Telegram Web
#አፋልጉኝ

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-43717 ኦሮ የሆነ ተሽከርካሪ ቅዳሜ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት1:40 ላይ ሀና ማርያም አከባቢ አቁሞ ቤት ገብቶ ሲመለስ መኪናው መሰረቁን ገልጾልናል።

ቤተሰባችን፥ "በመከራ የገዛሁት 5L ነው በሱ ነዉ እምተዳደረው አሁን ላይ ምንም የቤት ኪራይ ምከፍለዉ የለኝም መኪናውን ያያችሁ ወረታ ከፋይ ነን በዚህ ቁጥር ይደውሉልኝ 0965196715 /0903682823" ሲል የቲክቫህ ቤተሰቦች እንዲተባበሩት ተማጽኗል።

@TikvahethMagazine
😢15761🙏10🤔7🕊4👍2🤯2👎1👏1
🎁ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ  ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
    💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,118 ብር
    💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር  ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር  የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!

☎️ 0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp
16
💡አሁኑኑ የደመወዝ ብድር ያግኙ!

👉ዉል ብቻ ፈርመዉ
👉ወደ አካውንትዎ  ላይ የጠየቁት የደመወዝ ብድር ይገባል
👉ፈጣን እና ቀላል መሙያ
👉ከሉበት ቦታ ሁነው ማመልከት ብቻ
👉በአነስተኛ ያገልግሎት ክፍያ

📲 አሁኑኑ ያመልክቱ፦
🌐 https://forms.gle/9Z4Tys3LqeFTr91v9
📞6575 ሃሎ ይበሉን

💬 አብረን እናሳካለን፤ ሁሉም በ30 ደቂቃ ውስጥ!
12👍2
ሌሴቶ ከስራ አጥነት ጋር በተያያዘ እስከ 2027 የሚቆይ ብሔራዊ የአደጋ አዋጅ አውጃለች።

ሌሴቶ በሃገሯ የስራ አጥ ወጣቶች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ እስከ ሰኔ 2027 ድረስ የሚቆይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ማወጇ ተሰምቷል።

በሌሴቶ የስራ አጥ ምጣኔው 30 በመቶ ሲሆን የስራ አጥ ወጣቶች ምጣኔ ደግሞ 50 በመቶ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን ታሪፉ ለጊዜው እንዲቆም ቢደረግም በትራምፕ የ50 በመቶ የተጣለባት ሌሴቶ ከፍተኛው ታሪፍ የተጣለበት ሃገርም ነበረች።

የታሪፉ መጣል ክፉኛ እንደሚጎዳት ሲጠበቅ መንግስት በታሪፉ ላይ እርግጠኛ ባለመሆኑ ይህንን አዋጅ ማወጁ ተሰምቷል።

2 ሚሊየን ህዝብ ያላት ሌሴቶ በዚህ ጊዜም በጀቷን ለወጣቶች ስራ በሚፈጥሩ ፕሮግራሞች ላይ ታፈሳለች ተብሏል።

ሌሴቶ በአጎዋ ማዕቀፍ ወደ አሜሪካ ገበያ በተለይ የጂንስ ምርቶችን የምታስገባ ሲሆን የታሪፍ ውሳኔውን ተከትሎ ኢንዱስትሪዎቿ መንገዳገድ ጀምረዋል።

ይህም የሆነው በታሪፉ እርግጠኛ ያልሆኑ የአሜሪካ ገዢዎች ምንም ምርት ባለማዘዛቸው ነው ተብሏል።

በተጨማሪ መንግስት በመጪው መስከረም የአጎዋ ቆይታ ካልተራዘመ እስከ 40,000 ሰዎች ስራ እንደሚያጡ አስጠንቅቋል።

ሌሴቶ እስከ ባለፈው መጋቢት ወር ድረስ ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ በአደጋ ጊዜ አዋጅ ስር መቆየቷም ተገልጿል።

SOURCE: BBC

@TikvahethMagazine
41😢6👍4🤣2
ጃፓን የአለማችንን ፈጣኑን የኢንተርኔት ፍጥነት አስመዘገበች።

የጃፓን ተመራማሪዎች በሰከንድ የኢንተርኔትን ፍጥነት 1.02 ፔታባይት ላይ ማድረሳቸው ተዘግቧል።

የጃፓን ሳይንስቲስቶች  በ1118 ማይልስ ርቀት በሰከንድ 1.02 ፔታባይት ዳታ 19-ኮር ኦፕቲካል ፋይበር በመጠቀም አስተላልፈዋል።

በዚህ ፍጥነትም ኔትፍሊክስ ላይ የሚገኙ ፋይሎች በሙሉ በ1 ሰከንድ ውስጥ ከማውረድ በተጨማሪ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የ8K ቪዲዮዎችን በአንድ ጊዜ ማሰራጨት ይቻላል።

ይህ ፍጥነት በአማካይ በአሜሪካ ካለው ፍጥነት በ3.5 ሚሊየን እጥፍ የተሻለ ሲሆን ከህንድ በ16 ሚሊየን እጥፍ የተሻለ ነው።

1.02 ፔታባይት በሰከንድ ማለት 1.02 ሚሊየን ጊጋ ባይት በሰከንድ ማለት ነው።

ይህ ስኬት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ እና ቨርቹዋል ሪያሊቲ እየተመዘገበ ካለው ለውጥ ጋር ተያይዞ ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል።

Source: The Economic Times

@TikvahethMagazine
124🤯35👍19👏18
የስደተኞችን ፍልሰት የማይቀንሱ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት የሚያገኙት ድጋፍ ሊቋረጥ ይችላል ተባለ።

የአውሮፓ ህብረት ወደ አህጉሪቱ ከአፍሪካ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ካልቀነሰ ለአፍሪካ የሚሰጠውን ድጋፍ ሊያቋርጥ እንደሚችል ተዘገበ።

የአውሮፓ ኮሚሽን የ7 አመት የበጀት ዕቅድ ላይ እንደተመላከተው አፍሪካ ከህብረቱ የምታገኘውን የልማት ድጋፍ እንዳይቋረጥባት ከፈለገች ስደተኞችን መቀነስ አለባት።

በዕቅዱ መሰረት የስደተኞችን ፍልሰት የማይቀንሱ ሀገራት የሚደረግላቸው ድጋፍ ይቋረጣል።

ዕቅዱ በ2023 ከሰሜን አፍሪካዊቷ ሃገር ቱኒዚያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ወደ ሌሎች የአህጉሪቱ ሃገራት የሚያስፋፋ ነው ሲባል ይህ የበጀት ዕቅድ በቀጣይ ሳምንት ረቡዕ ይፋ እንደሚሆን እና በህብረቱ ፓርላማ እንደሚፀድቅ ተገምቷል።

እንደ ዊልፍሬድ ማርተንስ ማዕከል በ2023 ወደ አውሮፓ ከገቡ 2.5 ሚሊየን ሰዎች መካከል 17 በመቶ ወይም 470,000 ያህሉ ከአፍሪካ ሲሆን ይህ ቁጥር በህጋዊ መንገድ የገቡትን ብቻ ይመለከታል።

እንደ አለም አቀፉ የስደኞች ድርጅት መረጃ ከሆነ በ2025 ብቻ ከ68 ሺህ በላይ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ሲገቡ ከ900 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ከአፍሪካ በሜድትራንያን በኩል የሚገቡ ሲሆን በሜድትራንያን ባህር ዙሪያ የሚገኙ ሃገራት በተደጋጋሚ ከሰደተኞች ጋር በተያያዘ ሲፈተኑ ይስተዋላል።

Source: Politico

@TikvahethMagazine
55🤣18🤔4😢3👍1🕊1
የአለማችን ትልቁ የካንሰር የጥናት ኢንስቲቲዩት ከድጋፍ መቀነስ ጋር ተያይዞ ችግር ውስጥ መግባቱ ተነገረ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን መምጣት ተከትሎ ለብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩቱ የሚደረግ ድጋፍ በመቀነሱ ተመራማሪዎች መባረራቸው ተገልጿል።

በአሜሪካ በ2023 በካንሰር ምክንያት ከ613 ሺህ በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከልብ ህመም ቀጥሎ ለብዙ ሰዎች ሞት መንስኤ ሆኗል።

ተቋሙ በሚያደርጋቸው ምርምሮች የተነሳ በአሜሪካ ከ1990 ወዲህ የካንሰር ሞት በ34% ቀንሷል ሲባል አሁን የድጋፉ መቋረጥ ተቋሙን ችግር ውስጥ እንደጣለው ተነግሯል።

Source: KFF

@TikvahethMagazine
😢3330🤬5👍1
የኤምሬትስ አየር መንገድ ከደንበኞቹ ክፍያ በክሪፕቶ ከረንሲ ሊቀበል ነው።

ግዙፉ የኤምሬትስ አየር መንገድ ክፍያ በክሪፕፖ መቀበል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከCrypto. Com ጋር መፈራረሙ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ወደ ተግባር ይገባልም ተብሏል።

አየር መንገዱ የስምምነቱ በቴክኖሎጂ ለሚሳቡ ወጣቶች እና ክፍያን በዲጂታል የመገበያያ የገንዘብ አማራጮች መፈፀም ለሚፈልጉ ደንበኞችን ያገናዘበ ነው ብሏል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል መገበያያ ገንዘቦች ማዕከል ስትሆን የትምህርት ክፍያ፣ የትራንስፖርት እና የቤት ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ እንዲከፈል ከዚህ በፊት መፍቀዷም ይታወሳል።

በአካባቢው ያሉ አየር መንገዶች ክሪፕቶከረንሲን እንደ አንድ የመገበያያ አማራጭ እየተቀበሉ ሲሆን ኤይር አረቢያም የጉዞ ትኬት ክፍያን በክሪፕቶከረንሲ መቀበል እንደሚጀምር ማስታወቁ ይታወሳል።

Source: Al Arabiya

@tikvahethMagazine
92🤝7👍4🔥4🤬3👎1🤔1
#HIV_AIDS

አሜሪካ ድጋፍ በማቆረጧ የተነሳ በ2029 ከ4 ሚሊየን ሰዎች በላይ ከኤችአይቪ ኤድስ ጋር በተያያዘ ሊሞቱ እንደሚችሉ ተመድ አስታወቀ።

በአሜሪካ ድጋፍ መቀነስ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት በጊዜ ካልተሞላ በኤችአይቪ ላይ የተመዘገበውን ለውጥ በአስርት አመታት ወደኋላ እንደሚመልሰውም ነው የገለጸው።

ተመድ፥ አሜሪካ ድጋፍ በማቋረጧ በ2029 ተጨማሪ 6 ሚሊየን ሰዎች በበሽታው ሊያዙ እንደሚችሉም አስጠንቅቋል።

በኤድስ የሚያዙ ሰዎች እና በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ከ30 አመት በኋላ ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል ያለ ሲሆን የአሜሪካ ድጋፍ ማቋረጥ የተሰራውን ስራ ወደኋላ ይመልሰዋል ሲል ነው ስጋቱን የገለጸው።

ተመድ በድጋፍ መቋረጡ የተነሳ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት እንደሚጎዱ፤ ሁነቱ ከግጭት፣ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከኢኮኖሚያዊ ኢፍትሃዊነት ጋር ሲዳመር ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል ብሏል።

Source: Al Jazeera

@TikvahethMagazine
😢6760🤣7🙏5🕊5
📍ዱባይ ላይ ባለ 3 መኝታ ቤት ታውን ሃውሶችን ከ 160 ካሬ ጀምሮ በተለያዩ የካሬ አማራጮች ለሽያጭ አቅርበናል።

👉ቪላ ቤቶች
👉 አፓርትመንት

💰3% ቅድመ ክፍያ ብቻ

📌 በረጅም ጊዜ የአከፍፈል ሁኔታ
ለኢትዮጵያኖች በሚመች የአከፍፈል ሁኔታ አቀርንቦሎታል።

📍 በጣም ተፈላጊ በሆነ መገኛ ቦታ                               
  👉 ለኤርፖርት
  👉 ለሞል                   
ለዳውን ታውን የቅርብ እርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ለኑሮ በጣም አመቺ እና ተስማሚ ናቸው

📌እነዚህ ቤቶች እየተገነቡ ያሉት በእውቁ ሊዮስ ኢንተርናሽናል የሪሊስቴት አልሚ ነው  

☎️ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +971529180516 ያገኙናል
12👍4👎3🤝2🕊1
#Et_Coders -- Online Summer Bootcamp & SAT Preparation Program

ልጆችዎ ወይም እርሶ ባሉበት ሆነው የትም ሳይሄዱ በዚህ ክረምት በonline
👉 Computer Basics
👉 Website Development
👉Computer programming(Python)
👉 How to use AI + AI guided website development ይማሩ።

እንዲሁም scholarship apply ለምታደርጉ ለ SAT ፈተናቹ እነዚህን አዘጋጅተናል
🤜በፈተናው መሰረት ሁሉንም የ English Reading/Writing እና Maths topic የተብራራ ጥናት, mock exam መስራት, ከዚህ በፊት ከተፈተኑ ሰዎች የልምድ ልውውጦችን ማግኘት

ምዝገባ ሃምሌ 4 ይጠናቀቃል።
ክፍት ቦታዎች እየሞሉ ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ።


ለመመዝገብ: በስልክ ቁጥራችን
📞0944352126 📞0979779772 ይደውሉ።
ወይም www.etcoders.com ዌብሳይታችንን በመጎብኘት ይመዠገቡ
9👍2
" ከፕላስቲክ አምራቾች የሚነሳው የጊዜ ገደብ አንሷል ጥያቄ ተቀባይነት የለውም"- የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

በቅርቡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 መፅደቁ ይታወሳል።

አዋጁ መጽደቁን ተከትሎ የፕላስቲክ አምራቾች በአዋጁ ላይ የተሰጠን የ6 ወር የሽግግር የጊዜ ገደብ አንሷል፣ ለፕላስቲክ ማምረቻ የገዛናቸው ማሽኖች ከባንክ ተበድረን ነው የሚሉ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በማንሳት በተለያዩ መድረኮች ላይ ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ።

በመሆኑም የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን " ከፕላስቲክ አምራቾች የሚነሳው የጊዜ ገደብ አንሷል ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፣ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች ለመኖር እና ላለመኖር የሚደረግ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል " ብሏል።

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ላይ ለሚዲያ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ላይ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ " ፕላስቲክ አምራቾች ከዘርፉ እንዲወጡ ሲደረግ Recycle የሚደረጉ ምርቶችን እንዲያመርቱ የባንክ ብድሮችን እና ሌሎች አማራጮችን የማመቻቸት " ስራ እየሰሩ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የፕላስቲክ አምራቾች ከዘርፉ እንዲወጡ ሲደረጉ Recycle የሚደረጉ ሞርቶችን እንዲያመርቱ ማበረታታት ያስፈልጋል። ይሄንንም እየሰራን ነው፣ አዋጁ ተግባራዊ የሚደረገው በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሲወጣ ነው። ከታተመ በኋላ የ6 ወር ጊዜ አላቸው። በአጠቃላይ ሌሎች ጊዜዎችን ስንጨምራቸው አንድ አመት የሚሆን የሽግግር ጊዜ አላቸው ።

" ድርጅቶች ይሄ ስራ ያዋጣናል ብለው ነው የጀመሩት፣ በአግባቡ ሽፍት የሚያደርጉበትን ወይም የሚታገዙበትን  መንገድ ማየት ግድ ይለናል። ለዚህም ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከባንኮች ጋር ውውይት እየተደረገ ነው። ይሄ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል። አዋጁ ከወጣ በኋላ ብዙዎቹም Recycle የሚደረጉ ምርቶችን ወደ ማምረት እየገቡ ነው" ።

በአዋጁ ላይ የተለያዩ አካላት በሌሎች ሀገሮች የ3 አመት የጊዜ ገደብ ይሰጣሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ 6 ወር ብቻ ነው፣ ይህ አምራቾችን ይጎዳል የሚሉ ሀሳቦች እየተነሱ ነው ያሉት ዳይሬክተሯ ነገር ግን እውነታው የትኛውም ሀገር ከ6 ወር በላይ የሽግግር ጊዜ አልሰጠም፣ እንደምሳሌነትም ኬኒያን ማየት ይቻላል ነው ያሉት።

አክለው በእኛ በኩል ያሉ ክፍተቶችን ለማረም እና የአምራቾችን ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉን ጉዳዮች ላይ ለመወያየት አምራቾችን ጨምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቅርቡ ሊወያዩ መሆኑን ነው የጠቆሙት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@TikvahethMagazine
27👎20👍5🤔3🙏1
በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው።

አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ተቋማት የትኞቹ ናቸው ?

- ንግድ ቢሮ፣

- ገቢዎች ቢሮ፣

- መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣

- መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣

- ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን፣

- ህብረት ስራ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ በተጠቀሰው መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

@TikvahethMagazine
👎15978🤣36👍32🤔9🤷‍♂2🕊2🤬1
2025/07/13 00:10:30
Back to Top
HTML Embed Code: