❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለአዳም ለዘር ሁሉ ድኅነት ለተደረገባት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በስሟ የተሰራችው የመጀመርያ ቤተ ክርስቲያን በልጇ በወዳጇ እጅ ለተቀደሰችበት ለከበረችበት ዓመታዊ በዓሏና በዓለም ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል፣ እመቤታችን ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ለተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ለነገረችውና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ላደረገች፣ ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ በዓል፣ ለምስር አገር ለሆነ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለእስክድርያ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ከላድያኖስ ለዕረፍት በሰላም በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ሜሮን ከተገኘችበትና የአስታፍን ዐፅም ከተገኘችበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ፦ ሃሌ ሉያ "ተቀደሲ ወንሥኢ ኃይለ ኦ ቤተ እግዚአብሔር እስመ ናሁ ንጉሥኪ በጽሐ ዘያበርህ ለኪ በኃይሉ ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሐነፃ ወልድ ለዛቲ ቤት ወፈፀማ መንፈስ ቅዱስ። ትርጉም፡- የእግዚአብሔር ሆይ ቤተ ሆይ ተቀደሺ (ተከበሪ) ኃይልንም ውሰጂ (አድርጊ) እነሆ በኃይ የሚበራልሽ ንጉሥሽ ደረሰ፤ ይኽቺን ቤት አብ አስቀድሞ መሠረታት፤ ይኽቺንም ቤት ወልድ አነጻት (ሠራት) ፈጸማት (ጨረሳት)። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች።
❤ ይኸውም ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ቅዱሳን ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ። ሐዋርያትም እንዲ ብለው መለሱላቸው "ክብር ይግባውና ያለ ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው" እንዲህም አዘዙአቸው።
❤ በሱባኤውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾላቸው ሐዋርያትም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዩስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ቅዱሳን ጳውሎስና በርባስ ነበሩ ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲናት እንዲታነፁ የፈቀድኩባት ናት"። ይህንንም ብሎ በከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኵል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈጸመ ድረስ ሦስቱ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበር ጌታችንም ንዋየ ቅዱሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ።
❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን እጁን በቅዱስ ጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማዕዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም ሊቀ ጳጳሳት ማለት ነው "ለሐዋርያት አለቃ ለቅዱስ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል" እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ።
❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ መድኃኒታችን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው "በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው"። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያች ቀን ጀምሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያንሳንፁ ሆኑ።
+ + +
❤ በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በአባ ባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።
❤ ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ፤ ባለጸጋውም "ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው" አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና ዕንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት። ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዒሊ ሰጠው።
❤ እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛም ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።
❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳችው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው። ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ ጠበል አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ። እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ዘር በሃያ አንድ ቀን ነው።
❤ በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም "ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ" አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

❤ እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኞች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል ስለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሁኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው። እርሷን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እንድትወልደው ላደረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእርሷ በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ከምስር አገር የሆነ ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፦ ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራዎች ውስጥ ነበር ሰው ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልክ የሚያዝ የዲዮቅልጥያኖስ የመልእክት ደብዳቤ በተነበበ ጊዜ ይህም ቅዱስ ከሕዝቡ መካከል ተነሥቶ የንጉሡን ደብዳቤ ወስዶ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ የከሀዲውን ንጉሥ የመልክት ደብዳቤ ቀደደ።
❤ መኰንኑም ድፍረቱን አይቶ ወደርሱ ገሥግሦ ሔደና የራሱን ጠጉር ይዞ አንሥቶ በምድር ላይ ጣለው ታላቅ ድብደባም እንዲደበድቡት አዘዘ ሁለተኛም ሁለመናው እስቲደቅ እንዲደቁሱት አዘዘ እርሱም "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እርዳኝ" እያለ ይጮኽ ነበር። ጌታችንም ትዕግሥቱን አይቶ መልአኩን ልኮ ከሥቃዩ አድኖ ጤነኛ አደረገው ወደ መኰንኑም ቀርቦ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለምና አንተ ከሀዲ እፈር" አለው። ያን ጊዜም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው በመጋዝም መግዞ ሰቀለው ከዚያም በኋላ ሥጋው እንደ ሰም ቀልጦ እንደ ውኃ እስቲፈስ በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰለው ከከተማ ውጪም ጣሉት።
❤ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለምንም ጉዳት አንሥቶ ጤነኛ አደረገው። ወደ መኰንኑም ተመልሶ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለምና አንተ ከሀዲ እፈር" ብሎ ጮኸ። ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው ቁጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።
❤ መኰንኑም ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ሰኔ 21 ቀን ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። የድል አድራጊነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በድል አድራጊ ሰማዕት በቅዱስ ጢሞቴዎስ አማላጅነት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የእስክንድር አራተኛ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ፦ ይህም ቅዱስ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠምቀ እርሱም ዲቁናን ሾመው ደግሞም ቅስና ሾመው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርትና ሕግ ጠንቅቆ ተማረ።
❤ አባ ሜልዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ዐሥራ አንድ ዓመት ያህል በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው በትምህርት በምክር ሁሉ እንደሚገባ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ። ልዑል እግዚአብሔርም አገልግሎ ሰኔ 21 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ከላድያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 21 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወንሰግድ ውስተ መካነ ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ። ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ። አንተ ወታቦተ መቅደስከ"። መዝ131፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥39-57።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል። እግዚአብሔር ውስተ ማእከላ ኢትትሀወክ። ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ"። መዝ 44፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፊ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥4-11 እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ16፥13-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://www.tgoop.com/taodocos1221

Telegram
✝️ ታኦዶኮስ ✝️
ታኦዶኮስ ማለት -ቃሉ የግሪክ (ጽርዕ) ሲሆን ትርጉሙም-- ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ቃል እናት ናት (ሰው የሆነ አምላክ የተገለጠባት) ማለት ሲሆን ይህንንም የተናገረው አምደ ሃይማኖት የሚባለው ቅዱስ ቄርሎስ ነው፤ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ማንኛውም ሀሳብ ወይም አስተያየት በዚህ @taodocos1 ያድርሱን፤ ሊንኩን ሼር በማድረግ የበኩሎዎትን ይወጡ www.tgoop.com/taodocos1221
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሰኔ ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን ለነቢዩ ለሰማዕቱ ለካህኑ ለሐዋርያው ለመጥምቀ መለኮት ለተወለደበት (ለልደት) በዓልና በሕንደኬ ካሉ ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ ለአባ ጌራን ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ማርያና፣ ከማርታ፣ ከመነኰስ ገብረ ክርስቶስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሰምዑ አዝማዲሃ ወሰብአ ቤታ። እስመ አዕበየ እግዚአብሔር ሣህሎ ላዕሌሃ። ወተፈሥሁ ፍሥሃ ፈድፋደ። ወፈቀዱ ይስምይዎ በስመ አቡሁ ዘካርያስ። ወትቤ እሙ ዮሐንስሃ ይሰመይ"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ ነቢይ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ልደት፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው።
❤ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት።
❤ አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።
❤ ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና "ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት" አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።
❤ "የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"።
❤ ራሱ መድኃኒታችንም ስርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።
❤ ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ገድለኛው የሆነ አባ ጌራን፦ ይህም ቅዱስ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር።
❤ ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ ነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጎራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው "የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ከአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ" አለችው። እርሱም "ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ" አላት።
❤ በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ "የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ" አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጎኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋራ ተኝቶ ኃጢአት እደሚሠራ ሆነ። ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ።
❤ ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ድንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች።
❤ ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ጀምሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት።
❤ ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን።
❤ የተባረ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 30ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ። አዕበየ ገቢረ ሎሙ እግዚአብሔር። ወኮነ ፍሡሓነ። መዝ 125፥2፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥76-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወተወከልኩከ እንዘ ሀሎኩ ውስተ አጥባተ እምየ። ላዕሌከ ተገደፍኩ እማኅፀን። እምከርሠ እምየ አንተ አምላኪየ"። መዝ 21፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 7፥14-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 3፥7-10 እና የሐዋ ሥራ 19፥1-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥57-80። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የመጥምቀ መለኮት የልደት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

Forwarded from ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church. (Aschalew Kassaye)
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሐምሌ ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱስ ናትናኤል ለተባለው ለሐዋርያው ስምዖን ቀለዮጳ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክንድርያ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ ከላድያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባት መላእክት ይጎበኙት ለነበረ ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ለነበረ ለአባ ብስንዳ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከምትታሰበው፦ ከሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) አብራ ሰማዕትነት ከተቀበለች ከቅድስት ቴዎና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ መሐሪ ውእቱ ይሁብ ለዘራኢ፤ አዝ፣ ያሠርቅ እክለ ለሲሳይ ያነሥኦ እድ ለነዳይ፤ አዝ፣ ዘየኀይድዎ ሥልጣነኖ ዘይኤዝዝ ትፍሥሕት ለጻድቃኒሁ፤ አዝ፣ ወሠርዐ ሰንበት ለሰብእ ዕረፍተ ገባሬ ሕይወት ያርኁ ክረምተ በበዓመት ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ"። ትርጉም፦ ከዓለም በፊት ክርስቶስ ንጉሥ ነው፣ ክርስቶስ ይቅር ባይ መሐሪ ነው፣ ለዘሪ ዘርን ይሰጣል፣ የተዘራውን ዘር ለምግብ እንዲኾን ፍሬያማ ያደርገዋል፣ ደሀውን ከድህነቱ ያነሣዋል፣ ባለጠጋ ያደርገዋል። ክርስቶስ ንጉሥ ነው ሥልጣኑን የማይቀሙት፣ ለጻድቃን ደስታን የሚያዝ የሚሰጥ፣ እርሱ የሕይወት መገኛ በመሆኑ የፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ለዕረፍት ሠራ፤ ክረምትን በየዓመቱ የሚያመጣ ክርስቶስ ንጉሥ ነው፤ ክርስቶስ ንጉሥ ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ)፦ ይህንንም ሐዋርያ አይሁድ ጌታችንን ወንድም ያዕቆብን ከገደሉት በኋላ ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አድርገው ሐዋርያት ሾሙት። እርሱም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ ከአይሁድ ብዙዎችን ጌታችንን ወደማመን መለሳቸው ተአምራትንም አድርጎአልና በሽተኞችንም አድኗልና።
❤ ንጉሡ እንድርያኖስም ሴቶችን ከባሎታቸው እንደሚለይ ንጽሕናቸውንም እንዲጠብቁ እንደሚአዝዛቸው ስለ እርሱ ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ሐምሌ 10 ቀን እንዲቆርጡ አዘዘ ከእርሱም ጋር ቴዎና የምትባል አንዲት ድንግል ተገደለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁላችንም የክርስቲያን ወገኖች ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ከላድያኖስ፦ ይህም ቅዱስ አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዘጠነኛ የሆነ ነው። በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ መንበር ዐሥራ አራት ዓመት መንጋውን እየጠበቀ ከኖረ በኋላ ሐምሌ 10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ ከላድያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ አባት አባ ብስንዳ፦ ይህም ቅዱስ ጥልቅ በሆነ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቆሞ ሲጋደል ኖረ መላእክትም ይጎበኙትና ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ነበር። ከዚህም በኋላ ሐምሌ 10 ቀን በሰላም ዐረፈ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 10 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ ናትናኤል ዘቃና። እስራኤላዊ ንጹሐ ሕሊና። ሐዋርያ ሐዲስ ሠናየ ርሥእና። በረከተከ ከዐው ለሕዝብከ መንገለ ይትፈቀድ ፍና። ከመ ዝናማተ ይክዑ ደመና"። ሊቁ አርከ ሥሉስጨ(አርኬ) የሐምሌ 10።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ1፥44-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ዘያበቊል ሣዕረ ለእንስሳ። ወሐምልማለ ለቅኔ እጓለ እመሕያው። ከመ ያውፅእ እክለ እምድር"። መዝ 103፥15-16። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 9፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥15-ፍ.ም፣ ግብ፡ ሐዋ 27፥21-33። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥36-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ወይም የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ስምዖን ቀለዮጶ) የዕረፍት በዓልና የአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@sigewe
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
❤ በየቀኑ ፌስቡክ ላይ ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑትና lake አድርጉ።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church.
❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Forwarded from ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church. (Aschalew Kassaye)
#መስከረም_12
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ዐሥራ ሁለት መላእክት አለቃ #የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ #ጉባኤ_ኤፌሶን የቅዱሳን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ ሆነ
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት
መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚችም ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢይ ኢሳይያስ ላከው ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው። ንጉሱም ሚስት አግብቶ ምናሴን እስከወለደው ድረስ እንዲሁ ሆነ።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ለንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገለት ተአምር፡-
ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ዳዊት በኋላ በእስራኤል እንደ ሕዝቅያስ ያለ ሌላ ጻድቅ ንጉሥ አልተነሣም፡፡ ከሕዝቅያስ በኋላ የተነሡት ሁሉም ጣዖትን አምልከዋል፣ ለጣዖታቱም የሚሆን መሠዊያ ሠርተዋል፡፡ ንጉሡ ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ ግን ጣዖታትን ሰባብሯቸዋል፣ የእስራኤል ልጆች ያመልኩት የነበረውን የነሐስ እባብ ቆራርጦታል፡፡ እግዚአብሔርንም በማመኑ መንግሥቱ እጅግ ሰምሮለታል፡፡ እግዚአብሔርም ያሳጣው በጎ ነገርም የለም፡፡
ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዘመን የፋርሱ ነጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ኢየሩሳሌምን ከበባት፡፡ ይህም ሰናክሬም በወቅቱ እንደ እርሱ ያለ ኃይለኛ የለም ነበርና ሁሉም የምድር ነገሥታት ይፈሩትና ይገዙለት ነበር፡፡ ሕዝቅያስም ከሰናክሬም ግርማና የጦሩ ብዛት የተነሣ ፈርቶ ኢየሩሳሌምን እንዳያጠፋት ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ቢልክለትም ሰናክሬም ግን እጅ መንሻውን አልቀበልም ብሎ ኢየሩሳሌምን ያጠፋ ዘንድ ተነሣ፡፡ ለሕዝቅያስም ‹‹አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያደናችሁ ከቶ አይችልም›› የሚል የስድብን ቃል ላከለት፡፡
ሁለተኛም በልዑል እግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ጽፎ ደብዳቤ ላከለት፡፡ ሕዝቅያስም ይህን ሲሰማ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ፡፡ ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ የሰናክሬምን ድፍረትና በኢየሩሳሌምና በሕዝቧ ላይ ሊያደርስ ያሰበውንም ጥፋት ወደ እግዚአብሔር አሳሰበ፡፡ ቀጥሎም ሕዝቅያስ ሰናክሬም የተናገረውን ይነግሩት ዘንድ ስለ ሕዝቡም እንዲጸልይ ለነቢዩ ኢሳይያስ መልእክት ላከበት፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር አመለከተ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ስለ ንጉሡ ለነቢዩ መልእክትን አመጣለት፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም የመጣለትን መልስ እንዲህ ብሎ ለሕዝቅያስ ላከለት፡- ‹‹ልብህን አጽና፣ አትፍራ፡፡ በዓለሙ ሁሉ እንደ እርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ እግዚአብሔር ይሠራል›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ 185,000 (መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) የፋርስ ሠራዊቶችን በአንድ ሌሊት ገደላቸው፡፡ 2ኛ ነገ 17፣19፡፡ የለኪሶ ሰዎችም ሲነጋ በተነሡ ጊዜ ምድሪቱን በእሬሳ ተሞልታ ስላገኟት በድንጋጤና በፍርሃት ከንጉሣ ጋር ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ፡፡
ንጉሡ ሰናክሬምም ወደ አምላኩ ወደ ጣዖቱ ቤት ገብቶ ሲጸልይ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉትና ወደ አራራት ኩበለሉ፡፡2ኛ ነገ ምዕራፍ 19፡፡ ንጉሥ ሕዝቅያስም ከሰናክሬም እጅ ያዳነውን እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ከዚህም በኋላ ሕዝቅያስ ታሞ ለሞት በደረሰ ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹እግዚአብሔር ‹ትሞታለህ እንጂ አትድንም› ብሎሃል›› አለው፡፡ ነገር ግን ሕዝቅያስ አሁንም ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ ጸሎቱን ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ቅዱስ ሚካኤል እግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ ነቢዩ ኢሳይያስን ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ሄዶ በዕድሜው ላይ 15 ዓመት እንደተጨመረለት እንዲነግረው ያዘዘው፡፡
መልአኩ እንዳዘዘው ነቢዩ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን "እግዚአብሔር የአባትህ የዳዊት አምላክ ጸሎትህን ሰማሁ፣ ዕንባህንም አየሁ፣ እነሆ እኔ አድንሃለሁ፡፡ በዘመኖችህም 15 ዓመት ጨምሬልሃለሁ፡፡ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ፡፡ ይህችን አገር ስለ እኔና ስለ ባለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ›› ብሎሃል ብሎ የተላከውን ነገረው፡፡ ከዚህም በኃላ ንጉሥ ሕዝቅያስ የእግዚአብሔር ኃይል ስላደረበት የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈርተውት እየተገዙለት እጅ መንሻን ያገቡለት ጀመር፡፡ ንጉሡም ዕድሜው ከተጨመረለት በኃላ ሚስት አግብቶ ምናሴን እስኪወልድ ድረስ ቆየ፡፡ በመንበረ መንግሥቱም 29 ዓመት ነግሦ ከኖረ በኋላ እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም ዐረፈ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ጉባኤ_ኤፌሶን
በዚችም ቀን ደግሞ በኤፌሶን ከተማ የቅዱሳን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ ሆነ ይህም ለታላላቆች ጉባኤያት ሦስተኛ ነው።
ስብሰባቸውም የተደረገው የታላቁ ቴዎዶስዮስ ልጅ አርቃድዮስ የወለደው ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ በሃያ ዓመት ነው። የስብሰባቸውም ምክንያት የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በንስጡር ነው። እርሱ ስቶ እንዲህ ብሏልና እመቤታችን ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ አልወለደችውም እርሷ ዕሩቅ ሰውን ወልዳ ከዚህ በኋላ በውስጡ የእግዚአብሔር ልጅ አደረበት ከሥጋ ጋር በመዋሐድ አንድ አልሆነም በፈቃድ አደረበት እንጂ። ስለዚህም ክርስቶስ ሁለት ጠባይ ሁለት ባህርይ አሉት የተረገመ የከ*ሐዲ ንስጡር የከፋች ሃይማኖቱ ይቺ ናት።
ስለ እርሱም የተሰበሰቡ እሊህ አባቶች ከእርሱ ጋር ተከራከሩ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አምላክ እንደሆነ ገብርኤል መልአክ በአበሠራት ጊዜ ከተናገረው ቃል ምስክር አመጡ። እንዲህ የሚል እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው ከአንቺ የሚወለደውም ጽኑዕ ከሀሊ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል ።
ዳግመኛም እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ብሎ በትንቢቱ ከተናገረው ከኢሳይያስ ቃል ሁለተኛም ከእሴይ ዘር ይተካል ከእርሱም ለአሕዛብ ተስፋቸው ይሆናል።
ዳግመኛም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ ገሠጸው መከረው ስለዚህም እንዲህ ሲል አስረዳው ክብር ይግባውና የክርስቶስ የመለኮቱና የትስብእቱ ባሕርያት በመዋሐድ አንድ ከሆኑ በኋላ አይለያዩም አንድ ባሕርይ በመሆን ጸንተው ይኖራሉ እንዲህም አምነን ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አንዲት ባሕርይ ነው እንላለን።
ከ*ሀዲ ንስጥሮስ ግን ከክፉ ሐሳቡ አልተመለሰም ከሹመቱም ሽረው እንደሚአሳድዱትም ነገሩት። እርሱ ግን የጉባኤውን አንድነት አልሰማም ስለዚህም ከሹመቱ ሽረው ረግ*መው ከቤተ ክርስቲያን ለይተው አሳደ*ዱት ወደ ላይኛውም ግብጽ ሒዶ በዚያ ምላሱ ተጎልጒሎ እንደ ውሻ እያለከለከ በክፉ አሟሟት ሞተ።
እሊህም ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት አባቶች ሃይማኖትን አጸኑዋት በዚህም ጉባኤ ውስጥ እንዲህ ብለው ጻፉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእርሷ ሰው የሆነውን የእግዚአብሔርን አካላዊ ቃል በሥጋ ወለደችው።
ከዚህም በኋላ ሥርዓትን ሠርተው ሕግንም አግገው በእጆቻቸው ጽፈው ለምእመናን ሰጡ። እኛም የሕይወትንና የድኅነትን መንገድ ይመራን ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው። ለእርሱም ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም በከበሩ ቅዱሳን አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም እና #ከገድላት_አንደበት)

#መስከረም_13
#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሣርያ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ዐሥራ ሦስት በዚህች ቀን ታላቅና ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ባስልዮስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ልቡ እርሷን ወዶ እንደ እሳት እስከ ነደደ ድረስ እርሷንም ከመውደዱ ብዛት የተነሣ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው።
ይህም አገልጋይ ይህን ነገር ተቀብሎ ያ መሠርይ እንዳዘዘው አደረገ። በዚያንም ጊዜ ከሰይጣናት አንዱ መጥቶ ወደ አለቃቸው ወስዶ አደረሰው ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። እንዲህም ብሎ ጠየቀው "ንጉሥህ ክርስቶስን ትክደ*ዋለህን? ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላ ወደእርሱ አትመለስምን?" ይህም ጐስቋላ ባሪያ "አዎን ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለው። መስሐቲ ዲያብሎስም ይህን ልታደርግ በእጅህ ደብዳቤ ጻፍልኝ አለው። እርሱም በከበረ ደሙ የዋጀውን የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ በደብዳቤ ውስጥ የክህደቱን ቃል ጻፈለት።
በዚያንም ጊዜ ሰይጣን በጌታው ልጅ ልብ ውስጥ የፍትወት እሳትን አነደደ ይህንንም ባሪያ እጅግ ወደደችው ከእርሱም መታገሥ አልተቻላትም። ወደ አባቷ በመጮህ በግልጥ ከዕገሌ ባሪያህ ጋር ካላጋባኸኝ አለዚያ ራሴን እገድላለሁ ትለዋለች እንጂ መታገሥ አልተቻላትም። አባትና እናቷም ፈጽሞ አዘኑ በምንም በምን ሊያስታግሥዋት አልቻሉም። የዚያም አገልጋይ ፍቅሩ በየዕለቱ በልቧ ይጨመር ነበር እንጂ። ስለዚህም ራሷን እንዳትገድል አባቷ ፈራ ለዚያ ባሪያ ሰጠው። እርሱም የጌታውን ልጅ ተቀብሎ ወደቤቱ አስገባት። ከርሷ ጋር ያለውን ፍላጎቱንም ፈጸመ። ከእርሱም ጋር ረጅም ጊዜ ከኖረች በኋላ አባትና እናቷም ይቅር ብሎ ኀዘናቸውን ከላያቸው ያርቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ኀዘንንና ልቅሶን አብዝተው ነበር።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ጩኸታቸውን ሰማ ልመናቸውንም ተቀብሎ ይህ የወደደችው አገልጋይ ጐልማሳ ክርስቲያን እንዳልሆነ አስገነዘባት ከእርሷ ጋር በነበረበት በዚህ በረጅም ዘመን አንዲት ቀን እንኳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔድ ሥጋውንና ደሙንም ሲቀበል ወይም አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት ራሱን ሲአማትብ እርሷ አላየችውም።
ስለእምነቱም ጠየቀችው ግን አልገለጠላትም እርሷም እንዲህ አለችው "አንተ ክርስቲያን ከሆንክ ና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሒድና በፊቴ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበል።" እንዲህም በአስገደደችው ጊዜ ስለርሷ ያደረገውን ሁሉ ወደ ሥራየኛ እንደሔደም በሰይጣንም አምኖ እምነቱንም በክርታስ ጽፎ ያንን ክርታስ ለሰይጣን እንደ ሰጠው ነገራት።
ይህንንም ነገር ከእርሱ በሰማች ጊዜ ደነገጠች መሪር ልቅሶንም አለቀሰች ራሷንም በማወዛወዝ እጅግ ተጸጽታ አዘነች። ያን ጊዜም ፈጥና ተነሣች የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ ወደሆነው ወደ ሀገርዋ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደች ከእግሩ በታችም ወድቃ ሰገደችለት በላይዋ የደረሰውን ሁሉ አስረዳችው ለሰው ልጆች ጠላት ከሆነ ከሠይጣን እጅ ፈጽሞ ያድናት ዘንድ ብዙ በማልቀስ ለመነችው።
ቅዱስ ባስልዮስም ባሏ የሆነውን ባርያ ወደርሱ ልኮ አስመጣውና ጠየቀው እርሱም የሠራውን ሁሉ አስረዳው ቅዱስ ባስልዮስም "ተመልሰህ ክርስቲያን ልትሆን ከሰይጣንም እጅ ልትድን ትወዳለህን?" አለው ያም ባርያ "ጌታዬ ይሆንልኛልን?" አለ ይህ ቅዱስ አባትም የፈጣሪህን ስም እየጠራህ ልብህን አጽና አለው።
ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ በአንድ ቦታ ዘጋበት በመስቀል ምልከትም አማተበበት እንዲጸልይም አዘዘው ራሱ ቅዱስ ባስልዮስም ስለርሱ ጸለየ። ከሦስት ቀኖች በኋላም ጎበኘው እንዲህም አለው በእሊህ በሦስት ቀኖች የደረሰብህ ምንድን ነው እርሱም በላዩ በመጮህ ሠይጣናት ሲያስፈራሩት ያንንም ደብዳቤ ሲአሳዩትና በእርሱ ላይ ሲቆጡ በመከራ ውስጥ እንደኖረ ነገረው ቅዱስ ባስልዮስም ከእሳቸው ቁጣ የተነሣ አትፍራ እግዚአብሔር ይረዳሃልና አጽንቶም ይጠብቅሃል አለው።
ከዚህም በኋላ ጥቂት እንጀራና ውኃ ሰጥቶ ወደ ቦታው መለሰው ቅዱስ ባስልዮስም ስለዚያ አገልጋይ ሒዶ ይጸልይ ጀመረ። ዳግመኛም ከሦስት ቀኖች በኋላ ጐበኘውና በእርሱ ላይ ምን እንደ ደረሰበት ጠየቀው ያ አገልጋይም ጩኸታቸውን እሰማለሁ ግን አላያቸውም ብሎ መለሰለት። እንጀራና ውኃም ሰጠውና መከረው ወደ ቦታውም መለሰውና ስለርሱ ሊጸልይ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደ። እስከ አርባ ቀኖች ፍጻሜ ድረስ እንዲህ አደረገ። በአርባውም ቀን ፍጻሜ ከእርሱ ስለ ሆነው ጠየቀው ያ አገልጋይም እንዲህ አለው ቅዱስ አባቴ ሆይ ስለ እኔ ሰይጣንን ስትጣላውና ድል አድርገህ ጥለህ ስትረግጠው በዛሬዋ ሌሊት አየሁ አለው።
ቅዱስ ባስልዮስም ይህን ነገር ከእርሱ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው የገዳማቱን መነኰሳትና ካህናቱንም ጠርቶ ስለዚያ ሰው ያቺን ሌሊት መላዋን እንዲጸልዩባት አዘዛቸ። በነጋ ጊዜም ያንን አገልጋይ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲአመጡት የዚያችንም አገር ሕዝብ ሁሉንም ሰብስቦ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንሥተው አቤቱ ክርስቶስ ማረን ይቅር በለን እያሉ ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዲማልዱ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ።
እንዲህም እያሉ ሲማልዱ ያ ሰው ጽፎ ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ ሁሉም ደስ ብሏቸው ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የከበረ አባት ባስልዮስም ባረካቸው ሥጋውንና ደሙንም አቀብሎ ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በፍቅር አሰናበታቸው ። እነርሱም ስለ ኃጢአታቸው ስርየትና ስለ ድኅነታቸው ፈጽሞ ደስ እያላቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይህንን ቅዱስ አባት ባስልዮስን እያከበሩ ወደ ቤታቸው ገቡ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም)

#መስከረም_21
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም 21 በዚህች ቀን #ብዙኃን_ማርያም (ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት ነው) እንዲሁም #ቅዱስ_ቆጵርያኖስና #ድንግሊቱ_ዮስቴና በሰማዕትነት ያረፉበትም ቀን ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ብዙኃን_ማርያም
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤
#ጉባዔ_ኒቅያ
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አር*ዮስ የሚባል መና*ፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህ*ደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አር*ዮስ ክህ*ደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአር*ዮስ ክህ*ደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአር*ዮስ ክህ*ደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮ*ስን አው*ግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
#ዕፀ_መስቀል
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቆጵርያኖስና_ድንግሊቱ_ዮስቴና

በዚችም ቀን ቅዱስ ቆጵርያኖስና ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት አረፉ። ይህም ቅዱስ ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሀ*ዲና ሥራ*የኛ ነበር እርሱም ለሥራ*የኞች ሁሉ አለቃቸው ነው።
በሥራ*ዩም ሥራ ከመመካቱ ብዛት የተነሣ በሥ*ራይ የሚበልጠው ካለ ሊያይና ከዚያ ሊማር ከሌለ ግን በእነርሱ ላይ ሊመካባቸው ወደ አንጾኪያ አገር ሔደ።
ቆጵርያኖስም ወደ አንጾኪያ ከተማ በደረሰ ጊዜ ወሬው ተሰማ በአንጾኪያም ከተማ ከሀገር ታላላቆች ተወላጅ የሆነ አንድ ጐልማሳ አለ እርሱም ላህይዋ የሚያምር አንዲቷን ድንግል ብላቴና ተመኛት ወደ ቤተ ክርስቲያን በምትሔድ ጊዜ እያያት በእርሷ ፍቅር ልቡ እንደ እሳት ተቃጠለ በምንም በምን ሊአገኛት አልተቻለውም ገንዘብ በመስጠትም ቢሆን ወይም በማስፈራራት ወይም በሥ*ራይ ሥራ አልሆነለትም።
የቆጵርያኖስም ወሬው በተሰማ ጊዜ እርሱ ከሥራ*የኞች ሁሉ እንደሚበልጥ ስለርሱ ተነግሮአልና ያም ድንግል ዮስቴናን የተመኛት ጐልማሳ ወደ ቆጵርያኖስ ሒዶ በልቡ ያለውን ጉዳዩን ድንግሊቱን ዮስቴናን እንደተመኛትና እርሷን ማግኘት እንደተሳነው ነገረው ቆጵርያኖስም እኔ የልብህን ፍላጎት እፈጽምልሃለሁ አትዘን አለው።
ከዚያም በኋላ ያን ጊዜ ዮስቴናን ወደርሱ ያመጧት ዘንድ በሥራ*ዩ የአጋንንትን ሠራዊት ወደርሷ ላከ እነዚያም አጋንንት ወደርሷ በቀረቡ ጊዜ እርሷን መውሰድ አልቻሉም ከጸሎቷ የተነሣ ይቃጠላሉና እንዲህም ብዙ ጊዜ ላካቸው ግን ወደርሱ ሊያመጧት አልቻሉም ቆጵርያኖስም ሁሉንም አጋንንት ጠርቶ ድንግል ዮስቴናን ካላመጣችሁልኝ እኔ ከእናንተ ተለይቼ ክርስቲያን እሆናለሁ አላቸው።
ከዚህም በኋላ የሰይጣናት አለቃ ሊሸነግለው አሰበ አንዱንም ሰይጣን ከሰይጣናት ውስጥ በዮስቴና አምሳል ተመስሎ ለቆጵርያኖስ እንዲታየው አደረገ። ሰይጣኑም አለቃው እንዳዘዘው እንዲህ አድርጎ ተዘጋጀ እነሆ አሁን የዮስቴናን መምጣት ለቆጵርያኖስ ነገረው እርሱም እውነት መስሎት እጅግ ደስ አለው ሊቀበላትም ተነሣ። በእርሷ አርአያ የተመሰለውንም ምትሐት በአየ ጊዜ የሴቶች እመቤት ዮስቴና መምጣትሽ መልካም ሆነ አለ ይህንንም ስሟን በጠራ ጊዜ ያ በእርሷ አምሳል የተመሰለ ሰይጣን እንደ ጢስ ሁኖ ተበተነ።
በዚያንም ጊዜ የሽንገላው ምክንያት ምትሐ*ቱም ከንቱ እንደሆነ ቆጵርያኖስ አወቀ አስተዋለም በልቡም እንዲህ አለ። ስሟን በጠሩበት ቦታ እንደ ጢስ የሚበተኑ ከሆነ በፊቷ ሊቆሙ ሊሸነገሏትስ እንዴት ይቻላቸዋል ይህንንም ብሎ ወዲያውኑ የጥን*ቆላ መጻሕፍቶቹን አቃጠለ።
ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠምቆ የምንኲስና ልብስን ለበሰ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ዲቁና ሾመው። ዳግመኛም ቅስና ሾመው በትሩፋት ሥራና በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ለሀገሩ ምዕራብ ለሆነች ቅርጣግና ለምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ ተገባው ያን ጊዜም ቅድስት ዮስቴናን ወስዶ ለደናግል ገዳም እመ ምኔት አደረጋት።
በቅርጣግናም የቅዱሳን የአንድነት ስብሰባ በሆነ ጊዜ ከጉባኤው አባላት እርሱ አንዱ ነው።
ከብዙ ወራት በኋላም ከሀ*ዲው ንጉሥ ዳኬዎስ ስለእነርሱ ሰማ ወደርሱም አስቀረባቸውና የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖቶቹ እንዲሰግዱ አዘዛቸው። ትእዛዙንም ባልሰሙ ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ብዙ ሥቃይንም ከአሠቃያቸው በኋላ የቅዱስ ቆጵርያኖስንና የቅድስት ደንግል ዮስቴናን የሦስት ወንዶችንም ራሳቸውን አስቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኅ_መስከረም እና #ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረገጽ)