Telegram Web
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባዔ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት ተቃውሞ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በተጨማሪ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅንም አጽድቋል፡፡ አዋጁ በሶስት ተቃውሞ ፣በአራት ድምፅ ተአቅቦ ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

@tikvahethiopia
" ሰማይ ላይ ያየነዉ እንግዳ ነገር ፍርሀት ዉስጥ ጥሎናል " - ነዋሪዎች

ዛሬ ምሽት በበአርባ ምንጭ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ቡርጂ ፣ ሱሮ ባርጉዳ (ምዕራብ ጉጂ ዞን) እና ሌሎችም በርካታ ስፍራዎች በሰማይ ላይ የታየዉ ተምዘግዛጊ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ነገር ፍርሃት አንደጫረባቸዉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ " ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በሰማይ ቅርብ ርቀት ወደ ደቡብ አቅጣጫ መጓዙን አስተዉለናል " ብለዋል።

" አልፎ አልፎ እንደሚስተዋሉ ተወርዋሪ ኮከቦች ቶሎ ታይቶ የሚጠፋና በፍጥነት የሚጓዝ አለመሆኑ ነዉ ፍርሃት የጫረብን " ያሉን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች አሁንም " በርከት ያለ ህዝብ ሰማይ ሰማዩን እያዬ እየተጠባበቀ ይገኛል " ብለዋል።

ይኸው ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በኢትዮጵያ አልፎ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ አካባቢዎች እንዲሁም በኬንያ ሞያሌ በኩብ ታይቷል።

ለመሆኑ ነገሩ ምንድነው ? በሚል የዘርፉን ጉዳይ ወደሚከታተሉ አካላት ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም። ስልክም አያነሱም።

የባለሙያዎችን እና የዘርፉን ጉዳይ የሚከታተሉ ተቋማት ስልክ ተነስቶ መረጃው እንደደረሰን እናቀረባለን።

ሲሆን ሲሆን ለእኛ ሀገር እንዲህ ያለ ክስተት ሲያጋጥም እንዲሁም ዜጎች ግርታ ውስጥ ሲገቡ ወደ ሚዲያ ወዲያው ወጥቶ ማብራሪያ መስጠት ነገሩን ግልጽ ማድረግ ይገባ ነበር።

ቴክኖሎጂው ፤ የማህበራዊ ሚዲያው በእጃችሁ ላይ ነው ምናለ ቅልጥፍ ብላችሁ ሙያዊ ማብራሪያ ለምታገለግሉት ህዝብ ብትሰጡ ?


@tikvahethiopia
#USA 🔥 በአሜሪካ ፤ በሎስ አንጀለስ ታሪክ አውዳሚ ነው በተባለ የሰደድ እሳት እስካሁን በውል ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ ፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል።

እሳቱ በሎስ አንጀለስ ከተማ በብዙ ስፍራ እየተዛመተ ነው ተብሏል።

የሰደድ እሳቱ የሆሊውድ ምልክት በሚገኝበት የሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ እየተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

በሎስ አንጀለስ እና በአጎራባች ግዛቶች ቢያንስ 5 ሰደድ እሳቶች የተያያዙ ሲሆን ሶስቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም።

1. ፓሊሳድስ

ፓሊሳድስ የተሰኘ መጠሪያ የተሰጠው ሰደድ እሳት በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰው ማክሰኞ እለት ሲሆን በግዛቲቷ ትልቁ ነው። የፓስፊክ ፓሊሳድስ አካባቢን ጨምሮ ከ17 ሺህ 200 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ግዛት አውድሟል።

2. ኢቶን

ኢቶን የተሰኘው ደግሞ በሰሜናዊ የሎስ አንጀለስ እን አልታዴና ባሉ ከተሞች እየተዛመተ የሚገኝ ሲሆን 10 ሺህ 600 ሄክታርን መሬት በመሸፈን በግዛቲቷ ሁለተኛው ትልቁ እሳት ሆኗል።

3. ኸረስት

ኸረትስ የተሰኘው ሰደድ እሳት ማክሰኞ እለት ተከስቶ ከሳን ፈርናንዶ በስተሰሜን በኩል እየተዛመተ ይገኛል። ይህም እሳት 855 ሄክታርን ይሸፍናል።

4. ሊዲያ

ይህ ደግሞ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በሎስ አንጀለስ በስተሰሜን ተራራማዋ አክቶን አካባቢ ተቀስቅሶ ወደ 350 ሄክታርን መሬት በመሸፈን ተዛምቷል።

5. ሰንሴት

ይህ ሰደድ እሳት ረቡዕ ምሽት ላይ በሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች የተከሰተው ሰደድ እሳት ሲሆን ከሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ 20 ሄክታር እያደገ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ወደ 43 ሄክታር ተዛምቷል።

ውድሌይ እና ኦሊቫስ የተሰኙት ሰደድ እሳቶች በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአካባቢው የእሳት አደጋ ባስልጣናት ገልጸዋል።

የመረጃው ምንጮች ፦ ቢቢሲ እና ሲኤንኤን ናቸው።

ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሰማይ ላይ ያየነዉ እንግዳ ነገር ፍርሀት ዉስጥ ጥሎናል " - ነዋሪዎች ዛሬ ምሽት በበአርባ ምንጭ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ቡርጂ ፣ ሱሮ ባርጉዳ (ምዕራብ ጉጂ ዞን) እና ሌሎችም በርካታ ስፍራዎች በሰማይ ላይ የታየዉ ተምዘግዛጊ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ነገር ፍርሃት አንደጫረባቸዉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ " ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በሰማይ…
" የማጣራት ሥራውን እስክናጠናቅቅ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ በትህትና እንጠይቃለን " - የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ መታየታቸው ሪፖርት እንደደረሰው ዛሬ ጥዋት አሳውቋል።

" በደረሰን ተንቀሳቃሽ ምስል ለመመልከት እንደቻልነው የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ይመስላሉ " ብሏል።

" ስብስቡ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል " ሲል አክሏል።

" የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችለን ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራን የምንገኝ ሲሆን ፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል " ብሏል።

" የማጣራት ሥራ እንኪጠናቀቅ ድረስ  ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ በትህትና እንጠይቃለን " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

#ESSS

@tikvahethiopia
#telebirr

🌟 10% የገንዘብ ስጦታ ከተጨማሪ የዕድል ሽልማቶች ጋር!!

የገናን በዓል አስመልክቶ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ 10% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

💁‍♂️ በተጨማሪም 6ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ሲቀበሉ አጓጊ ለሆነው ልዩ የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!

1️⃣5️⃣ የቤት ዕቃዎች - እያንዳንዳቸው 100,000 ብር
2️⃣0️⃣ የበግ ስጦታዎች - እያንዳንዳቸው 15,000 ብር
5️⃣0️⃣ የበዓል አስቤዛ - እያንዳንዳቸው 10,000 ብር
3️⃣0️⃣0️⃣ የኪስ ገንዘብ - እያንዳንዳቸው 5,000 ብር
🌍🎁  እንዲሁም በርካታ የሞባይል ዳታ ጥቅሎች

የሚቀበሉት የገንዘብ መጠን ሲጨምር የጨዋታ ዕድልዎም ይጨምራል!
🗓 እስከ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Kenya

ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብርሃን ያላቸው የቁስ አካላት ስብስብ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍልም ታይተዋል።

እነዚህ ቁስ አካላት በኬንያ ቱርካና፣ ማርሳቢት፣ ሞያሌ አካባቢ መታየታቸውን የኬንያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቁስ አካላቱ " የጠፈር ፍርስራሾች ናቸው በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል (ኬንያ - ኢትዮጵያ ድንበር) ወድቀዋል ፤ ሲወድቁም ከፍተኛ ድምጽ ተሰምቷል ፤ ከሚቃጠል ነገር ጭስም ታይቷል ሽታም ነበረው " እያሉ ብዙ ተከታይ ያላቸው የኬንያ ፀሀፊዎች X ላይ ቢፅፉም የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ በይፋ የሰጠው ማረጋገጫ የለም።

እስካሁን የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ፥ ቁስ አካላቱ ኬንያ ውስጥ ስለመውደቃቸው ማረጋገጫ አልሰጠም ስለ ጉዳዩ መግለጫም አላወዋጣም።

ከሰሞኑን በኬንያ ማኩኒ ካውንቲ ሙኩኩ በተባለች ትንሽዬ መንደር ከሰማይ ወርዷል የተባለ 2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለውና 500 ኪሎግራም ክብደት ያለው ቁስ በርካቶችን አስደንግጦ ነበር።

የኬንያ የስፔስ ኤጀንሲ ሰዎች ቁሱ ወደወደቀበት ስፍ በማቅናት ምንነቱን ለማጥናት የሞከሩ ሲሆን ወደ ህዋ የመጠቀ ሮኬት ቁርጥራጭ ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል።

ቀለበት ቅርጹ ከሮኬት ከተነጠለ በኋላ የሚፈረካከስ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የየትኛው ሀገር ወይም ኩባንያ ንብረት እንደሆነ የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው። እስካሁን መደምደሚያ ላይ አልተደረሰም።

ተቋሙ " እንደዚህ አይነት ቁሶች (በኬንያ የወደቀው ቀለበት) ወደ ምድር ምህዋር ሲመለሱ ራሳቸውን እንዲያቃጥሉ አልያም ወደ ውቅያኖሶች እንዲገቡ ተደርገው የሚሰሩ ናቸው " ሲል ነው ያብራራው።

እንደ ኒውዮርክ ታይምስ መረጃ ከሆነ ባለፉት ስድስት አስርት አመታት በሀገራት መካከል የሚደረግ የህዋ ላይ ፉክክር መጠናከር ከሰማይ ላይ የሚወድቁ ቁሶች እንዲበራከቱ አድርጓል።

ባለፈው አመት ባወጣ የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ መረጃ በዝቅተኛ የምድር ምህዋር ውስጥ ከ14 ሺህ ቶን በላይ ቁሶች እንዳሉ ተገምቷል ፤ ከዚህ ውስጥም ከሲሶ በላዩ ለህዋ ምርምር የማያስፈልጉ ቁሳቁሶች ናቸው።

እንደ መረጀው ፥ በየአመቱ ከ110 በላይ የሳተላይት ማምጠቅ ሙከራዎች ይደረጋሉ ፤ በጥቂቱ 10 ሳተላይቶች እና ሌሎች የምርምር ቁሳቁሶች ወደ ትንንሽ ስብርባሪዎች ይቀየራሉ። ይህም ከህዋ ላይ ወደ መሬት የሚወድቁ ነገሮች እንዲበራከቱ አድርጓል።

መረጃው ከኬንያ የማህበራዊ ትስስር መድረኮች፣ ከኒውዮርክ ታይምስ፣ ከቢቢሲ፣ ከአል አይን ፣ ከኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
2025/01/10 11:26:51
Back to Top
HTML Embed Code: