Telegram Web
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam ዩኒቨርሲቲዎች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞችን ዛሬ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም መቀበል ጀምረዋል፡፡ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። በወጣው መርሐግብር መሰረት ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ይጀምራል፡፡ ፈተናውን…
#NationalExam🇪🇹

ነገ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሠጠት ይጀምራል።

ፈተናውን ለመውሰድ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም ዛሬ የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ሲሰጥ ውሏል።

ተፈታኞቹ በዩኒቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚያገኙት አገልግሎቶች (ምግብ፣ መኝታ፣ ጤና...) እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በተጨማሪም በፈተና ወቅት ስለሚከተሏቸው ህግና ደንቦች እንዲሁም ተያያዥ ስለሆኑ የፈተና ሂደቶችና አተገባበሮችን በሚመለከት ገለጻ ተሰጥቷቸዋል።

ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚወስዱት ፈተና ይጀምራል።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተጀመረ።

የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ፈተናውን አስጀምረዋል።

ዘንድሮ በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🤙🏽ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎች በመጠቀም ከ07 ➡️ 09 መስመር በእጥፍ ጉርሻ በሽ በሽ ብለን እንደዋወል! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ዛሬ ውይይት አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።

1. በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ወስኗል።

ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022) እንዲነሳ ወሳኔ አሳልፏል።

" አሁን ላይ የመንግሥት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉ፣ እንዲሁም መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለሟሟላት የውጭና ገበያ መር የሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየውን ይህ አስገዳጅ መመሪያ አሁን ላይ ማንሣቱ ተገቢ መሆኑን ኮሚቴው አምኖበታል" ብሏል።

ይህ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ለብሔራዊ ባንክ ቦርድ ቀርቦ ጸድቋል።

ስለ ግምጃ ቤት ቦንድ ፦ ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ በሚያስገድደው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ባንኮች መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 2022 ጀምሮ ከአጠቃላይ ዓመታዊ ብድራቸው አምስት በመቶ የሚሆነውን ለዚህ የቦንድ ግዥ ሲያውሉ ቆይተዋል።

በዚህ መመሪያ መሠረት የገዙት ቦንድ የሚመለሰው (ለቦንድ ግዢ ያዋሉት ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግላቸው) ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ ሲሆን ፣ ባንኮቹ መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ወር አንስቶ እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2024 ድረስ የገዙት የቦንድ መጠን 94 ቢሊዮን ብር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥት ዕዳ መግለጫ ያመለክታል።


2. በባንኮች ላይ የተጣለው የብድር ዕቀባ የተመለከተ ውሳኔ ተላልፏል።

በአሁኑ ወቅት በባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ላይ የተቀመጠው የ18 በመቶ ጣሪያ እስከ መጪው መስከረም 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲቀጠል ኮሚቴው ወስኗል።

" አሁን ላይ የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ እየተስተዋለ ቢሆንም ይህንን ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በባንኮች ላይ የተጣለው የብድር ዕድገት ጣሪያ ባለበት እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ብሏል ኮሚቴው።

3. የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን (National Bank Rate) አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይ፣ብሔራዊ ባንክ ለሚሰጣቸው ቋሚ የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት (standing deposit facility)፣ ለቋሚ የብድር አገልግሎት (standing lending facility) የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ፣ እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት የግዴታ መጠባበቂያ ምጣኔ በነበረበት እንዲቆይ ተወስኗል፡፡

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#NBE #REPORTER

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። የሲዳማ ክልል ከሰሞኑ በፀጥታዉ ዘርፍ እየወሰደ እንደሆነ በተገለፀዉ ተቋማዊ ሪፎርም ዛሬ የቀድሞ የክልሉ ኮሚሽነር የነበሩትን ሽመልስ ቶማስ በዛሬዉ ዕለት ከስልጣን ማንሳቱ የተሰማ ሲሆን ማምሻዉን ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟቸዋል። አዲሱ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ ሲዳማ በዞን…
" ' ከእነ እገሌ ጋር ናችሁ ትፈለጋላችሁ ገንዘብ አምጡ ' በማለት የሚያስፈራሩ ተረኛ ሌቦችና አጭበርባሪዎች እንዳሉ መረጃ ደርሶኛል " - ኮሚሽነሩ

በቅርቡ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙት ተስፋዬ ኤቢሶ ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት በክልሉ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ ይስተዋሉ የነበሩ ህገወጥነትና ሥርዓት አልበኝነትን ለማስተካከል የክልሉ መንግስት ቁርጠኛ አቋም ወስዶ በመስራት ላይ መሆኑን ገለጹ።

" ስልጣንን መከታ በማድረግ ህገወጥ ድርጊቶችን ሲፈጸሙና ሲያስፈጸሙ የነበሩ ባለሥልጣናት፣  ደላሎችንና ኮንትሮባንዲስቶችን እንዲሁም በጸጥታ ተቋም ውስጥ የጥቅም ትስስር በመፍጠር በተደራጀ መንገድ የሌብነት መረብ ከላይ እስከ ታች በመዘርጋት ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦችን ለህግ የማቅረብና ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ ነው " ብለዋል።

" ለዚህም ስራ የህብረተሰቡ ድጋፍና ትብብር በጣም አስፈላጊ ነዉ " ብለዋል።

ኮሚሽነሩ ' ወሮበሎች ' ሲሉ  የጠሯቸው የተወሰኑ ግለሰቦች " የህግ ማስከበሩን ተግባር ሽፋን በማድረግ የህግ አስከባሪዎች በመምስል ግለሰቦችን ' ከእነ እገሌ ጋር ናችሁ ትፈለጋላችሁና ገንዘብ አምጡ ' በማለት ሰዎችን የሚያስፈራሩ ተረኛ ሌቦችና አጭበርባሪዎች እየተንቀሳቀሱ ስለመሆናቸው መረጃ ደርሶኛል " ሲሉ አስታውቀዋል።

ኮሚሽነር ተስፋዬ ደቢሶ በወንጀል የተጠረጠረና በህግ የሚፈለግ ሰው ካለ በህጋዊ መንገድ እንጂ የሚያስፈራሩ ሰላዮችን በማሰማራት የሚሰራ እንዳልሆነ ታውቆ ማህበረሰቡ እንዲህ ዓይነት ተግባር ከሚፈፅሙ አካላት እንዲጠነቀቅ እና እንዲህ አይነቱ ተግባር ቢያጋጥመዉ ለፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

የሲዳማ ክልል በፀጥታው ዘርፍ እያካሄደ ባለ ሪፎርም ከዚህ ቀደም በየደረጃው ለሰላምና ፀጥታ ተቋማት ተጠሪ የነበረዉን የፖሊስ መዋቅር ለየመዋቅሩ አስተዳዳሪዎች እንዲሆን በማድረግ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስን ያለመከሰስ መብት አስነስቶ በቁጥጥር ስር ያዋላቸዉ ሲሆን የቀድሞ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽነር ከስልጣን ማንሳቱ አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
🔈#የሠራተኞችድምጽ

" አብዛኛዎቹ አሰሪዎች ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚገለጹ፤ ትላልቅ ህንጻችን በእንጨት ስካፍሆልዲንግ ሥራ የሚያከናውኑ ናቸው " - ኢሠማኮ

የኮንስትራክሽን ሠራተኞች በሥራ ቦታ በሚገጥማቸው አደጋ በተደጋጋሚ ሞትና ጉዳት እንደሚደርስባቸው ፤ አሁንም አደጋው እንዳልቆመ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በየቀኑ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች ከእንጨት መወጣጫ ላይ ወድቀው የሚሞቱበትና የሚቆስሉበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸው፣ ለዘርፉ ትኩረት እንዲሰጥ ተማጽነዋል።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ፌደሬሽን (ኢሠማኮ) የኢንደስትሪ ግንኙነትና ማደራጃ ዘርፍ ም/ፕሬዚደንት አቶ ደርቢሳ ለገሰ፣ በአሰሪዎች የጥንቃቄ ጉድለቶች፣ በተቆጣጣሪዎች ደግሞ ክፍተት እየተስተዋለ መሆኑን ገልጸዋል።

ምን አሉ ?


" ከሙያና ደህንነት ጋር በተያያዘ የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ በግልጽ ያስቀመጣቸው መስፈርቶች አሉ። ሆኖም ይህንን ለመከታተል የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ  ተስርቷል ማለት አይቻልም፡፡ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ከመስራት ይልቅ በሚደርሰው አደጋ መዘገብ ነው እንደ ልምምድ የወሰድነው።

የቁጥጥር ባለሙያዎች ቢመደቡም የሚቆጣጠሩባቸው መሳሪያዎች በብዙ ቦታዎች የሉም፡፡ እርምጃዎችን በመውሰድ ሂደትም በሚፈለገው ልክ አልተሰራበትም። ቅድመ ክትትልና እርምጃ መውሰድ ላይ ቢተኮር ኖሮ አሁን እየደረሱ ያሉ ጉዳቶች ባልደረሱ ነበር።

በአሰሪዎችም የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ጥንቃቄ አለማድረግና ቸልተኝነት አለ፡፡ በአንዳንድ ቦታ ይህን ለመከላከል የሚጠይቀውን ወጪ በማስላት የሰውን ጉዳት ቸል የማለት ሁኔታዎች አሉ።

ቀድሞ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ወጪን በመፍራት በሰዎች ሕይወት የሚደርስን አደጋ በዜና ማስተናገድን እንደ አማራጭ እንደ መውሰድ የሚቆጠርበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ትልቅ ችግር አለ። አብዛኛዎቹ አሰሪዎችም ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚገለጹ፤ ትላልቅ ህንጻዎችን በእንጨት ስካፍሆልዲንግ ሥራ የሚያከናውኑ ናቸው" ብለዋል።

በሥራ ቦታ የሚደርሱ አደጋዎች የሚከሰቱት እርምጃ ባለመወሰዱና የቅድመ ክትትል ሥራ ባለመሰራቱ መሆኑን ገልጸው፣ “ይህንን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል፣ መሳሪያዎች ሊኖሩ ይገባ ነበር፡፡ ነገር ግን መሳሪያዎች ለጥቅም ውለው አገልግሎት እየሰጡ ነው ማለት አይቻልም" ብለዋል።

ፌዴሬሽኑ ባለው መረጃ በሥራ ቦታ ላይ ስንት ሰራተኞች እንደሞቱ ስንጠይቃቸውም፣  "አብዛኛዎቹ አባሎቻችን ስላልሆኑ መረጃዎቻቸውን ማግኘት አንችልም” ብለው፣ ፌዴሬሽኑም መረጃ የሚያገኘው ከሥራና ክህሎት በሚቀርብ ሪፓርት መሆኑን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ማእከላይ ዞን ፍርድ ቤት የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከነሂጃባቸው እንዲማሩ ወሰነ። የወረዳ ፍርድ ቤት በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ላይ ያስቀመጠው የገንዘብ መቀጮም እንዲቀር ወስኗል። የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 30/2017 ዓ.ም በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ፤ ከአሁን በፊት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች…
#Axum

" የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ በመልበሳቸው ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንዳይወስዱ ተደርገዋል " - የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት

➡️ " ፈተና ማእከል ደርሳ ሂጃብ በመልበስዋ ምክንያት የተባረረች እንዲት ሙስሊም ተማሪ የለችም ፤ የፈጠራ ወሬና ጥላሸት መቀባት ይቁም " - የትምህርት ቢሮ ሃላፊ


የአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች የሂጃብ መልበስ ክልከላ ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ ወራትን አስቆጥሯል።

ዛሬ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ሲጀመር የአክሱም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ተነስቷል።

የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት ፥ " የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ክልከላ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንዳይወስዱ ተደርገዋል " በማለት አስተያየታቸውን በማህበራዊ የትስስር ገፆች አሰራጭተዋል።

" ሂጃብ ከመልበስ ጋር ተያይዞ እንዲት ሙስሊም ተማሪ ከፈተና ማእከል የተባረረች የለችም " በማለት ለተሰራጩት ፅሁፎችና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር)  " ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡት 24 ሴት ተማሪዎች በራሳቸው ፍላጎት ሳይመጡ ቀርተዋል " ብለዋል። 

" ሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ  የመፈተን ፍላጎት ካላቸው ሀሙስ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም በሚጀመረው ሁለተኛ ዙር ፈተና መፈተን ይችላሉ ፤ ከዚህ ውጪ ተማሪዎቹ እንዳይፈተኑ በመከልከል ሆን ተብሎ የሚፈጠረው የማጠልሽት ተግባርና ውሸት ለህዝብና አገር አይጠቅምም " በማለት አክለዋል።

ዛሬ በተጀመረው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 36 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
2025/07/01 02:06:18
Back to Top
HTML Embed Code: