የፍጥረት ሁሉ ደስታ - ልደታ ለማርያም
ግንቦት አንድ ቀን የእመቤታችን የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት ስለሆነ የደስታችን ቀን ነው፡፡ የቀደሙ አባቶቻችን ሁሉ በፍጹም ደስታ ያሳለፉት ቀን ነው፡፡
የልደቷ ቀን የሐና የደስታ ዕለት ነበር፤ "አንች ያልወለድሽ መካን ሆይ ደስ ይበልሸ የሚለውን ቃል ሰምታበታለችና" /ኢሳ 54፤1/፡፡ የልደቷ ቀን የኢያቄም የደስታ ዕለት ነበር፡፡ ከዕሴይ ግንደ በትር ይወጣል /ኢሳ 11፤1/ የሚለው ቃለ ነቢይ በውድ ልጁ ሲፈጸምና በበትሩ ሠራዊተ አጋንንትን ሲርቁ አይቷልና፡፡
በእርሷ ልደት ነቢያት ሁሉ ተደስተዋል፡፡ ትንቢታቸው ፍጻሜ ሲደርስ ፤ የንባባቸው መንፈሰ ሲገለጥ፣ ሕግ ለጸጋ፣ ኦሪት ለወንጌል ሊያስረክቡ፣ ነገደ ሌዊ ሊቀ ካህንነቱን ለነገደ ይሁዳ ሊያስረክብ ሲሰላለፉ አይተዋልና፡፡ የእርሷ ልደት የያዕቆብ ፍጹም ደስታ ነበረ፡፡ በሕልሙ ከመሬት እስከ ሰማይ ተዘርግታ ያያት መሰላል በእውን ከምድር ወደ ላይ በቅድስና ስትደርስ ለማየት በቅቷልና፡፡ ራስዋ ላይ እግዚአብሔር የተቀመጠባት እውነተኛዋ መሰላላችን በርግጥም ድንግል ማርያም ናት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራስ ወንድ ነው/1ኛ ቆሮ 11፤1/ አለ፡፡ የእርሷ ራስ ግን ያዕቆብ እንዳየው እግዚአብሔር ነው፡፡ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ያለችው ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራሰ ያለው ወንድ በእርሷ ዘንድ ስላልነበረ ነውና፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ልዩ መሆኗን ስለሚያውቅ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሺ፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ጽንስሽም እንደ ሌሎቹ ሴቶች አይደለም እያለ ሲሰግድላትና ሲያመሰግናት እርሱን አልፋ ለእግዚአብሔር መቀመጫ ዙፋን ማደሪያ መቅደስ መሆኗን ያየው አባታችን ያዕቆብ በእውነት ደስ አለው፡፡
አብርሃም ልጁን ይስሐቅን የተቤዠለትን አማናዊ በግ ይዛለት የምትወርደውን ዕፀ ሳቤቅ ተወልዳ አይቶ ደስ አለው፡፡ እርሷ ስትወለድ ያች ያያት ቀን መድረሷን አውቆ ፍጹም ደስ አለው፡፡ ይስሐቅም ከታሰረበት ያስፈታችውን ስለእርሱ ፋንታ ቤዛውን ይዛለት ከች ያለችውን ስትወለድ አይቶ በደስታ ቃል ዘለለ፡፡ ከሲኦል እስራት የሚፈታበት ቀንም እንደ ደረሰ በእርሷ ልደት ደወሉን ሰምቷልና ፈነደቀ፡፡
ሙሴ በእርሷ ልደት በደስታ ብዛት ቦረቀ፡፡ ከሩቅ ያያት የማትቃጠል ቁጥቋጦ በሐና ጭን ቁጭ ብላ ሲያይ እንደገነና ወደ እርሷ ሊገሰግስ ወደደ፤ ያኔ ጫማህን አውልቅ ያለውን ድምጽ አቃጨለበትና ባለበት ቆሞ ያያት ጀመር፡፡ ሲያያት ሕብረ ብዙ ሆና አስደነቀችው፡፡ ኦሪትን በሥነ ፍጥረት ሲጀምር በሁለተኛው ቀን ሰኞ እግዚአብሔር ከውኃ ጠፈር ያለውን ሰማይ እንዳሳየው ዛሬ ደግሞ ከመሬት አዳም የተወለደችውን ድንግል አዲስ ሰማይ ሁለተኛ ሰማይ አድርጎ ሲያሳየው ተገረመ፡፡ ያኛው ሰማይ ለዚህ ዐለም ፀሐይ ሲዘጋጅ ወደ ኋላ እንዳየ አሁን ደግሞ የአማናዊው የጽድቅ ፀሐይ መውጫ ስትወለድ ፀሐዩን ሊሞቅ ጊዜው መድረሱን አይቶ ተደሰተ፡፡ እንደገና ሲያያት ደግሞ አሁንም ሕብሯን ለውጣ ታየችው፡፡ ምደር ከመረገሟ በፊት ያለ ዘር ዕፀዋት አዝርእትን ስታበቅል አይቶ የነገረን ሙሴ ከእናቱ ከሔዋን ልጆች ሆና መርገም ያላረፈባት ያለወንድ ዘር የሕይወት እንጀራ ሆኖ የሚሰጠውን ፍሬ የምታስገኘውን አማናዊት ገራኅተ ሠሉስ አይቶ እንደገና አደነቀ፡፡
ሙሴ ከተመስጦ አልተመለሰም፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንደ ጣት አድርጎ በጽላት ላይ ቃሉን ጽፎ የሰጠው እርሱ አካላዊ ቃል ሰው ሆኖ የሚታይባትን ጽሌ ተወልዳ ሲያይ ተገረመ፡፡ ፊትህን አሳየኝ ሲለው ፊቴን ልታይ አትችልም ነገር ግን ጀርባዬን ታያለህ ያለው አምላክ የሚወልደባትን ተወልዳ ሲያይ የጌታን ጀርባ በደብረታቦር የሚያይበት ቀን መድረሱን አውቆ በደስታ ዘለለ፡፡ የመገናኛውን ድንኳን የተከለው ሙሴ ከድምፁ በቀር ያላገኘውን አምላክ የሚያገኝባት እውነተኛዋ የመገናኛው ድንኳን ተተክላ ባያት ጊዜ ደስ አለው፡፡ መቅረዝ ፣ ሙዳየ መና፣ ታቦትና የሥረየት መክደኛ ላይ ደም እየረጨ ሲያመልክ የነበረው ሙሴ አማናዊው ብርሃን የሚበራባት መቅረዝ፣ እውነተኛው መና የሚገኝባት ሙዳይ፣ እውነተኛው የሥረየት ደም የሚረጭባት ምሥዋዕ፤ አካላዊ ቃል የተቀረጸባት በሁለተናዋ ጽሩይ ወርቅ በተባለ ፍጹም ንጽሕና ተጊጣ ድንግሊቱን ባያት ጊዜ መደነቁን አበዛ፡፡ ድንኳኑን ሲያስብ እርሷ፣ ታቦቱንም ሲያስብ እርሷ፣ ጽላቱን ሲያስብ እርሷ፣ ሙዳየ መናውንም ሲያስብ እርሷ፣ መቅረዙንም ሲያስብ እርሷ፣ ማዕጠንተ ወርቁንም ሲያስብ እርሷ ስትሆንበት እንዴት አይደነቅ በእውነት፡፡ ሙሴ በዚህ አላበቃም፡፡ ሕግ የተቀበለበትን የጨሰውን ተራራ አስታወሰና ልጁን ዳዊትን ጠራው፡፡
ዳዊትም የአባቱን ሙሴን ጥሪ ሰምቶ ሲነሣ የረጋችው ተራራ ተወልዳ አያትና እርሱም በደስታ ዘለለ፡፡ አዎ "የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፤ የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ፤ እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው " /መዝ 68 ፤ 16/ ብሎ የተናገረላት ተራራ ስትወለድ አይቶ ደስ አለዉ፡፡ ሐላፊውን ብሉይ ኪዳን አባቱ ሙሲ ሲቀበል በነጓድጓድ ድምጽ በረዓድና በፍርሃት ነበረ፡፡ የማያልፈው ሐዲሱ ኪዳን ግን በጸና ተራራ እንደሚሰጥ የተናገረላት ያድርባት ዘንድ የወደደዳት አማናዊት የንጽሕና የቅድስና ተራራ ተወልዳ አይቶ ደስ እያለው መዝሙሮችን በአናት በአናት አከታተለ፡፡ ልጁ ሰሎሞንም "ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው" /መኃ 4 ፤ 1/ እያለ በምስጋና ተከተለው። ኢሳይያስም ንጹሕ ወረቀቱን አይቶ ደስ አለው፡፡ እንደ ታሸገች የተጻፈባት ሀዝብም አህዛብም ይህን ደብዳቤ ልናንብበው አንችልም ያሏት አካላዊ ቃል በድንግልና የሚጻፍባትን ንጹሕ ወረቀት /ኢሳ 29;11/ አይቶ ተደነቀ፡፡ ሕዝቅኤልም ሁለንተናዋ ዝግ ሆኖ እግዚአብሔር ብቻ ገብቶ የወጣባት መቅደሱን ተሠርታ አይቶ ደስ አለው፡፡
ተራ በተራ ሁሉም ነቢያት ትንቢቶቻቸውን ይዘው ስለእርሷ ያዩትን ራእይ፣ ምሳሌና ትንቢት ፍጻሜውን እያዩ ተደነቁ፡፡ መሐንዲስ የሕንጻውን ንድፍና የሚሠራውን ሕንጻ እንደሚያስተያይ እነርሱም በልደቷ ትንቢታቸውን ከፍጻሜው መጀመሪያ መሠረት ጋር እያስተያዩ ተደሰቱ፡፡
በመጨረሻም የፍትረት ሁሉ አባት አዳም ከልጆቹ ጋር ደስ አለው፡፡ አዳም ሆይ መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ያለው ጌታው ከጨለማ ሲኦል ሊያውጣው ልጁን ከመሬት ባሕርዩ አንሥቶ እርሷን ሰማይ አድርጎ ሲያያት በእርሷም ላይ እርሱ ፀሐይ ሆኖ ሊወጣ ወገግታውን ሲያሳየው በደስታ አነባ፡፡ የሰጠኸኝ ሴት አሳተችኝ ብሎ የከሰሳት ሔዋንን ተክታ የሚያመሰግናት ሌላ ሔዋን ተወልዳ ሲያይ ደስስስ አለው፡፡ ምሳሌና የሚተካከላት እንደሌለም ሲያይ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ "ለእኗቷ አንዲት ናት፣ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት" የሚለውን ዘምር አለው፡፡
ልጆቹ ሁሉ ከመረገሙ በፊት ያለ ክብሩን ስላላዩ በተገቢው መጠን የማያደንቁለትን ከስሕተት በፊት የነበረ ክብሩንና ጸጋውን ይዛ ስትወለድ በደስታ ተንሰቀሰቀ፡፡ የአዳምን ለቅሶ ሰምታ ሔዋን እናቷ የመርገም ጨርቋን ጥላ ብድግ አለች፡፡ አንድ ልጇን እያየች በደስታ አለቀሰች፡፡ በልጆቿ ሳይቀር ምነው እባብን ሰማሽው የሚል ወቀሳ እየሰማች ስታዝን የኖረች ምስኪን እናት መርገሟን ወርውራ በቅድስና ከብራ መላአክትን በልጣ እንደ ጨረቃ ስታበራ ስታያት መካሷን አይታ ፈነደቀች፡፡ ያሳታትን ዲያብሎስ በቅድስና መንገዷን ሰውራ የምታስተውን (ግራ

👍1
የምታጋባውን) መድኃኒት ልጇን ተወልዳ አይታ በደስታ አነባች፡፡ የፍጥረት እናትና አባት የሆኑ አዳምና ሔዋን ልጃቸውን እናታችን፣ ካሳችን፣ መድኃኒታችን፣ ሰማያችን ተወለደች እያሉ ሲደሰቱነ ሲያመሰግኑ ልጆቻቸውም ከእነርሱ ጋር የባሕርያችን መመኪያ የድኅነታችን ቀርን ዛሬ ተወለደች እያሉ ተደሰቱ፡፡ ከአንድ ከዲያብሎስ በቀር ሁሉም ደስ አላቸው፡፡
እርሷም በኋላ እንኳን የቀደመው የኋላው ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል አለች፡፡ እንግዲያስ በእርሷ መወለድ እንደ ዲያብሎስ አይክፋን፤ ይልቁንም የፍጥረት ሁሉ አባትና እናት እንደሆኑት እንደ አባታችን አዳምና እንደ እናታችን ሔዋን፣ እንደ ነቢያትና አበው ሁሉ አብረን ደስ ይበለን፡፡ እንኳን ደስ አለን፤ ዛሬ የባሕርያችን መመኪያ፣ ሰማይ የደረሰችው መሰላል፣ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር ሆኖ አማኑኤል ተብሎ ከእኛም ጋር እንዲሆን ምክንያት የሆነችልን የእመቤታችን ልደት የእኛም የሁላችን ልደት ነውና፡፡
ሰማይ የደረስሽው መሰላል፣ ከምድር ባሕርያችን የተሠራሽ ሰማይ ሆነሽ የጽድቅ ፀሐይን ያወጣሽልን ሰማይ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ዛሬም የዲያብሎስ ግሣት የሆነውን ኮረና ዘረኝነትን፤ ኮረና መለያየትን እና ኮረና ርኩሰትን ለተግሣጽ ከተላከለን ለጊዜውም ቢሆን ካስደነገጠን ኮረና ቫይረስ ጋራ አንድ ላይ አስወግጅልን፡፡ የባሕርያችን መመኪያ ሆይ ለአጋንንትና ለመናፍቃን መሳለቂያ አታድረጊን፡፡ በእኛ ጉድለት ምክንያት ታመነውባት አፈሩ፣ ተማጽነውባት መልስ አጡ እያለ ዝንጉዎችን እንዳያጠራጥር ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ በልደትሽ ስላስደሰትሻቸው ከሐፍረትና ከውረደትም ስላዳንሻቸው እናትና አባትሽ ስለኢያቄምና ስለሐና ፣ ስለአዳምና ሔዋን ብለሽ ድረሽልን፡፡ በእሥራኤል ትውፊት እሥራኤል በተጨነቁ ቁጥር ራሔል ስትጮህ ይሰማቸው እንደነበረ ዛሬም አንቺ ከጮሕሽ ልጅሽ ይምራልና በእውነት ይቅር ይለን ዘንደ ለምኝልን፤ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ በክርስትናው ለሚያምን ሁሉ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳንም ለእናታችን ልደት ለሁላችንም የጋራ የልደት በዓል አደረሰን፡፡
©ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ

❤1
Forwarded from Binyam Shitaye
❤1
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰባት አባላት ያሉት
የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴን ሰየመ።
ግንቦት ፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
ለ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህንት ጉባኤ አጀንዳ በማርቀቅ እንዲያቀርቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን የሰየመ ሲሆን ኮሚቴው በቋሚ ሲኖዶስ ተዘጋጅቶ የቀረበውን አጀንዳ በመመርመርና በማሻሻል ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በማቅረብ የሚያጸድቅ ይሆናል። የኮሚቴው አባላትም፦
፩.አቡነ ጎርጎርጎሬዎስ
፪.አቡነ ቀሌምንጦስ
፫.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ
፬.አቡነ ኤልያስ(አርባምንጭ)
፭.አቡነ ሩፋኤል
፮.አቡነ ዜናማርቆስ
፯.አቡነ ኤልሳዕ ሲሆኑ ምልዓተ ጉባኤው ከአጀንዳዎቹ መጽደቅ በኋላ የቅዱስ ፓትርያርኩን የመግቢያ መልዕክትና የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትን ሪፖርት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

❤4👍1
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
“ናሁ ውስተ አድባር እገሪሆሙ ለሰብአ ዜና ወይዜንዉ ሰላመ እነሆ የምሥራችን የሚሰብክ ሰላምን የሚያወራ (ሚጠትን የሚናገር) ሰው እግሮች በተራሮች ላይ ናቸው"
(ትን.ናሆም 1፣15 ትርጓሜ ቅዱስ ዮሐንስ አወፈርቅ)
በውጭ አህጉረ ስብከት ተመድበው ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በመፈጸም ላይ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ 1 ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) የሰሜን ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጅያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ወደ ሀገር ቤት በመግባት ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን እንዲሳተፉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ጥያቄ ማቅረቧ ይታወቃል፡፡
መንግሥትም ሀገራዊ ተቋማትን ለማጠናከር ያለው ቁርጠኝነት የጸና መሆኑን በገለጸበት መግለጫ እንደተመለከትነው የሀገራችንን ሰላም ለማጽናት፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን የታሪክ ገጽታ ለመጠበቅ ተቀራርቦ መነጋገር የተሻለ መፍትሔ መሆኑን ተረድቶ ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገር ገብተው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን እንዲሳተፉ መፍቀዱን ተረድተናል፡፡
በመሆኑም መንግሥት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያቀረበችውን ጥያቄ ተቀብሎ ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገር እንዲገቡ በመፍቀዱና ተግባራዊ ምላሽ በመስጠቱ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ወደፊትም እግዚአብሔር በሰጠን ምድር፣ አባቶቻችን ባቆዩልን ሀገር አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ለሀገራችንና ለሕዝባችን በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታችንን በማጠናከር በጋራ : ለመሥራት ዝግጁዎች መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም.

በቤቱ የማያገባው ባለቤት የለም።
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅብረት ሥር፦በሃይማኖት፣በጥምቀት፣በሜሮን፣በቁርባን፣በኅብረት፣በመስቀላዊት ሕይወት የምንኖር ሁላችንም የቤተ ክርስቲያን ልጆች ነን። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ማንኛውም ጉዳይ ያገባናል። በኅብረታችን መካከል የሚደረገውን ነውርን መታገሥም ጽድቅ አይደለም። አድርባይነት እና አስመሳይነት ነው። ማስመሰል ደግሞ ምትሀታዊ ኑፋቄ ነው።
የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት እያዩ መታገሥ ቸርነት አይደለም፤የእምነት መጉደል እና በመስቀላዊት ሕግ አለማመን ነው እንጂ። በቤቱ የማያገባው ባለቤት አለ ወይ? ካልደነዘዘ በስተቀር። የምእመናንን፣ የገዳማትን፣ የአብነት ደቀ መዛሙርትን.. ዕረፍት አልባ መከራ እያዩ ዝም ማለት ትህትና አይደለም። ይሄ በኦርቶዶክሳዊነት ኅብረት እና በዘለዓለም ተስፋ አለማመን ነው።
በአባትነት ስም ረቂቅ የአባትነት ሽፍታ የሆኑትን ዝም ማለት፦ ለአባቶች ክብር ሰጪነት አይደለም። የግድ የለሽነት ጥግ ነው እንጂ። ግድ የለሾች ደግሞ የፍዙዛን መናፍስት አምሳያዎች ናቸው።
ማንንም ሲያበላሽ እና ቤተ ክርስቲያንን ገደል ሲከታት እያዩ ይከፋዋል እያሉ ዝም ማለት የገዘፈ ስንፍናም ምንፍቅናም ነው። የቤተ መቅደሱ አደገኛ ቦዘኔዎችን ዝም ማለት ቸርነት አይደለም። በቤተ ክርስቲያን እናትነት አለማመን ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ሄሮድስን መገሠጹ፣ቅዱስ ኤልያስ አክዓብን መገሠጹ፣መድኅን ክርስቶስ ቤተ መቅደሱ ገበያ ያደረጉትን "ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችሁት። "ማቴ.፳፩፥፲፫ ብሎ ገልጾ በተአምራት ቤተ መቅደሱን ማንጻቱ ስህተት ነው? አይደለም። ነቢዩ ኤልያስም፣ መጥምቁ ዮሐንስም፣ መድኅን ጌታም ያሳዩን የጥብዓት እውነት መመሪያችን አይደለም ወይ?
በተለይም ጌታችን ካሳየን ሌላ ምሥክር ከየት ይመጣል? ከራስ በላይ ነፋስ እንደሆነ ከክርስቶስ በላይ አርአያ ከየት ይገኛል? በፍጹም። ከኤልያስ በላይ ነቢይ፣ከዮሐንስ መጥምቅ በላይስ ጥቡዕ ሐዋርያ ከየት ይመጣል?
"እንግዲህ በጎ መሥራትን አውቆ ለማይሠራው ሰው ኃጢአት ትሆንበታለች።"ያዕ.፬፥፲፯። ቤታችንን ከአጥፊዎች መጠበቅ ትክክለኛ ውሳኔ ነው። ሁሉም ክርስቲያን በያለበት ለዕቅበተ ቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን አለበት። ስንጥር ሸንበቆ ለመመረኮዝ መሞከር ግን ድጋፍም አይሆንም ለእጅም አደገኛ ነው።
የኔታ ገብረ መድኅን እንየው

👍5❤1
ማኀበረ ቅዱሳን ለሃይማኖታዊ ጥያቄ በስልክ ምላሽ የሚያገኙበት አገልግሎት አስጀመረ
#FastMereja I በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚፈልጉትን ሃይማኖታዊ ጥያቄ በስልክ ቁጥር ደውለው ማብራሪያ የሚያገኙበት አገልግሎት ማስጀመሩን ፋስት መረጃ ሰምቷል።
«ሃሎ መምህር» የተሰኘው አገልግሎቱ እንዲመለስልዎ የሚፈልጉትን ሃይማኖታዊ ጥያቄ በስልክ ቁጥር 0111 55 32 32 በመደወል ለጥያቄዎ ማብራሪያ እና መልስ ከመምህራን ያገኛሉ ተብሏል።
ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 4:00 እስከ ቀኑ 10:00 አገልግሎቱ የሚሰጥ ሲሆን ሰኞ፣ ረቡዕ እና ሐሙስ በአማርኛና በኦሮምኛ፣ ማክሰኞ እና ዓርብ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ አግልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

👍7🥰3
የእስር ዜና!!!
ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታሰረ‼️
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስብከት አገልግሎቱ፣በተለያዩ ስልጠናዎች ላይ ስልጠና በመስጠት፣በተለይም ተሃድሶውያንን በመዋጋት የምናውቀው ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች መወሰዱ ተሰማ።
እንደሚታወቀው የቅዱስ ሶኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሚካሄድበት ወቅት በተለይም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሚመረጥበት ግዜ ሁሉ ለቤተክርስቲያን ይታገላሉ የሚባሉ ወንድሞች እና እህቶች ይታሰራሉ። ዛሬም ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታስሯል።
የቅዱስ ሲኖዶስን ጸሐፊ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅን መምረጥ የመንፈስ ቅዱስ እና የብፁዓን አባቶች ድርሻ ነው። በዚህ ወቅት የሚታሰር አንዳችም ሰው መኖር የለበትም ።ወንድማችንን እንድትፈቱት እንጠይቃለን ።
መንክር ሚዲያ-Menker Media

👍6😢2
በአንድ ቀን አርባ አራት ጥንዶች ጋብቻቸውን ይፈጽማሉ
#Ethiopia | የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የቅድመ ጋብቻ ትምህርቱን የወሰዱ አርባ አራት ጥንዶች የፊታችን ሐሙስ ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጋብቻቸውን በስርዓተ ተክሊል እና በቅዱስ ቁርባን ይፈጽማሉ።
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በትዳር ሕይወት ላይ ያተኮረ ጠቃሚ የቅድመ ጋብቻ ትምህርት በመስጠት ይታወቃል። ይህ ትምህርት ለተሳታፊዎቹ ዘላቂና የተሳካ ትዳር ለመመሥረት የሚያስፈልጉትን መሠረታዊ እውቀቶችና ክህሎቶች በመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ይህ የብዙኃን ጋብቻ ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት አመት በፊት ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴደራል ተካሂዷል።

❤9🥰2👍1🤣1