን በመጋበዝ ፤ ለዘንድሮ ሙስሊም ሴት ተፈታኞች በ ሞራል ፣ በ ምክር እንዲሁም በ ልምድ ማጋራት( Experience sharing) ሊያሳሽቃቸው ዝግጅቱን እያገባደደ ነው።ሙስሊም ሴት ናችሁ?ለ ህይወታችሁ እድገት ቦታ አላችሁ? ባትሆኑም ሙስሊም ሴቶችን ማበርታት ትፈልጋላችሁ? እንግዲያውስ እንቀላቀል!
(12ተኛ የሆናችሁ ሴቶች ደሞ ግዴታ ነው!☺)
https://www.tgoop.com/HURQANN

Telegram
HURQAN
"Freed by wisdom! "
Forwarded from This generation🗯🤳
***
የፈገግታ ሃይል
የፊትዎ አገላለጽ (Facial ecpression) ስሜትዎን እንደሚለውጥ ያውቃሉ
ፈገግታ ጥሩ ስሜት ውስጥ ባትሆንም እንኳን አእምሮህን የበለጠ ደስተኛ እንድትሆን እንደሚያታልልህ ታውቃለህ? እሱም “የፊት አስተያየት መላምት” ወይም 'Facial Feedback Hypothesis' ይባላል። እናም አእምሮህ በአንተ ላይ የሚጫወተው ሃይለኛ ተንኮል ነው።
ፈገግ ስትል፣ ወደድክም ባትፈልግም አእምሮህ ደስተኛ መሆንህን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ይቀበላል፣ ይህ ደግሞ ስሜትህን ይጨምረዋል። . የሚገርመው ደግሞ ትንሽ ፣ የግዳጅ ፈገግታ እንኳን depression ወይም ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳል ፣ ይህም የበለጠ ዘና ያለ እና አዎንታዊ ስሜት እንዲሰማዎት ያደርጋል። ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ለእምሮህ ትንሽ ደስታን እንደመስጠት ያህል ነው።
እናም ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው 😊በሚቀጥለው ጊዜ የድካም ስሜት በሚሰማችሁ ጊዜ ይህን ቀላል ሆኖም ውጤታማ ዘዴ ሞክሩት። ፈገግ ..... መጀመሪያ ላይ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ቢመስልም አእምሮህ ዝም ብሎ ሊይዝ እና ስሜትህን ሊለውጠው ይችላል። እናም አስታውሱ፣ ደስታን ማስመሰል ብቻ አይደለም - ለራስህ የተፈጥሮ መነሳት እና ቀኑን ብሩህ ማድረግ ነው!
JOIN
👇👇👇👇👇👇👇👇
@factandfiction1
@factandfiction1
-----------------------------------------