Telegram Web
#ጥቆማ

#NationalEthioCyberTalentSummerCamp2025

" ስልጠናው የሚሰጠው በነፃ ነው። ምዝገባ ከተጀመረ ጀምሮ ከ1 ሺህ 7 መቶ በላይ ተመዝግበዋል " - የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ በ4ኛ ዙር ለማሰልጠን ምዝገባ ከጀመረበት ጀምሮ እስከ ግንቦት 5 ድረስ 1,725 ሰዎች መመዝገባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ስልጠናው በነጻ እንደሚሰጥ ገልጾ በባለፈው ዓመት በነበረው ጥሪ 6141 ታዳጋዊች መመዝገብ መቻሉንና የምልመላ ሂደቱን አልፈው መሳተፍ ከቻሉት 300 ሰልጣኞች ውስጥ 237ቱ መመረቃቸውንና ወደ ዘርፉ መግባታቸው አስታውሷል።

አሁን በ4ኛው ዙር የስልጠና መርሃ ግብር መሳተፍ የሚችሉት በተወሰ መልኩ አቅምና ታለንት ያላቸው ከተለያዩ ተቋማት ሰርተፍኬት ያላቸው እና በተቋሙ የሚደረጉላቸውን ቃለ መጠይቅ ማለፍ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው በአስተዳደሩ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቢሻው በየነ አስረድተዋል።

ዳይሬክተሩ አቶ ቢሻው በየነ በዝርዝር ምን አሉ ?

" በሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ  የተወሰነ አቅም ወይም ታለንት ያላቸው ሰዋችን ቻሌንጅ በመስጠት አቅማቸውን እንዲያሰፉ ነው የሚደረገው።

እድሜው ከ11 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው መመዝገብ ይችላል፣ እየሞከረ ያለም እና በእድሜ ትልቅ የሆነ ሰው ካለ እንቀበላለን።

ተመዝጋቢዎች ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ  እና በመሳሰሉት ላይ እየሞከሩ የነበሩ እና በነፃ ስልጠና ከሚሰጡ አካላት ስልጠና የወሰዱ እና ሰርተፍኬታቸውን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

በኦንላይን ስትመዘገቡም የግድ ያማረ እንግሊዘኛ አይጠበቅም፣ ነገር ግን በምትችሉት ቋንቋ በገባችሁ ልክ አቅማችሁን እና ፍላጎታችሁን መግለፅ ይጠበቅባችኋል።

ነገር ግን ምንም ታለንት የሌለውን ሰው ወይም ከዜሮ መጀመር ለሚፈልጉ ይህ ምዝገባ አይሆናቸውም። "

የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቢሻውበሳይበር ደህንነት፣ በዴቨሎፕመንት፣ በኢምቤድድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ ላይ ሉዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው በዚህ https://talent.insa.gov.et መመዝገብ እንደሚቻል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
1
2025/07/12 13:08:25
Back to Top
HTML Embed Code: