Telegram Web
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረመዷንን መድረስ ትልቅ ኒዕማ ነው!!

ጠለሃ ኢብኑ ዑበይደላህ ረድየላሁዐንሁ እንዳስተላለፉት፦

ሁለት ሰዎች ወደ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይመጡና በተመሳሳይ ሰዓት ኢስላምን ይቀበላሉ።
አንደኛው ዒባዳ ላይ በጣም የተበራታ ሲሆን ደግሞ ሌላኛው ደግሞ ጅሃድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ፤ እናም አንድ ቀን ጅሀድ ላይ ይገደልና ሸሂድ ይሆናል ፤ አንደኛው እርሱ ሌላኛው ከሞተ ከአንድ ዓመት በኋላ ይሞታል።

ጠለሃ እንዲህ ይላል፦ "አንድ ቀን በህልሜ ከነዚህ ሁለት ሰዎች ጋር በጀነት በር ላይ ቆሜ ነበር ፤ አንድ ነገር ከበሩ ይወጠና ከመጀመሪያው ሟች ቀጥሎ የሞተውን ሰው ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ድጋሚ ይመጣና መጀመሪያ የሞተውን ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ወደኔ ዞር ብሎ ‘ አንተ ሂድ ተመለስ ያንተ ጊዜ ገና ነው ’ አለኝ።
ጠለሃ ከዕንቅልፉ እንደተነሳ ስላየው ህልም ለሰዎች ይነግራቸውና ሰዎቹም ይገረማሉ ፤ እናም ይህ ወሬ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር ይደርሳል ፤ እሳቸውም ሰዎቹን "ምንድ ነው ያሰደነቃቹ?" ብለው ይጠይቃሉ።
ሰዎቹም አንደኛው ጅሀድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ሸሂድ ሆኗልም ነገር ግን ቅድሚያ ጀነትን እንዲገባ የተደረገው ቀጥሎ የሞተው ነው።"አሏቸው
የአላህ መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፤ " ቀድሞ ጀነትን የገባው ሰው ከመጀመሪያው አንድን ዓመት በሕይወት አልቆየምን?" ሰዎቹም አዎን ሲሉ መለሱ፦
የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ አለህሂ ወሰለም ፡ " ረመዳንን አላገኘምን?
አልፆመምን? ፤

ይሄን   ይሄን ያክል ሰላት አልሰገደምን ?"
ሰዎቹም አዎን አሉ።
የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦" ታዲያ በርሱና በዛኛው ሰውዬ መካከል የሰማይና የምድር ያክል በላይ ልዩነት አለ" አሏቸው።》
📚ኢብን ማጃህ (2/344,346)፤ ሸኽ አልባኒ በሲልሲላ አ‘ሰሂሃ ሰሂህ ብለውታል።
📃የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር

ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-

“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”

ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-

"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።

ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"

ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።

ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።

ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"

አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!

#ዝክረ_ረመዳን
_
🔴ሰበር ዜና
የዘንድሮው1446/2025 የረመዳን ወር ጨረቃ በሳውዲ አረቢያ ታይቷል!

በዚህም መሰረት ነገ ቅዳሜ ረመዳን 1 ይሆናል።

የተራዊህ ሰላት ከኢሻ ሶላት በኋላ በሁለቱ ሀረመይን መስጂዶች ይጀመራል።
እንኳን ለረመዳን በሰላም አደረሳችሁ
አላህ ይቀበልን፤ ይቀበላችሁ!!

تقبل الله صيامكم وصالح أعمالكم 🌙
Audio
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ

🎙 خطبة الجمعة
رمضان شهر القرآن

❗️
ረመዷን የቁርኣን
ወር!

🕌 ጎተራ ፈትህ 54 መስጂድ

🗓 ሸዕባን 28/1446 አ/ሂ

http://www.tgoop.com/sultan_54
የረመዳን የኢፍጣር ፓኬጅ

"ፆመኛን ያስፈጠረ ከፆመኛው ሳይቀነስ ለርሱም እኩል ምንዳ ይኖረዋል"

ለ1 ቤተሰብ 5,ዐዐዐ ብር ብቻ

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
1000461657455

ለበለጠ መረጃ፦
📱+251969437984

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
www.tgoop.com/merkezuna
وَالْعَصْرِ (1) إِنَّ الْإِنْسَانَ لَفِي خُسْرٍ (2) إِلَّا الَّذِينَ آَمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ (3)

«(1) በዘመን እምላለሁ፡፡ (2) ሰው ሁሉ በእርግጥ በክስረት ውስጥ ነው፡፡ (3) እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም ላይ አደራ የተባባሉት፣ በትእግስትም ላይ አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡»
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከተዘነጉ ሱናዎች ውስጥ

ከኡበይ ኢብኑ ከዕብ ተይዞ እንዲህ ይላል፦

﴿كان رسولُ اللهِ ﷺ إذا سلَّم من الوِترِ قال سُبحانَ الملِكِ القدُّوسِ ثلاثَ مرّاتٍ يرفعُ في الثّالثةِ صوتَه.﴾

“የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የዊትር ሰላትን በጨረሱ ግዜ  ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ሶስት ግዜ እንዲህ ይሉ ነበር፦ ‘ሱብሐነል መሊከል ቁዱስ’”

📚 ነሳዒ ሶሂህ ብለውታል: 1750
ረመዳን ሙባረክ!!
እንኳን ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ። አላህ  ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ መልካም የዒባዳ ግዜ እዲያደርገው እንለምነዋለን፡፡
ጾም እና ቁርኣን የቂያማ ቀን አማላጅ ይሆናሉ።
ጃዕፈር ኢቢኑ ሙሐመድ እንዲህ ብለዋል።

"የሚያከብርህ ሁሉ አክብር፣ አንተን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ከእሱ በመራቅ ራስህን አክብር።"

📚 ረውደቱ አል-ዑቀላእ (213)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
كيف أرتب وقتي في رمضان
الشيخ خالد إسماعيل
Audio
🔴 ወሳኝ ትምህርት ለሴቶች!


🎙ሐይድን የተመለከቱ አሕካሞች ከ ሀ እስከ ፐ!


http://www.tgoop.com/sultan_54
2025/03/03 19:50:14
Back to Top
HTML Embed Code: