Telegram Web
ለመንፈሳዊ ዩቲዩብ ቻናል (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ) ጋዜጠኛ ይፈለጋል

መንፈሳዊ ትረካዎችን
ቃለ መጠይቆችንና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶችን የመስራት በቂ ጊዜና ችሎታው ያላችሁ በተከታዮቹ አድራሻዎች አግኙን

ደሞዝ በስምምነት
ስልክ:- +251965135434
Telegram:-  @JOEth86
እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
በተጨማሪም ዛሬ የቃና ዘገሊላ ትክክለኛ ዕለቱ ነው እስራኤላውያን ሠርግ የሚደግሱት ለሰባት ቀናት ነው ሠርጉ የተጀመረው የካቲት 20 ነው ጌታ የተገኘው በሦስተኛው ቀን ማለትም የካቲት 23 ቀን ነው አባቶች የካቲት ወር ብዙ ጊዜ ዓብይ ጾም ላይ ስለሚውል የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር አብሮ ማክበር ይገባል ብለው እንድናከብር አድርጓል አንድም በአክሱም ከተማ ጥር 12 ቀን ደጋግ ሰዎች ማኅበር በሚጠጡበት ጌታ በአካል ተገኝቷልና ይህችውም ማኅበረ ደጔ ትባላለች። በእነዚህ ምክንያቶች ጥር 12 ቀን እንዲከበር ተደርጓል። ስለዚህ በሦስተኛው ቀን ሲል ከፊት አራት ቀናት ይቀራሉ ግን በሦስተኛው ቀን ማለቱ በዚህ ቀን ወይኑ ስላለቀ ነው። በቃና መንደር የተደረገው ሠርግ ደጋሹ ዶኪማስ ይባላል ሙሽራው ባቲለስ ሙሽራይቱ ዮአጊን ይባላሉ። ዶኪማስ የእመቤታችን ዘመድ ስለሆነ ጠርቷታል እመቤታችን ሠርጉ ቀድማ ተገኝታለች። ቃና ሠርግ ላይ ውኃ ተሞልቶባቸው የነበሩ ድንጋዮች እብነ አልማስ (የአልማስ ድንጋይ) ይባላሉ። ጌታችን ጋብቻን ለመባረክ ወደ ሠርግ ቤት መጥቷል ግን በቃና ሠርግ ጌታ ደቀመዛሙርቱ ብቻ አልተገኙም መላእክትም ተገኝቷል ግን ስለማይበሉ አልተጻፈም። በዚህ ጊዜ ነው ወይኑ ስላለቀ እመቤታችን
ምልጃዋ የተገለጠበት ጌታችንም አምላክነቱን ያሳየበት ነው ጌታችን ውኃውን ወደ ወይን የቀየረበት የወይኑም ጣዕም እጅግ በጣም ለየት ያለና ቃና የሚለው ቃል ጣዕምን የሚገልጽ ቃል የሆነበት ነው።
አንድ ሰው ውሃ አቅርቦ በራሱ ላይ በማፍሰስ ምሥጢረ ጥምቀትን መፈጸም እንደማይችል ሁሉ ሥርዓተ ጋብቻንም ከቤተ ክርስቲያን ውጪ መፈጸም አይችልም ምክንያቱም ከ7ቱ ምሥጢራት አንዱ ጋብቻ ነውና።
ቅበላ ማለት ክርስቶስን መቀበል እንጂ ስጋን እንደ አንበሳ መቀበል መብላት አይደለም ክርስቶስን የምንቀበልበት ጊዜ ማለት ነው።

መልካም ፆም 🙏
መምህር ካሣሁን እንግዳ በአድዋ ጦርነት ጊዜ የአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት ተሸክመው በባዶ እግራቸው የዘመቱ አባታችን ናቸው!
በረከታቸው ይደርብን!

ዓድዋ የዘመቱ ፈረሶችና የተያዙ ቁሳቁሶች ታሪካቸው ተመዝግቦ በሙዝየም ሲቀመጥ ታቦት ተሸክመው የወጡ ካህናት ታሪካቸው ይካተት ማለት ቦታውን የሃይማኖት ተቋም ለማድረግ ሳይሆን ታሪክ መቀነስ ስለሌለበት ነው!
ፍቅረ ኢየሱስ(ብንያም)ሌላ እህት ማርኮ በማምጣት አስጠመቀ::ሙሉን መረጃ በነገው ጉባኤ ላይ እንገልጠዋለን::ድል ለተዋህዶ::
Forwarded from @ነቅዐጥበብ
ይህ ከታች የተያያዘው ምስል የአንድ አክተር (ተዋናይ) ፎቶ እንጂ የጌታችን ሥዕለ አድኅኖ አይደለም!!!
በተቻለ መጠን ቅዱሳት ሥዕላትን መጠቀም ያስፈልጋል
አባቶቻችን በቅዱሳት ሥዕላት ላይ ያላቸው ጥንቃቄ አስገራሚ ነው!
በቅዱሳት ሥዕላት በኩል
• ሃይማኖት
• ትምህርት
• ምድራዊና ሰማያዊ ምሥጢራት
• በረከት
• ታሪክ ይተላለፉባቸዋል

ስለሆነም ስለ ጌታችን ሕማም ስለ ስቅለቱ ስንጽፍ ይህንን ፎቶ ባንጠቀምና በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት ቅዱሳት ሥዕላትን ብንጠቀም ለማለት እወዳለሁ

እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ፃማ ወድካም
ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም

አሜን!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
የቴሌግራም ቻናሌ👇
https://www.tgoop.com/QH7OEcjEvXswNDc8
2025/02/17 02:02:23
Back to Top
HTML Embed Code: