Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
3942 - Telegram Web
Telegram Web
Audio
  የተዳሰሱበት ነጥቦች

📌 ዊትር ሰላት ዋጂብ ነው ወይንስ ሱና

📌 የነብዩ ወሲያ መሆኑ

📌 የዊትር ሰላት ወቅቱ ከምን እስከምን እንደሆነ እንዲሁም በላጩ ወቅት የቱ እንደሆነ

📌 እንዴት እንደሚሰገድና የረካአዎቹ ብዛት

📌 እንዲሁም ስለ ቁኑትም በሰፊው ተብራርቷል
                     ይደመጥ

         🎙በውዱ ኡስታዛችን
ኡስታዝ አቡ ኢልሀም ሙሀመድ ኑር
                             حفظه الله

       🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
        ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞
https://www.tgoop.com/sunah123
በረመዷን ወቅት ቁርአን መቅራት

شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ. البقرة: ١٨٥
ረመዷን ቁርአን ለሰው ልጆች እንደ መመረያ፤ (በእውነትና በውሸት መካከል) መለያ እና ግልፅ መመሪያና ማስረጃ ሆኖ የወረደበት ወር ነው። {አል-ቁርአን 2:185}
ሙሉ የረመዷን ወር ከሌሎች ኢባዳዎች ጋር ቁርአን በመቅራት ልናሳልፈው ይገባል። አሏህ በሱረቱ ሉቅማን አንቀፅ 3 ላይ እንደገለፀው ቁርአን “ለመልካም ሰሪዎች መመሪያና እዝነት ነው።” ቁርአን ህይወት ፣ ሸፈአ ፣ ደስታ ፣ ምንዳ ፣ እዝነት ፣ መድሃኒት ፣ መለኮዊ አስተምህሮት ፣ ከህግም በላይ ህግ የሆነ ዘላለማዊ ጥበብ ነው።
በቡኻሪ በተዘገበ ሐዲስ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ቁርአን አንብቡ በእርግጥ በፍርዱ ቀን ሸፈአ(አማላጅ) ይሆንላችኋልና ብለዋል።
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በመጨረሻ አመታቸው ረመዷን ውስጥ ሁለት ጊዜ አክትመዋል። እኛ ሙስሊሞችም የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ በመከተል በረመዷን ወቅት ቢያንስ አንድ ጊዜ ማኽተም ይኖርብናል።
ይሁንእንጅ በአሁኑ ወቅት አብዛሃኛዎቻችን ቁርአን የምንቀራው በረመዷን ብቻ እየሆነ ነው። ይባስ ብሎ ለማክተም የሚደረግው ጥረት የተራዊህ ወይም የተሃጁድ ሶላት ላይ ነው። በተራዊህ ሶላት ለማኽተም ሩጫ ነው። በእርግጥ ይህ ተግባር የቁርአን አስተህሮትን ይቃረናል። ምክኒያቱም አሏሁ አዘወጀል “ቁርአንን በዝግታ አንብብ” ብሏል (73:4)።

ኢብን ከሲር ይህን የቁአን አንቀፅ ሲያብራሩ ይህ ማለት ቁርአንን ለመረዳትና ለማስተንተን ይረዳህ ዘንድ ቀስ ብለህ ቅራ ማለት ነው። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ይቀሩ የነበረውም እንዲህ ነው ሲሉ አብራርተዋል። ሆኖም ቁርአን ስንቀራ ወይም በረመዷን ለማኽተም ስንጥር ይህን የቁርአን አያ ተከትለን መሆን ይኖርበታል። የበለጠ ወደ አሏህ ለመቅረብ ስንቀራ እያስተነተን እና ተረድተነው ይሁን። ቁርአን ማንበብ የማንችል ሰዎች እያንዳንዷን ቀን በሲዲ የተቀረፀ ቁርአን ለማዳመጥ እንሞክር። ወይም ደግሞ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን የተተረጎመ ቁርአን በማንበብ ማሳለፍ ይኖርብናል።
https://www.tgoop.com/sunah123
Audio
የጁምአ ኹጥባ ቀደም ሲል የተደረገ
خطبة الجمعة

📌የኹጥባዉ ርዕስ የረመዳን ትሩፋት

📌فضل رمضان

#ብዙ ጠቃሚ ነገሮች ተወስቶበታል

# ረመዳን ሲመጣ ሰዎች በ 3 አይነት አቀባበል ይቀበላሉ?

#እነ ማን ይደሰታሉ?

#እነ ማን ይከፋሉ

ይደመጥ👂ይደመጥ👂ይደመጥ👂

🎙በኡስታዝ ሙሐመድ ኑር ሀፊዞሁላህ

https://www.tgoop.com/sunah123
https://www.tgoop.com/sunah123
Audio
የረመዳን ስህተቶችን እና ቢድዓዎችን ተጠንቀቅ በሚል የተደረገ ሙሃደራ


ይደመጥ 👂ይደመጥ👂ይደመጥ👂
ወሳኝ ትምህርት ነው እኛ ቀለል አድርገን የምናያቸው በሸሪዓ እይታ ግን ትክክል  ያልሆኑ



በኡስታዝ ሙሀመድ ኑር
https://www.tgoop.com/sunah123
አሏህን የመፍራት ወር

ረመዷን 11 ወር ሙሉ ስሜቱንና መጥፎ ምኞቱን ተከትሎ ለኖረ ሰው ሁሉ ልጎም ፣ ለመልካም ሰሪዎች በረካ ሲሆን አዲስ የለውጥ ቤዛ ነው። ታዲያ ፆምን ፆም የሚያደርገው የምግብና የመጠጥ ተአቅቦ ብቻ ሳይሆን አሏህ የከለከላቸውን ነገሮች ሁሉ በመከልከል ያዘዛቸውን ነገሮች በመታዘዝ መልካም ነገሮችን መስራት ነው። ፆም.....በእናንተ ላይ ተደነገገ አሏህን ትፈሩ ዘንድ (2:183)።
ይህን ላደረገ ሰው ሲሳዩ በዱንያም በአሂራም ይሰፋል፤ እንከኖቹን አስወግዶ እራሱን በኢስላም ድስፕሊን በማነፅ የለውጥ ምሳሌ መሆን ይችላል። በረመዷን ወቅት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከሌላው ጊዜ በበለጠ በኢባዳ ይተጉ ነበር።

⚡️⚡️ረመዷን: አሏህን የመፍራት ወር

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ. البقرة: ١٨٣
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ትፈሩ ዘንድ ፆም ከእናንተ በፊት በነበሩ ህዝቦች ላይ እንተደነገገው ሁሉ በእናንተም ላይ ተደነገገ። {አል-ቁርአን 2፡183}
ምስጋና ለሃያሉ አሏህ ይገባው። እናመሰግነዋለን ፣ እርዳታውን እንሻለን ፣ ምህተቱን እንለምናለን። ነፍሳችን ውስጥ ካለ ክፋትና ከወንጀል ስራዎቻችን ሁሉ በአሏህ እንጠበቃለን። አሏህ የመራውን ማንም አያጠምም፤ አሏህ ያጠመመውንም ማንም አይመራም። ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ አለመኖሩንና ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ ባርያና መልዕክተኛ መሆናቸውን እንመሰክራለን።
ረመዷን ከአምስቱ የኢስላም ምሶሶዎች አንዱ ሲሆን በሙስሊሞች የቀናት አቆጣጠር ደግሞ ዘጠንኛው ወር ነው። ሆኖም ይህን ወር አሏህ ቀን ላይ መፆምን ግዴታ ምሽት ላይ ደግሞ የተራዊህ ሶላትን ሱና አድርጎታል። የፆም ትርጉሙ መቆጠብ ሲሆን ከንጋት ጀምሮ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ከመብላት ፣ ከመጠጣት ፣ ከግብረስጋ ግኑኝነት ፣ ከእንቶፈንቶ ወሬ ፣ ከማጨስ ፣ ከሃራም ነገሮች ሀሉ መቆጠብ ነው።
አል-ቡኻሪ ጥራዝ 3 መጽሐፍ 31 የሐ.ቁ 120
ነብዪ(ሰ.ዐ.ወ) ጀነት ውስጥ ረያን ተብሎ የሚጠራ በር አለ። በትንሳኤ ቀን ፆመኞች በእሱ በኩል የሚገቡ ሲሆን እነሱ እንጅ ከነሱ ውጭ ማንም አይገባም ብለዋል።
በረመዷን ወቅት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከሌላው ወር በበለጠ በኢባዳ ይተጉ ነበር። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ቀኑን አሏህን በማስታወስ በዚክር ፣ በቂርአት ፣ በመማር ፣ ምክርና ትምህርት በመስጠት ያሳልፉ የነበረ ሲሆን ሌሊቱን ደግሞ ዱአ በማድረግ ፣ እራሳችነን ወደ አሏህ በማተናነስ በቂያመለይል ፣ እርዳታውን ፣ መመሪያውንና ድሉን በመሻት ያሳልፉ ነበር።
አል-ቡኻሪ ጥራዝ 3 መጽሐፍ 31 የሐ.ቁ 118
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አሏህ(ሱ.ወ.ተ) የሰው ልጅ የሚሰራው ሁሉም ስራ ለራሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለእኔ ነው። እኔ ምንዳውን እስጣለሁ። የመልካም ስራዎች ምንዳ አስር እጥፍ ነው
ረመዷን ለአሏህ ብለን የምንሰራቸውን ስራዎች የምናድስበትና የበለጠ መልካም ስራዎችን ለመስራት እራሳችነን የምናነቃቃበት አመታዊ የስልጠና ፕሮግራም ነው። ፆም እራስን መቆጣጠር ያዳብራል። እንዲሁም እራስወዳድነትን ፣ ስግብግብነትን ፣ ስስታምነትን ፣ ስንፍናን እና ሌሎች ስህተቶቻችነን ሁሉ እንድንቀርፍ ይረዳናል። ይህ የትዕግስት ወር ርሃብ ወይም ችግር ምን ማለት እንደሆነ የምናውቅበት እድል ሲሆን ለድሆች ወይም ለምስኪኖች ያለንን አመለካከት በደግነት የተሞላ እንዲሆን ያደርጋል። እንዲሁም ፆም ለምቾትና ለድሎት ያለንን ውዴታ እንድንቆጣጠር ያስተምረናል።
ይሁንና እየፆምን በጣም ቢደክመን በደስታ መቋቋም ወይም መታገስ እንጅ ማማረር አይኖርብንም። እንዲሁ በተራዊህ ሶላት ወቅት ድካም ቢሰማን ይህንንም በፅናት ልንቋቋመው ይገባል።
እዚህ ላይ ልብ ልንለው (ልናስተውለው) የሚገባ ነገር ቢኖር የፆም አላማው ሰዎችን ማስቸገር ወይም በእነሱ ላይ ጉዳት ማድረስ ወይም ደግሞ የማይቋቋሙትን ሸህም መጫን ሳይሆን ለሃያሉ አሏህ ትዕዛዛት እምቢተኝነትን የምናሳይባቸው ወንጀሎች ወይም ፈተናዎች ከቁጥጥራችን ውጭ እንዳይሆኑ ወይም ደግሞ እኛ የሰው ልጆች የስሜታችን ባሪያ እንዳንሆን ወሰጢያን (መካከለኛነትን) እና መንፈሳዊ ስርአት የምንማርበት ፣ የአሏህን ረህማ በማግኘት ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ዳግም የምንመለስበት ስለሆነ ነው። እውነተኛ የአሏህ ባሪያ ለመሆን ባህሪያችን እና መንፈሳዊ ስርአታችን በሸሪአ ከተገለፀው ጋር ሊገጥም ይገባል። ሆኖም ፆም ለባህሪ ፣ ለስብዕናና ለመንፈሳዊ ስልጠና እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።
በሙስሊም በተዘገበው ሐዲስ መሰረት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የረመዷን ወር በጀመረ ጊዜ የእዝነት በሮች (የጀነት በሮች) ይከፈታሉ። የጀሃሐነም በሮች ይቆለፋሉ፤ ሸይጧኖችም ይታሰራሉ ብለዋል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: ((قال الله عز وجل: كلُّ عملِ ابن آدمَ له إلا الصيام؛ فإنه لي وأنا أجزي به، والصيام جُنَّة، وإذا كان يومُ صومِ أحدكم، فلا يرفُثْ ولا يصخَبْ، فإن سابَّه أحدٌ أو قاتَله، فليَقُلْ: إني امرؤ صائم، والذي نفسُ محمد بيده، لخُلُوفُ فمِ الصائم أطيبُ عند الله من ريح المسك، للصائمِ فرحتانِ يفرحهما: إذا أفطر فرِح، وإذا لقِي ربه فرح بصومه)) متفق عليه
በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ ደግሞ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ፆም ጋሻ ነው (ከሃራም ነገሮች፤ ከወንጀሎች መጠበቂያ ነው)። እናም ፆመኛ ሰው ከሚስቱ ጋር ያለውን የወሲብ ግንኙነት ፣ ንትርክንና ጭቅጭቅን ያስወግድ። የሆነ ሰው ቢጣላው ወይም ቢሰድበው ፆመኛ ነኝ ይበል። ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ ከአሏህ ዘንድ የሚፆም ሰው አፍ ሽታ ከሚስክ ሽታ በላይ የተወደደ ነው። የሚፆም ሰው ሁለት የደስታ ጊዜያቶች አሉት። አንደኛው ፆሙን በፈታ ጊዜ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጌታውን በሚገናኝ ጊዜ ነው። እናም በመፆሙ ምክኒያት ይደሰታል ብለዋል።
ሰዎች ከረመዷን ውጭ ባሉ ወራቶች የሚፈፅሟቸውን መጥፎ ነገሮች በዚህ ወር አመፀኛው ሸይጧን እንዳይቀሰቅስባቸው ተጠፍሮ ይታሰራል። ታዲያ እዚህ ላይ ሸይጧን ተጠፍሮ ከታሰረ ለምን መጥፎ ነገሮች ወይም ወንጀሎች ይፈፀማሉ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። መልሱም መጥፎ ነገር በአመፀኛው ሸይጧን ምክኒያት ብቻ የሚፈጠር አይደለም። ሰዎች ለአስራ አንድ ወር ለሸይጧን ፣ ለስሜታቸው እና ለምኞታቸው ታዛዦች ሆነው ኑረዋል። ሆኖም ሸይጧን ቢታሰርም ፆመኛው ስሜቱንና መጥፎ ምኞቱን በኢማን በተቅዋ እስካለጎማቸው ድረስ መጥፎ ስራዎችን መስራቱ አይቀሬ ነው። ስለዚህ መጥፎ ነገር ሁሌም በረመዷን ውስጥም ሆነ ከረመዷን ውጭ ይፈፀማል።
ፆም ወደ አሏህ ፍራቻ የሚያደርስ መንገድ ነው። በቁርአን ውስጥ መፆም በእኛ ላይ የተደነገገው ተቅዋ (የአሏህ ፍራቻ) ይኖረን ዘንድ እንደሆነ ተገልፃል። በእርግጥ ይህ ተቅዋ በረመዷን ወቅት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ይጎለብታል። ዋናው ነገር ግን በዚህ ወር ያገኘነውን መንፈስና ትምህርት አመቱን ሙሉ እኛ ጋር እንዲቆይ ለማድረግ መጣር ነው። ሁላችነም ይህ ስሜት ወይም መንፈስ ከረመዷን ውጭ ባለው ህይወታችነም እኛ ጋር እንዲኖር መጣርና መታገል ይኖርብናል። በእርግጥም ትልቁ የረመዷን ግብና ፈተና ይህ ነው።
በሙስሊም በተዘገበው ሐዲስ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በአሏህ መንገድ ለሚፆም ማንኛውም የአሏህ ባሪያ በዚህ ቀን ምክኒያት አሏህ ፊቱን ሰባ አመት የሚያክል እርቀት ያህል ከጀሃንም እሳት ያርቅለታል ብለዋል።
ፆም የምግብና የደም ባንቧን ያጠባል። እነሱም የሸይጧን ቦዮች እንደሆኑ ይታወቃል። ይሁንና ፆም በጥጋበኝነት የሚፈፀም ወንጀልን ፣ ስጋዊ ስሜትንና ሃሳብን ፣ የእንቢተኝነትንና የትዕቢተኝነት ስሜት ያደክማል።
ፆም አካላዊ ጤናን ይጨምራል። ቆሻሻን ወይም የተመረዙ ነገሮችን ከአካላችን በማስወገድ ሆድን ያቀላል ፣ ደም ያጠራል ፣ የልብ አሰራርን የተስተካከለ ያደርጋል ፣ መንፈስን ያድሳል ፣ ስብዕናን ይቀርፃል። በፆምን ጊዜ ነፍሳችን የተነሳሳች ትሁት ትሆናለች፤ ስጋዊ ስሜታችነም ይወገዳል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ፆም ለአሏህ ትዕዛዝ ያለንን ታዛዥነት እና ባርነት የምናሳይበት እንደመሆኑ መጠን ትልቅ ምንዳ አለው።

https://www.tgoop.com/sunah123
Audio
ይደመጥ👂ይደመጥ👂

ወሳኝ ትምህርት ነው ሳታዳምጡ እንዳታልፉ
⚡️በዚች አለም ውስጥ ካሉት ነገሮች ሁሉ ጣፋጩ ተውሂድ ስለመሆኑ
⚡️ተውሂድ የሁለት ሀገር እርካታ ስለመሆኑ
⚡️ተቃራኒው ሽርክ ምንኛ አስከፊ እንደሆነ
⚡️ተዉሂድ አላህ ከባሮቹ የሚፈልገው አላማ ስለመሆኑ
⚡️እና ሌሎችም ነገሮች ተዳሰውበታል።
https://www.tgoop.com/sunah123
Forwarded from አብ አብደላ መደሲር
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ 
        
         🌿🌿አስቸኳይ የብስራት ዜና!🌿🌿

    👌  የተከበራችሁ በአዲስ አበባ ከተማ እና በአካባቢው የምትገኙ ሰለፍዮች በሙሉ
           እነሆ የፊታችን እሁድ ቀን 30/06/17 ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ዙሑር ሶላት ድረስ በአይነቱ ልዩ የሆነ ወርሃዊ የሙሀደራ ፕሮግራም  በቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ ስለተዘጋጀ እርሰዎን ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በአክብሮት ጋብዘንዎታል።

   ተጋባዥ እንግዶች
➊ ኡስታዝ አቡ ኡበይድ ባሀሩ ተካ
➋ ኡስታዝ አቡ ሀመውያ ሸምሱ ጉልታ

በተጨማሪ ሎሎችም ኡስታዞች የሚገኙ ይሆናል፡፡

👉  ይህ ፕሮግራም እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል !!!

🍀 ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር
ነው !!!

አዘጋጅ ፦ የቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ ጀመዓ

🕌 🕌 አድራሻ፦ ካራ ቆሬ ታክሲ መጨረሻ ወደ ባማ ሆስፒታል በሚወስደው ቅያስ 500 ሜትር ዝቅ ብሎ

ለበለጠ መረጃ፦ 0921566720
                       
0944189541

     " እውቀት መፈለግ በእያንዳንዱ ሙስሊም ወንድ እና ሙስሊም ሴት ላይ ግዴታ ነው"

https://www.tgoop.com/bilalibnurebahmedresa
https://www.tgoop.com/bilalibnurebahmedresa
https://www.tgoop.com/bilalibnurebahmedresa
2025/03/13 15:12:18

❌Photos not found?❌Click here to update cache.


Back to Top
HTML Embed Code: