ኒቆዲሞስ፡የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት
በመ/ር ጌታቸው በቀለ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሠረት ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በዚህ ሰባተኛው ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኒቆዲሞስ ለተባለ የአይሁድ አለቃ ያስተማረው ትምህርት ይነበባል፣ ይተረጎማል፣ ይዜማል /ዮሐ ፫፥፩-፳፩/፡፡
ኒቆዲሞስ ማን ነዉ?
ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል /ዮሐ ፩-፪/፡፡ በአይሁድ አለቆች ፊትም “ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሣ መርምርና እይ” አሉት እንጂ አልተቀበሉትም /ዮሐ ፯፥፵፰-፶፪/። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ /ዮሐ ፲፱፥፴፱/። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።
ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን የፈሪሳውያን አለቃ፣ የኦሪት መምህር ብቻ ሳይሆን የኦሪት ምሁርም ነበር፡፡ በእርሱ ደረጃ የነበሩ ታላላቅ የአይሁድ ምሁራን መንፈሳዊ ሥልጣናቸውና ሹመታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ረስተው በሕዝቡ ላይ የሚመጻደቁ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው ዕውቀትን የሚገልጥ እውነተኛ አምላክ፣ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም ሲገለጥ የአይሁድ ምሁራን የጌታን መገለጥ አልወደዱትም፡፡ የእርሱ ትሕትና የእነርሱን ትዕቢት የሚያጋልጥ ነበርና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሄዱትን ሁሉ ይነቅፉ ይከስሱ ነበር፡፡ ጌታችንም የፈሪሳውያን ሐሳባቸው በግብዝነት የተሞላና ከንቱም እንደሆነ ነግሯቸዋል፡፡ ለደቀመዛሙርቱም ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ የሚበልጥ ሥራን እንዲሰሩ አስጠንቅቋቸዋል /ማቴ.፭፥፳፤ማቴ.፲፮፥፮/፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ ጌታችን በሌሊት የሄደዉ ለምንድነው? ለምን በቀን አልሄደም?
ኒቆዲሞስ በመጀመሪያ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው በቀን ሳይሆን በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታችን ከሄደባቸው ምክንያቶች አንዱ በቀን መሄድን ስለፈራ ነው። ለዚህም የቤተ ክርሰቲያን አባቶች በዋናነት ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ፡፡ የመጀመሪያው የአይሁድ መምህር ሆኖ ሳለ በቀን በሕዝብ ፊት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መማር ስላፈረ ነው የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አይሁድ “ከእኛ ወገን በክርስቶስ ያመነ ቢኖር ከምኩራብ ይሰደድ” የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ነበርና ያንን ፈርቶ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ፍራቻዎች ኒቆዲሞስን ወደ ክርስቶስ ከመምጣት አላገዱትም፡፡
ኒቆዲሞስ በርቀት በአደባባይ ድንቅ ተአምራትን ሲያደርግ ያየውን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀርቦ መጠየቅ መማር ፈልጓል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው ተአምራት የተረዳው ነገር ቢኖርም ቀርቦ ደግሞ ከእርሱ ከራሱ ስለማንነቱ መስማት ፈልጓል፡፡ ወደ ክርስቶስም ቀርቦ “መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን” አለው /ዮሐ.፫፥፪/፡፡
ኒቆዲሞስ ግን ከእነዚህ ከፈሪሳዊያን መካከል የተገኘ ልዩ ምሁረ ኦሪት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ራሱን ለእውነት ልቡን ለእምነት አዘጋጅቶ ከሁሉ ቀድሞ በሌሊት ክርስቶስን ፍለጋ የመጣ ከእነዚህ ፈሪሳዊያን ወገን ተለይቶ ወደ ጽድቅ መንገድ የተጠራ ነው፡፡ ሹመት እያለው ሁሉ ሳይጎድልበት በዙርያው የነበሩት ከእኛ በላይ ማን አዋቂ አለ የሚሉ ከእውነት ጋር የተጣሉ ጌታችንን የሚያሳድዱ በእርሱም የሚቀኑና ጌታችንንም ለመግደልም ዕለት ዕለት የሚመክሩ ሁነው ሳለ ኒቆዲሞስ ግን እውነትን ለማወቅ እልቅናው ሳይታሰበው፣ ከአካባቢው ጋር መመሳሰልን ሳይመርጥ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሊማር በሌሊት መጣ፡፡ መምህረ ትሕትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የኒቆዲሞስን ትሕትናውን ተቀብሎ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትውልድ ሁሉ የሚማርበትን ረቂቁን ምስጢረ ጥምቀትን አስተማረው፡፡
ዳግመኛ የመወለድ ምስጢር
ኒቆዲሞስ ዳግመኛ የመወለድን ምስጢርን ለማወቅ ልቡናውን ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ ኒቆዲሞስ በመጀመርያ የጥምቀትን ነገር ሲሰማ ለመቀበል ተቸግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ግን የኒቆዲሞስን አመጣጥ በማየት ልቡናውንም ከፍ ከፍ ስላደረገ ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት፡፡ “ቅዱሱን ማወቅ ማስተዋል ነው” ተብሎ በምሳሌ መጽሐፍ እንደተጻፈ /ምሳ 9፥11/ ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ኅብረት ወጥቶ በትሕትና ወንጌልን ለመማር፣ በሃይማኖት ልቡናውን ለእግዚአብሔር ቃል አዘጋጀ፡፡ ለአብርሃም የግዝረትን ጸጋ የሰጠ ጌታ በትሕትና ለቀረበው ኒቆዲሞስ የግዝረት ጸጋ ፍጻሜ የሆነች የልጅነት ጥምቀትን ነገር አስተምሮታል፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ መድኃኔዓለም ለመማር የሄደው በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሚታሰብበት የዐቢይ ጾም ሰንበት በጸሎተ ቅዳሴ የሚዜመው የክቡር ዳዊት መዝሙር “በሌሊት ጎበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፣ ፈተንኸኝ፣ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር” ይህን የሚያስረዳ ነው /መዝ.፲፮፥፫/፡፡ ሌሊት በባሕሪው ሕሊናን ለመሰብሰብ በተመስጦ ለመማር የሚመች ነው፡፡ ክርስትናም በተጋድሎ ሕይወት በመትጋት ሥጋን በቀንና ሌሊት ለነፍስ እንዲገዛ በማድረግ የሚኖር ሕይወት ነው፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱን “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያንም በቀንና በሌሊት በኪዳኑ በቅዳሴው በማህሌቱ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡
ዮሐንስ ወንጌላዊ ይህንን የኒቆዲሞስን ምስክርነት “ከእነርሱ አንዱ በሌሊት ቀድሞ ወደ እርሱ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው። እነርሱም መለሱና፡- አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።” በማለት ገልጾታል /ዮሐ.፯፥፶-፶፪/፡፡ ኒቆዲሞስ ያለፍርሐትና ያለ ሀፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል፡፡ ካህናቱን መጽሐፍ ጠቅሶ እውነትን ተናግሮ አሳፍሯቸዋል፡፡ ኒቆዲሞስ እስከ መጨረሻው በመጽናት ለታላቅ ክብር በቃ፡፡

Telegram
✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
እንኳን ወደዚህ ቻናል በሰላም መጡ
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት ደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ።
share share share

ኒቆዲሞስም ከጌታችን በተማረው ትምህርት ጸንቶ ለመኖር የበቃ አባት ነው፡፡ የሃይማኖቱ ጽናትም በተግባር የተፈተነ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የአይሁድን ድንፋታ ሳይፈራ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል” ሳይል በድፍረት የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን በንጹሕ የተልባ እግር በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር፣ በጌቴሴማኒ የቀበረ ሰው ነው /ዮሐ.፲፱፥፴፰/፡፡ ኒቆዲሞስ ከሐዲስ ኪዳን ካህናት ቀድሞ የጌታችንን ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው ክቡር ሥጋ ለመገነዝ የበቃ አባት ነው፡፡ የጌታችንን ክቡር ሥጋ ገንዘው ሲቀብሩም በጸናች የተዋሕዶ እምነት ጌታ እንደገለጠላቸው “ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት” የሚለውን ቤተክርስቲያናችን እስከ ዕለተ ምጽአት የክርስቶስን ሥጋና ደም ስትባርክ የምትጠቀምበትን ጸሎት እስከ ፍጻሜው እየጸለዩ ነበር፡፡ በዚህም ኒቆዲሞስ ከሐዲስ ኪዳን ካህናት ቀድሞ ምስጢረ ጥምቀትን ከጌታ እንደተማረ፣ የሐዲስ ኪዳንን የምስጢራት አክሊል ምስጢረ ቁርባንንም እንዲሁ ተማረ፡፡ ይህንንም በሚመለከት ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ አብሮት ይቀድስ የነበረውን ንፍቅ ካህን በባረከበት አንቀጽ “በዚህ ምስጢር እየተራዳኝ ከእኔ ጋር ያለ ይህንን ካህን እርሱንም እኔንም ሥጋህን እንደገነዙት እንደ ዮሴፍና እንደ ኒቆዲሞስ አድርገን” /ቅዳሴ ማርያም፤ ቁ.115/ ብሏል፡፡
እንደ ማጠቃለያ
እኛም እንደ ኒቆዲሞስ በዕውቀታችን፣ በሥልጣናችን፣ በሀብታችን፣ ባለን ማንነት ሳንታበይ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ የእውነተኛ አባቶችን ትምህርት፣ ምክርና ተግሣጽ ልናዳምጥ በተግባርም ልናውለው ይገባናል፡፡ ምድራዊ አመክንዮ ሳያሰናክለን በቀንና በሌሊት ወደ አማናዊት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለምስጋና መሄድ ይኖርብናል፡፡ ክርስትና ምድራዊ ስጦታና ተዓምራት በሚገለጥበት በገሊላ ባሕር አጠገብ ብቻ ሳይሆን መከራና ስቃይ ባለበት በቀራንዮም መገኘትን ይጠይቃል፤ በፈተናና በመከራ ጊዜም ቢሆን በእምነት ልንጸና የበለጠም በመታመን ልናገለግል ይገባል፡፡
ከኒቆዲሞስ ሕይወት ተምረን በሃይማኖት እንድንጸና የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል” /ማር.፲፮፥፮/ በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ ይፍቀድልን፤ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፤ አሜን፡፡
ምንባባት ኒቆዲሞስ
መልዕክታት
✍️ ሮሜ ፯፥፩-፲፱
✍️ 1ኛ ዮሐ.፬፥፲-ፍጻ
ግብረ ሐዋርያት
✍️ ሐዋ.ሥራ ፭፥፴፬—ፍጻ
ምስባክ
✍️ መዝ.፲፮÷፫
ሐውጽከኒ ሌሊት ወፈተንኮ ለልብየ፥
አመከርከኒ ወኢተረክበ አመጻ በላዕሌየ፤
ከመ ኢያንብብ አፍየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው
ትርጉም፦ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፡፡
ወንጌል
✍️ ዮሐ.፫÷፩-፳
የዕለቱ ቅዳሴ
✍️ ቅዳሴ እግዚእ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ሃይማኖተ አበው
✍️ ቅዳሴ ማርያም
✍️ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
እንደ ማጠቃለያ
እኛም እንደ ኒቆዲሞስ በዕውቀታችን፣ በሥልጣናችን፣ በሀብታችን፣ ባለን ማንነት ሳንታበይ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ የእውነተኛ አባቶችን ትምህርት፣ ምክርና ተግሣጽ ልናዳምጥ በተግባርም ልናውለው ይገባናል፡፡ ምድራዊ አመክንዮ ሳያሰናክለን በቀንና በሌሊት ወደ አማናዊት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለምስጋና መሄድ ይኖርብናል፡፡ ክርስትና ምድራዊ ስጦታና ተዓምራት በሚገለጥበት በገሊላ ባሕር አጠገብ ብቻ ሳይሆን መከራና ስቃይ ባለበት በቀራንዮም መገኘትን ይጠይቃል፤ በፈተናና በመከራ ጊዜም ቢሆን በእምነት ልንጸና የበለጠም በመታመን ልናገለግል ይገባል፡፡
ከኒቆዲሞስ ሕይወት ተምረን በሃይማኖት እንድንጸና የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል” /ማር.፲፮፥፮/ በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ ይፍቀድልን፤ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፤ አሜን፡፡
ምንባባት ኒቆዲሞስ
መልዕክታት
✍️ ሮሜ ፯፥፩-፲፱
✍️ 1ኛ ዮሐ.፬፥፲-ፍጻ
ግብረ ሐዋርያት
✍️ ሐዋ.ሥራ ፭፥፴፬—ፍጻ
ምስባክ
✍️ መዝ.፲፮÷፫
ሐውጽከኒ ሌሊት ወፈተንኮ ለልብየ፥
አመከርከኒ ወኢተረክበ አመጻ በላዕሌየ፤
ከመ ኢያንብብ አፍየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው
ትርጉም፦ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፡፡
ወንጌል
✍️ ዮሐ.፫÷፩-፳
የዕለቱ ቅዳሴ
✍️ ቅዳሴ እግዚእ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ሃይማኖተ አበው
✍️ ቅዳሴ ማርያም
✍️ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
Telegram
✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
እንኳን ወደዚህ ቻናል በሰላም መጡ
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት ደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ።
share share share
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት ደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ።
share share share
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
https://www.tgoop.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk

ሆሣዕና በአርያም = እንኳን አደረሳችሁ!
☞ የዐቢይ ጾም ፰ኛ ሳምንት #ሆሣዕና
✔ የዕለቱ መዝሙራት፣ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል
❖ የሆሣዕና ዋዜማ /የቅዳሜ ማታ መዝሙር
«ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ።»
ትርጉም፦
የፋሲካ በዓል ሳምንት ሲቀረው የእውነተኛ አምላክ ደቀ መዛሙርት የእግዚአብሔር ሀገር ወደ ሆነችው ደብረ ዘይት ቁልቁለት ሲደርሱ ወደ እርሱ ለመታዘዝ ቀረቡ፤ ብዙ ሕዝብ፣ ልጆችና ሽማግሌዎችም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ተጭኖ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸው ዘንድ በፍጹም ደስታ ኢየሩሳሌም ገባ።
#መልዕክታት
➊. ዕብራ. ፰:፩-ፍጻሜ /8÷1-ፍጻሜ
ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን። (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➋. ፩ኛ ጴጥ.፩÷፲፫ እስከ ምዕ ፪÷፲፩
ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➌. ግብረ ሐዋርያት
የሐዋ. ፰:፳፮-ፍጻሜ /8÷26-ፍጻሜ
የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን
ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው
መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ፡፡
በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡
እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ፡፡
ትርጉም፦
በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና÷
(መዝ.፹÷፫)
.
✝ ወንጌል
ዮሐ.፲፪÷፩-፲፩
ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
፠ የሌሊት ሆሣዕና
+ ምስባክ
ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር።
ባረክናክሙ እምቤተ እግዚእብሔር፡፡ እግዚእብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ፡፡
ትርጉም፦
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤
ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ፡፡
ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤
(መዝ.፻፩፯÷፳፮)
.
✝ ወንጌል
ሉቃ.፲፱÷፩-፲፩
ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢያራኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር፡፡ እነሆ÷ የቀራጮች አለቃ ስሙ ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤
(ተጨማሪውን ያንብቡ)
✞ ዘነግህ
(በጊዜ ዑደት ውስተ ቤተ መቅደስ)
+ ምስባክ
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር።
ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ ኢየሩሳሌም።
ኢየሩሳሌምሰ ሕንፅት ከመ ሀገር።
ትርጉም፦
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝ ደስ አለኝ፡፡
ኢየሩሳሌም ሆይ÷ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ፡፡
ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት፡፡
(መዝ ፻፳፩ ፣ ፩ /121፥1)
+ ወንጌል
ማቴ. ፳፥፳፱-ፍጻሜ
ከኢያሪኮም በወጣ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተከተሉት፡፡ እነሆ÷ ሁለት ዕውራን በመንገድ አጠገብ ተቀምጠው ነበር፤ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር፡፡
ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን :-
እስመ አጽንዐ መናስግተ ኆኃትኪ፡፡
ትርጉም:-
ኢየሩሳሌም ሆይ÷ እግዚአብሔርን አመስግኚ÷
ጽዮንም ሆይ÷ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጸንቶአልና÷
መዝ.፻፵፯÷፩
.
★ ወንጌል
ማርቆስ ፲፥፵፮-ፍጻሜ
ወደ ኢያሪኮም ገባ፤ ከኢያሪኮም በወጣ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ብዙ ሰውም ነበረ፤ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
+ ምስባክ
ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት፣
በኃበ እለ ያስተሐምምዎ፣
አስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ።
ትርጉም፦
ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤
እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በሚያስተነትኑበት በደስታ በዓልን አድርጉ፡፡
(መዝ ፻፲፯፥፳፯)
.
+ ወንጌል
ማቴዎስ ፱፥፳፮ እስከ ምዕ ፲÷፲፰
.
☞መዝሙር => ዘምዕዋድ
አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ እስመ እምጽዮን ይወጽእ ሕገ ወቃለ እግዚአብሔር እምኢየሩሳሌም ንሣለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን
.
☞መዝሙር => <<ሰመያ አብርሃም>>
ሰመያ አብርሃም ወይቤላ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ በዕምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
.
☞መዝሙር => ወትቤ ጽዮን
ወትቤ ጽዮን አርኅው ሊተ አናቅጸ ይባኡ ሕዝብ ብዝዙኃን ወያዕትቱ ዕብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
.
✝ መዝሙር => "ባርኮ ያዕቆብ"
ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽእ እምኔከ ዘየሐጽብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦሙ ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
.
★+መልዕክታት
➊ ዕብራ ፱÷፲፩-ፍጻሜ
ክርስቶስ ግን ለምትመጣይቱ መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ÷ የሰው እጅ ወደ አልሠራት÷ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➋1ኛጴጥ ፬÷፩-፲፪
ክርስቶስ ስለ እኛ በሥጋው ከተሰለቀ÷ እናንተም ይህቺን ዐሳብ ጋሻ አድርጋችሁ ኑሩ፤ በሥጋዉ መከራ የተቀበለ ከኀጢአት ድኖአልና፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➌ የሐዋ/ሥራ ፳፰÷፲፩-ፍጻሜ
ከሦስት ወር በኋላም በዚያች ደሴት ወደ ከረመችው ወደ እስክንድርያ መርከብ ወጣን፤ በዚያች መርብ ላይም የዲዮስቆሮስ ምልክት ነበረባት፤ ይኸውም “የመርከበኞች
አምላክ” የሚሉት ነው፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ፡፡
በእንተ ጸላዒ፡፡
ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡
ትርጉም፦
ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡
ስለ ጠላት÷
ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡
(መዝ ፰:፪ /8÷2)
.
+ ወንጌል
ዮሐንስ ፭÷፲፩-፴፩ /5÷11-31
እርሱም መልሶ÷ “ያዳነኝ እርሱ፡- አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” አላቸው፡፡ አይሁድም... (ተጨማሪውን ያንብቡ)
✞ ቅዳሴ = ዘጎርጎርዮስ (ነአኵቶ) [በዕዝል ዜማ]
♦-♥ መልካም የሆሣዕና በዓል ♥ -♦

👉 ልዩ ዕለት
የዛሬቱ ዕለት ከሁሉም ዕለታት ልዩ ዕለት ናት የድንቅ ምሥጢር መገለጫ ልዩ ዕለት
ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ እንዲል ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይይዙታል ማለትም በሰባቱ ዕለታት ተፈጥረው የተመለኩ ፍጥረታት የአምላክን አምላክነት ይመሰክራሉ ማለት ነው የመሰከሩባት ልዩ ዕለት
አንድም ሰባቱ ተአምራት ተፈጽመው ጌትነቱን የሚሰብኩባት ልዩ ዕለት
➟ ፀሐይ የጨለመባት ልዩ ዕለት
➟ጨረቃ በደም የታጠበችባት ልዩ ዕለት
➟ከዋክብትም ጽናተቸውን የለቀቁባት ልዩ ዕለት
➟ካምስት መቶ ብቅ ከስድስት መቶ ዝቅ የሚሉ ሙታን ከመስቀሉ እግርጌ እንደ አሸን የፈሉባት ልዩ ዕለት
➟ መቃብራት የተከፈቱባት ሙታን የተነሱባት ልዩ ዕለት
➟ ድንጋዮች የተፈተቱባት ልዩ ዕለት
➟የቤተ መቅደሱ ከሦስት ካራት የተቀደደባት ልዩ ዕለት
➣ መድኀን ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በፈቃዱ የለየባት ልዩ ዕለት
➣ ምእመንንም የሞሸረባት ልዩ ዕለት
➣ እጁን በደም ነክሮ ለኖረ ሽፍታ ወንበዴም ምሕረት የወረደባት
➣ገነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችባት ልዩ ዕለት ወዘተርፈ
በአጠቃላይ ከሰው ልጆች ይልቅ ደግሞ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታት እግዚአብሔርነቱን የመሰከሩባት ልዩ ዕለት ናት
➣ እኛስ የፀሐይን ያህል መስክረን ይሆን ?
የጨረቃን ያህልስ እንባ አልቅሰን ደም ደም አልቅሰን እዝኅ በማለቅስ በእንባ በደም በመራጨት መስክረን ይሆን ?
የከዋክብትን ያህልስ መስክረን ይሆን ?
የሙታንን ያህልስ
የድንጋዮችን ያህልስ ልባችን ተሰንጥቆ ይሆን ?
የመጋረጃውን ያህል ምን ያህል ተብሰክስከን ይሆን ?
➟ ነገሩስ ከእነዚህ ሁሉ እንደምናንስ ምንም እንደማይሰማን ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ገልጾታል
እስኪ እንስማው
"ፀሐይ ሰኢኖ ጽዕለተ እግዚእ ጸዊረ ብርሃኖ ለጽልመት ሜጠ ወንሕነሰ እም ጽልመት አከይነ ወኢ እምልብነ ንፈቱ ንትነሳሕ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ ርእሶ ሰጠጠ ወንሕነሰ በእንተ ኀጢአትነ ኢተነሳሕነ ወኢ በልብነ ንፈቱ አጻብአ ፈረስ ወፀር ተንሢኦሙ አማሰኑ ብሔረነ ከመ ለእግዚአብሔር ፈሪሀነ ውስተ ንስሓ ንግባእ ወበዘሂ ኢተነሳሕነ ወኢደንገፅነ ንትነሳሕ እንከ"
➟ትርጉም
ፀሐይ እንኳ የጌታውን ስድብ መሸከም ተስኖት ብርሃኑን ወደጨለማ ለውጧል እኛ ግን ከጨለማ ከፍተናል ከልባችንም ንስሓ ለመግባት አልወድም የቤተ መቅደሱም መጋረጃ በደል ሳይኖርበት ራሱን ቀዷል እኛ ግን ስለኀጢአታችን ከልባችን ንስሓ ለመግባት አንወድም እግዚአብሔርንም በመፍራት ንስሓ ወደንስሓ እንድንመለስ የጠላትና የፈረስ እጣቶች ተነስተው ሀገራችንን አጥፍተዋል በዚህም ንስሓ አልገባንም ንስሓ ለመግባትም እንግዲህ አልደነገጥንም ።
ወንበዴውን የማረ ጌታ ይማረን
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
የዛሬቱ ዕለት ከሁሉም ዕለታት ልዩ ዕለት ናት የድንቅ ምሥጢር መገለጫ ልዩ ዕለት
ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ እንዲል ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይይዙታል ማለትም በሰባቱ ዕለታት ተፈጥረው የተመለኩ ፍጥረታት የአምላክን አምላክነት ይመሰክራሉ ማለት ነው የመሰከሩባት ልዩ ዕለት
አንድም ሰባቱ ተአምራት ተፈጽመው ጌትነቱን የሚሰብኩባት ልዩ ዕለት
➟ ፀሐይ የጨለመባት ልዩ ዕለት
➟ጨረቃ በደም የታጠበችባት ልዩ ዕለት
➟ከዋክብትም ጽናተቸውን የለቀቁባት ልዩ ዕለት
➟ካምስት መቶ ብቅ ከስድስት መቶ ዝቅ የሚሉ ሙታን ከመስቀሉ እግርጌ እንደ አሸን የፈሉባት ልዩ ዕለት
➟ መቃብራት የተከፈቱባት ሙታን የተነሱባት ልዩ ዕለት
➟ ድንጋዮች የተፈተቱባት ልዩ ዕለት
➟የቤተ መቅደሱ ከሦስት ካራት የተቀደደባት ልዩ ዕለት
➣ መድኀን ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በፈቃዱ የለየባት ልዩ ዕለት
➣ ምእመንንም የሞሸረባት ልዩ ዕለት
➣ እጁን በደም ነክሮ ለኖረ ሽፍታ ወንበዴም ምሕረት የወረደባት
➣ገነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችባት ልዩ ዕለት ወዘተርፈ
በአጠቃላይ ከሰው ልጆች ይልቅ ደግሞ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታት እግዚአብሔርነቱን የመሰከሩባት ልዩ ዕለት ናት
➣ እኛስ የፀሐይን ያህል መስክረን ይሆን ?
የጨረቃን ያህልስ እንባ አልቅሰን ደም ደም አልቅሰን እዝኅ በማለቅስ በእንባ በደም በመራጨት መስክረን ይሆን ?
የከዋክብትን ያህልስ መስክረን ይሆን ?
የሙታንን ያህልስ
የድንጋዮችን ያህልስ ልባችን ተሰንጥቆ ይሆን ?
የመጋረጃውን ያህል ምን ያህል ተብሰክስከን ይሆን ?
➟ ነገሩስ ከእነዚህ ሁሉ እንደምናንስ ምንም እንደማይሰማን ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ገልጾታል
እስኪ እንስማው
"ፀሐይ ሰኢኖ ጽዕለተ እግዚእ ጸዊረ ብርሃኖ ለጽልመት ሜጠ ወንሕነሰ እም ጽልመት አከይነ ወኢ እምልብነ ንፈቱ ንትነሳሕ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ ርእሶ ሰጠጠ ወንሕነሰ በእንተ ኀጢአትነ ኢተነሳሕነ ወኢ በልብነ ንፈቱ አጻብአ ፈረስ ወፀር ተንሢኦሙ አማሰኑ ብሔረነ ከመ ለእግዚአብሔር ፈሪሀነ ውስተ ንስሓ ንግባእ ወበዘሂ ኢተነሳሕነ ወኢደንገፅነ ንትነሳሕ እንከ"
➟ትርጉም
ፀሐይ እንኳ የጌታውን ስድብ መሸከም ተስኖት ብርሃኑን ወደጨለማ ለውጧል እኛ ግን ከጨለማ ከፍተናል ከልባችንም ንስሓ ለመግባት አልወድም የቤተ መቅደሱም መጋረጃ በደል ሳይኖርበት ራሱን ቀዷል እኛ ግን ስለኀጢአታችን ከልባችን ንስሓ ለመግባት አንወድም እግዚአብሔርንም በመፍራት ንስሓ ወደንስሓ እንድንመለስ የጠላትና የፈረስ እጣቶች ተነስተው ሀገራችንን አጥፍተዋል በዚህም ንስሓ አልገባንም ንስሓ ለመግባትም እንግዲህ አልደነገጥንም ።
ወንበዴውን የማረ ጌታ ይማረን
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
Telegram
✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
እንኳን ወደዚህ ቻናል በሰላም መጡ
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት ደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ።
share share share
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት ደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ።
share share share
ቅዳሜ፡–
ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡
የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ።
ጠዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡
ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡
ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡
ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡
በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል።

ብቻህን ማሰብ ስትጀምር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የብቻችን የሆነ ትምህርት የለም። በማኅበር እንማራለን ፤ በማኅበር እንጸልያለን ፤ አንድ ሆነን የተዘጋጀልንን ማዕድ ቅዱስ ቊርባን እንቀበላለን ፤ በመጨረሻም የተዘጋጀልንን የተስፋ አገር እንቀበላለን።
ክርስቶስ ያስተማረ በጉባኤ ነው ፤ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም ጉባኤአዊት ሆና ትቀጥላለች እንጅ ማንም ምንም ቢሆን የራሱን ትምህርት አምጥቶ ሊያስተምር የሚችልበት ዕድል የለውም።
የብቻው የሆነ ክርስቶስ ስለሌለው የብቻው የሆነ ትምህርትም ሊኖረው አይችልም።
ብቻህን ማሰብ ከጀመርህ ከጉባኤው የተለየ አስተምህሮ ማምጣትህ ስለማይቀር “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” የሚለውን የሃይማኖት መግለጫ አስቀድመን እንድናውቅ መደረጉ ስለዚህ ነው።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚኖር ማንም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ካስተማረችው ትምህርት የወጣ እንደሆነ መዐርጉ ፣ የዕውቀት ደረጃው ፣ የወገኑ የሀብቱ ብዛት ሊያድነው አይችልም። በመጀመሪያ ከቃሉ የሰሙ ሰዎች “የተናገርኸውን ትምህርት አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ብለው ይመክሩታል። ምክራቸውን ሰምቶ በዚህ ካቆመ ይተዉታል፤ ምክራቸውን አልሰማ ብሎ ከቀጠለ ግን ወደ መምህራን ያደርሱታል፤ መምህራንንም አልሰማ ካለ ወደ ጉባኤ {ሲኖዶስ} ይቀርባል። ሲኖዶሱን ካልሰማ ተወግዞ ይለያል።
በሰሞኑ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሰጡትን ትምህርት በቪዲዮ አንዲት ወዳጄ ልካልኝ ተመለከትሁት፤ ምናልባት ከባልንጀሮቻቸው ጋር ተማክረውበት ከበታቾቻቸውም ጋር ተከራክረውበት የነበረ ጉዳይ ከሆነ “አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ሊሏቸው ይገባ ነበር።
አሁን ግን በሹክሹክታ ሳይሆን በሰገነት ላይ የተሰበከ የስሕተት ስብከት ስለሆነ ጉዳዩ ከዚህ ያለፈ ይመስለኛል። ከረፈደም ቢሆን ባየሁት መረጃ መሠረት ብዙ ሊቃውንት ሀሳብ ሰጥተውበታል ፤ ይሄ ለብፁዕነታቸው መልካም ዕድል ነው ብየ አምናለሁ። ሀሳባቸውን የገለጹ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን በሊቅነታቸው የምታምንባቸው ሊቃውንት እንደመሆናቸው መጠን ምክሩን ይቀበሉታል ብየ ስለማምን ነው። ሀሳቡን ሳይንቁ በቶሎ በሰገነት ላይ ያጠፉትን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሰገነት ላይ ወጥተው ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። “አትደንግጡ” ብለውናል እንዳንደነግጥ ያድርጉን።
ይህንን ትምህርት አባቶቻችን አልነገሩንም መጻሕፍቶቻችን ላይ ተጽፎ አላገኘነውም።
ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ መጻሕፍቶቻችንን አባቶቻችንን ተቃውመዋል። ዛሬ መልስ አልጽፍም፤ ምክንያቱም መልሱን ከብፁዕነትዎ ስለምጠብቅ ነው።
ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ

🕊
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን
🕊 ልደታ ለማርያም ድንግል 🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
† ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: †
[ ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) ]
የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::
ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::
እመቤታችን ከአዳም ስሕተት ብኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: [ኢሳ.፩፥፱]
ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ፳፻፳፪ [2,022] ዓመታት በፊት ተወልዳለች::
"ሙሽራዬ ሆይ ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" [መኃልይ.፬፥፰]
ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ [አሮን] የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር::
ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::
ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ፵ [40] ቀናትም ሲጸልይ ቆየ:: በ፵ [40] ኛው ቀን ፪ [2] ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::
እርሷ ደግሞ :- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ፯ [7] ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::
በ፯ [7] ኛው ቀን [ማለትም ነሐሴ ፯ (7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::
እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: [ቅዳሴ ማርያም]
"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል [ያለ ጥፋት] ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." [መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ.፩፥፱]
እመቤታችን ነሐሴ ፯ [ 7 ] ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች::
የእመቤታችን የዘር ሐረግ :-
- አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
- በእናቷ :-
ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::
- በአባቷ በኩል :-
-ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::
ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::
የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::
አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ ግቢ ጉባዔ ሥነ ሥዕል ክፍል ገጽ የተወሰደ

https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0

𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes
https://www.tgoop.com/addlist/A7U6XVGLALJlNjI0

❗ጰራቅሊጦስ❗
................................................
🔷👉 ጸራቅሊጦስ የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው በግሪክ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ። ጸራቅሊጦስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሳ በኀምሳ በአረገ በአስር ቀኑ የሚከበር የመንፈስ ቅዱስ በዓል ነው።
#ጰራቅሊጦስ_ማለት
፪ኛ ናዛዚ (አረጋጊ)ማለት ነው ሰውን ሁሉ የሚአረጋጋ ነውና
፪ኛ ከሳቲ (ገላጪ)ማለት ነው ምሥጢራትን ሁሉ የሚገልፅ ነውና
፫ኛ መንጽሒ(የሚያነጻ) ማለት ነው ሰውን ሁሉ ከኀጢአት የሚያነጻ ነውና
፬ኛ መጽንኢ (የሚያጸና)ማለት ነው ሰውን ሁሉ በምግባር በሃይማኖት የሚያጸና ነውና
፭ኛ መስተስርዪ(ኀጢአትን የሚደመስስ)ማለት ነው የሰውን ሁሉ ኃጢአት የሚደመስስ ነውና
፮ኛ መስተፍሥሒ(አስደሳች) ማለት ነው ሰውን ሁሉ የሚያስደስት ነውና
አብ በዚህ ስም አይጠራም
ወልድም በዚህ ስም አይጠራም
ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ነውና
በአብ ስም ወልድና መንፈስ ቅዱስ አይጠሩም በወልድ ስምም አብና መንፈስ ቅዱስ አይጠሩም በመንፈስ ቅዱስ ስምም አብና ወልድ አይጠሩም
ስለዚህ ይህ ጰራቅሊጦስ የሚለው ስም የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው
🔷👉 ጰራቅሊጦስ እግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔር የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስማቸው ነው በዚህ ስም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጠራሉ ።
ጰራቅሊጦስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአረገ በአስረኛው ቀን ለመቶ ሃያ ቤተ ሰብእ በማርቆስ እናት ቤት ተሰብስበው ሳሉ ወርዶ በእሳትና በነፋስ አምሳል ተገልጦላቸዋል።
መቶ ሀያ ቤተሰቡ በዝግ ቤት እንዳሉ ፸፩ ቋንቋ ገልጾላቸዋል ።
ይህ ቋንቋ የተገለጸላቸው ለሐዋርያቱ ለሰብአ ሁለቱ አርድእት ለሰላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ነው ለሁሉም እንደ አቅማቸው ተገልጾላቸዋል
ከፍተኛው የተገለፀው ቋንቋ ፸፩ ሲሆን ለሐዋርያት ነው ።
ዝቅተኛው፲፭ ሲሆን ይሄም ለቅዱሳት አንስትና ለሰባ ሁለቱ አርድእት እንደ አቅማቸው ተገልጦላቸዋል ። ሐዋ 2+1
ይህ 71 ቋንቋ ሰብአ ከለዳውያን በከለዳ ምድር ግንብ ገንብተው ከፈጣሪያቸው ጋር በተጣሉ ጊዜ ቋንቋቸው ሲደበላለቅ ፸፩ ቋንቋ ሁኖ ስለ ነብር ያኔ የተደበላለቀው ቋንቋ በሐዲስ ኪዳን ለሐዋርያት ተገልጿል
ቋንቋ 5 መሰረታዊ ነገሮች አሉት
፩ኛ ፊደል የሚፃፍበት
፪ኛ ስም የሚጠራበት
፫ኛ ሀገር የሚነገርበት
፬ኛ ተናጋሪ ቋንቋውን የሚያውቅ
፭ተኛ ሰሚ ቋንቆው ሲነገር የሚሰማ
እነዚህን የማያሟላ ቋንቋ ቋንቋ አይደለም
የዘመኑ ሉተራውያን መንፈስ ቅዱስ ወረደልን ልሳን ተገለጠልን ብለው የሚዘላብዱት
የቋንቆው ስም ምን ነው? ፊደሉን ፃፉልን?ሀገሩስ የት ነው? ቢባሉ መልስ የላቸውም መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያቱ የገለጠው ቋንቋ ከተለያየ ሀገር ለተሰበሰቡ ሰዎች የሚያስተምሩበት ነው ሐዋ 2+1 #መንፈስ ቅዱስ ለፍጡራን የሚገለጠው ፍጡራንን መስሎ ነው
መንፈስ ቅዱስ ለአብርሃም ሲገለጥ በሰው አምሳል ነው።
እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት አብርሃም እግዚአብሔርን ለማየት ዓይኑን አነሳ ሶስት ሰዎች በፊቱ ቁመው አየ ይላል ዘፍ 18+1 ሶስት ሰዎች ከተባሉት አንዱ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ነው
ከዚህ ላይ ለአብርሃም የተገለጠለት በሰው አምሳል ነው እንጅ ሰው ሁኖ አይደለም
መንፈስ ቅዱስ ጌታችን ሲጠመቅ በርግብ አምሳል ተገልጧል።
እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ እርግብ ሲወርድ በእርሱም ላይ ሲወጣ አየ ይላል ማቴ3+16
መንፈስ ቅዱስ መሆኑ ርግብ አለመሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ?
ጌታችን የተጠመቅ ከሌሊቱ በአስረኛው ሰአት ነው አርጋብ በሌሊት አይንቀሳቀሱም በ ቀን እንጂ በዚህ ይቷወቃል የወረደው ከሰማይ ነው አርጋብ ከሰማይ አይኖሩምና
#ለምን መንፈስ ቅዱስ ርግብ አለው ቢሉ?
ርግብ ሀዳጌ በቀል ናት መንፈስ ቅዱስም ሀዳጌ በቀል ነውና ርግብ የጥፋቱን ውሃ መጉደል ለኖህ አብስራለች
መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበስራልና
ርግብክንፏን ቢመቷት እንቁላሏን ቢሰብሩባት ቤቷን ካላፈረሱባት ቦተዋን አትለቅም መንፈስ ቅዱስም ኀጢአት ቢሰሩ ካልካዱት አይለይምና ስለዚህ በርግብ ተመስሏል
#መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በእሳትና በነፋስ አምሳል ተገልጧል።
በአለ ኀምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚናጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ።ተቀምጠው የነበሩበትን ቤት ሁሉ ሞላው እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው
በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጡባቸው በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር ይላል ሐዋ 2+1
#መንፈስ ቅዱስ ለምን በነፋስ ተመሰለ ቢሉ ?
ነፋስ ረቂቅ ነው መንፈስ ቅዱስም ረቂቅ ነውና
ነፋስ ኀያል ነው መንፈስ ቅዱስም ኀያል ነወና
ነፋስ ፍሬውን ከገለባው ይለያል
መንፈስ ቅዱስም ጻድቃንን ከኀጥአን ይለያልና
ነፋስ በምላት ሳለ አይታወቅም ባህር ሲገስፅ ዛፍ ሲያናውጥ እንጂ
መንፈስ ቅዱስም በምላት ሳለ አይታወቅም ቋንቋ ሲያናግር ምሥጢር ሲያስተረጉም ነው እንጂ
ነፋስ መዓዛ ያመጣል መንፈስ ቅዱስም መዓዛ ጸጋ ያመጣልና ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በነፋስ ተመስሏል።
#መንፈስ ቅዱስ በእሳት ለምን ተመሰለ ቢሉ?
እሳት ምሉዕ ነው መንፈስ ቅዱስም ምሉዕ ነውና
እሳት ጣእም መዓዛን ያመጣል
መንፈስ ቅዱስም ጣእመ ጸጋን መዓዛ ጸጋን ያመጣልና
እሳት በመጠን ቢሞቁት ሕይወት ይሆናል ከመጠን አልፎ ከሞቁት ያቃጥላል መንፈስ ቅዱስ በሚገባ በተጻፈው የመረመሩት እንደሆነ ሕይወት ይሆናል በማይገባ ገተጻፈው ወጥቶ የመረመሩት እንደሆነ ይቀስፋል እሳት ያቀረቡለትን ሁሉ ያቃጥላል መንፈስ ቅዱስም ሕዝብ አሕዛብ የጸለዩት ጸሎት ያቀረቡትን መሥዋዕት ይቀበላልና
እሳት ውሃ ገደል ካልከለከለው ሁሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋል መንፈስ ቅዱስምቸርነቱ ካልከለከለው በቀር ሁሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋልና
እሳት ዱር ይገልጻል መንፈስ ቅዱስም ምሥጢር ይገልጻልና
እሳት የበለው መሬት ለእህል ለተክል ይመቻል መንፈስ ቅዱስም ያደረበት ሰውነት ለገድል ለትሩፋት ይመቻልና
እሳት ከአንድ ዛላ ላይ ሌላ ሀምሳ ስልሳ ቢያበሩ ተከፍሎ የለበትም መንፈስ ቅዱስም ተከፍሎ ሳይኖርበት እስከ ምጽአት ድረስ ሲሰጥ ይኖራልና
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በእሳት ተመስሏል
#በዓሉም በሦስት ስያሜዎች ይገለጻል:-
፩ኛ. በዓለ ሃምሳ:- የሃምሳኛው ቀን በዓል ማለት ነው።
፪ኛ. ጰንጠቆስጤ (በዓለ ጰንጠቆስጤ) ይህም በግሪክኛ ሃምሳ ኛው ቀን ማለት ነው። ፫ኛ.ጰራቅሊጦስ (በዓለ ጰራቅሊጦስ) ይባላል።
ይህ በዓል ከአምላካችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ በመሆኑ እና የቤተክርስቲያንም ልደት ወይም ቤተክርስቲያን በይፋ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተመሰረተችበትም ቀን በመሆኑ ታላቅ በዓል ነው።
#ጰራቅሊጦስ ወይም መንፈስ ቅዱስ ማነው ስንል መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል:-
፩. ፈጣሪ ነው።
" የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።" (ኢዮብ ፴፫: ፬)
፪. እግዚአብሔር ነው።
ቀንም ቀጥረውለት ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያው ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት ጠቅሶ እያስረዳቸው፥ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ይገልጥላቸው ነበር።"
(የሐዋ ፳፰: ፳፫)

፫.በአካል ልዩ ነው።
"ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።"(ኢሳ ፵፰: ፲፮)
፬. በስሙ ልዩ ነው
" አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።"(ኢሳ፮:፫)
፭. ሠራጺ ነው።
" ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤"
(ዮሐ 15: 26)
፮. አጽናኝ ነው።
"አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።" (ዮሐ፲፬:፳፮)
#ጰራቅሊጦስ ለምን በበዓለ ሃምሳ ወረደ?
፩. ኃይልን ለመስጠት
" እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።" (ሉቃ፳፬:፵፱)
፪. ሐሰተኛውን ዓለም ለመውቀስ
"እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል"(ዮሐ፲፮:፰-፱)
፫. ሰዎችን ሁሉ ወደ እውነት ለማድረስ
" ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።" (ዮሐ ፲፮: ፲፫)
፬. ሁሉን ለማጽናናት
" ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤"
(ዮሐ ፲፬: ፲፭-፲፮)
፭. ስለ ወልድ ሊመሰክር
" ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።"
(፩ ቆሮ ፲፪: ፫)
፮. ሁሉን ወደ ጽድቅ ለመምራት
" አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።"
(መዝ ፻፵፪(፻፵፫): ፲)
#ጰራቅሊጦስ ለሕይወታችን
፩. የክርስቶስ ቤተሰብ አድርጎናል።
" አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።" (፩ቆሮ ፲፪: ፲፫)
፪. በሕይወታችን ይኖራል
"የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ። (፩ቆሮ፫:፲፮-፲፯)
፫. የሕይወታችን ማህተም ነው
" ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።" (ኤፌ፬:፴)
፬. ሕይወታችንን በፍቅር ያረሰርሳል
" በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።"
(ሮሜ ፭: ፭)
፭. የጸሎትን መንፈስ ይሰጠናል
" እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤" (ሮሜ ፰: ፳፮)
፮. ከሞት ለዘለዓለም ሕይወት ያስነሳናል
" ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።" (ሮሜ ፰: ፲፩)
#ጰራቅሊጦስ ለቤተክርስቲያን
፩. ዳግም የተወለደችበት ነው
" ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" (ዮሐ ፫: ፭)
፪. ለአምልኮተ እግዚአብሔር ያነሳሳል
" እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና።"
(ፊልጵ ፫: ፫)
፬. ወንጌልን ትሰብካለች
" እነርሱም ከመሰከሩና የጌታን ቃል ከተናገሩ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በሳምራውያን በብዙ መንደሮችም ወንጌልን ሰበኩ።"
(የሐዋ ፰: ፳፭)
፭. ይመራታል ይገልጥላታል
" መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥" (፩ጢሞ ፬: ፩-፪)
፮. ውሳኔዋን ያስተካክላል
" ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።" (ሐዋ ፲፭: ፳፰-፳፱)
#ጰራቅሊጦስ ከአብ ብቻ የሠረጸ ቅዱስ መንፈስ ነው።
"ዘሠረጸ እም አብ ወወልድ" ወይም ከአብም ከወልድም ሠረጸ ይህንን የምታምነው ካቶሊካዊቷ ቤተክርስቲያን ናት።
አስቀድመን ከላይ እንዳየነው በዓለ ጰራቅሊጦስ (በዓለ ሃምሳ) ወይም ርደተ መንፈስ ቅዱስ ይህ ዕለት ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ በተነሳ በአርባኛው ቀን ፤ በዐረገ ደግሞ በ10ኛው ቀን ለሐዋርያቱ "አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ"(ሉቃ፳፬፡፵፱) ብሎ በገባለቸው ቃል መሰረት በአንድነት ተሰባስበው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ የመጣበት እንዲሁም ቤቱን ሁሉ የሞላበት ዕለት ነው፡፡(ሐዋ፫፡፩)
🔷👉 የመንፈስ ቅድስ አንድነት አይለየን❗
ሸር በማድረግ ለአንባቢ አድርሱ

#ሰኔ_12
ዝ ክ ረ - ቅ ዱ ሳ ን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን!!!
✞ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ✞
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለገናናው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር። ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል።
ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም። በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው። መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል። "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል። ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና።
በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል። እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል: መግቧልም። ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)
ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው። ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ። ደስ ብሎት ይታዘዛታል። ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል። ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ።
ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች እናከብረዋለን:-
1. በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
2. ቅዳሴ ቤቱን (ግብፅ ውስጥ)
3. ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
4. ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
5. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
6. ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን፤ የከበረች ረድኤት በረከቱና ምልጃ ጸሎቱ አትለየን።
--------------------------------------------
"በሰማይም ሰልፍ ሆነ። ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ። አልቻላቸውምም። ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም። ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ።"
(ራዕይ. 12:7)
✟ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✟
#ስንክሳር_ዘወርሃ_ሰኔ
#ይቀላቀሉን!!
https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze

✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️
በዚህ ቻናልየተለያዩ ትምህርቶች ያገኛሉ
ከነዚህም ውስጥ ✝️የግዕዝ ትምህርት
✝️የተለያዩመፅሐፉን
✝️ የተለያዮ መንፈሳዊ ስብከቶች ✝️መንፈሳዊፊ ልሞች ወ.ዘ.ተ ያገኛሉ።
ከነዚህም ውስጥ ✝️የግዕዝ ትምህርት
✝️የተለያዩመፅሐፉን
✝️ የተለያዮ መንፈሳዊ ስብከቶች ✝️መንፈሳዊፊ ልሞች ወ.ዘ.ተ ያገኛሉ።
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes
https://www.tgoop.com/addlist/A7U6XVGLALJlNjI0
https://www.tgoop.com/addlist/A7U6XVGLALJlNjI0
https://www.tgoop.com/addlist/A7U6XVGLALJlNjI0
መልካም ዕድል!!!
𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes
https://www.tgoop.com/addlist/A7U6XVGLALJlNjI0
https://www.tgoop.com/addlist/A7U6XVGLALJlNjI0
https://www.tgoop.com/addlist/A7U6XVGLALJlNjI0
ሠኔ ፳ እና ፳፩ በእመቤታችን ስም የተሠራች የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤ/ክ እና ቅዳሴ ቤት የእመቤታችን ፪ኤቱ ክብረ በዓላት ታሪክ
በሠኔ ፳ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በፊልጵስዩስ የተሠራችው ሕንፃ ቤ/ክ ትታሰባለች፤ ይኸውም የቤ/ክ ታሪክ እንደሚያስረዳን ጳውሎስና በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ከተማ ገብተው ባስተማሩ ጊዜ ሕዝቡ “መካነ ጸሎት ለዩልን” ብለዋቸዋል፤ ይኽነንም ለጴጥሮስ በነገሩት ጊዜ ጌታችን የሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን አሠራር እንዲገልጽላቸው ሱባዔ ገቡ፤ ሱባዔውም ሲፈጸም ጌታ ሐዋርያትን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፨
“በናቴ ስም አብያተ ክርስቲያናት ሊታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ላሳያችኊ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናትን ላስተምራችኊ ሰብስቤያችኋለኊ” ብሏቸው፤ ወደ ምሥራቅ አገር ይዟቸው ወጣ፤ በዚያ በምሥራቅ ሀገር ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ ተራርቀው የነበሩትን አቀራረባቸው፤ ጥቃቅን የነበሩትን ታላላቅ አደረጋቸው፤ ቁመቱን ወርዱን ለክቶ ሰጣቸው፤ ቁመቱ 24 ወርዱ 12 ክንድ ነው፡፡
፳፬ቱ የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ ፲፪ቱ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፤ ከዚኽ በኋላ ሥራ ጀመሩ፤ ሲሠሩትም ሰም እሳት ሲያሳዩት እንዲለመልም በእጃቸው ላይ እየተሳበ ሠርተው ፈጽመውታል፤ ይኽ የኾነ እመቤታችን ባረገች በአራተኛው ዓመት በሠኔ ፳ ቀን ነው፨
በሠኔ ፳፩ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ መጣ፤ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋያትን ልኡካን አድርጎ፤ ጌታ ዐቢይ ካህን ኾኖ ቀድሶ አቊርቧቸዋል፤ ከዚያም “እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ” (ከእንግዲኽ ወዲኽ እናንተ እንዲኽ ሥሩ) ብሎ አዝዟቸው ዐርጓል፤ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረ በቅድስት ድንግል ስም ነው፡፡
ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው ፫ ከላይ ሕንፃቸው ፩ ነው ይኽም የአንድነታቸው የሦስትነተኛው አምሳል ነው፤
አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፡-
“በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ
ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ
አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ
እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ
ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ
ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ”
(ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራት ከፈጸመ በኋላ፤ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግል በከበሮ ምስጋናን አቀረቡ) በማለት ገልጸዋል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯ በሰማያት አምሳል እንደኾነ ሊቃውንት ይተነትናሉ፤ ይኸውም የመጀመሪያዋ ሰማይ “ጽርሐ አርያም” ስትባል ከእሳት ብርሃኗን ነሥቶ ከብርሃን ብርሃንን ጠምቆ አጥርቶ፤ ኹለንተናዋን በብርሃን ቀለም ሸልሟታል “አልቦ ሰማይ ዘይጼልል ላዕሌሃ እስመ መልዕልታዊት ወጽንፋዊት ይእቲ ወኲለንታሃ ብርሃን ፍጹም ዘኢይትነገር በልሳነ ኲሉ ፍጡር ወኲሎሙ ብርሃናት አምሳለ ቀለምጺጸ እሳት በኀቤሃ” ይላል ፤ ብርሃኗን ማንም ከቶ ሊገልጸው አይችልም፤ ከርሷ ብርሃን አንጻር ሲታዩ ሌሎቹ ብርሃናት የእሳት ፍንጣሪ ያኽላሉ፤ ከሰማይ ኹሉ በላይ ስትኾን ከርሷ በላይ ምንም ሰማይ የለም፤ ከዚኽ የተነሣ “ሰማየ ሰማያት” ትባላለች (ዘዳ ፲፥፲፬፤ ፩ነገ ፰፥፳፯)፡፡
ምሳሌነቷን ሊቃውንት በመጽሐፈ ቅዳሴ መቅድም ላይ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ስለመሠራቱ ሲተነትኑ በጽርሐ አርያም ውስጥ መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን፣ አራቱ ጸወርተ መንበር፣ ኻያ አራቱ ዐጠንተ መንበር ይኖራሉ፤ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፤ መንበረ ብርሃን የመንበር፤ ታቦተ ብርሃን የታቦት፤ መንጦላዕተ ብርሃን የመንጦላዕት፤ አራቱ ጸወርተ መንበር የአራቱ ሊቃነ ጳጳሳት፤ ፳፬ቱ ዐጠንተ መንበር የጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል ናቸው፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ሰዓታቱ ላይም “ወኊልቈሙ ለእሙንቱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት... ወቡርክት ዛቲ ቤተ ክርስቲያን እንተ አሕዛብ ትመስል ኀይለ ሰማያት” (የእነዚኽ መላእክት የመላእክት አለቆች ቊጥርም መናብርትና ሥልጣናት፣ አጋዕዝትና ኀይላት፣ ሊቃናት፣ ኪሩቤልና ሱራፌል ነው፤ እየጮኹም እንዲኽ ይላሉ የእስራኤል አምላክ ይመስገን የሕዝቡ የአሕዛቡ የምትኾን የተባረከች ቤተ ክርስቲያን የሰማያት ኀይልን ትመስላለች) ይላል፡፡
ሊቁ ሰራዊተ መላእክትን በሚያመሰግንበት በዚኽ ክፍል ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯና እና አከፋፈሏ በመላእክት ከተማ እና በአሰፋፈራቸው ልክ የተመሰለች መኾኗን አስረግጦ አስተምሯል፡- ይኸውም ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች (መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌት) የሦስቱ ዓለመ መላእክት ምሳሌ ሲኾን ይኸውም መቅደስ የኢዮር፤ ቅድስት የራማ፤ ቅኔ ማሕሌት የኤረር ምሳሌ ናቸው፡፡
ኢዮር በተባለችው ሰማይ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኀይላት ይኖራሉ፡፡ ራማ በተባለችው ሰማይ አርባብ፣ መናብርት፣ ሥልጣናት ይኖራሉ፡፡ ኤረር በተባለችው ሰማይ ሊቃናት፣ መኳንንት፣ መላእክት ይኖራሉ፡፡ እነዚኽ 9ኙ ነገድ የ፱ቱ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን አምሳል ናቸው፡፡
ይኸውም በኢዮር ከሚኖሩት መላእክት ውስጥ ኪሩቤል የሊቃነ ጳጳሳት፤ ሱራፌል የጳጳሳት፤ ኀይላት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል፡፡
በራማ ሰማይ ከሚኖሩት ነገደ መላእክት ውስጥ አርባብ የቆሞሳት፤ መናብርት የቀሳውስት፤ ሥልጣናት የዲያቆናት አምሳል፡፡
በኤረር ሰማይ ከሚኖሩት ነገደ መላእክት ውስጥ ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፤ መኳንንት የአናጒንስጢሳውያን፤ መላእክት የመዘምራን አምሳል ናቸው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ስለ ክብረ ቤተ ክርስቲያን፦
✍️ “እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ ወተቀደሰት በደሙ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጊሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ” (በስሙ ታነጸች፤ በደሙም ከበረች፤ በዕፀ መስቀሉም ተባረከች፤ ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ኺዱ የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና) ይላል፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ተአምኆ ቅዱሳን በሚባለው ታላቅ መጽሐፉ ላይ፡-
“ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ” (የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፡፡
ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ መልኩ እናትነቷን በሰባቱ ጊዜያት የሕማማት ሰላምታው ላይ፡-
“ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ ዘትጼንዊ መጽርየ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ
ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ”
(እንደ ቀጋ የምትሸትቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኊ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል)
“በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ
ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ”
(ሰላምታ የተገባሽ እናታችን ቤ/ክ ሰላም ሰላም እንልሻለን፤ በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ፤ ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ፤ ልመናሽም ከእኛ ጋራ ይኹን) በማለት እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አወድሷል፡፡
በተጨማሪም ሠኔ ፳፩ ቀን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ ቃል ኪዳን መቀበሏም ይታሰባል።
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በረከት ይደርብን፡፡
በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ