Telegram Web
#ጋምቤላ

የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ ከሚከርባቸው አካባቢዎች አንዱ ጋምቤላ ነው። በጋምቤላ ጥምቀት በባሮወንዝ ዳር መከበሩ ልዩ ድምቀትን ይሰጠዋል።

@tikvahethmagazine
#ባቱ

የጥምቀት በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው አካባቢዎች መካከል በባቱ ከተማ  ደምበል ሐይቅ ላይ ያለው አከባበር ነው።

በሐይቁ አምስት ደሴቶች ያሉ ሲሆነ በደሴቶቹ ልክ አምስት አብያተ ክርስቲያናት አሉ። እነሱም፥ የገሊላ ካህናተ ሰማይ፣ የደብረ ሲና ድንግል ማርያም፣ የጠዴቻ አብርሃም፣ የፉንዱሮ አርባዕቱ እንስሳ፣ የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም ናቸው።

የታቦቱ የጀልባ ጉዞ ከሌሎቹ የሚለየውና በዓሉን የሚያደምቀው ሲሆን ከአምስቱ ገዳማት አቡነ ተክለሃይማኖትና ደብረ ጽዮን ከደሴታቸው በመውጣት ሦስት ኪሎ ሜትር የሚሆነውን የሐይቁን ክፍል አቋርጠው ምድር ላይ በዓሉን ያከብራሉ።

@tikvahethmagazine
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በተገኙበት ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በብፁዕ ካስዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን መሪነት በመሥዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በመላው ሀገሪቱ ባሉ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከብሮ የሚውልም ይሆናል። (ሰላም ካቶሊክ ቲቪ)

@tikvahethmagazine
#አዲስአበባ

የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መሪነት በሥርዓተ ጸሎት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።

በአዲስ አበባ በዓለ ጥምቀት በጃን ሜዳ መከበር የጀመረው በ1887 ዓ.ም እንደሆነ ይነገራል። ባህረ ጥምቀቱ ደግሞ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በ1936 ዓ.ም የተሰራ ሲሆን በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ማሻሻያዎች ተደርገውለታል።

በጃን ሜዳ በትላንትናው ዕለት 14 ታቦታት ወደ ጃን ሜዳ ወርደው ያደሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት እንዲሁም በመጪው ቀናት ታቦታቱ ወደ መንበረ ክብራቸው የሚመለሱ ይሆናል።

በአዲስ አበባ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው በውጣት ወደ ወደ ተዘጋጀላቸው 66 ጊዜያዊ ማረፊያ በማምራት በዚያ ያደሩ ሲሆን የጥምቀት በዓል በእነዚህ ቦታዎች ላይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

@tikvahethmagazine
2025/02/02 23:10:18
Back to Top
HTML Embed Code: