Telegram Web
ዶናልድ ትራምፕ የላይቤሪያ አቻቸውን እንግሊዝኛን የት እንደተማሩ መጠየቃቸው አነጋጋሪ ሆኗል!

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ5 የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ጋር በነጩ ቤተመንግሥት ተገናኝተው መክረዋል።

ትራምፕ ያገኟቸው የሴኔጋል፣ ላይቤሪያ ፣ ጊኒቢሳው ፣ ሞሪታኒያ እና ጋቦን መሪዎችን ነው።

ውይይቱ በሃገራቱ እና አሜሪካ መካከል ያለውን የውድ ማዕድናት ንግድ በተመለከተ ነው ሲባል ትራምፕ ሃገራቸው ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ ያለ ድካም እየሰራች መሆኗን ገልፀዋል።

ትራምፕ" ከእርዳታ ወደ ንግድ ፊታችንን አዙረናል" ያሉ ሲሆን አምስቱ ሃገራት በመጪው ነሐሴ 1 ከሚጣለው ታሪፍም ነፃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅትም ትራምፕ የላይቤሪያውን ፕሬዚዳንት እንግሊዝኛ ማድነቃቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

ትራምፕ የላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦኣካይ ንግግር ካደረጉ በኋላ "በጣም ጥሩ እንግሊዝኛ ነው፤ እንደዚህ በቆንጆ ሁኔታ መናገርን የት ነው የተማርከው "ሲሉ ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንት ቦኣካይም እንግሊዝኛ የሃገራቸው የስራ ቋንቋ መሆኑን ሳይነግሯቸው ለትራምፕ በላይቤሪያ መማራቸው ገልፀዋል።

ትራምፕ የላይቤሪያ የስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሆኖ ሳለ ይህንን ነገር መጠየቃቸው ግርምትን ጭሯል።

ትራምፕም በጣም ቆንጆ እንግሊዘኛ እንደተናገሩ በመግለፅ በዚህ ጠረጴዛ ላይ መጥተው በአግባቡ መናገር የማይችሉ ሰዎችን እንዳስተናገዱ ተናግረዋል።

Source: UPI, SKY NEWS

@TikvahethMagazine
🤣17875🤔12🤬9👍2👎1
በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፉ ያሉ ቁጥራዊ መረጃዎች፦

ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን ይፋ ሲያደርግ የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፉ የዲጂታል አካውንቶች ብዛት ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው በ16 በመቶ በመጨመር 222.1 ሚሊየን መድረሱን ገልጿል።

የዲጂታል ግብይቶች ብዛት በአንጻሩ በ68 በመቶ በመጨመር 3.02 ቢሊየን መድረሱንና በእነዚህ የዲጂታል የገንዘብ ዝውውሮች የተፈፀመ የግብይት መጠን በ87 በመቶ በመጨመር 12.5 ትሪሊየን ብር መሆኑን ገልጿል።

ባንኩ፥ የኤቲኤሞች ብዛት በ18 በመቶ ፣ የፖስ ማሽኖች ብዛት በ35 በመቶ እንደዚሁም የሞባይል ገንዘብ ወኪሎቸ ቁጥር በ56 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል።

የሞባይል ወኪሎች ቁጥር ደግሞ 56 በመቶ እድገት በማሳየት 508,367 የሞባይል ገንዘብ ወኪሎች መኖራቸውን አስታውቋል።

በአጠቃላይ የዲጂታል ብድር በተመለከተም 27 ቢሊየን ብር መድረሱን ሲገልፅ የዲጂታል ቁጠባ ደግሞ 8 ቢሊየን ብር ሆኗል ተብሏል።

መረጃው የብሔራዊ ባንክ ነው።

@TikvahethMagazine
37👍2
የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ዘርፍ የገቢያ ድርሻና ውድድር ምን ይመስላል ?

በኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ዘርፍ ገበያው አብዛኛው ድርሻ በአንድ አካል የበላይነት የተያዘ መሆኑ ቁጥራዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። ለዚህም አዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡ ተቋማት ተወዳዳሪ ይሆናሉ ወይ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

ቁጥራዊ መረጃዎች ምን ይላሉ ?

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከ222.1 ሚሊየን በላይ የሞባይል ገንዘብ አካውንቶች ያሉ ሲሆን 52.5 ሚሊየን የሚሆኑት የቴሌብር ተጠቃሚዎች ናቸው።

7.5  ሚሊየም ዜጎች የቴሌ ብር ሱፐር አፕ ተጠቃሚ ሲሆኑ በቴሌብርም 4.18 ትሪሊየን ብር የገንዘብ ዝውውር መከናወኑን ኩባንያው ከወራት በፊት "ዘመን" የተሰኘ ዲጂታል ገበያን ይፋ ባደረገበት ወቅት አስታውቆ ነበር።

በተመሳሳይ ወቅት በወጣ መረጃ በሳፋሪኮም ስር በሚገኘው የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ M-PESA 2.4 ሚሊዮን የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞችን በማገልገል 15.8 ቢሊዮን ብር ዝውውር መፈጸሙ ተገልጿል።

የሞባይል ገንዘብ አካውንቶችን በተመለከተ ከቴሌብር ቀጥሎ በሁለተኝነት የተቀመጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ ሲቢኢ ብር አገልግሎት ሲሆን በቅርብ በወጡ መረጃዎች ባንኩ ከ34 ሚሊየን በላይ የሞባይል ገንዘብ አካውንቶች ማስከፈት ችሏል።

ለመሆኑ ጎረቤት ሀገር ኬንያ ያለው የገቢያ ውድድር ምን ይመስላል ?

በኬንያ በገበያው ላይ በንቃት የሚሳተፉትን የሳፋሪኮሙ ኤምፔሳ እና በኤይርቴል መካከል ያለውን የገቢያ ድርሻ መረዳት የተወሰነ ግንዛቤን ይሰጣል።

በኬንያ የሞባይል ገንዘብ ገበያ ውስጥ ኤምፔሳ ለረጅም ጊዜ ተወዳዳሪ ያልነበረው ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን የገበያ ድርሻ ይይዝ ነበር።

በኋላ ኤይርቴል ኤምፔሳን ከመምሰል ይልቅ በኤምፔሳ የማይሸፈኑ የነበሩትን አካባቢዎች እንደዚሁም አገልግሎቶች ማቅረብ ጀመረ።

አሰራራቸውን ቀላል በማድረግ ደንበኞችን መሳብ፣ ከናይሮቢ ወጥተው በገጠር ገብተው ደንበኞችን ማፍራቱን ተያያዙት።

ቁጥር ላይ ትኩረት ከማድረግ ጥራት እና ተደራሽነት ላይ መስራት መረጡ፣ ከባንኮች እና ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር ተቀናጅተው መስራት ጀመሩ።

ከዛ በኋላ የኤይርቴለ የሞባይል ገንዘብ ወኪሎች ድርሻ ከነበረበት 8 በመቶ ወደ 27.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየት ቻለ። ኤምፔሳ በገበያው ውስጥ የነበረው ድርሻም ከ92 በመቶ ወደ 66 በመቶ ወረደ።

ኤይርቴል በ2023 በየወሩ ከ60 ሚሊየን በላይ ዝውውሮችን በተሳካ ሁኔታ ሲፈፅም በ2022 ከነበረው በእጥፍ ያደገም ነበር።

በ2020 ከነበሩት 18,000 ወኪሎችም የወኪሎቹን ቁጥር ወደ 70,000 ከፍ ማድረግ ችሏል።

ኤይርቴል እዛው በሚካሄዱ የእርስ በእርስ ዝውውሮች ምንም ክፍያ የማያስከፍል ሲሆን አጠቃላይ ገንዘብ የማውጣት ወጪም(Withdrawal Cost) ከኤምፔሳ አንፃር በ40 በመቶ ያነሰ ነው።

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት አንዱ ከአንዱ ገልብጦ ከመመሳሰል እና አንድ አይነት ስትራቴጂን ከመከተል የገበያ ድርሻቸውን ለማሳደግ በልዩነት ወጥተው መታየት እና የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ይጠበቃል።

የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት እንደሚጠቁመው የባንክ አካውንት ያላቸው አዋቂዎች ቁጥር ከግማሽ በመቶ ብዙም የተሻገረ አይደለም። የባንኩ ብሄራዊ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ -2 / 2021 ይህንን ቁጥር በ2025 70 በመቶ የማዳረስ እቅድ ያስቀመጠ ነው።

@TikvahethMagazine
66👍4👎4
#አፋልጉን

ሙሉ ኦሪጅናል ዶክመንት በፓስታ የታሸገ ቀን 2 /11/2017 አዲስአበባ ውስጥ በባስ ስንቀሳቀስ ሲሆን የጠፋብን ያገኛችሁ በስልክ ቁጥር 0911986377 ይደውሉልን ወሮታውን እንከፍላለን።

@TikvahethMaazine
🙏3822👍12🤣9
የኬንያው ፕሬዚዳንት ፖሊሶቻቸው በተቃውሞ በወጡ ሰዎች እግር ላይ እንዲተኩሱ ትዕዛዝ ሰጡ።

ፕሬዚዳንቱ ውሳኔውን ያስተላለፉት ቢዝነሶችን የሚያስተጓጉሉ ተቃዋሚዎች ላይ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎች እግራቸው ላይ እንዲተኩሱ ማዘዛቸው ነው የተነገረው።

በኬንያ ከሳምንታት በፊት የጀመረው ተቃውሞ ቀጥሎ እስካሁን ከ31 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ከሰኞ ጀምሮ በናይሮቢ አብዛኛው ሱቆች ዝግ ሆነው ቆይተዋል። በተቃውሞ ወቅትም ሱፐር ማርኬቶች እና ሆስፒታሎች መጎዳታቸውና መዘረፋቸው ተነግሯል።

ፕሬዚዳንት ሩቶ "የሰዎችን ንብረት የሚያቃጥል ሰው በጥይት እግሩ መመታት አለበት" ያሉ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎቻቸው ሰዎችን እንዳይገድሉ አስጠንቅቀዋል።

ባለፈው ዓመት በኬንያ ከታክስ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በርካቶች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ወር ደግሞ ታዋቂው ፀሐፊ በእስር ቤት ውስጥ መሞቱን ተከትሎ ተቃውሞ ዳግም መቀስቀሱ ይታወሳል።

Source: Reuters

@TikvahethMagazine
46🤬46👍10🤣10👎7🤯3😢3🕊2💔2🙏1
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) መጥፎ ገጽታው!

በህክምና ላይ የሚሰሩ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ፕሮግራሞች የሰዎችን ቀለም ወይም ዘር ሲያውቁ የተሳሳተ ግንዛቤ እየያዙ መሆናቸው ጥናት አመላክቷል።

በNPJ የህክምና ጆርናል ላይ የወጣው ምርምር እንደሚያሳየው ፕሮግራሞቹ የአዕምሮ ህመም ያጋጠማቸው ሰዎች አፍሪካ አሜሪካውያን መሆናቸውን ሲያውቁ ይሰጡት የነበረው የህክምና ምክር ተቀይሯል።

ፕሮግራሙ፥ ታማሚዎችን ምን ያህል መለየት እንደሚችሉ እና የህክምና ምክር መስጠት እንደሚችሉ ሲሞከር ይህ ነገር ማጋጠሙ ነው የተነገረው።

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፕሮግራሞቹ በመጀመሪያ ምንም የዘሩ ቀለሙ ሳይነገራቸው፣ በሁለተኛው አፍሪካ አሜሪካዊ እንደሆነ ተነግሯቸው በሶስተኛው ደግሞ በስሙ ላይ ተመስርተው ዘሩን እንዲያውቁ ተደርጎ ሙከራ ሲደረግባቸው ለየት ያለ ነገር ማሳየታቸው ተነግሯል።

ፕርግራሞቹ ታካሚው አፍሪካ አሜሪካዊ መሆኑን ሲያውቁ የተለያየ ምክር የሰጡ ሲሆን ሁለት ፕሮግራሞች ደግሞ ምንም አይነት ምክር እና እገዛ ለማድረግ አልፈለጉም ተብሏል።

አንዳንዶቹ ፕሮግራሞች ጭንቀት ውስጥ ላሉ የአፍሪካ አሜሪካውያን ታካሚዎች የአልኮል መጠን እንዲቀንሱ እና ጥበቃ እንዲደረግላቸው መክረዋል።

ተመራማሪዎች ፕሮግራሞቹ በተሰጣቸው መረጃ መሰረት እንደሚመልሱ በመግለፅ  መረጃ በሚሰጣቸው ወቅት ጥንቃቄ ካልተደረገ ከባድ ጥፋትን እንደሚያስከትሉ አስጠንቅቀዋል።

Source: US news

@TikvahethMagazine
🤣6749🤬8👍5😢5🕊3🤔2👎1
#አፋልጉኝ

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-43717 ኦሮ የሆነ ተሽከርካሪ ቅዳሜ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት1:40 ላይ ሀና ማርያም አከባቢ አቁሞ ቤት ገብቶ ሲመለስ መኪናው መሰረቁን ገልጾልናል።

ቤተሰባችን፥ "በመከራ የገዛሁት 5L ነው በሱ ነዉ እምተዳደረው አሁን ላይ ምንም የቤት ኪራይ ምከፍለዉ የለኝም መኪናውን ያያችሁ ወረታ ከፋይ ነን በዚህ ቁጥር ይደውሉልኝ 0965196715 /0903682823" ሲል የቲክቫህ ቤተሰቦች እንዲተባበሩት ተማጽኗል።

@TikvahethMagazine
😢14959🙏10🤔5🕊4👍2🤯2👎1👏1
🎁ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ  ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
    💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,118 ብር
    💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር  ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር  የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!

☎️ 0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp
13
💡አሁኑኑ የደመወዝ ብድር ያግኙ!

👉ዉል ብቻ ፈርመዉ
👉ወደ አካውንትዎ  ላይ የጠየቁት የደመወዝ ብድር ይገባል
👉ፈጣን እና ቀላል መሙያ
👉ከሉበት ቦታ ሁነው ማመልከት ብቻ
👉በአነስተኛ ያገልግሎት ክፍያ

📲 አሁኑኑ ያመልክቱ፦
🌐 https://forms.gle/9Z4Tys3LqeFTr91v9
📞6575 ሃሎ ይበሉን

💬 አብረን እናሳካለን፤ ሁሉም በ30 ደቂቃ ውስጥ!
9👍1
ሌሴቶ ከስራ አጥነት ጋር በተያያዘ እስከ 2027 የሚቆይ ብሔራዊ የአደጋ አዋጅ አውጃለች።

ሌሴቶ በሃገሯ የስራ አጥ ወጣቶች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ እስከ ሰኔ 2027 ድረስ የሚቆይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ማወጇ ተሰምቷል።

በሌሴቶ የስራ አጥ ምጣኔው 30 በመቶ ሲሆን የስራ አጥ ወጣቶች ምጣኔ ደግሞ 50 በመቶ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን ታሪፉ ለጊዜው እንዲቆም ቢደረግም በትራምፕ የ50 በመቶ የተጣለባት ሌሴቶ ከፍተኛው ታሪፍ የተጣለበት ሃገርም ነበረች።

የታሪፉ መጣል ክፉኛ እንደሚጎዳት ሲጠበቅ መንግስት በታሪፉ ላይ እርግጠኛ ባለመሆኑ ይህንን አዋጅ ማወጁ ተሰምቷል።

2 ሚሊየን ህዝብ ያላት ሌሴቶ በዚህ ጊዜም በጀቷን ለወጣቶች ስራ በሚፈጥሩ ፕሮግራሞች ላይ ታፈሳለች ተብሏል።

ሌሴቶ በአጎዋ ማዕቀፍ ወደ አሜሪካ ገበያ በተለይ የጂንስ ምርቶችን የምታስገባ ሲሆን የታሪፍ ውሳኔውን ተከትሎ ኢንዱስትሪዎቿ መንገዳገድ ጀምረዋል።

ይህም የሆነው በታሪፉ እርግጠኛ ያልሆኑ የአሜሪካ ገዢዎች ምንም ምርት ባለማዘዛቸው ነው ተብሏል።

በተጨማሪ መንግስት በመጪው መስከረም የአጎዋ ቆይታ ካልተራዘመ እስከ 40,000 ሰዎች ስራ እንደሚያጡ አስጠንቅቋል።

ሌሴቶ እስከ ባለፈው መጋቢት ወር ድረስ ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ በአደጋ ጊዜ አዋጅ ስር መቆየቷም ተገልጿል።

SOURCE: BBC

@TikvahethMagazine
35😢5👍2🤣2
ጃፓን የአለማችንን ፈጣኑን የኢንተርኔት ፍጥነት አስመዘገበች።

የጃፓን ተመራማሪዎች በሰከንድ የኢንተርኔትን ፍጥነት 1.02 ፔታባይት ላይ ማድረሳቸው ተዘግቧል።

የጃፓን ሳይንስቲስቶች  በ1118 ማይልስ ርቀት በሰከንድ 1.02 ፔታባይት ዳታ 19-ኮር ኦፕቲካል ፋይበር በመጠቀም አስተላልፈዋል።

በዚህ ፍጥነትም ኔትፍሊክስ ላይ የሚገኙ ፋይሎች በሙሉ በ1 ሰከንድ ውስጥ ከማውረድ በተጨማሪ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የ8K ቪዲዮዎችን በአንድ ጊዜ ማሰራጨት ይቻላል።

ይህ ፍጥነት በአማካይ በአሜሪካ ካለው ፍጥነት በ3.5 ሚሊየን እጥፍ የተሻለ ሲሆን ከህንድ በ16 ሚሊየን እጥፍ የተሻለ ነው።

1.02 ፔታባይት በሰከንድ ማለት 1.02 ሚሊየን ጊጋ ባይት በሰከንድ ማለት ነው።

ይህ ስኬት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ እና ቨርቹዋል ሪያሊቲ እየተመዘገበ ካለው ለውጥ ጋር ተያይዞ ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል።

Source: The Economic Times

@TikvahethMagazine
95🤯30👍16👏15
የስደተኞችን ፍልሰት የማይቀንሱ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት የሚያገኙት ድጋፍ ሊቋረጥ ይችላል ተባለ።

የአውሮፓ ህብረት ወደ አህጉሪቱ ከአፍሪካ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ካልቀነሰ ለአፍሪካ የሚሰጠውን ድጋፍ ሊያቋርጥ እንደሚችል ተዘገበ።

የአውሮፓ ኮሚሽን የ7 አመት የበጀት ዕቅድ ላይ እንደተመላከተው አፍሪካ ከህብረቱ የምታገኘውን የልማት ድጋፍ እንዳይቋረጥባት ከፈለገች ስደተኞችን መቀነስ አለባት።

በዕቅዱ መሰረት የስደተኞችን ፍልሰት የማይቀንሱ ሀገራት የሚደረግላቸው ድጋፍ ይቋረጣል።

ዕቅዱ በ2023 ከሰሜን አፍሪካዊቷ ሃገር ቱኒዚያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ወደ ሌሎች የአህጉሪቱ ሃገራት የሚያስፋፋ ነው ሲባል ይህ የበጀት ዕቅድ በቀጣይ ሳምንት ረቡዕ ይፋ እንደሚሆን እና በህብረቱ ፓርላማ እንደሚፀድቅ ተገምቷል።

እንደ ዊልፍሬድ ማርተንስ ማዕከል በ2023 ወደ አውሮፓ ከገቡ 2.5 ሚሊየን ሰዎች መካከል 17 በመቶ ወይም 470,000 ያህሉ ከአፍሪካ ሲሆን ይህ ቁጥር በህጋዊ መንገድ የገቡትን ብቻ ይመለከታል።

እንደ አለም አቀፉ የስደኞች ድርጅት መረጃ ከሆነ በ2025 ብቻ ከ68 ሺህ በላይ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ሲገቡ ከ900 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ከአፍሪካ በሜድትራንያን በኩል የሚገቡ ሲሆን በሜድትራንያን ባህር ዙሪያ የሚገኙ ሃገራት በተደጋጋሚ ከሰደተኞች ጋር በተያያዘ ሲፈተኑ ይስተዋላል።

Source: Politico

@TikvahethMagazine
48🤣16🤔4😢3👍1🕊1
የአለማችን ትልቁ የካንሰር የጥናት ኢንስቲቲዩት ከድጋፍ መቀነስ ጋር ተያይዞ ችግር ውስጥ መግባቱ ተነገረ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን መምጣት ተከትሎ ለብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩቱ የሚደረግ ድጋፍ በመቀነሱ ተመራማሪዎች መባረራቸው ተገልጿል።

በአሜሪካ በ2023 በካንሰር ምክንያት ከ613 ሺህ በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከልብ ህመም ቀጥሎ ለብዙ ሰዎች ሞት መንስኤ ሆኗል።

ተቋሙ በሚያደርጋቸው ምርምሮች የተነሳ በአሜሪካ ከ1990 ወዲህ የካንሰር ሞት በ34% ቀንሷል ሲባል አሁን የድጋፉ መቋረጥ ተቋሙን ችግር ውስጥ እንደጣለው ተነግሯል።

Source: KFF

@TikvahethMagazine
😢2921🤬3👍1
የኤምሬትስ አየር መንገድ ከደንበኞቹ ክፍያ በክሪፕቶ ከረንሲ ሊቀበል ነው።

ግዙፉ የኤምሬትስ አየር መንገድ ክፍያ በክሪፕፖ መቀበል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከCrypto. Com ጋር መፈራረሙ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ወደ ተግባር ይገባልም ተብሏል።

አየር መንገዱ የስምምነቱ በቴክኖሎጂ ለሚሳቡ ወጣቶች እና ክፍያን በዲጂታል የመገበያያ የገንዘብ አማራጮች መፈፀም ለሚፈልጉ ደንበኞችን ያገናዘበ ነው ብሏል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል መገበያያ ገንዘቦች ማዕከል ስትሆን የትምህርት ክፍያ፣ የትራንስፖርት እና የቤት ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ እንዲከፈል ከዚህ በፊት መፍቀዷም ይታወሳል።

በአካባቢው ያሉ አየር መንገዶች ክሪፕቶከረንሲን እንደ አንድ የመገበያያ አማራጭ እየተቀበሉ ሲሆን ኤይር አረቢያም የጉዞ ትኬት ክፍያን በክሪፕቶከረንሲ መቀበል እንደሚጀምር ማስታወቁ ይታወሳል።

Source: Al Arabiya

@tikvahethMagazine
72🤝7🔥4👍3🤬3🤔1
#HIV_AIDS

አሜሪካ ድጋፍ በማቆረጧ የተነሳ በ2029 ከ4 ሚሊየን ሰዎች በላይ ከኤችአይቪ ኤድስ ጋር በተያያዘ ሊሞቱ እንደሚችሉ ተመድ አስታወቀ።

በአሜሪካ ድጋፍ መቀነስ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት በጊዜ ካልተሞላ በኤችአይቪ ላይ የተመዘገበውን ለውጥ በአስርት አመታት ወደኋላ እንደሚመልሰውም ነው የገለጸው።

ተመድ፥ አሜሪካ ድጋፍ በማቋረጧ በ2029 ተጨማሪ 6 ሚሊየን ሰዎች በበሽታው ሊያዙ እንደሚችሉም አስጠንቅቋል።

በኤድስ የሚያዙ ሰዎች እና በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ከ30 አመት በኋላ ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል ያለ ሲሆን የአሜሪካ ድጋፍ ማቋረጥ የተሰራውን ስራ ወደኋላ ይመልሰዋል ሲል ነው ስጋቱን የገለጸው።

ተመድ በድጋፍ መቋረጡ የተነሳ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት እንደሚጎዱ፤ ሁነቱ ከግጭት፣ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከኢኮኖሚያዊ ኢፍትሃዊነት ጋር ሲዳመር ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል ብሏል።

Source: Al Jazeera

@TikvahethMagazine
😢3213🙏4🕊1
2025/07/12 00:51:52
Back to Top
HTML Embed Code: