Telegram Web
🕋🌠 ኢቅረእ ኦንላይን መድረሳ 🌠🕋

        የሚንሰጣቸው የደርስ
          /ትምህርት አይነት

1) 📖 አዲስ ጀማሪዎችንና ከዚህ በፊት ቁርኣን ያላ ኸተሙትን ከቃዒዳ (አሊፍ) አስጀምረን በተጅዊድ በ5 ወር ዉስጥ ብቻ ሙሉ  (30 ጁዝ) ቁርኣን ማስኸተም።
2) 📖 ከዚህ በፊት ቁርአን ያኸቸሙና አሁን ድጋሚ በተጅዊድ ማጣራት ለሚፈልጉ ከቁርአን በተጨማሪ (2) ደርስ እንሰጣለን።እነሱም
   ★)ፊቅሂ ሠፊና   â˜…) ሐዲስ አርበዒን
3) 📖 ቁርኣን በተጅዊድ ያኸተሙ ከሆነ ደሞ ፊቃዳቸው ከሆነ ሒፍዝም እናስተምራለን በተጨማሪም መሠረታዊ የሆኑ የተወሰኑ ኪታቦችንም እናስቀራለን።

       ☘የቂራአት አሰጣጥ☘
☘ፕሮግራም በ3 አይነት ሲሆን☘

1)  ለየ ብቻ...ይሄ ማለት ለ1 ተማሪ አንድ አስተማሪ በመመደብ ተማሪው የሚመቸዉን ሠአት መርጦ የሚቀራበት
2)  በጀመዓ በላይቭ... ይሄ ደሞ በተለያየ ቦታ ያሉ ሠዎች ወይም ቤተሠብ ሆኖ 1 ላይ መቅራት የሚፈልጉ የቂራት ደረጃቸው ተመሳሳይ ከሆነ ኡስታዙ ላይቭ ገብቶ ተማሪዎቹ በያሉበት ሆኖ 1 ላይ የሚማሩበት ዘዴ ነው።
3)  ደርሱ የሚሰጠው በሳምንት ለ3 ቀን እና ለ4 ቀን ሲሆን አንድ ተማሪ ከሁለቱ አንዱን መርጦ መመዝገብ ይችላል።

ብዙዎች እየ ተጠቀሙበት ያለና የወደዱት የቂራአት ፕሮግራም ነው። እርሶም ባሉበት ሆኖ ባሎት ትርፍ ሰአት አመቻችቶ የአሏህን ቃል ቁርኣን እንድማሩና የዲን እውቀቶን እንድያዳብሩ እናስታውሳለን።

🕋🌠ኢቅረእ ኦንላይን መድረሳ🌠🕋

ለመመዝገብ
በTelegram ወይም በWhatsap
👇        
+251 9 03 76 98 12 
+251 9 11 59 80 81

ይሄን ንኩት   👉
@Ahlenbik

https://www.tgoop.com/onlinekuranmedresa

ይመዝገቡ በየ ግሩፑም ሼር ያርጉ የአጅሩ ተካፋይ ይሆናሉ።ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን።
ምርጥ የዱአ ኪታብ.pdf
18.5 MB
ምርጥ የዱአ ኪታብ

እጥር ምጥን ያለ ምርጥ ዱአ ነው አውርዱና ተጠቀሙበት ወላሂ ይጠቅማችኋል እንዳያልፋችሁ!!!



ካወረዳችሁ ቡሀላ save ማድረጋችሁን አትርሱ!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📝እናቱን ለሚወድ ሁሉ ይሁንልኝ

!!
-----------------------
ሰው የመሆን ሰበብ መነሻ ጅምሬ፡
የእዝነት የደግነት መልካም መምህሬ፡
ገና በልጅነት በጨቅላው እድሜየ፡
በጆችሽ ስር ሁኜ በጀርባሽ ታዝየ፡
ያላስብ ስቦርቅ ሁሉን ላንቺ ጥየ፡
አወ ያኔ ገና አዝለሽኝ በጀርባሽ፡
ልጅሽን ለማዳን ገደል እየገባሽ፡
አምሳያ የለሽም ይስባል ሙሀባሽ፡

ያኔ ውስጤ ገብቶ ሚስጥረ-ናትነት፡
ከልቤ እማይጠፋ ሆኖብኝ ቀረ እምነት፡
የብርሀን ተስፋ የዘጠኝ ወር ቤቴ፡
ሁሌም ዝቅ የማትይ ክቡር እመቤቴ፡
የበሽታዬ ፈውስ ግሩም መድሀኒቴ፡
የመኖር ትርጉሜ አንች ነሽ እናቴ፡
~
በክብር በሞገስ ከተራራ ገዝፈሽ፡
ከማንም አይለሽ በልቤ ተፅፈሽ፡
አምሳያሽ ቢፈለግ በአለም ዳርቻ፡
አንችን የሚተካ አይገኝም አቻ፡
የመኖር ስበቤ ሆነሽ አንቺ ብቻ፡
ባሳቤ እየመጣሽ በአመትም በመንፈቅ፡
አለሁ ዛሬም ድረስ አንችን በመናፈቅ፡
!!
አለሁ እማማየ በናፍቆትሽ ብትር እየተሰቃየሁ፡
ባንች ከፍ ብዬ ከህያዋን ተርታ ስኬቴን እያየሁ፡
የልፋትሽ ፋና ልጅሽ ላይ ይታያል፡
ከማንኛውም ሴት ያንቺኮ ይለያል፡
ሌላ እናቶችን ሳይ ይይዘኛል ቅናት፡
፡
~
የኔ ማማ!!
ልጄ በሚል ጥሪሽ ዳቦ የቆረሰ፡
በፈገግታሽ ደምቆ በእጂሽ የጎረሰ፡
እየተንከባከብሽ ወልደሽ ያሳደግሽው፡
ጠንክርልኝ ልጄ ብለሽ የመከርሽው፡
ማንም ምንም ቢለው አይፈልግም ሌላ፡
አለም ቢሰበሰብ ከእናቱ በኋላ፡
እናት የሌለው ልጅ አይበላም ትኩስ፡
ከጎራ ላይ ዘልቆ ካልመታው ነፋስ፡
ከማንስ ይገጥማል ያንች መልካምነት፡
ይለያል ከሌሎች ያንችስ እናትነት፡
ልክ እንደ መፅሀፍ አንበሽ ፊቶቸን፡
ገላየን አጥበሽኝ አፅድተሽ ልብሶቸን፡
እሰይ የኔ አንበሳ ስትይኝ ጀግናዬ፡
ጉንጨን ስትስሚኝ ፈክቷል ልቦናዬ፡
ፊቴን ተመልክተሽ ስሜቴን በማጤን፡
ቶሎ እየተረዳሽ ሀሳቤን የውስጤን፡
ስስቅ አብረሽ ስቀሽ ስከፋ ተከፍተሽ፡
ወዳጅ ጠላትሽን በኔ ላይ ለይተሽ፡
ልጀን የወደደ ካንጀቱ ወደደኝ፡
እሱን የጠላ ሰው እኔን ይፋረደኝ፡
ብለሽ የተናገርሽ የዘመን ግሩም ሴት፡
የኔ እናት ነሽና ይሰማኛል ሀሴት፡
~ ~
!!
ልጄ የሚለው ድምፅ ዘገየብኝ ካፍሽ፡
የእዝነት የደግነት ናፈቀኝ እቅፍሽ፡
እኔን እንዲሞቀኝ አንቺ ተበርደሻል፡
ልጅሽ እንድጠግብ ብዙ ተርበሻል፡
ውርጭና ፀሀዩን አፈራርቀሽዋል፡
መከራ ስቃዩን ለኔ ችለሽዋል፡
እማ ያንቺኮ ይገርማል.....!!
ከማንስ ይገጥማል.....!??
እኔ አለሁ በህይዎት ዛሬ ያሁሉ አልፎ፡
አንችን እያሰብኩኝ ሚዛኔ ተዛንፎ፡
አንቺ ሁሉን ሁነሽ እኔ ሳይጎልብኝ፡
እኔ ዛሬም አለሁ አንች ግን ሔድሽብኝ፡
እውነቱን ልንገርሽ ስሚኝ ውዷ እናቴ፡
መግለፅ ቢችል አንቺን ተናግሮ አንደበቴ፡
አወራልሽ ነበር፤
እስከ አለም ፍፃሜ እስከለተ ሞቴ፡
ግን አልችልምና ጨርሸ ልገልፅሽ፡
በትዝታሽ ልኑር ሁሌም ሳላምፅሽ፡
እኔን ሰው ለማድረግ አንቺ እንደኖርሽልኝ፡
፡
!!
በህይዎት እያለሽ ሰጥተሽኝ አደራ፡
ብለሽኝ ነበረ ልጄ ባንተ ልኩራ፡
እኔም ብየሽ ነበር ኢንሻ አሏህ ማማ፡
ሞት ሳይመጣ በፊት አንችን ሳልቀማ፡
ሀዘን ውስጤ ሰርፆ አሁን ተሸነፍኩኝ፡
ትዝ ባልሽኝ ቁጥር በእንባ እየታጀብኩኝ፡
ብዙ አመት አስቆጠርኩ ከተኮላተፍኩኝ፡
ልጅ ከናቱ ጋር ሳይ ውስጤን ይሰማኛል፡
ሰውነቴን ሁሉ ሀዘን ይነዝረኛል፡
መታገስ አልችልም ያንቀጠቅጠኛል፡
አንዳንዴዬ ደግሞ ደስ ደስ ይለኛል፡
ያንች ልጅ መሆኔ ፅኑ ያደርገኛል፡
ይህች ግሩም አለም አውነት ጨለማ ናት፡
፡
~
የእናቴን ውለታ፤
ግሩም ትዝታዋን እኔ ስስልልህ፡
በተቻለኝ አቅም፤
መልካም ማንነቷን ስዘረዝርልህ፡
!!

በብር አይገዛ አይከፈል ዋጋ፡
ህይዎት ያለሷ አያምር ምሽት ቶሎ አይነጋ፡
ትዝታዋ አይለቅህ ቆላ ብቴድ ደጋ፡
ግርፋቱ አያቆም የናፍቆቱ አለንጋ፡
እንደትስ ይቻላል ይህ ከባድ አደጋ፡
እንደምን ይረሳል የናትነት ፀጋ፡

በኑረዲን አል አረቢ (ከገጠር)
~~

بارك الله في كل الأمهات تحيا أكثر صحة وصحة🤲🤲

@rezakuhakimu
@rezakuhakimu
@rezakuhakimu
*⬇️ አች ውድ እህቴ⬇️*
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️አች ዉድ እህቴ ወዴት ነዉ ያለሽዉ
▪️ፌስቡክና ቲክቶክ ግዜሽን ያረግሽዉ
▪️በዚህኛዉ በኩል ዩቱ ላይ ያለሽዉ
▪️ዉዴቷ እህቴ ወዴት ነዉ ያለሽዉ
▪️እዉቀትን ከመማር የተዘናጋሽ
▪️በየሶሻል ሚዲያዉ እዳሻሽ የሆሽ
▪️ ለምዕራሙ አለም መጫወቻ እየሆሽ
▪️ሀያዕሽን በመግፈፍ እዳሻሽ እየሆሽ
▪️የኢስላም ጥላቶች በወጥመድ ጠልፈዉሽ
▪️ለርኩስ ስሜታቸዉ መጫወቻ አረጉሽ
▪️ክብርሽን በመግፈፍ አደባባይ ወተሽ
▪️የኢስላም ጥላቶች መጫወቻ አረጉሽ
▪️እባክሽ እህቶ ካለሽበት ንቂ
▪️ኢስላም አክብሮሻል በክብርሽ ድመቂ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️ዉዲቷ እህቴ ነይ ወደ እዉቀት ማዕድ
▪️ተማሪ ዲንሽን በቀደምት አረዳድ
▪️ጁህልና በሽታ ድቅድቅ ጨለማ ነዉ
▪️ከጁህልና በሽታ መዉጣት የምችለዉ
▪️ቁርአን ሀዲስን በሰለፍ አረዳድ ስንማር ብቻ ነዉ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️ለኛ ዉድ ነብይ አሏህ ሲነግራቸዉ
▪️አብብ በማለት ነዉ ቅድሚያ ያዘዛቸዉ
▪️ተዉሒድና ሽርክን ማወቅ የምችለዉ
▪️ስንማር ብቻ ነዉ እዉቀት ሲኖረን ነዉ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️እኒያ ምርጥ ትዉልድ የረሱል ሶሀቦች
▪️እዉቀትን ተምረዉ በተግባር ሰሪወች
▪️አንድ ሀዲስ ለመማር 1ወር ተጓዥወች
▪️ነበሩ ብርቅየ የኢስላም ጀግናወች
▪️የተዉሒድ አበሳ የሽርክ ጥላቶች
▪️ናቸዉ ምርጥ ጀግና የአሏህ ውድ ባሮች
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️ዉዲቷ እህቴ እዉቀትን ተማሪ
▪️ልክ እደቀደምቶች በሱና ተመሪ
▪️ፌስቡኩ ላይ ቲክቶክ ላይ መጃጃልን ትተሽ
▪️ቁርአንን ቅሪ አሊፍባታ ብለሽ
▪️ኪታቦችን ቅሪ ከቲክቶክ ላይ ወተሽ
▪️ነገ ለልጆችሽ የምታወርሽዉን
▪️እዉቀትን ተማሪ ላችም ጠቃሚዉን
▪️ለዉድ ልጆችሽ መድረሳ ነሽ አች
▪️ከቲክቶክ በመዉጣት በኢልም ላይ በርች
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️ያች ተምሳሌቶች መሆን ያለባቸዉ
▪️እኒያ ምርጥ ትዉልድ እኒያ ሶሀባወች
▪️ ለአሏህ ትዛዝ ፍሙም ታዣዥወች
▪️ናቸዉ ያች ሞዴል እኒያ ብርቅየወች
▪️አዒሻ፣ ኸድጃ፣ ሌሎች ሶሀባቶች
▪️ አርጊ ተምሳሌትሽ እኒንያ እቁ ሴቶች
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
✍🏻ኡሙ አይመን 🌸
​​​​

    
          ያልጎደለ ማነው❓


ማነው ግን ያልዋሸ ከሐሰት ያልዋለ?
በምላስ ወለምታ ሰው ሆኖ ያልዛለ
እውነት ያልጎደለው ማስመሰል ያልቻለ
የእውነት ስፍር እምነት ቃል ያላጎደለ?
እስኪ ሰው ፈልጉ ውሸትን የናቀ
ሐቅን ቤቱ አድርጎ ከርሷ የዘለቀ
ትዳሩን አክባሪ ለጓደኛው ታማኝ
ጥላቻ ያልነካው ፍቅርን አቀንቃኝ
ለተራበው አጉራሽ መንፈግን የማያውቅ
በፍርድ አደባባይ እውነትን የሚያደምቅ
የሰው የማይፈልግ አመስጋኝ አብዝቶ
በፍቅር የሚኖር ካለው ግማሽ ሰጥቶ
የማይመፃደቅ በራሱ የማይኮራ
ጥቂትን ለግሶ ብዙ ማያወራ
ለእውነት ብቻ ነዋሪ ሰው መሆን የገባው
ውሸት ያልበረዘው ተንኮል ያልበከለው
በሉ ሰው ፈልጉ ያልጎደለ ማነው?
በሆነ አጋጣሚ ሁሉም የዋሸ ነው

https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
➧ግን ምን ነካሽ ❓❓
➮➮➮➮➮➮➮

ሽቱ ተቀብተሽ  እራስሽን በቀለም ለቅልቀሽ  ተሳፋሪን መንገደኛን ረብሸሽ     የረሱልን ትዕዛዝ ጥሰሽ  ከቤት ስትወጪ  አይደብርሽም ?? ምነው ሀያዕ ከበደሽ??
||
አለባበስሽን  አበላሽተሽ ብጥቅጣቂ ደራርበሽ  ልብሰሻል አይባል ራቆትሽ! አለበሽም አይባል ቁራጭ ነገር ጣል አድርገሽ  ሙስሊምነትሽን ረስተሽ ከቤት ትወጫለሽ??
  ታሳዝኛለሽ !ጌታሽን አፈሪም??
||
ግን ምን ፈልገሽ ነው ይሄን ሁላ የደከምሽ  እራስሽን ያረከስሽ ??  እስልምናሽ  የከለከለሽን  አልቀበልም ብለሽ የማንም መጫወቻ የሆንሽ  ?? ምን ነካሽ ? ? አረ ይቅርብሽ!!
||
    የውጮችን እስታይል ኮርጀሽ   የራስሽን ማንነት ጥለሽ  በሰው ማንነት ተጠልለሽ የተራ የፊልም አክተር ፈለግ ተከትለሽ  የውዱን ነብይ ፈለግ ጥሰሽ  እራስሽን    ታረክሺያለሽ??  አረ አያምርም !! ይቅርብሽ !! እንዳውም ሙስሊም ሁነሽ??
||
አለባበስሽን ኮርጀሽ ፣አነጋገርሽንም ኮርጀሽ፣ አካሄድሽንም ኮርጀሽ ፣አንቺነትሽን ለውጠሽ ! በሁለመናሽ ኮፒ ከሆንሽ !? ታዳ አንቺ ማነሽ!! በማንነትሽ?? ያፈርሽ !!

||
እኔ የምመክርሽ.

• ሀያዕ ምንግዜም አይለይሽ ! ሂጃብሽ ይሁን መጠለያሽ!!  ማንም ያላገኜውን ክብር ታገኚያለሽ።

• መጥፎ ጓደኞችን ርቀሽ  ጥሩ ጓደኞች ይኑሩሽ !! በጥሩ የሚያዙሽ ከመጥፎ ነገር የሚከለክሉሽ  ለቂረአት የሚገፋፉሽ   ጓደኞች ይኑርሽ!

• ቂረአትሽን ቅሪ  ያልቀሩትንም አቅሪ  ዳዕዋዎችን አዳምጪ ቂላ ወቃለ አታብዢ  

•  የሚድያ አጠቃቀምሽ ላይ ገደብ ይኑርሽ! ፌስቡክ ፣ቴሌግራም፣ ዋትሳፕ ፣ ላይ ሙሉ ግዜሺን አትጨርሺ ።

• ትኩረትሽን ኢልም ላይብቻ ማድረግ አለብሽ!  ያላወቅሺውን ለማወቅ ጥረት አድርጊ ያወቅሻትን ላላወቁት አሳውቂ!!

•  በጥቅሉ በሚጠቅምሽ ነገር ላይ ቢዚ ሁኚ  ነው የምልሽ።

✍አቡ ሁዘይፋ ይማም አያሌው



@rezakuhakimu
     @rezakuhakimu
          @rezakuhakimu
                @rezakuhakimu
                     @rezakuhakimu
                          @rezakuhakimu
🦋 አላህየ እወድሀለሁ 🦋

☪በእስልምና ላይ እኔን የፈጠርከኝ
ምድር ላይ እንድኖር እድል የሰጠኸኝ
የነቢ ኡመት ሰው እንድሆን ያረከኝ
ከሚገባኝ በላይ ብዙ የረዘቅከኝ
የምድር ፣የሰማይ የሁሉም ፈጣሪ
ጥያቄን መላሽ ወንጀልን መሀሪ
ንፍሴን በዳይ ሆኜ ከመንገድህ ብርቅ
አንተን ችላ ብየ ወንጀል ውስጥ ብዘፈቅ
ምድርን ቢሞላት ሀጢያቴ በዝቶ
ሀራምን ቢዳፈር ልቤ አንተን ዘንግቶ
አንተ መሀሪ ነህ ከልብ ለጠየቀህ
ከሁሉ የላቀ ነው ምህረትህ እዝነትህ
ህይወቴ፣እምነቴ፣ኑሮ፣መሠረቴ
ማንነት፣አለሜ፣መኖር እና ሞቴ
ሁሉም ላንተ ናቸው ለአንድ ጌታየ
ሙስሊም ላደረከኝ ለውድ ፈጣሪየ
"ኡሂቡክ" ያ አላህ የአለማት ጌታ
የእኔነቴ ትርጉም የህይወቴ አለኝታ
ሁሉ ሰው ቢርቀኝ ከቶ ምን ቢሸሸኝ
ሁሌ ደሥተኛ ነኝ እኔ አንተ ካለኸኝ
ስራየን አዋቂ ተግባሬን ተመልካች
ንፍሴን ተከታታይ መንገድ አመላካች
ጥሪን ሁሉ ሠሚ ሁሉንም አዋቂ
ከጠየቅነው በላይ ሲሳይን ረዛቂ
ኧረ እንደው በቃላት እንዴት ይገለፃል
የምህረትህ ስፋት እጅግ ያስገርማል
"ኢላሂ ሀያቲ" ሁሌ እወድሀለሁ
ሲነጋም ሲመሽም አንተን እገዛለሁ
በሚገባህ መጠን አላመለኩህም
ብዙ አድርገህልኝ አላመሰገንኩም
አንተ ፊት መቆምን ሂሳብን ረስቼ
አትስሪ ያልክኝን ብዙዉን ሰርቼ
ስሪያቸው ያልክኝን አብዛኛውን ትቼ
ሸክማቸው ክብዶኛል ብዙ ወንጅሎቼ
አላሁ ይቅር በለኝ ብዙ አጥፍቻለሁ
ንፍሴን ተከትዬ ድንበር አልፌያለሁ
እዚህ ዋልያለሁ አኼራን ዘንግቼ
በዚች በድንያ ላይ እጅግ ተደስቼ
አንተ ሩህሩህ ጌታ ለፍጡራኖች ቸር
መንገድህ ላይ አፅናኝ እስክገባ አፈር
"ኢላሂ!ኢላሂ" ብዬ እጣራለሁ
ቸሩ ፈጣሪዬ ሁሌ ወድሀለሁ!!!

✍✍ሱመያ ቢንት ኑሬ

ተቀላቀሉን👇👇👇👇

☆🍓 https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
🦋🌙🦋🌙🦋🌙🦋🌙🦋
☆🍓 https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
[የስደት አቋምሽ ፍፁም አይለይሽ]
 
----------------------------------------
አድምጭኝ እህቴ የልቤን ላማክርሽ፣
ይጠቅማል ያልኩትን ለነፍሴ ለነፍስሽ፣
ስደት ስበብ ሁኖ ድንሽን ተምረሽ፣
ካደግሽበት ህይወት ራስን ቀይረሽ፣
ቀን ከሌት በመልፋት ተውሂድ ተገንዝበሽ፣
ከሽርክ  ከኹራፋት ከመሠሉ ፀድተሽ፣
ሱናን በመከተል ከቢዲዓ ርቀሽ፣
በሰለፎች መንገድ ጉዞውን ጀምረሽ፣
እውቀት ለመፈለግ ጊዜ ቦታ ሰጥተሽ፣
ሀቅና ባጢሉን ልዩነቱን አውቀሽ፣
በሂጃብ በመዋብ ስትር ቁጥብ ሁነሽ፣
በተስተካከለው በጠራው መንሀጂሽ፣
በዚህ ባማረ አቋም ስደት ላይ  ቆይተሽ፣
---------------------------------------------
መመለስን ካሠብሽ ብሎ ወዳገርሽ፣
ከዛ ካደግሽበት  ከቤት ከሰፈረሽ፣
ዲንሽን አትርሽ ፅኒ በአቋምሽ፣
ቃለረሱል ብለሽ ሀዱሡን ሞጥለሽ፣
የሸሪዓን እውቀት ስትቀስሚ ኑረሽ፣
በፍፁም አይገባም ጃሂል ሰው ሊያታልሽ፣
ሀገር ብትቀይሪ አይቀርም መሞትሽ፣

በሰራሽው ሾል  ቀብር መጠየቀሽ፣
እህቴ ነቃበይ ለአኼራ ቤትሽ፣
ከሁሉም በላይነው ይቀደማል ድንሽ፣
ከባልሽም ይሁን እድሁም ከልጅሽ፣
ከምትወጃቸው ከእናትና አባትሽ፣
ከቅርብ ጓደኛ ብሎም ከገንዘብሽ፣
እዳትታለሊ ቀዳሚ ነው ድንሽ፣
ሂጃቡም  አይውረድ ፍፁም ከአካልሽ፣
ከቤትሽ ተቀመጭ ኑሪ ተሰትርሽ፣
በዲንሽ ከመጡ  ካቋምሽ ሊያወርዱሽ፣
አትሸፋፈኒ ካሉ ሊያራቁቱሽ፣

እዳትፈሪያቸው ከላይነው ትዛዝሽ፣
ግደታ መሆኑን አሳውቂ አብራርተሽ፣
ከቁርአን ከሀድስ ማሥረጃን አጣቅሰሽ፣
ሀቁን እያወቁ አንቀበል ካሉሽ፣

ኒቃብ መልበስሽን ካልወደደ አባትሽ፣
ኒቃብ በመልበስሽ  ቅር ካለው ባልሽ፣
አንሰማሽም ካሉ በሰው አስመክረሽ፣
ያንች ምርጫ ይሁን መኖር ተለይተሽ፣
ወዳጅሽ ላይጠቅም የጠላ ላይጎዳሽ፣
ተሸፋፍነሽ ኑሪ ይሄ ነው ውበትሽ፣
ወደኋላ እዳትይ ፍፁም  ከአቋምሽ፣
አብሽሪ እህት አለም አላህነው ወኪልሽ፣

ከቢንት
  ሙሀመድ




https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
አህቴ  ሆይ  ንቂ !
~~~~~~~~~~~~
ፈገግታ እያበዛ በአስመሳይ ጥርሱ
ወደድኩሽ  እያለ በቅቤ ምለሱ
ፍቅርን ሲገልፅልሺ ቃላትን ቀምሞ
እመኝኝ  እያለ ሲነግርሽ ደጋግሞ
እንዳትሸወጂ ብልጥ ሁኝ አደራ
ፍቅርን አይገልፀውም የቃላት ድርደራ
ያንቺ  ያልሆነን ሰው በፍጹም አታፍቅሪ
በሀሳብ መንምነሺ ከንቱ እንዳትቀሪ
ከኔ አያልፍም ብለሺ ምኑንም ሳታቂ
የፍቅር አባዜ ጠልፎሺ እንዳትወድቂ
ደግሜ ልንገርሺ እህቴ ሆይ ንቂ
ከእንድህ አይነት ነገር በጭራሽ ራቂ
ለምኑም ለምኑም አትጨናነቂ
አላህ ባለ  ግዜ  ይሆናል አወቂ
ያንን ቀን በተስፋ ከጌታሺ  ጠብቂ ፡፡

~~~~~~~~~~~~~~~~~
☞ ኡክታየ የጌታሺን ትዕዛዝ
አስቀድሚ ተፈለጊና ውድ ትሆኛለሺ!!!!


https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
ባንተ_ብቻ_አይደለም

"መኖር ድክም ብሎኛል ፣ ተስፍ ልቆርጥ ነው የምትሉ በሙሉ ኑና ይሄን ግጥሜን ልጋብዛችሁ" 👇

አንዳንዴ ስትኖር .....
  እንዳሰብከው ሳይሆን ፣
        አንተ እንደጠበከው 
ፍፁም ተቃራኒ  ፣
            ሁኖ ነው ሚገኜው
ጎንህ ላለው በርቶ ፣
                አንተ ጋር ጨልሟል
ሌተቀን እየጣርክ ፣
                ትርፍህ ድካም ሁኗል

ያቀድከው  ያለምከው፣
                 አልሳካ  ብሎህ
መጣ ያልከው ቀርቶ፣ 
             ደግ ያልከው ከፍቶብህ
የኔ ያልከው  ወዳጅ  ፣
            የሩቅ ሰው ሁኖብህ

  ውስጥህ  ብቸኝነት ፣
                ተሞልቶ ባዶነት 
  ድንግርግር  ብሎህ  ፣
                 ትርጉሙ የሂዎት  
በቃ ሁሉም ነገር  ፣ ስልችት ብሎሀል
          በዚህ የተነሳ
ከተስፋ መቁረጥ ፣ ስር ካፍፉ ቁመሀል
,
,
ልብ በል ወዳጄ   " መኖር ይቀጥላል"
እስኪ ልጠይቅህ ....?

የሂዎትን ጉዞ   የመኖርን  መንገድ
ማን ቀጥብሎ ሄደ ማን ሳይወላገድ ?

ማንስ ነው የኖረው ሁሌም እንደሳቀ
ለአፋታም ሳይከፋው ሰርክ እንደቦረቀ ?

ማንስ ይሆን ከቶ
          በእንባ ምንጭ ያራሰ
ሀዘን ሳይዳስሰው ብሶት ሳይጎበኜው
በ አልጋ ባልጋ ድሎት ዛሬን የደረሰ ?

      ማ•••••••••ን•••••••••ም
           እየህ  አይደል ጓዴ
          ይብዛም ይነስ እንጂ
                       •
                       •
በመኖር እንቅፋት ሁሉም ተደናቅፏል?
የግዜን አቀበት በማቃሰተ አልፏል ?
የተፃፈለትን የእጣ_ፈንታ ድርሻ ?
የማሩን የሬቱን የ'ሰው' ነት ቅምሻ ?
            መልል ጣፋጩን
           ውጧል የድርሻውን
እ    ና   ም  •••••••   እ   ል   ሀ   ለ   ው
አሁንህ ቢጨልም ባይሆን እንዳሰብከው
             አይዞህ ቀና በል  💪
        ባንተ ብቻ አይደለም
እስኪነጋ ድረስ በትእግስት እለፈው
•
•
ቢለያይ ነው እንጂ ስፋቱ ጥበቱ
ሽንቁር አልባ ኗሪ የለም በምድሪቱ።




ግልባጭ :- ለእህቴም ነው አድርሱልኝ

▬▬▬▬๑۩🌹۩๑▬▬▬▬▬

ለአስተያየት @Arehimu

https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
አንቺ ዱንያ
እስኪ ልጠይቅሽ ምንድ ነው አላማሽ
እኔ አየኻደምኩሽ ምንም ላይጎልብሽ
ሁሉን አካላቴን መሰዋት አርጌ እያዘባነንኩሽ
በነጋ በመሸ እንደ ባሪያ ሁኔ እያገለገልኩሽ
ቁርአንን ትቸ ሶላት አንጓድጀ ብዙ ለፍቸልሽ
ችላ ብለሽኛል የጎድን እያየሽ!
እኔም አልወኩት ምን እንዳስቀየምኩሽ
ዱንያ
ሶላትም ስሰግድ ትወሰውሻለሽ
ቁርአን ስቀራ ግርጥ ትያለሽ
ለሊትም ስተኛ ትቀሰቅሻለሽ
አላህን ስጣራ ትከለክሊያለሽ
እንቅልፌ ሲመጣ ሃሳብ ታመጫለሽ
ጨክኜ ስተኛ ትዝ ትይኛለሽ በህልሜ እየመጣሽ
ምን ያልሆንኩት አለ ቀኑ ነግቶ እስኪመሽ
ዱንያ
ታዋጫለሽ ብየ ብዙ ለፋውልሽ
ዛሬ ግን ደከመኝ ይሄው ወደኩልሽ
ልብሽን ቆልፈሽ በጥርስሽ እየሳቅሽ
ምንም ቦታ ሳሰጭ ታቾፊብኛለሽ
አላሰብሽልኝም አንቺ ግን  ጨካኝ ነሽ
አወ አንቺ ግን ጨካኝ ነሽ ያውም አረመኔ
ራህመት የሌለሽ የማትይ ወገኔ
ወላሂ በቅቶኛል ከንግድህ በኋላ ጓደኛ መሆኔ
ዱንያ

ከህፃን ጀምሮ እስካሁኔ ድረስ ብዙ ለፋውልሽ
አንድ ቀን ስደሰት እንድ ቀን ስከፋ ይሄው አለውልሽ
የሃሳብ እንጀራ ለብዙ አመታት አየበላውልሽ
በአላህ ንገሪኝ የት አለ ውለታሽ
አንድት ነገር ብቻ እስኪ ልጠይቅሽ
መቸ ነው በአላህ የምገላገልሽ
ከልብ ቋጠሮ አውጥቸ የምጥልሽ
ጌታችን ሃያሉ ፈጥሮሽ ለፈተና
አንደው አስቀረሽው ስንቱን ጎበዝ ጀግና
አንቺ እርጉም ቆሻሻ ውለታ የሌለሽ
በይ ቶሎ ተፋችኝ ልቦናየ ሁላ ጨርሶ ሰይቆሽሽ
አሃ
አሁን ግን ስረዳ ለካ አንቺ ጠፊ ነሽ
የዚህ ኢልሙ ጠፍቶኝ ብዙ አመት ስፈትሽ
ሀድስን አንብቤ አሁን ተረዳሁሽ
ሲገባኝማ እኮ አሁን ሳስተውልሽ
ሁሉም ለካ ሟች ነው የረጋው በላይትሽ
ሃያሉ አላህ ሲቀር ያ የፈጠረሽ
ዱንያ
ከንግድች በኃላ በጣም ቀንሻለው ከንቺ ጓደኝነት
መያዝ ጀምሪያለሁ የኢማን ዘለበት
በኋላ እንዳልገባ ቁጭትና ፀፀት
ኻቲማየ እንድያምር እንድገባ ጀነት
አላህ እንዳረገኝ የረሱል ጎረቤት
ጀነተ ነዒም ላይ እንቀናኝ ድሎት
አረህማኑ አንድለኝ በል ዘውትር በጀነት
ለዚህ የሚያበቃ ምንም ስራ የለኝ
ይልቁንስ ብቻ ውደታህ አለብኝ
እባክህ ጌታየ ይህ አይነቱ ኑሮ አልሰጠኝም ምቾት
አላህ ያርህማኑ ወስደኝ በጀነት
ከወዳጆችህ ጋር ዝንታለም ልደሰት
ፊርዶስ ከተማ ላይ አኑረኝ ሰገነት(2)።
ዱንያ
አጥፍብሽ ነበር በቀንም በለሊት
ፈርቸ ነው አንጅ አንባቢን ማሰልቸት።

በወንድማችሁ አቡ አይመን ሙሀመድ አሊ
ሶፈር/29/1444 ዓ—ሂ


https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
የኒቃብ አድናቂም ደጋፊም ነኝ..!!

      ........አንቺ ማለት እኮ……
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በጣት ጥፍሮችሽ ላይ ላስቲክ አስገጥመሽ፣
አርቲፊሻል የሆንሽ ዘመንሽን ቀድመሽ፡
በራስሽ ላይ ደግሞ የዊግ ቆብ አጥልቀሽ፡
ሰውነት የቸከሽ ሴት መሆንን ፍቀሽ፡
ከንፁህ እሳቤ በጣሙን እርቀሽ፡
ፆታሽን ቀይረሽ ወንድ መሆን ናፍቀሽ፡
በሰው ሰራሽ ነገር የምትመሰጪ፡
ለትዳር ለሀላል የማትቀመጪ፡
አሻንጉሊት የሆንሽ ከሰው ተራ ወጥተሽ፡
የተፈጥሮን ፀጋ አራክሰሽው ትተሽ፡
የሚገርመው ነገር እንደዚህ ነሽ አሉ፡
አብረውሽ ያደጉት ነገሩኝ በሙሉ፡
ሴት እንደዚህ ሲሆን በጣሙን ያስጠላል፡
በአንድ ፊቱ ከአንችስ ህፃናት ይሻላል፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ዱርዬ ልበ-ቢስ ይሉሻል አንዳንዴ፡
ሴትነትን ጥለሽ የምትሆኝ ወንበዴ፡
ኸረ ብዙ ሰማሁ እውነት ይሆን እንዴ!!
የፈጣሪን ጥበብ አንች ቀይረሽው፡
ጌታሽ የሰጠሽን ማንነት ፍቀሽው፡
የአለሙን ዳኛ አሏህን ደፍረሽው፡
ዛሬ ከእቃ በታች ረክሰሽ አረፍሽው፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▸የኔ ጀግና ደግሞ.....!!
ፋሽን ተከታይዋ ቆማ ተገትራ፡
ሙስሊሟ ቆንጆ ግን አምራ ተሰትራ፡
በኒቃብ አጊጣ ስራዋን ስትሰራ፡
ያች ሱሪ ለባሽ ገባች አሰንሰራ፡
ኒቃቢስት እህቴን ለማራከስ ደፈርሽ፡
ድንኳን ለባሽ ብለሽ ለመሳለቅ ሞከርሽ፡
በሸይጧን እሳቤሽ ቅናት ይዞሽ ሰከርሽ፡
ስሜቷን ትከተል በማለትም መከርሽ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▸ውድ ነሽ አይዞሽ...!!
ኒቃቢስቷ አንች ግን ቀጥ በይ በአቋምሽ፡
የማንም ዘለፋ ፈፅሞ እንዳያምሽ፡
ሁሌም ከአሏህ ዘንድ ከፍ ያለ ነው ስምሽ፡
እንደ ዘመኑ ሴት ቻፕስቲክ ያላየሽ፡
ከመጥፎ ጓደኛ ቀድመሽ የተለየሽ፡
ዘር ጎሳና ብሔር መልክ ሳትቆጥሪ፡
የሰጠሽ ተፈጥሮን ለማርከስ ሳ'ጥሪ፡
ዘመናይ ነኝ ምትል ኋላ ቀሯን ቀድመሽ፡
በኒቃብ ተውበሽ ሁሉን አስደምመሽ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ከልብ የምትገቢ ነሽ የአይን አበባ፡
ወንድን የሚረብሽ የለሽም ወለባ፡
ምርት በአንች ታይቷል ሌላው ነው ገለባ፡
ከአሏህ ቃል ውጭ ያላቆመሽ ታኮ፡
ከነቢ ትዕዛዝ ውጭ ንግግርሽ ሾልኮ፡
ከውጭ ያልተሰማ ድምፅሽ አፈትልኮ፡
የሴቶች ልዩ ነሽ አንች ማለትኮ....!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ የሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም አህለል ኸይር ጀመአዎች በሙሉ
ዛሬ አንድ ነገር ልናስታውሳችሁ ነው

ወንድማችን ሪድዋን ዛሬ እያስጨነቀ ያለው የየቲሞች እና ሚስክኖች ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ ሁላችንም ሊያስጨንቅ የምገባ ጉዳይ ነው

ወንድማችን ሪድዋን ባለፈው በተፈጠረው የመስጂዳችን ፈረሳ ጉዳይ መረጃ አሰልፈህ ሰተሀል በማለት አስሮ ክፉኛ ጎድቶታል
አሁንም በህክምና ላይ ያለ ስሆን ነገር ግን ከላይ የሱን ንግግር እንደሰማችሁት እሱን እያስጨነቀ ያለው በለፉት ጊዜያት በአላህ ፊቃድ እና እገዛ ከጎናቸው ሆኖ አብሽሩ ስላቸው የነበሩትን የየቲሞችና የሚስኪኖች ጉዳይ ነው።

ይህ ነገር ደግሞ ሰምተን መለፍ ስለለብን ኢንሻአላህ እኛም በቀሩት ዙልሂጃ ቀናቶች በመነየት በማስነየት በአስቤዛ በሀሳብ በዱዓ ከጎናቸው ልንቆም ይገባልና
ሀገር ውስጥ ከሀገር ውጪም ያላችሁ እህት ወንድሞች ሁላችንም ያቅማችን ልንረባረብ እና አብሽሩ ልንላቸው ይገባል ።
ኢንሻአላህ በቀሩት ዙልሂጃ ቀናቶች በሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም የኒያና ፕሮግሞች ይኖረናል

📓📖📚📚📚🌴🌴🌴🌴

www.tgoop.com/ewketnfelig
www.tgoop.com/ewketnfelig

የሶደቃ ትንሽነት የለውምና ሁላችንም በውንድማችን ሪድዋን የምንነይት ይሆናል።

ንግድ ባንክ
1000375043298
ሪድዋን መሀመድ አህመድ

ሀሳብ አስተያየት
@Sohebiyat

ወንድማችን ሪድዋን ለማታቁት
ይሰራቸው ከነበሩት ስራዎች ውስጥ
👇

https/www.tgoop.com/ALHIDIYAWOCH

ወንድሜ አላህ ሙሉ አፊያህን ይመልስልህ ረጅም እድሜም ከአፊያ ጋር ይስጥህ ኢንሻአላህ ከዚህም ቡኋላ ቡዙ ኸይር ስራዎች የምትሰራ ለሌሎችም ተምሳሌትና እና አስተማሪ የምትሆን አላህ ያድርግህ።
ይህም ያልፋል

አንድ ባይሆን የሕይወት ውሏ
        ..........ስቃይ ደስታ መባባሏ
በአይን እንባ ፊት ቢታጠብ
       አካል ዝሎ ውድቀት ቢያብብ
ግዴለም ይህ ቀን ያልፋል
................የታመመም ይፈወሳል
ይሄን ሲሉት ያኛው ቢያመልጥ
          ቀን ባይሞላ ችግር ቢሰጥ
ይህ ከሆነ የሕይወት ክሱ
ትዕግስት ነው ለዚህ መልሱ
.........ዝም ማለት መታገሱ.........
ውስጥ ያጣውን ሳቅ ያገኛል
         .......ልብ ያሻውን ይገናኛል
አንድ ባይሆን የሕይወት ውሏ
       ..........ስቃይ ደስታ መባባሏ
ቀን ይጥላል ቀን ያነሳል
       ግን ግዴለም ይህም ያልፋል፡፡

ታገስ/ሺ  !!!

https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ

ተማሪ አብደላህ ኡመር እባላለሁ የ12 ክፍል Natural ተማሪ ነኝ አሁን ወደ ፈተና እየገባሁኝ ነው እዛ ለ6 ቀን ያህል እቆያለሁ ይሄንን ፅሁፍ የምታዩ ወንድም እህቶቼ አንብባችሁ ዝም ብቻ አትበሉ እስከምመለስ ድረስ ሁሌም በየቀኑ በዱአችሁ አስታውሱኝ ይሄንን ፈተና አላህ ውጤቱን እንዲያመጣልኝ እንዲያሳልፈኝ ለአላህ ስትሉ ከልብ ከልባችሁ ዱአ አድርጉልኝ ?!

አይታወቅም ምናልባች ከእናንተ አንድኛችሁ ዱአችሁ ሙስተጃብ ሊሆን ይችላል ።


ጀዛኩሙላህ ኸይር
🔔🔔 አዋጅ አዋጅ አዋጅ 🔔🔔


እናንተ ሙስሊሞች ፣ አማኞች ሆይ ለአላህ ብላችሁ አዳምጡኝ ስሙ ፣ የተኛች ተነሱ ፣ የፈዘዛችሁትም ንቁ በጣም በጣጣጣም ትልቅ ሌባ መጥቷል

ለአላህ ብላችሁ ሁሉንም አንብቡት ጀምራችሁ እንዳታቋርጡት


➡️ ይህ ትልቅ ሌባ ማን ነው ❓❓❓

#መልስ፦

➡️ ሌባው ጊዜን የሚሰርቅ ሌባ ነው


➡️ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለውናል፦ ‛‛ከሌባ ሁሉ መጥፍ ሌባ ብሎ ማለት ጊዜህን የሚሰርቅብህ ነው''።


➡️ እነዝህ የጊዜ ሌቦች እነማን እነማን ናቸው ❓❓❓

لصوص ساعة


የጌዜ ሌቦች የሚባሉት ፦

1️⃣ ቴሌግራም

2️⃣ ዩቲዩብ

3️⃣ ፌስቡክ

4️⃣ ቲክቶክ

5️⃣ ቲውተር

6️⃣ ኢኒስታግራም

7️⃣ ዋትሳብ

8️⃣ ኢሞ

9️⃣ ቴሌቪዥን (TV)

🔟 መጥፎ ጓደኛ

1️⃣1️⃣ ጫት

1️⃣2️⃣ ብዙ መተኛት etc

የመሳሰሉት የሰውን ልጅ ጊዜ ሊያጠፋ ሆ ብለው የተዘጋጁ ሌቦች ናቸው።


➡️ ነገር ግን በአግባቡ በጥሩ በሀላል መንገድ የማንጠቀምባቸው ከሆነ ነው ። ጥቅም የላቸውም ማለት አይደለም በጥሩ ፣ በሀላል መንገድ ጊዜን ሳናሰርቅ ሳናባክን ብዙ ሰአት ሳንቆይ የምንጠቀም ከሆነ ብዙ ፋኢዳ እናገኛለን ነገር ግን በእነዝህ ኢሽቲጋል (ቢዚ) ይምንሆን ከሆነ ጊዜአችንን እያሰረቅን ነው


➡️ እነዝህን ከላይ የተጠቀሱት አብዘሀኞቻችን በአግባቡ ፣ በጥሩ ነገር እየተጠቀምንባቸው ነውን ስንቶቻችን ነን ቴሌግራም ላይ ቀኑ አልበቃን ብሎ ማታ ሌሊቱን ቻት የምንፃፃፈው ስንቶቻችን ነን በአሉባልታ ወሬ ጊዚያችንን የምናሰርቀው ስንቶቻችን ነን ፌስቡክ ላይ የምናፈጠው ሀራም ነገር የምንፖስተው ስንቶቻችን ነን ዩቲዩብ ላይ ፈሳድ ነገር የምንለቀው የምናየው እዛ ላይ በማፍጠጠን ጊዜአችንን የምናሰርቀው በተለይ በተለይ ቲክቶክ የሚባለው ነገር የአላህ ትልቁ አይል ትንሹ እዛ ላይ ቀኑ አልበቃ ብል ሌሊቱን በማፍጠጥ ጊዜአችን የሚሰረቀው ስንቶቻችን ነን ቴሌቪዥን (TV) ላይ ቀኑ አልበቃ ብሎ ሌሊቱን ፊልም ፣ ሙዚቃ ፣ ሙሰልሰላ ድራማዎች በማፍጠጥ ጊዜአችንን የምናሰርቀው ስንቶቻችን ነን መጥፎ ጎደኛ ይዘን በየጫት ቤቱ ፣ በየቡና ቤቱ ፣ በየሰፈሩ ዝምብለው ቁጭ ብለው ዲጋ የሚያሞቁ ወደ አልባሌ ነገሮች እየወሰዱን ጊዜዎቻችንን የሚሰርቁን ስንቶቻችን ነን ጫት እየቃምን ሶላት ሰአት የምናሳልፈው አሁንማ ጭራሽ የ200 ብር የ300 ብር ጫት ካልተቃመ ቂምሀ አይባልም ተባለ ሱብሀንአላህ አንዷን ቅጠል እንኳን ማን ፈቀደልህ ሀራም አይደለምን ጫት በመቃም ሶላት እያሳለፍን ጊዛአችንን የምናሰርቀው። እና ከዝህ የበለጠ ጊዜን የሚሰርቅ የሚያጭድ መጥፎ ሌባ አለን❓

➡️ ነገ የውመል ቂያማ ከ 4 ጥያቄዎች መካከል አንዱ ‛‛ ወጣትነትህን ፣ ጊዜህን በምን አሳለፍከው ተብለን እንጠየቃለን'' ያኔ ነገ አማመላህ ፊት ስንቆም ምንድን ነው መልሳችን ቲክቶክ ፣ ፌስቡክ ፣ ቴሌግራም ፣ ዩቲዩብ እየጎረጎሮኩ ነው ወጣትነቴን ፣ ጌዜዬን ያሳለፍኩት ፣ ጊዜዬን ያሰረኩት ብለን ነው መልስ የምንሰጠው አላህን እንፍራ ነገ አላህ ፊት ቁመን ከሚተሳሰበን በፊት አስቀድመን አሁኑኑ ነፍሳችንን እንተሳሰባት።

➡️ አላላላህ እንፍራ በህይወታችን አንቀልድ ጊዜአችንን በአሉባልታ ፣ በከንቱ ነገሮች አናሰርቅ ፣ አናሳልፍ።።


➡️ ‛‛ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ነው’'

ይህ የቁርአን አንቀፅ 👆👆👆 አብዘሀኞቻችን ሞትን የምንረዳው በቃ የመጨረሻ አዱንያን ልትለቅ ስትትል እሩሀችን ልትወጣ ገርገራ ስትደርስ ሞትን መቅመስ ማለት ያኔ ብቻ አይደለም በኒአደም ሁሉ በየደቂቃው ፣ በየሰከንዱ ፣ በየማይክሮ ሰከንዱ ሞትን እየቀመስን ነው ያለነው ማለት አንድ ደቂቃ ባሳለፍን ቁጥር አጀላችን (እድሜአችን) እያበቃ እያበቃ ወደ ዋናው ሞት እየቀረብን ሞትን እየቀመስን እንሄዳለን። ሞትን በየደቂቃው እየቀመስን ነው ያለነው ።

➡️ ሀታ እንኳን አሁን እኔ ይሄን በምፅፍላችሁ ጊዜ ሞትን እየቀመስኩ ነው ምክንያቱም ይሄንን በምፅፍበት ጊዜ ደቂቃዎች እየቆጠሩብኝ ነው ከእድሜዬ ላይ ዝቅ እያለ እየቀነሰ ነው የሚሄደው

➡️ እናንተም እንደዛው ይሄንን በምታነቡ ጊዜ ሞትን እየቀመሳችሁ ነው ምክንያቱም በምታነብበት ጊዜ ደቂቃዎች እየቆጠሩ ነው እድሜአቹሁ ዝቅ እያለ እየቀነሰ ነው ወደ ሞት እየተቃረባችሁ ነው ። ሞትን መቅመስ ማለት ሩህ ገርገራ ላይ ስትደርስ ብቻ አይደለም

➡️ ጊዜአችንን ሰው ሰራሽ በሆኑ በሀራም ነገሮች አናሰርቅ አላህን እንፍራ።

➡️ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከሌባ ሁሉ መጥፍ ሌባ ማለት ጊዜን የሚሰርቅ ነው ብለውናል ።

➡️ ገንዘብ ፣ ንብረት ቢሰረቅ ቢወድም መልሶ ይገኛል ፣ ልጅ ቢሰረቅ ቢሞት ሌላ ልጅ ይወለዳል ነገር ግን ጊዜ ከተሰረቀ መቼም መቼም አይገኝም

➡️ የጊዜ ሌቦች በእኛው ቁጥጥር ስር ናቸው ነፍስያችንን አሸንፈን ጊዜያችንን እንዳንሰረቅ ፣ እንዳንዘረፍ ማድረግ እንችላለን ነገር ግን ከተሰረቅን ፣ ከተዘረፍን ቡሀላ ያንን ጊዜ ደግመን መመለስ አንችልም ።።

➡️ የገንዘብ ፣ የንብረት ሌባን ከሞላ ጎደል መመለስ ፣ መቆጣጠር አንችልም ነገር ግን ገንዘባችንን ፣ ንብረታችንን መመለስ እንችላለን በአላህ ፍቃድ

➡️ የጊዜን ሌባ አስቀድሞ መቆጣጠር እንጂ መመለስ አይቻልም ጊዜ ከተሰረቀ ተሰረቀ ነው ካመለጠ አመለጠ ነው መቼም ፣ በፍፁም መመለስ አይቻልም ነገር ግን የገንዝን ፣ የንብረተን ሌባ መመለስ ይቻላል ገንዘብን ፣ ንብረትን መልሶ ማግኘት ይቻላል ።።።

➡️ ወላሂ ብዙ ቢወራ ፣ ወደ ውስጥ ቢጎረጎሮ አያልቅም ፅሁፍ አበዛሁባችሁ መሰለን አፍወን

➡️ ለአላህ ብላችሁ ይህንን መልእክት ለጓደኞቻችሂ በተለይ ለወጣቱ Sher አድርጉት


➡️ if you like it sher it



✍️✍️✍️ @Ebnu_Oumer




@rezakuhakimu

@rezakuhakimu

@rezakuhakimu
❝ጥርዝ አትበላት❞
⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘


ያልፍልኛል ብላ ስዴት በተጓዘች፣
ቤተሰብ ለማቅናታ ደክማ ባስደሰተች፣
ለ24ሰአት በቁሟ በሰራች፣
ሂወት ለመቀየር ለፍታ በደከመች፣
የሰዉ ሀገር እሳት እየተገረፈች፣

ድካምና ናፍቆት እያፈራረቀች፣
ዛሬ ሞላ ነገ በስስት እያየች፣
ሰዴት በቃኝ በላ ሀገሬን እያለች፣
በድኗ ጠንክራ ኒቃብ በለበሰች፣
አልቀርብም ይቅርበኝ አላህን ፍሪ ነኝ
የወጣሁት ስዴት በደንብ ለወጠኝ፣

መጥፎና ጥሩዉን እደለይ አረገኝ፣
ደኔን መገንዘቤ ክብሬን መጠበቄ፣
ተዉሂድን ተመሬ ሱናን በማወቄ፣
መጥፎና ጥሩዉን ለይቸ ማወቄ፣

አልሃምዱሊላሂ ስደትን ወደድኩኝ፣
ከትናንቱ ዛሬ ለዉጥን አገኘሁኝ፣
እኔን ባለማወቅ ጥርዝ አትበለኝ፣
ስድብ መስሎህ እንደሁ እኔ ለዉጥ ላይ ነኝ፣

ለስራ ለለዉጡ ስዴት የተጎዝኩኝ
ቂርዓት ቀርቸ ድኔን የተማርኩኝ
ለቤተሰብ ደስታ ቁሜ የታጠቁኝ
ለመልካም ነገሮች ቀደሜ የሆንኩኝ
የስዴት እንቁ ነኝ ከመጥፎ የራኩኝ
በአሏህ እገዛ ትልቅ ህልም ያቀድኩኝ

የሰዉ ሀገር ኑሮ እጅግ የመረረኝ
ሀገሬ ለመግባት እቅድ  ያወጣሁኝ
ብለፋ ብደክም ምኞቴን የኖርኩኝ
ስዴት በቃኝ ብየ ሀገሬ ቢያመጣኝ
ከሜዳ ተነስተህ ጥርዝ አትበለኝ


✍𝑆𝒆𝒍𝒂𝒉𝒖𝒅𝒊𝒏 ᵃᵇᵘ ᵒᵘᵇᵉⁱᵈᵃ

𝐓𝐞 ~ www.tgoop.com/selahudin_Islamic_knowlages
2024/10/03 23:33:47
Back to Top
HTML Embed Code: