Telegram Web
ZZ #ለእኔ_ብቻ 😍😍

ይኸውልሽ ፍቅሬ.....
መልዕክቴን አድምጪ
ለወደደሽ ሁሉ ልብሽን አትስጪ
በእንቡጥ ከናፍርሽ ሌላ አትሳሚበት
እኒን ብቻ ስመሽ......❤️
ፍቅርሽን ቀምሼ በደስታ ልርካበት

በጨረቃ አይኖችሽ እኔን ብቻ እይኝ
አንድዬ በለገሰሽ....
ጣፋጭ አንደበትሽ እኔን ብቻ አዋሪኝ
ከሚያወራው ሁሉ እኔን ብቻ ስሚኝ
ለኔ ብቻ ኖረሽ እኔን ብቻ አፍቅሪኝ


ይህን ሁሉ ስልሽ.....
ራስ ወዳዱ ሰው ብለሽ እንዳጠሪኝ ከክፋት መፃህፍት ስሜን እንዳፅፊኝ


እውነቱን ስነግርሽ...
ለኔና ለግሌ ብቻ ያደረኩሽ
በማይነትበው ልቤ ዝንታለም ያኖርኩሽ
ብወድሽ መሠለኝ ባፈቅርሽ አለሜ
አንችን ለኔ ብቻ የምል ደጋግሜ.።


ግሩም በለጠ

💘· @snthufdire ·💘
ልቧ ችሎበታል _ የናቀውን መናቅ
የተወውን መተው _ የራቀውን መራቅ
መውደዷ ያልታየው  _ ያነሰበት ፍቅሯ
ዛሬው ጥርግ ይበል _ አትለማመጥም
             ዋጋዋ ገብቷታል
ግድ ቆዩ ብላ    _ ክብሯን አትጥልም

@snthufdire
#አንቃን_በጥበብህ 🙏
   መውደድ ስንችል ጠልተን ፣
    መሆን   ሳለም   መስለን ፣
አስታርቁ ስንባል ለማኳረፍ ቋምጠን፣
ከቦታችን ወርደን ሰው ከመሆን ጎለን ፣
ከሙገሳ ይልቅ ቀሎን መወቃቀስ ፣
በእልህ ተቃርኖ አብሮነት ስናፈርስ፣
በሳቃችን   ጀርባ   ቅናት   ተለጥፎ ፣
ባንደኛው መደሰት ሌላኛው አኩርፎ፣
ደርሰን ተከፋፍለን ፀንተን በልዩነት፣
ድንበር   እያበጀን  ርቀን  ከእምነት ፣
የውሼት እንደኖርን እንዲሁ እንዳንሞት
አንቃን በጥበብህ ሰው አርገን የእውነት
@snthufdire
ጥቁር ሰው አፍቅሮ መለየት መከራ ነው...

ቤት ገብተህ ከሰል ባየክ ቁጥር ሆድ ይብስካል
😁😂

የደረሰበት ያቀዋል
@snthufdire
-ከተወዳጀኋት በርካታ ቀን ሆነን ። ስራ ነው ያገናኘን ። መልከ-መልካምነቷ ቢስብም ፤ የግንባሯ መቋጠር አያቀርብም ።ቁጥብ ያለች  elegant ነች።

አንድ ቀን መንገድ እየሄድን አንድ ጎረምሳ የአንዲትን ልጅ ቂጥ ቸብ አደረጋት ፤ ልጅቷ ተናደደች ፤ ልጁ ደግሞ አሽካካ ። በሰጨኝ ሰደብኩት  ሰደበኝ ፤ ተገለገልን ፤ ቤተሳይዳ ደነገጠች ፤ ለማረጋጋት ሞከረች ፤ ተናደድኩ እንዴት እንደዚህ ይሆናል ።

ሰው ክቡር ነው።  ሊያውም ያልደረሰብሽ ፤ ሊያውም የማታውቂው ፤ ሊያውም  ሴት ልጅ
አልኩ ። 

ንዴቴ ሲተን በግርምት ዝም ብላ ስታየኝ ፤ አየኋት  ። በሌላ ቀን ስንገናኝ ከበፊቱ ትንሽ ቀረበችኝ ። 

ደሞ በሌላ ቀን ፤ ከፊታችን የሚመጡ የተጎሳቆሉ  እናትን ከኋላ ቀረት ብዬ ብር ሰጠኋቸው 

ምርቃቴን ፣ በረከቴን ወስጄ ስመለስ ፤ ምን አድርገህላቸው ነው አንዲህ ተጎንብሰው
እጅ የሚነሱህ አለችኝ ።ምንም ብዬ አድበሰበስኩት ።

ፍጥጥ ፤ ፈርጠም ፤ ደረቅ ብላ ጠየቀችኝ ። መለመን  አልጀመሩም እንጂ ኑሮ ከብዷቸዋል ፤ ቡና መግዣ ሳንቲም ነገር ሰጠኋቸው  ይኸው ነው አልኳት ።

ሳይለምኑህ አለችኝ ?

አይናችንን ስንከፍት ፤ ከቃል በላይ ገፅታ ሁሉንም ይናገራል አልኳት ። ቃል አልተናገረችም ። 

በሌላ ቀን  ስንገናኝ ።
እጮኛ አለሽ አልኳት?? የለኝም ወንድ አላምንም አለችኝ !

በእርጋታ ለምን አልኳት ?

እ ዝም  አለች

ዝም ብዬ ሳያት ቀጠለች

አባቴ ሃይለኛ ነው ። እናቴ ስታናደው በር ዘግቶ በቀበቶ ነበር የሚገርፋት ። እንፈራዋለን ። ይጮህብናል ። ዝም የሚል ነበር ፤ ሲስቅ እንኳን አይቼው አላውቅም  ። እናቴ በጣም ታሳዝነኝ ነበር  ። እኔን እንኳን እንደሚወደኝ ለማሳየት ቃል ሳያወጣ ፀጉሬን ነበር የሚያሻሸው ፤ በቃ እቺ የፍቅሩ ማሳያ አፅናፍ ነበረች። 

ከቁጣ በስተቀር ገርፎኝ አያውቅም ግን እናቴ ሳበሳጫት ለአባትሽ ነው የምነገርው ስትለኝ ፤ ሽንቴ እንሲኪያመልጠኝ ነበር የምደነግጠው ፤ ብርገጋዬን ስለምታውቅ በቀላሉ በአባቴ አታስፈራራኝም ።

አንድ ቀን ለስራ ክፍለ-ሀገር በሄደ በአራተኛ ቀን መኪና ተገልብጦ የአባቴ በድን በሳጥን ተጀቡኖ መጣ ።  ሃዘን ሆነ ። እናቴ በጣም ስታዝን ገረመኝ ፤ ይመታት ፤ ይቆጣት ፤ ትፈራው አልነበር እንዴ ለምንድን ነው እንዲህ የምታዝነው አልኩ ።

ጊዜ ሄደ ። እናቴ ኑሮ በጣም ከበዳት ።  አበራ የሚባል ፤ ሴት ወሲብ ብቻ የምትመስለው ሸፋዳ አገባች ።

ኑሮ ቀለል አለን ፤ አበራ ቸር ነው ገንዘብ አይሰስትም ።ነገር ግን  ባዳው መሆኔን እይታው ይነግረኛል ። እናቴ ከሌለች ይጎነትለኛል ፤ ይተሻሸኛል ፤ ወደ ራሱ ይስበኛል

እናቴ ተሳቀቀች ። እኔም ቤታችን እናቴ ከሌለች
ያለመደኝ ተናካሽ ውሻ ያለበት ግቢ ነው የሚመስለኝ ። ከአቅሜ በላይ ሲሆን ፤ የጭቅጭቃቸው ምክንያት ስሆን ፤ ትምህርቴን አቋርጬ ፤ መስተንግዶ ገባሁ ፤ ጥንጥ ቤትም ብቻዬን ተከራየሁ ።

ለካ ሁሉም አበራ ነው። ትንሽ ያወራኸው ፤ ፈገግ ያልክለት ወንድ ሁላ እራት ልጋብዝሽ ፤ ሌላ ቦታ እንገናኝ ፤ እንቀምቅም ፤ ልሳምሽ ፤ እንዋሰብ እንመቻች ፤ ወሬያቸው ቢቋጭ ፣ ቢገመድ ፣ ቢሰፋ ከዚህ አይዘልም ።

የወንዶች መስገብገብ ነው ወሲብን ወንድ ብቻውን የተለየ ደስታ የሚያገኝበት ያስመሰለው።  ፍትወታችንን ያፈዘዘልን መንቀዥቀዣቹ ነው ።

ከከስተመሮቼ  ቃለዓብ ደስ ይላል ። ረጋ ያለ ። ትንሽ ፈገግታ ፤ ከትንሽ ቲፕ ጋ የሚሰጥ ነው።  በጣም ከብዙ ጊዜ በኋላ ተግባባን ።መደዋወል  መገናኘት አበዛን ። በአባቴ ፍርሃት እና በአበራ ሴሰኝነት ፤በከስተመሮቼ ሴት አውልነት ተፅዕኖ   የተበጃጀሁት ቤተሳይዳ በቃለዓብ ምክንያት አንድ አንድ ወንድ አለ ማለት ጀመርኩ ።

ትንሿ ቤቴ ይመጣል ። ተስፋ ፤ ገንዘብ ፤ክብር ፍቅር ፤ ትርጉም ሰጠኝ።

ወደድኩት ።ያቺ የወንድ ገላ የሚሸክካት ቤተሳይዳ

ገላዬ ከገላው ሲነካካ ፤ ሰውነቴ ይለዋወጣል ይቅበዘበዛል ፤  ይከፋፈታል ። እቅፍቅፍ አደርገዋለሁ ፤ ጉያው ውስጥ እገባለሁ ፤ አንገቴን ሲስመኝ ደስታ መላ አካሌ ላይ ሲርመሰመስ ይሰማኛል። ስንራከብ እና ውስጤ ሲጨርስ ሃሴት ሲያጥለቀልቀኝ ከፀጉሬ  እስከ ጥፍሬ እርካታ ይመዘምዘኛል ።

ቃለአብን ወደድኩት ። እንደዚህ ከሆን አምስት  ወር ከሰባት ቀን በኋላ ።
ቃለአብ ድንገት ጠፋብኝ ፤ ፈለኩት የለም።
በህልሜ አየሁት ፤ ቃዠው ለፈለፍኩ ፤ በአይነ ስጋ ዳግም  ማግኘት ግን አልተቻለኝም ።

እጦት ፤ ናፍቆት ፤ ፍቅር ፤ ስጋት ተባብረው ከደቆሱኝ ከትንሽ እለት በኋላ አንድ ጓደኛው ሚስቱ እና ልጁ ጋ አሜሪካ  መሄዱን በማያጠራጥር መልኩ  ነገረኝ ።

ማርያም  ደጅ  ሄድኩኝ እና ለምን አልኳት ፤ እንዴት አንቺ እያለሽልኝ ከክፉ ነገር አልጋረድሺኝም ። እንዴት አላጋለጥሺውም ፤ ነገሩ እንደሆነብኝ ቢሆንበት ፤ የዘራውን ቢያጭድ ፤ እሱ ይጎዳል እንጂ እኔ ስብራቴ አይድን!!

ምነው ማርያም?  ምነው?  ምነው ብርሃኔ ? ከስንት አፈ ጮሌ ፤ ከሰንት መደለያ ቁስ አስመልጠሺኝ ፤ ምነው ዛሬ ተውሺኝ ምነው ማርያሜ ?!
እንዴት አንቺ እያለሽ ያመንኩት ፤ ራሴን የሰጠሁት ሲያጠፋኝ ዝም አልሺኝ እያልኩ አነባው ፤ አዘንኩ ተደበትኩ ። አሁን ጠባሳው ልቤ ውስጥ ተሰንዷል"

አለችኝ

-በገጠመኝ ባየሁት ፤ በሆነብኝ ምክንያት ወንድ አላምንም አለችኝ ። ብዙ ባገኘኋት ቁጥር ፤
የልቧን እውነት ባጫወተቺኝ ብዛት ፤ ከአባቷ ፣ ከእንጀራ አባቷ ፣ ከቦይፍሬንዷ በኋላ ፤ ዛሬም ፊት ለፊት የልቧን  የሚሰማትን ልጅ ለማመን ዋዜማ ላይ ነች ። አንዳንድ ወንድ አለ ልትል ነው።

ማስታወሻ፦
ሰው መሆን  እንዲህ ነው


@snthufdire
ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል!

💙ፍቅር የሚታየውና የሚለካው በግጭት ውስጥ ነው።ግጭት በሌለበት ፍቅር አይታይም። የፍቅር ከፍታና ልክ ማሳያው ግጭት ነው። የሚፋቀር ሰው ግጭትን ይታገሳል፣ ታግሶም ያልፋል። ፍቅር ላይ ታች እንደሚል የሚዛን ጨዋታ ነው።

💜በሚዛን ጨዋታ ከታች ወደላይ፣ ከላይ ወደታች፣ እንደገናም ከታች ወደላይ እያለ ጨዋታው ይቀጥላል። በሚዛን ጨዋታ ሚዛኑ አይሰበርም።ትዳርም እንደማይሰበር የሚዛን ጨዋታ ነው።ትዳር ከፍና ዝቅ አለው።

💛በሚዛን ጨዋታ የተቀመጡት ሰዎች አይወድቁም። የተቀመጡት ልጆች ፈሪዎች ከሆኑ ግን ፈርተው ወይም ተገን ፍለጋ ወደ አንድ ጎን አጋድለው ይወድቃሉ።

❤️በትዳር ውስጥ ሆናችሁ አትፍሩ! ሁሌም ጥሩ ሁኑ! ሌላው ወገን ጥሩ ባይሆን እንኳ እናንተ ጥሩ ሁኑ። ፍቅር ማለት ያ ነው፤ ሌላው ወገን ሲከፋባችሁ፣ ሳይመቻችሁ ሲቀር ታግሶ መቆየት ነው። ስንት ዓመት እንታገስ? አይዞኝ አንቸኩል! ውሎ አድሮ ምናልባትም ዓመታት ቆይቶ ነገሩ ይስተካከላል።

💜"ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ስራው" ይላል ታላቁ መጽሓፍ። ታገስ! አትቸኩል። ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ የሀይማኖት መሪ፣ አዋቂ፣ ... ብቻ ማንም ይሁን ማን የሚላችሁን ሰምታችሁ ትዳራችሁን አታፍርሱ፣ ቤተሰብ አትበትኑ። ጽናት እንጂ ፍቺ አያኮራም!ፍቅር ስምምነት አይደለም። ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር ይታገሳል፣ ፍቅር አይታበይም!

❤️ፍቅር የሚገለጸው በግጭት ውስጥ ልዩነትን በመቻል ነው። በእያንዳንዱን ልዩነት በመበሳጨት፣ ልዩነቱን መሸሽ፣ በልዩነቱ ወደ ፍቺ መሮጥ የፍቅርን ፍሬ አያበላም።

💙የፍቅር ፍሬ ሰላም ነው፣ ደስታ ነው፣ ቤተሰብ ነው።ፍቅር በልዩነት ውስጥ፣ በግጭት ውስጥ፣ ነገሮችን ታግሶ በመቻል ውስጥ ያለ የሚከፈል ክፍያ ነው።ልዩነትን መታገስ አቅቶን ፍቅር የለም። በልዩነት ምክንያት እየተሰዳደብን ፍቅር የለም። በልዩነት ምክንያት ወደ ፍቺ እየሮጡ ፍቅር የለም።

💜በፍቅር ውስጥ ስስት አለ። በፍቅር ውስጥ የማጣት ፍርሃት አለ። በፍቅር ውስጥ ናፍቆት አለ። በፍቅር ውስጥ ጉጉት አለ። በፍቅር ውስጥ አድናቆት አለ። በፍቅር ውስጥ ትዕግስት አለ። በፍቅር ውስጥ ተስፋ አለ።በፍቅር ውስጥ ስድብ የለም። በፍቅር ውስጥ ተስፋ መቁረጥ የለም። በፍቅር ውስጥ ሽሽት የለም።

💛ፍቅር ማለት ሁሌ ምቾት፣ ሁሌ ሽርሽር፣ ሁሌ ሳቅ፣ ሁሌ መዝናናት፣ ሁሌ ጥጋብ አይደለም።ፍቅር ትዕግስት፣ ናፍቆት፣ መውደድ፣ መቻል፣ ወድቆ መነሳት እና መስዋዕትነት ነው! ፍቅር እስከ መቃብርን አላነበባችሁም።የፍቅር ጠላት ጥርጣሬ፣ አለመከባበር፣ አለመታመንና አለመተሳሰብ ናቸው።
የፍቅር ዋና ጠላት ግን ይቅርታ ማለት አለመቻል ነው።የፍቅር ጠላት ራስ ወዳድነት ነው።

❤️ፍቅር አንዳንዴ ስቃይ ያለው መውደድ ይሆናል። ቢሆንም ፍቅር ከነስቃዩም ያስደስታል፤ ተስፋም አለው። ፍቅር በምቾትም በስቃይም አብሮ መሆን ነው።

ፍቅር ትርፉ ብዙ ነው፤ ለፍቅር ስትሉ ታገሱ! ፍቅር አትራፊ ነው። ፍቅር የበረከት ምንጭ ነው።
@snthufdire

🙏ማጋራት እንዳይረሳ🙏
"‼️እግር ወደመራህ ሳይሆን ልብህ ወደፈቀደው ሂድ፤
ጭንቅላትህ ያሰበውን ሳይሆን ልብህ ያመነውን አድርግ፤
ከልብህ ለምታደርገው ነገር በህይወትህ አትፀፀትም፡፡"መልካምቀን
#ፍቅር\ያሸንፋል
@snthufdire
❤️የሚወድህ ሰው
ለራሱ ማድረግ
የማይችለውን ነገር
አንተን ስለሚወድህና
ስለምያፈቅርህ ብቻ
ለአንተ ግን ያደርገዋል


@snthufdire
(እኔ ከሞትኩ....)
===============

የእውነት ካሰብክልኝ
የእውነት ከወደድከኝ
ለበጎ ከሆነ እሷን የነፈግከኝ
ይሁን እችላለው
የምኖር ነኝና አንተ እንደፈለግከኝ
ግን እኔም አንዳንዴ ስለማስብልህ
ዘንበል በል አድምጠኝ...
:
ያቺ የለመንኩህ ልጅ
የሻትኳት ለነፍሴ
የልቧ ቅንነት የለምና በምድር ያውም በዚህ ጊዜ
ደሞ አትቀርምና
ለኪዳን ማህሌት ለሰዓታት ቅዳሴ
ከዓለም ተላምዳ ሳትበላሽብህ
በከንቱ ውዳሴ
ታገለግልህ ዘንድ የቅርብ የልብህ ሴት
አድርጋት መነኩሴ !

/// ዳግም(ኪዮርና) ///

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@snthufdire
አንድ ፈረስ ብቻ የነበረው አንድ ገበሬ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን፥ ፈረሱ ለግሞ ከቤቱ ያመልጣል።

ጎረቤቶቹም እቤቱ መጥተው “ፈረስህ መጥፋቱንና ማዘንህን ሰማን። ልናፅናናህ መጥተን ነው።” አሉት።

ገበሬውም “ አላዘንኩም! ለበጎ ነው” አላቸው።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ፈረሱ ከጠፋበት ቦታ ብዙ ወርቅና ማዕድናት፥ አስለምዶ ከጫነው ሰው አምልጦ ገበሬው ጋ ይመለሳል።

ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ መጥተው "እንኳን ደስ አለህ። ፈረስህ ብዙ ወርቅና ብር ይዞልህ በመምጣቱ እንደተደሰትክ ሰምተን መጣን። " አሉት።

እሱም "ብዙም አልተደሰትኩም። ለበጎ ነው!" አላቸው።

ከጥቂት ጊዜም በኋላም ፈረሱ የብቸኛ ወጣት ልጁ እግር በርግጫው ይሰብረዋል።

ጎረቤቶቹም አሁንም መጥተው " የልጅህ እግር መሰበር አይተህ እንዳዘንክ ሰምተን ልናፅናናህ መጣን። " አሉት።

እሱም በመቀጠል እንዲህ አላቸው "ብዙም አላዘንኩም። ለበጎ ነው!"

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ከፍተኛ ጦርነት ተከፍቶ፤ ሁሉም ጤነኛ ወጣት በግዴታ እንዲዘምት አዋጅ ተላለፈ። የጎረቤቶቹም ልጆች ሲዘምቱ፤ የእርሱ ልጅ እግሩ ስለተሰበረ ከዘመቻው ይቀራል።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነቱ አለቀ። ከጦርነቱ የተረፈ አንድም ወጣት አልነበረም። ጎረቤቶቹም ልጆቻቸው መሞታቸው ተነገራቸው።

ገበሬውም ወደ ሰማይ አንጋጦ "የልጄ እግር መሠበር ለበጎ ሆነለት። ተመስገን!" አለ።

ወዳጄ በነገር ሁሉ 'ሁሉም ለበጎ ነው!' በል
😍🙌

@snthufdire
#አዎ_እጨነቃለሁ
          ፧
ታውቂያለሽ? አታውቂም?
እንዲህ ሆኜ አላውቅም፣
የጠፋሽብኝ ቀን እጨነቃለሁ ስል፣
  "ለምን?" ለምን አትበይኝ
ከፍቅርሽ ሌላ የተለየ ጉዳይ ያለብኝ ይመስል፣
        አዎ እጨነቃለሁ፥
        እሳሳልሻለሁ፥
        ባንቺ ፍቅር ምክንያት፥
        ልቤ ሆኗል የእናት፥
        ስጠፊ ለሰከንድ፥
        እሳት ሆኜ ስነድ፥
        ቦታዬ እንድረጋ፥
        አትጥፊ ከኔጋ፥
        ሆዴን አይጭነቀው፥
        ልብሽ እያወቀው፥
        የጠፋሽ እንደሆን፥
        ፍቅሬ ሰውም አልሆን፣
ጠፍተሽ አትቀሪም እንደማትቆዪም
በልቤ አውቃለሁ፣
ፍቅርሽ አስሮኝ የለ ልቤን የእናት አርገሽ
ሁሌ እጨነቃለሁ፣
        ስለማፈቅርሽ ነው።
      

✍️ Safi Abde

@snthufdire
¹
ጨረቃ ስትሞላ ነው የምትጠፋ ፍቅርና ጨረቃ አንድ ናቸው ፥ የሚለው ማን ነበር።
ፍቅራችን ሲሞላ እንዳይጠፋ እሰጋለሁ ፥ ሁልጊዜ አዲስ . . . ሁልጊዜ ለመሙላት የምንጥረው ፥ ጎዶሎ ቢሆን ምኞቴ ነው። ለመሙላት መልፋት ውስጥ ህመም አለ ፥ ደስ የሚል ህመም . . . የፍቅር ህመም። መሙላትን አርቀን . . . ለሙላት እንፋቀር ፥ ቀን ሳንጠብቅ ቀን በቀን እንወለድ . . . ፍቅር እንደ አዲስ መወለድ አልያም እንደ አዲስ መኖር መጀመር አይደለ ( . . . )

²
ያረፈደ ቃል ታውቂያለሽ . . . የሻገተ . . . ቢነገርም ትርጉም የሌለው . . . በጊዜ ምርኮ ልሳን የሆነ ፥ ልክ ዲቃላ ሆሄ እንደበዛበት [ ኋለኳዟጇጯቧ] . . . ለሰው ጆሮ ትርጉም አልባ ተራ ድምፅ ብቻ . . . እንደዛ ነው አንቺም ጆሮ ሲደርስ ፥ ዘግይቻለሁ ለህይወት ቀን እየቆጠርሽ ነው ( . . . ) ለካስ የእውነትም ዘግይቻለሁ ፥ ቃል ጊዜን ሲከተል አቅም ያጣል . . . የቃል ሀይሉ በጊዜ ፥ ከጀርባ ሲታይ ነው።

³
እኛ የአራዊትን አልያም የእርያዎችን ቋንቋ ፥ ድምፅ ብቻ . . . ትርጉም አልባ ፥ ደመ ነፍሳዊ የምንለው ፥ በምን ያህል ዘግይተን . . . አልያም . . . በምን ያህል ቀድመውን ይሆን ?
መቼስ በክብ አለም የቀደመን ማወቅ . . . እቀድማለሁ ማለትም ትዕቢት ነው የሚሆነው ፥ ከኋላ የምታየው ከኋላህ ነው የሚያይህ . . . ይህች አለም እንደዚህ ነች።

Dawit

@snthufdire
...
🌹🌹🌹💝💝
❤️​​ከማፍቀር የሚገኝ ደስታ የራስ ነዉ:: ማፍቀር ምላሽ አይጠይቅም ፣የግድ መፈቀርም አይሻም ማፍቀር በራሡ ደስ ይላል ቀኑን በመልካም ስሜት ሸፍኖ ሌቱን በመልካም ህልም ያሳርፋል::
#አፍቃሪው

መልካም ውሎ
ያጣናቸው ሰዎች ከላያችን ላይ ቦጭቀው የሚወስዱብን ነገር አለ።በመሄዳቸው ያጎሉብናል። እነዚህ ጉድለቶች ቀን በገፋ ቁጥር ልብ ላይ ዘልቀው የሚፈጥሩት ህመም በቀላሉ አይሽርም። ወደ ውስጥ በተመለከትን ቁጥር ጎዶሎነታችን ላይ የምንደርስበት ሰዎች አለን። በራሱ ጨለማ ተውጦ የማያውቅ ማነው?.... አመታት ቢያልፉም እንደ አዲስ የምናለቅስለት ሰው አናጣም። ይህ ስቃያችን በጎጇችን ሰላም፤ በመኝታችን ደግሞ እንቅልፍ ይከለክለናል ....

ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?

    ┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                 🌺 እኔ እና እሷ🌹
                 join & share
@Snthufdire
🫶🫶🫶
በቃ ሄደች ሕልሙን እንኩትኩት አድርጋ ሰብራ,ህይወቱን ምስቅልቅል አድራጋ ተስፋውን አጨልማ እመለሳለሁ የሚል ተስፋ ብቻ አስቀርታለት ወደ.
ቦሌ air port ሄደች.

ሲሮጥ የሄደው ለካ .አስፓልት ላይ የፍቅሩን ፍፃሜ ሊሰማ ነዉ.... ..

አሁን የቀረውን ትመጣለች የሚል ተስፋ
ይዞ .. ለሷ ያለውን እምነት ጠብቆ ከ 30 አመት በላይ እዛው ቦታ ላይ እየጠበቃት ነዉ.. ...

አልሞተም.... ያልተመለሰው ሞቶ አደለም

ፍቀር ማለት ምን እንደሆነ ለኛ ሊያሳየን በፍቅር ሞቶ አዛው ቦታ ላይ ቆሟል... .. እሷም ታሪኩን ሰምታ ከሆነ አመት በፊት መታ ነበር... ግን አላስታወሳትም .. ምንም ሊያናግራት አልቻለም አሷ ተመልሳ አንደሄደች ሰምቻለሁ አሱ ግን ዛሬ እራሱ ብኬዱ እዛው ቦታ ታገኙታላቺሁ....


እሱ ማለት ለኔ የፍቅር መንታ ወንድሙ..

ለሰማዩ አለቃ.
ለምድሩ ባለቤት

የቤት ስሙ ፍቅር ለውሆነው
አምላክ

. ለለዑል እግዚአብሔር ደሞ
እውነተኛ ልጁ ነዉ ፍቅርን ያድለን
,,,,,,,,,,,,,, አብርሃም

@snthufdire
#አሞራ ☺️
.
"ዛሬ አብረን አናድርም?ፆም ሊገባ እኮ ነው!"🥹 (ድምፁን አለስልሶ በፍቅር እያወራኝ) "ዳን... እረፍ እንዲህ አይነት ቀልድ እንደማልወድ ታቃለህ ☹️
"ያንቺ ግን አልበዛም?" 🤷‍♂️
"አዎ በዝቷል ግን ደሞ አይሆንም!!"🙅‍♀️
ከዳን ጋ ይሄ ጉዳይ ሲያጨቃጭቀን የኖረ ስለሆነ ዛሬ ብርቅ አይደለም በጠዋት አደዋወሉም አብረን እንደር ለማለት መሆኑንም ጠርጥሬ ነበር።

ሲጀምር እኔና እሱ ፍፁም የተለያየ አለም ያለን ሰወች ሆነን እዚህ ድረስ መቆየታችንም ይገርመኛል.. እኔ ከአስተዳደጌ ሰንበት ትምህርት ቤት እሱ ደሞ የጥምቀት ክርስትያን ነው ሲለው ደሞ እንደ ኤቲስትም ያደርገዋል።
ከዳን ጋ ይሄ መንፈሳዊ ህይወቴ እና የሀሳብ መቃረናችን እያሰጋኝ እያፈቀርኩት እንድንለያይ ብጠይቀውም ዳን ግን ሊስማማበት አይደለም ሀሳቡን ይጠላዋል፤ የሚፈልገውን ነገር እንዳያደርግ የገደብኩት ይመስለኛል። እሱ ግን ከኩርፊያዬም ከቁጣዬም ተላምዶ ሊለየኝ አይፈልግም ....

"እኔ ምልህ ዛሬ እስቲ ቤ/ክ እንሂድ"😊 (ወሬውን ለማረሳሳት ያነሳሁት ርዕስ ነበር ) "አልሄድም!!አንቺ ከሄድሽ አይበቃም?!)🤨 (ድምፁ ውስጥ ከፍተኛ ኩርፊያ እንዳለ ያስታውቃል።)

"በ'ናትህ እስቲ ዛሬን እንኳ እሺ በለኝ??"
"አንቺም እስቲ ዛሬን እንኳ ስሜቴን ተረጂ.. እኔ አብሬሽ እሄዳለሁ ግን አንቺ አብረሺኝ ታድሪያለሽ?" 🤗
"ምን??ከቤ/ክ ወጥቼ አልጋ ቤት??ዝሙት??"😳
"ምን ችግር አለው ነገስ የኔ አይደለ ደሞ እኔስ ሳልፈልግ አደል አብሬሽ ምሄደው😊"
"እሺ ተስማምቻለሁ!!"(አልኩት ከአፌ የሚወጣው ቃል እሬት እሬት እያለኝ::

ዳን በቀጠሯችን መሠረት ለእራት በሚመጥን አለባበስ ተሽቀርቅሮ በሰአቱ ደረሰ... እንደዛሬም ሰአት አክብሮ አያውቅም፣ ፊቱ ላይ አንዳች መፍለቅለቅ እና ደስታ ይነበባል እኔ ደሞ ከሱ ተቃራኒ ሰውነቴ ድንዝዝ ብሎብኝ ፊቴ ደመና መስሎ አይኔ የእንባ ዝናብ ቋጥሯል። ምን ያህል ስሜቴን ገድቤ እዚህ እንደደረስኩ አውቀዋለሁ ዛሬ ለአንድ ወንድ ብዬ ከአምላኬ ጋር የገባሁትን መሀላ ላፈርስ መሆኑን እያሰብኩ ተሽሞንሙኖ የመጣውን ፍቅሬን አቅፌው የቤተክርስትያኗን ደጃፍ አልፈን ወደ ውስጥ ገባን። ዳን ተሳልሞ ከዚህ ግቢ አንጠልጥሎኝ እስኪወጣ ቸኩሏል
ስሜቱ በልጦበት ያለበትን ቦታ ረስቶታል ፆም መያዣ በሚል ሰበብ አልጋ ላይ ሊጥለኝ ቋምጦ እየተቁነጠነጠ እኔ ደሞ በልቤ እየፀለይኩ... ድንገት ዛፍ ላይ የተቀመጠችው አሞራ ፊቱ ላይ ኩሷን ለጠፈችበት..😁 ዳን እንደዛ ተሽሞንሙኖ ፊቱ እና ልብሱን ባበላሸችው አሞራ ሲበሳጭ እሱም እንዲታጠብ እኔም አያ ዳምጤን ሰላም ልላቸው ቤታቸው ስንደርስ በራቸው ላይ ደበሏቸውን ደርበው አገኘናቸው...

"አያ ዳምጤ እንዴት አረፈዱ..ውሀ ይሰጡኛል?" "እንዴት አለሽ ምጥኔ ኑ ግቡ እሰጣችኋለሁ"☺️
አያ ዳምጤ የቤ/ክ ሞጋድ(እንጨት) ፈላጭ ሲሆኑ ህፃን እያለሁ ጀምሮ የማውቃቸው ትልቅ አዛውንት ናቸው። እሳቸው ያልቆነጠጡት ያልመከሩት ሰንበት ተማሪ የለም ለአያ ዳምጤ ስለ ወፏ ነግሬያቸው እየተሳሳቅን በመሀል ፀጥ ብለው ቆይተው...

"አይ ምጥኔ እኔማ ታዘብኩሽኮ"😒አሉ ወደጎን ገርመም አድርገው እያዩኝ
"ውይ ምነው አያ ዳምጤ ምን አደረኩ"😥
"እንደው እኔስ አላሳደኩሽም? አግብተሽ ከኔ ትደብቂያለሽ?"😔(እጃቸውን አገጫቸው ላይ አስደግፈው በትዝብት እያዩኝ።

አረ አያ አላገባሁም እኮ ግን ያው እጮኛዬ ነው። (በማፈር የዳን ትከሻ ስር እየተወሸቅኩ) "ነው እንዴ? በሉ እግዚሀር ፍቅራችሁን ያስምርላችሁ በኔ የደረሰ በእናንተ አይድረስ::
"እንዴ አያ ምነው እርሶ ምን ሆኑ"😳

"መቼስ ሰው አይደለሁ ወጣት እያለሁ እንዲሁ እንደናንተ የከንፈር ወዳጅ ነበረቺኝ መልኳ መቼስ ለጉድ ነው ረጅም አመት አብረን በፍቅር ቆይተን እድሜያችን እየጨመረ ሲመጣ ስሜት ይፈታተነን ጀመር እሷ ውሎዋ እዚሁ
ቤ/ክ ሲሆን እኔም በሷ ሰበብ እየተመላለስኩ ጥሩ ክርስትያን ሆኜ ነበር ግን ደሞ ውሎዬ ከመጥፎ ልጆችጋ ስለነበር የነሱን ህይወት እያየሁ አብረሺኝ ካልተኛሽ ብዬ መፈናፈኛ አሳጣኋት። ወጣትነት ካላወቁበት ክፉ ነው። "ትንፋሻችንን ዋጥ አድርገን እየሠማን" አያ ዳምጤ በሀሳብ ጭልጥ አሉ::

"አያ እና አብራችሁ ተኛችሁ?" (ዳን መልሳቸውን ለመስማት እየተጣደፈ
"አይ የልጅ ነገር ልነግርህ አይደል... ታድያ ይሄንን ሀሳቤን እንድንተው አንዴ በካህን አንዴ በመምህራን አስመክራኝ ቢያቅታት ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ታላቁ ፃም ሊገባ የቅበላ ቀን ልንገናኝ በሀሳብ ረትቻት ተስማማን። የኔ ፍላጎት ከጓደኞቼ የሠማሁትን ነገር እስካደርግ ስለነበር እስኪመሻሽ ድረስ አዲስ አበባ በኛ ጊዜ አለ የተባለ መሸታ ቤት ወሰድኳት። ደስተኛ አልነበረችም ፊቷን ከስክሳው አለመፈለጓን ብታሳየኝም እኔ ግን አልረዳ አልኳት ሰአቱ እየመሸ እኔም ለድፍረት በሚል ሰበብ እየጠጣሁ መሸታ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ፀብ ተነሳ:: ሁሉም የያዘውን መወራወር ያገኘውን ማነቅ ሲጀምር ከየት እንደተወረወረ እንኳ የማላውቀው ጠርሙስ የፍቅረኛዬን አናት ከፈለው..::"

ያኔ ታሪክ ሁሉ ተገልብጦ አዳሬን ልዘሙት ያቀድኩት ቀርቶ ለሊቱን ሆስፒታል አነጋሁ ዛሬ ድረስ ምነው ስታስመክረኝ ስትለምነኝ እሺ ብላት ስሜቴን ብገራው ኖሮ እያልኩ እፀፀታለሁ:: ግን ምን ያደርጋል ያቺ ምስኪን አናት ላይ ያረፈው ጠርሙስ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሰባት በህመም ለወራት ስትሰቃይ ቆይታ አረፈች። ሁሌ ቅበላ እያለ ሰው ለስጋ ምኞቱ ሲተራመስ ሳይ እፈራለሁ የስጋ ምኞት እውር ያደርጋል ልብ ያደነድናል ስሜቱ ያሸነፈው ሰው ለሞት እንኳ አይመለስም ዝሙትን የፍቅር ማጣፈጫ ያደረገ ሰው መጨረሻው የከፋ እንደሆን በምክር እምቢ ብዬ በተግባር አየሁት።ከዛ ቀን ወዲ ለሴት ልቤ እምቢ አለ የምወደው ትምህርቴን አቋርጬ እዚሁ ገባሁ እኔ ለክህነት ለሰባኪነት የማልገባ ሰው ነኝ ግን ደሞ እሱን ማገልገል ስለምፈልግ
ለቤተልሔም ሙጋድ ፈላጭ ሆንኩኝ

አሁን ከማንም በላይ ደስተኛ ነኝ እኔን አምላኬ የጠራኝ አንዴ እንዲህ ነው...
እየውላችሁ ...ወጣትነት ፈተናው ብዙ ቢሆንም ላወቀበት ግን ወጣትነት ሰማእትነት ነው:: በቅበላ ሰበብ ለስጋ ፈቃድ በመሮጥ ፅድቅ አይገኝም።
ቅበላ ማለት ዋና አላማው ፆሙን ለመቀበል ራስን ማዘጋጀት ንሰሐ መግባት የበደልነውን መካስ ሲሆን በሌላ መልኩ ደሞ ቤ/ክ ምእመናን ስጋ ይብሉ ስትል ፆሙ ስለመጣ ሀሴትን እናድርግ ፃሙን ከፈጣሪ ጋ በደስታ እንቀበል ማለቷ እንጂ ቅበላ የስጋ አምሮት መወጣጫ በፆሙ ዋዜማ መዳርያ የዝሙት ቅበላ አይደለም!!

እንደውም ''ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።'ሮሜ6፥13 እያለች ነው ምታስተምረው።ሁሉ በጊዜው ሲሆን ነው የሚያምረው ልጆቼ ከኔ ተማሩ
አያ ዳምጤ አስገራሚ ህይወታቸውን ነግረውን ሲያበቁ ዳን አንገቱን አቀርቅሮ እጁ ላይ አንባው ሲንጠባጠብ አየሁት እግዚአብሔር እዚህ ድረስ ያመጣን በምክንያት ነበር።አያ ዳምጤም ነገር ቶሎ ስለሚገባቸው የዳንን ማዘን ሲያዩ መርቀው ሸኙን።

ከኔጋ ለመተኛት ቋምጦ ሲፍለቀለቅ የነበረው ዳን እግራችን ከቤ/ክ ሳይወጣ እቅፍ አድርጎኝ እያለቀሰ ስብር ባለ ድምፅ
"ይቅርታ" አለኝ እኔም ደሞ በተራዬ ፀሎቴ ስለተሰማ እየተፍለቀለቅኩ እቅፍ አደረኩት ቅበላን ከአያ ዳምጤ ምክር ተቀብለን ፍቅራችን ታድሶ በበረከት ተመለስን።

ከስጋችን ይልቅ በመንፈስ በረከት የምንቀበልበት ፆም ያድርግልን!!


መልካም ፆም

@snthufdire
አፈቀርሻለሁ አትበለኝ
........,,,,,,,,, ........,,,

አፈቅርሻለሁ ስትል ቢሰማም ጆሮዬ
መማንን አልሻም ነገሬን ሁሉ ጥዬ

የፈቀርኩሽባዬች ቃል እዉነት ነዉ እያልኩ
መገኘትን አልሻም አስሩን እየማኩ

ፍቅር በቃል ብቻ እዉነት ሁኖ አያቅም
በተግባር ካልቃኙት ለዘበት አይደምቅም

ፍቅር እንደቀልድ በቃላት ድርደራ
አይደለም ሊፈካ ጭራሹን አይበራ

ጭላንጭል ብርሀን ድቅድቅ ባለ ጨለማ
ለአለም አታበራም እራሷን አስታማ

ፍቅርም እንደዛዉ ነዉ ጠልቆ መኖር ይሻል
ከላይ ከላይ ብቻ ላይመጣ ይሸሻል

አንተም ከማለት መሰለኝ እኔም ከምጎዳ
በቃላቶች ስብጥር ብቻ ፍቅርን አንቅዳ

ግና እንደገና

አፈቀርሻለሁ አትበለኝ ፍቅር አይነገርም
በተግባር ካልቃኙት መኖር አይጀምርም

Share and Like ❣️❣️

❣️❣️ @snthufdire
🍁ሁሉም ሰው እንደ ጨረቃ🌙 ነው ላማንም የማያሳየው ግማሽ ጎን አለ

ሰላም እደሩልኝ
@snthufdire
2024/11/20 03:51:41
Back to Top
HTML Embed Code: