Telegram Web
" ባለፉት 6 ዓመታት ከተተከሉ ከ40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ውስጥ ከ 10 ቢሊየን በላይ (27.5 በመቶ) የሚሆኑት በአባይ ተፋሰስ አካባቢዎች የተተከሉ ናቸው " - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው የ2017 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትርና የአረንጓዴ አሻራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተገኙ ውጤቶችን ይፋ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያዊ በአፈር መሸርሸር ምክንያት ወንዞች በየአመቱ 1.9 ቢሊየን ቶን አፈር ወደ ጎረቤት ሃገራት ይወስዱ ነበር ያሉ ሲሆን ባለፉት ስድስት አመታት ቁጥሩን ወደ 208 ሚሊየን ቶን አፈር ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ከእርሻ መሬቶች በየዓመቱ 130 ቶን ሄክታር በዓመት ይሸረሸር የነበረውም በተመሳሳይ ወደ 54 ቶን ሄክታር በዓመት ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

የደን ሽፋንን በሚመለከትም በ 2011 ዓም ከነበረበት 17.2 በመቶ በ 2016 ዓ.ም ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት። የችግኝ ጣቢያዎችም በ2011 ዓ.ም ከነበሩበት 45 ሺ ወደ 130 ሺህ በላይ ማደጉን ተመላክቷል።

የግብርና ሚኒስትሩ፥ " ባለፉት ስድስት አመታት ከተተከሉ ከ 40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ውስጥ ከ 10 ቢሊየን በላይ ይህም 27.5 በመቶ የሚሆነው በአባይ ተፋሰስ አካባቢዎች የተተከሉ ናቸው " ብለዋል።

በዚህም በአባይ ተፋሰስ አከባቢዎች የነበረውን የደን ሽፋን ከ19 በመቶ በ2024 እ.ኤ.አ ወደ 25 በመቶ ማሳደግ መቻሉን አንስተዋል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የከርሰ ምድር ውሃ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጸዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩም ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው የተናገሩ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 63 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ 40 ቢሊዮን ችግኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል 40 ቢሊዮን ዶላር የአየር ንብረት ፋይናንስ ከሀገር ቤት (Public Finance / Domestic Climate Finance) አዋጥታለች።

ነገ በሚጀመረው የ 2017 ዓም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 7.5 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#መሰቦ

ፋብሪካው ጥሬ እቃ ከሚያገኝባቸው አከባቢ ማህበረሰብ በተከሰተው ችግር ምክንያት ስሚንቶ ማምረት ማቆሙ አስታወቀ። 

ፋብሪካው ተከሰተ ያለውን ችግር ከማብራራት ተቆጥበዋል።  

የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ በሰጠው መረጃ ፥ በኳሪ ሳይቱ ባጋጠመው ጊዚያዊ ችግር " ማምረት አቁሚያለሁ " ብሏል።

ፋብሪካው ችግሩ መቼና ? እንዴት ? እንደሚፈታ አስመልክቶ ያለው ነገር የለም።

" የፋብሪካው ምክንያት አሳማኝ አይደለም " በሚል የተቋወሙ አስተያየት ሰጪዎች " ማምረት አቁሚያለሁ የሚለው ከነጋዴዎች በመመሳጠር ገበያ ለማስወደድ ነው " ብለዋል።

የፋብሪካው ኮሙኒኬሽን ኮርፓሬት በሰጠው አስተያየት " ይህ ከእውነት የራቀ ውሸት ነው " ብሎታል።

" ፈጠራ " ሲል ያጣጣለው አስተያየቱን ፋብሪካውን ጥላሸት የሚቀቡ ያላቸውን ግለሰቦችና አካላት በህግ እንደሚጠይቅ አሳስቧል።

የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ጥሬ እቃ ከሚያገኝባቸው አከባቢ ማህበረሰብ ከሚያጋጥም ችግር ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ማምረት እንደሚያቆም ቲክቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
🔈#የአሽከርካሪዎችድምጽ

" በአንድ ሳምንት ሦስት አሽከርካሪዎች በሙቀት ሳቢያ ሞተዋል። ' ጂቡቲ ገብታችሁ ነው የምትመዘገቡት ' ስለሚባሉ ቀድመው ሂደው እስከ 40 ቀናት የሚቆዩበት አጋጣሚ አለ " - ማኀበሩ

የከባድ ተሽከርካሪ ሾፌሮች ግብዓት ጭነው የመመለሻ ጊዚያቸው ሲቃረብ ወደ ጅቡቲ ሊላኩ ቢገባም ቀድመው እንዲሄዱ ስለሚገደዱ ከ10 እስከ 40 ቀናት ሙቀት ላይ ስለሚቆዩ መኪናቸው ውስጥ በተኙበት በሙቀት ሳቢያ ሞተው እየተገኙ መሆኑን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

በሳምንት ሦስት አሽከርካሪዎች በፀሐይ ሙቀት በጅቡቲ እንደሞቱ፣ አንዱ ሟች የኢንሹራንሳቸው አባል በመሆኑ የኢንሹራንስ ፕሮሰስ ሲያልቅ የሚገባውን እንደሚያገኝ ገልጾ፣ " አዋሽ ላይ ነው መኪናው ውስጥ ተኝቶ ጠዋት ሞቶ የተገኘው " ነው ያለው።

" ሁለቱ አሽከርካሪዎችም በአንድ ቀን ነው በመንገድ እያሉ መኪናቸው ላይ ተኝተው አድረው በሙቀት የሞቱት " ያለው ማኀበሩ፣ " በሳምንት ሦስት አሽከርካሪዎች በሙቀት ሳቢያ ሞተዋል " ብሏል።

" ' ጂቡቲ ገብታችሁ ነው የምትመዘገቡት' ስለሚባሉ ቀድመው ሄደው እስከ 40 ቀናት የሚቆዩበት አጋጣሚ አለ " ያለው ማኅበሩ " አንድ አሽከርካሪ ወረፋ ደርሶት ለመጫን ሦስት አራት፤ ቀናት ሲቀሩት ወደ መጫኛ ስፍራው ቢሄድ ቶሎ ጭኖ ሙቀቱ ሳይበላው ይመጣል " ሲልም አስገንዝቧል።

ማኀበሩ፣ የችግሩ መንስኤ ሹፌሮች ከመነሻቸው (አዲስ አበባ) እያሉ ከጂቡቲ የሚጭኑበትን ቀን (ወረፋቸውን) እንዲያውቁ ሳይደረግ እንዲሄዱ መገደዳቸው መሆኑን አስረድቷል።

መፍትሄው ምንድን ነው ?

ቅድሚያ ግብዓት የሚጭኑበት ቀን ለሾፌሮች ቢነገራቸውና የተወሰኑ ቀናት (የጂቡቲ መንገድ ሁለት ቀናት ነው ጉዞው) ቀደም ብሎ ተነግሯቸው በቶሎ ጭነው እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባ ማኅበሩ አስረድቷል።

" ነዳጅ በኢትዮጵያ በቀን ከ250 እስከ 270 ቦቴዎች ናቸው የሚጫኑት። ግን በአሁኑ ወቅት ከ2000 በላይ ቦቴዎች ቆመው ነው የሚታዩት። ባለሃብቶቹም፣ ካምፓኒዎቹም ሹፌሮቹን ቀድማችሁ ግቡ ነው የሚሏቸው። ጁቡቲ ሲገቡ ነው ለወረፋ የሚመዘግቧቸው " ብሏል።

ጂቡቲ ከሄዱ በኋላ ለመጫን እስከ 40 ቀናት ስለሚቆዩ ከሞቱ ባሻገር እስከ 40 ሺሕ ላላስፈላጊ ወጪ እየተዳረጉ በመሆኑ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠይቋል።

በሌላ በኩል፣ ከወራት በፊት በአማራ ክልል ነዳጅ የጫነ ቦቴ በታጣቂዎች ተመትቶ ነዳጁ እንዲፈስ በተደረገበት ወቅት በጥይት የተመቱ ሾፌር ጥይቱ ከእግራቸው እንዳልወጣ ማኀበሩ ገልጿል።

በወቅቱ ታጣቂዎቹ፣ " ከመኪና አውርደው ነው በጥይት እግራቸውን የመቷቸው እግራቸው ውስጥ ጥይቶቹ አሉ " ሲልም ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahEthiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo፣ ሌላ ስኬታማ የንግድ፣ የፈጠራ እና የልዩ ልዩ ምቹ ዕድሎች ቀንን በአዲስ አበባው ሚሊኒየም አዳራሽ አሳልፈዋል።
20+ ሀገራት የተውጣጡ ኢግዚቢሽን አቅራቢዎች፣ ዘመን አፈራሽ የሆኑ ምርቶቻቸውን፣ የቀጥታ የምርት ስኬታማነት ሙከራዎቻቸውን እና ሁነኛ የግንባታው ዘርፍ አማራጮቻቸውን ሲያስጎበኙ ውለዋል።
🚨በነገው የመጨረሻ የንግድ ትርዒቱ ቀን፣ እንኳን መቅረት - ማርፈድ ያስቆጫል!

በነጻ ይመዝገቡ : https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia
ዋሪት ፈርኒቸር

የቢን ባግ መቀመጫ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ያውቁ ኖሯል?
🛋 ሰውነትዎን በትክክል በመደገፍ ምቹ አቀማመጥን ይሰጣል
💪 የጡንቻ ህመምን ይቀንሳል
😴 ለመዝናናት፣ መጽሐፍ ለማንበብ አልያም ፊልም ለማየት ምርጥ ናቸው !

ወደ ማሳያ ክፍሎቻችንን በመምጣት ይጎብኙን !
* 22 - ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* አዳማ - ሶረቲ ሞል * ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት * ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
*ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ዜጎች ብዙ ወጪ ወጥቶ ከያሉበት ተሰባስበው ወደ ሀገር እንዲመጡ ጥረት ይደረጋል የዛኑ ያክል ደግሞ በተለያየ ቀዳዳ ሰዎች ሲወጡ ይታያል ” - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በማይናማር ከእገታ ወጥተው በካምፓኒ የሚገኙ፣ አሁንም በእገታ ያሉ ወገኖች መንግስት ጓደኞቻቸውን እንደመለሰው ሁሉ እነርሱንም እንዲመልሳቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እየተማጸኑ ይገኛሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር…
" የወጣቶቹ ህይወት በአደጋ ላይ ነው " - አስተባባሪ

ማይንማር ውስጥ አሁንም በአጋቾች እንደተያዙ ነው የተባሉ 42 ኢትዮጵያውን እጣ ፈንታ አለመታወቁን በማይንማር የተጎጂ ወጣቶች ቤተሰቦች አስተባባሪ ተናግረዋል።

" ከአጋቾች ነጻ ከወጡ 751 ኢትዮጵያውያን የመጨረሻዎቹ 49 ዜጎች አገራቸው ገብተዋል " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የተናገሩት አስተባባሪዋ ወ/ሮ አበበች ሲመል " ሆኖም ከአጋቾቻቸው ካምፕ መውጣት ያልቻሉ 42 ኢትዮጵያውያን ግን አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ " ብለዋል።

" ከአጋቾች እጅ መውጣት እየፈለጉ ከዚህ ቀደም ሌሎች ሲወጡ አጋቾቹ ያስቀሯቸው 42 ወጣቶች አሁን ላይ በሶስት ኩባንያዎች ውስጥ በጉልበት ብዝበዛ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

በፖሊስ እጅ ያልገቡ  የእነዚህ ወጣቶች ህይወት በአደጋ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ወጣቶቹ  የመጀመሪያ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ያላቸው እንዲሁም ከመካከላቸው የህክምና ዶክተሮች እንደሚገኙበትም የተጎጂ ቤተሰብ አስተባባሪዎቹ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። ወደ ማይናማር የሄዱትም  " ከፍተኛ ደመወዝ ታገኛላችሁ " ተብለው ተታለው ነው።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba #እንድታውቁት

ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ሴንተር ወይም በሜክሲኮ ማከፋፈያ ትራንስፎርመር ላይ አስቸኳይ የጥገና ሥራ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

በዚህም ምክንያት ፦
- በሜክሲኮ፣
- በአፍሪካ ህብረት፣
- በቄራ፣
- በገነት ሆቴል፣
- በደንበል፣
- በመስቀል ፍላወር፣
- በወሎ ስፈር፣
- በመስቀል አደባባይ በባምቢስ እና አካባቢው ኤሌክትሪክ ተቋርጦ እንደሚቆይ አሳውቋል።

የጥገና ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ነዋሪዎች ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

#EEP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሰባት አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል። አንድ አሽከርካሪ ደግሞ ተገድሏል፤ ተሳፋሪዎችም ታግተዋል " - ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

በአማራ ክልል ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም፣ "ከ20 በላይ አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገደሉ" በተባለበት የጎንደር መስመርና በአካባቢው ከጥቃቱ በኋላም በታጣቂዎች የግድያና እገታ ጥቃት መፈጸሙን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ማኀበሩ በሰጠን ማብራሪያ፣ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም፣ " አምስት ሹፌሮች ታግተዋል። ስድስተኛው በዚሁ እለት ከእገታ አምልጦ ነበር ከመሪው ተደብቆ፤ 100 ኪሎ ሜትር ከተጓዘ በኋላ ግን ሌላ ቦታ ገደሉት " ብሏል።

" ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ/ም ከጎንደር መተማ መንገድ ሁለት ሹፌሮች ታግተዋል። በቀን 16 የግድያ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ" ያለው ማኀበሩ፣ "ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ታግተዋል። አንድ አሽከርካሪ ደግሞ ተገድሏል። ተሳፋሪዎችም ታግተዋል " ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ሁለቱ ሹፌሮች የታገቱት ሰሞኑን ከ20 በላይ ሹፌሮች ተገደሉ የተባለበት መንገድ፣ አምስቱ ሹፌሮች በሌላኛው በአብራሂጅና ሶረቃ መካከል፣ አንዱ ሹፌር የተገደለውና ተሳፋሪዎች የታገቱት ደግሞ ደለሎ አካባቢ መሆኑን ማኀበሩ ገልጿል።

" አሽከርካሪዎችን 'ችግር ባለባቸው አካባቢዎች አትሂዱ' ብለናቸዋል፤ አለመሄድ ቢቻል ውጤት ይመጣ ነበር። በቀን 16 ሹፌሮች ተገድለው እያለ በማግስቱ ሄደው ነው የታገቱት። በአሊ ዶሮ መንገድ ግድያ የቀረው ማታ መንጓዝ ቀርቶ ነው " ሲልም ገልጿል።

በሌሎች አካባቢዎች ያለው እገታና ግድያ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ስንጠይቀውም፣ "ከደብረታቦር ጋይንት ባለው መንገድ ቀድሞ መሻሻሎች አሉ እየተባለ ነው። ኦሮሚያ ክልልም የሌሊት ጉዞ ስለቀረ ብዙ ነገሩ ሴፍ ሆኗል" ሲል መልሷል።

በቀን 16 የግድያ ጥቃት የተፈጸመበት መንገድ በጸጥታ ችግር ለወራት ተዘግቶ አሽከርካሪዎች ለ140 ኪሎ ሜትር መንገድ አላስፈላጊ ጉዞ ተዳርገው መቆየታቸውን ማኀበሩ አስታውሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጋምቤላ

" አራት ሴቶች በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነዉ ተወስደዋል " - የጋምቤላ ክልል ፖሊስ

➡️ " በአንድ ዓመት ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በታጣቂ ቡድኑ ተወስደዋል ! "


የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኦጉላ ኡጁሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በትናትናው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት አከባቢ በአኝዋክ ብሔረሰብ ዞን በጎጊ ወረዳ ተዶ በሚጠራዉ አከባቢ የሙርሌ ታጣቂዎች አራት ሴቶችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉን ተናግረዋል።

" ሙርሌ" የተሰኘዉ የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ቡድኑ ከ14 እስከ 27 ዓመት ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ አራት ሴቶችን ወደ ፒኝውዶ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተኩስ በመክፈት አፍኖ እንደወሰዳቸዉ የገለፁት ኮሚሽነሩ አስቀድሞ በአከባቢዉ የነበሩ የጎግ ወረዳ ፖሊስ አባላትና ሚሊሻዎችን በኋላም የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ መዋቅር የጋራ ግብረ ሃይል ታፍነዉ የተወሰዱትን ለማስመለስ ቡድኑን እየተከታተሉ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል።

በደቡብ ሱዳን የሚንቀሳቀሰው የሙርሌ ታጣቂ ቡድን ከጋምቤላ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች በተደጋጋሚ ሰዎችን እያፈነ እንደሚወስድ የተናገሩት ኮሚሽነር ኦጉሉ በፀጥታ ሃይሎች ኦፕሬሽን ከተመለሱት በስተቀር አብዛኞቹን እንደሚገድልና ሱዳን ወስዶ ለጉልበት ስራ እንደሚሸጣቸዉም መረጃዎች እንደሚደርሷቸዉ ገልፀዋል።

ኮሚሽነሩ አክለዉም በ2017 ዓ/ም ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በነዚህ የታጠቁ ቡድኖች ተዘርፈዋል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
2025/06/28 00:02:41
Back to Top
HTML Embed Code: