Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
Channel created
Channel photo updated
100 members ስንደርስ ትምሕርት እንደምራለን
ቅድስት

የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት

የቅድስና ባለቤት የሆነው እርሱ እግዚአብሔር አምላክ ነው። እቀደስ አይል ቅዱስ፣ እባረክ አይል ቡሩክ ነው። በእርሱ የባሕርይ ቅድስና እኛን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ቡሩክ ሆኖ ባረከን፣ ቅዱስ ሆኖ ቀደሰን፣ሕያው ሆኖ ሕያዋን አደረገን። የጸጋ ቅድስናንም ከእርሱ አገኘን። ቅድስናው የተለየ፣ የከበረ፣ የሚመሰገን፣ የሚሰጥ/የሚያድል፣ የሚያነጻ፣ የሚባርክ እናም የሚያስተሰርይ ስለሆነ እንከን፣ ጉድለት የሌለበት ምሉዕ ነው። ለባለሟሎቹ ቢሰጠው የማይጎድል፣ ተከፍሎ የሌለበት ቅድስና ሆኖ እኛም የቅድስና በጸጋ ተካፋይ ሆነናል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Audio
🌸 ከሀጥያተኛው ድንኳን 🌸


ከሀጥያተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመሀል
ልጄ የትናት ብለህ እኔን ፈልገሀል
አንተ ስላለኸኝ ቀሏል መከራዬ (2)
ለኔ ጋደረከው ብዙ ነው ጌታዬ(2)

🌸 አዝ : : : : : : : : :


እንኳንስ አርገኸኝ ጌታዬ ሙሉ ሰው
እንዲሁም ይሄን ነው ልቤ የሚናፍቀው
የዘመናት ሸክም ቀረ ጉስቁልና
የጠፋውን ድሪም አግኝተሀልና

🌸 አዝ : : : : : : : : :

ባገኘኸኝ ጊዜ ሸፍናኝ በለሷ
ከፊትህ ያነበብኩት ፍፁም አይረሳ
ከዚህ የበለጠ ታያለሽ ምትለኝ
አይንህ ይናገራል እንደ ማትረሳኝ

🌸 አዝ : : : : : : : : : :

ምን አለኝ ብለህ ነው ደጅ አፌን የምትመታ
እኔ ደካማ ነኝ አንተ ቅዱስ ጌታ
ከእንግዲ አላርስም ምንጣፌን በእንባ
መንጦላይቴን ከፍተህ በምረትህ ግባ
🌸 አዝ : : : : : : : : : :

እኔኮ አውቅሀለው ሁሉን ስታፈቅር
የአናብስቱን ጉድጓድ የሞት አዋጅ ስትሽር
እንዲህ እያለ ነው የሚቀኘው ውስጤ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምግቤና መጠጤ

በዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

በማርያም ከተመቻቹ በታማኝነት ሼር አድርጉ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
  ።።@tewahdo_haymanotea።።
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
"ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።" ዮናስ ፫፥፰

የምሕረትና የይቅርታ አባት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ፳፻፲፯ ዓ.ም ጾመ ነነዌ በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !
ብፅዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከፌስቡክ ገፃቸው የተወሰደ
@tewahdo_haymanotea
@tewahdo_haymanotea
@tewahdo_haymanotea
ጾመ ነነዌ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአጽዋማት ቀኖና መሠረት ሰባት የዐዋጅ ጾም አጽዋማት አሉ። ከሰባቱ አጽዋማት አንዷ በዕለታት ተወሳክና በዓመቱ መጥቅዕ ድምር ውጤት ወይም በመባጃ ሐመር የምትውለዋ ጾመ ነነዌ ናት።

ጾመ ሰብአ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች ጾም) የምትጾመው ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፉ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ድረስ ነው፡፡ በእነዚህ ፴፭ ቀናት/ዕለታት/ ስትመላለስ ትኖራለች፡፡ ከተጠቀሱት ዕለታት አይወርድም፤ አይወጣም ማለት ነው፡፡ በዚህም ቀመር መሠረት የ፳፻፲፯ ዓ.ም ጾመ ነነዌ የካቲት ሦስት ጀምሮ በአምስት ያበቃል፡፡

ጾመ ነነዌን የጾሙት በነነዌ የሚኖሩ ሰዎች በአምላካችን እግዚአብሔር ትእዛዝ እና በነቢዩ ዮናስ ነጋሪነት ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት አምላካችም ነቢዩ ዮናስ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ወደ ነነዌ ሕዝብ እንዲሄድ አዘዘው፡፡ (ዮናስ. ፬፥፲፩)

እግዚአብሔርም “ሄደህ በነነዌ ላይ ስበክ” ባለው ጊዜ “አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ” ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩት ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ “በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ” ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም “የሰው ደም በእጃችን እንይሆንብን አይሆንም” ብለው ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ነጋድያኑም ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያው የእግዚአብሔርን የማዳን መልእክት ዮናስ እንዲያደርስ፣ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ነነዌ አደረሰው፡፡

ዮናስም ከእግዚአብሔር መኮብለል አለመቻሉን ሲረዳና ነነዌ መሬት ላይ መድረሱ ሲነገረው ለነነዌ ሰዎች “ንስሐ ግቡ” ብሎ መስበክ ጀመረ፤ (ዮናስ ፩ እና ፪)፡፡ መጀመሪያ ከተልእኮው ቢያፈገፍግም “ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፦ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ” እንደተባለው ነቢዩ ዮናስ የኋላ ኋላ ወደ ነነዌ ሄዶ የእግዚአብሔርን መልእክት ዐውጇል። (ዮናስ ፴፫፥፬) በዚያን ጊዜ የነበሩት ሰዎችም እንዲህ አደረጉ፤ “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ” (ቁጥ.፭) እንዲል፡፡

መጽሐፉ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር እንደማራቸው ይገልጻል፡፡ (ዮናስ ፫) ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አምላካችን ቅልን ምሳሌ በማድረግ አስረዳው፡፡ (ዮናስ ፬) ነቢየ ሐሰት እንዳይባልም ለቅጣት የመጣው እሳት እንደ ደመና ሆኖ ታይቶአል፡፡ የታላላቅ ዛፎች ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ የእሳቱ ወላፈን ነክቷቸው ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ በንስሐ በጾምና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀው ከጥፋትና መዓት ድነዋል።

እኛንም ካለንበት መከራ፣ ችግርና ሥቃይ እንዲያወጣን፣ በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት እንዲያኖረን እንደ ነነዌ ሰዎች ንስሐ እንግባ፤ በጸሎት፣ በጾምና በበጎ ምግባር ተወስነን በሃይማኖት እንጽና! 
[ ✔️ Minte Boy WAVE ✔️ ]

መመዝገብ የምትፈልጉ ማሟላት ያለባቹ መስፈርት .....!

➛| ግዴታ ከ 20K በላይ መሆን አለበት ቻናላቹ !
➛|የኦርቶዶክስ ቻናል ቢሆን ይመረጣል !
➛| ከ 20K በታች አትምጡ 🙏

👆 ይሄንን ያሟላ በ
@Minte_boy በኩል ያናግረኝ!

𝐅𝐨𝐥𝐝𝐞𝐫 𝐋𝐢𝐧𝐤 👇
https://www.tgoop.com/addlist/bV7vKqmFYXU3NmVk

Ⓜ️
2025/02/24 08:01:27
Back to Top
HTML Embed Code: